ጥቃቅን ጡጫ እያውለበለበ በ ካረን ሃይንስ

Page 1

ውይይት ለቫክሲን አመንቺዎች----

ደጋፊዎች……..

ጥቃቅን
እያውለበለበ
ካረን ሃይንስ
ጡጫ
እናም
1  ለክትባት አመንቺዎች....... ......እናም ደጋፊዎች ጭዉዉት “በኮቪድ ወቅት አርቲስቶች ይህን አስቸጋሪ ጊዜ እንድንረዳ እንዲረዱን ማድረግ ትኩረታችን ነበር ፡፡ ስለዚህም ዶ/ር ፒተር ሴንተር ለክትባት ማመንታት ፕሮጀክት ላይ ስለመስራት ሲያናግረን አዎንታዊ ምላሽ መስጠት ነበረብን ምክንያቱም ይህ የክትባት ጉዳይ ጓደኛሞችን ፤ ቤተሰቦችን ብሎም ማህበረሰብን ሲለያይ እያየን ነዉ። እንደ አርቲስቶች ሰዎችን ወደ አንድ ለማምጣት እና የዚህን በሽታ መጥፎ አሉታዊ ተፅኖ በመከላከል የድርሻችንን ለመወጣት እንፈልጋለን፣ በህዝቡ መሃካል እየተፈጠሩ ያሉ መግባባት የመጡ ልዩነቶችና ክፍፍሎችን ማለት ነዉ፡፡ በክትባት በሚያመነቱ እና ክትባት ወዳጆች መካከል እያጋጠሙን ባሉ በሁለት ተቃራኒ ፅንፎች ጭዉዉት የሚሆን እና አስቸጋሪ አጋጣሚዎች ላይ ዕዉቀት እና መረዳትን ሊሰጥ የሚችል የህይወት ተሞክሮ ያላቸዉን አራት የተዉኔት ጭውውቶችን መድበናል፡፡ እነዚህንም ጭዉዉቶች አብዛኞቻችን እራሳችንን እንደምናገኝባቸዉ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን የተላበሱ ትያትር አድርገን ነዉ የምናያቸዉ፡፡ ከራስዎ ጋርም ሆነ በዙሪያዎ ካለ ሰዉ ጋር በሚወያዩበት ወቅት እኚህ አጫጭር ተዉኔቶች ይህን ጉዳይ በማስተዋል እና በዓፅኖት እንዲረዱት ያግዞታል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡” ሼሪይ ጄይ ዩን ጄይ ዶጅ አርቲስቲክ ዳይረክተር አርቲስቲክ ዳይረክተር በካ ዴል ሉፓ በካ ዴል ሉፓ
2  ስለ ቦካ ዴል ሉፖ የቦካ ዴል ሉፓ ተልዕኮ ለየት ያሉ ትዕይንቶችን ባልተለመዱ ቦታዎች መፍጠር ነዉ፡፡ድርጅቱ ለተደራሽነት የቆመ እና ተሳትፎን እና ግንዛቤን ለማስፋፋት እንዲሁም ዘመናዊ ተዕይንቲችን በካናዳዉያን የባህል ብዝሃዊነት ዉስጥ የሚሰራ ነዉ፡፡በአርቲስቲክ ዳይሮክት ሼሪይ ጄይ ዩን እና አርቲስቲክ ፕሮድዩሰር ጄይ ዶጅ እየተመራ ከምስረታዉ 1996 ጀምሮ ቦካ ዴል ሉፓ ከ 60 በላይ አዳዲስ ስራዎችን ፈጥሯል፡፡ ዝግጅቶቹ በሃገር እና አለም አቀፍ መድረክ ላይ በመጓዝ የተዘጋጁ ሲሆን ድርጅቱ “ስላም” የተሰኘ ንቁ አርቲስት ማጎልበቻ ፕሮግራም ያዘጋጃል፡፡ ድርጅቱ ባሳለፋቸው ዘመናት የጃሲን የምርጥ ዲዛይን፣ ምርጥ ዝግጅት፣ ታላቅ ጥበባዊ ውጤት እና ምርጥ ትዕይንት፤ የፈጠራ ተቺዎች ምርጫ ሽልማት፣ የአልካን ጥበባዊ ትዕይንት ሽልማት እናም የፓትሪክ ኦኒል ሽልማትን የተጎናጸፈው እኚህን ለክትባት የሚያመነቱ እና ክትባት ወዳጆች መሃከል የሚደረግ ጭውውቶችን መነሻ በማድረግ ነበር። ቦካዴልሉፖ.ኮም
3  በፔንደር ደሴት ላይ ደንገዝገዝ ብሏል። በባህር ዳርቻ የሚገኘው በበፖኤት ሪዞርት ቴራስ ላይ ወጣት ጥንዶች ከተጋቡ ከአፍታ ቆይታ በኋላ ለስለስ ያለ ማዕበል የባህር ዳርቻውን ይጋጭ ነበር። አየሩ ሞቃታማም ነበር፣ ግን እየቀዘቀዘ ነው። ሰማዪም ጥርት ብሎ ነበር። በሰርጉ ላይ የታደሙ እንግዶች ከተቀመጡበት ታጣፊ ነጫጭ ወንበሮች ተነስተው ወደሚያምረው ሰማይም እያንጋጠጡ ድግሱ የሚገኝበት ‘ሲግላስ አዳራሽ’ መሄድ ጀመሩ። በአዳራሹ መግቢያ ላይ በሚገኙት ለስለስ ያሉ አንጸባራቂ ብርሃን ባለው በር ውስጥ እንግዶቹ ሲያልፉ አስፈላጊ የነበረውን የግብዣ ‘ኪውአር ኮድ’አቸው እየተረጋገጠ ነበር። በአያቷ እቅፍ ውስጥ ትንሽዬ ህጻንም አለች።ወደ አዳራሽ ሲገቡ ሙሽራዋ ተንጠራርታ የህጻኗን ፊት ዳበሰች፤ ሙሽራውም ክርኑን በቤተሰቦቹ ላይ ጣል አድርጎ ነበር። በቅርበት በሪዞርቱ ግቢ ዳርቻ ላይ የሙሽራዋ እህቶች ‘ቪኪ እና ቬዳ’ 6 ጫማ ተራርቀው የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ አድርገው ወደ ባህሩ እያማተሩ ነበር። ለስለስ ያለው ንፋስ በጣም ተመሳሳይ የሆነውን የመንትያዎቹን ቪኪ እና ቬዳ ጸጉር እያንቀሳቀሰ ነበር። ቬዳ፡ በጣም ነው የሚያምረው። ቪኪ፡ ሰርጉ ወይስ ሀይቁ? ቬዳ፡ ሁለቱም በሁለቱም መካከል ጸጥታ ሰፈነ። ጸጥ ባለ ውሀ ውስጥ አሳዎቹ እየቀዘፉ እና የበሀር ነስሮች ደግሞ ሽቅብ ይበራሉ። ቪኪ እና ቬዳ: እእእምም ጸጥታው እንደቀጠለ ነው። ከአዳራሹ የኤልቪስ”በፍቅር አለመውደቅ አይቻልም” ዘፈን ይሰማል። ቪኪ፡ ወደ አዳራሹ መግባት አለብሽ። ‘ኦይስተር’ ሳያልቅ ድረሺበት። ቬዳ፡ ግርግሩ እስኪያልፍ ድረስ ካንቺ ጋር መቆየት እፈልጋለሁ።
4  ቪኪ፡ የግብዣው ግርግር? ቬዳ፡ አዎ፤ በትክክል። ቪኪ ውሃውን በተመስጥዎ እየተመለከተች፣ ቬዳ ደግሞ ወደ ሰማዩ እያንጋጠጠች። ከትንሽ ጊዜ በኋላ.... ቬዳ፡ ክትባት መድሃኒት ቤት እየተሰጠ እንዳለ ታውቂያለሽ አደል። ቪኪ፡ አላውቅም ነበር¡��በእርግጥ አውቃለሁ። አመሰግናለሁ ግን አያስፈልገኝም። ቬዳ፡ ይቅርታ። አሳዎቹ ወደ ውስጥ ቀዘፈው ከእይታ ተሰወሩ። ከትንሽ ቆይታ በኋላ ሰማዩ ደማቅ ሰማያዊ ሆኗል። ቪኪ ከዋክብቶችን እየተመለከተች ቬዳ ደግሞ ጁፒተርን በከዋክብቶች መካከል ለማየት እያፈላለገች ነው። ቪኪ፡ ለኔ ማዘን አይጠበቅብሽም። ጉዳዩን ልክ ውሻ እንዳለው ሰው ቁጠሪው። የፈለገው ቦታ ለምሳሌ ምግብ ቤት፣ ስፖርት ቤት፣ ቤተ መጽሐፍት.....የታናሽ እህት ሰርግ ላይም ከውሻው ጋር መሄድ አይችልም። ውሻ ቢኖረኝ ኖሮ እዚህም ቦታ ላይ ከእሱ ጋር ነበር የምሆነው። ውሻዬም ይህን ባህር እያሸተተ በጣም ደስተኛ ይሆን ነበር። ቬዳ፡ (እየቀለደችባት) ምናባዊ ውሻ አለኝ እያልሺኝ ነው? ቪኪ፡ (በአዎንታ) ኮኮ ይባላል። ቬዳ፡ ኮኮ እኮ ምናባዊ አይደለም ቪኪ፡ የኛ ምናበኛ ካልሽ አሺ። እሱ በጣም ስርዐት ያለው ነው። ቬዳ፡ ምናባዊ ባይሆን ኖሮ ህጻን አይቪን ማየት ይፈቀድለት ነበር።
5  ቪኪ፡ አይሆንም። ምክኒያቱም እንሥሣቶች እኮ ቫይረሱን እንደሚሸከሙ እኮ የተረጋገጠ ነው። በፍሎሪዳ ባለፈው ሳምንት ሁለት ትንንሽ ሽናውዘር ውሾች ተይዘዋል። ቬዳ፡ ቁጥሩን ስናይ ሁለት ብዙ አይደለም እኮ። ቪኪ፡ ስታስቲክሱን ስናይ እኮ ብዙዎች እንሥሦች እኮ አይመረመሩም። በዛም ላይ የበሽታ ተሸካሚዎችም ጉዳይ አለ። ቬዳ፡ በሽታ ተሸካሚዎች? ቪኪ፡ በሽታ ተሸካሚዎች ማለት ማንኛውም ኢንፌክሽን ተሸካሚ የሆነ ነገር ነው። ለምሳሌ ልብስ፣ የማብሰያ ዕቃዎች፣ ጠረጴዛ ወ.ዘ.ተ...ምናልባትም ሽናውዘር ውሾች ሊሆኑ ይችላሉ። ይህን ሳይንስ አታውቂም እንዳትዪኝ። ቬዳ፡ እኔ እንደማስበው ራሄል እነኚህን በሽታ አስተላላፊዎችን የምትፈራ አይመስለኝም። ቪኪ፡ ነበር። ልጅ ከወለደች በኋላ ግን አይመስለኝም። ቬዳ፡ በትክክል። (ስሜታዊ ሆና) ልጅ ቢኖረኝ ኖሮ ምን ላደርግ እንደምችል አላውቅም። ቪኪ፡ ብዙ የማይጠበቅ ነገር ታደርጊ ይሆናል። አፍታዊ ዝምታ፤ የባህር አንበሳ ከሳቱርና ሀይቅ ዳርቻ እየጮሀ ነው። . ቪኪ፡ አኔም እንደ ራሄል ነው ምሆነው። እራሴንም ቢሆን አላስጠጋም ነበር፤ ማስክ ባደግም ባላደርግም። ይገባኛል ራሄል የወለደችው በቀዶ ጥገና ነበር። ትንሿ እህታችንን ልንጠብቃት ይገባናል። የእህቴን ልጅ በመስታወት በር አሻግሬ ማየት እኔንም አልከበደኝም ማለት አይደለም። ወ..ይ... እነኛ ትናንሽ ጭኖቿ፣ እንጥልጥል ያሉ ጉንጮቿ፣ የምታወዛውዛቸው ትንንሽ ቡጢዎቿ። ቬዳ፡ አይቪ በርግጥ እጆቹዋን አወዛወዘችልሽ? ቪኪ፡ ራሄል የአይቪን ጥንንጥ ቡጢዎቹዋን አንስታ አወዛወዘቻቸው.... ይቺ ጸረ ክትባት የሆነችውን
6  አክስትሽን ደስ አሰኛት አለቻት። በርቀት ጭለማው ሲበረታ የአዳራሹ ብርሃን እየፈካ መጣ። የሰርጉ እንግዶችም መንቀሳቀስ ጀምረዋል። በሐይቁ ዳርቻ ላይም የባህር ‘ኦተር’ በዝግታ ወደውስጥ እየቀዘፉ ጥፍር በሌለው እግራቸው እየዋኙ ሽቅብ ይወጣሉ። ቪኪ፡ ወደ ውስጥ መግባት አለብሽ። ቬዳ፡ እገባለሁ። ‘ኦይስተር’ መመገብ እወዳለሁ። ቪኪ፡ ትንንሽ ጣፋጭ ልጆችንም ቬዳ፡ አዎ ይቅርታ ሶስት ተጨማሪ ከዋክብት ወጡ፡፡ ይቅርታ ለጊዜው ካንቺ ጋር እዚሁ እቆያለሁ፡፡ ቪኪ፡ ትንሽ ቆየት ብዬ ቢሆንም ክትባቱን መውሰዴ አይቀርም፡፡ ቬዳ፡ ምን እየጠበቅሽ ነው? ቪኪ፡ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ምን እንደሚሆኑ ለማየት ትንሽ እቆያለሁ፡፡ ቬዳ፡ ክትባቱን የወሰዱ ሰዎች ምን እንደሚሆኑማ ታውቂያለሽ። ቪኪ፡ ተጨማሪ ሰዎች ምን እንደሚሆኑ ማወቅ እፈልጋለሁ፡፡ ቬዳ፡ በሒሳባዊ ስሌት ለመናገር የተከተቡ ሰዎች ልክ እንደ አብዛኛው መኪና አሽከርካሪዎች አደጋ አይደርስባቸውም ምናልባትም በተሻለ፡ ፡ ነገር ግን በቫይረሱ የተያዙት በሂሳባዊ ስሌት ከዚህ በተቃራኒ ሁኔታ ነው የሚገጥማቸው፡፡ ቪኪ፡ እኔ ተይዤ የተያዙ ሠዎችን ቁጥር እጨምራለሁ ብዬ ሳይሆን ምክንያታዊ ያልሆነ ፍርሃት በውስጤ ስላለ ነው፡፡ ቬዳ፡ ልክ ነሽ፡፡ እኔ የማይገባኝ ነገር ለምን በትክክልም መፍራት ያለብሽን ነገር አትፈሪም? ለምን ሸረሪቶችን አትፈሪም? በእነርሱ መነደፍ እንደሚገልሽ

ቬዳ፡ ህመሙ የቆየብኝ ለአንድ ቀን ብቻ ነው፡፡ በጣም አልታመምኩም፡

፡ ደግሞም አላስታወስኩትም

7  ግልጽ ነገር አይደለም እንዴ? ግልፅ የሆነው ነገር ነርሶች እና ግለሰቦችን ተንከባካቢ ሠራተኞች ስለዚህ ጉዳይ ምን ያስባሉ የሚለው ነው፡፡ ቪኪ፡ እስኪ አሁን አቁሚ፡፡ ምክንያቱም ግልፅ የሆነው ነገር ያ አይደለም፡፡ ይህንን ፈጥረሽው ነው፡፡ ምናልባት ነርሶቹ ይሄ ጉዳይ ተምችቷቸው ይሆናል፡ ፡ እናም ‘’ይሄ መሆን ያለበት ነገር ነው፣ ይሄም ያልፋል፣�� ይሄም ያልፋል” እያሉ ያስቡ ይሆናል፡፡ ቬዳ፡ በትክክል . ቬዳ ስልኳ ላይ መልዕክት ገባላት÷ የጥሪው ድምፅ በጣም ለስለስ ያለ ነው፡፡ ቪኪ በሩቅ እየመጣች ያለቸውን የትንሽ ጀልባ ነፀብራቅ እየተመለከተች ነው፡፡ ቬዳ፡ ወደ አዳረሹ መግባት አለብኝ፡፡ ቪኪ፡ እሺ . ግን ቬዳ ወደ አዳራሹ አልገባችም፡፡ በጣም ብዙ ክዋክብቶች መታየት ጀመሩ፡ ፡ ብዙ አሣዎች ወደ መኝታቸው ወደ ጥልቁ ባህር እየቀዘፉ ሄዱ፡፡ ቬዳ፡ መብረርንም የመርከብ መስመጥንም አትፈሪም፡፡ ቪኪ፡ ልባችን የሚፈራውን ነው የሚፈራው፡፡ ክትባቱ አንቺን ስላሳመመሽ እኔን ረብሾኛል፡፡
ወይም ሌላ ነገር አልነበረኝም፡፡ በርግጥ የምሞት አይነት ስሜት ተሰምቶኝ ነበር፡፡ ከመጠን በላይም ተደናግጬ አንቺ ጋር መደወል አልነበረብኝም፡፡ ለአንድ ቀን ሶፋ ላይ ተኝቼ ኔትፍሊክስ ስመለከት ዋልኩኝ፡፡ ‘ዘ ዋየር’ የሚለውን ፊልም አላየሁትም ነበር፡፡ በርግጥ አሁን ሩፖውል ማን እንደሆነ በደንብ አውቄዋለሁ፡፡ ምስጋና ለክትባቴ ይሁንና፡፡ ከዙም ለአንድ ቀን ማረፍ ነበረብኝ፡፡ ‘ሴክስ እና ዘ ሲቲ’ ፊልሞችን የመጀመሪያዎቹን ክፍሎች ለማየት ችያለሁ፡፡ እጅግ በጣም ጥሩ ፊልሞች ናቸው፡፡ ቪኪ፡ የተወሰኑ ሰውች ሞተዋል፡፡
8  ቬዳ፡ የሚያሽከረክር ሰው ላይ አደጋ ሊደርስ እንደሚችል ብታውቂውም አንቺ ግን ማሽከረርከር አትፈሪም። ቪኪ፡ አዎ እኔ የምነዳ ከሆነ (በድብቅ) መንገደኛ ወፎች በጣም በከፍታ እየበረሩ ቤታቸውን እየፈለጉ ነው፡፡ ቪኪ፡ እኔ ሳይንስ የማነብ አይመስልሽም አይደል፡፡ ስለኔ ምንም አልገባሽም፡፡ እኔ የአዲሱን ጥናት ውጤት እየጠበኩ ነው፡፡ አዲሱ ጥናት እንደሚጠቁመው ሰዎችን መከተብ የአዲስና አደገኛ ቫይረስ ተሸካሚ ማድረግ ነው፡፡ በእዚህ አይነት ቫይረስ መሞት የነበረባቸው ሰዎች በክትባቱ ምክንያት አይሞቱም ግን ለሌላ ሰዎች እነዚህን አዳዲስ ገዳይ ቫይረሶችን ያስተላልፋሉ፡፡ ቬዳ፡ እናስ እራስሽን ለመስዋትነት እያዘጋጀሽ ነው? ቪኪ፡ አይ እንደውም በተቃራኒው ነው፡፡ እኔ እንደውም ሌላ ሰዎች እራሳቸው መስዋዕት እንዲያደርጉ እየጠበኩ ነው፡፡ ቬዳ፡ መንጋው ቪኪ፡ አዎ መንጋው ቬዳ፡ መንጋው ያለው ፅኑ ህሙማን ክፍል ነው፡፡ ከብቶቹ የመተንፈሻ ማሽን ላይ ከመደረጋቸው በፊት፤ ነርሱዋ ምን ጋር መደወል እንዳለባት እየተጠየቁ ነው፡፡ እኔን ያልገባኝ ነገር እንዴት የተከተቡ ሰዎች አደገኛ ና ገዳይ የሆነውን አዲሱን ቫይረስ ካንቺ በተለየ እንደሚያስተላልፉ ነው፡፡ ቪኪ ሰርገኞቹን ለማየት ፊቷን��አዞረች፤ የሰርግ አዳራሹ ፈክቷል፤ ታዳሚዎቹም “ሄሎ” በሚለው ዘፈን እየተወዛወዙ ነው። ቪኪ፡ እኔ ወደ ውስጥ መግባት ስለማልችል አንቺ መግባት አለብሽ። ግቢና ህጻኗን እቀፊ። ቬዳ፡ ትንሽ ልቆይ እና እገባለሁ። ቪኪ፡ አትረባም ብለሽ ነው አደል ምታስቢው?
9  ቬዳ፡ በፍጹም። ቪኪ፡ የማልፈራ ይመስልሻል፤ ብቸኝነትም የማይሰማኝ ይመስልሻል። ቬዳ፡ እንደሱ ሳይሆን፤ ሊገባኝ ስላልቻለ ነው። ቪኪ፡ ምን እንደምጠብቅ ጠይቀሽኝ ነበር፤ ምን አንደምጠብቅ የማልነግርሽ አንቺ ምክንያቴን የማይረባ አድርገሽ ታስቢዋለሽ ብዬ ስላሰብኩ ነው፡፡ አፍታዊ ዝምታ ከአዲሱ የላማ (ለማዳ ግመሎች) ሙከራዎች ውጤት እየተጠባበኩ ነው ቬዳ፡ ላማ (ለማዳ ግመሎች) ላይ የሚደረገው ሙከራ ምንድን ነው? ቪኪ፡ ኮሮና ቫይረስን አፍንጫ ውስጥ በሚነፋ መድሃኒት ለመከላከልና ለማከም ምርምር እያደረጉ ነው፡፡ መድሃኒቱም የሚሠራው ‘’ከእጅግ ጥቃቅን ነገሮች’’ ማለትም ከጥቃቅን በሽታ ተከላካይ ‘አንቲ ቦዲዎች’ ላማዎችና ግመሎች በተፈጥሮአዊ መንገድ በሽታን ሲከላከሉ የሚያመርቱት ነው፡፡ ሳይንቲስቶች እንዳሉት አንዴ በሰዎች ከተሞከረ በሁዋላ በቀላሉ በአፍንጫ በሚነፋ ተደርጎ ይዘጋጃል፡፡ ኢንፌክሽንን ይከላከላል እንዲሁም ያክማል፡፡ ስለዚህም ምንም ክትባት አያስፈልግም፡፡ እንዳሉት ከሆነ በጣም አስደሳች ነው፡፡ አየሽ ፀረ ሳይንስ አይደለሁም፡፡ ቬዳ፡ በለማዳ ግመሎች አፍንጫ ውስጥ ሳይንሳዊ ሙከራ ሊያደርጉ ነዋ? ቪኪ፡ እንዳሉት ከሆነ እጅግ ጥቃቅን ነገሮችን ‘ናኖ ቦዲስ’ በለማዳ ግመሎች አፍንጫዎች ውስጥ ያበቅላሉ ከዚያን አይጦችን ኮቪድ ቫይረስ ያሲይዙዋቸዋል ና ያክሟቸዋል፡፡ አይጦችም በጣም እየተሸላቸው ነው፡፡ ታዲያ ለምን መርዝ ባለው ክትባት ሰውነቴን እሞላለሁ፡፡ በለማዳ ግመሎች ውስጥ በተፈጥሮአዊ ሁኔታ በአይጥ ላይ ተሞክሮ የተረጋገጠ በአፍንጫ የሚነፋ መድሃኒት ተሰርቶ መጠበቅ እያለ? ቬዳ: እና ይሄ ከመርፌ ይሻላል ነው ምትይው? በጣም ትንሽ መርፌ ሆኖ በአጉሊ መነጽር የአቶሚክ መጠን ያላቸው አቶሞችንስ ይይዛል? ለዓይን የማይታዩ ሆነው ግን የሰውነትን በሽታ የመከላከል ዐቅምን በፍጥነት ያነቃቃሉ? እናም በአከባቢ ፋርማሲ ውስጥስ ይገኛሉ? አሁን ላይስ ይገኛሉ? ከሎኪ

ከባድ የድመት ጭረት ትኩሳት ይዞሽ እኮ ነበር። ያ ግን “ያጋጥማል!”።

ቪኪ፡ አዎ፤ ቢሆንም ግን ሎኪን እወደው ነበር። እና እማዬም በህይወት

እንዳይቆይ አደረገችው።

ቬዳ: ከቆይታ በኋላ ነው እሱ የተከሰተው።

ቪኪ፡ በ መርፌ ነበር።

ቬዳ: ግራ አያጋባሽኝ ነው።

ቪኪ፡ እኔ በቦታው ላይ ነበርኩኝ እኮ።

ቬዳ: አልነበርሽም።

10
ቪኪ: በቦታው ብኖር ይሻለኝ ነበር። የሚሻል እንደሚሆን በማሰብ እማዬን እንድትገልጽልኝ ጠይቅያት ነበር። ቲክ (የጡንቻ መሸማቀቅ)ም እንዲሁ ትንሽ ነው - እና እሱም በሽታ የመከላከል ስርዓትን ወደ “ሩማቶይድ አርትራይተስ” (ቁርጥማት በሽታ) ይቀይራል። ይህ ሳይንሳዊ መረጃ ነው። ቬዳ: እውነት ነው። ነገር ግን በሳይንስ መሰረት, የምትወስጂው መርፌ ከጡንቻ መሸማቀቅ ይልቅ በድመት መቧጨርን ነው ሚመስለው። ቪኪ: የሳይንስ መረጃዎችሽን ከየት ነው ምታገኚው (ምታመጪው)? ቬዳ: ከሳይንቲስቶች ነዋ! እንዳንቺ በአሥራዎቹ ዕድሜ ካሉ ልጆች አይደለም። ቪኪ: አይ፣ እኔ የሳይንስ መረጃን እንኳን ማገኘው የሃርቫርድ ምሩቃን በሚያዘጋጁት “ፖድካስቶች” (ዘጋቢ ስርጭቶች) ላይ ነው። ቬዳ: እነሱ ሳይንቲስቶች አይደሉም፤ ጸሐፊዎች እንጂ። እኔ ማምነው በአግባቡ ሳይንስን ያጠኑ ሰዎችን ነው። ቪኪ: ታስታውሻለሽ ያኔ በ 80 ዎቹ፣ መርዛማ የሆነውን ቲሌኖል ኬሚካል በቲሌኖል ጠርሙስ ውስጥ ያስቀምጥ የነበረውን ሰውዬ? እናም አሁን በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ምርቶች የደህንነት መጠቅለያ እና መክደኛ አላቸው?

ይዬ አካባቢያዊ አደጋ በአንድ ሰው ምክኒያት ነው? እሱም ሳይንቲስት ነበር።

ቬዳ: እና በዚህ ምክኒያት ነው ቫክሲኑን ምትቃወሚው (የማትፈልጊው)?

አፍታዊ ዝምታ

ቪኪ: በእርግጥ ቫክሲኑን በጥብቅ እፈልጋለሁ፤ ግን እጅግ

አነጋገር (ስታቲስቲክስን ከግምት ካስገባን)፡-

ቬዳ: እና በሌላ በኩል የላማ (ለማዳ

11
በጣም ፈርቻለሁ ቬዳ። ይህ አመት በጣም ከባድ ነበር። ቬዳ: አዎን፣ በእርግጥም ከባድ አመት ነበር። አፍታዊ ዝምታ ስድስተኛ ክፍል እያለን ታስታውሻለሽ፣ መማሪያ ክፍል ለያይተውን እናም ሁለታችንም በተመሳሳይ ቀን ላይ የሀዘን ስሜት ተሰምቶን ነበር ከዚያም ሳናውቀው በተመሳሳይ ጊዜ ከተለያየንባቸው ክፍሎች ትምህርት አቋርጠን ወተን ሁለታችንም ‘ዴሪ ክዊን’ ወደሚባለው ቦታ ሄደን እዛው የተገናኘንበትን ቀን? ቪኪ: አዎ፣ አስታውሳለሁ ቪኪ እምባዋን እያበሰች፤ ቬዳ ከውሃው ገጽታ አሻግራ እየተመለከተች ነበር። ሰማዩ እጅግ በጣም ግልፆ ነው፤ ኮከቦችም ማንጸባረቃቸውን ቀጥለዋል። ‘ኦተር’ (የባህር አንበሳ) በሆዱ ድንጋይ ላይ ያሉትን ቅርፊቶች ሲሰነጥቅ ይታያል። ቬዳ: እኔን የማይገባኝ ግን በአንድ በኩል ለዘፋቀደ ነገሮች ያለሽ ፍራቻ እንዳለ ሆኖ፦
በስታቲስቲክስ
ቪኪ:
ግመል) የአፍንጫ እርጥበት እንደመፍትሄ መጠበቅሽ፡ቪኪ: በጣም ተቀራራቢ ነው። ይህንንም ያነበብኩት ከ “ጋርዲያን” ዘገባ ነው፣ የመረጃዬን ምንጭ ከፈለግሽ። እስቲ አንቺ ማንን ታውቂያለሽ በኮቪድ የተያዘ ሰው? እኔ ማንንም አላውቅም። የድንገተኛ ክፍል መደበኛ የታካሚዎች ቁጥርስ ቢሆን እንዴት አውቃለሁ? የጽኑ ህሙማን (አይሲዩ) ክፍሎችንስ
12  ቢሆን? በእርግጥም አስፍተን ካየነው የታማሚው ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም። አስፈላጊው ጥንቃቄ ከተደረገ በበሽታው የመያዝ እድል በጣም ኣናሳ ነው፣ ምንም እንኩዋን ተፃራሪው አመለካከት ጎልቶ ቢታይም። ልክ አንቺ ስለ ተሽከርካሪ አደጋ በምሳሌነት እንዳነሳሽው። ቬዳ: የመኪና አደጋ ሰለባዎች ግን አይሲዩውን እያጥለቀለቁ አይደለም። ከዚያም ስለ ዮሐና አስታውሺ። አፍታዊ ዝምታ ቪኪ: አዎን፣ ስለ ዮሐና አስታውሳለሁ። ቢሆንም የሱዋ ህመም ኮቪድ
አናውቅም። ቬዳ: ኮቪድ መሆኑማ እርግጥ ነበር። ከመጀመሪያዎቹ ታማሚዎች መሆኗ ነው እንጂ። ማንም አላወቀም ነበር። ጥር ነበር። ቪኪ: አውቃለሁ፤ ጥር 20/2020 ነበር። ቬዳ: ከፊሊፒንስ በምሽት በረራ “ታይፔ” ላይ በመሃል አርፋ ትመጣ እና የህመም ስሜት ውስጥ ሆና ስራ ትገባለች። እናቷን ከሳል ለመጠበቅ የምድር ውስጥ ባቡር በመጠቀም ወደቤቷ ትሄዳለች፤ ብቻዋንም ትሆናለች። ከዚያም ህይወቷ ያልፋል። በጣም ጥሩ፣ ሰው ተንከባካቢ እናም አሳቢ የነበረች ሰው የሚንከባከባት አጥታ አለፈች። ይህን ማሰብ ለኔ በጣም ከባድ ነው። ቪኪ: እኔም ይህን ማሰብ እኮ በጣም ይከብደኛል። ግን ይህ ማለት የሷ ህመም ኮቪድ ነበር ማለት አይደለም። ስለሷ ማሰብ እጅጉን ይከብደኛል። ቬዳ: ስለሷ እንዲሁም እንደሷ ስላሉ ነርሶች ባጠቃላይ አለማሰብ አልችልም፣ ቪኪ። ቪኪ የውይይቱ ርዕስ ስላስጨነቃት ማጉረምረም እና ጆሮዋን መያዝ ጀመረች ቬዳ: አንቺን በዛ ሁኔታ ውስጥ ስዬ ማየት ለኔ የማይታሰብ ነገር ነው፣ እንዲሁም አንቺን ለማዳን የሚከቡሽን ሃኪሞች፤ አያድርገው እና ህጻኗ አይቪ ወድቃ ያ ጨቅላ ጭንቅላቷ ቢገጭ እና አይሲዩው ቢሞላ ከዚያም ራሄል ከልጇ አጠገብ መሆንን ብትከለከል፤ እኔ እህትሽ አብሬሽ መሆን ባልችል፣ እናም በጣም ስራ
መሆኑን

አንቺን ለማን ጥዬ? ለምናባዊው ውሻሽ!?

ቪኪ: በቃ ተይኝ። ብቸኝነት የማይሰማኝ ይመስልሻል?

ቪኪ: አውቃለሁ።

አፍታዊ ዝምታ

13  በዝቶባቸው ስልክ ላንቺ ማቀበል ባይችሉ፤ ጉዳትሽ ጽኑ ሆኖ ደግሞ ስልክ እንኳን ብታገኚ በራስሽ መደወል ባትችዪ። ይህ ማለት ለኔ ሲኦል ነው። ቪኪ: እባክሽን አቁሚ። ሂጂ እና ግብዣውን ደሰታ ከተሞሉ ሰዎች ጋር ታደሚ ቬዳ:
በብቸኝነት መሞትስ አያስፈራትም ብለሽ ታስቢያለሽ? ይህን ሰርግ በመታደም ላይ ያለው ሰው በጠቅላላ የሚታዘበኝስ ትዝብት ማይሰማኝ ይመስልሻል? ይህንን ፍርሃትስ መቆጣጠር እንደማልችል ይገባሻል?
ለጊዜው
ለጊዜው
እሺ፣ በቃ እሺ፤ አይዞሽ!፤ አዝናለሁ ተጠግቼ አቅፌ ላበረታታሽ ባለመቻሌ።
ቬዳ:
ቪኪ:
ቬዳ:
እንደማደርገው ነው አሁን ማሰብ ያለብኝ።
በጸሎት ወይም በሂፕኖሲስ ሊሆን ይችላል ቬዳ፤ ይሄም ልክ እንደ ሲኦል ነው። አፍታዊ ዝምታ በነገራችን ላይ እኔም ስለ ዮሐና ማሰብ ይከብደኛል። ግን ይቅር ይበለኝ እና ቫክሲኑን ምፈራው ለዛ ነው፤ እኔም የሷ እጣፋንታ ይደርስብኝ ይሆን ብዬ። ቬዳ: ይህ አመክንዮአዊ እንዳልሆነ ታውቂያለሽ ቪኪ: ለግዜው ይህን በተመለከተ ስለምንም ነገር እርግጠኛ አደለሁም ቬዳ: እሺ!
ቪኪ: አደርገዋለሁ። እንዴት
ምናልባትም

አፍታዊ ዝምታ

ቪኪ: እኔም እንደዛው

አፍታዊ ዝምታ

ቪኪ: እእእ.... ትንሽ ለብቻዬ ሆኜ ማሰብ እየፈለኩ ነው

ቬዳ: አጓጉል የሆኑ ሃሳቦች እስካላሰብሽ ችግር የለውም፣ ውዷ አእህቴ።

ቪኪ: እሞክራለሁ

ቬዳ ራሄል ሙሉ ነጭ ልብስ ለብሳ ጨቅላዋን አይቪን ለማጥባት ስትወጣ

ቪኪ: በይ ሂጂ

ቬዳ: (ለስለስ ባለ ድምጽ) እሺ፤ ካልሽ

ቬዳ ወደ ራሄል እና ህጻኗ አመራች። ቪኪ አይኗን ወደ ባህር ዳርቻው አፋፍ

14
ተመለከተቻት
አማተረች ቬዳ: ቻው! አይዞሽ፣ ሁሉም ነገር ይስተካከላል። (በእጆቿ እራሷን እያቀፈች ለራሷ ለስለስ ባለድምጽ) አይዞሽ። ቀና ብላ ከዋክብቶችን አየች። የባህር አንበሳ ድምጽም በቅርበት ይሰማል። ተፈጸመ
15  © 2021 KAREN HINES ምንም አይነት የዚህ መጽሐፍ ክፍል በማንም ቢሆን ማባዛት፤ በምስልም በኤሌክትሮኒክስም ወይንም በሜካኒካልም አይችልም። በተለየ ፍቃድ ማለትም ለትምህርታዊ አላማዎች እባክዎን ቦካ ዴል ሉፖ በ info@bocadellupo.com ያግኙት። ዲዛይን፡ ካቢን + ከብ ዲዛይን ካረን ሃይንስ ተሸላሚ የትያትር፣ የቴሌቪዥን እንዲሁም የፊልም ተውኔት ፀሃፍት፣ ተዋናይት ብሎም ዳይሬክተር እና ተሸላሚ የሀገር አቀፍ መፅሄት ፀሃፍት ነች። በቅርብ ጊዜም የቴአትሩ የሲሚኖቪች ሽልማት የመጨረሻ ተወዳዳሪ እንዲሁም የፖችሲ ተውኔት እና ድራማ፣ የሙከራ ክፍል የገቨርነር ጀነራልስ የስነፅሁፋዊ የድራማ ሽልማት የሁለት ጊዜ የመጨረሻ ተወዳዳሪ ነች። ሃይንስ የሲቢሲ ኤሚይ ሽልማት አሸናፊ የሆነው የዜና ክፍል ላይ ካረንን በመሆን ለሶስት ተከታታይ ምዕራፎች የቀረበች ሲሆን የኒዮርክ ፊልሞችም ላይ በቶሮንቶ በብዙ አስቸጋሪ የረዳት ተዋናይነትም ላይ ተሳትፋለች። የፖቺን ገፀባህሪይ የተላበሰው አጭር ፊልሟ በአለም አቀፍ ደረጃ የቀረበ ሲሆን የግሏ የሆነው ክራውል ስፔስ (በቅርቡ በቦካ ዴሉፖ የቀረበ) በሰፊው ታይቷል፤ (ክራውል ስፔስ ባሁኑ ሰዓት የሲቢሲ ፕለይ ሚ ፖድካስት ነው)። የመጨረሻው ‘ኦል ዘ ሊትል አኒማልስ አይ ሃቭ’ የተሰኘው የሃይንስ ፀለምታዊ ኮሜዲ ከ 2020 የቶሮንቶ መክፈቻው በፊት በኮቪድ-19 ምክኒያት የተቋረጠ ቢሆንም በዝጉ ጊዜ ተቀይሮ በሜይ ሞንትሪያልስ ጃማኢስ ሉ ፌስቲቫል ላይ ቀዳሚው የፈረንሳይኛ ትርጉም ይሆናል። ከጥቂት የአሁኑ የቦካ ፕሮጀክቶች ጋር ካረን በአሁኑ ሰዓት አራተኛውን የፖቺን ተከታታይ ክፍል በመፃፍ ላይ ትገኛለች፤ ፖቺይ 4፣ ልቤ ይሰበርልሃል።

Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.