የማይከዳ ወዳጅ (Amharic) Jesus Never Fails booklet

Page 1

የማይከዳ ወዳጅ (
) በሮበርት ራን (ቄስ) የሉተራን ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን መሥራች ህትመት፡ A publication of the LUTHERAN HERITAGE FOUNDATION 51474 Romeo Plank Rd. Macomb, MI 48042 USA www.LHFmissions.org
JESUS NEVER FAILS

Amharic Jesus Never Fails

1st edition, printed 10,000 copies, May 2019.

Copyright ©2018

Published by Lutheran Heritage Foundation 51474 Romeo Plank Road Macomb, Michigan 48042, USA.

www.LHFmissions.org info@LHFmissions.org

The translation and publishing of this book has been made by Lutheran Heritage Foundation. All rights reserved. No part of this book may be reproduced, stored in a retrieval system, or transmitted, in any form or by any means, electronic, mechanical, photocopying, recording, or otherwise, without the prior written permission of Lutheran Heritage Foundation.

Funding for the publication of this volume has been provided by the Sukup Family Foundation.

Soli Deo Gloria!

Not for commercial use.

የማይከዳ ወዳጅ
የማይከዳ ወዳጅ (ትርጉም፡ ቄስ ድንቁ ለሜሳ በቶ)
እትም መጋቢት 2011 ዓ.ም. 10,000 ቅጂ የዚህ መጽሐፍ ትርጉምና ሕትመት የተካሄደው አድራሻው ከላይ በተጠቀሰው በሉተራን ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን ነው። ሙሉ መብቱ የተጠበቀ ነው። የዚህን መጽሐፍ የትኛውንም ክፍል እንደገና ለማባዛት፣ እንደገና እንዲገኝ አድርጎ ለማስቀመጥ፣ ወይም ለማስተላለፍ፣ በየትኛውም ቅርጽና መንገድ፣ በኤሌክትሮኒክ፣ በሜካኒካል፣ ቅጂ ለማድረግ፣ በድምፅ ለመቅረጽ፣ ወይም በሌላ መንገድ ለመጠቀም፣ አስቀድሞ ከሉተራን ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን የጽሑፍ ፈቃድ ማግኘት ያስፈልጋል። ለአገር ውስጥ ግንኙነት የሚከተለውን ፖስታ ሳጥን ቁጥር ወይም ድረገፅ መጠቀም ይቻላል። ሉተራን ሄሪቴጅ ፋውንዴሽን-ኢትዮጵያ ፖ.ሳ.ቁ. 687 ኮድ 1250 አዲስ አበባ ኢትዮጵያ info@LHFmissions.org የዚህ መጽሐፍ የሕትመት ወጪ የተሸፈነው በ ሱኩፕ ፋሚሊ ፋውንዴሽን ነው። ክብሩ ለእግዚአብሔር ብቻ ይሁን!
የመጀመሪያ
የዚህን ጽሁፍ አጠቃቀም አስመልክቶ የቀረበ ምክር፡ • በሕይወታቸው ውስጥ ለሚገጥማቸው ጥያቄ መልስ ለሚሹ ሰዎች ወንጌሉን ለማካፈል • ለአዳዲስ ወይም በፍለጋ ላይ ያሉ አማኞችን ወይም ጓደኛን ለማበርታታት፤ • ቄሶች/መጋቢዎች ወይም እረኞች ለሚያማክሯቸው ሰዎች፤ ታመው ለተኙ፤ ወይም አቅመ ደካማ ሰዎችን በሚጎበኙበት ጊዜ ይህን መልዕክት ሊያካፍሉ ይችላሉ። ይህ አጭር ጽሁፍ ምንጊዜም ከማይከዳህ ብቸኛ ወዳጅ ጋር ያስተዋውቅሃል። ስሙም ኢየሱስ ነው። ኢየሱስ ለእኛ መውደቅና ኃጢአት ይቅርታን ለማስገኘት በእግዚአብሔር ተላከ። ይቅር እንዲለን፤ እንዲመራንና ከሰይጣንና ከክፉ ሁሉ እንዲጠብቀን በኢየሱስ ልንታመን እንችላለን። በዚህ በማይከዳ ወዳጅ በኢየሱስ ላይ ለምን እምነትህን ማድረግ እንደሚገባህ ይበልጥ ለመረዳት ይህን ጽሁፍ ማንበብህን ቀጥል ።
የማይከዳ ወዳጅ! የመውደቅ ስጋት የዘመናችን እንቆቅልሽ ሆኗል። ውድቀት በየቀኑ በተለያየ መልኩ ሲገለጥ በማናይበት ዓለም ውስጥ የምንኖር ቢሆን ኖሮ ሕይወት መልካም ይሆን ነበር። ውድቀትን በተመለከተ መልካም ዜና አለ። ይህም ድል መነሳቱ ወይም መሸነፉ ነው። ከዚህ ቀደም ራስህ ወድቀህ ወይም ደግሞ ሌላ ሰው ከድቶህ ከሆነ፤ ውድቀትን ድል የነሳውን ወይም ያሸነፈውን እርሱን ላስተዋውቅህ እወዳለሁ። ይህ እንዴት እንደሆነ ማወቅ ትፈልጋለህ? አዎን፤ የዚህ ትንሽ ጽሁፍ ዓላማም ይኸው ነው፤ ማለትም ከዚህ በፊት ያጋጠሙህንም ሆነ ወደፊት ሊገጥሙህ የሚችሉትን ውድቀቶች አልፈህ የምትሄድበትን መንገድ ማሳየት ነው። እውነት ነው፤ ልንጋፈጠው የሚገባን ውድቀት አለ። እርሱም ኃጢአት ነው። ውድቀትን ለመጀመሪያ የቀመሱት በኤደን ገነት የነበሩት የመጀመሪያዎቹ ወላጆቻችን እንዲሁም የገዛ ወላጆቻችን ብቻ አይደሉም። እኛም ያንን ውድቀት ወርሰናል። ኃጢአት ዐለማችንን አጥለቅልቋል። ኃጢአት፤
በሞት፤ በተስፋ መቁረጥና፤ ግራ በመጋባት አዘቅት ውስጥ ጥሎናል። ነገር ግን ጉዳዩ በዚህ ብቻ እንደማያበቃ ልነግርህ እወዳለሁ። ከዚህ ችግር መውጫ መንገድ ተዘጋጅቷል። ሰዎች/ ጓደኞች ይከዱናል እውነት ነው ሰዎች፤ ወዳጆቻችን እንኳን ቢሆኑ፤ ይከዱናል። የተማመንነው ሰው ትቶናል። የወደድነው ሰው አሳዝኖናል። ወዳጅነታችንን ያሳየናቸው ሰዎች ወዳጅነታቸውን ነፍገውናል። ስለዚህም ሰዎች እንዲሁም ወዳጆቻችን ክደውናል፤ ያለንበትን ሁኔታና አጋጣሚም አልተረዱም ወደሚል፣ ልብ የሚያዝል ድምዳሜም ደርሰናል። ሰዎችና ወዳጆች ያልናቸው ወገኖች እጅግ በምንፈልጋቸው ጊዜ ትተውናል። እስቲ ቆም ብለህ ይህን ለመገመት ሞክር! እግዚአብሔር ወዳጆቹ እንዲሆኑ ፍፁም አድርጎ የፈጠራቸው ሰዎች በከዱት ጊዜ የተሰማውን ሃዘን ልትገምት ትችላለህ?
ንብረት ይተወናል
ንብረት በማከማችት ተግባር
አሳልፈህ ይሆን? ይህ በብዙዎች ዘንድ የተለመደ ውድቀት ነው፤ እየሆነብን እያለ እንኳን የማናስተውለው። ደስታን የሚያስገኝልን እየመሰለን ጉልበታችንን፤ ጊዜያችንን፤ ዕውቀታችንን ብዙ ንብረትና ሀብት በማከማቸት ላይ እናሳልፋለን። ከዚያም አንድ ነገር ይፈጠርና የቱንም ያህል ያከማቸነው ገንዘብ፤ ንብረትና፤ ቁሳቁስ እርካታ ሊያመጣልን ብሎም ከፍርሃትና ከሥጋት ሊያወጣን እንደማይችል እንገነዘባለን። አዎን ንብረት/ቁሳቁስ ይከዳናል። ጤና ይከዳናል በወዳጅና በሀብት መክዳት አስቸጋሪነት ላይ የጤና መክዳት ሲጨመር ምን ይሰማን ይሆን? አንዳንዶች፤ “ጤና ካለህ ሁሉም አለህ፤” ይላሉ። ግን ጤናችን ሲከዳን ምን እንሆን ይሆን? “ካንሰር” “የልብ ሕመም” የሚሉት ቃላት የእኛን የጤና ሁኔታ አስመልክቶ ሲነገሩ ከመስማት የሚበልጥ አስፈሪ ወይም አስደንጋጭ ነገር ያለ አይመስልም። ወዴት እንሸሻለን? ሐኪሙ “ከዚህ በላይ ልናደርግልህ የምንችለው ነገር ሊኖር አይችልም” ሲለን
ሕይወትህን
ላይ
ማነው ሊያወጣን የሚችለው። ጤና ሲከዳን
ይኖር ይሆን? ኢየሱስ ፈጽሞ አይተውህም ፈጽሞ ሊከዳህ ወይም ሊተውህ የማይችል አንድ ወዳጅ እንዳለህ ታውቃለህ? አዎን፤ ጓደኞችህ ሊተውህ ይችላሉ፤ ንብረትም ሊከዳህ ይችላል፤ ጤናህም እንዲሁ። ነገር ግን . . . ፈጽሞ ማይከዳህ አንድ ወዳጅ አለ። ይህን የምናውቀው እንዴት ነው? ይህን የምናውቀው፤ ኢየሱስ መሠረታዊና እጅግ ጥልቅ የሆነውን ችግራችንን መፍታት በመቻሉ ነው። ይህንን ጥልቅ ችግር መፍታት የቻለበት መንገድ ሊያስገርምህ ይችል ይሆናል፤ ዳሩግን የገዛ ራስህን ውድቀት፣ የወዳጅንም ሆነ፤ የንብረትን፤ እንዲሁም የጤናን መክዳት ሁሉ በድል እንድትወጣ
ተስፋ
ወይም እንድታሸንፍ የሚያስችልህ ነው። ምናልባት መሠረታዊው/ጠሊቁ ችግራችን ምን እንደሆነ እንኳን ለይተን አናውቅ ይሆናል። ያም የጓደኛ፤የንብረት፤ወይም የጤና ፍላጎት አይደለም። አዎን እነዚህ አይደሉም፤ ዳሩ ግን መሠረታዊው ፍላጎታችን ለውድቀታችን፤ለጉድለታችን ወይም ለኃጢአታችን ይቅርታን ማግኘት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል፡ “ቸርነት የሚያደርግ የለም፥ አንድ ስንኳ የለም…ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል” (ሮሜ. 3:12፡23) ። አስደናቂው የኢየሱስ ወዳጅነት! “ነፍሱን ለወዳጆቹ ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም።” ኢየሱስ፤ ከእርሱ በተለየን ጊዜ የገባንበትን ትልቁን ችግራችንን ተመልክቷል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚል፡ “ልዩነት የለምና፤ ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል (ሮሜ 3:23) ፤ በተጨማሪም፡ “ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና” (ሮሜ. 3፡28) ይላል ።
መንገዱን የከፈተልን ኢየሱስ ብቻ ነው። “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም” (ኤፌ. 2:8፣9) ። ትልቁ ችግራችን በኢየሱስ መፍትሔ አግኝቷል ለችግራችን መፍትሔ የሰጠበት መንገድ እንግዳና የሚገርም ነው። “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል” (ሮሜ 5:8)። እንግዲህ ብናስተውለውም ባናስተውለውም፤ እዚህ እንደተገለጸው በእጅጉ የሚያስፈልገን ነገር የኃጢአት ይቅርታ ነው። ይህንንም ኢየሱስ አቅርቦታል። ይህን እንዴት እናውቃለን? እርሱ ወደ መስቀል ሄደ፤ በዚያም ከጨለማና ከኩነኔ አዳነን። “እርሱ ከጨለማ ሥልጣን አዳነን፥ ቤዛነቱንም እርሱንም የኃጢአትን ስርየት ወዳገኘንበት ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግሥት አፈለሰን (ቆላስይስ 1:13-14) ።
ለጥልቁ ችግራችን መፍትሔ የሰጠው እንዴት ነው? “እኛ በእርሱ[በክርስቶስ] ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ [እግዚአብሔር] ኃጢአት አደረገው” (2ኛ ቆሮንቶስ 5:21) ። በኢየሩሳሌም የሚፈጸምበትን መከራ እና ሞት እያወቀ ፊቱን ወደዚያው አቀና። እንዲህ አለ፡ “እኔ [ነፍሴን] በፈቃዴ አኖራታለሁ እንጂ ከእኔ ማንም አይወስዳትም። ላኖራት ሥልጣን አለኝ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ”(ዮሐ.10:18)። ስለዚህም ተራ ወንጀለኛ በሚቀበለው መከራና ስቃይ ተካፋይ ሆነ። ተዘበተበት፤ ተገረፈ። የእሾህ ጉንጉን (አክሊል) በራሱ ላይ አኖሩ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ለዓለም ኃጢአት ወደሚሞትበት ወደ ቀራንዮ ኮረብታ ወጣ። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና” (ዮሐ. 3:16) ።
በመስቀል ላይ ያደረገው አንድ ነገር ቢኖር የአንተን የኃጢአት ዕዳ መሸከም ነው። “የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል። በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” (1ኛ ዮሐ.1፡ 7፣9)። የእኛን ኃጢአት ተሸክሞ ተሰቃየ፣ ሞተም፤ ነገር ግን በጠላቶቻችን ሁሉ ላይ የተቀዳጀውን ድል ያሳይ ዘንድ ከሙታን ተነሣ!በሥቃዩና ሞቱ. . . የእኛን ጥልቅ ችግር ፈቷል አስታውስ፣ ለውድቀታችን መድሃኒትና ትልቁ መሻታችን ወይም ፍላጎታችን የኃጢአት ይቅርታ ነው። እንግዲህ ይህንን ጥያቄ ላቀርብልህ እወዳለሁ፤ እርሱ ለትልቁ ችግራችን ማለትም ለኃጢአት ይቅርታ መፍትሔ ከሆነልን፤ ከዚያ ለሚያንሱት ችግሮቻችን ወይም ጉዳዮቻችን መፍትሔ ሊሰጥ አይችልምን? በእርግጥም ወዳጆቻችን፣ ሀብትና ንብረት፤ እንዲሁም ጤና ሊክዱን/ሊጥሉን ይችላሉ። ነገር ግን . . .
ኢየሱስ ፈጽሞ አይጥልህም “ዓመፃቸው የተሰረየላቸው ኃጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው” (ሮሜ 4:7)። ነገር ግን መናፍስት ስለ ተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ፥ ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ (ሉቃስ 10:20) ። አዎን፣ እንግዲህ ማረጋገጫ አለህ፦ ኢየሱስ ፈጽሞ አይተውህም!
በገጠሩ የሜኒሶታ አካባቢ ይኖሩ በነበሩት ገበሬ ወላጆቼ ቤት ግድግዳ ላይ ከተጋቡበት ዕለት ጀምሮ ለ62 ዓመታት ተሰቅሎ የነበረ አንድ ጥቅስ እንዲህ ይላል፦ ኢየሱስ ፈጽሞ አይጥልም (ምስሉን ከዚህ መጣጥፍ የጀርባ ገፅ ላይ ተመልከት)። ወላጆቼ በወራት ጊዜ ውስጥ ተከታትለው ከሞቱ በኋላ ሁላችንም ካደግንበት ቤት ማስታወሻ የሚሆነንን ነገር መምረጥ ጀመርን። እኔም ከላይ የተጠቀሰውን የግድግዳ ጥቅስ መርጬ ወሰድሁ። ዛሬ ይህ የግድግዳ ጥቅስ ቢሮዬ ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሎአል። ጥቅሱን በቢሮዬ ግድግዳ ላይ ከማኖሬ በፊት ወደ አንድ ማተሚያ ቤት ወስጄው የግድግዳ ጥቅሱ የመጽሐፍ ዕልባት (ቡክ ማርክ) ሆኖ ሊታተም ይችል እንደሆን ጠየቅሁ። ዛሬ፤ ይህ የመጽሓፍ ዕልባት (ቡክ ማርክ) በብዛት ተራብቶ በዓለም ላይ ተሰራጭቷል። የዚህን የግድግዳ ጥቅስ መልዕክት ግልፅ ለማድረግ ይህ እያነበብህ ያለው መጣጥፍ በብዙ የዓለም ቋንቋዎች በመተርጎም ላይ ይገኛል። ቄስ ሮበርት ራን የሉተራን ሄሪተጅ ፋውንዴሽን መስራች

Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.