The King / Amharic

Page 37

አዎን። ሁሉም ነገር እንደ እግዚአብሔር እቅድ እየተከናወነ ነበር። እራት በሚበሉበት ጊዜ እየሱስ እንጀራውን አንስቶ እግዚአብሔርን አመሰገነ። ከዚያም ቆረሰና “ይህ ሥጋዬ ነው አለ። ወይኑንም ቀዳና ይህ ስለብዙዎች የሚፈስሰው በእግዚአብሔርና በሰዎች መካከል የሚሆን የቃል ኪዳን ደሜ ነው“ አላቸው።

እንዴት እንግዳ ነገር ነው? ደ

ቀመዛሙርቱም እንደዚህ ያስቡ ይመስለኛል። ነገር ግን ማንኛቸውም አልተናገሩም። የሆነው ሁሉ የገባቸው ካለፈ በኋላ ነገር ሁሉ ከተፈጸመ በኋላ ነበር። እየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ በዚያች ሌሊት ሊሆን ያለውን ነገር ይነግራቸው ነበር። ”ሁላችሁም ለብቻዬ ትታችሁኝ ትበታተናላችሁ“ አለ። ጴጥሮስ ግን ”ሁላቸውም ቢተውህ እኔ ግን አልተውህም“ አለው።

እየሱስ ግን ”አዎን ትተወኛለህ። በዚህች ሌሊት ዶሮ ሁለተኛ ሳይጮህ ሶስት ጊዜ ትከደኛለህ“ አለው።

ጴጥሮስ ”ፈፅሞ አይሆንም“ ሲል፤ ሌሎችም ደቀመዛሙርት ባንድ ላይ የእርሱን አባባል አስተጋቡ። ከዚያ እየሱስ አስራ አንዱን ደቀ መዛሙርት ይዞ ጌቴ ሰማኒ ወደሚባለው የወይራ አትክልት ሥፍራ ሔዱ። እየሱስ እርሱ ሲጸልይ ሲሄድ በዚያ እንዲቆዩ ነገራቸውና ጴጥሮስን ያዕቆብንና ዮሀንስን አሰከትሎ ወደፊት ሔደ።

እነዚህ ሶስት የሞተችዋን ልጅ ሲያስነሳ አብረውት የነበሩት ናቸው?

35


Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.