መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ንስንስ ትኩረቷን በLBQ ላይ አድርጋ በየሩብ ዓመቱ በኩዊር ኢትዮጵያ የምትታተም መጽሔት Nisnis - A quarterly magazine published by Queer Ethiopia focusing on LBQ Issues አጋሮቻችን
ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ queerethiopia.com ethioqueer QueerEthiopia etqueerfamily@gmail.com t.me/queeret «ኩዊር ኢትዮጵያ» የተለያዩ ፆታዊና ወሲባዊ ዝንባሌ ላላቸው ኢትዮጵያዊ ኩዊር ሴቶች እንዲሆን ታስቦ በኩዊር ሴቶች የተመሠረተ አማራጭ ምኅዳር ነው። ይኽውም ሌዝቢያን፣ ባይሴክሽዋል ወይም ኤሴክሽዋል የሆኑ ሴቶችንንና ትራንስ ሴቶችን ያካትታል። ይህ ምኅዳር የኩዊር ማኅበረሰብ ታሪክ እና የሕይወት ልምድ ትልቅ ሥፍራ የሚይዝበት ነው። እንደ’ኩዊር ማኅበረሰብ የዕለት ተዕለት ሕይወታችንን ገጠመኞች፤ የተለያዩ ሰዎችን የግል ታሪኮች፤ ቃለ- መጠይቆች እንዲሁም ሥነ-ጥበባትን እንደምናካትት ተስፋ እናደርጋለን። ከነዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ እና በዳያስፖራ ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ራሳቸውን ሆነው የሚመጡበት የበይነ-መረብ ማኅበረሰብ መድረክ ሆኖ እንዲያገለግል ማስቻል ፍላጎታችን ብቻ ሣይሆን ጥረታችንም ጭምር ነው።
1 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
2 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ማውጫ አጋሮች አሏችሁ? 42-00 04-8 አጋሮች ከነሁለመናችን ሲደግፉን የአርታዒያን መልዕክት 12-23 ወንድማዊ ፍቅር፥ ያለቅድመ ሁኔታ ተቀባይነት 28-30 ሲረጋገጥ 9-11 ኢትዮ ኩዊር ፖድካስት ውይይት 38-41 የተዘረጉ ክንዶች: የአክስቴን ልጅ ስቀበል 32-34 የአንዲት ሴት አጋርነት ጉዞ 24-27 ፍርሃትን ማሰስ 35-37 ከአጋርነት ወደኩዊርነት ግንዛቤ
ማሰብ ማቆም እንዳለብኝ ተረዳሁ።” ትለናለች። ታሪኳ በትውልድ የተሰጣቸውን
3 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
የሚቀበሉንን ኢትዮጵያውያን ማግኘት ሁሌም የሚያስደስት ነገር ነው፤ ያ ሰው የ69 አመት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ልጅ አባት እንደሆነ ማወቅ ደግሞ በደስታ ሊያስለቅስ የሚችል ነገር ነው። ልጃቸው በነገረቻቸው ወቅት አቶ አለማየሁ መልሳቸው “እወድሻለሁ፣ ልጄ ነሽ የፈለግሽውን መሆን ትችያለሽ።” ነበር እንኳን ወደሰባተኛው የንስንስ እትም በሰላም መጣችሁ፣ በዚህ እትም አጋርነት ላይ እናተኩራለን ። አጋር የምንላቸው ከራሳቸው የተለዩ ለሆኑ ሰዎች እኩልነት እና መብት የሚቆሙን ነው። በኛ መነጽር ስናየው የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪዎችና የሁለቱ ጾታ አባላት የሆኑ ሰዎች የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን ተቀብለው መብታቸው እንዲከበርላቸው ከጎናቸው የሚቆሙትን ማለት ነው። በሚያስፈልገን ወቅት ድጋፍ ይሰጡናል ከኛ በላይ መሰማት ይችላሉ እናም በተለይም እንደኢትዮጵያ ባሉ ሀገራት መብታችን እንዲከበር ሁኔታዎችን ማሻሻል ይችላሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ለመብታችን መናገር እስር እና ሞትን የሚያስከትል አደጋ ያለው ነው። አጋሮቻችን ግን ከኛ በተሻለ ደህንነታቸው ተጠብቆ መናገር ይችላሉ። በዚህ እትም አጋርነትን በተለያየ መልኩ እንመለከተዋለን። አንዷ ባለታሪካችን የጾታ መደብ ለሌላቸው ሰዎች እንዴት አጋር እንደሆነች የምትነግረን የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሴት ናት። “ራሴን ለጭቆና ደረጃ ስሰጥ እና በትውልድ የተሰጠኝን ጾታ በመቀበሌ ያገኘሁትን ልዩ መብት ለመጠበቅ ስሞክር አገኘሁት። ስህተቶቼን ለማወቅ ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም። ብዙዎች እንደሚሉት ሁላችንም ነጻ እስካልሆንን ድረስ ማናችንም ነጻ አይደለንም። እናም ነጻነት በትንሽ አቅርቦት ያለ እና ለሁላችንም የማይዳረስ
ጾታ የሚቀበሉ ሰዎች ለምን አጋር መሆን እንዳለባቸው የሚያሳይ ነው። ሌላዋ የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ኢትዮጵያዊ ሴት የአክስቷ/አጎቷ ልጅ ስለጾታዊ ማንነቷ ስትነግራት እንዴት በደስታ እንደተቀበለቻት ታስታውሳለች። የፈጠረችውን ቅርርብ እና ለአክስቷ/አጎቷ ልጅ የፈጠረችው የደህንነት ስሜት በኢትጵያውያን ላይ ያለንን እምነት የሚመልስ ነው። ስሜታዊ እና ቁምነገር የተሞላበት ከሁለት እህት እና ወንድም ጋር ያደረግነው
የናሆም በጣም ቀለል ያለ
መንገድ ተስፋ የሚሰጥ ነው። “ጥያቄው በጣም አስፈላጊው ነገር ምንድነው የሚለው ነው፣ በተሳሳተ አመለካከታችሁ ምክንያት የቤተሰባችሁን አባል ለማጣት ዝግጁ ናችሁ?” ሲል ይጠይቃል። ቤተሰቦቻችን ከጎናችን ለመቆም እንደሚችሉ የሚያሳይ ነው። ልዋም የምታገኘው ድጋፍ እና በዚህም የሚሰማት ሰላም አጋሮች ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆኑ የሚያሳይ ነው። ሁለቱ ባለታሪኮቻችን ከአጋርነት እንዴት ወደተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነታቸውንe ወደመቀበል እንደሄዱ ይነግሩናል። “ከኮቪድ ወረርሽኝ መነሳት ሁለት ወራት በኋላ የጾታዊ ማንነቴ ግራ የሚያጋባ ሆኖ አገኘሁት። ለአንድ ማህበረሰብ ደጋፊ በመሆን በትንሹም ቢሆን ለመብታቸው መታገል እና የማህበረሰቡ አባል መሆን የተለያዩ ነገሮች ናቸው።” ትለናለች አንዷ ባለታሪካችን። ለአንባቢያን “ትልቁ አጋራችሁ ማነው ለምን” ስንል ለጠየቅነው ጥያቄ ያገኘናቸው መልሶች ኢትዮጵያ ምንም እንኳን ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችንና ትራንስጀንደሮችን ጠል ሀገር ብትሆንም ከኢትዮጵያዊነታችን እና የጾታ ማንነታችን ጋር የሚቀበሉን እና የሚደግፉን ድንቅ ሰዎች በመሀላችን እንዳሉ የሚያስታውሰን ነው። ንስንስን ስለምታነቡ እናመሰግናለን። ለእትሙ ታሪካችሁ ላጋራችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው ያለእናንተ ይህ እትም መሳካት አይችልም ነበር። መልካም ንባብ
የአርታዒያን መልዕክት
አድርጌ
ቃለመጠይቅም የእትማችን አንዱ አካል ነው።
እህቱ የተቀበለበት
አጋሮች ከነሁለመናችን ሲደግፉን
4 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
በፎቶ የሚታዩት አቶ አለማየሁ ከበደ ከልጃቸው ብሌን ጋር የነበራቸውን ውይይት ያስታውሳሉ “በራሴ እንግዲህ ገና ቃሉን ስሰማ ምንም ነገር አላልኩም። ታዲያ ምናለበት አንቺ ደስተኛ ከሆንሽ ምንም ለምን አትሆኚም ነው ያልኳት።”
አቶ አለማየሁ ከበደ እድሜያቸው ወደ69 ይጠጋል። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ልጅ አባት ናቸው። ንስንስ አጋር ስለመሆናቸው ልታዋራቸው እንደምትፈልግ ስንነግራቸው እጅግ ደስተኛ ነበሩ። ማህበረሰቡን ሊደግፉ የሚችሉበትን መንገዶች እየፈለጉ
እንደነበር እና ይህ ትልቅ እድል
አመሰግናለሁ። ሁልግዜ ጭንቅላቴ ውስጥ ያለ ነገር ነው”
ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ኢትዮጵያዊ ልጅ የሚቀበል አባት ማግኘት ሎተሪ እንደማሸነፍ ነው። ድምጽ ለመሆን ፍቃደኛ
ጾታ አፍቃሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደርስባቸውን ተቃውሞ በአካል እና በኦንላይን
የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ለቤተሰቦቻቸው ስለማንነታቸው ማሳወቅን ያስቡ እንደሆን ሲጠይቅ የሁሉም በሚባል ሁኔታ መልሳቸው አናስብም ነበር። አንዱ መላሽ “እናቴ
መሀል አንዷ ትክክለኛ ስሟን ብንጠቀም ችግር እንደሌለውም ነገረችን።
ብዙ ኢትዮጵያውያን
ነገር እኔ በደንብ ያወቅኩት እዚህ አሜሪካን ሃገር ከመጣሁ በኋላ ነው። ግን ሃገር
የመግለጽ መብት እንደምትሰጥ ተመለከቱ። ሰዎች ተፈጥሯዊ የነጻነት መብት አላቸው የሚለው
ነው ይላሉ። ይህ እፍረት ወላጆች ልጆቻቸው ራሳቸውን እንዲሆኑ እንዳይፈቅዱ ስለሚያደርግ ያላቸው ግንኙት እንዲበላሽ ያደርገዋል። አቶ አለማየሁ ልጃቸውን እንዲቀበሉ ያደረገው ነገር ለልጃቸው ያላቸው ጥልቅ ፍቅር እና ስለወሲባዊነት ያላቸው መረዳት ነው። ወሲባዊነት እንደየሰው የሚለያይ ነገር ነው ይላሉ። እንደአብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን
5 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
እንደሆነ ነገሩን። በኢትዮጵያ የተመሳሳይ ጾታ ማህበረሰብ ውስጥ አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት በቂ እድል የለም ይላሉ አቶ አለማየሁ። ለቃለመጠይቅ አድራጊያችን ይህን ከመንገር አልተቆጠቡም። “መጀመሪያ ይሄንን ቃለመጠይው ለማድረግ ስለጠየቅሽኝ በጣም
የሆነ አባት ደግሞ እንደብርቅዬ እንስሳችን ዋልያ በቀላሉ የማይገኝ ነው። የተመሳሳይ
በሚሰጡ አስተያየቶች ማየት ይቻላል። ለማህበረሰቡ አባላት ተብሎ የሚዘጋጅ ጽሁፍ እንኳን ብዙ ጊዜ ወደስድብ ያመራል። ለምሳሌ በቅርቡ በኢትዮኩዊር ፖድካስት ላይ አንድ ሴት ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ እህቷ ያላትን ድጋፍ ስትገልጽ “አንቺ እህቴ ብትሆኚ ያንቺ ምርጫ ሞት መሆኑን አሳይሽ ነበር ሬሳ” የሚል አስተያየት ተጽፎ ነበር። እንደ 2007 የፒው ግሎባል አቲትዩድስ ጥናት መሰረት 97 ፐርሰንት የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ መሆን በማህበረሰቡ ተቀባይነት ማግኘት እንደሌለበት ያምናሉ። በዛ ጥናት
ያለመቀበል ደረጃን የሚበልጡት ሁለት ሀገራት
ከፕሮጀክቱ
መረጃ
ስለተመሳሳይ
አሁንም አልተቀየረም።
ከምታውቅ ሞቴን እመርጣለሁ” ብሏል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረጉ የጾታ እና ጾታዊ ማንነት ንግግሮች ብዙውን ጊዜ ወደጥላቻ ስድቦች ያመራሉ። እውነታው ይህ በመሆኑ ለዚህ ጽሁፍ ቃለመጠይቅ የምናደርግለትን ሰው ማግኘት ከባድ ይሆናል ብለን አስበን ነበር። ይሁንና ብዙ ሰዎችን ማግኘት ቻልን። ቃለመጠይቁን ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆኑት
ላይ ከተሳተፉት 47 ሀገራት የኢትዮጵያ
ብቻ ነበሩ።
የተገኘው ይህ
15 አመታት ያስቆጠረ ቢሆንም
ጾታ አፍቃሪዎች ያለው አመለካከት ግን
ኩዊር ኢትዮጵያ በፌስቡክ
ምእራባውያን ያመጡት ሰይጣናዊ ነገር ነው የሚሉትን ማንነት እንዴት አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ሊቀበሉት ቻሉ። በአሜሪካ ለሚኖሩት አቶ አለማየሁ ይህ ሰዎችን የማክበር እና ለሴት ልጃቸው ቦታ የመስጠት ያህል ቀላል ነገር ነው ይላሉ። “በእውነቱ ይሄንን
ቤት እንዲህ አይነት ነገር አለ፣ ይሄ ፍናፍንት ነው፣ ይሄ ወንዳገረድ ነው፣ እቺ ሴታገረድ ነች፣ እየተባለ ይወራ ነበር እና ሰዎቹ ብዙዎቹ ቤት ውስጥ አገልጋዮች ናቸው። እና እንደስድብ ነበር የሚጠቀሙበት ይሁኑም አይሁኑም ምንም አይገባኝም ነበር ግን ወሬውን እሰማ ነበር።” አሜሪካ ከገቡ በኋላ በስራ ቦታቸው የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን ተዋወቁ። አሜሪካ ለሰዎች በጾታ ማንነታቸው ያልተገደበ በነጻነት የመኖርና ጾታቸውን
አመለካከት እሳቸውም ነገሩን የሚመለከቱበትን መንገድ እንዲቀይር አደረገ። አሜሪካ ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች መብት መከበር ቢያስደንቃቸውም የማህበረሰቡ አባል የሆነች ልጅ ትኖረኛለች ብለው አላሰቡም። “የእኔ ልጅ እንዲህ ትሆናለች ብዬ አልጠበኩም ነበር። ግን ነኝ ብላ ስትነግረኝ ምንም አይነት ሃዘኔታ ስሜት አልተሰማኝም። “የፈለግሽውን ሁኚ እኔ እወድሻለሁ ልጄ ነሽ እዚህ አለም ላይ አምጥቼሻለሁ እስከፈለግሽው
ልጃቸውን
በተጨማሪ አብዛኛው በስደት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ማንነቷን እንደችግር እንደሚያዩት ተረድተው ነበር። ይህም የሆነው ወላጆች ስለልጆቻቸው ይህን እውነት ሲያውቁ ስለሚያፍሩ
የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጠል ከመሆን ይልቅ ሰዎች የማህበረሰቡን አባላት መቀበል እንዳለባቸው ይናገራሉ። “ልጄ ምንም አልሰረቀችም፣ ሌባ አይደለችም፣ ዝሙት አልፈፀመችም፣ ምንም የሚያሳፍር ነገር አላደረገችም። እንደዚህ ነኝ ብላ በነገረችኝ ግዜ እኔ እሷን የማልቀበልበት ምንም ምክንያት የለኝም። ጥፋት አይደለም ይሄ በስሜት የሚመጣ ነገር ነው። ሰውን
ድረስ ደጋፊሽ ነኝ” ብዬ ግን ነግሬያታለሁ።
ከመቀበላቸው
ለመጨቆን የሚያደርጉት ጥረት እንደሆነ ተረዳች።
“ሁላችንም የተለያየ ልምድ አለን። እንዴት መኖር እንደምንፈልግ መግለጽ ግን መሰረታዊ የሆነ ሰዋዊ ፍላጎት ነው። አንቺ ሰላም ካልሆንሽ እኔም ልሆን አልችልም። ያን ያህል የተሳሰርን ነን። ጭቆና ሰዋዊነትን
6 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ አለስሜትህ ኑር በግድ ብሎ መያዝ አይቻልም።” ዓወት በአዲስ አበባ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ወጣት ነው። ራሱን እንደአጋር ሳይሆን የተመሳሳይ ጾታ ጠልነትን መረዳት እንደማይችል ሰው ይገልጻል። ሁሉም በሰው ያለመገለል፣ ያለጭቆና እና ጥላቻ የመኖር መብት አለው ሲል ያምናል። “ማንም ሰው አያገባውም ብዬ ነው የማስበው” ይላል። “ሁለት ራሳቸውን የቻሉ ሰዎች ቤታቸው ውስጥ የሚያደርጉት ነገር ሌላን ሰው እስካልጎዳ ድረስ እኔን ሊመለከተኝ አይገባም። ይመለከተኛል ካልኩ ግን ትልቅ ችግር አለብኝ ማለት ነው።” ሀይማኖትን ይጠቅሳል- በተለይም ስለሰዶም እና ገሞራ ያለውን ታሪክ ከባህላችን ጋር ተጨምሮ ኢትዮጵያውያን የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን እና ትራንስጀንደሮችን ጠል አድርጓቸዋል ይላል። ሀይማኖታዊ አስተምሮህቶችን መጠየቁ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማህበረሰብን እንዲቀበል ረድቶታል። የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አመለካከት ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ እሱ እንዴት እንደዚህ እንዳሰበ ስንጠይቀው “ቀላል ነው። ምክንያታዊ እና ሰውን የምረዳ መሆን በቂ ነበር።” ለማህሌት በኢትዮጵያ የሚገኙ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች መብት የሰብዓዊ መብት ጥያቄ ነው። ተመሳሳይ ሰዎች ጾታ አፍቃሪዎች እና የተለያየ ስርዓተ ጾታ ያላቸው ሰዎች እንደማንኛውም ሰው በሰውነት የመኖር ነጻነት ሊሰጣቸው ይገባል:: “ማንም ሰው በወሲባዊ ማንነቱ ምክንያት እንዲገለል አልፈልግም። ሰብዓዊ መብት ነው ይህ ደግሞ ለተወሰኑ ሰዎች ብቻ የሚሰጥ ነገር አይደለም።” ትላለች። ማህሌት ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሰው የተዋወቀችው አኳኋኑ የልብ ጓደኞቿን ትኩረት የሳበ አንድ ሰው አግኝታ እንደሆነ ታስታውሳለች። ስርዓተ ጾታዊ አገላለጹ “የሴት” የሚመስል ነበር፣ በዚህም ጓደኞቿ “ጌይ” ነው ብለው አሰቡ። በሁኔታቸው ደስተኛ እንዳልነበረች ታስታውሳለች። እሱ ሲኖር ሰዎች ምቾት እንደማይሰማቸው ማየቷ ጥሩ ስሜት አልፈጠረባትም። አብዛኞቹ ጓደኞቿ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ጠል በመሆናቸው ስሙ ሲነሳ የሚያጥላሉ አስተያየቶችን ይሰጣሉ። በነዚህ ውይይቶች ወቅት ሀይማኖት እና ባህል ለማህበረሰቡ ያላቸውን ጥላቻ ለመግለጽ እና ከኢትዮጵያውያን ጋር አይሄዱም ብለው ለማግለል እንደሰበብ ይጠቀሙት ነበር። ምንም እንኳን ልጁ ብዙ የወንድ ጓደኞቿ ራሳቸውን ከሚገልጹበት መንገድ የተለየ ስርዓተ ጾታዊ አገላለጽ ቢኖረውም ለማህሌት ምቾትን አልነሳትም። እንደውም ጥያቄዎች እንድትጠይቅ አደረጋት። “ለማወቅ ፈልጌ ነበር እናም ለነበሩኝ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት ነበረብኝ። ከተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ማህበረሰብ ጋር የተገናኘሁት በሱ በኩል ነበር። መጀመሪያ ላይ ብዙ ባንቀራርብም በኋላ ግን በደንብ መግባባት እና እኔም ለጥያቄዎቼ መልስ ማግኘት ጀመርኩ።” አዲስ ነገሮችን በንጹህ አእምሮ ለመረዳት የነበራት ፍላጎት የመነጨው ቤተሰቧ ይሰጣት ከነበረው ነጻነት ጋር የተያያዘ እንደሆነ ትናገራለች። ለምሳሌ የቅርብ ጓደኛዋ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ መሆኑን ሲነግራት በደስታ በመቀበሏ ጓደኛዋ ግራ ተጋብቶ ነበር። “ለመናገር ተጨንቆ ነበር እና ቀላል ይሆናል ብሎ አልጠበቀም ነበር። ሲነግረኝ ግን “እሺ በደንብ ንገረኝ” ነበር ያልኩት ዛሬም ንግግራችን እንዴት ቀላል እንደነበር ያስታውሳል። “ በእንደዚህ አይነት ንግግሮች ውስጥ እንዴት መደገፍ፣ መናገር እና ማበረታታት እንዳለባት ለማወቅ ፍላጎቷ ይታያል። የማህበረሰቡ አጋር ለመሆን የነበራት ፍላጎት ግን ዋጋ የሚያስከፍል ነው። ብዙ ጊዜ ከተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች እና ትራንስጀንደር ጠል በሆኑ ሰዎች መሀል ራሷን ብቸኛ ሆና ታገኘዋለች። ለማህበረሰቡ ባላት ድጋፍ ውስጥ ሰዎች ራሳቸውን የመግለጽ ፍላጎት
የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን
እንዳላቸው እናም የጾታ ማንነትን ጠልነት ሰዎች
ሰውነት
የጣሰ ነው።” ስትል ትናገራለች። የሀኒም የአጋርነት ጉዞ እንደማህሌት አዳዲስ ሀሳቦችን ለመቀበል እና ከባድ ውይይቶችን ለማድረግ ባላት ፍላጎት ላይ የተነሳ ነው። አባቷ ስለወሲብ በነጻነት ያዋራት ነበር። ሁለቱም ወላጆቿ ስለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች መጥፎ ነገር ሲሉ ሰምታ አታውቅም። ይሁንና ምንም እንኳን ነጻ አስተሳሰብ ቢኖራቸውም ይቀበሉኛል ብላ አታስብም። በ23 አመቷ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ስለሚያጋጥሟቸው ችግሮች በደንብ ለመረዳት ቻለች። “ለኔ አዲስ ነገር አልነበረም አልተቃወምኩትም። የተለየ ነገር ነው ብዬም አላሰብኩም እና ለመቀበል አልከበደኝም” ትላለች። ከጓደኞቿ ጋር ባላት ግንኙነት እና አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ በማየት ሃኒ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ያለው ጥላቻ ምክንያታዊ ሆኖ ያለማሰብ ችግር የተነሳ እንደሆነ ታምናለች። ሰዎች ሳይንሳዊ የሆነውን እውነታ ከመረዳት ይልቅ ሌሎች የሚሉትን ማመን
ራሳቸውን የቻሉ ሰዎች ቤታቸው ውስጥ የሚያደርጉት ነገር ሌላን
7 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ “ሁለት
ሰው እስካልጎዳ
ሊመለከተኝ አይገባም።
ግን ትልቅ ችግር አለብኝ ማለት ነው።” ዓወት
ድረስ እኔን
ይመለከተኛል ካልኩ
“ስለኔ ያላቸውን ሀሳብ ሳይቀየሩ ይህን ንግግር ማድረግ መቻል ደህንነቴ የሚጠበቅበት ቦታ እንዳለሁ እንዲሰማኝ ያደርጋል ምንም ነገር ለመቀየር የቻልኩ አይመስለኝም። ግን የሰዎችን ወሲባዊ ማንነት ስለመቀበል እናወራለን።
ጉዟቸው እና አጋርነታቸው የተለያየ ቢሆንም አቶ አለማየሁ፣ ዓወት፣ ማህሌት እና ሃኒ ጥላቻ በተሞላበት ሀገር ውስጥ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነትን
ይናገራሉ። ብዙዎች ለወላጆቻቸው ስለወሲባዊ ማንነት ከመናገር ሞትን እንመርጣለን በሚሉበት ሀገር የዚህን አባት ማግኘት ተስፋ የሚሰጥ ነው።
8 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ይመርጣሉ። ልክ ነኝ ብሎ አጉል መተማመንን ስለሚመርጡ እውነታው ሲነገራቸው መቀበል አይፈልጉም አጋርነቷን መግለጽ እና ለማህበረሰቡ መቆም አንዳንዴ ከባድ ሆኖ ታገኘዋለች። ከጥላቻቸው ብዛት ሰዎች ለመስማት ራሱ ዝግጁ አይደሉም። እንደዛም ሆኖ በሃሳቧ ከማይስማሙት
ጓደኞቿ ጋር የማህበረሰቡ አጋር ስለመሆኗ በይፋ ታወራለች።
ደግፈው ይናገራሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተመሳሳይ ጾታ ያለው አመለካከት እየተሻሻለ ነው ማለት ነው? ጊዜ የሚነግረን ነገር ነው። እንደአቶ አለማየሁ ያሉ አባቶች የሚመኙት ወደፊትም ነው። “ልጆች ብዙ ነገር ያደርጋሉ እና ሃጢያት ነው ማለት አይደለም፤ ጌይ ነኝ፣ ሌዝቢያን ነኝ፣ ኩዊር ነኝ ማለት ሀጢያት አይደለም። እና ለልጆቹ ክፍት የሆነ የንግግር መድረክ ማህበረሰቡ እንዲያዘጋጅ እና በመረጡበት መንገድ በሰላም እን”ዲጓዙ ማድረግ የሚቻልበት ሁኔታ መፍጠር ቢቻል ጥሩ ነው። እኔ ራሴ ለማዋራት ዝግጁ ነኝ። አንድ ልጅ አንድ ህይወት ማዳን ከቻልኩ ለእኔ ትልቅ ነገር ነው።” ሲሉ አቶ አለማየሁ
“ጭቆና
ሰዋዊነትን
የጣሰ ነው።” ማህሌት
9 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ - አይዳፖድካስቱ ላይ ምንም ተጨማሪ የምሰጠው ሃሳብ የለኝም ወድጀዋለሁ፤ እንደውም የሚያዝናኑ ሰዎች ነው ያቀረቡት። ስለ ደጋፊዎች ነው ያቀረቡት እና እንደዚህ አይነት ሃሳቦች እኛ ከምንሰማቸው የተሻለ ማህበረስቡ ቢሰማቸው ጥሩ ይመስለኛል። ምክንያቱም መልእክቱ ለእነሱ ነው እናም ያው ግንዛቤውን ለመፍጠር እና ደግሞ ትንሽ ተቀባይነትንም እንዲፈጥር ለማድረግ የተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ክሊፕ እየተደረጉ፣ ወይ አኒሜሽን ቪዲዮዎችን ወይ የሆነ ቪዲዮ ስቶሪ እየተሰራ ቲክቶክ ላይ ፖስት ቢደረግ ብዙ ሰው እንዲሰማው ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ። የማውቃቸውም ነገሮች ቢሆኑም እንኳን እነሱ ተሰብስበው ሲያወሩ የሆነ የሚያዝናና ነገር አለው እና እንዳልኩሽ ተደራሽነቱ ላይ ቢሰራ ጥሩ ነው ምክንያቱም ፔጃችን ብላ ስታወራ የሰማሁት ኢንስታግራም፣ ፌስቡክና ትዊተር ነው እና ቲክቶክ አካውንት ቢከፈትና ቪዲዮዎች ፖስት ቢደረጉ አንደኛ ብዙ ሰው ያየዋል ነገር፣ ሁለተኛ ደግሞ ራሱን ለመቀበል የሚታገለው ጋ ይደርሳል ብዬ አስባለሁ። እንደዚህ ተደራሽነቱ ላይ ደግሞ በጣም ቢሰራ ጥሩ ነው ምክንያቱም ፖድካስቱ አሪፍ ነው። ኢትዮ ኩዊር ፖድካስት ሶስት ኩዊር ደጋፊዎችን ለውይይት ጋብዛ አጋርነት ምን ማለት እንደሆነ እና ለLGBTQ+ ማህበረሰብ ያላቸውን መልዕክት እንዲያካፍሉ አወያይታ ነበር። ከኩዊር ማህበረሰብ ሰፊ የውይይት መድረክን የከፈተ ውይይት ነበር። ከታች ያስቀመጥናቸው የአድማጮቻችን አስተያየቶች የውይይቱን አስፈላጊነት በግልፅ የሚያሳዩ ናቸው።
አይቼ አላውቅም። ልጆቹ በጣም ነው ደስ የሚሉት ፤ ጥሩ ስሜት እንዲሰማኝ ነው ያደረጉት። ይቺ ሃገር ተስፋ እንዳላት እና እንደምንግባባ ተስፋ እንድናደርግ ነው ያደረጉት። ትንሽ ከሃይማኖት አንፃር የሰጡት ነገር
ያው ለሃይማኖተኞች አሳማኝ አይደለም። በርግጥ የግል አመለካከታቸው
ነው ግን መፅሃፍ ቅዱስን ወይም ደግሞ ቁርአንን ካነሳሽ ክርስቲያኑን
አለበለዚያ ሙስሊሙን ነው ልታስረጂ የምትሞክሪው ያ ደግሞ አሳማኝ
አልነበረም። በግል እንደሃይማኖተኛ የግል ሃሳባቸው ጥሩ ነው ግን እነዛ
ሰዎች የሚያምኑበትን መፃህፍትን ሲነኩ እነዛን ሰዎች የሚያሳምን ንግግር አልነበረም፤ ምክንያቱም እነሱንም ማሳመን በሚቻል ደረጃ መጽሃፉን
መግለጽ ይቻላል።
አሁን እኔ ስለቁርአን ባላውቅም መጽሃፍ ቅዱስን እነሱን በሚያሳምን ሃይማኖተኞች ነን የሚሉትን መጽሃፉን የሚያነቡትን
10 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ - ሰናይትየምር በጣም ደስ የሚል ነገር ነው የሰማሁት፣ እውነት ለመናገር እስከዛሬ ከሰማኋዋቸው ራሱ ለእኔ ይሄ ይበልጥብኛል፤ ማንነትሽን የሚያውቁ ሰዎች በዙሪያሽ ሊኖሩ ይችላሉ፣ እኔጋ እንኳን ባይኖሮ ብዙ ሰዎች ጋ ሊኖሩ ይችላሉ። ግን አምነውት ተቀብለውት ይህ የራስ ምርጫ ነው ትክክል ነው ብለው ሳይሆን የዛ ሰው ወዳጅ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት ሌላም ነገር ስለሆኑ ምናምን እያሉ አብረው ይሆናሉ እንጂ በዚህ ደረጃ አምነውበት በዚህ ደረጃ መብት እንደሆነ፣ በዚህ ደረጃ ምርጫ እንደሆነ አምነውበት ተቀብለው የሚደግፉ ሰዎች እውነት
ሰዎች በሚያሳምን ደረጃ ስለሰዎች ፍቅር መስበክ ይቻላል። እንደግል ግን በጣም ደስ ይላል በውነት አገላለፃቸው፣ ቃላታቸው ፣ የድምጻቸው ቅላጼ ላይ እውነትን እኔ ሰምቼበታለሁ እና መኖራቸውን እንወደዋለን። እስካሁን ከሰማኋቸው ይሄ በልጦብኛል።
11 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ - ኤደንእውነት ለመናገር በጣም ደስታ ነው የተሰማኝ በቃ ማለት ሆሞፎቢክ በበዛበት ሃገር እንደዚህ አይነት ፖዘቲቭ የሆኑ ሰዎቸ ኤልጂቢቲኪውን ደግፈው ፖሰቲቭ የሆኑ አይዲያዎችን ዲስከስ ሲያደርጉ በጣም ነው ደስታ የተሰማኝ። እነሱን የመሰሉ ሌሎች ኢትዮጲያውያን አሉ ብዬ እንዳምን አድርጎኛልና በጣም ነው ደስ ያለኝ፤ እጅግ በጣም ነው ደስ ያለኝ። በጣም ተስፋ ሰጪ ነው እና ለሌሎችም አርአያ መሆን የሚችል ውይይት ነበር። ያው ሌሎች ኢትጲያውያንም ይሄንን አግኝተው ደጋፊ እንደምናገኝ አልጠራጠርም። ያው የተለየ ብዬ ያልኩት አንድ ተሳታፊ አለ በዛ ግዜ ጓደኛው የነበረ ጌይ መሆኑን ሳያውቅ ከዛ ካወቀም በኋላ የወሰደው አክሽን የሚበረታታ ነው። ጓደኝነቱ በዛው መቀጠሉ እና ምንያህል ኤልጂቢቲኪው ማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ ሰዎች ጥሩና ደጋፊ መሆናቸው የሚያሳይ ነው። የልጁም ባህሪ ራስን አውቆ አክሴፕት አድርጎ መቀጠሉ የሚበረታታ ነው። ሌላ ሰው ጋር ያላየሁትና ለየት ያለ ብዬ የማስበው ይሄን ነው። ብዙ ግዜ ካወቁሽ ማንነትሽን ሲያውቁ የሚርቁሽና የሚፈርጁሽ በበዙበት ሃገር እሱ ግን በፖዘቲቭ ወስዶ ድጋፍ እያደረገ መቀጠሉ ለኔ ለየት ያለ ነገር ነበር ብዬ አስባለሁ። ውይይቱ እኔ ውስጥ ሲመላለሱ የነበሩ ነገሮችን አካትቷል እና ጥቅም አግኝቼበታለሁ በሃማኖትም ዙሪያ እና በብዙ ነገሮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። ለአድማጭ በተለይም ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲደርስ እንዲህ አይነት ውይይቶች ቢቀጥሉ ባይ ነኝ። እኔ የዚህ አይነት ውይይት የመጀመሪያዬ ነው እናም እንዲህ አይነት እውቀትም ብዙም የለኝም ነበር። እንዲህ አይነት ደጋፊዎችም አሉ ብዬ አላስብም ነበር። እና እኔም ደጋፊዎች አሉ ብዬ እንዳስብ ያደረገኝ ውይይት ስለነበር በይበልጥ ደግሞ ደጋፊዎችን እያመጣን ውይይቶችን በሰራን ቁጥር ህዝቡ ግንዛቤ የማግኘት እድሉ ሰፊ ይሆናል ብዬ አስባለሁ።
ሁኔታ ተቀባይነት
ንስንስ፡ ሁለታችሁም
ለቃለመጠይቁ ስለተስማማችሁ
እናመሰግናለን። ካንቺ እንጀምር
ልዋም። ለናሆም ስለወሲባዊ
ማንነትሽ ለመንገር የነበረው
መንገድ ምን ይመስል ነበር?
ልዋም፡ እንዴት እንደነበር
ለማስታወስ የተለዋወጥናቸውን
መልክቶች እያሰብኩ ነው።
ከሴት ጋር የፍቅር ግንኙነት
ከጀመርኩ ከአንድ አመት በኋላ
ነው የነገርኩት። ለአንድ አመት
ቤተሰቤ ውስጥ ላለ ለማንም
ሰው አልተናገርኩም። በይፋ
ያሳወኩት እኔ ስለራሴ ካወኩ ከአመት በኋላ ነው። ግን በዛ አንድ
ውስጥ ቤተሰቤ ምን ሊል
13 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ያለቅድመ
“ለአንድ አመት ቤተሰቤ ውስጥ ላለ ለማንም ሰው አልተናገርኩም”
አለኝ።”
“ልነግርህ እያሰብኩ ነበር፣ ሴት ፍቅረኛ
“ሁሉም
መስማት
የምፈልጋቸው
ነገሮች ነበሩ።”
እንዴትስ ልጋፈጠው የሚለው ሀሳብ በውስጤ ሲመላለስ ሁሌም እሱን አስበው ነበር። እና ስለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነት አውርተን ማወቃችንን አላስታውስም ግን እንደሚቀበለኝ ተሰምቶኝ ነበር። ባሰብኩት ቁጥር ውስጤ በፍርሀት ይሞላ ነበር ምክንያቱም ለኔ አስፈሪ ነገር ነው፤ ግን ስለሱ ሳስብ ቢያንስ አንድ ልነግረው የምችለው ቤተሰብ አለኝ ምንም አልሆንም” ብዬ እረጋጋለሁ። ሁሌም ያ ስሜት ነበረኝ። በይፋ የነገርኩት ግንኙነት ከጀመርኩ ከአንድ አመት በኋላ ቢሆንም ለቤተሰቤ ስለመንገር ማሰብ የጀመርኩት ከዛ በፊት ነበር። የነገርኩት ቀን አስቤበት የተፈጠረ አልነበረም። መኝታ ቤቴ ሆኜ ዋትስአፕ ላይ እየተጻጻፍን እንደሆነ አስታውሳለሁ። እና በፍቅር አብረን የምንሆናቸው ሰዎች ጋር ምን ሊያለያየን ይችላል የሚለውን እያወራን ነበር እና ሰውን ከነማንነቱ
አመት
ይችላል፣
የሚቀበሉ መሆን አለባቸው አለኝ። ቤተሰባችን ውስጥ ከዚህ ጋር የተያያዘ ብዙ ችግሮች አጋጥመውን ያውቃሉ እና ፍቅረኞቻችንም
ከተለያየ ሀይማኖት እና የመሳሰሉት የሚመጡ ሰዎች መቀበል እንዳለባቸው በማውራት ነበር የጀመርነው። እናም “ሰዎች በማንኛውም
ካመነበት ከሴት ጋር እንደሆንኩና ስለሷ እነግረዋለሁ አልኩ። እናም እዛው ጋር ጻፍኩለት። “ለብዙ ጊዜ ልነግርህ እያሰብኩ ነበር፣ ሴት ፍቅረኛ አለኝ።” “ልደውልልሽ” ሲል ጠየቀኝ። ከዛም ለአንድ ሰአት ከግማሽ ያህል አወራንበት። እንዴት እንዳወኩ እና
14 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
ሁኔታ
ይህን ሲለኝ ጊዜው አሁን እንደሆነ ተሰማኝ። በወቅቱ እነግረዋለሁ ብዬ አስቤው አልነበረም ግን ንግግራችን መቀጠል እና መንገር አለብኝ ብዬ ወሰንኩ። እናም የእውነት ይህን
ለመረዳት የሚረዱትን አይነት ጥያቄዎች ጠየቀኝ። ደስ የሚል ውይይት ነበር። በድንገት የተፈጠረ ስለነበር ደንግጬ ነበር። ቢሆንም ለመጀመሪያ ጊዜ ለቤተሰቤ አባል ይህን ነገር መንገሬ ጥሩ ስሜት የፈጠረብኝ እና ነጻነት እንዲሰማኝ ያደረገ ነበር። እሱም የነገረኝ ነገሮች ድጋፍ እንዳለኝ እና እንደሚኮራብኝ ነበር። ሁሉም መስማት የምፈልጋቸው ነገሮች ነበሩ። በጣም በጣም ደስ የሚል ራስን የመግለጽ ልምድ ነበር። ለቀሪው ቤተሰቤ በተለይም ለቤተሰቦቼ መናገሬ ቢያሳስበኝም ከውስጤ ከባድ ነገር የተነሳልኝ ያህል ቅልል አለኝ። አንድም ሰው ቢሆን ይህን ማወቁ ለአእምሮ ጤንነቴ በጣም ጥሩ ነገር ነበር። አንድ ነገር ቢፈጠር ወይም ከዚህ “በጣም በጣም ደስ የሚል ራስን የመግለጽ ልምድ ነበር። ...” ልዋም
ፍቅርን ካገኙ ሊቀበሉት ይገባል፤ ሀይማኖት፣ ጾታ እና ሌሎችም ሊገድቧቸው አይገባም” አለኝ።
ጋር በተያያዘ እርዳታ ብፈልግ መደበቅ እንደማይኖርብኝ ገባኝ። ቤተሰቤ ውስጥ የማምነው እና ሁሌም ለኔ በጎን የሚመኝና ሚስጥሬን
ላካፍለው የምችለው ሰው እንዳለ ማወቄ ብዙ ነገር አቀለልኝ። ከዛን ጊዜ ፍቅረኛዬ ጋር ጉዞ ስናደርግ የት እንዳለሁ እና ከማን ጋር እንዳለሁ እነግረው ነበር።
ንስንስ፡- ልዋም ስለወሲባዊ ማንነቷ ስትነግርህ ምን ይመስል ነበር፤ እንድትረዳት ያደረገህ ነገር ምንድነው?
ናሆም፡- እውነት ለመናገር የጠበኩት ነገር አልነበረም። የምትጠራጠሪው አይነት ነገርም አልነበረም። አንድ የተለመደ ቀን ላይ ስንጻጻፍ በድንገት ነው የነገረችኝ ስለዚህ ለኔ ድንገተኛ ነበር። ይሁንና ለኔ ትልቁ
15 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
ነገር ለሷ ደስተኛ መሆኔ እና በወቅቱ ከምትወደው ሰው ጋር መሆኗ ነበር። በአጠቃላይ ለማድረግ ከባድ የሆነ ነገር እንደሆነ ይገባኛል ምክንያቱም የኛ ማህበረሰብ በጣም ወግ አጥባቂ በመሆኑ መቀበል አይደለም ስለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነት ለማውራት ራሱ የማይቻልበት ሁኔታ አለ። እናም ለሷ ይህንን ጉዞ ማድረግ ከባድ እንደሆነ መረዳት ችያለሁ። ከልዋም ጋር ከነበረኝ ንግግር በፊትም ቢሆን የዚህ አይነት አስተሳሰብ ማህብረሰቡ በማይረዳው መልኩ ብዙዎችን እንደሚጎዳ አጥብቄ አምን ነበር። በዛ ላይ ደግሞ ሰዎች ለመረዳት ጥያቄዎች አይጠይቁም። ባደጉበት መንገድ፣ ባህል፣ እና ሀይማኖት “ጉዞውን ብቻዋን እንድታደርገው አልፈለኩም። አሁን ብቻዋን መሆን የለባትም የቤተሰቧ አባል፣ ወንድሟ ከጎኗ አለ።” ናሆም
ነበር።
ንስንስ፡- እህትህን እንድትቀበል ያስቻለህ ምንድነው; ለዚህ አመለካከትህ አስተዋጽኦ ያደረገ ነገር አለ?
ናሆም፡-ዋናው ነገር ማንነቴ ይመስለኛል። ማህበረሰቡ የሚያምንበትን ሁሉ በጭፍን የምከተል ሰው አይደለሁም። አንዳንድ ነገሮችን እንደ እሴት ብቻ አልወስዳቸውም፣ ለምን እንደዚህ ሆነ ብዬ እጠይቃለሁ፤ በመጨረሻም ማህበረሰቡ የማይቀበለው ቢሆንም በራሴ የማምንበት መደምደሚያ ላይ እደርሳለሁ።
እና ቅድም ልዋም ያለችውን ነገር ላይ ያጋጠመኝ ነገር ነበር። የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆነች ሴት ጋር የፍቅር ግንኙነት ነበረኝ። ይህ በማህበረሰቡ ዘንድ ብዙም ተቀባይነት የሌለው
16 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
ያደጉበት ጊዜ እና እድሜያቸው
ልዋም
አመለካከቴን ከዛ በፊት ለልዋም ነግሬያት እንደነበር አላስታውስም። እውነት ለመናገር ያንን ያልኳት እሷ ለመናገር ምቾት ይሰጣታል ብዬ አልነበረም። ሁሌም የማምንበት ነገር ነው። እናም ልዋም ስለወሲባዊ ማንነቷ ስትነግረኝ ለራሴ እምነቴ ላይ ይበልጥ ጽናት እንዲኖረኝ አደረገ። አጋጣሚ ሆኖ እህቴ ሆና ተገኘች። ዝም ብሎ ለማውራት ሳይሆን በራሴም ህይወት እህቴ ጋር ያለ ነገር ስለሆነ የሚያስፈልጋትን ፍጋፍ ሁሉ መስጠት ነበረብኝ። በንግግራችን ሁሉ የምላት የነበረውም ያንን ነበር። ለምን ያህል ጊዜ እንዳወቀች እና ስለፍቅር ግንኙነቷ በምጠይቅ ጊዜ ሁሉ ማንነቷ ምንም ችግር እንደሌለው ለማሳወቅ ጥሬያለሁ። በማህበረቡም ሆነ በቤተሰባችን ሊያጋጥሟት ስለሚችሉት ችግሮች እንድትረዳ ፈልጌ ነበር። እናም ለቤተሰባችን ማሳወቅ ቀላል ሊሆን እንደማይችልም ነገርኳት። እነዚህን ሁኔታዎች ስለተረዳሁ እሷም እንድታውቅ እና ስለማንኛውም ነገር እኔን ማዋራት እንደምትችል እንድታውቅ አደረኩ። ያጋጠሟትን ችግሮች በተጋፈጠችበት መንገድ እጅግ እንደኮራሁባት እንድታውቅ እና በተለይም በኛ ቤተሰብ ሁኔታ ለመናገር መድፈሯ ለሷ ምን ያህል ከባድ ሊሆን እንደሚችል እንደምረዳ ነገርኳት። በተወሰነ መልኩም ቀሎኝ ነበር ምክንያቱም የራሷን እውነት መኖር እየጀመረች እንደሆነ ተረድቻለሁ፣ ይህም በጣም ከባድ ነው። ሁሌም ቢሆን ትክክለኛ ማንነታችንን እና ማህበረሰቡ ከኛ የሚጠይቀውን አስማምቶ መኖር ከባድ ነው። ለኔ ያ ጉዞዋ ከባድ እንደነበር ግልጽ ነበር። ደስተኛ የምትሆንበትን ጉዞ ብቻዋን እንድታደርገው አልፈለኩም። አሁን ብቻዋን መሆን የለባትም የቤተሰቧ አባል፣ ወንድሟ ከጎኗ አለ። እናም መጀመሪያ የተሰማኝ እንደዛ
“
እንደዚህ የሚያስቡት
መጥፎ ሰዎች ስለሆኑ ሳይሆን
ያሳደረባቸው ተጽእኖ ነው ይለኛል።”
ስር ተከልለው ከዛ ውጪ ያለውን ነገር መጠየቅ አይፈልጉም።
ነገር እንደሆነ በትንሹም ቢሆን ተረድቻለሁ። ቢሆንም ግን ዋናው ነገር ስለወደድሽው ሰው ብቻ መሆን አለበት ብዬ አስባለሁ። እሴቶቻቸውን እና ማንነታቸውን የሚቀረጸው በአስተዳደጋቸው ቢሆንም የራሳቸውን የሆነ ማንነት መገንባት አለባቸው ብዬ አስባለሁ። እዚህም እንደዛው ነው። ተመሳሳይም ሆነ ተቃራኒ ጾታ ከሌላ
የሚረዱ ይመስለኛል። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነትም እንደዛው ነው።
በነዚህ ንግግሮች ምክንያት ከሰዎች ጋር ያለን ግንኙነት ሊበላሽ
ሁሉ ነገሮች ስለሚያምንበት ነገር ኖሮ ያሳየባቸው ሁኔታዎች ነበሩ። ከእህትና ወንድም እና በዙሪያችን ካለ ሰዎች ብዙ እንማራለን፤ በሚነግሩን ብቻ ሳይሆን በሚያሳዩንም
17 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ሰው ጋር ላለሽ ግንኙነት ቦታ መስጠት አለብሽ። እናም እኔም በራሴ መንገድ ያለፍኩበት ነገር ነው፤ ልዩነቱ ይሄ የሀይማኖት ጉዳይ መሆኑ ነው። ማህበረሰቡ ብዙውን ጊዜ ምቾት የሚነሳውን ነገር መሞከር አይፈልግም ስለዚህ አንዳንዴ የማያምኑባቸው አመለካከቶችን ሊቀበሉ እንደሚገባ ለማሳየት እነዚህን ችግሮች መጋፈጥ እና መስዋእትነት መክፈል ያስፈልጋል። ስለሀይማኖት ሲነሳ ከባድ ንግግሮች እናደርጋለን እና ቤተሰቤ ከበፊቱ በተሻለ አሁን
በትንሽ ለመቀየር በመሞከር ከኛ በኋላ ላለው ሰው የተሻለ ሁኔታን ማመቻቸት እንችላለን። ማህበረሰቡ የሚሻሻለው በዚህ መንገድ ይመስለኛል በአንድ ጊዜ ትልቅ ለውጥ ማምጣት ከባድ ነው፣ ህመም ሊኖረው እንደሚችልም መረዳት ያስፈልጋል ግን ድጋፍ የሰጠሁበትን አንዱ ምክንያትም ያ ይመስለኛል። ጥያቄዎች እጠይቃለሁ ምንም ነገር በጭፍን አልቀበልም። ልዋም፡- እሱ ያለው ላይ ትንሽ መጨመር ፈልጋለሁ። ስናድግ ከሱ የምማረው ነገር ይህን ነበር። ናሆም የመሰለውን ነው የሚያደርገው። በአፍሪካ ወይም በኢትዮጵያ ቤተሰብ ውስጥ ብዙ ጊዜ ልጆች ተሰሚ አይደሉም። አመለካከት ሊኖርሽ ይችላል ግን መጨረሻው ወላጅ የሚለው ነው “እኔ ስላልኩ ታደርጊዋለሽ” ትባያለሽ እና ናሆም ከልጅነቱ ለምን ብሎ ይጠይቃል “እኔ ስላልኩ” የሚለው ነገር ደግሞ አያሳምነውም። ደረቅ ነበር ከልጅነቱ የራሱን መንገድ ይከተል ነበር። ያንን እያየሁ እና እያደነኩለት ነው ያደኩት። ሁሌም ነገሮች በራሱ መንገድ ማድረግን ይመርጣል። ቅድም በወሬ መሀል ስለወሲባዊ ማንነት መቀበል ነግሮኝ እንደሆነ አላስታውስም ብዬ ነበር። ለምን ምቾት ይሰማኝ እንደነበር እርግጠኛ አልነበርኩም ግን ሁሌም በልቤ እንደሚቀበለኝ ይታወቀኛል እና እንደዛ የተሰማኝ ይሄን አስተሳሰቡን ስለማውቅ ይመስለኛል። ሁሌም የራሱ አመለካከት ሲኖረው እና መስሎ መኖርን ሲጠላ አየዋለሁ። ከሌላ ሀይማኖት ተከታይ ጋር ስለነበረው ግንኙነት እና የቤተሰቦቻችንንም አቀባበልም እንዴት እንዳስተናገደ ተመልክቻለሁ። እነዚህ
ነገርም ጭምር። እና እሱ ቤተሰባችን ምንም ቢያስብም በሚያምንበት መልኩ ህይወቱን የሚኖርበትን መንገድ እያየሁ ነበር። ለሱ ከማሳወቄ በፊት እንድንተማመንበት ያደረገኝም ያ ነው። ንስንስ፡ ካሳወቅሽው በኋላ ስለወሲባዊ ማንነትሽ በተደጋጋሚ አውርታችኋል? አዎ የአንድ ጊዜ ብቻ ወሬ አልነበረም። ለአመታት በቤተሰቤ “... ለኔ
ነገር
ደስተኛ መሆኔ እና በወቅቱ ከምትወደው ሰው ጋር መሆኗ ነበር። ...” ናሆም
ቢችልም አመለካከታቸውን ትንሽ
ትልቁ
ለሷ
አይችሉም
ምክንያቱም ወላጆቼን ያውቃቸዋል። ከቤተሰቤ ውጭ ያሉ
ሰዎች የማያውቁትን ብዙ ነገር እሱያውቃል እናም ምንም ያህል ከሌሎች የቤተሰባችን አባላት ጋር የሚፈጠረው
በራስ መተማመንን ይሰጥሻል።
ንስንስ፡- ናሆም እንደአጋር የጥላቻ እና የተመሳሳይ ጾታ
አፍቃሪዎች ጠል ስለሆኑ ንግግሮች ምን ትላለህ?
ናሆም፡- አስፈላጊው ነገር ላይ ማተኮር ያለብን
ከምትወጃቸው ጎን መሆን። አለም በጣም የሚያስጠላ
ቦታ እንደሆነ መረዳት አለብን። ሰዎች የተለመደ ከሚባለው
ረዥም ጉዞ
ነው። ማለት ኢትዮጵያን እርሱት እና አሜሪካን ተመልከቱ
በጣም ተራማጅ እና
20 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ እንዳልሆነ አውቄያለሁ። ምንም ቢመጣ መጋፈጥ እንዳለብኝ እና እየሆኑ ያሉትን ነገሮች በራሴ መንገድ መረዳት እንዳለብኝ ገብቶኝ ነበር። ሳልነግረውም ያመንኩት ነገር ነበር። ራስን የመቀበል
እንዳደግሽ እና በባየሎጂካልም ሆነ በአካባቢ ብዙ የተጋራሽው ሰው ትክክለኛ አንቺነትሽን ማወቁ የሚሰጥሽ በራስ መተማመን አለ። ከጓደኞችሽ ጋር ቢሆንም ለቤተሰብ ስለመንገር ስትነግሪያቸው የፈለገውን ያህል ሊረዱሽ ቢሞክሩም ከወንድሜ የበለጠ ሊረዱኝ
ጉዞው በጣም አስፈላጊ ነው ያንን ደግሞ አድርጌው ነበር። ማን እንደሆንሽ እንዴት
ነገር መጥፎ ቢሆንም እሱ እንዳለልኝ እና እንደሚደግፈኝ ማወቄ በራሴ እንድተማመን አድርጎኛል። እውነት ለመናገር ናሆም የሚቀበለኝ ግን ወላጆቻችን ፊት የማይከራከርልኝ ወይም ከጎኔ የማይቆም አይነት ሰው ቢሆን ሁኔታዎች የተለዩ ይሆኑ የነበረ ይመስለኛል። ምክንያቱም ብዙ ሰዎች በቤተሰብ ውስጥ ይቀበሉሻል ግን እነሱም በተወሰነ መልኩ ስለሚፈሩ ላንቺ አይከራከሩልሽም። ከሱ ጋር ግን ቢመጣበት እንኳን አብሮኝ እንደሚጋፈጠው አውቃለሁ። እንደሚጠብቀኝ አውቃለሁ። እና ለቤተሰብ መንገር ብቻ ሳይሆን የምትነግሪው ሰው ሸክምሽን እንደወንድም እንደሚጋራሽ ማወቅ ትልቅ ነገር ነው። ይህም እንደተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ያለሽን ልምድ እና ራስሽን ወደፊት እንዴት ትገልጫለሽ የሚለው ላይ አስተዋጽኦ አለው። ነገሮች መልካም ባይሆኑ እንኳን በጽናት እንድትታገይ
ይመስለኛል።
ደግሞ
አንደኛው ሁሌም ለእውነት መቆም ነው ሌላው
ነገር
ከማንም
ግን ደግሞ ከዛ መደበቅም አደጋ ያለው ይመስለኛል። ማህብረሰብን መቀየር
ወጣ ሲሉ ብዙ ጥቃት ይደርስባቸዋል ይህን ደግሞ
በላይ ታውቁታላችሁ።
ዴሞክራሲያዊ ተብሎ በሚታሰበው ሀገር ራሱ የዚህ አይነት ክርክሮች አሁንም ድረስ ስለ ጋብቻ እኩልነት፤ የእኩልነት መብት እና ሌሎችም ይደረጋሉ። እናም ይህ ረዥም ጉዞ ነው መደበቅ ግን አያስፈልግም። ባይኖሩ ብሎ መመኘት ወይም የተሻሉ በሆኑ ኖሮ ብሎ ማለት ብቻ በቂ አይደለም። ለውጥ እንደዚህ በቀላሉ አይፈጠርም፤ በዝግታ፤ ከጊዜ ብዛት የሚፈጠር ከባድ መንገድ ነው። ስለዚህ ጥያቄው የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች እና አጋሮቻቸው የወደፊቱ “በራሳችሁ መንገድ በውስጣችሁ ራሳችሁን መቀበል ትችላላችሁ።” ልዋም
ላይ በማተኮር ለመጪው ትውልድ የተሻለ ነገር ለመፍጠር ዛሬ
ላይ ህመም የበዛበትን ጉዞ ለማድረግ ምን ያህል ዝግጁ ናቸው
የሚለው ነው። ስለዚህ ለኔ ይህ ራእይ ካለን ከባዱን ወቅት
የምንቋቋምበት ጥንካሬ ይሰጠናል እላለሁ። አንድ መጥፎ ነገር
የሚናገር ሰው ቢኖር ማተኮር ያለብን እሱ ላይ አይደለም ንግግሩ
በመደረጉ ሌሎች ደግሞ በአዎንታዊ መንገድ እንደተቀየሩ ላይ
መሆን አለበት።
እንደንስንስ እና ኩዊር ኢትዮጵያ የምትሰሩት ስራ ላይም
ሁሉም ሰው አጋር እና የሚደግፈው ቤተሰብ የለውም። ስለዚህ አንዳንዴ እንደዚህን ታሪኮች አንብበው “እኔ እኮ እንደአጋር
የሚደግፈኝ ሰው የለም” ብለው ሊያስቡ ይችላሉ። ብዙ ሰዎች
ስትነግረኝ ስልኩን እንደዘጋን ያልኳት ነገር ለኔ ለመንገር አንድ አመት ሙሉ በመጠበቋ እንደተሰማኝ ነበር። ምክንያቱም ለአንድ አመት ብቻዋን ይህን ነገር መጋፈጥ ነበረባት። እናም ከዚህ በኋላ አእምሮሽ
ያለውን ነገር ለመንገር ረዥም ጊዜ እንደማትወስጂ
አይነት ሁኔታ ውስጥ ማለፋቸውን ሲያነቡ ትንሽም ቢሆን
ለውጥ እንዳለ ተስፋ ይሰጣቸዋል ብዬ አስባለሁ። ይህን
ድጋፍ የሚያገኙት በኢንተርኔት ሊሆን ይችላል በራሳቸው መንገድ ታሪካቸውን ሊናገሩ ይችላሉ። እናም ከዛ አንጻር እየሰራችሁ ያላችሁት ስራ በጣም ትልቅ ነው እናም ሰዎች በዚህ መንገድ በሚያልፉ ሰአት ህመም ሊኖረው እንደሚችል ማወቅ ያስፈልጋል።
ንስንስ፡ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች እህትና ወንድሞች
ወይም ሌላ የቤተሰብ አባላት ሆነው አጋርነታቸውን ላልገለጹ ምን ትላለህ? ናሆም፡-የመጀመሪያው
ማህበረሰቡ ቋሚ ሀውልት እንዳልሆነ ለማስረዳት መነጋገር ያስፈልጋል። ስለዚህ ጥያቄ መጠየቅ እና ይበልጥ ለመረዳት መሞከር አስፈላጊ ነው።
እንዳልኩት አንዳንድ ሰዎች እነዚህን እሴቶች የሚይዙት
መጥፊ ሰዎች ስለሆኑ ሳይሆን ጥያቄዎችን ባለመጠየቃቸው ነው።
21 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
በዛ
ስለራሳቸው
ከሌሎች ጋር ስለመጋራት በሚያስቡበት ወቅት። በነገራችን ላይ ልዋም መጀመሪያ
ውስጥ
ተስ አደርጋለሁ አልኳት። እናም ለኔ ቤተሰባቸው ወይም ከጓደኞቻቸው ውስጥ እንደዚህ አይነት ሰው የሌላቸው ሰዎች በኢንተርኔትም ሆነ በሌላ አለም ክፍል ያሉ ሰዎች በእንደዚህ
ሁኔታ ውስ ጥ አሉ እናም በጣም ከባድ ነው በተለይም
የሚያውቁትን እውነት
ነገር ለምን ብሎ መጠየቅ ነው። ድፍን ያለ ድምዳሜ ላይ መድረስ ከባድ ነው። ለምንድነው ድጋፍ መስጠት ያልፈለጉት› ለኔ እንዳልኩት አስተዳደግ እና ባህል እና ሀይማኖት የሚፈጥረው ተጽእኖ ይመስለኛል። ስለዚህ እነዚህ ነገሮች የሚቀየሩ እንደሆኑ እና
ቢኖራቸው
ሊቀይሩ ይችላሉ። ምክንያቱም ሆን ብለው ሰውን ለመጉዳት እየሞከሩ አይደለም። ስለራሳቸው ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ሲሉ ብቻ መጥፎ ነገር የሚናገሩ ሰዎችም ግን አሉ። እነሱ የተሻለ የሚያደርጉት ነገር ስለሌለ ነው ስለዚህ
ምናልባት የኔ የሚሉት ሰው ቢሆን ወይም የተለየ አመለካከት
ሀሳባቸውን
ንግግር ስናደርግ ከማን ጋር እንደሆነ ማወቅ እና የምንጠቀመውን
ቋንቋ መለየት አስፈላጊ ነው። “ከምንም በላይ አስፈላጊው ነገር ምንድነው?” ብዬ
እጠይቃለሁ። አክራሪ ሀይማኖተኛ ለሆነ እና ስለዚህ ጉዳይ
ሀሳበቸውን መቀየር ለማይፈልግ ሰው ሲባል እውነትሽን
ትክጂያለሽ? ከዛስ ምን፣ የቤተሰብሽን አባል ብታጪስ፣ እሺ
ላንቺ በጣም አስፈላጊ የሆነው ነገር ምንድነው፣ ይህን ጥያቄ በተናጠል ወይም ለሁሉም ሰው መመለስ አልችልም ግን እነዛ ሰዎች ይህን ጥያቄ ራሳቸውን መጠየቅ ያለባቸው ይመስለኛል።
ስለሚያምኑበት ነገር ከዛም መቀየር መፈለጋቸውን፣ ከዛስ ቀጥሎ የሚከሰተውን የቤተሰባቸውን አባል ለማጣት ዝግጁ መሆናቸውን
መጠየቅ አለባቸው። ያንን ውሳኔ ከወሰኑ እውነት ለመናገር
ቀረባቸው ምንም
ሰዎችን ምንም ልታደርጊያቸው አትችይም።
ልዋም እንደአንቺ የሚደግፋቸው
ያስፈራኛል። በርግጥ ይህ አረፍተነገር ውስጥ ብዙ የተሰጠኝ ልዩ ነገር ስላለ እንደሆነ እረዳለሁ። ድንገተኛ የሆነ
አልተጋፈጥኩም። ከቤተሰቤ የኢኮኖሚ ድጋፍ ነጻ ነበርኩ፣ ከሞላ ጎደል ጤናማ ሰውም ነኝ። ስለዚህ የራሴን እውነት ለመኖር የሚያስችለኝ
ፈልጋለሁ። እና ተስፋ የማደርገው እነዚህ ሰዎች የዚህ አይነት ማህበረሰብ ውስጥ እንዲሆኑ
ካልተሳሰርነው ሰው ጋርም የዝምድና ያህል ቁርኝት ሊኖር እንደሚችል እርግጠኛ ነኝ። በስጋ ቤተሰቦቻችሁ
ያስከተለውን ህመም ወዲያው የሚያጠፋ ነገር
22 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
መቀጠል
የእውነት
አውለብልቢ፤ ፍልሚያውን ተፋለሚለ ከዛም መንገድሽን ቀጥይ። ሀሳባቸውን መቀየር የማይፈልጉ
ወይም ቤተሰብ ለሌላቸው የተመሳሳይ
ትያለሽ? ልዋም፡- ከባድ ነው። እውነታችሁን ለመኖር የሚያስፈልጋችሁን ጥንካሬ በውስጣችሁ ፈልጉት ነው የምለው። ለኔ እውነትን ተናግሮ ተቀባይነት ከማጣት ይልቅ ውሸትን
ልዩ ጥቅም ነበረኝ። እና ራሱን አሳውቆ ሁሉም ሰው የራሱ ጉዳይ የማይልን ሰው ለማጣጣል አይደለም። ግን በራሳችሁ መንገድ በውስጣችሁ ራሳችሁን መቀበል ትችላላችሁ፤ የስጋ ቤተሰቦቻችሁ ባይቀበሏችሁ እንኳን በምርጫ ቤተሰብ የምታደርጓቸው ሰዎች በህይወታችሁ ትልቅ ትርጉም ሊኖራቸው እንደሚችል አምናለሁ። እናም ከስጋ ቤተሰባችሁ ድጋፍ ባታገኙም ለትክክለኛ ማንነታችሁ የሚወዷችሁ ብዙ ሰዎች በዚህ አለም አሉ ማለት
ነው። ቤተሰብ ለኛ ምን ማለት እንደሆነ በየግላችን የምንገልጸው ነገር ነው። በደም
ማለቴ ግን አይደለም። በዛ ውስጥ ማለፍ ከባድ ሊሆን እንደሚችል ይገባኛል፤ ሁሌም ህመሙ የማይጠፋም ይሆናል ግን ከጊዜ ብዛት ለራሳችን እውነት መሆን ስንጀምር ያንን ህመም እንዴት መቻል እንዳለብን እናውቃለን። እናም ለኛ በጣም አስፈላጊ የሆነውን ነገር እወቁት እላለሁ “ምንድነው ይበልጥ የሚያስፈራችሁ” ጉዞው ከባድ ቢሆንም ትክክለኞቹን ሰዎች “ለኔ
ተናግሮ ተቀባይነት ከማጣት
ውሸትን
ያስፈራኛል።” ልዋም
ልታደርጊያቸው አትችይም። መንገድሽን
አለብሽ።
ባንዲራሽን
ንስንስ፡-
እህትና ወንድም
ጾታ አፍቃሪዎች ምን
መኖር
አደጋ
አለመቀበል
ነው
እውነትን
ይልቅ
መኖር
ካገኛችሁ የተሻለ ይሆናል።
ንስንስ፡ ለልዋም የራሷን እውነት ስለመኖር እና ወሲባዊ
ማንነቷ የምትላት ነገር አለ?
ናሆም፡- ተቀባይነትን ማግኘት እና የተመሳሳይ ጾታ
አፍቃሪነት ምን እንደሆነ ለሰዎች ማስረዳት ከባድ ነገር
ነው። ግን የእናንተ ስራ እና ልዋም በሌሎች መንገዶች
ቤተሰብ የምንለውን ፈልገን ማግኘት ያለችው ጠቃሚ ነው።
ሁሌም ስለህይወት ስናስብ በቅርብ ያለውን እና እንዴት
እንደምንገልጸው መረዳት አለብን። በምንፈልገው መንገድ
የሚቀበለንን ሰው ማግኘት ቀላል አይደለም። ዋናው ነገር
ፍቃደኛ የሆኑትን ሰዎች እንዴት ከሚፈልጓቸው ጋር ማገናኘት
ይቻላል የሚለው ነው።
ቀን በቀን ላላገኙት እንዴት
ጉዞው ረዥም ነው፤
ራስን ስለማግኘት እና ራስን ስለመረዳት ነው፤
ስህተት እንዳልሆነ እና ልትቀበይው እንደሚገባ ማወቅ ያስፈልጋል። ግን ደግሞ ከሌሎች ሰዎች ብሎም ከማህበረሰቡ ይህን ድጋፍ የማግኘት ጉዞው ከባድ እና ረዥም
23 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
ቀላል ልናደርግላቸው እንችላለን። ለኔ ረዥም ጉዞ ነው ግን ሰዎች ድጋፍ የሚያገኙበትን እና በተመሳሳይ መንገድ እያለፉ ካሉ ሌሎች ሰዎች ጋር የሚገናኙንበትን መንገድ መፍጠር ታሪካቸውን እንዲያጋሩ ማድረግ፣ እና የሚኖር ህይወት እንዳለ እንዲያውቁ ማድረግ አስፈላጊ ነው። መንገዱ ከባድ ስለሆነ እዛ አይደረስም ማለት አይደለም። እና ሰዎች ተስፋ እንዳይቆርጡ እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ እንዲያገኙ ምኞቴ ነው። ራሳቸውን እንዳይጠራጠሩ እና ችግር አለብኝ ብለው እንዳያስቡ ተስፋ አደርጋለሁ። ራሳቸውን አውቀው እና ተቀብለው ራስን ካለመቀበል እና ጥርጣሬ ጋር የሚመጣውን ችግር ባይጋፈጡ እላለሁ። ከምረዳው እናንተ የምትሰሩት ስራ ሰዎች ታሪካቸውን በማጋራት ወደአንድ የሚመጡበትን መንገድ የከፈተ ነው። እናም ሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ከሚያገኙበት አንዱ መንገድ እንደሆነ እምነቴ ነው። ንስንስ: አሁን ያልካቸው ነገሮች ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች በአጠቃላይ የሚሆኑ ናቸው። ልዋም እንዳላቸው ግን እሷም ካሳለፈቻቸው ከባድ ጊዜያት እና አንተም ከሰጠሀት ድጋፍ አንጻር ለእህትህ ምን የምትላት ነገር
ናሆም:-
እንዳልኩት
በዋናነት
ማንነትሽ
ስለዚህ ነገሮችን በሰፊው መመልከት እና ያለሽበት ጎዳና ቀላል እንዳልሆነ ማወቅ አለብሽ። በተመሳሳይ ሰአት ድጋፍ ማግኘት የምትችይበትን መንገድ ፈልጊ፤ እውነትሽን ኑሪ ከባዱን ፍልሚያ ተፋለሚ። ንስንስ፡ ሁለታችሁንም አመሰግናለሁ
አለ?
የተለየ የምላት ነገር ያለ አይመስለኝም።
ተቀባይነትን የማግኘት
ነው።
“ድጋፍ ማግኘት
ከባዱን
የምትችይበትን መንገድ ፈልጊ፤ እውነትሽን ኑሪ
ፍልሚያ ተፋለሚ።” ናሆም
24 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
እኔ ግን ለመቀበል ዝግጁ አልነበርኩም።
ተከትሎ
ጣጣ ፈራሁ። ህይወት ምን ያህል የተለየ ሊሆን ይችላል?
ፍርሃትን ማሰስ
ሰዎች ካወቁ
የሚመጣውን
25 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ራሴን መቀበል የጀመርኩት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ አይደለሁም ብዬ መከራከሬን ትቼ “ብሆንስ?” በማለት
ነው።
ያደኩት ምን እንደሆንኩ ሳላውቅ ነው።
ለመግለጽ የሚያስፈልገውን ቃላት ካለማወቄ ባሻገር ወሲባዊ ስሜቴን መረዳትም አልችልም
ነበር። ስለዚህ አብዛኛው ሰው የሚያደርገውን አደረግኩ። የወሲባዊ ማንነቴ እኔነቴ ውስጥ
የማይካተት እንደሆነ በማሰብ የተለመደውን የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪነትን ተቀብዬ ትክክለኛ ማንነቴን ገደብኩት። በርግጥ በልጅነቴ “ወንዳወንድ” የምባል ስለነበርኩ ለመደበቅ ቀላል አልነበረም። ስለወሲባዊነት ምንም እውቀት ባይኖረኝም አብሬያቸው ከምማረው ሴቶች የተለየሁ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር። ሴት መሆን አለባት ተብሎ የሚታሰበውን መስፈርት የማሟላ መስሎ አይሰማኝም። ያንን ልዩነት ለማሳየት ስልም “የወንድ” ልብሶችን መልበስ እና “እንደ ወንድ” መሆንን አዘወተርኩ። ይህም ማለት ለሁለቱም ጾታ ፍላጎት የኖረኝ በወሲባዊ ማንነቴ ይሁን ወይም እየመሰልኩ የኖርኩት የስርአተ ጾታ ልምዶች ያደረጉብኝ ተጽእኖ ይሁን መለየት አልቻልኩም። ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጋር የተገናኘሁት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን ላጠናቅቅ አካባቢ ነው፣ በጣም ደንግጬ ነበር። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች በተለይም ኢትዮጵያውያን የሆኑ የሉም ተብለው በሚታመንበት ማህበረሰብ ውስጥ እንደማደጌ መኖራቸውን ሳውቅ ይህን እውነት ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላወኩም። እንደተመልካች ከውጪ ሆኖ ሁኔታውን ማየት አሳዛኝም ተስፋ ሰጪም ነበር። ቀስ በቀስ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች እንቅስቃሴ ሰፊ የሆነ የእኩልነት ፍትህ እና ነጻነት ጥያቄ እንደሆነ መረዳት ጀመርኩ። የማህበረሰቡ አካላት ራሳቸውን ሆነው ለመኖር ምን ያህል እንደሚከብዳቸው እና በብዙ እንደሚጎዱ እንዲሁም በህግ እና በሰዎች አመለካከት የተነሳ መኖራቸው እንደወንጀል እንደሚታይ ተመለከትኩ። ስለተረዳሁት ነገር ከጓደኞቼ ጋር ማውራት እና የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ላይ የሚነገሩ የተሳሳቱ አመለካከቶችን እና ቀልዶች ሲያጋጥሙኝ መከራከርን ስራዬ አደረኩ። ይሁንና ያኔም ቢሆን ነገሩ ፋሺዝምን ወይም የበላይነትን ከመቃወም በተለየ በግል የወሰድኩት ነገር አልነበረም። ለረዥም ጊዜ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች የማደርገው ፍልሚያ ፍትህና እኩልነት ለሁሉም ከሚል ጠቅለል ያለ ሀሳብ የተለየ ነገር እንዳለው አልተረዳሁም፡ ራሴን እንደተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ማሰቤ ስለተመሳሳይ ጸታ አፍቃሪዎች በነጻነት እንድናገር እና መንግስትም ሆነ ሌሎች ጥቃት ሊያደርሱብኝ ይችላሉ ከሚል ፍርሀት ገድቦኝ ነበር። ምክንያቱም የነበሩኝ ጾታዊ ግንኙነቶች ሁሉ ከተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ወንዶች ጋር ነበሩ። ለኔ ቅርብ የነበሩ ግን እኔ ከማመኔ በፊት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነቴን አውቀው ነበር። ስለማህበረሰቡ ባለኝ አመለካከት እና የሚስቡኝን ሰዎች በምገልጽበት መንገድ ማንነቴን ተረድተዋል። የራሴ ወሲባዊ ማንነቴን መረዳት ጊዜ ቢወስድብኝም ከተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ እህት ወንድሞቼ ጋር የነበረኝ መግባባት ቀጥ ያለ መስመር ያልሆነውን እና ውጣ ውረድ የበዛበትን የራስን ፍለጋ መንገዴን እንድጀምር ረድቶኛል። ራሴን መቀበል የጀመርኩት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ አይደለሁም ብዬ መከራከሬን ትቼ “ብሆንስ?” በማለት ነው። ብዙዎች ለነገር የምለው መስሏቸው ዝም አሉኝ። እኔ ግን ለመቀበል ዝግጁ አልነበርኩም። ሰዎች ካወቁ ተከትሎ የሚመጣውን ጣጣ ፈራሁ። ህይወት ምን ያህል የተለየ ሊሆን ይችላል? የስራ አጋሮቼ፣ አስተማሪዎቼ፣ የድሮ ጓደኞቼ፣ ዘመዶቼ ምን ይሉኝ ይሆን፣ ይንቁኝ ይሆን፣ የኔ ብዬ የማስባቸው ሰዎች ፍቅርና ድጋፋቸውን መስጠት ይቀጥሉ ይሆን፣ የማምናቸው ሰዎች ይክዱኝ ይሆን፣ ይጠቁሙብኛል፤ የአእምሮ ህክምና ሆስፒታል ይልኩኛል፣ በሰንሰለት አስረውኝ ጸበል ቢወስዱኝስ፣ እነዚህን ጥያቄዎች ለመጋፈጥ ዝግጁ አልነበርኩም። ከፊቴ ቢሆንም መሻገር ያልፈለኩት ድልድይ ነበር። በብዙ ነገሮች የተለየ የሆነ ህይወትን ለመጀመር ምንም ሊያዘጋጀኝ 26 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
አልቻለም። ራሴንም ፈርቼ ነበር። እጅግ ግልጽ ከሆኑልኝ ሰዎች ማንነቴን ደብቄ በመቆየቴ ራሴን ብጠላውስ፤ የመኖር መብት ራሱ አለኝ? ወግ አጥባቂ የሚባል ማህበረሰብ ውስጥ እንደማደጌ ራሴን እስክጠላ ድረስ ያስጨንቁኝ የነበሩ ጥያቄዎች ናቸው። ከረዥም እና ከባድ ውጣ ውረድ በኋላ ግን በሰዎች ተቀባይነት ለማግኘት ስል ራሴን እና ማንነቴን ወደአልሆንኩት መንገድ መግፋት እንደሌለብኝ ተረዳሁ። ሌሎች ባይቀበሉኝም፣ ድጋፍ ባይሰጡኝም የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ እህት ወንድሞቼ እንዲያገኙ የምመኘውን መልካምነት እና አክብሮት ለራሴ መስጠት ጀመርኩ። ራሴን ፈልጌ ለማግኘት እና ለመቀበል ፍቃደኛ በመሆኔ ጾታዊ ማንነቴ በአንድ የሚወሰን እንዳልሆነ አወኩ። የተመሳሳይም የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ብቻ የሚያስብሉ መስፈርቶችን አላሟላሁም፣ በማህበረሰቡ ውስጥ ያለኝን ተቀባይነት ለማረጋገጥ ሲባልም ሟሟላት ያለብኝ ነገር አልነበረም። የሁሉም ስርዓተ ጾታ አፍቃሪ መሆኔና እና ከአንድ በላይ የፍቅር አጋርን የምቀበል መሆኔን ለማመን ጊዜ የወሰደብኝ እና ለአመታት ቀስ በቀስ ያመንኩበት ነገር ነው። ብዙ የቸልተኝነት፣ ያለማመን፣ ጉጉት፣ ግራ መጋባት፣ ሌላ መንገድን ፍለጋ በመጨረሻም መቀበልን የተከተለ መንገድ ነበር። ራሴን የማወቅ ጉዞዬ አሁንም እየቀጠለ ቢሆንም ራሴን መቀበሌ ግን የግሌ እና ብዙ በንጹህ አእምሮ ከጎኔ የነበሩ፤ ከራሳቸው የተለየ ማንነት ያላቸውንም የሚያከብሩ እና የሚቀበሉ ሰዎች ድጋፍ ብርታት የተሞላበት ነበር። 27 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
ትክክል
ያልሽው ነገር
አይደለም አልልሽም
ምንም የምላት ነገር አልነበረኝም፤ ዝም ብዬም የውሽት ነገር ፈጥሬ ለመናገርም ፍላጎት አልነበረኝም። ሆኖም ግን መንገር የምፈልገው
ነገር እንዳለ ግን ጊዜ እንድትሰጠኝ ጠየኳት። ለወሬ በጣም
እንደሌለኝና እና የኔ ስሜት ለሴት
እንደሆነ ነገርኳት። ትንሽ እንደመደንገጥ አለች። እኔም ታውቂያለሽ አለባብሴን ታያለሽ ከልጅነቴ ጀምሮ ማን ላይ እንደምመሰጥ ታውቂያለሽ። አልኳት። የመጀምሪያ ታዋቂ ሰው የወደድኳት ሴት ዘፋኝ እና ፊልም ሰሪ እንደሆነ አስታወስኳት። ያው አፍ አውጥቼ ባልነግራትም ብዙም ነገሬ ከሷ የተደበቀ እንዳልሆነ
ለእህቴ ራሴን ያሳወኩበት ቀን በጣም የምውደው ታሪኬ ነው። ከእህቴ ጋር ብዙ ወንድም እና እህቶች ባለመኖሩ እና ታላቄ ብትሆንም በእድሜ ተቀራራቢ ነን። በጣምም እንንቀራረባለን እናም
አብረን እያጠፋን ለሁሉም ነገር ከጎኔ ናት። እንደታላቅ እህት እንደምሳሌ አያታለሁ፤ አከብራታለሁ። ብዙም አትቀበለኝም የሚል ፍርሃት ሳይኖር ግን እራሴን ለመቀበል የወሰደብኝን ጊዜ ስለማውቀው ከሷም ጋር በዚህ ጉዳይ ለማውራት ድፍረት አላኝሁም ነበር። ግን ያው ትንሽ ብርሃን ላየ ሰው አይቶኝ ብዙም ላይጠረጥር አይችልም፤ ትንሽም ቢሆን ሰው ከማንንነቴ አይቶ ሊጠራጠር የሚያስችል አይነት ሁኔታ ነው ያለኝ። እህቴ ፖስት የማደርገውን፣ ፕሮፈይሌን፣ ቴሌግራሜን እና ሌላ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የለኝን እንቅስቃሴ ስታይ የሆነ ነገር እናዳለ ይገባታል። ነገር ግን ህይወቴ ውስጥ ፍቅረኛ እንደሌለኝ ታውቃለች፤ በተለይ ወንድ። ብዙ ጊዜ ግን ጥያቄ ታበዛላች፤ “ለምንድን ነው እንደዚህ ብለሽ ፖስት ያደረግሽው? ምን ለማለት ፈልገሽ ነው?” ትለኛለች። ለእናታችን እንኳን “እቺ ልጅ ሁሌ እንደተጎዳች አርጋ ነው የምትጵፈው” ብላታለች። እና “ይቺ ልጅ ምንድን ነው የሆነችው?” እስኪሉ ድረስ ነው የደረሱት። ለሷ አሳሳቢ ደረጃ ሲደርስባት ጊዜ በቀጥታ “እሺ አሁን ይሄ ፖስት ምን ማለት ነው?” ብላ ጠየቀችኝ። በሰአቱ ስላልተዘጋቸሁበት
ሲረጋገጥ
መልካሙንም ጥፋቱንም
እንደጎጎች
ግን እንድምትጠብቀኝ ነገረችኝ። በጣም የማደንቃት ግን እኔ እራሴ ጊዜዬን ወስጄ፣ አስቤበት እስክነግራት ድረስ ምንም ነገር ሳትል በትእግስት ነው የጠበቀችኝ። ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ብቻችንን ስንሆን ዳር ዳር ማለት ጀመርኩኝ፤ ከዛም ለወንድ ልጅ ስሜት
እና መታገስ እንደማትችል በቀልድ ጎንትላኝ በትእግስት
ነገርኳት። መጀመሪያ ላይ ስነግራት የደነገጠችው አስባበት ስለማታውቅ እንደሆነ አስረዳችኝ። እኔም ስሜቴ ለወንድ እንዳልሆነ ከተሰማኝ ቀን ጀምሮ እራሴን እስከተቀበልኩብት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሁኔታ በግልጵ አጫወትኳት። ካዳመጠችኝ በኋላ በጣም ደስ ያሰኘኝ እኔን የተቀበለችበት ፍጥነት ነው። ብዙ ሰው ከሁኔታሽ፣ እና ከአለባበስሽ ቢገምትም ሊቀበለው ጊዜ ይወስድበታል፤
ይሁን ያደኩበት አካባቢ የእኔ አይነት ሰዎች አልነበሩም። ስለዚህ ከሰው ዝም ብዬ እንዳልተቀበልኩት
እንደማልጓጓ ታውቃለች። በተጨማሪም ቤተ ሰብን የሚያስቀይም ወይም ከቤተሰብ ጋር የሚያቃርን ነገር ማድረግም እንደማልወድ
ታውቃለች። በምርጫም ከቤተሰብና
መንገድ ብቻ ሳይሆን በሌላ ሰው አይንም ነገሮችን ለማየት እና ለምረዳት መሞክሯ አስታዋጵኦ
ተካፋይ ከመሆኗም በላይ በህይወቴ ያለውን ነገር በግልፅ የማወያየው ሰው አግኝቼለሁ።
30 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ያንገራግራልም። እሷ ግን እኔን ለመቀበል ምንም አይነት ጊዜ አልወሰደባትም። በራሷ አንደበት በወቅቱ ቶሎ የተቀበለችኝም ምክንያት ስታስረዳኝ እንደዚህ ነው ያለችኝ “በሃይማኖት ዙሪያ ያለሽን ነገር አውቃለሁ እና በቤተሰብ ዙሪያም ያለሽን ነገር አውቃለሁ። ምን ያህል ለቤተሰብም እንድምትጠነቀቂ አውቃለሁ እና ይህንን ያህል አስበሽ ማንነቴ ይሄ ነው አልቀይረውም ያልሽውን ነገር እኔ ትክክል አይደለም አልልሽም። ከአንቺ በላይ አላሰብኩብትም፤ ከአንቺ በላይም አላስብበትም። እቀበልሻለሁኝ” አለችኝ። እኔ ሳስበው ልትቀበልኝ የቻለችው በደንብ ስለምታውቀኝ ይመስለኛል። የማያቅሽ ሰው ሲሆን ገና ጌይ ነኝ ወይም ሌዝቢያን ነኝ ስትይው፤ ለምን ይህን እንደሆንሽ የራሳቸውን ነገር ያስቀምጣሉ። በጣም መሰረት ከሌለው ኢሉሚናቲ ፣ 666 ናች ሁ እና ብዙ ብር ተከፍሎችሁ ነው ከሚለው ጀምሮ ብዙ ነገር ይላሉ። እሷ ግን በደንብ ማንነቴን ስለምታውቅ እነዚህ ነገሮች ውስጥ እንደሌለሁኝ ጠንቅቃ ትረዳለች። በዛ ላይ እኔ ውሎዬ ከማይሆኑ ሰዎች ጋር እንዳልሆነ በደንብ ታውቃለች። ይሄ ማለት ደግሞ በሰው ተጽእኖ ማንነቴን እንደማልመሰርት ይመሰክራል። እነ በተለምዶ ወንዳወንድ እንደሚባል ሴት ብሆንም የተወለድኩበት አካባቢም
ከልጅነቴ ጀምሬም ነገሮችን ዝም ብዬ እንደማልሞክርና ለመሞከርም
ከማህበረሰቡም ጋር ቢሆን ቅራኔ ውስጥ የመግባት ፍላጎትም እንደሌለኝም ታውቃለች። እውነት መተው ቢቻል ልተወውም እፈልጋልሁ ምክንያቱ ደግሞ ያው ከቤተሰብም ሆነ ከማህበረሰብ መጣላት አልፈልግም። እናት አባቴም እንዲያዝኑብኝ አልፈልግም። በሃይማኖቴም ቢሆን ጠንከር ያለ አቋም ነው ያለኝ። እና እራሴን መቀበሌ ማንነቴ እንጂ መተው የምችለው ነገር እንዳልሆነ ግልፅ አድርጎ ያሳያት ይመስለኛል። በጠቅላላው ይሄ ነገር ከራሴ ውጭ ያልመጣ ጫና እንደሆነ ይገባታል። ይሄ ነገር እራሴ የሆንኩት፣ የውስጤ ማንነቴ እንደሆነ ግልፅ ሆኖላታል ብዬ አስባለሁ። ሌላኛው እንድትቀበልኝ ያደረጋት ነገር የራሷ ማንነት ይመስለኛል። እህቴ ሰውን በጣም በቀላሉ የምትረዳ ሰው ናት። በራሷ
አድርጓል። አንድ ሰው አንቺ የመጣሽበትን መንገድ ማየት የሚችለው ባንቺ መንገድ ቆም ብሎ ለማየት ሲሞክር ብቻ ነው። ቸኩላ ወደ ስድብ እና ጥላቻ የማት ሄድ መሆኗም የበለጠ እንድታስተውል እና እንድትቀበልኝ አድርጓታል ብዬ አምናለሁ። ለእኔ ያላት ፍቅር ጠንካራ ባይሆን ኗሮ ለመቀበልም ያዳግታት ነበር። እህቴ በህይወቴ ውስጥ ትልቅ ሚና ያላት ሰው እንደምሆኗ መጠን ተቀብላኝ እሷ ጋር ነፃ መሆን መቻሌ ትልቅ ሰላም ነው የሰጠኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ስነግራት አንደኛ አይኔ ካረፈባት ሴት ጀምረን በግልፅ ብዙ አወራን። ከሁሉም በላይ ግን ከነገርኳት በኋላ ትልቅ እረፍት ነው የተሰማኝ። በነፃነት ስለ ህይወቴ ማውራት ቻልን እናም ከሌሎች ሰዎች ጋር ያጣሁትን ነገርም በሷ ተካስኩኝ። ከብዙ ጓደኞቼ እና አብሮ አድጓቼ በዚህ ጉዳይ ተራርቀናል። የሙጥኝ ብለው ስለህይወቴ አጥብቀው ሲጨቀጭቁኝ እና ሲያስቸግሩኝ እንድርቃቸው ተገድጄያልሁኝ። እሷ ግን በፍፁም ልርቃት አልፈልግም ነበር ምክንያቱም ከእህትነቱም በላይ በጣም ለህይወቴ ጠቃሚ ሰው ናት። አቅጣጫ በማስያዝና በማመላከት ረገድ ትልቅ ትምህርት ነው የምትሰጠኝ። እንደዚህ አይነት ሰው ሲቀበለኝ ደስታዬ ወደር የለውም።ከነገርኳት ቀን ጀምሮ የጭንቀቴ
ከእህትነትም አልፋ ጓደኛዬ ሆናለች። እንደውም ጓደኞቼን ማማከር የማልችለውን ነገር እሷን ማማከር ችያልሁ። ለእህቴ ራሴን በማሳወቄ በጣም አትርፌያለሁ። በህይወቴ ደስተኛ ካደረጉኝ ነገሮች ውስጥ አንዱ ነው።
ይገባታል።
በድንብ
31 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ የራስዎን ድምፅ ያድምጡ... https://soundcloud.com/ethioqueer Season 2, Episode 4 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 3 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 2 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 1 Produced by Queer Ethiopia QUEERETHIOPIA ኩዊር ኢትዮጵያ ምዕራፍ 2: ኢትዮኩዊር ፓድካስት | Season 2: Ethioqueer Podcast Season 2, Episode 5 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 6 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 7 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 8 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 9 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 10 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 11 Produced by Queer Ethiopia Season 2, Episode 12 Produced by Queer Ethiopia
የአንዲት ሴት አጋርነት ጉዞ
32 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ የትኛውን መጸደጃ ልጠቀም የሚለው ጥያቄ ሁሌም አእምሮዋ ውስጥ እንዳለ ይሰማታል። ራቅ ወዳለ ህንጻ ሄዳ የትኛው መጸዳጃ በየትኛው ሰአት ብዙ ሰው እንደማይጠቀመው ታጠናለች። አንዳንዴም እንደስርዓተ ፆታ እና ስነጥበባት ያሉ “ሊበራል” ዲፓርትመንቶች የሚገኙበትን ህንጻ ትመርጣለች። የፆታ መረዳቴ “ባህላዊ” የሚባል ባይሆንም እኔም ከአንዴ በላይ “ይህ የሴቶች መጸዳጃ ነው” ተብዬ አውቃለሁ የሚመች መጸዳጃ ፍለጋም ኳትኛለሁ። ነገሩን ሙሉ በሙሉ ለመረዳት የሚያስችል እውቀት አልነበረኝም። የዚህችን ሴት መጸዳጃ ቤት ፍለጋ ውጣ ውረድ ከሰማሁ በኋላ ትራንስ መሆኑን በግልጽ ያሳወቀ አንድ ሰው ልምዱን ያካፈለበት የውይይት መድረክ ላይ የመገኘት እድሉ ነበረኝ። ውይይቱ ሁለት ሰአት ያህል ርዝመት የነበረው ሲሆን ይህ ትራንስ ሰው ስለህይወቱ ብዙ ነገር የተናገረበት ነበር። ከሁሉም በላይ በውስጤ የቀረው ግን “ከምንም በላይ እውነቴን ያጸናልኝ ነገር በአደባባይ ቲሸርቴን አውልቄ መጓዝ መቻሌ ነው” ያለው ነው። አየሩ ጥሩ በሆነበት ወቅት ራሱ ያለቲሸርት እንደሚንቀሳቀስ ተናግሮ ነበር። ውይይቱ ፆታን በሁለትዮሽ መንገድ ብቻ ለሚያይ ለእንደኔ አይነት ሰው ግራ የሚያጋባ ነበር። ጀማሪ ፌሚኒስት ነበርኩ። ከኢትዮጵያ ከሄድኩ ቅርብ ጊዜዬ ስለነበር ፆታን ከባዮሎጂ እይታ ውጪ ለመረዳት የቋንቋ ብቃቱም አልነበረኝም። የጾታ ልዩነት ምን ማለት እንደሆነ አልገባኝም፤ ጾታን መቀየር የሚለው ደግሞ ለኔ ይበልጥ እንግዳ ነበር። ይሁንና ለዚህ ልምድ እና ማንነት ቦታ ሊኖረኝ እንደሚገባ ተረዳሁ። በኮንፈረንሱ ላይ ከፆታ ልዩነት ጋር በተያያዘ ያሉ ጉዳዮችን ርእስ ባደረጉ ውይይቶች ላይ ተሳተፍኩ፤ እውነት ለመናገር የተወሰነው ብዙም አልገባኝም። ህብረተሰቡ “ትክክለኛ” ፆታ ብሎ ከማይፈርጃቸው እና ከተለመደው ህግጋት ወጣ ያሉ ሰዎችን መረዳት ብቻ ሳይሆን በአጋርነት መቆምን አላማዬ አድርጌ ያዝኩ። ይህ ውሳኔዬ የግል የሆነውን ያህል ፖለቲካዊም ነበር። የአጋርነትን አስፈላጊነት ከመረዳቴ በተጨማሪ ጭቆናዎች እንዴት እንደሚዛመዱ እና ቢያንስ ማንም ሰው ራሱን ባቀረበበት መንገድ ወይም ስለሰውነታቸው በተሰማቸው ስሜት ምክንያት እንዲሰቃይ አልፈለኩም። የሰዎችን ስሜት መረዳቴ ለሌሎች ቦታ እንድሰጥ እንዲሰማኝ አድርጓል። ብዙ መረጃ ባይኖረኝም ፌሚኒዝምን ሰፋ ባለ መንገድ መረዳቴ ነገሩ በቀላሉ እንድቀበል አድርጎኛል። ከማንኛውም በላይነት እና ጭቆና የጸዳ አለምን ማየት ፈልጋለሁ። ቀሪውን መረዳት ግን ጊዜ ወስዶብኛል። ለመማር ምን አደረኩ? በመጀመሪያ ወደ ቤተመጻህፍት ሄጄ ስለ ጾታ ልዩነት፣ ትራንስ ሰዎች እንዲሁም ጾታ ሁለት ብቻ ነው የሚለውን አመለካከት ስለሚቃወሙ ሰዎች ብዙ አነበብኩ። ከኢትዮጵያ ውጪ ከመጓዜ በፊት ጾታን ከሁለቱ ጾታዎች ውጪ አድርጌ አስቤው አላውቅም ነበር። ሰዎች ጾታን በሸፈነ፤ በደባለቀ እና በአንድ ባልተወሰነ መንገድ እንዴት እንደሚገልጹት ተረድቻለሁ ይሁንና ሁለቱንም መሆን ወይንም አንዱንም አለመሆን እንዲሁም ከጾታዊ
ስርአተ ፆታን ከሁለቱ ፆታዎች ውጪ
አድርጌ አስቤው አላውቅም ነበር
33 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
34 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ማንነት ጋር ስላለው ትስስር መረዳት ለኔ አዲስ ነገር ነበር። እነዚህ ሀሳቦች ትርጉም እንዲሰጡ ማስቻል ቀላል ነበር ማለት አልችልም። ለቀናት ሳነብ ቆይቻለሁ። አንዳንድ መጽሃፎችን እስክረዳቸው
የተባለውን መጽሀፍ ደግሚ ሳነብ እና ወንድም ሴትም አለመሆን ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት ስሞክር አስታውሳለሁ። የራሳቸው የሆነ አዲስ ማንነትን ለመግለጽ የነበራቸውን ጽናትም አድንቄያለሁ። መጽሀፉን ሳነብ “አሁን እኔ ማነኝ፣ ሴት ወይስ ወንድ፣ ያሉኝ ምርጫዎች ሁለቱ ብቻ እስከሆኑ ድረስ ይህ ጥያቄ መጠየቅ ቢኖርበት እንኳን መቼም አይመለስም” የሚለውን መስመር በድጋሚ ሳነብ ሙሉ በሙሉ ባለመረዳቴ የቅርብ የምለውን ሰው እንድጠይቅ ድፍረቱን ሰጥቶኛል። ጁዲዝ በትለር ሌላ የመረጃ ምንጬ ነበሩ። ጽንሰሀሳቡ ከባድ ቢሆንም ተስፋ አልቆረጥኩም። “ስርዓተ ጾታ አንድ ሰው የሆነው ነገር ሳይሆን፤ የሚያደርገው ነገር ነው፤ ድርጊት እንጂ ማንነት አይደለም” ይላሉ። ስርዓተ ጾታን እንደድርጊት አስቤው አላውቅም ነበር። ይሁንና እነዚህ ደራሲዎች ራሴን በደንብ እንድፈትን አደረጉኝ። ካነበብኩ በኋላ ለመረዳት የሚከብዱኝን ሀሳቦች ጾታን ከኔ በተሻለ መንገድ የሚያውቁ ወይም ፌሚኒስት የሆኑ ሰዎች እንዲያስረዱኝ ጠይቃለሁ። ሁሉም ነገር ቀላል አልነበረም። ብዙ ስህተቶችን ፈጽሜያለሁ አንዳንዴም ላለመሳሳት ስል ዝምታን እመርጥ ነበር። የሰዎችን ጾታ ተሳስቼም አውቃለሁ። ስህተቴን ማመን እና ይቅርታ መጠየቅን ተማርኩ። መጀመሪያ ላይ የትራንስ ሰዎች መብት የሴቶችን መብት ጥያቄ እየተጋፋ እንደሆነ አስብ ነበር። ራሴን ለጭቆና ደረጃ ስሰጥ እና በትውልድ የተሰጠኝን ጾታ በመቀበሌ ያገኘሁትን ልዩ መብት ለመጠበቅ ስሞክር አገኘሁት። ስህተቶቼን ለማወቅ ብዙ ጊዜ አልወሰደብኝም። ብዙዎች እንደሚሉት ሁላችንም ነጻ እስካልሆንን ድረስ ማናችንም ነጻ አይደለንም። እናም ነጻነት በትንሽ አቅርቦት ያለ እና ለሁላችንም የማይዳረስ አድርጌ ማሰብ ማቆም እንዳለብኝ ተረዳሁ። ጊዜ ወስዶብኛል። አሁንም አንዳንዴ እሳሳታለሁ። የተማርኩት ትልቁ ትምህርት ግን ጾታዊ ልዩነት ካላቸው ሰዎች ጋር በአጋርነት መቆም ማለት አለመሳሳት ማለት እንዳልሆነ ነው። አጋርነት መደገፍ፤ በአብሮነት መቆም፤ ለመብታቸው መናገር፤ ሌሎችን መጋፈጥ እና ሁሌም የተሻለ ሆኖ ለመገኘት ዝግጁ መሆን ነው። ነጻነት በትንሽ አቅርቦት ያለ እና ለሁላችንም የማይዳረስ አድርጌ ማሰብ ማቆም እንዳለብኝ ተረዳሁ ።
ድረስ ደጋግሜም አንብቤያለሁ። የሌስሊ ፋይንበርግን <<ስቶን ቡች ብሉስ>>
ከአጋርነት ወደኩዊርነት ግንዛቤ
35 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
በወቅቱ የማውቀው ጾታዊ ማንነት ይህን ብቻ ነበር። ብዙ የተማርኩትን ነገር እንድተው
ሰአት የቅድሙን ጥያቄ ጠየኩ። “ልጃችሁ የተመሳሳይ
ጾታ አፍቃሪ ቢሆኑ ምን ታደርጋላችሁ” ጓደኞቼ የምጠብቀውን
መልስ ሰጡኝ። “እክዳቸዋለሁ” “አባራቸዋለሁ” “እጸልይላቸዋለሁ”
የኔ መልስ ወደአጋርነት የመራኝ የመጀመሪያ ምልክት ይመስለኛል።
“ልጃችሁ ወደኔ ቢመጣ ግን እቀበለዋለሁ” አልኩ። ጓደኞቼ
ሃሳባቸውን እና ተቃውሟቸውን ገለጹ ከዛ ርእሳችን ተቀየረ።
ለኔ ግን ትክክለኛው ንግግር የጀመረው ያኔ ነበር፤ አሁን 7 አመት
አስቆጥሯል። ፖለቲካዊ እውቀታችን እየጨመረ ነው። እኔ በይፋ ኣጋር በሆንኩበት ሰአት ራሱ በፖለቲካ ወደግራ ዘመም ስናደላ ተመልክቻለሁ።
36 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ከእኔ በፊት እንደነበሩ ራስወዳድ ሰዎች በዚህ ጽሁፍ ስለራሴ አወራለሁ። ስለዚህ ብዙ “እኔ” “የኔ” የሚሉ ቃላቶችን ለማንበብ ተዘጋጁ። ምክንያቱም ይህ የኔ ታሪክ ነው። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ልጅ ቢኖረኝስ ብዬ ያሰብኩት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ሆኜ ነው። አክራሪ ሀይማኖተኛ ከነበረው አስተዳደጌ ወጥቼ በራሴ መንገድ ይህ የወሲባዊ ማንነት ምን ማለት እንደሆነ መረዳት እየጀመርኩ ነበር። የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችም እንደማንኛውም ሰው ሰብአዊ መብት ይገባቸዋል ብዬ ገና ማሰብ መጀመሬ ነበር። ይህ አዲስ አመለካከቴ በዋናነት የመጣው ወግአጥባቂ አስተዳደጌን መቃወም እንድጀምር በረዳኝ የኢንተርኔት ግኝቴ ነው። የፌስቡክ አካውንት መክፈቴ ነበር። እድሜዬን ይናገርብኝ ይሆናል ግን በወቅቱ ፌስቡክ የማህበራዊ ድረገጾች ቁንጮ ነበር። ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎችን የተዋወኩት እዛ ላይ ነበር። ሁሉም እንደማንኛውም ሰው የሆኑና ምንም የተለየ ነገር ያላየሁባቸው ነበሩ። እውነት ለመናገር ትንሽ አሳዝኖኝ ነበር። በፈጣሪ የሚጠሉት የተረገሙት ሰዎች በቃ እንደዚህ ናቸው፡ የአለምን ፍጻሜ ያመጣሉ የተባሉት እነሱ አልነበሩም እንዴ፤ ከጠበኳቸው በታች ሆነው ስላገኘኋቸው አበሳጭቶኝ ነበር። ያ ሁሉ የሰማሁት የሚያርድ ወሬ ምንም ፍሬ አልነበረውም። ይበልጥ ባዋራኋቸው ቁጥር ምንም ያላደረጉ ሰዎችን ታላላቆቼ እና ቸርች በተነገረኝ ብቻ በመነሳት እንደጠላሁ ገባኝ። ከሆነ ጊዜ በኋላ አስፈላጊነቱ አልታየኝም። “የፈነዳሁበት” ጊዜ ስለነበር የተነገረኝን ሁሉንም ነገር የፈጣሪን መኖር ጭምር እጠይቅ ነበር። ስለዚህ ስለጌዮች ላይ ያለኝንስ አመለካከት ለምን አላስብበትም; ግልጽ ለማድረግ ይህን ስል ጌይ እና ሌዝቢያን ማለቴ ነው፤
ያደረገኝ ጥያቄ ነበር በመጨረሻም ራሴን አጋር ሆኜ አገኘሁት። LGBTQIA+ምን
እንደሆነ
በነበርኩበት
ማለት
በደንብ ተረዳሁ። በደንብ ለመረዳት ከጓደኞቼ ጋር
37 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ጠንካራ አጋር መሆኔ ብዙ ጓደኞቼ ወሲባዊ ማንነቴን እንዲጠራጠሩ አድርጓቸዋል። እኔ ግን በደፈናው “አጋር ስለሆንኩ ብቻ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ነኝ ማለት አይደለም፤ እኔ የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ነኝ” ብዬ እከራከር ነበር። ርእሱ በተነሳ ቁጥር ለመመለስ ቀዳሚ ነበርኩ። ለኔ ትርጉም የሚሰጥ አልነበረም “እሺ ህይወታቸው ሰውን መውደዳቸው እና አኳኋናቸው ከእናንተ ይለያል፣ እና ምን ይሁን” ስል እጠይቃለሁ “ምን አገባችሁ እናንተን አይመለከትም” እላለሁ። ይህም ወግአጥባቂ ከነበረው አስተዳደጌ ላይ የነበረኝን ተቃውሞ አጠናከረው። የማህበረሰብ ፍትህ ፈላጊ ሆንኩ። ከዛም በቻይና ወደ20000 የሚሆኑ ሰዎች በኮቪድ ታመሙ። ያ ቁጥር በፍጥነት ወደ 5 ሚሊዮን አደገ። ቤት ውስጥ ያለምንም ስራ ለመቀመጥ ተገደድን። ከራሴ ጋር ለማውራት ጥሩ ጊዜ ነበር። ወረርሽኙ ከተነሳ ከሁለት ወራት በኋላ የወሲባዊ ማንነት መወዛገብ ውስጥ ገባሁ። ሴቶች፣ ወንዶች፣ ከሁለተዮሽ ስርዓት ውጪ የሆኑ ሁሉም ሰው እንደሚማርከኝ ተረዳሁ። ይህን ማመን ለኔ ከባድ ነበር። ያስፈራል። ለአንድ ማህበረሰብ ጭቆናቸው እንዲቀር መከራከር እና የማህበረሰቡ አባል መሆን የተለያዩ ነገሮች ናቸው። እናቴ ብታውቅስ የሚለው ፍርሀት ምን ያህል አስጨንቆኝ እንደነበር አስታውሳለሁ። ቤተሰብ ላይ ስለሚያስከትለው “ውርደት”፣ የማላውቃቸው ሰዎች ስለሚያደርሱብኝ ጥቃት እና በህግ መጠየቅ በጣም አስፈሩኝ። የብቸኝነት እና አስፈሪ ጊዜ ነበር። በደንብ እንዲገለጽልኝ ያደረገው ነገር ከአንድ የማውቀው ሰው ጋር የሁለቱም ስርዓት ጾታ አፍቃሪ ስለሆነ የሪያሊቲ ሾው አባል ያደረግነው ንግግር ነበር። ያ ሰው በቲቪ ስላየው ሰው በሚወዱት ሰው ብቻ በመነሳት ያላቸውን ንቀት ስመለከት ነገሮች ተቀየሩ። እንደበፊቱ በወረቀት መረዳት ብቻ አልወሰድኩትም አሁን በኔ ላይ የደረሰ ጥቃት ነው አልኩ። የሚያስደነግጥ እውነታ ነበር። 12ኛ ክፍል ሆኜ እንደተፈጠረው ይህን አዲስ ህይወት መልመድ ነበረብኝ። አሁን አጋር ብቻ ሳልሆን የማህበረሰቡም አባል ነኝ። ይህም አዲስ ህይወትን እንዴት መምራት እንዳለብኝ እንድማር እና ከሰዎች ጋር ለአመታት የገነባኋቸውን ግንኙነቶች መለስ ብዬ እንዳይ አደረገኝ። ስለፍቅር ግንኙነት ከሌላ አቅጣጫ መመልከት ደስ የሚል ጉዞ ነው። ለራሴ ማንነቴን ከተቀበልኩ ሶስት አመት ሆኖኛል። ፍርሀቱ፣ ውጣውረዱ፣ የእለትተእለት መሰናክሎቹ እንዳሉም ሆነው ይህንን ማንነቴን ማወቄ ተገቢ ነበር። ይህን ማመን ለኔ ከባድ ነበር። ያስፈራል።
የተለያዩ ጥጎች ኑሯችንን ጀመርን። በነዛ አመታት
ግን በየራሳችን መንገድ ነበር። እንገናኛለን እንባባል እና ለመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሳምንታት አውርተን ከዛ
እንጠፋፋለን።
ስለተደረገ ቤት ውስጥ ነበርን። ቤተሰባችን ውስጥ ስላሉ ችግሮች፣ ብንራራቅም ስለሚያመሳስሉን
ልጠብቅ ...
አገኘኋት። በንግግራችን ግንኙነታችን ውስጥ የነበረውን
ውስጥ ስለምንኖር እንደሆነ ባላውቅም በፖለቲካ በኩል ብዙ የሚያስማሙን ነገሮች
ነበሩ። ይህም በደንብ እንድንወያይ እና አንዳችን ከአንዳችን
እንድንማር ረድቶናል። የምናወራበትን እና በኢንተርኔት
አብረን የምንሰራበትን ጊዜ በጉጉት እጠብቅ ነበር። እውነተኛ
ለሆኑ ውይይቶች እና ትርጉም ያለው ግንኙነት እንዲኖረን
ለማድረግ ሁለታችንም ዝግጁ ነበርን። ስለሀዘን፤ ልብ
ስብራት፣ፍቅር እና በ20ዎቹ እድሜ ውስጥ ስለመኖር እናወራለን። ቤተሰባዊ ግንኙነት ላይ የተመሰረተ ጓደኝነት በመሆኑም በአጭር ጊዜ ጠንካራ ሆነ። አንድ ጊዜ ለረዥም ሰአት ካወራን በኋላ ስላወራንበት ርእስ የተሰራ ሚም አይቼ ልልክላት ፈለኩ። ሁለታችንም ባለፉት አመታት አዳዲስ አካውንቶች ስለከፈትን ኢንስታግራም ላይ ጓደኞች አልነበርንም እናም የምጠቀምበትን ስም ነግሬያት
38 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ በ2021 ለአራት ሰአታት በቆየ የስልክ ንግግራችን መሀል የምወዳት የአክስቴ ልጅ ስለወሲባዊ ማንነቷ ነገረችኝ። ለአመታት በመሀላችን ርቀት የነበረ ቢሆንም በ2020 የኮቪድ ወረርሽን ሲጀምር ግንኙነታችንን
ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት
በሀገሪቱ
የምንሄደው
በድጋሚ
በ2020
ላይ ከቤት
ለሰአታት
ስለምንከታተለው ሚዲያም ጭምር
ወሬያችን ቅርበታችን እንዲጨምር እና ይበልጥ እንድንተዋወቅ ረዳን። ደግ፣ አስቂኝ፣ ታጋሽ እና ለማውራት የማትከብድ ሆና አድጋ የተዘረጉ ክንዶች
መራራቅ ማጥበብ ቻልን። ሁለታችንም የስነጥበብ ኮሌጅ ስለተማርን ይሁን፣ አዋዋላችን ተመሳሳይ ስለነበር፣ ወይም የሚመሳሰል ፖለቲካዊ አመለካከት ያላቸው ከተማዎች
ወደድሮው መለስነው።
በኋላ ወደ አሜሪካ መጥተን
የቤተሰብ ፕሮግራሞች ላይ አልፎ አልፎ ብንገናኝም
ስትደውልልኝ ሁለታችንም ያለንባቸው ከተማዎች
እንዳንወጣ እገዳ
ነገሮች በአጠቃላይ ስለሁሉም ነበር
በስልክ አወራን። ስለ ጥበብ አለም፣ ፖለቲካና
አልቀረንም።
: የአክስቴን ልጅ ስቀበል ላንሳባት ወይስ ዝም ብዬ ራሷ እስክትነግረኝ
አባል መሆን ምን ማለት ነው የሚለውን ማሰብ ጀመርኩ። አዲስ አበባ ውስጥ እንደማደጌ
አያውቅም። የተማርኩት አንድ ስርዓተ ጾታ ብቻ የሚማሩበት ትምህርት ቤት ነበር። ሳድግ አልፎ አልፎ ሴቶች
ተደርገው የሚወሰዱ ነበሩ። አንዳንድ ሴቶች እንደውም ቻፒስቲክ ለመዋዋስ በሚል
ወቅት
አድናቂዎቻቸው በሚያሳዩት ድጋፍ ነው። ይህን ለማለት የፈለኩት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች
ጠል በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ባድግም ማንነቱ በተለይም
ነጥለን ማየት ለምንችለው ግን በዙሪያችን ነበር ለማለት
ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታችንን ልናጠናቅቅ አካባቢ
ሁለት ሴቶች ፍቅረኞች እንደሆኑ አሳወቁ። በኋላ ላይ ግን
አንዳቸው “ሀሰት ነው” በማለታቸው ማንነታቸው ተደብቆ
39 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ... ይፋ
እንድትከተለኝ ጠየኳት። የጓደኝነት ጥያቄዋን ስትልክኝ ከአካውንቷ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ መሆኗን ተረዳሁ። ከአካውንቷ እና ከዚህ በፊት በወሬ መሀል ከምትላቸው ነገሮች በመነሳት ገምቼ ነበር። ለሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ርእሱን ላንሳባት ወይስ ዝም ብዬ ራሷ እስክትነግረኝ ልጠብቅ ብዬ ከራሴ ጋር ተሟገትኩ። በዚህ ግራ መጋባት ውስጥ እያለሁ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ማህበረሰብ
የማህበረሰቡ አባል መሆናቸውን ይፋ ካደረጉ ሰዎች ጋር ምንም አይነት ትውውቅ ኖሮኝ
እንደሚሳሳሙ
ማንነት ሳይሆን እንደ ‘‘አስቂኝ” ወይም “የተጋነነ የሴቶች ጓደኝነት” መገለጫ እንደሆኑ
በአደባባይ ይሳሳሙ ነበር። ስርዓተ ጾታን በተለያየ መንገድ የሚገልጹ ተማሪዎችንም ተመልክቻለሁ። አለባበሳቸው፣ ጫማቸው፣ አረማመዳቸው፣ አነጋገራቸው ወይም ጸጉራቸውን አያያዛቸው ውስጥ የሚታይ ነበር። ሁሉም ሰው አንዳይነት በሆነበት ሁኔታ ውስጥ ራሳቸው በተለየ መንገድ የሚገልጹትን ነጥሎ ማውጣት ቀላል ነበር። እነዚህ ተማሪዎች የሚገለሉ አልነበሩም እንደውም ትምህርት ቤት ውስጥ ታዋቂ ነበሩ፣ ለየት ያሉ በመሆናቸው ሴት ተማሪዎች “ክረሽ” አለብን ይሏቸውም ነበር። ይህ “ክረሽ” በደንብ ይታይ የነበረው በአብዛኛው የወንድ ተብለው የተመደቡ ገጸባህርያትን በድራማ ላይ በሚጫወቱ
ካደረጉ ሰዎች ጋር ምንም አይነት ትውውቅ ኖሮኝ አያውቅም
እሰማ ነበር። እነዚህ ክስትቶች ግን እንደወሲባዊ
ቀረ።
ነው”
ክፍላችን ውስጥ ስለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪነት “ስነምግባራዊነት” ብዙ እንከራከር ነበር። እኔ “አዎ ልክ
ከሚሉት ወገን ነበርኩ። ከዚህ ክርክር በፊት ግን
አእምሮዬ
ክፍት ሆነ። በክፍል ውስጥ ክርክሩን ስናደርግ አስተማሪዬ በምከራከርበት
ነጥብ ከልቤ እንደማምን ስረዳ ደንግጦ ነበር። ክፍሉ ከማለቁ በፊት
አስተማሪዬ “ስነምግባርሽ ከ10 ሁለት ነው” አለኝ። በአስተማሪዬ መወደድ
እፈልግ ስለነበር ለኔ
ተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያንን ያየሁት በአሜሪካ ፊልሞች ላይ በሚተውኑ ወንድ ገጸባህርያት ውስጥ ነበር በመሆኑም እንደማንነት ምን ማለት እንደሆነ መረዳቱ አልነበረኝም። ይሁንና ታታሪ ተማሪ ስለነበርኩ የተሰጠኝን ርእስ
ብዙ አነብ ነበር። በዚህም የተመሳሳይ ጾታ
ለመደገፍ እንዲረዳኝ
አፍቃሪዎች እንድደግፍ
ከባድ ነበር ግን ቤት ሄጄ ለእናቴ ስነግራት በራሴ ትክክል የመሰለኝን መወሰኔ ጥሩ እንደሆነ ነገረችኝ ስለዚህ እንዳሰብኩት መጥፎ ነገር እንዳልሆነ አሰብኩ። ኮሌጅ ለመግባት ወደውጪ ስሄድ የሄድኩበት ዩኒቨርስቲ “የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ሴቶች መካ” ተብሎ እንደሚጠራ አወኩ፣ በአጠቃላይ ለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪዎች ገነት የሚባል ነበር። የመኝታ ደባሌም የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ነበረች፣ እናም ከብዙ የማህበረሰቡ አባላት ጋር ጓደኛ ልሆን ቻልኩ። ራሴን አጋር እንደሆንኩ አስብ የነበረ ቢሆንም ብዙ መቀየር ያለብኝ የተሳሳቱ አመለካከቶች እንዳሉብን ተረዳሁ። ስለጾታዊ ማንነት የምማርበትን እድል አገኘሁ። ይህን እድል ማግኘት መቻሌ ልዩ ጥቅም እንደሆነ ይገባኛል። ከዚህ የተማርኩት ትልቁ ነገር ግን ያሉኝን የተሳሳቱ አመለካከቶች መቀየሬን መቀጠል እንዳለብኝ እና የማህበረሰቡ አባል ባልሆንም ነገሮች
ጾታ አፍቃሪ መለያን ለምን እንደምትጠቀም ጠየኳት። ጥያቄዬን በቁምነገር ባለመውሰድ
ለመገላለጽ የተወሰኑ ደቂቃዎች ወሰድን። የአክስቴ ልጅ ከልብ ጓደኞቼ አንዷ ናት። የተሻለ ሰው እንድሆን የምትረዳኝ እጅግ ውብ ሰው ናት። በዙሪያዋ ላሉ ሰዎች እንዴት መልካም ጓደኛ እንደሆነች እና እነዚህን ግንኙነቶች እንዴት እንደምትገነባ በማየት እደነቃለሁ። የምነጫነጭበት፣ የማለቅስበት እና የተሻለ ሰው መሆን የምችልበትን ቦታ ሰጥታኛለች። በሚገባኝ ወቅት ተጠያቂ ታደርገኛለች፣ ግን ደሞ ሁሌም ከጎኔ እንደሆነች አውቃለሁ። ከምንም በላይ ለመወደድ ቀላል ሰው እንደሆንኩ
ለራሴ የምሰጠውን ግምት ማሟላት በማልችልበት ወቅት እንኳን በቂ እንደሆንኩ፣ ፍቅር እና ክብር እንደሚገባኝ እንዲሰማኝ ታደርጋለች። በጣም እወዳታለሁ። ለወደፊት የምናስባቸውን
እቅዶች፣ የምናወራቸውን ቀልዶች እና ሀሜት በጣም እወደዋለሁ። ይሄን ጽሁፍ የሚያነቡ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጓደኞቻቸው ወይም ቤተሰቦቻቸውን እንዲያስቡና ምን ያህል እንደሚወዷቸው እንደሚያስታውሳቸው ተስፋ አደርጋለሁ።
የተሻሉ ማድረግ እንዳለብኝ ነው። ከአመት በፊት ትርጉም ባለው መንገድ ወደህይወቴ የመጣችው የአክስቴ ልጅ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ መሆኗን በገመትኩበት ወቅት የነበረኝ አመለካከት ይህ ነበር። ካነበብኳቸው መጽሃፎች እና ከምከታተላቸው ሚዲያዎች እንደተረዳሁት በሷ መንገድ እስክትነግረኝ መጠበቅ ትክክለኛው ውሳኔ ነበር። ይሁንና ለማሻሻል እየሞከርኩ ያለሁት ነገር ቢሆንም ትግስተኛ አይደለሁም እናም ከጥቂት ሳምንታት በኋላ በኢንስታግራም አካውንቷ ላይ የተመሳሳይ
እንደቀልድ ያደረገችውን ነገር እንደሆነ ነገረችኝ። ያለችውን አመንኳት። እናም ወሲባዊ ማንነትን የሚገልጽን ነገር እንደቀልድ መጠቀሟ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጠል ትሆን ብዬ እንዳስብ አደረገኝ። በቀጣዮቹ ሳምንታት በወሬያችን መሀል እኔ ስለጉዳዩ ያለኝን አመለካከት ገለጽኩላት። አንድ የእረፍት ቀን ተገናኝተን በደንብ እያወራን ነበር። ይህ ወቅት ይበልጥ እንድግባባ እና እንድንተማመን ረዳን። ከረዥም ጊዜ በኋላ በተለመደው የስልክ ንግግራችን ስለፍቅር ግንኙነት እያወራን ነበር። በመሀል የአክስቴ ልጅ ንግግሯን ቆም አድርጋ “የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ነኝ” አለችኝ። ተቀበልኳት። ወደተለመደው መቃለዳችን ከመሄዳችን በፊት የተፈጠረውን ለመረዳት እና ፍቅራችንን
እና
ትርጉም የሚኖረው እነዚህ አጋሮች ያለንበትን ሁኔታ ለመረዳት እና እኛን ለመደገፍ ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ ካደረጉ ብቻ እንደሆነ አምናለሁ። አለበለዛ “ጌይ
የምትመኘው ነገር አልነበረም ግን
በንጹህ አእምሮ ልትረዳኝ እና ልትደግፈኝ ሞክራለች። በተለይም ብዙ ጊዜ አብረናቸው
ከምናሳልፋቸው ሰዎች ጋር ራስን መሆን መቻል ሰላም የሚሰጥ ነገር ነው። ይህንን
ማንነቴን ቢያውቁ በሰከንድ ሊገድሉኝ የሚወስኑ ማሰብ የማይችሉ ሰዎች በዙሪያዬ እንዳሉ ራሴን በየጊዜው በማስታወስ ለመጠንቀቅ እሞክራለሁ።
42 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ አጋሮች አሏችሁ? ካሉ እነማን ናቸው? እንዴትስ ነው ድጋፋቸውን የሚያሳዩት? እነዚህ ምላሾች ከፌስቡክ ገፅ የተወሰዱ ናቸው ... አንድ ጓደኛዬ ትጠራጠር ስለነበር ሰክሬ ጠየቀችኝ። ከዛም ነገርኳት በመልካም ሁኔታ ነበር የተቀበለችኝ። እውነት ለመናገር ለራሷም ሆነ ለሌላ ሰው
ግን ደግሞ በማደርገው ነገር ላይ መብት ያላቸው ሰዎች መኖራቸው እና እነዚህ ሰዎች ምንም የማያውቁ ደደቦች መሆናቸውን ሳስብ እበሳጫለሁ። ስለማንነቴ የሚያውቁ እና የሚደግፉኝ የተወሰኑ የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ጓደኞች አሉኝ። ሰፋ ባለ መልኩ ባለኝ ሌላ የጓደኝነት ቡድን ውስጥ ደግሞ “አትጠይቁ አልናገርም” ብለን ሳናወራ የምንግባባበት ሁኔታ አለን። ከአመታት በፊት እኔና የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጓደኞቼ የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ የሆኑ አጋሮችን ስናገኝ በደስታ ጓደኛ እናደርጋቸው ነበር። አሁን ግን ይህ ጓደኝነት
ጓደኛ አለኝ” ለመባል ብቻ ጓደኝነትን መመስረት አልፈልግም።
43 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ ለአመታት ጾታዊ ማንነቴን ይፋ አድርጌ በመቆየቴ አሉታዊ ጎኑ የሚያውቁኝ እና ከነማንነቴ የሚቀበሉኝ ሰዎች “ታሳካዋለህ” “የምታደርገውን ቀጥልበት” “የምትሰራውን ነገር ወድጄዋለሁ” በማለት የሚደግፉ አለመሆናቸው ነው። ሁሌም ሰውን የምረዳው እኔ ሆኜ መገኘት አድካሚ ነው። “ትልቅ ድጋፍ” የተጋነነ ነገር ነው ብዬ አስባለሁ።
ሰላም በጸሎት እባላለሁ። አዎ የሚደግፉኝ እና የሚቀበሉኝ ቤተሰብና ጓደኞች አሉኝ።
ከቤተሰቦቼ መሀል አንዱ ታላቅ ወንድሜ ነው። እሱም የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ነው፤
ታናሽ እህቴ የተቃራኒ ጾታ አፍቃሪ ብትሆንም ሁሌም ከጎኔ ናት። አጋርነታቸውን
የሚያሳዩኝ ሶስት ጓደኞችም
44 ንስንስ መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩
አሉኝ። የነገርኳቸው ቀን በጾታዊ ማንነቴ ደስተኛ እንደሆኑ እና ጓደኝነታችን ላይ የሚፈጥረው ለውጥ እንደሌለ ነግረውኛል። ይህ ሁሉ የሚደግፈኝ ሰው ስላለ ፈጣሪ ይመስገን።
45 ንስንስ | መጋቢት 2015 ቅፅ ፫ | ቁጥር ፩ የቅርብ ወዳጆቼና ጓደኞቼ ጌይ እንደሆንኩ ያውቃሉ። ይህን የሚያውቁት እኔ ስለምነግራቸው ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ ጉዳዩ ሲነሳ ረጋ ብዬ ለማስረዳት እሞክራለሁ ። ይህን ከሚቃወሙት ጋር አልታገልም። ስለዚህ፣ ዜጋ ያልሆኑ ሶስት ጓደኞቼ ስለ እኔ እና ሌሎች አምስት ጓደኞቼ እኔ ዜጋ መሆኔን ያውቃሉ። እህቴ ደጋፊዬ ናት፤ ፌስቡክ ላይም አንድ ጓደኛ አለኝ። ጌይ ባሆንም ይወደኛል ይደግፈኛል።
የኡጋንዳ ፓርላማ የLGBTQ+ ማንነትን ወንጀል የሚያደርግ ህግ አውጥታለች።ፕሬዚዳንት ሙሴቬኒ ህጉን እንደማይፈርሙ ተስፋ እናደርጋለን:: በኡጋንዳ ከሚገኙ የኩዊር ቤተሰቦቻችን ጋር በአጋርነት ቆመናል። QUEERETHIOPIA ኩዊር ኢትዮጵያ