LITS

Page 1

Beyond Production

2020

ከማምረት በላይ

Beyond Production

2013 ዓ.ም



የኢትዮጵያ እንስሳት ልየታ፣ ምዝገባና ክትትል ስርዓት እና የኳራንቲን ኢንስፔክሽን ሰርተፊኬሽን የአሰራር ሂደት


ይዘት መግቢያ.................................................................................1 I. የኢትዮጵያ እንስሳት ልየታ፣ ምዝገባና ክትትል ስርዓት አሰራር ሂደት 1.

የእንስሳት ልየታ እና ምዝገባ ስርዓት የጆሮ መለያ አጠቃቀም የአሰራር ሂደቶች.........3 1.1.

ወደ ማሰራጫ ጣቢያዎች የሚደረግ የጆሮ ላይ መለያ ወጪ ሂደት..............4

1.2. የእንስሳት ባለቤት ከማሰራጫ ጣቢያዎች የጆሮ መለያን የሚገዛበት ሂደት........5 2.

ብሄራዊ የኢትዮጲያ የእንስሳት የጆሮ ላይ መለያ አጠቃቀም መመሪያ.................6 2.1. መለያዎችን በጆሮ ላይ የማስቀመጥ ቅድመ ሁኔታዎች......................... 6 2.2. የጆሮ መለያ አቀማመጥ ሂደት..............................................9 2.3. የጆሮ መለያ መተካት.........................................................11

3.

የእንስሳት ልየታ እና ምዝገባ የመረጃ ቋት ስርዓት....................................11 3.1. የማዕከላዊ የመረጃ ቋት......................................................11 3.2. የእንስሳት ማቆያ ስፍራ ምዝገባ..............................................12

II. የቁም እንስሳትን ወደ ውጪ ሀገር ለመላክ ከእርስዎ ምን ይጠበቃል

1.

የቁም እንስሳት ወደ ውጪ ለመላክ በቅድሚያ ምን ያስፈልጋል? ........................15

2. የቁም እንስሳት ማቆያ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልቷል የሚባለው መቼ ነው? ......... 15 3.

እንስሳት በኳራንቲን የቁጥጥር ስርአት ውስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል ሲባል ምን ማለት ነው?. 16

4.

እንስሳትን ወደ ማቆያ ከማስገባት በፊት ምን ያስፈልጋል? ..............................17

5. እንስሳት ወደ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ከተፈቀደ በኃላ ምን ይደረጋል ? ...................19 6.

በኳራንቲን የቆይታ ጊዜ እንስሳቱ የትኞቹን ክትባቶች ይከተባሉ? .........................

7.

ለየትኞቹ በሽታዎች የላብራቶሪ ምርመራ ይደረጋል? .................................. 20

8.

ከሒወት ደህንነት (Biosecurity) አንጻር በእንስሳት ማቆያ ውስጥ ምን ምን የጥንቃቄ ተግባራት ይከናወናሉ? ...........................................................17

9. የእንስሳት ጤና ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማግኘት የሚቻለው ምን ተሟልቶ ሲገኝ ነው? .........19 10. የእንስሳት ጤና ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የማይሰጠው ምን ሲያጋጥም ነው? ...............20

11. የኳራንቲን አገልግሎት እንዲቋረጥ ወይም እንዳይሰጥ የሚደረገው ምን ሲከሰት ነው? ...21


1

መግቢያ ሀገራችን ያላትን የእንስሳት ሃብት በመጠቀም የቁም እንስሳትና እንስሳት ተዋፆኦ በብዛትና በጥራት በአለም ገበያ ላይ ይዛ እንዲትቀርብ እና ተወዳዳሪ

እንድትሆን

ለማድረግ

የእንስሳት ልየታና ክትትል ሥርዓትን መከተል እና ተግባራዊ በማድረግም ሆነ የእንስሳት ደህንነትን መጠበቅ ወሳኝ ነው፡፡ የዓለም የእንስሳት የጤና ድርጅት የቁም እንስሳት ምዝገባና ልየታ ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ገዢ አገራት የሚጠይቁትን የቁም እንሰሳትና የእንስሳት ተዋፅኦ ንግድ መስፈርቶች ከማሟላት ባሻገር ሌሎች ፋይዳዎችም እንዳሉት ተጠቁሟል፡፡ የእንስሳት ልየታ ምዝገባ ቁጥጥርና ደህንነት ዳይሬክቶሬት የእንስሳት ልየታና ምዝገባ ስርዓት ተግባራዊ ለማድረግ በዘርፉ ለተሰማሩ የቁም እንስሳት ላኪዎች፣ ማህበራት፣ ነጋዴዎች፣ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች ስራ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት አጋዥ የሚሆን የአሰራር ሂደት መመሪያ ተዘጋጅቷል፡፡

የኳራንቲን አገልግሎት ማለት ከሀገራችን ወደ ውጪ ሀገራ በቁማቸው ለእርድ ለሚላኩ የዳልጋ ከብቶች፤ግመሎች፤ፍየሎች እና በጎች በተቀባይ ሀገራት እና በኢትዮጵያ የተቀመጡ መስፈርቶችን በሟሟላት ከሰውና ከሌሎች እንስሳት ንክኪ ተገልለው ጤንነታቸውንና ደህንነታቸውን በማረጋገጥ ከሀገር ለመውጣት ብቁ መሆናቸውን የሚገልጽ የእንስሳት ጤና ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የሚሰጥበት የአሰራር ስርዓት ነው፡፡በዚህም መሰረት ጤንነቱና ደህንነቱ የተረጋገጠ የቁም እንስሳት ወደ ተቀባይ ሀገራት በመላክ የተቀባይ ሀገራትን ፍላጎት በማሟላት በኳራንቲን የቁጥጥር ስርዓታችን እምነት እንዲኖራቸው በማድረግ ከዘርፉ የሀገር ተጠቃሚነትን ማሳደግ ነው፡፡


2

ዓላማ . የቁም እንስሳትን ወደ ውጭ ሀገራት ለሚልኩ እና አዳዲስ ወደ ስራው ለመግባት ፍላጎት ላላቸው ግለሰቦችና ድርጅቶች በቅድሚያ ማወቅ ስላለባቸው ጉዳዮች ጥርት ያለ መረጃ ማቅረብ ነው፡፡

ትርጉም

U ‘የቁም እንስሳት’ ማለት የዳልጋ ከብትን፤በግን፤ ፍየልን እና ግመልን ያካትታል U ‘የቁም እንስሳት ላኪ’ ማለት የቁም እንስሳትን ወደ ውጭ ገበያ ለመላክ በንግድ ሚ/ር ፈቃድ የተሰጠው ሰው ወይም ድርጅት ነው

U የእንስሳት መለያ’ ማለት የቁም እንስሳትን አንዱን ከአንዱ ለመለየት በጆሮ ላይ ወይም በሌላ የእንስሳው አመቺ የሰውነት ክፍል ላይ የሚቀመጥ የመለያ ቁጥር ነው

U ‘የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት’ ማለት የተቀመጠውን መስፈርት ያሟላና የቁም እንስሳትን በውስጡ ለመያዝ የሚያስችል የእንስሳት ማቆያ ላላቸው የቁም እንስሳት ላኪ የሚሰጥ ሰርተፍኬት ነው፡፡

U ‘ማዕከላዊ የመረጃ ቋት' ማለት የተደራጀ የኮምፒዩተር መረጃ ማስቀመጫ ያለውና ለእንስሳት ልየታና ምዝገባና ክትትል ሥርዓት የሚጠቅም መረጃ ነው

U ‘እንስሳት መለያ ቁጥር’ ማለት በብሔራዊ ደረጃ የታወቀና የተለየ የእንስሳት መለያ ቁጥር ፡ ሲሆን ለእንስሳ ወይም ለተሰበሰቡ እንስሳት በቋሚነት የሚሰጥ የእንስሳት መለያ ነው

U ‘የእንስሳት እንቅስቃሴ’ ማለት አንድ ወይም ከአንድ በላይ ቁጥር ያላቸው እንስሳትን ሁለት ወይም ከሁለት በላይ የተመዘገቡ ማቆያዎች ወይም ቦታዎች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ነው

U “የቦታ መለያ ቁጥር’ ማለት ብሔራዊ ስልጣን በተሰጠው አካል የተሰጠ በመረጃ ቋት ውስጥ የተመዘገበና የታወቀ ለእንስሳት መቆያ ወይም የቦታ ቁጥር ነው


3

1.

የእንስሳት ልየታ እና ምዝገባ ስርዓት የጆሮ መለያ አጠቃቀም የአሰራር

ሂደቶች ከ28 ነሀሴ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ በሁሉም የግብርና ሚኒስቴር ኳራንቲን ጣቢያዎች በኩል ክትትል የሚደረግላቸው የዳልጋ ከብቶች በሙሉ የኳራንቲን ኢንስፔክሽን እና ሰርተፊኬሽን አገልግሎቶችን ለማግኘት ሀገር አቀፍ የሆነውን የእንስሳት ልየታ ምዝገባ እና ክትትል ስርዓት የእንስሳት ጆሮ ላይ መለያ (ታግ) እንዲጠቀሙ መመሪያ ተላልፏል በዚህም መሰረት የታግ አጠቃቀም ስርዓት ከዚህ በታች እንደተጠቀሰው ይከናወናል፡፡ 1.1 የጆሮ መለያዎች ግዢ እና ስርጭት

የእንስሳት የጆሮ ላይ መለያዎችን ግዢ፣ ክፍፍል እና የእ/ል/ም/ክ/ደ/ጥበቃ ዳይሬክቶሬት በበላይነት የሚመራ ስሆን ለባለድርሻ አካላት የሚደረገውን የእንስሳት የጆሮ መለያ የስርጭት ሂደት በተዘጋጀው ማዕከላዊ የመረጃ ቋት አማካኝነት የሚከታተል ይሆናል:፡ የመረጃ ቋቱ የጆሮ ላይ መለያዎችን ኢምፖርት፣ ግዢ እና ክፍፍል ለኦዲት በሚያመች መልኩ ክትትል ያደርጋል፡፡

የእንስሳት ልየታ፣ ምዝገባ እና ክትትል ስራዎች ከመጀመራቸው በፊት የእ/ል/ም/ክ/ደ/ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ተገቢውን ስልጠና

በጆሮ መለያዎች አጠቃቀም፣ የእንስሳት ምዝገባ፣

የመረጃ ጥራት አጠባበቅ፣ እንዲሁም ተጓዳኝ ስራዎች ዙሪያ ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች፣ የእንስሳት ባለቤቶች እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ይሰጣል፡፡ በስርዓቱ ትገበራ ውስጥ

የሚሳተፉ

የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች መረጃዎችን ወደ መረጃ

ቋቱ

ያስገባሉ፡፡ ባለድርሻ አካላት አድላቢዎች፣ ኤክስፖርት ቄራዎች እና የቅድመ-ኳራንታይን ባለቤቶች


4

በከብቶቻቸው ሁለት ጆሮዎች ላይ ተመሳሳይ ቁጥር ያለውን የእንስሳት የጆሮ መለያ ገዝተው መጠቀም አለባቸው፤ በተጨማሪም እንስሳው በሚንቀሳቀስበት ወቅት ያለውን የይለፍ ፈቃድ ና አጠቃላይ መረጃ መያዝ አለባቸው ፡፡ የጆሮ መለያ ለባለድርሻ አካለት እንዲሸጥ የተፈቀደለት የኳራንታይን ቢሮ ከእንስሳት ልየታ ዋና ክፍል የሚሰጠውን የጆሮ መለያ በአካል በመገኘት ይረከባል የተረከበውን የጆሮ መለያ ብዛትና የተከታታይ ቁጥር በመረጃ ቋቱ ላይ ይመዘግባል፡፡

የታግ አጠቃቀም ጥራት አጠባበቅ እንዲሁም ተጓዳኝ ስራዎች ዙሪያ ለእንስሳት ጤና ባለሙያዎች፣ የእንስሳት ባለቤቶች እንዲሁም ለሚመለከታቸው አካላት በሙሉ ይሰጣል:፡ በስርዓቱ ትገበራ ውስጥ የሚሳተፉ የእንስሳት ጤና ባለሙያዎች መረጃዎችን ወደ መረጃ ቋቱ ያስገባሉ፡፡

1.1 ወደ ማሰራጫ ጣቢያዎች የሚደረግ የጆሮ ላይ መለያ ወጪ ሂደት የሚመለከተው የግብርና ሚኒስቴር ባለሙያ ከግብርና ሚኒስቴር ግምጃ ቤት የጆሮ መለያ ወጪ መጠየቂያ ያዘጋጃል:: አስፈላጊውን የእቃ ወጪ አሰራር ሂደት ተከትሎ የእንስሳት ልየታ ምዝገባ ደህንነትና ጥበቃ ዳይሬክቶሬት ፍቃድ ሲያገኝ የጆሮ መለያዎች ከግብርና ሚኒስቴር ግምጃ ቤት (ስቶር) ወጪ ይደረጋል:: የጆሮ መለያዎች በማሰራጫ ጣቢያዎች (ለምሳሌ፡- አዳማ ኳራንቲን ጣቢያ፣ ጅግጅጋ፣ ድሬዳዋ…) ግምጃ ቤት (እስቶር) ለተጠቃሚዎች ስርጭት ተዘጋጅተው ይቀመጣሉ::


5

1.2 1. 2 የእንስሳት ባለቤት ከማሰራጫ ጣቢያዎች የጆሮ መለያን የሚገዛበት ሂደት የእንስሳቱ ባለቤት በበረቱ ውስጥ እንስሳትን ለማስገባት ሲያቅድ በኳራንቲን ጣቢያዎች በመገኘት የጆሮ መለያ ግዥ በደብዳቤ ይጠይቃል የእንስሳቱ ባለቤት በኳራንቲን ጣቢያዎች የጆሮ መለያ ክፍያ በካሽ ወይም በኳራንቲን ቢሮ በኩል በሚሰጥ የግብርና ሚኒሰቴር የገንዘብ ማስገቢያ አካውንት አማካኝነት ክፍያ ይፈፀማል በሚቀርበው የባንክ ደረሰኝ መሰረት በእንስሳት ልየታ ምዝገባ እና ክትትል የጆሮ መለያ ወጪ ሰነድ እና ዳታቤዝ ላይ አስፈላጊው ማመሳከርና ምዝገባ ተካሂዶ የጆሮ መለያዎች ለእንስሳት ባለቤቶች ይሰጣሉ የእንስሳት ባለቤቶች የጆሮ መለያውን ይዘው ወደ እንስሳት ማቆያዎቻቸው (በረቶቻቸው) በመሄድ በኳራንቲን ባለሙያዎች ክትትል ስር ሆነው የመለየት ስራ ይሰራሉ እያንዳንዱ የሚለይ (የጆሮ መለያ የሚደረግለት) እንስሳ መሰረታዊ መረጃ በወረቀት በተዘጋጀ የመረጃ መያዣ ሰነድ ላይ በጥንቃቄ ይመዘገባል በተዘጋጀው የመረጃ መያዣ ሰነድ መሰረት በእንስሳው ባለቤት ወይም በኳራንቲን ጣቢያ ባለሙያ አማካኝነት የእያንዳንዱ የተለየ (የጆሮ መለያ የተደረገለት) እንስሳ መሰረታዊ መረጃ በዳታቤዝ ላይ ይመዘገባል የተመዘገበውን መረጃ በባለሀብቱ አማካኝነት ከሆን የመረጃውን ትክክለኛነት ማለትም በመረጃ ቋት ውስጥ እና በበረት ላይ ያለውን መረጃ ተመሳሳይነት የኳራንቲን ባለሙያዎች በኢንስፔክሽን ያረጋግጣሉ በዳታቤዝ (መረጃ ቋት) ላይ የተመዘገበዉ መረጃ በተፈለገው መልኩ መያዙን የእንስሳት ልየታ እና ምዝገባ ባለሙያዎች ይከታተላሉ ትብብር


6

ሲያስፈልግም አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡ የእንስሳት ልየታ እና ምዝገባ ባለሙያዎች በየሳምንቱ መጨረሻ በወረቀት የተያዘውን እና በመረጃ ቋት ላይ የተመዘገበውን የእንስሳት የጆሮ ላይ መለያ መረጃ ያመሳክራሉ ሪፖርትም ለሚመለከተው የበላይ አካል ያቀርባሉ::

2. የኢትዮጲያ ብሄራዊ የእንስሳት የጆሮ ላይ መለያ አጠቃቀም 2.1 መለያዎችን በጆሮ ላይ የማስቀመጥ ቅድመ ሁኔታዎች የአዝራር አይነት መለያው በግራ ጆሮ የባንዲራ አይነት የአስተዳደር መለያው በቀኝ ጆሮ ይቀመጣል። መለያ በማድረግ ሂደት ውስጥ ለኢንፌክሽን የመጋለጥ አደጋን ለመቀነስ ተገቢው ንፅህና መጠበቅ አለበት፡፡ የታግ መምቻውን ጫፎች እና ታግ የሚደረግለትን ጆሮ አካል በአልኮል ወይም በንፅህና መጠበቂያ በሚገባ ያፅዱ፡፡ ከታች በምስሉ ላይ እንደሚታየው የጆሮ መለያዎችን በአፕሊኬተሩ ላይ በሚገባ ያስቀምጡ፡፡ እንስሳት ከተለዩ በኋላ በተገቢው መንገድ ጤንነታቸው ተጠብቆ እንዲቆይ መደረግ አለበት፡፡ መለያ በተደረገበት የጆሮ ክፍል ላይ ሀይድሮጅን ፐርኦክሰሳይድ ለተከታታይ ከ5-7 ቀን መጠቀም እንስሳቱ ለኢንፌክሽን እንዳይጋለጡ ይረዳል፡፡ ለተጨማሪ እርዳታ በአካባቢው የሚገኘውን የእንስሳት ሀኪም ያማክሩ፡፡


7

ቴ ክፍል ሴ የ ፡ 2 ል ስ ም

1 ስል

ወን

ክፍ


8

3 ስል

የኢ

ጵ ትዮ

ን የእ

ያ ለ መ

ሳት

ጆሮ

ላይ


9

2.2. የጆሮ መለያ አቀማመጥ ሂደት 1.

2.

3.

መለያዎችን በጆሮዎች ላይ ከማድረግ በፊት በአፕሊኬተሩ ላይ ተመሳሳይ የመለያ ቁጥር በወንዴ እና ሴቴ ክፍሎቹ ላይ መቀመጡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል እንስሳውን በተገቢው ሁኔታ ከእንቅስቃሴ መገደቡን ማረጋጥ በእንስሳው እና መለያውን በሚያደረገው ባለሙያ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ይረዳል ከእንስሳው ጭንቅላት ወደ ጆሮው ጫፍ አንድ ሶስተኛ እንዲሁም ከእንስሳው የጆሮው ጫፍ ወደ እንስሳው ጭንቅላት ሁለት ሶስተኛ እርቀት ላይ በትክክል መቀመጡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል::

ምስል 2፡ ትክክለኛ የጆሮ ላይ መለያ አቀማመጥ

4. 5.

6.

7.

8.

የጆሮ መለያዎችን በተገቢው ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ማፅዳት መለያዎቹ በጆሮዎች ላይ ከመቀመጣቸው በፊት በትክክል በአፕሊኬተሩ ቀዳዳዎች ላይ መግባት መቻላቸውን በሙከራ ማርጋገጥ ያስፈልጋል አፕሊኬተሩን በታለመለት የጆሮ ክፍል ላይ አስተካክሎ በመምታት በፍጥነት መልቀቅ መለያው በጆሮ ላይ በሚመታበት ጊዜ ባለሙያው የክሊክ ድምፅ መስማቱን ማረጋገጥ አለበት መለያው በጆሮ ላይ ከተቀመጠ በኋላ በማዟዟር እና በማንቀሳቀስ በትክክል፣ ጆሮን ባልጎዳ መልኩ ጠብቆ መቀመጡን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡


10

ምስል 3፡ የጆሮ መለያዎች በእንስሳት ላይ የማስቀመጥ ሂደት

ማሳሰቢያ- የጆሮ መለያ ከእንስሳው ጆሮ ጋር በቀላሉ እና በፍጥነት መያያዝ ማሳሰቢያ መቻል አለባቸው አንድን የጆሮ መለያ ጆሮ

ላይ ለማስገባት ከ 20 ሰከንድ በላይ

መፍጀት የለበትም ፡፡ አብዛኛው የጆሮ መለያ ለኪሳራ የሚዳረገው በተገቢ መንገድ ባለመደረጉ ነው፡፡ በተጨማሪም የእንሰሳት ተንከባካቢዎችን ደህንነት የጆሮ መለያዎችን ዲዛይን መምረጥ ላይ ከግምት ውስጥ ማስግባት አለበት:: የጆሮ መለያዎች ከተበላሹ ወይም ከአገልግሎት ውጪ ከሆኑ ከዳታቤዝ ውስጥ መወገድ እና እንደገና ምትክ እንዲሰጣቸው ወደ ETLITS ክፍል መጠየቅ አለበት:፡


11

2.3. የጆሮ መለያ መተካት የተመዘገበ የጆሮ መለያ ከጠፋ (በአንድ ጆሮ ላይ የተቀመጠው)፣ ባለድርሻ አካላት ወዲያውኑ ለ LITS የመረጃ ቋት አስተዳዳሪ (ወይም ለኳረንቲን)

በአካል በመገኘት

እንደጠፋባቸው ማሳወቅ አለባቸው በምትኩም እንደበፊቱ በማርከር የተፃፈ ተመሳሳይ ቁጥር ያለው የጆሮ መለያ እና እንደተተካ የሚያመለክት ፊደል “R” የያዘ ተለዋጭ የጆሮ መለያ ማግኘት አለባቸው ፡፡

3. የእንስሳት ልየታ እና ምዝገባ የመረጃ ቋት ስርዓት የኢትዮጲያ የእንስሳት ልየታ እና ምዝገባ ስርዓት በዘመናዊ የመረጃ ቋት የተደገፈ የእንስሳትን ታሪክ፣ ለእንስሳቱ ተጠያቂ የሆኑ ሰዎችን፣ ተቋማትን፣ የማቆያ ስፍራዎችን፣ የእንስሳት እንቅስቃሴዎችን እና ሌሎች መዝገቦችን ከእንስሳ መለያ ጋር በማካተት እና በማገናኘት ለይቶ ለማወቅ እና እንስሳ ወይም የእንስሳት ቡድንን ለመከታተል የሚያስችል ነው፡፡

3.1 የማዕከላዊ የመረጃ ቋት የእንስሳት ልየታ ምዝገባ ስርዓት መረጃ ቋት የሚከተሉትን መረጃዎች ለመያዝ ያስችላል የእንስሳት ማቆያ ድርጅቶችን/ ስፍራዎችን የእንስሳት ጠባቂዎችን እና ሌሎች ሰዎችን፣ የእንሰሳት መለያዎችን ስርጭት፣ በስርዓቱ መለያ የተሰጣቸውን እንስሳት፣ የተመዘገቡና የተለዩ እንስሳትን የጉዞ እንቅስቃሴ፣ የእንስሳቱን ጤንነት እና ሌሎች አጋጣሚዎችን የሚመለከት መረጃ፣


12

3.2 የእንስሳት ማቆያ ስፍራ ምዝገባ ማናቸውም እንስሳትን ለማቆያነት የሚያገለግሉ በረቶች፣ የእንስሳቱ ናሙና ወይም ቅሪተ አካል ምርመራ ማድረጊያ ስፍራዎች በተዘጋጀው የስፍራ ምዝገባ ሰነድ መሰረት ወደ መረጃ ቋት ውስጥ ከዚህ የሚከተሉትን መረጃዎች በመያዝ መስፈር አለባቸው ሀ. እንስሳቱን የሚይዘው ሰው ስም፣የመኖሪያ፣የፖስታ ሣጥን አድራሻ ዝርዝር ለ. እንስሳቱ የሚቆዩበት ቦታ ስም፣አድራሻ፣የፖስታ ሣጥን አድራሻ እና የመገኛ ዝርዝር ሐ. እንስሳቱ የሚቆዩበት ስፍራ የስነ ምኅዳር ማመላከቻዎች (ጂኦኮድ)፣ መ. የማምረቻ ዓይነቶች(የእርባታ ዘዴ)፣ የተመዘገቡ እንስሳትን የሚይዝ ሰው እንስሳቱን በተመዘገቡ ማቆያዎች ዉስጥ ሊያስገባ ካዘጋጀበት ቀን ጀምሮ ለሚመለከተው የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያ ማሳወቅ አለበት፣ የተመዘገቡ እንስሳትን ከአንድ በበለጠ ስፍራ የያዘ ሰው በተናጠል እንስሳቱን በየማቆያ

ስፍራቸው ለፌደራል የእንስሳት ኳራንቲን ጣቢያ ማሳወቅ አለበት

የኳራንቲን እንስሳት ጤና ባለሙያው አስፈላጊው መረጃ ከተሰበሰበ በኋላ የእንስሳቱን ማቆያ ስፍራ መረጃ ወደ ማዕከላዊ የመረጃ ቋት ውስጥ እንዲመዘገብ ያደርጋል እንዲሁም እንስሳቱ የተቀመጡበት ስፍራ መለያ ኮድ መሰጠቱንም ያረጋግጣል፣


13

የተመዘገበ እንስሳ ባለቤት የእንስሳ ማቆያ ስፍራ መለያ ኮድ ከወሰደ በኋላየሚደረግ የመረጃ ለውጥ ካለ ለኳራንቲን እንስሳት ጤና ባለሙያው በ3 ቀን ውስጥ ማሳወቅ አለበት፣

• ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በየጊዜው ከህዝብ ክንፍ ጋር በመሆን አመቺ የልየታ፣ ምዝገባና ክትትል አሰራ አሰራር ር ስነ ስርዓት ያዘጋጃል፣ ይመክራል እንደ አስፈላጊነቱም ማሻሻያ ያደርጋል፣ ያደርጋል ፣ • የማዕከላዊ የመረጃ ቋት አሰተዳዳሪ ሆኖ የሚሰራው የመንግስት ተቀጣሪ የሆነ የእንስሳት ሐኪም ነው፡፡ በስራውም ማንኛውንም የእንስሳት ልየታ እና ክትትል እንቅስቃሴዎች በየጊዜው ይመዘግባል • የመረጃ ቋት አስተዳዳሪው ማንኛውንም መረጃ የመለያ ዘዴዎችንና ግንኙነቶች ሁኔታዎችን በማገናዘብ መረጃዎችን ለተፈቀደላቸው ተጠቃሚዎች ተደራሸ ያደርጋል እነዚህም መረጃዎች፡ለእንስሳቱ የማጓጓዣ ፈቃድ ለመጠየቅ እና ለመፍቀድ፣ የእንስሳቱን ጉዞ ለማሳወቅ፣ የተፈቀደላቸው የመረጃ ተጠቃሚች በየጊዜው ለመከታተል እንዲችሉ ማስቻል፣ በእንስሳት ማቆያ ድርጅቶች ውስጥ የሚገኙ እንስሳት ያጋጠሟቸውን የእንስሳት ጤና ጉዳዮች ሪፖርት ለማድረግ፣ አለም አቀፍ የእንስሳት ጤና መረጃ ልውውጥ ማድረግ፣


14

የኳራንቲን ኢምፖርት ኤክስፖርት ኢንስፔክሽንና ኢንስፔክ ሽንና ሰርተፍኬሽን ዳይሬክቶሬት

የቁም እንስሳትን ወደ ውጪ ሀገር ለመላክ ከእርስዎ ምን ይጠበቃል ???


15

v

የቁም እንስሳት ወደ ውጪ ለመላክ በቅድሚያ ምን ያስፈልጋል ?

1. በግብርና ሚ/ር የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟላ የቁም እንስሳት ማቆያ 2. የታደሰ የቁም እንስሳት ላኪነት የንግድ ፍቃድ 3. እንስሳቱ በኳራንቲን የቁጥጥር ስርዓት ውስጥ እንደሚያልፉ ማወቅ 4. የቁም እንስሳት መላክ እንዲችሉ ሀገር ውስጥ ከሚገኝ ባንክ የተሰጠ የባንክ ፐርሚት 5. የተቀጠረ ግል ባለሙያ ያለው በእንስሳት ሀኪም ወይም ረዳት የእንስሳት (ዲቪም ዲግሪ ወይም ቢኤሲሲ) እውቅና ካለው የትምህርት ተቋም የተመረቀ

የቁም እንስሳት ማቆያ የተቀመጠውን መስፈርት አሟልቷል የሚባለው መቼ ነው? የእንስሳት ማቆያው ዙሪያው በግንብ የታጠረ ከሆነ የእንስሳት መመገብያ፤መጠጫ፤ የታመሙ ቦታ እና የበድን ማቃጠያ ካለው የታመሙ እንስሳት ማግለያ ከመመገቢያና መጠጫ ጭምር ያለው ከሆነ በአግባቡ የተሰራ የመኖ መጋዘን ሲኖረው የእንስሳቱ መመገቢያውን እና መጠጫውን ከፀሐይ ከዝናብ የሚከልል እንዲሁም እንስሳቱ የሚጠለሉበት ጥላ ያለው ከሆነ የተደራጀ መረጃ ለመያዝ የሚያስችል ቢሮ ሲኖረው የሰራተኞች ልብስ መቀየሪያ፤መጸዳጃ፤ገላ መታጠቢያ እና መመገቢያ ክፍሎች ካለው የእንስሶችን ጤንነት የሚከታተል የእንስሳት ሀኪም ወይም ረዳት ሀኪም ካለው የህክምና መገልገያዎች እና መድሀኒቶች የያዘ የእንስሳት ክሊኒክ ያለው ሲሆን በመግቢ በሮች ላይ የመኪና ጎማ እና የእግር መንከሪያ የተዘጋጀለት ከሆነ


16

እንስሳት እንስ ሳት በኳራንቲን የቁጥጥር ስርዓት ውስጥ እንዲያልፉ ይደረጋል ሲባል ምን ማለት ነው? ማንኛውም የቁም እንስሳት ላኪ ግለሰብ ወይም ድርጅት እንስሳቱን ወደ ውጪ ሀገር ከመላኩ በፊት በአቅራቢያው ለሚገኝ የኳራንቲን ጣቢያ ለእንስሳቱ የኳራንቲን አገልግሎት እንዲሠጥለት ጥያቄውን በማመልከቻ ያቀርባል፡፡ ማመልከቻው ተቀባይነት ካገኘ የዳልጋ ከብቶችና ግመሎች ለተከታታይ 30 ቀናት የኳራንቲን ቆይታ ጊዜ ሲኖራቸው፤ የበግና የፍየል የኳራንቲን የቆይታ ጊዜ ደግሞ 21 ቀናት ይሆናል፡፡በተቀመጠው የኳራንቲን የቆይታ ጊዜያት የኳራንቲን ጣቢያው ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተግባራት በማከናወን የእንስሳቱ ጤንነትና ደህንነት የተጠበቀ እንዲሆን ያደርጋል፡፡በዚህ ወቅት አገልግሎት ጠያቂው ድርጅት የተቀመጡትን ተግባራት በአግባቡ እንዲከናወኑ የመተባበር ግዴታ ይኖርበታል፡፡ 1ኛ. እንስሳትን ወደ ማቆያ ከማስገባት በፊት የሚከተሉት ይተገበራሉ? 8 የእንስሳት ማቆያውን በአግባቡ ማስተካከል 8 በቂ የመጠጥ ውሀ እና መኖ ማዘጋጀት 8 ስልጠና የወሰዱ የእንስሳት ተንከባካቢዎች ማዘጋጀት 8 የእንስሳት ማቆያው እንዲታይለትና እንስሳት የማስገቢያ ፈቃድ ለማግኘት በአቅራቢው ለሚገኝ የኳራንቲን ጣብያ ማመልከቻ ማቅረብ


17

2ኛ. እንስሳት ወደ ማቆያ ውስጥ እንዲገቡ ከተፈቀደ በኃላ የሚከተሉት ክትባቶች እንዲሰጡ ይደረጋል። በተገቢ መጓጓዣ ተጓጉዘው ከመጡት እንስሳት ውስጥ ብቁ የሆኑትን እየለዩ ወደ ማቆያ ማስገባት ከኳራንቲን ጣቢያው የተገዛውን የጆሮ መለያ በአግባቡ በእንስሳቱ ላይ ማድረግ በመንገድ ላይ እያሉ ጉዳት ያጋጠማቸውን እንስሳት ለብቻ ለይቶ ማከምና መመገብ የውጪና የውስጥ ጥገኛ ተዋህሲያንን ለማጥፋት የሚረዳ ሕክምና መስጠት እንስሳቱ በምግብ ለውጥ የተነሳ ህመም እንዳያጋጥማቸው ለመጀመሪዎቹ ሶስት ቀናት ደረቅ ሳር/ገለባ ብቻ በመስጠት በሚቀጥሉት ቀናት ግን ተደባልቆ የተዘጋጀውን ምጥን በትንሽ በትንሹ ብዛቱን እየጨመሩ መመገብ የኢትዮጵያን እና የተቀባይ ሀገራትን መስፈርት መሰረት ያደረገ ክትባቶችን መከተብ እና የላብራቶሪ ምርመራ ተካሂዶ በምርመራው ነጻ የሆኑት እንዲለዩ ይደረጋል፡፡ አካላዊ ክብደታቸው የሚለያዩ እንስሳትን እንደመጠናቸው ለያይቶ መመገብ 

ተላላፊ/ተዛማች የእንስሳት በሽታ ቢከሰት ባፋጣኝ የታመመውን እንስሳ ከሌሎቹ በመለየት ማከም ወይም ማስወገድ እንዲሁም ለሚመለከተው አካል ማሳወቅ 3ኛ. በኳራንቲን የቆይታ ጊዜ እንስሳቱ ክትባቶች ይከተባሉ? የዳልጋ ከብቶች

ፍየሎችና በጎች

ግ መሎች

1. አባ ጎርባ (Black Leg

1. የበጎች ጎሮርሳ (Ovine Pasteruollosis)

1. አባሰንጋ (Anthrax)

2. አባሰንጋ (Anthrax)

2. ተላላፊ የፍየሎች ሳምባ በሽታ (CCPP)

2. የግመል ፈንጣጣ (Camel Pox)

3. የአፍ ተግር በሽታ (FMD)

3. የበጎችና ፍየሎች ፈንጣጣ (Pox)

4. ጎሮርሳ (Pasteruollosis)

4. የበጎችና ፍየሎች ደስታ መሰል በሽታ (PPR

5. ጉርብርብ (Lumpy skin disease) 6. ተላላፊ የከብት ሳምባ በሽታ(CBPP)


18

4ኛ. ለየትኞቹ በሽታዎች የላብራቶሪ ምርመራ ይደረጋል? ለእንስሳቱ የሚደረጉ የላብራሪ ምርመራ አይነቶች የተቀባይ ሀገራትን ጥያቄ መሰረት አድርጎ የሚወሰን ይሆናል፡፡ 5ኛ. ከሒወት ደህንነት (Biosecurity) አንጻር ምን ምን ጥንቃቄ ይደረጋል? የእንስሳት ማቆያው አጥር እንስሳትና አራዊቶችን የማያሳልፍ (የማያሾልክ) መሆኑን ማረጋገጥ የሰውና ተሽከርካሪ መግቢያ በር ላይ ፀራ ተዋሲያን ኬሚካል የተጨመረበት ውሃ ሁል ጊዜ መኖሩን ማረጋገጥ ወደ ማቆያ ውስጥ የሚገባ ማንኛውም ሰው ተገቢውን ቅድመ ጥንቃቄ አድርጎ እንዲገባና ከእንስሳቱ ጋር ንክኪ እንዳይኖረው ማድረግ እያንዳንዱ፤ የበረት ሰራተኛ ከተመደበበት የስራ ቦታ ውጭ እንቅስቃሴ እንዳያደርግ መገደብ የተለያዩ የእንስሳት ዓይነቶችን በማቆያ ውስጥ በአንድ ላይ አለማስቀመጥ፤ ጤነኛና የታመሙ እንስሳት በረት ውስጥ አንድ ላይ አለመቀላቀል፤ የእንስሳት ማቆያውን በየጊዜው በመከታተል ማጽዳት የውሃ መጠጫና መመገቢያ ገንዳዎችን ሲቆሽሹ ማጽዳት ለተለያዩ ህክምና እና ለክትባት አገልግሎት የሚውሉ ቁሳቁሶችን በየጊዜው ማጽዳት የመጀመሪያው ሁር የገቡት እንስሳት ተጠቃለው ከወጡ በኋላ አዲስ እንስሳት ከመግባታቸው በፊት ማቆያው በደንብ መጽዳት ይኖርበታል፡፡


19

6ኛ. የእንስሳት ጤና ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማግኘት የሚሰጠው ምን ተሟልቶ ሲገኙ ነው? እንስሳቱ በኳራንቲን የቁጥጥር ስርአት ውስጥ ያለፉና የኳራንቲን የቆይታ ጊዜያቸውን መጨረሳቸው ሲረጋገጥ፡፡ በኳራንቲን ቆይታቸው ወቅት ከተቀባይ ሀገሮች ጋር ስምምነት የተደረሰባቸውን መስፈርቶች መሰረት ያደረገ ህክምና እና ክትባቶች መውሰዳቸው እንዲሁም የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ከበሽታ ነጻ መሆናቸው ሲረጋገጥ፡፡ እንስሳቱን በተመለከተ ያሉ መረጃዎች ማለትም የወሰዱት መድኃኒት (ህክምና) ፣ክትባትና ምርመራ በሚገባ መመዝገቡና ወደ መረጃ ቋት መግባቱ ሲረጋገጥ፡፡ እንስሳቱ ከእንስሳትና እንስሳት ተረፈ ምርት የተቀነባበረ መኖ ወይም እድገትን የሚያፋጥን ሆርሞን ያልተመገቡ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ እንስሳቱ የጆሮ መለያ የተደረገላቸውና በኳራንቲን ቆይታቸው ወቅት ከሌሎች እንስሳት ጋር ያልተነካኩ መሆናቸው ሲረጋገጥ፣ ከኳራንቲን ጣቢያዎች ወደ መውጫ በሮች ( port of exit) የሚደረገው የእንስሳት ጉዞ ጫናን በማይፈጥርና የመጓጓዣ መኪናዎችም ደረጃቸውን የጠበቁ መሆኑ ሲረጋገጥ፣ እንስሳቱ ወደ ውጪ ከመጫናቸው በፊት ባለው 24 ሰአት ውስጥ ለጉዞው ብቁና ጤናማ መሆናቸው በኢንስፔክሽን ሲረጋገጥ ለጭነት ብቁ ያልሆኑና ጤንነታቸው ያልተሟላ እንስሳት ኤክስፖት አለመደረጋቸውንና እስኪያገግሙ ድረስ በተለየ ሁኔታ በእንክብካቤ እንዲያዙ መደረጉ ሲረጋገጥ፡፡ የእያንዳንዱ እንስሳ ክብደት 320 ኪ.ግ እና ከዛ በላይ መሆኑ ሲረጋገጥ የሰውነት የይዞታ መስፈሪያ (Body mass index) 3 እና ከ 3 በላይ መሆኑ ሲረጋገጥ


20

7ኛ. የእንስሳት ጤና ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የማይሠጠው ምን ሲከሰት ነው ? የእንስሳው ክብደት ከ 320 ኪ.ግ በታች ከሆነ እንስሳው የከሳ፤የንቃት ማነስ ያለበት፤የምግብ ፍላጎት የሌለው ወይም የምግብ ፍላጎቱ የቀነሰ ከሆነ 

እንስሳው የሚያነክስ ከሆነ፣እብጠትና ቁስል ካለው፣የተቅማጥ እና የሆድ መነፋት ምልክት ካለው

በአፍ፣በአይንና በአፍንጫ አካባቢ በብዛት ፈሳሽ የሚፈሰው ወይም የአፍና አፍንጫ አካባቢ መድረቅና ትኩሳት ከታየበት

እንስሳው ያልተለመደ ባህርይ ካሳየ፣የቆዳ በሽታ ካለበት፤አንዱ ወይም ሁለቱም አይኑ የጠፋ ከሆነ

እንስሳው የሳል፣የትንፋሽ መቆራረጥ ወይም የአተነፋፈስ መዛባት ከታየበት

እንስሳው በኳራንቲን የቁጥጥር ስርአት ውስጥ ያለፈ ካልሆነ

እየተሰጠ የነበረ የኳራንቲን አገልግሎት እንዲቋረጥ ከተደረገ

እንስሳቱ ወደ ውጭ ሀገር ሊላኩ በተቃረቡበት ወቅት የበሽታ ፍንዳታ መከሰቱ ከተረጋገጠ


21

እየተሰጠ የነበረ የኳራንቲን አገልግሎት እንዲቋረጥ ወይም እንዲከለከል የሚደረገው ምን ሲከሰት ነው? ከኳራንቲን ጣቢው ፈቃድ ሳያገኝ እንስሳትን ወደ ማቆያው የሚያስገባ ግለሰብ ወይም ድርጅት ሲኖር 

እንስሳቱ ተቆጥረው ፤ ተመዝግበው ፤የጆሮ መለያ ከተደረገላቸው እና ክትባት ከጀመሩ በኃላ ተጨማሪ አዲስ እንስሳ በማቆያ ውስጥ ተደባልቆ ከተገኘ የእንስሳት ማቆያው በነበረበት ደረጃ ላይ አለመሆኑ ታውቆ፤ድርጅቱ እንዲያስተካክል ተነግሮት በአፋጣኝ ማስተካከያ የማያደርግ ከሆነ እንስሳት የጆሮ መላያቸውን ጥለው በምትኩ ሳይደረግላቸው ቀርቶ የጆሮ መለያ ቁጥር ያሌለው እንስሳ በማቆያው ውስጥ ከተገኘ የበሽታ ፍንዳታ በማቆያው ውስጥ የተከሰተ መሆኑ ከተረጋገጠ ድርጅቱ በማቆያው ውስጥ የሚሰሩ ስራዎችንና የሚያጋጥሙ ክስተቶችን መዝግቦ የማያስቀምጥ እና ለኳራንቲን ጣቢያው ሪፖርት የማያቀርብ ከሆነ ድርጅቱ እንዲያስተካክል ለሚጠየቀው ጥያቄ ተባባሪ የማይሆን ከሆነ ድርጅቱ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የሆነ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ ለኳራንቲን ጣቢያው ሳያሳውቅ እንስሳቱን ወደ ሌላ ቦታ ካዛወረ፤ቀንሶ ከሸጠ፤የሞቱ እንስሳትን ሪፖርት ካላደረገ፡የበሽታ ፍንዳታ መከሰቱን በቶሎ ካላሳወቀ ወይም ሌሎች መሰል ተግባራትን ፈጽሞ ከተገኘ






Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Issuu converts static files into: digital portfolios, online yearbooks, online catalogs, digital photo albums and more. Sign up and create your flipbook.