Skip to main content

ጓዳዊ ድጋፍ፣ እርጉዝ ሆነሽ ከኤች አይ ቪ ጋር ለምትኖሪ (AM)

Page 1

ድጋፍ:ከኤች አይ ቪ ( HI V)ጋር ለምትኖር እርጉዝ ሴት

pos i t hi vagr uppen. s e/ 3p


ከእርግዝና በፊት፣በእርግዝና ወቅትና ከእርግዝና በኋላ ከኤች አይ ቪ ጋር ለምትኖሩና ድጋፍ ለምትፈልጉ3ፒ( Pos i t i v ePr egnanc yPeer s ) ለናንተ አለላችሁ።እናንተ ያለፋችሁበትንና የምትኖሩትን ህይወት ከሚ ጋሩ ደጋፊዎች ጋር ተገናኙ።

ስዊድንውስጥ ከኤች አይ ቪ ጋር እየ ኖርሽ ባለሽበት ግዜ፣የ መውለድ ጉዳይ እ ንዴት እ ንደሚስተናገ ድ ማወቅ ትፈልጊያለሽ?ከእርግዝናበፊት ወይም ከወሊድ በኋላ ትረበሺያለሽን? የ ኤች አይ ቪ ዲያግኖስንበማስተናገ ድ በኩል ድጋፍ ትፈልጊያለሽ፣ማለትም የ ህክምናአገ ልግሎቱ እ ንዴት እ ንደሚሰራናምንመብቶች እ ንዳሉሽ ማወቅ ትሺያለሽ?እ ንዳንቺው ከኤች አይ ቪ ጋር የ ምትኖርናአርግዛ ከወለደች ሰው ጋር የ ማውጋትና የ መዋየ ት ፍላጎ ት ይኖርሽ ይሆን? እንግዲያውስ3Pአለልሽ። እነ ማን ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ? ለማርገ ዝ እቅድ ያላቸው፣ወይም በቅርብ ልጅ የ ወለዱናከኤች አይ ቪ ጋር የ ሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የ ስሪ ፒን( 3P)ድጋፍ መጠያቅ ከፈለጉ በደስታ ኣ ንቀበላቸዋለን። ድጋፍ የሚ ሰጡ ትስ እነ ማን ናችው ? ድጋፍ ሰጪ ሰዎቹ በሙ ሉ ከኤች አይ ቪ ጋር የ ሚኖሩ፣እርግዝናእና ልጅ መውለድንም በራሳቸው ኑሮ ያሳለፉናየ ሚያውቁ ናቸው። በተጨማሪሁሉም የ ጓዳዊድጋፍ ( peer s t öd)አሰጣጥ መሠረታዊ ሥልጠናየ ወሰዱ ናቸው።


አሰራሩ እንዴት ነ ው? ያንቺን ግላዊ ፍላጎ ት ካወቅን በኋላ፣ከፍላጎ ትሽ በመነ ሳት አ ንቺን ልትረዳሽ ከምትችል ሰው ጋር እናገ ናኝሻለን።ድጋፍ ሰጪ ሴቶቹ የ ተለያየዕድሜ ያላቸው፣ከተለየ ዩ ሃገ ራት የ መጡናብዙ የ ተለያዩ ቋንቋዎች የ ሚናገ ሩ ሰዎች ናቸው። ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞቻችን በአካል በመገ ናኘትም እ ንዲሁም በዲጅታል ዘመናይ መገ ናኛ ዘዴም አገ ልግሎት ይሰጣሉ።ለምሳሌ ያህል፣የ ሃኪም ቀጥሮ በሚኖርሽ ግዜ፣ያንቺ ፍላጎ ት ከሆነ ፣አብራሽ ካንቺ ጋር ወደ ሃኪም ልትሄድ ሁላ ትችላለች። ድጋፍ ሰጪ ሴቶቹ ሚስጥር የ መጠበቅ ግዴታ አለባቸው፣ስለሆነ ም ስላንቺ ጉዳይ የ ሰሙ ትን ሆነየ ሚያውቁትን ለማንም ሰው አያወሩም።

ድጋፍ ያስፈልግሻል? •0775–668333ደውዪና“ 1”ቁጥርን ተጫኚ።አብዛኛውን ግዜ በአዘቦት ቀን ከ09. 00–15. 00ባለው ግዜ ውስጥ ስልክ እንመልሳለን። •አልያም በሚከተለው ኢሜል3p@posi t hi v agr uppen. seመልዕክት ላኪ። •በቀኝ በኩል ያለውንQRkodስካን ማድረግም ይቻላል፣ ወይም ደግሞ የ ሚከተለው ድረገ ጽ ላይ የ ሚገ ኝውን ድጋፍ መጠየ ቂያ ቅጽ መሙ ላት ይቻላል። posi t hi v agr uppen. se/ 3pamar i nj a

ስለ3Pእና ኤች አይ ቪ ፖዚቲቭ እድር( Pos i t hi v aGr uppen) ስሪፒ( 3P–Pos i t i v ePr e gna nc yPe e r s )የ ኤች አይ ቪ ፖዚቲቭ ሰዎች እድር ሲሆን ከ” Al l mä nnaa r v s f onden”በሚገ ኝገ ንዘብ የ ሚተዳደር የ ጓዳዊድጋፍ ፕሮጀክት ነ ው።ይህ የ ኤች አይ ቪ ፖዚቲቭ እድር በስዊድን ካሉ የ ህሙ ማን አደረጃጀቶች ሁሉ ከኤች አይ ቪ ጋር ለሚኖሩ ሰዎች ታላቁ ነ ው።


የ ምስል ቅንብር: -Ha nnaBöhm


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
ጓዳዊ ድጋፍ፣ እርጉዝ ሆነሽ ከኤች አይ ቪ ጋር ለምትኖሪ (AM) by Posithiva Gruppen - Issuu