Skip to main content

Amharic - Stars in Scriptures (Stellar Astronomy)

Page 1

በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ያሉ ኮከቦች የጣቶችህን ሥራ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን ሰማያትህን ሳስብ፤ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድን ነው? የሰው ልጅስ ትጎበኘው ዘንድ ምንድር ነው? መዝሙረ ዳዊት 8:3-4

ፔንታቱች እግዚአብሔርም ሁለት ታላላቅ ብርሃናትን ፈጠረ፤ ትልቁ ብርሃን በቀን እንዲገዛ፥ ትንሹም ብርሃን በሌሊት እንዲገዛ፤ ከዋክብትንም ደግሞ ፈጠረ። ዘፍጥረት 1:16 ወደ ውጭም አወጣውና። ወደ ሰማይ ተመልከት፥ ከዋክብትንም ልትቆጥራቸው ትችል እንደ ሆነ ንገራቸው አለው። እርሱም። ዘርህ እንዲሁ ይሆናል አለው። ዘፍጥረት 15:5 እኔ በባርክህ እባርክሃለሁ፥ ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብትና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ አበዛዋለሁ፤ ዘርህም የጠላቶቹን ደጅ ይወርሳል፤ ዘፍጥረት 22:17 ዘርህንም እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛዋለሁ፥ እነዚህንም አገሮች ሁሉ ለዘርህ እሰጣለሁ፤ የምድርም አሕዛብ ሁሉ በዘርህ ይባረካሉ። ዘፍጥረት 26:4 ሌላም ሕልም አለመ፥ ለወንድሞቹም ነገራቸው፥ እንዲህም አለ። እነሆ፥ ሌላ ሕልም አልሜአለሁ፤ እነሆም፥ ፀሐይና ጨረቃ አሥራ አንዱም ከዋክብት ሰገዱልኝ አለ። ዘፍጥረት 37:9 በራስህ የማልህላቸውን ባሪያዎችህን አብርሃምን፣ ይስሐቅንና እስራኤልን አስብ፤ ዘራችሁን እንደ ሰማይ ከዋክብት አበዛለሁ፤ የተናገርኋትንም ምድር ሁሉ ለዘራችሁ እሰጣለሁ፤ ለዘላለምም ይወርሱአታል። ዘጸአት 32:13 አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ አየዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤልም በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሼትንም ልጆች ሁሉ ያጠፋል። ዘኍልቍ 24:17 አምላካችሁ እግዚአብሔር አብዝቶአችኋል፥ እነሆም፥ እናንተ ዛሬ እንደ ሰማይ ከዋክብት ብዛት ናችሁ። ዘዳግም 1:10


Turn static files into dynamic content formats.

Create a flipbook
Amharic - Stars in Scriptures (Stellar Astronomy) by Filipino Tracts and Literature Society Inc. - Issuu