Page 1


8

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም


ጤናይስጥልኝ! እንኳን አደረሳችሁ! መቼም በሰው ሀገር ሲኖሩ እን ደሀገሩ ፣ እንደህዝቡ ፣ እንደባህሉ መኖር ግድ ይላልና ፤ የሀገሬውን ጽዋ መ ቅመስ ፣ ደስታውንም ሆነ ሀዘኑን መካፈል ፣ በዓላቱን አብሮ ማክበሩ የተለመ ደ ነው። ታዲያ በሁለት ካላንደር መቁጠሩ በሁለት ባህል መኖሩ ብዙ መልካ ም ነገሮች እንዳሉት ሁሉ ፤ መጥፎ ጎኖችም ይኖሩታል። በይበልጥ በእንዲህ አይነቱ የኢኮኖሚ ድቀት ወቅት ፤ ሁለት አንድ አይነት በዓላትን ማክበር ከ ሚፈጥርው ደስታ ይልቅ ፤ ለዚያ በሚደረገው ወጪ የሚፈጠረው ውጥረት ና ኪስ መራቆት ኑሮን ያዳክማል። በዓል ለማክበር የሚደረገው ስጦታ መል ካም ቢሆንም ጊዜውን በመረዳት ከልክ ያለፈና ለታይታ የሚደረገውን ወ ጪ ሰብሰብ በማድረግ ፤ እራስን ከብክነት ቆጥቦ አቅም የፈቀደውን በማድረ ግ ሰላምና ደስታ የተሞላበት በዓል ማድረግ የተሻለ ነው እንላለን። ታዲያ በሌላ መልኩ ደግሞ ሁለት አዲስ ዓመት ማክበሩ የምንገባ ውን የአዲስ ዓመት የለውጥ ምኞት ቃል በየስድስት ወሩ በማድረግ ሁለቴ እ ንድንሞክረው እድሉን ይሰጠናል። በህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት ብርቱ ሙከራ ማድረግና በመልካም እራስን መቀየር እራሱን የቻለ በዓል ነው። ያ ለፈው ዓመት ጥረታችን ሰምሮና ያሰብነው ተሳክቶ ስናይ ደግሞ ለዚህ ዓመ ቱ ብርታት እናገኛለን። የተመኙትን ለመፈጸም በጥንካሬ መነሳቱ የብርቱዎች መንፈስ ነውና ፤ በዓልን ለብክነት ሳይሆን ለእድገት ማድረግ የተሻለ በመሆኑ ያበርታችሁ እንላለን። እኛም ስጦታችን የሆነችውን ፣ይህንን ምክር እንካችሁ ያልንባት ን ፣ ብዙ ጉዳዮችን የምታስተናግደውን ይህች መጽሄታችንን በማሳደግ አሁን ካላት መልክና ይዘት ሊታከልባት የሚያስፈልገውን በማከል ፤ አሻሽለን ልና ቀርብላችሁ ቃል እንገባለን። እንግዲህ ለሁላችንም መልካም ዓውደ-ዓመት! ማለፊያና የተሻለ የለውጥና የስኬት ዓመት እንዲሆንልን የዝግጅት ክፍላች ን መልካም ምኞቱን ይገልፃል። ሰለሞን አባተ

Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

9


10

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም


ደብዳቤዎቻችሁ መጽሄታችሁ አንድ ጥሩ መጽሄት መያዝ የሚገባውን ነገር ሁሉ ይዟል። የህትመት ጥራቱ ፣ ይዘቱ ፣ በይበልጥ ደግሞ በመጨረሻው ገጽ አካባቢ ስለ አባይ ግድብ ስብሰባ የሰጣችሁት የግለሰቦች አስተያየት ነፃና ወገናዊነት የሌለው በመሆኑ በጣም ያስደስታል። ጥሩ ባህል ነው ቀጥሉበት እላለሁ። ጌትነት ከላስቬጋስ እናመሰግናለን ጌትነት ከሀገራችን ውጪ በይበልጥ በሰሜኑ አሜሪካን የምንኖር ኢትዮጵያዊያን ፤ በስራ ብዛትና በ ምግቡ አይነት ብዙዎቻችን በበሽታ የምንሰቃይ ሲሆን ፤ በመጽሄታችሁ ላይ ጠቃሚ የሆኑ የጤና መ ረጃዎችንና ምክሮችን በቋንቋችን በመተንተን ስለችግራችን እንድንረዳና እንድንጠነቀቅ ለሚረዳን ወን ድማችን ዶ/ር ሰለሞን ማሞ እባካችሁ ምስጋናዬን አድርሱልኝ። ዳዊት ከሳንሆዜ አቶ ዳዊት መልክትዎን እናስተላልፋለን በተጨማሪም እናመሰግናለን። ጥያቄ አለኝ እኔና ባለቤቴ በገንዘብ ነገር ላይ አልተግባባንም። ወጥታ ማባከን ለርሷ እንደማ ባከን አትቆጥርውም እኔ ደግሞ ለምን እላለሁ እና መፍትሄው ምን ይመስላችኋል? ስማቸው እንዳይገ ለጽ የፈለጉ አንባቢያችን ከዲሲ። “ለምንድነው ፈረንጆቹ እንደሚያደርጉት የሀገራችንን መጥፎ ገጽታ የሚያሳዩ ቆሻሻ ፎቶዎ ች ብቻ በመጽሄታችሁ ላይ የምታወጡት? ዛሬ ሀገራችን ብዙ የሚያማምሩ ፎቆች አሏት እናም እርሱን ለምን አታወጡትም?” አቶ ነጋሲ እባላለሁ ብለው በስልክ አስተያየትዎን የለገሱን አንባቢ። አቶ ነጋሲ እናመሰግናለን! ያወጣናቸው ከሀገራችን የተነሱ ምስሎች ብዙውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚወክሉ እውነተኛ የሀገራችን ህዝብ የእለት-ተለት ኑሮ ሲመራ የሚያሳዩ ምስሎች እንጂ ፤ እ ንዳሉት መጥፎና ቆሻሻ ገጽታ አይደሉም። ዝቅተኛ ኑሮ የሚኖሩ የሀገራችን ሰዎች ፎቶ ቆሻሻ ተደርጎ መተየትም የለበትም። ስለዚህ የዝግጅት ክፍላችን በመጽሄታችን ላይ የሚያወጣቸው ማንኛቸውም ጉ ዳዮች ሁሉ የምናምንባቸው እውነታዎች ሲሆኑ ፤ ወደፊትም ይህንን አቋም ሳንለቅ ወገናዊነት በሌለው መንገድ በጽሁፍም ሆነ በፎቶግራፍ በተደገፈ መልኩ የምናስተናግድ መሆናችንን እንገልፃለን። ባለፈው እትማችን ስደት በባእድ ምድር በሚለው አምዳችን “ይድረስ ለአያ ሻረው” የሚለ ውን ግጥም ደራሲ ማንነት ባለማወቃችን ስሙን ሳንጽፍ በማለፋችን ይቅርታ እየጠየቅን ፤ ግጥሙን ያ ገኘነው በአደራ ባለቤትነት ከተላለፈላት ከኤልሳ ይልማ መሆኑን ልንገልጽ እንወዳለን። እናመሰግናለን ኤልሳ!

Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

11


ሁልጊዜ ስለ አለባበስና ፋሽን ስናስብ ሁላ ችንንም ሊያስማማ የሚችል የተወሰነ ስርዓት ይኖራ ል። ይኸውም ዋነኛው ነገር ለምን አይነት ጉዳይና ዝ ግጅት ምን መለበስ ይኖርበታል የሚለው ነገር ይመ ስለኛል። በይበልጥ ለኛ ለሴቶች ልክ በአንድ ዝግጅት ወይም ግብዣ ላይ እንድንገኝ መጋበዛችን ሲነገረን ወ ይም የጥሪው ካርድ ሲደርሰን የመጀመሪያው በአዕም ሮአችን የሚፈጠረው “ደግሞ ምን ይሆን የሚለበሰ ው?” የሚለው ጥያቄ ነው። በርግጥ ተራና የማይረባ አባባል ሊመስል ይችላል ግን ደግሞ በዝግጅቱ ላይ ከ ሚኖሩት እንግዶች ጋር ተመጣጥኖ ፣ ሙሉ እርግጠ ኝነት ተሰምቶን፣ በአለባበሳችን ተደስተን፣ የበታችነት ሳይሰማን ፣ በስፍራው ከተገኙት ጋር በእይታም ይሁ ን በቃል የምንጠብቃቸውን መልካም አስተያየቶች ለ ማግኘት በተጨማሪም ማንነታችንን በተለያየ መልኩ የምናወጣበት ቦታ በመሆኑ ከግብዣው ጥሪ ቀን ጀም ሮ እንደ ዝግጅቱ ትልቀትና ልዩነት የሚደረገው መሰ ናዶ ይጀምራል። ታዲያ እኮ መዘጋጀቱ አንድ ራሱን የቻለ ወስጣዊ ደስታ የሚሰጠን ነገር ነው። ቀኑ እየተቃረበ በሄደ ቁጥር ቁምሳጥናችን መበርበር ይጀምራል አልጋ ችን በልብስ ክምር ይጨናነቃል። ይለካል፣ ይጣላል፣ እንደገናም ይለካል ስንት ሰዓትና ገንዘብ ተፈጅቶባቸ ው የተገዙት ልብሶች ይወጣሉ ግን አይን አልሞላ ይላ ሉ። አንዳንዴም ይሄን ለገሌ ሰርግ ልብሼው ታይቻለ ሁ። ይሄን ደግሞ ለእገሌ፣ ይሄ ያምራል! እወደዋለሁ! ግን አሁን ደግሞ አድርጌው ብታይ “ አሁንስ ይሄን ል ብስ እላይዋ ላይ ተነቀሰችው እንዴ?” ነው የሚሉኝ። ይሄ ደግሞ ሆዴን ያወጣዋል! . . . ኤጭ ምን ይሻላል ሮጥ ሮጥ ብዬ መክሳት ሲገባኝ ሁሌ ልብስ መልበስ ሳ ስብ ነው የሰውነቴ ነገር የሚሰማኝ. . . ከመኝታ ቤታ ችን መስታወት ጋር ያለው ጭውውት ይጦፋል። በመ ጨረሻ ሁሉም ይቀርና አዲስ የመግዛት ውሳኔ ላይ ይደረሳል። ከስራ በኋላ ወደሞል እየተሄደ ሌላ ጊዜ ባ ጋጣሚ የታየውም ይሁን አዲሱ ይሞከራል። ልንለብ ሰው የምንፈልገው አይነት ልብስ ካልተገኘ ወይም የ ምንለብሰውን ካላወቅን ውስጣችን አይደሰትም ለጓደ ኛችን እኔ አልሄድም ባክሽ የሚሉ ውሳኔዎች ሁሉ ይ ፈጠራሉ። ግን ለምንድነው ለዚህ ነገር መልስ የማና ገኝለት? የብዙ ዓመታት የፋሽን ስራ ውጤቶች በሞ ሉበት ፣ የተለያዩ ስለ ፋሽን የሚያሳዩ መጽሄቶች ባሉ በት ፣ ብዙ መቶ የልብስ አይነቶች በየመደብሩ ተደር ድረው በሚታዩበት ፣ የመግዣ ገንዘቡም ቢሆን እንደ አቅም ባልጠፋበት ሀገር ችግሩ ምኑ ጋር ይሆን? እስ ቲ መፍትሄውን ባለፈው ሳምንት ከአንዲት የፍሽን ባ ለሞያ ጋር በአንድ የእራት ግብዣ ላይ በአጋጣሚ ጠ ረጴዛ ተጋርተን አርስቱ ተነስቶ ያካፈለችኝን ላካፍላች ሁ። መጀመሪያ የምንሄድበትን ቦታ ስናስብ “ለእያንዳንዱ አይነት ዝግጅት ምን አይነት አለባበስ

እንደሚያስፈልግ መገንዘብ ጥሩ ነው። ያም ማ ለት ለስራ ኢንተርቪው ፣ አዲስ ለተዋወቅሁት ልጅ የመጀመሪያ ቀን ቀጠሮ ፣ ለምራቃ በዓል ወይም ለሰርግ ጥሪ መልበስ የሚገባኝ የተለያየ በመሆኑ ነው። የምንሄድበት ጉዳይ ወይም ዝግ ጅት ምን ያህል ሰዎችና እንዴት አይነት ሰዎች እንደሚገኙበት ማወቅ ያስፈልጋል። ይኸውም የሚበዙት በምን አይነት የእድሜ ክልል ላይ ያ ሉ እንደሆኑ ፣ ታዋቂ ሰዎች ይገኙበታል ወይስ? ብዙ ወግ አጥባቂ ሰዎች መኖራቸውንና አለመ ኖራቸውን ከልጆች ጋር የሚኬድበት ቦታ ነው ወይስ?. . .” የወቅቱ እና የዕለቱ ያየር ሁኔታ ሌላ ው ወሳኝ ነገር ነው። በክረምት ወይም በብርድ የሚለበሰውን በበጋ በፀሀይ ቀን ብንለብስ ወይ ም የበጋውን ለክረምት ብናዘዋውረው አንደኛ ምቾት አይሰማንም በግብዣው ላይ የተገኘው ሰውም ምን ሆናለች ብሎ መመምልከቱ አይቀ ሬ ነውና። ለምሳሌ ቤተሰብ ካለንና የምንሄድ በት ዝግጅት ከልጅ ጋር ከሆነ ፤ ልጆችን ሊስብ የሚችል ቀለም ያለውና ከልጆቻችን ጋር ቁጭ ብድግ ለማለት አመቺ የሆነ ነገር ብንለብስ ይ መረጣል። ከዚያ ደግሞ ከመልካችን ፣ ከቁመ ታችንና ከሰውነታችን አወራረድ ጋር የሚሄዱ ትን ልብሶች መረዳቱ ዋነኛውና ማወቅ የሚገባ ን ትልቁ ነገር ነው። አቅሙ ካለ አማካሪዎችን የ ትኛው ቀለምና የስፌት አይነት እንዲሁም ልብ ሱ የተሰራበት ማቴሪያል እንደሚስማማ ማወ ቁ ብልህነት ነው ። ሌላው ስለቀለም ማወቅ የሚገባን የ ልብሶቹ ቀለም ከወቅቱ ጋር ተንተርሶ ስለሚሰ ራ በብዛት የምናገኛቸው ቀለሞች ከኛ ጋር ላይ ሄዱ ስለሚችሉ ፍለጋው ሊያደክመን ይችላል። ልብስን የሚያሳምረው የነዚህ ከላ ይ የጠቀስኳቸው ነገሮች መጣመር እንጂ ውድ ነቱ አይደለም። በአካልችን ላይ ለኛ እንደተሰራ ሆኖ መታየቱ ዋናው ልክንቱ ነው። አንዳንዶ ች በውድ ተጨንቀው ገዝተው ለብሰው ሳይታ ይባቸው ሌላዋ በርካሽ የተገዛ ግን በትክክል የ ተመረጠውን ለብሳ የዝግጅቱን ሁሉ አይንና አ ስተያየት ወደርሷ ሰብስባው ስታመሽ ትታያለ ች። በተጨማሪም ከልብሱ ጋር አብረው መታ ሰብ የሚገባቸው አቋቋሙ ፣ አቀማመጡ፣ አረ ማመዱና ለልብሱ ተጨማሪ ህይወት መስጠቱ ሲሆን ፤ በመጨረሻም መረሳት የማይገባው የ ሚደረገው ጫማ ቁመቱ ከፍ ያለና እንደዚያ አ ይነት ጫማ ለረዥም ጊዜ ያላደረግን ከሆነ በቤ ታችን ውስጥ መለስ ቀለስ በማለት እራስን ማዘ ጋጀት ያስፈልጋል። እንግዲህ ሌላዋ ስለለበሰች ውና ስላማረባት ፣ ውድ ስልሆነ ወይም ተሰቅ ሎ ስላየነው ብቻ በመግዛት የማይያስደስተንን ሰብስበን ቤታችን በመውሰድ የምንከምራቸው ን አዲስ ልብስና ጫማዎች ወጪም ይቀንስልና ልና ነው ያካፈልኳችሁ። ማራኪ ውበት ነኝ ከዋሽንግተን ዲሲ


Modern time Technology has improved our lives for so many years. Microprocessors in computers, cell phones and other new hand held portable devices have allowed us to access the World Wide Web called the internet. 20 years ago we couldn’t imagine how powerful the internet could be, but now we can’t seem to live without it. The internet started out as a military program to create a network of computer connected to transfer information faster. But since it was available to the public in the early 1990’s it is widely used by the public all over the world. As resourceful as the internet is, it also comes with an issue of security of the data being transferred by those who use it. For both government and the public hackers are serious issue because they steal important information and misuse it. Besides using data retained illegally by hacked for identity theft others hackers from another country break in to steal sensitive government data of another country. This is a form of war between countries called cyber war and it is far more serious than people think of it. Cyber warfare could be the next generations of mass 16

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

destruction as countries fight to keep hackers out of classified government data and other institutions such as banks and airlines by electronic means. Computers are linked through standard set of TCP/IP protocols making it easy and fast for hackers to break through public and private sectors. Viruses and worms could be spread in such a short time making it hard to recover in case of security breach. When we think of hacker, we tend to think of them as a single outlaw. But when it comes to cyber warfare, countries are involved as they purposely train their own people in computer intelligence. To mention some countries who are highly involved in computer intelligence in their military; India, China, Pakistan and Russia are a few. These countries are among others who are getting ready for the future as potential cyber warfare threatens their network boarders. Above all the United States is the center of the network world as it advances in its intelligence services over any other country. Moreover the United States outsources their programing of software to other countries such as


those mentioned above making the United States a target for non-allied countries and terrorists for many reasons. After 9/11 the United States formed the Department of Homeland Security for defense against outsider attackers. Regarding to cyber warfare, there isn’t a sold prediction of what would happen in such a case for the department to make policies to protect the country. Some argue that the whole U.S. empire is built on a system based on electronic structure from military to economics and cyber attach could potentially bring down the whole country. And some say it is impossible for that to happen and it should not be a big threat. As our world is becoming more connected to networks; cyberattacks occur often on different levels. Financial institutions, communication industries and transportation agencies are often a target for hackers. And since more military forces are based on network-centric and other country attacking another is like waging a war.

Examples of cyber warfare: • In 1998, the United States hacked into Serbia’s air defense system to compromise air traffic control and facilitate the bombing of Serbian targets. • In 2007, in Estonia, a botnet of over a million computers brought down government, business and media websites across the country. The attack was suspected to have originated in Russia, motivated by political tension between the two countries. • Also in 2007, an unknown foreign party hacked into high tech and military agencies in the United States and downloaded terabytes of information. • In 2009, a cyber spy network called “GhostNet” accessed confidential information belonging to both governmental and private organizations in over 100 countries around the world. GhostNet is believed to have generated in China although they deny it. In May 2010 the U.S. military had created a subcommand for cyber command, authorizing them to legally conduct offensive

attacks in the “domain.” The president now has the power to order any counter offense over cyber space. In 2009, U.S. hacker Albert Gonzalez (Reuters) pled guilty to helping steal forty million credit and debit card numbers from major retail stores via the Internet, one of the largest cases of identity theft in history. The small town of Râmnicu Vâlcea in Romania-known as”Hackerville” (Wired) to international law enforcement--has become a notorious sanctuary for operators in ecommerce scams and malware attacks. These cyber-schemes funnel tens of millions of dollars into the Transylvania region and have become a primary source for the area’s economic boom. Shortly after assuming office in 2009, President Obama requested a complete review of federal efforts to defend the nation’s digital infrastructure, and declared cyberspace a strategic national asset that the United States should use all means to protect. Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

17


“አቤት! የእኛ ሰው እኮ አያድርስ ነው! . . . ድሮስ ሀበሻ . . . ! እኔስ ፈረንጅ ይግደለኝ! . . . ሀበሻን አትመን!” . . . “እኔ ሀበሻ የበዛበት አፓርትመንት መከራየት አልፈልግም። . . . አዚያ ሀበሻ የበዛበት ስታርባክስ? . . . ሀበሻ ማየት ነው ያስጠላኝ። . . . ሀበሻ እንደሁ አያልፍለት! . . . ምን እኮ የሀበሻ ቤት ነው የሚመስለው . . . አሁንማ ሀበሻ ከመብዛቱ የተነሳ ሀገር ቤት ያለሁ ነው የሚመስለኝ . . . ። አየሀው ሀበሻ መቼም ካለ ካምሪና ኮሮላ አይነዳ! . . . “ሀበሻ! . . . ሀበሻ! . . . ሀበሻ! . . .

በሰሜኑ አሜሪካ የሚኖረው የሀገሬ ሰው እንደ ዕለት የአዝማች ግ ጥም ሲደጋግማቸው የሚደመጡ ስንኞች ናቸው። ባልሳሳት ብዙዎቻችን እ ንዲህ ያሉትን አስተያየቶች የሰማነውም ከሀገር ከወጣን በኋላ ይመስለኛል። ከራሱ የተጣላ ህዝብ አያስመስልብንም ትላላችሁ? ዘወትር ይህንን ድግግሞ ሽ ሳዳምጥ ሀገሬ ሳለሁ አንድ ጓደኛዬ ቤት ግድግዳ ላይ ተንጠልጥሎ ያየሁት “ሰው እኮ!” የሚል ጥቅስ ብዙ ጊዜ ትዝ ይለኛል። ያየሁት ያኔ በለጋ እድሜዬ ፤ ሙሉ ትርጉሙ ሳይገባኝ ወይም ሰው የሚለው ማንነት በመልካም ይሁን በመጥፎ የታየው ለመተርጎም በማልጨነቅበቱ ጊዜ ስለነበር ፤ ጠልቄ ለመመ ራመር ሳልሞክር አልፌው ነበር። ዛሬ ግን በዚህ ሁለት ቃላት ውስጥ ሊገለጽ የተፈለገው የሰውን ልጅ ውጥንቅጥነት ፣ በጥቅሉ ማንነቱንና ምንነቱን ለመ ግለጽ እንደነበር ከዘመናት በኋላ በቅጡ ለመረዳት ችያለሁ። ሀገሬን ለቅቄ በመምጣቴ አባባሉ ከሰው ዘርነት ተለውጦ ፤ ለአን 20

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ድ ዘር ሊያውም ለእራሴው ዘር! በራሱ በሀበሻ ምላስ ፤ በአሉታዊ መግለጫ ነት “ሀበሻ እኮ!” ሲባል በማድመጤ ሁሌም ቢያሳዝነኝም ለምን የሚለውን ጥያቄ ደግሞ ፈጥሮብኛል። ታዲያ “ሀበሻ እኮ!” ብሎ ነገርን ከመጀመር ይል ቅ “ሰው እኮ!” ብንል ፤ አንድን ማህበረሰብ በጥቅል ከመናገር ራስን ለመመ ልከት አይረዳንም? ለመሆኑ “ሀበሻ” የሚለው ስም በይበልጥ በአሁኑ ጊዜ ከ ስሙ ባሻገር ያለውን የፓለቲካ ድብብቆሽ ትቶ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝ ብን የሚወክል ይመስለኛል። ነገሩ የሁለቱ ሀገር ሰዎች ዜግነት በመለየት ላለ መጥቀስ ወይም የፖለቲካ ልዩነታቸውን ላለማጉላትና ፤ እንደው አልዋጥ ያለ ንን የመገንጠል ነገር ሳይጠቀስ ለመሸዋዋድ “ሀበሻ ነህ? ወይም ሀበሻ ነሽ?” በመባባል የጋራ መጠሪያ አድርገን የተቀበልነው የሽፋን ስም ሆኗል። ለነገሩ ሀበሻነት የሚለው ስም ከሰማኒያ ሚሊዮን በላይ ህዝብን ይወክላል ለማለት እንጂ ስለመገንጠል አለመገንጠሉ ለማውራት ፈልጌ እንኳን አይደለም። ሀበሻ በሚለው ስም መወከልን ከተስማማን “ሀበሻ . . . እኮ!” ብለ


ን የምንደረድረው መልካም ያልሆኑ የባህሪ ነጸብ ራቆችን አስተካክለን እኛ ሀበሾች እኮ! እንዲህ እ ናደርጋለን ብንል ትንሽ ወደ ራሳችን ስለሚያስጠ ቁመን ፤ በሌሎች ማየት የምንፈልገውን መልካም ስነምግባር በራሳችን መጀመር እንዳለብን ስለሚ ነግረን የተሻለ ያደርገው ነበር። ሰው ስለሆንን እርስ በርሳችን ባንወካ ከልም ፤ “ሀበሻዊነት” ያደግንበት ባህልና የህብረ ተሰብ አኗኗር ልምድ ፤ ተመሳሳይ ድርጊቶችን ሊ ያስደርገን ይችላል ብለን ካመንና ፣ እንዲወክለ ን ከፈለግንም ፤ ስነምግባራችን እኛን እንደሚወ ክል ሁሉ ስማችን ደግሞ ስነምባራችንን እንዲወ ክል መጣር ይገባናል። “እኔ እኮ መጥፎነኝ!” እያ

ቅበት እንጂ ለምን በጋራ የሰማኒያ ሚሊዮን ህዝ ብ መጠሪያ በሆነው ስያሜ ልንዘብትበት እንፈል ጋለን። ለመሆኑ የእኛ ማህበረሰብ “ሀበሻ!..” እየተባለ የሚተቸው ፣ የሚወቀሰውና የሚንቋሸ ሸውስ ለምንድን ነው? እስቲ ሀበሻ የሚለውን ስ ያሜ ለጊዜው ላርቀውና። አንድ ኢትዮጵያዊ ትክ ክለኛ ያልሆነ ድርጊት ሲፈጽም መታየቱ “ሀበሻ” ስለሆነ ነው የሚል ድምዳሜ ላይስ ለምን እንደር ሳለን? አንዳንችን ከሌላው የሀገራችን ሰው ጋር ተ መሳሳይ የሆነ ነገር ካለን ወይም ካደረግን የድርጊ ታችን ምክንያቱ ሀበሻነት ነውን? ሀገራችን ጠንከ ር ያለ ቡና ጠጪዎች በመሆናችን ስታርባክስ ያ

ካም ለውጥ ሳይሆን ፤ እርሷን ያሳሰባት ከምትገዛ በት ቤት ሌሎች ያገሯ ልጆች እንዳይገዙና እርሷ የምታደርገውን ማድረግ እንዳይችሉ ማድረጓ ብ ቻ ነበር። አያሳዝንም? ጋግራው የራሷ የሆነውን ቅመማ አላስይም ብትል ትደነቅ ነበር። በማህበ ርዊ ኑሮአችን ከቤተሰብ ፣ ከጎረቤት ፣ ከጓደኛ . . . ያየነውን መልካም ነገር ተከትለን ስናደርግ ስላደ ግን ፤ ብናደርገስ ወንጀሉ ምኑ ጋር ይሆን? ነገሩ እንዲህ ከ ጅ ወንጀል የሚሆነው እኮ የአንድን ግ ለሰብ በህግ የተጠበቀ የፈጠራ ስራ ያለፈቃድ ኮ ፒ ሲደረግ ብቻ ይመስለኛል። ለምሳሌ ፦ በየከተ ማችን የባለሞያዎችን ሲዲዎችና ዲቪዲዎች ያለ ፍቃድ ኮፒ አድርገው እንደሚነግዱት ነጋዴዎች

ለ መጥፎነቱን የማያርም ያለ አይመስለኝም ፤ መ ጥፎነቱን ይደብቅ ይሆናል እንጂ ፤ ካለ ግን የተሳ ሳተ ይመስለኛል አሊይም ትንሽ “ቀዌ” ቢጤ ሳይ ሆን አይቀርም። ከግራህም ከቀኝህም “አቤት! ሀ በሻ ሁል ጊዜ . . . ” ብሎ መጥፎ ነገሮችን መደር ደር ሲጀምር “አቤት! አንተ እና እኔ ሁልጊዜ . . .” እያለህ መሆኑን የዘነጋው ይመስለኛል። ትክክለ ኛ ወይም ጥሩ ስነምግባርን ማጉደል እኮ በየትኛ ውም የሰው ዘር ዘንድ የሚገኝ እንጂ ፤ በሀበሻ ዘ ር ብቻ ያለ ቫይረስ አድርጎ ማሰቡና ማስተጋባቱ የተሳሳተ እንደሆነ ማወቅ ይገባል። ያንን ነገር የሌ ላው ህብረተሰብም ያደርገዋል ፣ ይኖረዋል . . .። እርስ በርሳችን ሙሉ ብቃት ያለን ሰዎ ች መሆናችንን አለመቀበል ካልሆነ በስተቀር ፤ አ ንዳችን የምናደርገውን ሌላችን ልናደርግ የማንች ልበት ነገር አይታየኝም። የመጣንበት ቦታ ፣ ዘራ ችን ወይም ድህነታችንና ሀብታምነታችን . . . ሁ ሉ ይህን ከማድረግ አያግዱንም። እንደማንኛው ም ህዝብ ብዙ መልካምና መጥፎ ባህል ቢኖረን ም። ጥሩ ወይም መጥፎ ማድረግን በግል እንጠየ

ንን ስለተካልን ስታርባክስ ብንሄድ ወይም ደግሞ ቶዮታን የሚነዳ ሀበሻን ስላየን እርሱም የገዛው ሌላው ሀበሻ ሲነዳ ስላየ ነው ብንል አልተሳሳት ንም? ቢሆንስ ወገኑ የሚነዳውን መኪና በመንዳ ቱ እንደጥፋትስ ለምን ይታይበታል። መልካምና ጠቃሚ የሆነ ነገርን ኮፒ ማድረግ (መኮርጅ) እኮ መጥፎ አይደልም። ማንኛችንም የምናደርገው ነ ገር ሁሉ በሌሎች የተደረገ መሆኑን ካልዘነጋን በ ቀር። እንደውም አንድ ጊዜ አንድ የምቀርባት ል ጅ ኬክ ገዝታ ወደ አንድ ግብዣ አምጥታ ስንመ ገብ ፤ የገዛችው ኬክ በጣም ጥሩ ስለነበር ሁላች ንም ከየት እንደገዛችው ለማወቅ ጓግተን ጠየቅና ት ፤ ነገር ግን ለመናጋር አልፈለገችም ነበር። ነገ ሩ ስለገረመኝ ከጥቂት ቆይታ በኋላ ለብቻዋ ስት ሆን ለምን ልትናጋር እንዳልፈለገች ብጠይቃት ፤ “ይህ የኔ ኬክ ቤት ነው! ሀበሻ ያየውን መኮረጅ ስ ለሚወድ መጥቶ ሊኮርጅ ፈልጎ ነው። ብላ የተና ገረችው ሁልጊዜ ይገርመኛል ። ያልተረዳችው እ ዚያ የቀመስነው ሁሉ ከዚያ ኬክ ቤት ሄደን ብን ገዛ ፤ በነጋዴው ህይወት ላይ የሚያመጣው መል

ማለቴ ነው። በርግጥ ሌላ ሰው ያላደረገውን ማ ድረግ እና መፍጠር በጣም የሚደነቅ እና የሚደገ ፍ ችሎታ ሲሆን ፤ ሁሉ ሰው ግን የፈጠራ ችሎታ ያለው ባለመሆኑ ከሌሎች ቢመለከት ነውር አይ መስለኝም። በዓለማችን ላይ ያልተኮረጀ ምን ነገ ርስ ይገኛል? በሌሎች ፈጠራ ላይ የተሻለ ለውጥ በማከል የፈጠራ ውጤቶችን ማሳደግ ሌላው ች ሎታ ነው። በቴክኖሎጂውም ዓለም እንኳን አሁ ን የምንጠቀምበት ኮምፒዩተር ጅማሬው ወይም ጽንሰ ሀሳቡ የመጣው ከአንድ ግለሰብ ነበር። ነገ ር ግን አሁን በብዙ የሚቆጠሩ የኮምፒዩተር አቅ ራቢዎች። የእኛ ስራ በማለት ከመጀመሪያው ስ ራ ለውጦችን በማከል ለግልጋሎት እያቀርቡት ነ ው። መኪናው ፣ ቤቱ ፣ ባጠቃላይ የመገልገያ መ ሳሪያዎቹ . . . ምኑ ቅጡ። የሰው ልጆች ፍላጎት ብዙና የተለያየ በመሆኑ ፤ አንዱ ብቻ እነዚህን ፍ ላጎቶች ለማሟላት ባለመቻሉ ምክንያት የተለያዩ ሰዎች የፈጠራ ውጤቶች ዓለማችንን እያሳደጋት ነው። ሰዎች ሌላው ያደረገውን የማይደግሙ ቢ ሆን ኖሮ ፋብሪካዎች በሙሉ ለያንዳንዳችን የተ Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

21


ለያየ ሞዴል የመገልገያ ምርቶችን ባመረቱ ነበር። ታዲያ ይሄ እርስ በርስችን ያለን አሉታዊ አመለካከት ፤ በማህበራ ዊውም ህይወት ሆነ በስራውና በንግዱ ዓለም ላይ ያለንን ግንኙነት የሚያጠ ናክር ፣ ማህበረሰቡን የሚያሳድግና የሚያበረታ አላደረገውም። አንድ አይነት የመግባቢያ ቋንቋና ባህል ቢኖረንም ቀና የሆነ አመለካከት ከሌለን ፤ አትድረ ስብኝ አልደርስብህም በሚል የሽሽት ስሜት ሁሉን ነገር በግላችን እንጂ በጋ ራ እንዳንሰራ አድርጎናል። ሀበሻ የሌለበት ቦታ ሄዶ መኖር ፣ መገብየት ፣ መ ጫወት . . . በአጠቃላይ የሀብሻ ዘር ባለበት ቦታ ላለመያየት ስንሞክር ፤ በን ግድ ስራ ፣ በህክምና ፣ በህግ ሞያ ፣ እንዲሁም በተለያዩ የአገልጎሎት መስጫ ዎች የተሰማሩትን ባለሞያ ወገኖቻችንን እድገት ስኬታማ እንዳይሆኑና ፤ የራ ሳችንን ሰው አምኖ ከመገልገልና ከመገበያየት ይልቅ ወደ ሌላ ዜጋና ማህበረ ሰብ ሄደን ግልጋሎቱን መጠቀም እንድንመርጥ አድርጎናል። በርግጥ እዚህ ላ ይ ሳልጠቅሰው ማለፍ የማልፈልገው ነገር ፤ አንዳንድ የሀገራችን የንግድ ሰዎ ች በደንበኝነት የተገለገላቸውን ሰው ሚስጥር ሳይጠብቁ ለሌሎች በመናገር ፤ ያ ሰው በቤተሰቡ ፣ በጓደኞቹና በህብረተሰቡ ዘንድ መጥፎ ስም እንዲሰጠው በማድረግ ለሀበሻው ዘር ሽሽት አስተዋጽኦም ያደርጋሉ። “ቶኪንግ ዶላርስ ኤንድ ሜኪንግ ሴንስ። ሀብት የማግኛ መንገድ ለ ጥቁር አሜሪካኖች” በሚል እርዕስ ብሮኪ ስቲፈንስ የምትባል አንድ ጥቁር አ ሜሪካዊት ጸሀፊና ኢኮኖሚስት ፤ በዋሽንግተን ዲሲ የሚኖሩትን የተለያዩ ማ ህበረሰቦች በማነጻጸር ፤ አንድ ዶላር በእነዚህ ማህበረሰብ ኑሮና ንግድ ዙሪያ ምን ያህል ጊዜ እንደሚሽከረከር ወይም እንደሚቀባበል በመከታተል ጥናት አድርጋ ነበር። ታዲያ ይህ ጥናት የተደረገው በሰሜን አሜሪካ የእኛ የሀበሻው ማህበረሰብ በቁጥር ትልቁ በሚኖርበት በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ ነበር። ጥናቱም አንድ ዶላር ወደ “ኤዥያን ማህበረሰብ ባንኮች ፣ የቤት አ ሻሻጭ ደላሎች፣ ሱቆች፣ የንግድ ባለሞያዎችና ድርጅቶች ኪስ ከገባ ጊዜ ጀም ሮ ፤ ከአንዱ ወደ ሌላው ሲተላለፍ ቆይቶ ወጥቶ ወደ ሌላ ማህበረሰብ የሚሻገ ረው ከ28 ቀናት በኋላ ሲሆን። በጂውሾች (በእስራኤሎቹ) ማህበረስብ ውስ ጥ ደግሞ 19 ቀናትን አስቆጥሮ ይወጣል። በነጩም ማህበረሰብም እንደዚሁ ለ17 ቀናት ያክል ከኪስ ወደኪስ ይዘዋወራል። ነገር ግን ይህ አንድ ዶላር በአ ፍሪካን አሜሪካን ማህበረሰብ ኪሶች፣ የንግድ ተቋሞች ፣ ካዝናዎች ውስጥ የ ሚቆየው ለ6 ሰዓታት! ብቻ እንደሆነ ለመረዳት ተችሏል። ታዲያ ከዚህ ጥና ት የምንረዳው በሌሎች በሰሜን አሜሪካን በሚኖሩ ማህበረሰቦች ያለው የእ ርስ በእርስ ትምምን እና የአገልጎሎት ቅብብሎሽ ሰፊና የተሻለ መሆኑን ነው። አንድ የኤዥያ ወይም የጁ ማህበረሰብ አባል የራሱ ዜጋ ያቀረበለት ግልግሎት ከሌለ ብቻ እንደሆነ ወደ ሌሎች ዜጎች ንግድ ተቋሞች ሄዶ የሚገለገለው ያሳ የናል። እነዚህ ዜጎች በተለያዩ ምክንያቶች በራሳቸው ዜጋ የሚሰጠውን ግልጋ ሎት በመምረጥና በማህበረሰባቸው መካከል የሚደረገውን የገንዘብ ቅብብል ጠንካራ እንዲሆን ከማድረጋቸው ባሻገር ፤ በንግድና ግልጋሎት ዘርፍ የራሳቸ ውን የመገበያያ ማዕከሎች በማስፋፋት ፣ ለወገኖቻቸው የስራ እድልን በመፍ ጠርና በግል ለብቻቸው ሆነው ለማደግ ከሚያደርጉት ጥረት ይልቅ በአንድ አካባቢ መሰባሰቡ የተሻለ ውጤት የሚያስገኝ መሆኑን በመረዳት እድገታቸ ውን ሲያፋጥኑ ይታያል። በዚያ በተሰባሰቡበት ማዕከልም የአንድ ጸጉር ቤት ገቢያ ማግኘት ፤ ከጎኑ ላለው የጫማ መደብር ገበያ እንዲያግኝ አደረገ ማለት ነው። ወይም ካጠገቡ ያለው ካፍቴሪያ በወረፋ መጠበቅ ላይ ያለውን ሰው ተ ራው እስከሚደርስ በማስተናገድ ያገለግላል። አልፎ ተርፎም በዚያው ማዕከ ል ለእለት ኑሮ አስፈላጊ የሆኑ ቁሳቁሶችን ከዚያው አካባቢ ከሚገኙ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር በመግዛት ሁሉን አጠቃሎ ወደቤቱ ለመሄድ ይመቸዋ 22

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ል። በዚህም የተነሳ የራሱንም ጊዜና የነዳጅ ወጪ . . . ይቆጥባል ፤ የማህበረ ሰቡንም ኢኮኖሚ በማሳደግ ይረዳል። ከላይ ያየናቸው እነዚህ ኤዥያዎች ወይም ጁዎች እርስ በእራሳቸ ው ቀና የሆነ አመለካከት ባይኖራቸው ኖሮ ፤ ተማምነው እና ተከባብረው ግ ልጋሎት መለዋወጥን ባልቻሉ ነበር። ነጋዴውም የተጠቃሚውን ፍላጎት በ ማርካት ፣ በማክበርና ሊስበው የሚችሉ ነገሮችን በመፍጠር ፤ እንዲዚህ ስ ኬታማ ሆነው እንዲጠቃቀሙ አድርጓቸዋል። በተለያየ ሀገርና ከተሞች የሚ ኖረው ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ቁጥር እንደመብዛቱ በፓለቲካ ፣ በእምነት ፣ በዘር እና . . . የመለያየቱም መብዛት ደግሞ ያሳዝናል። ዳሩ በጋራ ጨምድደ ን “ሀበሻ!” ብለን እንውቀጥህ የምንለው ህዝብ ፤ በጋራ እንደሚጠራው ሲኖር ና ሲሰራ ካልተገኘ እንዴት ሆኖ ነው በወል የሚወቀሰው? ለውጥ እኮ በጋራ የሚመጣ ሳይሆን ፣ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በግሉ ቀና በማሰብና በስደት በ ሚኖርበት ሀገር የሚኖረውን ወንድሙን መርዳቱ ትልቅነት እንደሆነ በማመ ን ሲያደርገው ነው ። ለራሳችንም ሆነ ለሌሎች ቀና አመለካከት ሲኖረን ከላይ የተጠቀሱ ትን ልዩነቶች በማቻቻል እድገትን ማፋጠን ይቻላል። አንድን ግለሰብ ከነዚ ህ ልዩነቶች አርቀን እንደሰው ብንቀበለውና ልዩነቱን ብናከብር እኛም እንደ ሌሎቹ ፈጣን እድገት ይኖረናል። በሌሎቹም ህዝቦችና ማህበረሰቦች ፍጹም የሆነ መቀባበል ወይም አንድነት አለ ማለት ሳይሆን ፤ በጋራ የመኖርን ጥቅም በመረዳት ፤ ከሌሎች ህዝቦች በተሻለ አብሮ መስራትን ለእድገታቸውና ለስኬ ታማነታቸው ይጠቀሙበታል። አንድ ጊዜ በስራ ቦታ በእረፍት ክበብ ውስጥ አብረውኝ ከሚሰሩ አራት የተለያዩ ዜጎች ጋር ሻይ እየጠጣን ስንጨዋወት ፤ እንደ አጋጣሚ ስለተ ለያዩ ህዝቦች መደጋገፍና በጋራ መስራት ተነሳና ፤ ከመካከላችን አንዷ አው ሮፓዊ ሴት “እናንተ ፊሊፒኖዎች በጣም ትረዳዳላችሁ አይደል?” ብላ ፊሊፒ ኖዋን ብትጠይቃት ፊሊፒኖዋ የእነርሱ ዜጋ እርስ በእርሳቸው እንደሚደጋገ ፉ ስትናገር። ከጎኔ የነበረው ፓኪስታን ስለራሱ ዘር ሲመልስ “የእኛ ዜጋ አይ ደጋገፍም። እንደውም ሲሳካልህም ማየትም አይፈልግም” ሲል ሌላይቱ የርሱ ው ሀገር ሰው “እርግጥ ነው! በጣም ነው የምንፎካከረው” ብላ አረጋገጠችል ን። በመልሳቸው ተደንቄ ጥያቄው ወደ እኔ ዞረና እንደምናየው የእናንተ የኢ ትዮጵያ ሰዎች እንኳን ባጣም እንደምትረዳዱ ግልጽ ነው አይደል?” በማለት ቢጠይቁኝ ፤ በውስጤ “ነገሩስ ውስጡን ለቄስ ነው!” ብዬ መቼም እጅ ላለመ ስጠት እንደው በድፍኑ አዎ የሚል ምላሽ ሰጠሁ። ጫወታውን ያነሳሁት እን ዲህ አይነቱ ስለራስ ዘር ያለው ትክክለኛ ያልሆነ ግንዛቤና አመለካከት ያለው በእኛ ማህበረሰብ ብቻ እንዳልሆነ ለማሳየት ነው። በማህበረሰባችን ውስጥ እ ንደሌሎች ዘሮች ሁሉ በአማለካከትም ሆነ በአኗኗር ጥሩም መጥፎም የሚፈ ጽሙ ዜጎች አሉ። ጥሩ ዜጎችን ለማፍራት ከአመለካከታችን ይጀምራል። በቀ ና ብንተሳሰብና ብንተያይ ከሌሎች ዜጎች የምናንስ አይደለንም። በምንኖርበ ት የባዕድ ምድር የአንዳችን ስኬት እና እድገት የሁላችን መኩሪያ እንደሆነ አ ድርገን ብንመለከት ፤ የበለጠና የተሻልን እንድንሆን ይረዳናል። “ ሀበሻ እኮ እ ንዲህ ነው ከምንል “ሰው እኮ” በሚለው አባባል ብንቀይረው ደግሞ የበለጠ ገላጭ ይሆናል እላለሁ። በሉ እንግዲህ ያነበብነውን በልቦናችን ብቻ ሳይሆን ለተግባራችን ያድርግልን እላለሁ። ይርጋለም ሶሩታ


26

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም


ባህል ምንድን ነው?

ሥልጣን ባህልና አገዛዝ ፖለቲካና ምርጫ ከሚለው መጽሀፍ የተወሰደ።

ባህል ምን ማለት ነው? ባህል የተፈጥሮ አይደለም ፤ ባለመሆኑም ከቦታ ቦታ ፤ ከህዝብ ህዝብ ዓይነቱ ይለያያል ፤ እንዲያውም በአንድ ሕዝብ ም እንኳን ከጊዜ ወደጊዜ ይለያያል ፤ ነገር ግን ባህል የሚጀመረው ከተፈጥሮ ፍላጎቶች ላይ ነው። የተፈጥሮ ፍላጎቶች ከጠፈጥሮ ግዲታዎች የሚመነጩ ና ቸው፤ ስለዚህም ባህል የአጠቃላይ ኑሮ መሠረት ነው፤ የተፈጥሮ ባሕሪይ አ ይደለም፤ ነገር ግን ከተፈጥሮ ባሕርይ የሚመነጭ ነው፤ የተለያዪ የተፈጥሮ ፍላጎቶች ፡ በሰው ላይ ተጽእኖ አላቸው። እነዚህን የተፈጥሮ ፍላጎቶች ለማ ሟላት በአለበት ግዴታ ምክንያት ሰው እየለፋ ፤ እየወጣና እየወረደ ኑሮው ን ለማካሄድ ይጥራል ፤ አንዳንዱ የተፈጥሮ ፍላጎት ፋታ አይሰጥም ፤ ከዚያ ም በላይ የማያቋርጥ በየቀኑና በየሰዓቱ እየታደሰ እንደ አዲስ የሚመጣ ፍላ ጎት አለ (ለምሳሌ ረሀብና ውሀ ጥም) አንዳንዴ የአየር ጠባይ የሚለወጥበት ን ወቅት እየጠበቀ የሚመጣ ፍላጎት አለ። አንዱ ሰው ለሌላው ሰው በበጎም ይሁን በክፉ የሚያድርበት ስሜት እንደየስሜቱ የተለያዩ ፍላጎቶችን ይቀሰቅ ሳል። በትኛውም አቅጣጫ ቢመጣ ፍላጎትን ለማስተናገድ የሰው ልጅ ሁሉ ይንቀሳቀሳል። እንደየሁኔታውና እንደየችሎታው ፍላጎቶቹን ለማርካት ይፍ ጨረጨራል። ባህል የሚባለው የዚህ ሁሉ ክምችት ነው። የሰው ልጅ በተፈጥሮና በባህል መሀከል ተወጥሮ፤ ከሁለቱም ጋር እየታገለም፤ በሁለቱም እየታገዘና እየተገነባም ኑሮውን ያካሂዳል፤ ምስል አን ድን መመልከት ነው። በመሠረቱ ባህል ግለሰባዊ ሳይሆን ማኅበረሰባዊ ነው ፤ ኑሮ በሚገ ነባበት ጊዜና ቦታ ሁሉ ባህል ይፈጠራል ፤ እንደምግብ ፤ ልብስና መጠለያ ባ ሉ የተፈጥሮ ግዴታዎች ዙሪያ ባህል ይከማቻል ፤ ኑሮ ማኅበራዊ እንደመሆ ኑ መጠን ሰዎች እርስበርስ የሚኖራቸው ግንኙነት በተለያዪ መልኩ ሌላ የባ ህል መከማቻ ይሆናል ፤ ሰዎች በጨዋነትም ሆነ በባለጌነት ፤ በደግም ይሆን በክፋት የሚፈርጁበት የባህል ሚዛን ይኖራል ፤ ማኅበረሰቡ የሚተዳደርበት ሕግና ሥርዓት በግድ አስፈላጊ ይሆናልና አገዛዝ ከዚህ ጋር ተያይዞ የመጣና ባህል ሆኖ ይቀራል። ብዙ ሰዎች ፤ በጣም የተማሩ ሰዎችም ጭምር ባህልን የኅብረተሰ ብ መገነዣ ከፈን አድርገው ይመለከቱታል ፤ ባህል የማይለወጥ ፤ ሊለወጥ የማይገባውና እንደበረሀ ዛፍ ደርቆ የሚቀየር ነገር ፤ የማንነት መገለጫና የክ ብርና የኩራት ምንጭ ያደርጉታል ፤ ለእኔ ይህ በጣም የተሳሳተ አስተሳሰብና አመለካከት ነው ፤ ይህ ዓይነቱ አመለካከት የሚራባበት ምክንያት ሁለት ብ ቻ ይመስለኛል ፤ አንዱ ምክንያት አለማሰብ ነው፤ የወረሱትን ሁሉ እንደልዪ ሀብት እያደረጉ በመቀበልና አፍተልትሎ ባለማየት በጎውንና ክፉውን ለይቶ አለማወቅ ነው፤ ሁለተኛውና ዋናው ምክንያት ግን ብልጠትንና ተንኮልን ያ ዘለ ነው ፤ የደላቸውና የተመቻቸው ለመዝረፍ ፤ ለመግዛት ፤ ከሕግ በላይና

ከሰው በላይ ሆነው እንደልባቸውና እንደፈቀዳቸው ተንደላቅቀው ለመኖር የሚፈልጉ ሰዎች ባህል የሚባለው ነገር ይመቻቸዋል ፤ እንደ ሕግም ያውጁ ታል ፤ አንዳንድ ለነሱ የሚጠቀማቸውን ቅጽል ሰው ላይ በመለጠፍ ከሰው ነት ደረጃ ያወጡትና የሕግ ከለላን እንዳያገኝ ያደርጉታል ፤ ለምሳሌ ሴቶችን መደብደብና ማጥቃት ተገቢ እንደሆነ አድርገው ያውጁታል ፤ ስለዚህም መ ጥለፍ ወንጀል መስሎ አይታያቸውም ፤ ስለዚህም ሴትን ከሰውነት ደረጃ ማ ውጣትና የሕግ ከለላ እንዳታገኝ ማድረግ ልማድ ይሆናል ፤ ሴቶችም በውድ ም ይሁን በግድ ይህንን እየተቀበሉ ያድጋሉ፤ ለልጆችም እንዲሁ ሌሎች ቅ ጽሎች ይሰጣቸውና እንደፈለጉ ለመግራት ያስችላቸዋል ፤ ሌሎች ሰዎችን ባ ሪያ፤ ቀጥቃጭ ፤ ጠይብ ፤ ፉጋ … እያሉ አንዳንድ ቅጽል በመለጠፍ ከሰውነ ት ደርጃና ከሕግ ከለላ አስወጥተው ለጥቃት ያመቻቿቸዋል ፤ በአለፉት አር ባ ዓመታት ውስጥ እንኳን በደርግ የአገዛዝ ዘመን አድኃሪ ፤ አሁን በወያኔ ዘ መን ደግሞ ነፍጠኛ ፤ ኪራይ ሰብሳቢ … የሚባሉ ቅጽሎች ሲወጡና ለጥቃት ሲዘጋጁ አይተናል። ማናቸውም ማህበረሰብ ሕግንና ስርዓትን በግድ ይፈልጋል ፤ አለ ዚያ ጠዋት ከቤት ወጥቶ ማታ ለመመለስ ከባድ ፈተና ይሆናል ፤ ሠርተው ያፈሩትን የማንም ጉልበተኛ እየቀማ መሥራትን ዋጋ ያሳጠዋል፤ ሕግና ሥር ዓት ከሌለ ማሕበረሰቡ በጉልበተኞች እየታመሰ በሕገ አራዊት ስር የሚተዳ ደር ይሆናል ፤ ይህ እንዳይሆን ማኅበረሰቡ ሕጋዊ ጉልበት ወይም ሥልጣን ያለው ድርጅት ያስፈልገዋል ፤ አንድ ማኅበረሰብ አለሥልጣን አስገዳጅ ኃይ ል ሊኖርና አባሎቹም እንደ ልባቸው ለመሥራትና ለመንቀሳቀስ አይችሉም ፤ አስገዳጅ ሕጋዊ ኅይል ከሌለ በአባሎቹ መሀከል ያለውን የተለያየ ግንኙነ ት በሥርዓትና በመተማመን ሊፈጽሙ አይችሉም ፤ የድሮ አባቶቻቸን በሕ ግ አምላክ ሲባል እንኳን ሰው ውሀ ይቆማል ሲሉ በማኅበረሰባዊ ኑሮ የሕግ ን አስገዳጀነት ለማመልከት ነው ፤ ማኅበረሰቡን በሕግ አስገዳጅነት ማስተዳ ደር ማኅበረሰቡን አስገድዶ ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት በጣም የተለየ ነ ው ፤ እንዲያውም የሰዎችን ኑሮ ለመቆጣጠር የሚደረገው የጉልበተኝነት ጥ ረት ማኅበረሰቡ የሚያምንበትን ሕጋዊ ስርዓት ያፈርሰዋል ፤ ስለዚህ ሁሉ ም ሲመቸው ሕግን ይጥሳል ፤ አንዱ ሰለሌላው ሰው ማሰብን ያቆማል ፤ በቅ ን መንፈስ ከመተሳሰብ ይልቅ በግዴታ መጨካከን ያስከትላል። አገዛዝ ባህል ይሆናል:: አገርን መግዛትና ሕዝብን መግዛት በአን ድ በኩል የገዢዎች የማይበርድና ሥርዓት-አልባ ፋክክር ባህል ሲሆን፤ በሌ ላ በኩል ደግሞ ሕዝቦች የጉልበተኞች መጫወቻ እየሆኑ የአቅመ-ቢስነትና ጸጥ-ለጥ ብሎ የመገዛት ባህል ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወረሰ ሲተላለ ፍ ፤ ሁለት ተቃራኒ ባሕርዮች የገዢነት ባሕሪይ ለገዢዎቹ ፤ የተገዢነት ባሕ ርይ ለተገዢዎቹ ባህል እየሆኑ ይወረሳሉ ፤ በአጠቃላይ ሲታይ ይህ ያልሰለ Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

27


ጠኑ ሕዝቦች ሁሉ ተመሳሳይ ባህል ነው ለማለት የሚቻል ይመስለኛል ፤ ለዚህ አንድ ጥሩና የማያ ከራከር ምሳሌ በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ግፍና ጭቆና ነው ፤ ይህንን ግፍና ጭቆና ሴቶችም ወን ዶችም እንደባህል እያዪ ለብዙ ዘመናት ተቀብለ ውታል ፤ ከአንድ መቶ ዓመት በፊት በብሪታንያ ሴቶች እንደዕቃ ይቆጠሩ ነበር ፤ በህንድ አንድ ሴ ት ባሏ ሲሞት አብራው ትቀበር ነበር ፤ እስከ ጥቂ ት ዓመታት ድረስ በስዊትዘርላንድ ሴቶች የመም ረጥ መብት አልነበራችውም ፤ በሌላ በኩል ደግ ሞ ከሃምሳ ዓመት በፊት በመላው አውሮፓና በአ ሜሪካ ጥቁሮችን ከሰው በታች አድርጎ መመልከ ትና ባሪያ ማድረግ ባህል ነበረ ፤ እነዚህ ባህሎች የሰውን ልጅ የአእምሮና የመንፈስ እድገት የገቱ ነ በሩ ፤ በኢትዮጵያም ቢሆን ባሪያ መፈንገል፤መሸ ጥና መለወጥ ፤ ለሙሽሮች እንደስጦታ ማበርከ ት የሚኮራበት የአገዛዝ ባህል ነበር፤ ይህንን እኔ በዕድሜዬ ደርሼበታለሁ። ሴቶችን በአጠቃላይ እንደዕቃ በመቁ ጠር፤ በጦርነትም ይሁን በሕግ-አልባነት ሰበብ እ የፈለጉ ሰዎችን ወደባርነት በመለወጥ ማኅበረሰ ቡ በጣም እንደሚጎዳ ለመገመት ከአራት መደ ብ በላይ የሂሳብ እውቀትን አይጠይቅም፤ አገዛ ዝ የተለያዪ ስሞችን እየሰጠ ከመብት ውጭ፤ከ ሕግ ውጭ፤ ከማሕበረሰቡ የእድገትና የመሻሻል ዓላማ ውጭ የሚያደርጋቸው ዜጎች አምራችነታ ቸውም ፍጆታቸውም ዝቅተኛ ነው፤ አገዛዝ ሕዝ ቡ በሙሉ ደሀ ቢሆን አይጠላም ምክንያቱም ደ ሀ በትንሹ ጸጥ ለጥ ብሎ ይገዛል፤ ከደሀ የሚፈለገ ው ጉልበቱ ብቻ ነው፤ ጠቃሚነቱ ጉልበቱን እያ ከራየ ሆዱን በከፊል እስከሞላ ብቻ ነው፤ የጠገበ እንደሆነ ችግር ይፈጥራል ተብሎ ይፈራል፤ ይህ ሁሉ የማኅበረሰቡ ሸክምና የእድገት ማነቆ ባህል እየተባለ ይቀጥላል።

ባህል ማለት ምን ማለት ነው?

ሀ. አንዳንድ ሰዎች ባህልን እንደረጋ ውሃ ይመለከቱታል ፤ ከውጭ ምንም አይገባበት ም ፤ ከውስጥም ምንም አይወጣውም። በእኔ አ ስተያየት ይህ የተሳሳተ ግምት ነው። ለ. አንዳንዶቹ ሰዎች ደግሞ ባህልን እ ንደዘመን አመጣሽ ወግና ፈሊጥ አድርገው ይገም ቱታል። በዚህ አስተያየት ባህልን ዘመን ይፈጥረ ዋል፤ ዘመን ይደመስሰዋል። ይህም በእኔ አስተያ የት ትክክለኛ ግምት አይደለም። ሐ. እኔ ባህልን የምመለከተው እንደ መሰረት ነው። መሠረቱ የጠነከረ ቤት ከባድ ግ ርግዳና ጣራ ለመሸከም እንደሚችልና ከማናቸ ውም ዓይነት የውጭ ኃይል ሊያድን እንደሚች ል ጠንካራ ባህልም ኅብረተሰቡን ፤ ሕዝቡን ፤ ከ ማስተሳሰሩም በላይ ፤ የውጭ ሃይልንም ለመመ ከት የሚችል መሆን አለበት። የቤቱ ግድግዳ እ ንዳይሰነጣጠቅ ፤ ጣራው እንዳይወድቅ ከተፈለ ገ መሰረቱ መታደስ አለበት። ፎቅ ቤት ለመስራ 28

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ት ከተፈለገም አዲስና በጣም ጠንካራ መሰረት ያ ሻል። ለምድር ቤት በተሰራው መሰረት ላይ ፎ ቅ ቤት መሞከር አደገኛ ድካም ነው። ስለዚህ ባ ህል እንደረጋ ውሃ የሞተ የሚበሰብስና የሚያፍን ነው ማለት የተሳሳተ ግምት ነው። የሕያው ህዝ ብ ባህል ሕያው መሆን ብቻ ሳይሆን፤ ሕይወትን የሚያድስ መሆን አለበት። ባህልን ዘመን አመጣ ሽ ነገር ነው ያልን እንደሆነም ባህልን በአንድ ዘመ ን ወይም ባንድ ትውልድ ልንወስነውና ዋናውን የማስተሳሰርና የመሠረትን ባሕሪይን ልንነሳው ነ ው። ይህንን ከተረዳን ባህል አራት ዋና ዋና ቁም ነገሮችን ያዘለ ሀሣብ ሆኖ እናገኘዋለን። ሀ. አንደኛው ቁም ነገር የባህል መሠረ ትነት ነው። ባህል መሠረት በመሆኑ የአንድ ሕ ዝብ ወይም ኅብረተሰብ ያለፈው ታሪኩ፤የአሁኑ ኑሮውና የወደፊት አላማው የተገነባበት መነሻ ነ ው። ለ. ሁለተኛው ቁም ነገር የባህል ሰንሰ ለትነት ነው። ሰንሰለት የሚሆነው ብዙ ቀለበቶች እርስ በርሳቸው ሲቆላለፉና ሲያያዙ ነው። እንዲሁም አንድ ሕዝብ ወይም ህብረ ተሰብ በትውልድና በአስተዳደግ በሀብትና በኑሮ ደረጃ፤ በቋንቋና በሃይማኖት የተለያዪ ወገኖችን ሁልጊዜም የሚጠቀልልና በአንድ መሠረት ላይ የ ቆሙ መሆናቸውን የሚገልጽ ሀሳብ ነው። በአን ድ ዓይነት ልዪነት ብቻውን የአለው ወገን እንደአ ንድ ቀለበት ሆኖ፤ ብዙዎች ወገኖች እንደብዙ ቀ ለበቶች የተያያዙበትና የተሳሰሩበት ሰንሰለት የባ ህል ባሕሪይ ነው። ሐ. ሦስተኛው ቁም ነገር የመለየትና የ መከላከል ነው። አንድ ባህል በአንድ መሠረት ላ ይ ቆሞ እንደሰንሰለት የተያያዘውን ሕዝብ ወይ ም ኅብረተሰብ ከሌላው ሕዝብ ወይም ኅብረተሰ ብ የሚለይበትን የግሉ የሆነ መልክ አለው። ው ስጥ ያለውን ሲያስተሳስር ከውጪ ከባዕዱ ጋር ደግሞ ይለየዋል ማለት ነው። ይህ ብቻ አይበቃ ውም፤ ሰንሰለቱ እንዳይላላና እንዳይፈለቀቅ ከው ጭ ወይም ከባዕድ ባህል ይከላከላል፤ የውጪው ን ወይም የባዕዱን እያናቀ የራሱን ከፍ ከፍ ያደር ጋል፤የውጪውን እያጥላላ የራሱን ያዋድዳል። መ. አራተኛው ቁም ነገር ደግሞ ለው ጥ የመቀበል ችሎታ ነው። ምንም እንኳን እያንዳ ንዱ ባህል መሠረቱ እንዳይናጋበትና ሰንሰለቱ እ ንዳይላላበት ከባዕድ ባህል በጉልህ ለመለየትና በ ንክኪት ሊገባ የሚሞክረውንም የውጭ ተጽዕኖ ለመከላከል ቢጥር በተለይ አሁን በምንኖርበት ዘ መን ይህ በጣም ከባድ ነው። የመገናኛና የመመላ ለሻ ዘዴዎች ስለተስፉፉ እየተዘዋወሩ ልዪ ልዪ ባ ህሎችን በማየትም ሆነ ወሬ በመስማት አንዱ ሕ ዝብ የራሱን ባህል ከሌላው ባህል ጋር እያወዳደ ረና እያመዛዘነ ድካሙንም ኃይሉንም ለመገመት ይገደዳል። የእውቀትን ኃይል የምንረዳው እዚህ ላይ ነው። የተሻለ የበለጠ ነገር መኖሩ ከታወቀ በኋላ አለመሻት ተስፋ የሌለው ድንቁርና ይሆና

ል። ስለዚህ አንድ ባህል ድካሙንና ኃይሉን በመ ረዳት ድካሙን ለመቀነስ ኃይሉን ለማጠናከር አ ልፎ አልፎ እየመረጠ ለውጥን የመቀበል ችሎታ እንዲኖረው ያስፈልጋል። አለዚያ ሕያው መሆኑ ቀርቶ የሞተ ይሆናል፤ ኑሮውን የሚያድስ መሆኑ ቀርቶ እንድገትን የሚቀጭ መሻሻልን የሚያፍን ይሆናል።

ባህልና ፖለቲካ

ባህል ምን ማለት እንደሆነ ከሞላ-ጎደል በሁለተ ኛው ምዕራፍ ገለጨዋለሁ በመጨረሻም ላይ “ባ ህል የግል ሳይሆን የህብረተሰቡ የኑሮና የለውጥ መሳሪያ ነው!” ብያለሁና ከዚያ እንጀምር ባህል የ ግለሰብ አለመሆኑን ያህል ፓለቲካም የግለሰብ አ ይደለም። ፓለቲካ ማህበራዊ ነው ፡ፖለቲካ የሚ ጀምረው ከሰው ልጆች እኩልነት ነው። ፓለቲካ የሚጀምረው የአንድ አገር ዜጎች እኩልነት በታወ ጀበትና በተግባር ስራ ላይ በዋለበት ነው። የሰው ልጆችና የዜጎች እኩልነት ባልታወጀበት ፓለቲካ አልተጀመረም።ሰላማዊና ሕጋዊ የስልጣን ሽግግ ር ባልተጀመረበት ፓለቲካ የለም። የስልጣን ወን በር በጠመንጃ ኃይል ብቻ በሚወጣበት ፓለቲካ የለም፤ምንም አይነት ልዪነት ሳይኖር ዜጎች ሁሉ በአንድ ሕግ ጥላ ስር ለሕግ ተገዠዎች ባልሆኑበ ት ፓለቲካ የለም፤አንድ አመለካከት ብቻ በነገሰበ ት፤አንድ እምነት ብቻ በሚሰበክበት አንድ ሰው ብቻ ሉዓላዊ ኃይል ይዞ ማኅበረሰቡን በሚያሽከ ረክርበት ፓለቲካ የሚባል ነገር የለም። ፖለቲካ በውይይት እና በክርክር በሚጣጣሙ ልዪነቶች ላይ የተመሰረተ ማኅበራዊ የኑሮና የእድገት፤የለ ውጥና የመሻሻል መሣሪያ ነው፡ ግለሰቦች በእግዚአብሔር ስም ወይም በጠመንጃ ኃይል ስልጣን ላይ በተቆናጠጡበት አገር ዜጎች የሕግ ሳይሆን የሰው ተገዢዎች ናቸ ው፤ዜጎች የኑሮና የለውጥ መሣሪያ የላቸውም። የኑሮና የለውጥ መሣሪያ በትእዛዝ መልክ ከላይ ይዘንብላቸዋል። የዜጎች እኩልነት በሕግና በተግ ባር ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ዜጎች በማኅበር ተደ ራጅተው ኃይላቸውን የሚያጠነክሩበትና የጋራ ጥቅማቸውን በኅብረት የሚያዳብሩበት መንገድ የለምና በበላይ ትእዛዝ ብቻ የሚሽከረከሩ ናቸ ው። እንዲህ ያለው የጌታና የሎሌ ሥራዓት ለብ ዙ ምዕተ-ዓመታት ሲሠራበት በመቆየቱ ብቻ ባ ህል ይሆናል፡ የምዕራቡ ዓለም እየተለወጠ መሄድ ከጀመረ ቆይቷል ፤ እ.ኣ.አ በ1215 በብሪታንያ ማ ግና ካርታ የተባለው ሰነድና በ1689 የወጣው የ መብቶች አዋጅ የተባለው ለምዕራቡ ዓለም ዓይ ኑን የከፈቱ መሠረታዊ ሰነዶች ናቸው፤በኋላ በአ ሜሪካ የነጻነት አዋጅና(1776)ሕገ መንግሥታቸ ው (1789) አዲስና በጣም ሰፋ ያሉ ዓለም-አቀፍ ይዘት ያላቸውን የመብት ሀሳቦች የሚያስተጋቡ ነበሩ ፤ በዚያው ዓመት ፈረንሳዮች የሰው ልጆች ና የዜጎች መብቶችን አዋጅ አወጡ፤እንግዲህ ም


ዕራቡ ዓለም በስድስት መቶ ዓመታት ጊዜ ውስ ጥ የአገዛዝን ባህል እየገዘገዘ በማፈራረስ ወደ ዴ ሞክራሲያዊ ሥርዓት ውስጥ ገባ ማለት ነው፤ በ ዚህም የአገዛዝን ባህል እየናደ የዜጎችን ሥልጣን የመገንባቱን ተግባር በቆራጥነት ተያያዘውና በአ ገዛዝ ባህል ምትክ የዴሞክራሲን ባህል እያዳበረ መጣ። የአውሮፓና የአሜሪካ አገሮች የዴሞክ ራሲያዊ ሥርዓትን ለመመሥረት ምዕተ-ዓመታት ፈጅቶባቸዋል የሚል መከራከሪያ የሚያመጡ የ አገዛዝ ሸፋጮች(ጠበቆች) ከአውሮፓና ከአሜሪ ካ ውጭ ያለው ሕዝብ በአርአያ ሥላሴ የተፈጠ ረ አይደለም ብለው የሚክዱ ናቸው። ጥቁር ቆዳ ያላቸው አቀንቃኞቻቸውም በጥቁር ሕዝብ ላይ ንቀት ላላቸው ነጮች በማስረጃነት የሚቀርቡ ና ቸው። የዴሞክራሲን መመሥረቻ ዘመን በማቆየ ት የአገዛዝን ዕድሜ ለማራዘም የሚሹ የሰው ል ጅ በእውቀትና በቴክኖሎጂ(ጥበብ) ፣ በህክምና ፣ በመገናኛና በሌሎች የኑሮ ክፍሎች ባገኘው ድ ል እኛ ተጠቃሚዎች እንሁን ባዮች ናቸው። ዴ ሞክራሲ ከነዚህ የሰው ልጅ ድሎች አንዱ ነውና በሱ ተጠቃሚ ለመሆን ረጅም ጊዜ ያስፈልጋል የ ሚሉ ወይ ዘረኞች ወይ ሕመምተኞች ናቸው። አገረ-መንግሥትን (state) በመመሥረት ኢትዮ ጵያ የአውሮፓ አገሮችን ሁሉ የምትቀድም ቢሆ ንም ዛሬም ከአገዛዝ ባህል የወጣችና የዜጎች እ ኩልነት የተረጋገጠባት አገር አልሆነችም። ዛሬም በኢትዮጵያ የተንሰራፋውና እየተጠናከረ በመሄ ድ ላይ ያለው ባህል የጌታና የሎሌ ነው። የኢት ዮጵያ ሕዝብ ደሀነት የጌታና የሎሌን ባህል ለማ ዳበርና ለማስፋፋት በጣም ይመቻል ። የጌታና ሎሌን ባህል ለማስፋፋት ሁለት ነገሮች ያስፈልጋ ሉ ፤ አንዱ ጉልበት አንዱ ሀብት፤ እንደምንም ብ ሎ የአገሩን ሀብትና ጉልበት መቆጣጠር የቻለ አ ገዛዝ ሕዝቡን ይቆጣጠራል፤በጉልበቱ እያስፈራ ራና ከሀብቱም እየቆነጠረ በማደል ሎሌዎቹን ያ በረክታል። ደርግ ጉልበቱንም ሀብቱንም ለተወሰነ ጊዜ በቁጥጥሩ ስር ያደረገው ለደሀው ተቆራቋሪ በመምሰል አብዛኛውን ደሀውን ሕዝብ ሀብታም ከተባሉትና በጌትነት ወንበሩ ላይ ከነበሩት ጋር በ ማጋጨት ነው። ሀብታሙን አደኽየው እንጂ የደ ሀውን ኑሮ እምብዛም አልለወጠውም፤ በዚህ የ ማርክስና የሌኒን ዘዴ የጉልበትም የሀብትም ባለ ቤት ሆነ፤ አገዛዙን መልካም ቀለም ለመቀባት ሕ ዝቡን እያሰለፈ በይስሙላ ምርጫ የመግዛት ፈ ቃድ ያገኘ አስመሰለ፤ ሕዝቡም ሆድ ሲያውቅ ዶ ሮ ማታ እያለ ድምጹን ጣለ፤ የአገዛዝ ባህል ፤ የ ጌታና የሎሌ ባህል አማራጭ በሌላው ምርጫ ቀ ጠለ ፤ዜጎች ጉልበትም ሆነ ሀብት የሌላቸው በት እዛዝ ብቻ የሚንቀሳቀሱ ግዑዛን የአገዛዝ መሣሪ ያዎች ሆኑ፤በዚህ ባህል ላይ ዴሞክራሲ አይተከ ልም፤አይበቅልምም። ደርግ በማርክስና በሌኒን ፍልስፍና ጉ

ልበትንና ሀብትን ለመጨበጥ የተጠቀመበትን ደ ሀውንና ሀብታሙን የማጋጫ ዘዴ ደርግን የተካ ው ወያኔ/ኢሕአዴግ በዘር ወይም በጎሣ ተካው ና አዲስ አገዛዝ መሠረተ ፤ የአገዛዝ ባህል ለብ ዙ ምዕተ-ዓመታት በተንሰራፋበት ሕዝብ መል ኩን እየለወጠ ቢመጣ ህዝቡ “ያው በገሌ” እያለ ፤ ወይም እግዚአብሔር ፈቅዶለት ነው እያለ ሎ ሌነቱን እያሳመረ ይኖራል። ጮሌዎች የሆኑት ወ ፍራም እንጀራ ለመብላት ጭራቸውን እየቆሉ በ ሎሌነት የመሣሪያነታቸውን ዋጋ ያገኛሉ። በደሀ ሕዝብ መሀከል ለወፍራም እንጀራ ፉክክር ዋና ው የአገዛዝ መሣሪያ ይሆናል፤የየእለቱ ለእንጀራ ፉክክር የሰውነትን ፋይዳ፤የዜግነትን እኩልነት፤የ ኢትዮጵያዊነትን ኩራትና ክብር እየፋቀ ታዛዥ ሎሌዎችን እየፈለፈለ የአገዛዝን ባህል ያጠናክራ ል፤ስለዚህም ጉልበትንና ሀብትን መቆጣጠር ከ ቻለ፤በሰው ህይወትና ንብረት ላይ መወሰን በጣ ም ቀላል ከሆነ፤ ደሀ ማኅበረሰብ ውስጥ ሰዎችን በሆዳቸው ብቻ ወደ ግዑዝ መሣሪያነት ለመለወ ጥ ከተቻለ ከላይ ላሉት የተደላደለ ምቾት ከታች ላሉት ስቃይና ችግር ኑሮ ሆኖ ይቀጥላል፤ከላይ እስካሉ ስቃይና ችግሩ በጭራሽ አይታየም፤ ምሳ ሌዎች ሞልተውና፤ የደርግን ትተን በአለፉት አስ ራ አምስት አመታት ውስጥ ስንት ታዝበናል፤ከወ ያኔ የተለዪትን ታላላቅ አባላት ሲያወጡት በነበረ ው ጋዜጣ የተጻፍውን ያነበበ እስከዛሬ የት ነበሩ? ብሎ ቢገረም አያስደንቅም፤ ላይ የነበሩ ጊዜ ያላ ዪትን ሲወርዱ አዪት! ላይ ሲሆኑ የማይታየው ሲወርዱ ግልጽ ሆኖ ይታያል፤ አቶ ታምራት ላይ ኔ ዛሬ የክርስቶስ ሎሌ መሆኑ የብዙ ሎሌዎች ጌ ታ በነበረበት ጊዜ ያሳየው ትዕቢት ታሪክ አይፍቀ ውም፤ ንስሐውንና እንባውን የሚቀበለው እግዚ ያብሔር ነው፤ ታምራት ላይኔ ወንበሩ ላይ በነበ ረበት ጊዜ ጥፋቱን ተገንዝቦ በፈቃዱ ከወንበሩ በ መውረድ ጥፋቱን ቢያርም ወደትልቅነት ይጠጋ ነበር፤ በወንጀለኛነት ተፈርዶበት ለጥፋቱ ቅጣቱ ን ከተቀበለ በኋላ ጣጣውን የጨረሰ ሰው ነው። ከላይ የሚሆኑት የሚማሩት ከወንበሩ በጉልበት ወርደው ሲታሰሩ ወይም ሲሰድዱ ብ ቻ ከሆነ መማር የሚጠቅምበት ጊዜ አልፎባቸዋ ል፤ከታች ያሉት የሚማሩት ከላይ የተጫኗቸው መልካም ፈቃዳቸው ሆኖ ለነጻነትና ለእኩልነት ሲጋብዟቸው ብቻ ከሆነ ነጻነትና እኩልነት የሚ ማሩበት ጊዜ አይመጣላቸውም። የላይኞቹ በም ቾትና በመንደላቀቅ፤ የታችኞቹ በደሀ ምኞትና ጉ ጉት መማር የሚገባቸውን ሳይማሩት ያልፋሉ። ትውልድም ይህንኑ ባህል እየተቀባበለ አገዛዝና ጭቆና ይቀጥላል። ከላይ ያለው የታችኛውን አበሳ የሚያ ይበት ምክንያት ምንድን ነው ? ብሎ መጠየቅ በ ግድ ወደሌላ ጥያቄ ያመራል፤ ከታች ኖሮ በአበሳ የሚኖረውስ የራሱን ስቃና የራሱን አበሳ እንዴት ይመለከታዋል? ከላይ ከታች ያለው በባህላዊ አ ስተሳሰብ የተቆረቆረ በመሆኑ የተሳሰረና የተያያ

ዘ ነው፤ አንዱ ያለ አንዱ ህልውና የለውም፤ አብ ዛኛው ሕዝብ የባህል ተገዢ በመሆኑ ወይ የአር ባ ቀን እድላችን ነው፤ ወይ የእግዚያብሔር ፈቃ ድ ነው፤ ወይ አለአቅም መንፈራገጥ መላላጥ እያ ለ ራሱን ያድክማል፤ ነጻነትንና እኩልነትን ለራሱ ለማወጅ መከጀል አጉልና የማያዋጣ ጀብደኛነት ይመስለዋል፤ ስለዚህም ጎመን በጤና ባህል የሚ ያደነድነው የኑሮ መመሪያ ይሆናል፤ ስለዚህ የላ ይና የታቹ ገዢና ተገዢው፤ ጨቋኝና ተጨቋኝ ፤ መናጢ ደሀውና ሞልቃቃ ጌታው ተስማምተው በአንድ አገር ይኖራሉ። በነጻነትና በእኩልነት የተመሰረተ ፖለ ቲካ ለጎመን በጤና ስምምነት አይመችም፤ እንዲ ያውም ተቃራኒ ነው፤ በመሰረቱ ፓለቲካ የመብ ቶች አዋጅ ነው፤ የዜጎች የስልጣን ባለቤትነት አ ዋጅ ነው የዜጎች የሀብት ድልድል ባለሥልጣንነ ት አዋጅ ነው፤ የዜጎች ሠርቶ የመኖር መብት አዋ ጅ ነው፤ የዜጎች በጤና ፤በሰላምና፤ በነጻነት የመ ኖር አዋጅ ነው፤ ለዚህ ሁሉ መሠረታዊ የሐገርና የሕዝብ ጥያቄዎች ዜጎች ሁሉ በአንድ አይነት አ መልካከትና አንድ አይነት ሀሳብ አይኖራችውም፤ የፖለቲካ መሠረቱ ይህ ስለአገር አመራር፤ ስለአ ገር ልማትና ስለሕዝብ የኑሮ መሻሻል ተድጋግፎ በአንድነት ለመራመድና ስለዘዴው በዜጎች መሀ ከል የሚከሰተው ልዪነት ነው፤ ይህ ልዪነት የአስ ተሳሰብ ልዪነት ነው፤ የሀሳብ ልዪነት ነው፤ ስለዚ ህ ልዪነቱን በማጥበብና የስምምነቱን አድማስ በ ማስፋት ወደ ጋራ የእድገትና የብልጽግና የማያቋ ርጥ ጎዳና ውስጥ መግባት የሚቻለው በአንድ ዘ ዴ ብቻ ነው፤ በሰላማዊ መንገድና በሕጋዊ ስርዓ ት ንግግር፤ ውይይትና ክርክር ብቻ ነው፤ ጥላቻ ስድብ፤ ድብድብና ጦርነት ፓለቲካ አይደለም፤እ ንዲያውም ጸረ-ፓለቲካ ነው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በረጅም ታሪኩ የ ሚታየው ዋናው ውድቀት ሥልጣንን መግራት ያቃተው መሆኑንና ሰላማዊና ሕጋዊ የፓለቲካ ት ግልን መማር አለመቻሉ ነው። ሰላማዊ ትግልን መማር ስላቃተው በድብድብና በጦርነት ፤ ከዚ ያም መለስ ሲል ጌቶቹ ሎሌዎቻቸውን በሹክሹክ ታና በሴራ እያናቆሩ በመግዛት ነው። የዚህ የባህል ውጤት በአንድ በኩል ስልጣንን ከሕዝብ እየነጠቁ ለራሳቸው የግል ጥ ቅም የሚያውሉ ገዢዎችን ከነሎሌዎቻቸው ሲያ ጠናክር ፤ በሌላ በኩል ሕዝቡን ወደባሰ ደሀነትና ደካማነት በማዋረድ ኢትዮጵያ እንዳታድግና የ ኢትዮጵያ ሕዝብም ኑሮ እንዳይሻሻል ማድረግ ነ ው። ምክንያቱን ለመረዳት አስቸጋሪ አይደለም፤ የሎሌነት ባህል የሰውን ልጅ አእምሮ ያደነዝዛል የሰውን ልጅ የሕያውነት መንፈስ ይገድላል፤ የሰ ውን ልጅ ህሊና ወደ ግዑዝ መሣሪያነት ይለውጣ ል፤ የእያንዳንዱ ዜጋ ሉዓላዊነትና የራሱን እድል በራሱ የመውሰን መብቱ ይጠፋል፤ ልዩነት ከሉ ዓላዊና ራሳቸውን ከቻሉ ዜጎች ነጻ አመለካከትና ሀሳብ እየመነጨ በውይይትና በክርክር መፍትሔ Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

29


ን እያስገኘ ወደ እድገት የሚገፋ ሳይሆን፤ ገዢዎች ለራሳቸው ጥቅም ሲሉ በሚፈ ጥሩትና በዜጎች ላይ በሚጭኑት መፍትሔ በሌላው የሚያነታርክ ልዩነት ላይ ይሆ ናል። እንደዚህ ያለው ባህል በሚለመልምበት አገር እውቀት ይጫጫል፤ እውቀት ዋጋ ያጣል፤ ጮሌነትና ታዛዥነት ዋና የወፍራም እንጀራና የክብር ምንጮች ይሆ ናሉ፤ የሥልጣን ምንጭ አንድ ሰው፤ የእውቀት ምንጭ አንድ ሰው በሆነበት የአገ ር እድገትና ልማት፤ የኑሮ መሻሻልና ብልጽግና ከየትና እንዴት ብሎ ሊመጣ ይችላ ል? የእውቀት ዘርፉና ምንጩ ብዙ ነው፤ ያንን ምንጭ የሚያደርቅ ባህልና ዘዴ ወ ደእድገትና ልማት አያመራም። ዜጎች ሁሉ በእኩልነትና በነጻነት ቆመው አንገታቸውን ቀና አድርገው ያ ለምንም ፈርሃትና ስጋት ሀሳባቸውንና እምነታቸውን በአደባባይ የሚገልጹበት ማ ኅበረሰብ በእያንዳንዱ ዜጋ ሕያው የአካል፣ የአእምሮና የመንፈስ ግፊት እንቅስቃ ሴው የሚራመድበትና የወደፊቱ ታሪክ የሚጠነጠንበት የፖለቲካ ስርዓት ያለው ነ ው። ፖለቲካ የተለያዩ ሀሳቦችና አመለካከቶች ሰላማዊና ሕጋዊ ውድድር ነው። ፓ ለቲካ የሕዝብ ሉዓላዊነትን መግለጫ ነው። ፖለቲካ ሕዝብ የአገሩ ባለቤትና የመ ጨረሻው የሥልጣን ምንጭ መሆኑን ማረጋገጫ ነው። ፖለቲካ ሕዝብ ከቀረቡለ ት አማራጮች መሀከል እየመረጠ በድምጹ መንግስትን መሾምና መሻር የሚችልበ ት መሣሪያ ነው። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ወደ ፖለቲካ ሲገባ ከልጅነት እስከ እውቀት በ ውስጡ የተመረገውን የጌታነትና የሎሌነትን ባህል ፍቆ ፈቅፍቆ ማራገፍ አለበት። የግድ የአስተሳሰብ የጽዳት ዘመቻ ያስፈልገናል። የዓላማን ማጥራት ዘመቻ ያስፈል ገናል። በግድ የእኩልነትና የነጻነት አራማጆች ለመሆን በቁርጠኛነት መንሳትና ማ ሳየት ያስፈልገናል። በብዙዎች የተቀናቃኝ መሪዎች ላይ የሚታየው የድሮው መኳ ንንትና መሳፍንትን ለመምሰል የመሞከር ጠባይና ከዚህም ጋር ተያይዞ ሎሌዎች ን በገንዘብም ሆነ በወደፊት ተስፋ እየገዙ የአገዛዝን ባህል ለማራመድ የሚደረገው ሙከራ የፖለቲካውን ስርዓት አይራመድም። ጥረቱ ሁሉ በስልጣን ላይ ያሉትን ሰ ዎች ለመለወጥ እንጂ ስርዓትን ለመለወጥ አይመስልም። ሕዝቡም ይህንን የተቀና ቃኝ ቡድኖች በግል ጥቅም ላይ ያተኮረና ከአገዛዝ የማያወጣ ዓላማ እየተገነዘበው መሆኑን ባለፈው ምርጫ ምልክት የሰጠ ይመስላል።

30

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም


መቼም ሰው ነኝና በህይወት ጎዳና ብዙ ጊዜ ወድቄ ተነስቻለሁ። እንደ ልጅነቴ በአካል ብቻ ሳይሆን ብዙ ጊዜ በገንዘብ፣ በ ንብረት በግንኙነትና በመንፈስም ውድቀት ደርሶብኛል ። ዛሬ ግን ከዚህ ሁሉ መውደቅ ና መነሳት በኋላ ራሴን ችዬ ለመቆም በቃሁ። አወዳደቁና በውድቀቱ ላይ የሚደርሰው ጉዳ ት ቢለያይም ፤ በህይወት ጉዞ ውስጥ የመው ደቅና የመነሳትን ነገር የማያውቅ ያለ አይመ ስለኝም። ለዚህ ነው ይህ ልምዴ ያስተማረኝ ን ለመቆም የረዱኝን አምስት ነጥቦች ላካፍላ ችሁ የተነሳሁት።

ን ማስወገድ እንዳለብን ሳይሆን ፤ አሁን ምን ማድረግ፣ ምን መፍጠር፣ የት መድረስ እንዳ ለበን ማሰብ ነው። ራሳችንን መጠየቅ የሚገ ባን የጀመርነው አዲሱ የህይወት ልምምድ እ ንዴት ይዞናል? እንዴትስ ነው ቀለል አድርጌ የለት ተለት ህይወቴ ልምድ ላደርገው የምች ለው? የሚሉትንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ነ ው።

ሀ/ ይህ ሰው ያለኝን ሀሳብ፣ ህልሜ ን ፣ችግሬን ማንኛውንም ሚስጥሬን ላዋየው የምችል ሰው ነው? ለ/ ደስተኛ በማልሆንባቸው ቀናት ና ወደጥንት ልማዴ ብመለስ ወይም ብወድ ቅስ ሊያበረታታኛና ሊያነሳኝስ ይችላል? ላ ምነውስ እችላለሁ? ሐ/ ይሄ ሰው ለሌሎች ያ ለው አመለካከት እንዴት ነው? ቀናና ደግ አ ሳቢ ነው? ወይስ ሰዎችን የሚያንጓጥጥ ፣ ዝ ቅ ዝቅ የሚያደርግ ፣ የሚያጣጥልና ዘወት ር ስለሌሎች አሉታዊ አመለካከት ያለው ነ ው? ታዲያ እኔስ እንዲህ አይነት ጥያቄዎ ች ቢቀርቡልኝ ለሌሎች እንዲ ህ አይነቱ ሰው መሆን እችላ ለሁ? ከላይ እንደጠቀስኩት ይህንን አሟልቶ አይዞህ በ ርታ ትችላለህ እያለ የሚያ በረታታ ሰው ብናገኝ እን ኳን የህይወት ውጣ-ው ረድ አድካሚና አስቸጋ ሪ መሆኑን በመረዳት ጥ ንካሬ የምናገኝባቸውን አ ማራጭ መንገዶች በመሉ ማጠናከር ያፈልጋል።

1ኛ/ ኛ/ በማንኛውም ረገ ድ ለለውጥ ስንነሳ ለዚያ ላሰብ ነው ጉዳይ በሙሉ ልብና በ ቁርጠኝነት እራስን አሳልፎ መስጠትን ይጠይቃል። ከ ነበሩበት አዘቅት ለመውጣ ት፣ አንድን ነገር ከግብ ለማ ድረስ፣ ውጤታማ ሆኖ በ ብቃት ለመኖርና ለመለወ ጥ መሰጠት. . . በግማሽ ል ብ ሆኖ እየተጠራጠሩ ሙሉ ለሙሉ ግብ መምታት አይቻ ልምና። በሙሉ ልብ ቁርጠኛ 5ኛ/ በተጨማሪም የትምህር ውሳኔንን መወሰን ይፈልጋል። ት ፣ ስልጠና ፣ ወይም በዚህ በ ኛ/ በሙሉ ልብ በቁርጠ 2ኛ/ ያዝነው ጉዳይ ላይ የሚሰጡ ወርክሾፖች ኝነት የተነሳንለትን ዓላማና ጉዳይ ምን ማድ ና ፕሮግራሞች ያስፈልጉናል። ዛሬ የተለያ ረግ እንደሚገባን ማወቅና መገንዘብ ያስፈል ዩ ድህረ ገጾች የተለያየ መረጃዎችን ፣ ወር ጋል። ምክንያቱም የለውጥ መንገዳችንን በት ክሾፖችንና ኮርሶችን በእርዳታ መልክና በነፃ ላንት ልምዳችንና እውቀታችን ላይ ተመርኩ ይሰጣሉ። ከቤታችን ሳንወጣ ሌሎች ጉዳዮ ዘን የምንጓዝ በመሆኑ ፤ ያን የተለመደ አሮ 4ኛ/ እርዳታ ሊያደርግልን የሚችል ሰው ከጎ ቻችንን እየፈጸምን እንኳ መከታተል እንችላ ጌ ልምድ በመደጋገም አዲስ ነገርን ለመፍጠ ናችን ያስፈልጋል። ከቤተሰብ ወይም ከምን ለን። ድጋፍናከፍተኛ መሪነትስለሆነ በቀላሉ በቅጡ እንዲረዱ ልጅየባለሞያ የማወቅ ፍላጎት ብቻወዳ ሳ ርም አስቸጋሪልጆቻችን በመሆኑ ዓለምን ነው። አንዳንዴ ምን ያስፈልጋል። ይህንንም ስል ዓለማችን የምታስደንቅና የሰው ቀርበው ጓደኛ ይህንን የጀመርነውን ለውጥ ሰብንበት ቦታ እንድንደርስና እንድንጠነክር፣ ይሆን የወዲፊቷን ዓለም የተሻለ ፕላኔት ለማድረግ እንዲችሉም በመመኘት ጭምር ነው። ም ጠንካራ ብንሆን በዚያ በድሮ ልምድ መ ሊያበረታታን በተ እንደምንችል መንገዳችንም ቀናናእውቀት ቀላል እንዲሆን ወደኋላ ካለፉመመልከት ስህተቶቻችን ታርመን ወደስ ተሻለ በሀሳብ መንገድ ሊደግፍ ለመጓዝ ፤፣ማን እንደሆንንናወይም ምን ማድረግ ለመረዳት ያስፈልገናልይረዳና ።ሰ ዳከምና ሊያጋጥመን ብዓዊ ፍጡር ፍጹም ባለመሆኑ የምንፈጽማቸው ማንኛውም ድርጊቶች ውጤት ባካባቢያችን ያሉትን መሰል ፍጡሮች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ስለ ለያዩ መንገዶች ሊያግዘን የሚችል ሰው ያስ ል። አስታውሱ የጀመርነውን የለውጥ መንገ ለሚችል ፤ ወደዚያ ወደድሮ ልምዳችን እንድ ሚነካ የሌሎችን መብት በማክበር ፣ በጥንቃቄ በመቻቻል ፣ በሰላም መኖርን ማወቅ ሰብዓዊነት ያስፈልጋል። “መስታ ፈልገናል። አንዳንዴ ቤተሰብ ወይም ጓደኛ ስእንደሆነድለትውልድ በትላንት ማስጨበጥ ልምድና እውቀት በመጓዝ ፤ በአ ንመለሰ የሚገፋን ነገሮች ምን እንደሆኑ ፣ ለ ወት ቤት ያለው ድንጋይ አይወረውርም እንዲሉ።”ለሆነ ብቻ የጀመርነውን ወይም ያሰብነውን ሮጌ የህይወት ምልልስ አዲስ መፍትሄ መፍ ምንስ ልናደርጋቸው እንደምንፈልግ ፣ በምን ትውልድ ስለሀገሩ፣ ስለወገኑ የሚያስብናጉዳይ የሚቆጭ እንዲሆን ፦ ከቤት ውስጥ አቋም ያለው በመልካም ግብረገብና ስነምግባር ሊያንጸው ከ ሊደግፈን ይችላል ማለት ግን አይደለ ጠር አስቸጋሪ በመሆኑ ፤ ትምህርትና ስልጠ አይነት ሁኔታ ፣ ጊዜና አጋጣሚ ለማድረግ እ ሚችል ወላጅ ጀምሮ ያገር ሽማግሌ ፣ የሀይማኖትም። መሪ ባጠገባችን ፣ ቀናና ራዕይካሉ ያለው የሀገር መሪ ፣ እንዲህ በውቀትና በሞያቸው በህብረተሰቡ እድገ ሰዎች መካከል ና አዲስበማህበራዊ የሆኑ ዘዴናኑሮና ስልቶችን ፣ የአፈጻጸም ንደምንገፋፋ ማጤን፣ መገንዘብና ት ላይ ውጤት ያመጡ ፣ የሀገርንናእራሳችን የህዝብን ሀብት የማይመዘብሩ ፣ በውነተኛ የብልጽግና መንገድ በንግዱም ሆነ በተለያዩ የኢኮኖሚ አውታሮች ላይ ፤ አይነቱን ሰው ማግኘት አስቸጋሪ ከሆነ ፤ ተስ ስርአቶችንና መንገዶችን ስለሚያስተምረን ን መጠየቅ በድክመታችን አዎንታዊያስፈልጋል። ለውጥን ያመጡ ፣ እገሌ ሊባሉጊዜየሚችሉፋታላላቅ ድንቅዬ የሀገር ምሳሌ የሆኑ ዜጎችን እያየ ማደግ ይኖርበታል። ሳንቆርጥ ወጥተን አዲስ ሰዎችን በመተዋ እየወደቅን ከምንነሳበት መንገድ ወጣ ብለን ለራሳችን አሳማኝ ፣ ብቃት የሌላ አባትየሚመስሉ አልባ ትውልድ መፍጠር አሳዛኝ ፣ ለሀገር እና ለወገን ጥፋትና ማፈሪያ ታሪክ ማቆየት ነው። በምንኖርባት ዓለም ባለን የተረኛነት ዘመን ወቅ ፣ ጓደኛን በማፍራት የተለያየ እርዳታን ባልሞከርነው አዲስ ዘዴና መንገድ አዲስ የለ ቸውና የማይረቡ ምክንያቶችን ለትውልድ ልናወርሰው የሚገባንበመደርደር ፦ ጠንካራና ብቁ የሆነ ዜጋ እንዲሆን ፣ በመከባበር፣ በመተሳሰብ፣ በጋራ በመኖር መልካም መሆኑን ለዚህም ከቂም ር ልናገኝ የምንችልበትን መንገድ መፈለግ ይኖ ውጥ ህይወትን ልንኖር የምንችልበትን መን እራሳችንን ማዘናጋት እንሞክራለ ቆ ይቅር ማዳከምና ማለትን እንዲችል፣ የሌሎች በአፈጣጠርም ሆነ በአኗኗርና በአስተሳሰብ ልዩ መሆን ለዓለማችን ውብት እንደሆነ እንዲያውቅ ፣ ሚዛናዊነትን የ ርብናል። በዚህ የእርዳታ ፍለጋ ወቅት እንዴ ይከፍትልናል። በህይወት ጎዳና ስኬታ ን። ዘወትር ዋናው መመሪያው የለውጡን እንዲሆን፡፡ ጫወታ ህግለትውልድ በመከተ መልካም ነገርን የሚቆይ ትውልድ እንዲሆን ፣ ለሀገር ለወገኑገድ የሚያስብና የወዲፊቷን ዓለም የተሻለ ፕላኔት ት እርዳታ ሰጪውንመልካም ሰው እንደምንመርጥ እ ይከታል ማ ለመሆን እነዚህንከምን? ቁልፍ መንገዶች መሞ ለማድረግ የሚጥር እንዲሆን መንገድ ማስያዝ ያስፈልጋል ። እንግዲህ አባት እጁን ከኪሱ እንዲሉ እጃችን ል እራስን ከጫወታው አለማግለል ነው። ራሳችንን መጠየቅ የሚገባን ነገሮች ይኖራሉ ከሩ ጠቃሚ ነው እላችኋለሁ። ይሳካላችሁ። 3ኛ/በውጥናችን ውስጥ ማስታወስ የሚገባን ዋነኛ ነገር ከድሮው ልምዳችን ምን Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

31


ታሪኩ እንዴት እንደነበር ልተርክላችሁ ሳይሆን ለምፈልገው የመተንፈስ እር ዕስ መነሻ እንዲሆነኝ እንደማስታውሰው ላጫውታችሁ ነው። ይገርማችኋል ባለፈው ሳምንት አይኔን ለመታክም ፤ ከአንድ የአይ ን ዶ/ር መጠበቂያ ክፍል ውስጥ የቀጠሮዬ ሰዓት ደርሶ እስከምጠራ መጽሄት እያገላበጥኩ ስጠብቅ ፤ ድንገት የመጠበቂያው ክፍል በር ተከፍቶ ሁለት ኢ ትዮጵያዊያን የደራ ጨዋታቸውን ይዘው ይገባሉ። ሲያዩኝ በመጠራጠር “ሰ ላም!” ብለውኝ ከፊት ለፊቴ ከነበሩት ሁለት ወንበሮች ላይ አረፍ ብለው ጫ ወታቸውን ይቀጥላሉ። ለጥቂት ቆይታ የያዝኩትን መጽሄት ባገላብጥም ፤ ሳ ላስበው ልቤ በጫወታቸው ተሳበና እነርሱን ማዳመጤን ተያያዝኩት። ከኔ ፊት ለፊት የተቀመጠው ጠይም ረዘም ያለው ልጅ ከሚናገረው ቁምነገር አ ንድ እንኳን ጠብ የሚል ነገ አልነበረውም። ከናካቴው የኔንው ህይወት የሚ ተርክ እስኪመስለኝ ድረስ በንግግሩ ተመስጬ ፤ ሳላውቀው መጽሄቱን ዘግ ቼ እነርሱንው እየተመለከትኩ ጨዋታውን ማዳመጡን ቀጠልኩ። ውስጤን ስለነካው ጭራሽ አንዳንዴ እምህ! እያልኩና አንገቴን በአዎንታ እየወዘወዝ ኩ መስማማቴን ለመግለጽም ሞከርኩ። ወጣቱ ባህላችን በውጪ በምንኖር ኢትዮጵያዊያኖች ላይ እያደረሰብን ያለውን ተጽዕኖ ፣ ችግርና እንዴት ኑሮአ ችን እያከበደብን እንዳለ ነበር የሚያወራው። “አየህ አንዳንዴ ለማንም ይሁ ን ለማን መተንፈስ ያስፈልጋል። እኛ ኢትዮጵያዊያን እንደሆንን በሰው ሀገር ታፍነን ነው የምንሞተው። ከሞትን በኋላ ግን የሚያውቀንም ሆነ የማያውቀ ን ሁሉ እርሱ እንዲህ ይልነበረ ፣ እንዲህ ያስብ ነበር . . . እንዲህ ያደርግ ነበ ር . . . እያለ የሆነ ያልሆነውን ጉዳችንን ይዘከዝካል። ካለቀልን በኋላ! . . . ት ዳራችን ሊፈርስ አንድ ሳምንት ሲቀረው ነው ሽማግሌ የሚገባው። አሁን ባ ለፈው ጊዜ ያቺን ልጅ ገድሎ እራሱን ያጠፋውን ልጅ ችግር አታስታውስም? 34

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ታዲያ እንዲህ ዓይነቱ ምክንያቱ በቅጥ ያልታወቀ አሟሟት በየከተማው ም ን ያህል እያደገ እንደመጣ ልብ ብላችኋል? ለዚህ ሁሉ የምንዳረገው ሁሉን ነገር በሆዳችን አፍነን መኖራችን ነው። “በሽታውን ያልተናገረ መድሀኒት አ ይገኝለትም” እንዲሉ ነው። አታያቸውም የዚህን ሀገር ሰዎች ፤ በጠዋት ስራ ም ላይ ይሁን ጉዳይ ለመጠበቅ ከተሰለፍክበት ቦታ ስትቀላቀል ሰላም ካልካ ቸውና ህይወት እንዴት ነው ካልካቸው ፤ ከተመገቡት አንስቶ ሌሊቱን ከባ ለቤታቸው ጋር እንዴት እንዳደሩ ሳያቀር ውልቅ አድርገው ሰጥተውህ ቴራ ፒያቸውን አድርገውብህ ይሄዳሉ። ከዚያ ትንፍስ ብለው ቅልል ብሎአቸው ቀኑን በሰላም ስራቸውን ሲሰሩ ይውላሉ። የቀረም ቢኖራቸው ለመጣው ሁ ሉ እየወተወቱ ሲያራግፉት ውለው ሰላማዊ ስራ ሰርተው ይገባሉ። ከከፋባ ቸውም ወደ ህክምና ባለሞያም ለመሄድ አይፈሩትም። ታዲያ መተንፈሱ ከመታመቅ (ስትረስ)፣ ከጭንቀት፣ በችኩል ካ ልተመከረበት ውሳኔ . . . ያላቅቀናል። መተንፈሳችን እፎይታም ይሰጠናል። ለምን እኔ ብቻ ብለን በዚህ ዓለም ላይ በተናጥል በራሳችን ላይ ብቻ የደረሰ የሚመስለንን ችግር ፤ ሌሎችም ላይ መኖሩን ከመወያየት ልምድ እንድንማር ይረዳናል። በማካፈላችን የተሻለ መፍትሄ ሊያማክረን የሚችል ሰው ሊያጋ ጥመንም ይችላል። ስለዚህ ስደት ላይ መልመድ ከሚገባን ነገር አንዱ እኮ ይህ ነው። ያ! ሲስተም ውስጥ መግባት ከሚባለው አንዱ እኮ መተንፈስ መልመድ አይ መስልህም? እንጂ ቢል መክፈል ብቻ እኮ አይደለም። ደግሞ መርሳት የሌ ለብህ ለጆርጅ ወይ ለስሚዝ ብትነግረው የአቶ እገሌ ልጅ እንዲህ አለኝ ስለ ማይልህ አትፍራ! ታፍኖ ከመሞት መተንፈሱ አይሻልም? ብሎ ወደኔ አይኑ ን በጥያቄ ቢያፈጥ እንዴት አድርጌ ወደ ጨዋታው እንደምገባ በጉጉት እየ


ጠበቅሁ ስለነበር እንዴታ! . . . የምትለው ነገር በ ሙሉ ምንም ሀሰት የለውም አልኩት። ሙሉ ጨ ዋታውን ከነርሱ ጋር እንደነበርኩ ለማረጋገጥ። ታዲያ ሁለቱም እንድቀጥል መፍቀዳቸውን ለማ ሳየት ወደኔ እየተመለከቱ የሚቀጥለውን አስተ ያየቴን ለማዳመጥ በጸጥታ ጠበቁኝ። የተባለውን መተንፈስ እዚያው እነርሱው ላይ ተያያዝኩት። ከየት እናምጣው ብላችሁ ነው? ያደግነው እኮ ዝ ምበል እየተባልን ነው። “አዋቂ ሲጫወት ልጅ አ ይገባም ዝም በል። . . . ደግሞ አንተ ምንታውቃ ለህ! ዝምበል! . . . ሰው ገበናውን እንዴት ለሌላ አሳልፎ ይሰጣል? ዝምበል! . . . ወንድ ልጅ አያ ለቅስም . . . እነዚህና የመሳሰሉ ዝምበሎች! ተደ ራርበውብን ፈንቅለን ለመውጣት እኮ ከብዶን ነ ው። ከዚህም አልፎ ዛሬ በውጪ የሚገኘው የሀ ገራችን ሰው ሚስጥር ብለህ የነገርከውን ነገር ሁ ሉ ሊዘከዝክልህ ስለሚቸኩል ለማንስ ነው የምት ነግረው? “አትንገር ብዬ ብነግረው አትንገር ብሎ ነገረው።” ይባል የለ? ብዬ ሳልጨርስ ካፌ ነጠቅ አድርጎ አየህ መተው ካለብን ነገር እኮ አንዱ እር ሱ ነው። ቅድም ሰምተኸኝ ከሆነ ፤ የዚህ ሀገር ሰ ዎች እኮ አትንገር ብለው አይደለም የሚነግሩህ ፤ እነርሱን ያንተ ለሌላ መናገር ሳይሆን የሚያሳስባ ቸው ጆሮ አግኝተው የነርሱን መተንፈስ ነው። ል ዩነታችንም ይሄ ነው። እንደገና ወደ እውነታው መለሰኝ ። ስለሌሎች አትጨነቅ በዚህ ዓለም ላይ ሚስጥር ነው ብለህ የሚያስጨንቅህ ነገር ሁሉም ቤት ውስጥ አለ ። ትዳር ውስጥ መጋጨቱ ፣ መ ፋታቱ ፣ መጠጣቱ ፣ መቆመሩ ፣ ከሰው መጋጨ ቱ ፣ ገንዘብ ማጣቱ . . . አንዱ የሌላውን እያካበ ደ ሲያዳንቅ ፣ ሲፈርድና እና በሌላው ላይ በመኮ ፈስ ለመከበር ፈልጎ እንጂ ሁሉም እኮ የዕለት ተ ለት ኑሮው ነው። ታዲያ ምኑ ነው ሚስጥሩ? ይ ልቅ መፍትሄው ምንድነው ? የሚለውን ነው መ ያዝ ። አየህ ! መፍትሄው እንደነገርኩህ ከቻልክ ለምትቀርበው ካልቻልክ ደግሞ እንደነርሱ ላገኘ ኸው የየትኛውም ሀገር ዜጋ ቢሆን በቻልከው ቋ ንቋ ተንፍሰው። እፎይ . . . !!! ትላለህ። መተንፈ ስ እያለ ታፍኖ መሞት? እውነትክን እኮ ነው አልኩ እንደው ፈ ሪ ሆንን እኮ። ስለደሞዝህ ፣ ስለትዳርህ፣ ስለፖ ለቲካ ፣ ስለጤናህ . . . ለማውራት ፈርተን ፣ ደ ብቀን ዋሽተን ፤ እንድውም ውሽውቱን ለመሸፈ ን በውሸት ላይ ውሸት እየደራረብን መጨነቅ! እ ንዴት ይሆናል? አይገርምም?! የመጣሁት አይኔ ን ለመታከም ነበር ግን በጠዋቱ ሁለተኛ ህክምና ውስጤን አስተነፈስካት። በል እግዚአብሔር ይ ስጥህ ውዳጄ! ታዲያ ከዚህ በላይ ህክምና የት ይ ገኛል? ብዬ ተራዬ ደርሶ ወደ አየን ህክምናዬ ገባ ሁ እላችኋለሁ ሳለውቀው እኮ ላጫውታችሁ ብ ዬ አሁንም ለናንተ ተነፈስኩት። በሉ እናንተም ለ ሌላ ተንፍሱት። በሚቀጥለው እስክንገናኝ ደህና ቆዩኝ። ወሬ ጠላሁ ከዲሲ


እውነተኛ ታሪክ

ጊዜው ቢረዝምም “የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳ!” እንዲሉ እትብቴ የተቀበረበትን ቀዬ ለቅቄ ስወጣ ፤ በመንገዳችን ላይ ያሰ ቃየንን ያን! የክረምት ወር ዶፍ ዝናብ እና በቆንጥር እየተሰቃየሁ የተጓዝኩትን የእግር ጉዞ ዘለዓለም ከአእምሮዬ ሊያወጣው የሚችል ነገር የለም። አንዳንዴማ ከዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ እንደ ሲኒማ ፍንትው ብሎ ነው የሚታየኝ። በጊዜው በነበረው የደርግ መንግስት ካድሬዎች አሳዳጅነት ፤ የጓደኞቼ መገደልና ከቀጣዮቹ ተገዳዮች ዝርዝር መካከል እንደ ሆንኩ ከቅርብ ጓደኛዬና የጥናት ክበብ መሪዬ ሲነገርኝ ፤ ከሌላ አብሮ አደግ ጓደኛችንና አብሮን በጥናት ሴል ውስጥ ከነበረው ጓደኛች ን ከእሸቱ ጋር ሆነን ሀገር ለቀን ለመጥፋት ወሰንን። ዳሩ ለመንገድ የሚሆን ስንቅ ልንቋጥርበት የሚያስችል የቤተሰብም ሆነ የግል ጥሪ ት ባልነበረን ፤ በዚያ ጨቅላ እድሜ ፤ ወዴት መሄድ እንኳን እንዳለብን ሳናውቅ ፤ እንደው ከመሞት መሰንበት መሻሉን መርጠን ፣ ህ ይወታችንን ለማትረፍ መንደራችንን ለቀን ፤ ወደ ጎረቤት ሀገር ለመጓዝ ወሰንን። ዳሩ ውሳኔያችን በወቅቱ ከተማ ውስጥ ብዙ ወጣቶ ች ላይ የደረሰ በመሆኑ ፤ እንሰማው በነበረ ወሬ እንጂ ስለጎረቤት ሀገሩ ጉዞም ሆነ ኑሮ የምናውቀው ምንም ነገር አልነበረም። ሶሻሊዝም ከሚያደርሰው አስከፊ እስራት ፣ ግርፋትና ግድያ ለማምለጥ በወቅቱ በብዛት ይሞከር የነበረው በጎንደር በኩል ወ ደ ሱዳን መውጣት ስለነበር ፤ በገበሬ ማህበር እንዳትያዝ ረድተው በገንዘብ የሚያሻግሩ አሉ ሲባል የሰማነውን ይዘን ቤተሰብ ሳይሰ ማ፤ የቤተሰቦቻችንን ወርቅና ከቤት ውስጥ ያገኘናትን ለቃቅመን ፣ ለማንም ሳናማክር አንድ ጠዋት ማልደን ወደ ክፍለሀገር አው ቶቡስ ተራ ሄደን ። የጎንደሩን አውቶቡስ ትኬት ቆርጠን ፤ የሀገራችን ጠረፍ አሻግሮ ወደ ሱዳን ይወስዳል የተባለውን መንገድ በጥየቃ መጓዟችንን ተያያዝነው። አይደረስ የለ ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ወደተባለው የሱዳን ሀገር ተወጣ።

38

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2003 2004 ዓ/ም


ዘወትር የእግር ውስጥ እሳት የሆነብኝና አልቅሼ የማይወጣ ልኝ ሀዘኔ ፤ እናቴ የደረስኩበት ባለመታወቁና አንድያ ልጇን ከጎኗ በ ማጣቷ ሀዘን ምክንያት መሞቷን በመጀመሪያው የስደት ሀገር የሰማሁ በት ቀን ነበር። በኋላም በተለያዩ ጊዜያት የቤተሰቦቼን መሞት በተራ በተራ በየደረስኩበት ምድር ተረዳሁት። የመኖሪያ ፍቃድ ባለማግኘቴ ብር ብዬ ሄጄ በቀብራቸው ላይ ተገኝቼ እርሜን እንዳላወጣ አደረገ ኝ። ሀዘኔ በውስጤ ተዳፍኖ እያሰቃየ ኑሮን እንድገፋና ፤ ቆይ አንድ ቀ ን ሲሳካልኝ በሚል ምኞት ጉጉት ዓመታት እያለፉ . . . እንዲሁ እያለ ፉ . . . እንደው እንደወጣሁ ቀርሁ። በኋላ በኋላም የመኖሪያ ፍቃዱን ባገኘውም ፤ በመሰንበቱ ብዛት ፣ የሰውን ሀገር ኑሮ ለምጄውና የቤተሰቦቼም ማለቅ ተደምሮ ወደ ሀገሬ የመመለስ ስሜቴ ሞተ። ታዲያ ዛሬ ከሰላሳ ዓመታት የስደ ት ህይወት በኋላ በምኖርበት ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን፤ ቤተሰ ቦቻቸውን ጠይቀው ሲመለሱ በሚያጫውቱኝ ጨዋታና ጉትጎታ ፤ ዘ መዶቼም ባይኖሩ መቼም ሀገሬ ነውና እንደሰው ያደግሁበትን ሰፈርና አካባቢ ለማየት እንደገና ናፍቆት አገረሸበኝ። ከብዙ የራስ ጋር ክርክር በኋላ ይኸው በዚህ ዓመት እንደምንም ደፍሬ ለአንድ ወር እረፍት ቢ ሆን ለመጓዝ ወሰንኩ።

ሜቱ አንድ የ ማላውቀው እንግዳ ሀገር የገባ ሁ ያክል ነበር የተሰማኝ። ያ! የናፈቀኝ ድ ሮ የጨርቅ ኳስ የተራገጥኩበት፣ ጥቢጥቢ ያን ጠባጠብኩበት፣ ፓስቲና እሸቱን የተናጠቅሁበት ፣ አድጌም ከጓደኞቼ ጋር የሰፈራችን ውሀ ልክ ላይ ቁጭ ብለን ስለአየነው አዲስ ሲኒማም ይሁን ስለዚያ ን ሰሞኑ ኳስ ማንና እንዴት እንዳገባ አቃቂር ያወጣንበ ት፣ ስንከራከርና ስናወጋ የኖርንበትን ሰፈሬን ለማየት ከ መጓጓቴ የተነሳ የያዝኩትን ሻንጣ ሆቴል ክፍሌ ውስጥ ወ ረወር አድርጌ ነበር የወጣሁት። ከዚያ ከማላውቀው የሆቴ ል ህንጻ ወርጄ እበሩ ላይ ከቆሙት ታክሲዎች መካከል አን ዱን ጠርቼ ወደ እድገት ሰፈሬ እንዲወስደኝ ጠየቅሁት “80 ብር ይከፍላሉ” አለኝ። በርግጥ ተጉዘው የተመለሱ ሁሉ የኑ ሮውን ውድነት ፣ የዋጋውን መናር ሲያወሩ ብሰማም ፤ የያን ጊዜው የሀምሳንቲም የታክሲ ጉዞ በዛሬ ኮንትራት ዋጋ ሲነግ ረኝ ደነገጥኩ። ቢሆንም ለነዋሪው እንጂ እኔማ በ17 መንዝሬ ስለምጠቀም ምንም ማለት አልነበረም።

ውሳኔዬን እውን ለማድረግ ውስጤ ብዙ ተሟገተ። አልቀር ም ወሰንኩ። ትኬቴን ቆርጬ በጄ እስካገባሁበት ቀን ድረስ እውነት አ ልመሰለኝም ነበር። ዳሩ እንደማያልፍ የለ ቀኑም ደረሰ። ባለፈው ሳም ንት ቤተሰቦቹን አይቶ የተመለሰ አንድ የማውቀው ሰው ለመሄድ መ ወሰኔን ስነግረው ፤ አርፎበት የነበረ አንድ አዲስ ከተገነቡት መካከል ጥሩ የተባለውን ሆቴል ስልክ አውጥቶ ሰጥቶኝ ስለነበር ፤ ከዚሁ ከአ ሜሪካን ሆኜ በስልክ ማረፊያዬን አዘጋጀሁ። አይደርስ የለ ይኸው ቀኑ ደርሶ ከአስራሶስት የበረራ ሰዓት በኋላ አውሮፕላኑ መሬት ሲነካ ውስ ጤ በጭንቀት ተወጠረ። ለነገሩ የሚቀበለኝ ዘመድና ጓደኛም አልነበረ ም። ከአውሮፕላን ማረፊያው ስወጣ ከቆሙት ታክሲዎች መካከል አ ንዱን ይዤ ወደ ሆቴሌ እንዲወስደኝ ነገርኩት። በመንገዳችን ላይ የማ የው ለውጥ ሁኔታ እያስገረመኝ ፤ ምንም እንኳን የትውልድ ሀገሬ ቢ ሆንም ፣ የማየው ሁሉ የሀገሬን ልጆች መልክና የማዳምጠውም ቋንቋ ዬን ቢሆንም ፤ ከዚህ ሁሉ ዓመታት የስደት ኑሮ በኋላ በመመለሴ ፤ ስ

ያኔም ቢሆን ካገሬ ስወጣ በነበረኝ የእድሜ ገናነት ከም ንኖርበት ሰፈር ለሲኒማ ወይም ካምቦሎጆ ለመሄድ ካልሆነ በቀ ር ከሰፈራችን ወጥቼ ሌላውን የከተማውን ክልል ጠንቅቄ አው ቀዋለሁ ባልልም ። ዛሬ ግን ከተማው እኔ አውቀው ከነበረው ጊ ዜ ጭራሽ ተቀይሯል። ከሰፈሩ ስም እንኳን የማውቀው ጥቂቱን ነው። “የት ሀገር ነው የሚኖሩት?” አለኝ ታክሲውን የሚያሽከ ረክረው ሰው። በእርግጠኝነት ከውጪ ለመምጣቴ ጥርጥር ሳይ ገባው። “ምነው አስታውቃለሁ እንዴ?” ብለው። ሳቅ እንደማለ ት ብሎ ይሉኝታ በተሞላበት አነጋገር ። ማንኛውም ሰው ሊለየ ኝ እንደሚችል ገለጸልኝ። ዳሩ እውነቱን ነው ፤ እኔም ብሆን የህ ዝቡ መጫጫት ፣ የተጎዳ መልክና አለባበስ ፣ በየመንገዱ መብራ ት ላይ የተመለከትኩትን የኔቢጤ ብዛትና ሁኔታ እያብሰለሰልኩ እንዴት አይለዩን አልኩ በሆዴ። “ታዲያስ እንዴት አዩት ሀገሩን? ፈረንጅ ሀገር ቆይተዋ Ethiopia Magazine Issue 3 | 2011 2012

39


ል? ሀገራችን አልተለወጠብዎትም?” አለኝ ለ ነገሩ እኔም እንደርሱው የፈረንጁ ሀገር ታክሲ አሽከርካሪ በመሆኔ ጥያቄዎቹን ብረዳቸውም ፤ ለኔ ግን ዘመድ አዝማዴ ሁሉ አልቀው ብቻ ዬን ከቀረሁበት የትውልድ ሀገሬ ለመጀመሪ ያ ጊዜ ተመልሼ እንዲህ አይነቶቹን ጥያቄዎች ሲያቀርብልኝ ፤ ከቤተሰቦቼ መካከል አንዱ የ ሚያናግረኝ ሆኖ ነበር የተሰማኝ። ቆዩ ወይ? ነው ያልከኝ አልኩና ፈገግ ብዬ አይ ትንሽ ከረ ምኩ እንጂ። ብዬ ሰላሳ ዓመት መኖሬን አጫ ወትኩት። ኡ!!! . . . ሀገሩን አያውቁትማ አለ ተገርሞ ። የጀመረውን ጥያቄ መልሼ ቀሪውን ጉዞ እኔው በጥያቄ አጣደፍኩት። የቻለውን ያ ክል መረጃ ለማሰባሰብ እንደሚፈልግ ጋዜጠ ኛ የቀረኝም አልነበር ። አንድ የትራፊክ መብ ራት ላይ ስንቆም ፤ ድንገት ታክሲ ሲያስፈልግ ዎ ስልኬን ልስጥዎ ብሎ በአንዲት ብጣሽ ወ ረቀት ላይ አስፍሮ ይሰጠኝና ጥቂት ከተጓዝን በኋላ መድረሳችንን ገልጾልኝ ጥግ ሲይዝ ፤ አ መስግኜ ባለፈው መጥቶ የተመለሰው ጓደኛ ዬን ልኬ ለታክሲ ይሆነኛል ብዬ ያስመነዘርኩ ት ሁለት መቶ ዶላር ስለነበረኝ አውጥቼ ያገል ግሎቱንና የጨዋታውን ሁሉ ጨማምሬ ከፈ ልኩ። ገንዘቡን ቆጥሮ ባገኛት ያገልግሎት ዋጋ ደስታ የተመለከትኩትን ፍልቅልቅ ፊትና እጅ አነሳስ እየተመለከትኩ “ሰው ባገሩ ሰው በወን ዙ ቢበላ መቅመቆ . . . የሚለው ግጥም ድንገ ት ወደ አእምሮዬ መጣና በደስታ ኮራ አልኩ ኝ። ከታክሲው ከወረድኩበት ደቂቃ ጀ ምሮ ያን ያደግሁበትን ሰፈር ግራና ቀኝ ባማ ትር ፤ አንድም የማዋቀው ሰውም ሆነ የማው ቃቸው ቤቶች አልነበሩም። ኮረኮንች የነበረ መንገድ በሰፋ አስፓልት ተቀይሮ ፣ ጥንት የተ ማርንበቱ በአስቤስቶስ ተገንብቶ በተለያየ የ ትምህርት አይነት ስእሎች የተዥጎረጎረው ት/ ቤት ፤ ዛሬ ባለ አራት የሸክላ ህንጻና ባለዩኒፎ ርም ተማሪዎች ሲተራመሱበት አየሁ። ከመን ገዱ ዳር የተደረደሩትን አዳዲስ ህንፃዎች አን ዳቸውንም አልውቃቸውም። የሰፈሬን የድሮ መልኩን ለመሳል ሞከርኩ። በመልካም መለ ወጡ ቢያስደስተኝም የናፈቅሁትን የመንደሬ ን አቀማመጥ ባለማግኘቴ ግን ውስጤ ተሰበ ረ። ግራና ቀኙን ሳማትር ድሮ እንቆምባት የነ 40

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

በረች አንድ ኪዮስክ በማየቴ ልክ ድንገት ከ ዚህ ሁሉ ዓመታት በኋላ ዘመዱን እንዳየ እ የተጣደፍኩ ወደ ኪዎስኳ ሄድኩ። “እንዴት አደርክ ወንደም? ባለቤቱ ሲራጅ አለ?” ብዬ ብጥይቀው። ተሳስተዋል ባለቤቱ እኔ ነኝ አለ ኝ። ለነገሩስ ቆይቷል ድሮ ባለቤቱ ሲራጅ ይ ባል እንደነበር ነግሬው ምናልባት አንተ ልጁ ትሆን አልኩ። ልጁም አይደለሁም እኔ ሻሚ ል እባላለሁ ብሎኝ ስራውን ቀጠለ። የምፈል ገውን ሰው ባለማየቴና የጠየቅሁትን ባለማወ ቁ አዝኜ ፤ ከራሴ ጋር እየተግሞቶሞትኩ ቁል ቁል የሚወስደውን ቀጭን መንገድ ይዤ አካ ባቢውን በእግሬ መዘዋወሬን ቀጠልኩ። በገዛ ሀገሬ በተወለድኩበት ባደግሁበት መንደር ለ ሀገሩ ባዳ ለቀየው እንግዳ ሁንኩ። ትንሽ ዝቅ እንዳልኩ ከሁለት ህንጻዎች መካከል አጣብቂ ኝ ተይዛ የምታቃስት የመሰለች አንዲት ትንሽ ጠላ መሸጫ ቤት ተመለከትኩና ጠጋ ብል ፤ እበረንዳዋ ላይ ቆባቸውን ጉልበታቸው ላይ ደፍተው ፣ በጭራ ዝምባቸውን እየተከላከሉ ፣ ልትደፈን አንድ ሳምንት የቀራት በመትመስ ል አይናቸው ወዲያና ወዲህ የሚያማትሩ አ ዛውንት አይቼ “ጤና ይስጥልኝ! አባቴ!” አል ኩ። ደንገጥ ብለው “እንዴት አደርክ ልጄ? ጎ ራ በል እንጂ! አንዲት ብርጭቆ የሰንበት ጠላ ልጋብዝህ።” ብለው ከያዟት ጣሳ እንድካፈል ጋበዙኝ። ለጊዜው የተሻለ አጋጣሚ ባለመኖ ሩ ፣ ለጨዋታም ይመቸኛል በማለት እሽታዬ ገልጬ ወደተቀመጡበት በረንድ ላይ በመ ውጣት በሳጠራ ከተሰራች ያረጀች ወንበር ላ ይ አረፍ አልኩ። በዚያች በደከመች ድምጻቸ ው ወደቤት እየተጣሩ ብርጭቆ እንዲመጣ አ ዘዙ። ጥቂት ቆይተውም በኋላ አንድ ጠና ያ ሉ ሴት ከቤቱ ውስጥ ብርጭቆ ይዘው ወጡ። እጅ እየነሱኝ ደግሞ ዛሬስ ማንን አገኘህ? ብ ለው ሽማግሌውን እየጠየቁ ካጣሳው ቀዱል ኝ። ውሀ የጠማው እንግዳ ነዋ። አየሽ ወንድ ልጅ ውሀ እየተጎነጨ ነው የሚጨዋወት! አ ሉ። “እስቲ ይሁና! ምንክፋት አለው ታዲያ!” ብለው ተመልሰው ገቡ። እዚህ ሰፈር ብዙ ኖሩ? ብዬ ጥያቄ አቀርብኩላቸው። ኖሩ ነው ያልከኝ? አዬ . . . ምን ኖሩ ብቻ አፈጀሁ እንጂ። እንደው ሰፈሩ ተቀይሮ ባይ ገርሞኝ እኮ ነው። አልኳቸው።

ሰፈሩን ታውቀው ነበር? ብለው እንደመተከ ዝ አሉና “አዬ ልጄ የድሮዋ የቀኛአዝማች ሰ ፈር . . . ዛሬ ቀን ወጥቶላት ይኸው ሁሉም በ የአካባቢው ከንዶ ነው የሚባል ህንጣ ላይ እ የሰቀሉት ኸደ። ባጋጣሚ ቅያሱ ለጊዜው የእ ህቴን ቤት ባለመንካቱ ፤ እዚህች እርሷ በረን ዳ ላይ ጠላዬን እየተጎነጨሁ እንዲሁ እንዳን ተ የሚያዋራኝን እስከማገኝ አላፊ አግዳሚው ን ፣ ወጪ ወራጁን ስቃኝ እውላለሁ።” ይገር ምሀል ይሄ ኮንዶ የሚሉት ሰቀላ ቤት ግሩም ቢሆንም እንደ እህቴ ጠላ ነግደው የሚያድሩ ትን ግን ጦማቸውን አሳድሮአቸዋል። አንዳን ዶች የማውቃቸው የኔብጤ አዛውንቶችም ሊ ጠይቁኝ መጥተው ሲያጫውቱኝ፤ የህንጣው ደረጃ አበዛዙና እርሱን ላይ ታች ማለቱ አድ ካሚ ስለሆነብን ከቤት ሳንወርድ የምንውልበ ቱ ቀን ይበዛል ብለውኛል። አየህ ልጄ! አልወ ስደኝ ብሎ ፣ ለመርዶ ነጋሪነት አስቀርቶኝ እን ጂ ፤ በገዛ ቀየህ ባይተዋር ስትሆን ምን ደስታ ይሰማሀል? እድሩ ፣ እቁቡ፣ ቡና አጣጭህ ሁ ሉ ጥሎህ ኸዶ ፣ ጓደኞችህ አልቀው፣ ባረጀህ በትና በተከበርክበት ሰፈር በስምህ ጠርቶ ሰላ ም የሚልህ ስታጣ! ምን ህይወት ነው? ከለየ ለት ከማታውቀው ሀገር ስደት ይሻላል እንጂ . . . ያው ስደት ነው! ብለው ፊታቸው በሀዘ ን ተለወጠ። እውነትዎን እኮ ነው አባቴ ፤ እኔ ም ዛሬ በሰላሳ ዓመቴ ይኸው ከፈረንጆቹ ሀገ ር ብመለስ ፤ ባደግሁበት ቀዬ በአያቶቼ ስም በሚጠራው ሰፈር የማውቀው አጥቼ ሁለተኛ ስደት ሆኖብኝ እኮ ነው። ብዬ ታሪኬን አጫ ወትኳቸው። በመገረም አዬ ጊዜውን አስታወ ስኩት እገሌን ታውቅ ነበር። ብለው ያኔ ከተገ ደሉት የሰፈራችን ልጆች መካከል የአንዱን ስ ም ጠርተው ልጃቸው እንደሆነ አጫወቱኝ። ለመሄድ ስነሳ ሌላ ጣሳ አዝዤ ለእጃቸው የም ትሆን ጥቂት ገንዘብ ወሸቅ አድርጌላቸው። በ ሉ እንግዲህ እግዜር ከርስዎ ጋር ይሁን። ብዬ ተስፋ ሳልቆርጥ የጀመርኳትን ቀጭን መንገድ ቁልቁል በግሬ ተያያዝኩ ምንም የማውቀው ሳለገኝ ታክሲ ላገኝ ወደምችልበት ዋና መንገ ድ ላይ በመድርሴ ፤ ባጋጠመኝ ሁለተኛ ስደ ት እያዘንኩ ታክሲ አስቁሜ ወደ ሆቴሌ ተመ ለስኩ። ቸሩ ነኝ ከሎስ አንጀለስ


በአንዲት የህይወት አጋጣሚ የግሸን ማሪያምን ለመሳለም ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር ባደረጉት ጉዞ ፤ ህይወታቸው ተቀይሮ ዛሬ የብዙ ዎች እናት ፣ የሀገር መኩሪያና የትውልድ ተምሳሌት ለመሆን የበቁትን ፤ የክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና አኩሪ ስራና ታሪክ እናስነብብዎ። የአበቡ ቤተሰቦች ከጣሊያን ወረራ በኋላ ፤ አበበችን በወለዱ በወ ሩ በጣሊያን እጅ በመገደላቸው ፤ አበበች በአያት ለማደግ ተገደዱ። አበበች የወለዱት የራሳቸው የሆነ ልጅ የላቸውም። ለነገሩ ወደትዳር ዓለም የገቡት እንኳ ገና የአስር ዓመት ህጻን ሳሉ ነበር። ዳሩ የልጅነት የትዳር ኑሮ ስላልተ ስማማቸው ፤ ከትዳራቸው ተለያይተው ብር ብለው ጠፍተው ወደ አዲስ አ በባ በመጓዝ ለሁለተኛም ጊዜ አግብተው ለመኖር ሞክረው ነበር። ግን የመ ውለዱ ነገር አልተሳካም ። “ጥሩ ስራና ኑሮም ነበረኝ” ይላሉ ወ/ሮ አበበች። እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1972 ዓ/ም ግሸን ማሪያምን ለመሳለም ወደ ወሎ ክፍለ ሀገር በተጓዝኩበት ወቅት ፤ በኢትዮጵያ ላይ በተከሰተው የረሀብ ችግር ሳቢያ ፤ በ ወሎ ክ/ሀገር ብዙ ሺህ ህዝብ በረሀብ በማለቅ ላይ ይገኝ ነበር። ከደሴ ወደ ሀ ይቅ ተጉዤ ግሸንን ተሳልሜ በነጋታው ምሽቱን ስመለስ ፤ በመንገዳችን ላይ የሬሳ መኪና ቆሞ ያን ቢነሳ የማያልቅ በረሀብ የረገፈ ህዝብ ይለቅም ነበር። የ ተረፈችኝን ትንሽ ዳቦ መንገድ ላይ ለወደቁ ሁለት ወንዶች አጉርሼ ፤ ሶስተኛ ዋን ሴት ለማጉረስ ስጠጋ ነበር ፤ የእናቷ ሬሳ ላይ ተኝታ ጡት የምትጠባው 44

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ን ህጻን ያገኘኋት ፤ የሬሳ መኪና አሽከርካሪውም እናትየው እንደሞተችና ል ጅቱን ከሬሳ ጋር ላለመጫን እየጠበቀ እንደሆነ ሲነግረኝ ፤ እርሷን እኔ እወስ ዳታለሁ ብዬ አነሳኋት። ሁለተኛዋን ህጻን ታንጉትን ደግሞ ፤ ከሬሳዎች መ ካከል ተኝቶ በጣዕረ-ሞት ላይ የነበረ አንድ አባት ፤ ተጣርቶ የልጄን ነፍስ አ ድኚልኝ ብሎ ልጁን በአደራ ሰጥቶኝ ፤ ከአንዲት መነኩሴ ለምኜ ባገኘኋት አ ንዲት ስኒ ውሀ ፤ የበጠበጥኩትን በሶ ከአፉ እንዳደረገ ህይወቱ ከፊቴ አለፈ ች።” ወ/ሮ አበበች ሁለቱን የሙት ልጆች ይዘው ወደ ቤታቸው ሲመለሱ ነበ ር ህይወታቸው የተቀየረው። ከዚያም በዓመቱ ሀያአንድ ልጆችን ሰበስበው ማሳደግ ይጀምራሉ። ታድያ ያኔ ዘመድ አዝማድ በሙሉ “ያምሻልና አማኑኤ ል ወደተባለው የአእምሮ በሽተኞች መታከሚያ ሆስፒታል እንውሰድሽ” ብ ለው የጠየቁኝ። ባለቤቴም ሆነ እሰራበት የነበረው መስሪያቤት ከስራሽ ወይ ም ኪዚህ ድርጊትሽ ብለው ምርጫ አቀረቡልኝ ፤ ስራዬንም ለቅቄ ወጣሁ። ከትዳሬም ተለያየሁ። ውስጤ በተነካበት የነፍስ ማዳን ነገር አንዴ ህይወቴ ተቀይሮልና ወደኋላ ላልል ወሰንኩ።” ጉለሌ እስላም መቃብር አካባቢ ዶሮ ለማርባት ገዝተውት ከነበረ መሬታቸው ላይ በሳጠራ ቤት ከልለው ፣ በጭቃ መደብ በመስራት የሰበሰ ቧቸውን ሀያ አንድ ልጆች ህይወት ለወግ ለማረግ ለማብቃት ጉዟችውን ቀ ጠሉ። ከቤታቸው ይዘው የወጧትን ወርቅ በመሸጥ ፤ ልብሳቸውን እየቀደ ዱ ለልጆቹ ልብስ በእጃቸው በመስፋት ፤ ህጻናቱን በልተው እንዲያድሩ ቀ ን ከሌት በመልፋት ማሳደጉን ተያያዙት ። የዛን ጊዜው ውሳኔያቸው ትክክ


ልና ወጤታማም ሆነ። ዛሬ የአፍሪካዋ ማዘር ቴሬዛ ለመባልና ፤ ከጂማ ዩኒቨ ርሲቲ የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ተሸላሚ ለመሆን አበቃቸው። ታዲያ እስከ 1979ዓ/ም ድረስ ያለምንም እርዳታ እንጀራና ቆሎ በመሸጥ ፤ በዚያ ጫካ ከ ጅብ ጋር እየተጋፉ ህጻናቱን ያሳድጉ ነበር። በዚያም ብቻ አላቆሙም ፤ በኋላ ም ከተለያዩ ሰዎች እርዳታን በማግኘት በ1986ዓ/ም ይህን ድርጊታቸውን በ መንግስት ደረጃ የተመዘገበና እውቅናን ያገኘ የሙታን ህጻናት ማሳደጊያ ድ ርጅት እንዲሆን አደረጉ። ዛሬ ያ በሁለት ህጻናት የጀመሩት የአበበች ጎበና የህጻናት እንክብካ ቤ ወደ 300 የሚደርሱ ቋሚ ሰራተኞችን የሚያስተዳድር ሲሆን ፤ ከ14000 በላይ የሚሆኑ ህጻናትን በተለያየ መንገድ ይረዳል። 200 አዳሪ ተማሪዎች 482 ተመላላሽ ተማሪዎችን ያስተናግዳል። እንዲሁም ይሄ ድርጅት 1000 የ ሚሆኑ ፤ በሌላ ት/ቤት ለሚማሩ የችግረኛ ቤተሰብ ልጆች የትምህርት ክፍ ያ ያደርጋል። ከ1800 በላይ ህጻናትን ከህጻናት ስፖንሰርሺፕ ተጠቃሚ እን ዲሆኑ እያደረገ ሲሆን ፤ ከ200 በላይ ለሚሆኑ ህጻናትና እናቶች የምግብ ድ ጎማን ያደርጋል። በአዲስ አበባ የሚገኘው ድርጅት የራሱ የጤና ክሊኒክ ፣ የ መማሪያ ት/ቤት ፣ የማደሪያ ክፍሎች ፣ የመዋዕለ ህጻናት ፣ የስተዳደር ቢሮ ዎችና . . . ያለው ሲሆን በተለያዩ የሀገራችን ክልሎችም ተመሳሳይ ፕሮጀችቶ ችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል። ወ/ሮ አበበች ህጻናቱ ተምረው በተለ ያዩ የስራ መስኮች እንደ አናጢነት ፣ ሽመና፣ የብረት ስራ፣ በኤሌክትሪክ ስ ራ ፤ በፎቶ ግራፍና የህትመት ስራዎች በመሳሰሉት ሰልጥነው ፤ ህብረተሰቡ ን ሊያገለግሉ የሚችሉ የወድፊቷ ኢትዮጵያን ተረካቢ ዜጎችን በማፍራት ላ ይ ይገኛሉ። በዚህ የሰላሳ ዓመታት የበጎ አድራጊነት ህይወት ጉዞ ብዙ ችግሮች ን እንዳሳለፉና ፈጣሪያቸው ብርታትን እንደሰጣቸው ይናገራሉ። ድህነት ፣ ኋላቀርነት ፣ ረሀብ ፣ ኤድስና የተለያዩ የተፈጥሮም ሆነ ሰው ሰራሽ አደጋዎ ች ብዙዎችን በሚጨርሱበት ዘመን ፤ የሙታን ልጆች የመኖር ትርጉም በሌ ለው ሀገር ፤ ገንዘብን ማካባት ብቻውን ጥቅም እንደሌለው የሚገልጹት እኝ ህ ሴት ፤ በሺህዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን ህይወት በርሀብ ከመጠበስ ፣ በየበረ ንዳውና ጎዳናው ላይ አድገው ለሀገር ሸክም ከመሆን ለማትረፍ ፤ ያላቸውን ጥሪትና ህይወታቸውን ለሰላሳ ዓመታት አሳልፈው በመስጠት እየደከሙ ያ ሉ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ክብርት ዶ/ር አበበች ጎበና በተለያዩ ጊዜያት ከሀገር ውስጥና ከዓለም ዙሪያ ከመቶ በላይ ሜዳሊያዎችን ፣ ዋንጫዎችንና የክብር ሽልማቶችን ተሸላሚ ሆነዋል። በያዝነው ዓመትም ዶ/ር አበበችን የ ክብር ኢዩበልዩ ተሸላሚ ለማድረግ ፤ በተለያዩ ኢትዮጵያዊያንና የሌላ ሀገር ዜጎች ፣ ታዋቂ ግለሰቦችና ድርጅቶች ብዙ ጥረት ተደርጓል። ኢትዮጵያ መጽ ሄትም መልካሙን የሚከውን ሁሉ መከበርና መወደስ ይገባዋል ትላለች። ለ እኝህ ድንቅዬና ህይወታቸውን ለሌሎች አሳልፈው በመስጠት እንደጧፍ ለ ሚንቦለቦሉ እናት ፤ ለሀገርና ለወገን ኩራት ፣ ለተተኪው ትውልድ የሚቆይ መልካም ጥሪትና ታሪክን ላቆዩ ዜጋ ፤ ጤናና ረዥም እድሜ ትመኛለች። በተ ጨማሪም ይህንን ነፍስ አድን ድርጅት በገንዘብም ሆነ በማናቸውም ረገድ በ መርዳት የመልካም ምግባሩ አካል ለመሆን ከፈልጉ ፤ ከታች በተጠቀሰው የ ድርጅቱ አድራሻ በመጻፍም ሆነ በመደወል ከድርጅቱ ጋር ቀጥታ ግንኙነት መፍጠር ይችላሉ። ከዝግጅት ክፍላችን Abebech Gobena Children’s Care and Development Organization P.O.Box 24998 , Addis Ababa , Ethiopia Tel +251-11-1553622; Fax +251-11-1550152 E-mail: agoheld@ethionet.et

www.abebechgobena.org

Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

45


“ቃላቶች ያጥሩኛል ምን ብዬ ላድንቅሽ እንደው በደፈናው ሞናሊ ዛዬ ነሽ።” አንጋፋው ድምጻዊ ማን ነው ብለን ተራ ጥያቄ ለማቅረብ አንከጅ ልም። አዎ ጥላሁን አዳንዶች ጥልዬ፣ ሌሎልች ደግሞ ጥላችን የሚሉት ይኖ ራሉ። አፈር ይቅለለውና በርግጥም የኛው ጥላሁን ገሰሰ ነበር። የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ዓላማ በብጣሽ ወረቀት ሳይሆን በትልቅ ደጓሳ መድብል እንኳ ታሪ ኩ ተፅፎ ስለማያልቀው ድምፃዊ ለማውጋት ሳይሆን ለበርካታ መቶዎች ዓመ ታት አድናቆቷን ሳትጥል የሰው ልጅ የጥበብ ስራዎች ሁሉ የበላይ ሆኖ ስሟ በዓለም ሲነሳ ስለምትኖረው የሞናሊዛ ስዕል ሲሆን ፤ ከብዙ አቅጣጫ ስትሰ ሙት እነበራችሁት ላይ ጥቂት ለመጨመር ነው የዛሬው ሙከራዬ። . . . የሞናሊዛ ፈጣሪና ሰሪ ታዋቂው የስዕል አባት ፣ አንጋፋው ሒሳብ ቀማሪና ባለትልቁ ጭንቅላት ፣ ፈላስፋው ሊዎናርዶ ዳቬንቺ ነው። ሊዮናር ዶ ዳቬንቺ በብዙዎቻችን የሚታወቀው በሰዓሊነቱ ሲሆን ታዋቂ የሂሳብ ሰ ውና ሳይንቲስት መሆኑ የታወቀው በቅርቡ ነው። ለምሳሌ የመጀመሪያውን ከእንቅልፍ ቀስቃሽ ሰዓት ወይም ዓላርም ፣ የቀደምቱን የሔሊኮፕተር ዲዛይ ን ፣ ሊፍት ወም አሰንሳር የተባለውን በኤለክትሪክ የሚሰራ የፎቅ መወጣጫ ያ ንድፍ ያረቀቀ ምስጉን ሳይንቲስት ሲሆን ዓለም በድጋሚ ልትፈጥራቸው ካልቻለቻቸው ምርጥ ልጆቿ አንደኛውና ግንባር ቀደሙ ነው። ወደፊት እድ ሉን ካገኘ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ የዳቬንቺን ሙሉ አስደናቂና አስጎምጂ ታሪ ክ እንድሚያቀርብ ቃል እየገባ ዛሬ ግን ወደተነሳበት ወደ ሞናሊዛ ታሪክ ይዘ ልቃል። ሞናሊዛ ማናት? ማንን ትመስላለች? ለምንስ ተሰራች? ሊዮናርዶ ዳቬንቺ ምን ነው በዚህች ስራ ላይ ልዩ ትኩረት አደረገ? የሚሉ በርካታ ጥያ ቄዎች የተነሱ ሲሆን ፤ ገሚሶቹ እስካሁን መልስ ሳይገኝላቸው ቀርተዋል እን ዲያው ለአጠቃላይ እውቀት ቢሆን ከዚህ በታች ያሉትን ጉዳዮች እንመልከ ት። በሊዮናርዶ ዳቬንቺና በብርቅዬ ስራው በሞናሊዛ ላይ የተደረጉት ጥናቶች ፤ አንዳንዴ እርስ በእርሳቸው ቢጋጩም ፤ ብዙዎቹ ግን ተመሳሳይ ሆነው ተገኝተዋል። ሊዎናርዶ ሞናሊዛን ለመስራት መቼ ቡሩሹን እንደጨ በጠ ባይታወቅም ይህ ይበቃታል ፣ የምፈልጋት ሞናሊዛ ይህች ናት ብሎ የ ልቡ ደርሶና ስዕሉን ጨርሶ ቡሩሹን አጣጥቦ ስራውን ያጠናቀቅበት ጊዜ ግን

46

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

በታሪክ ተመዝግቧል። ሊዮናርዶ ዳቬንቺ የሞናሊዛን ስዕል አጠናቆ የጨረ ሰው በ1503 ፤ ሲሆን ከሁለት መቶ ዓመት በኋላ ስዕሉ ተወዳጅነቱ እየጨ መረ በመምጣቱና ስዕሉም የዛራፊዎችን ቀልብ በመሳቡ ኢንሹራንስ ሊገባለ ት እንደሚያስፈልግ ተወስኖ ፤ በ1962 ዓመተምህረት ኃላፊነቱን ለመውሰ ድ በኢንሹራንስ ባለቤትነት ሊረከበው የፈለገ አንድ የጣሊያን ኢንሹራንስ ኤ ጀንሲ ፤ ስዕሉን 201 ሚሊዩን የአሜሪካን ዶላር የገመተው ከ41 ዓመት በፊ ት ነበር። ከጣሊያን ሀገር የተገኘው አንድ አፈ-ታሪክ ደግሞ እንዲህ ይላል . . . “አንድ በጣሊያን ሀገር የሚገኝ ቱጃር ታዋቂውን ሰዓሊ ሊዮናርዶ ዳቬን ቺን አፈላልጎ ያገኘዉና ፤ ባለቤቱን በህብረ ቀለማት አሳምሮ እንዲሰራለት ይ ጠይቀውና ፤ እቤቱ ምሳ ጋብዞ ባለቤቱን ያስተዋውቀዋል። ሊዮናርዶም በታ ዘዝው መሰረት ባለቤቱን ልቅም አድርጎ ካስተዋላት በኋላ በተፈጥሮ ባጎናጸ ፈችው የጥበበ ስጦታው የባለጸጋው ባለቤት አሳምሮ ይሰራና ፤ በቀጠሮው ቀን ወደባለጸጋው ቤት በመሄድ ስዕሉን ሲያስረክበው ፤ በሊዮናርዶ ዳቬን ቺ አምራና ተውባ የተሰራችው ሴት ምስሏን ትኩር ብላ ተመልክታ “እውነት ሊዮናርዶ ታላቅ ሰአሊ ነህ ፤ ግን አንድ ነገር ልጠይቅህ ፍርዱን ላንተ ትቼዋ ለሁ ፤ እውነት ይህንን ስዕል ከመሰልኩ ይህንን ያህል ዘመን ከዚህ ሰው ጋር መኖሬ አላሳዝንም!? ብላ በቀልድ መልክ ቁም ነገሯን ጣል በማድርጓ ነው ይ ላሉ። ባለፀጋው ሰው በተደፈርኩና በቅናት ተናዶ “ስዕሉም ባለቤቴን አይመ ልስም ለጊዜውም የምከፍልህ ገንዘብ የለኝም በማለት ስዕሉን ለዳቬንቺ ያስ ታቅፈዋል። ሰአሊው ሊዮናርዶም ሳይናደድ ውብ ስዕሉን ይዞ ወደ ቤቱ ተ መለሰ ይላሉ አፈ ታሪክ ተናጋሪዎች። አንዳንዶች ደግሞ በጥንት ጊዜ የነበረች የፍሎረንስ ልዕልት ናት ሲ ሉ ፣ በአብዛኛዎቹ የታሪክ ተመራማሪዎች ሊዮናርዶ ዳቬንቺ የሳለው በሴት አስመስሎ የራሱን ገጽታ ነው ይላሉ። በርግጥም ሊዮናርዶ ዳቬንቺ ተወዳዳ ሪ የማይገኝለት መልከቀናና የሴቶች ቀልብ የሚስብ መልከኛ ሰው እንደነበር ይነገርለታል። በመጨረሻም ሞናሊዛዬ ነሽ የሚለውን ማራኪ የጥላሁን ገሠሠ ዘ ፈን የግጥሙ ደራሲ ማን እንደሆነ ያውቁ ነበር? አዎ የግጥሙ ደራሲ ሟቹና ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ ነው። አቡሽኮቭ ከም ዕራብ ላስ ቨጋስ


ብዙ ጊዜ በተለያዩ የመሀበራዊ ህይወት ግንኙነቶች ፤ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ሲሰባሰቡ ከሚነሱ ጉድዮች ፤ ነገር ግን በግልጽ ለመወያየት አስቸጋሪና በቂ መልስ ሳይገኝላቸው ከሚታለፉት አርዕስት መካከል ፤ አንዱ የግንኙነትና የትዳር ጉዳይ ነው ። ባህላችንና አስተዳደጋችን በወንድ እና በሴት መካከል ያሉንን ችግሮች በግልጽ ማንሳትና ከሌሎች ጋር መወያየት “ገበ ናን አሳልፎ መስጠት ነው።” በሚል አባባል ስለሸበበን ፤ በችግራችን ላይ ከመወያየት ይልቅ ፤ አፍነን በመያዝ ለተለያየ ጭን ቀት ፣ ለጎጂ ሱሶች ፣ እራስ ማጥፋት ፣ በትዳር ጓደኛ ላይ አደጋን መጣል ፤ አሊያም ችግራችን አድጎ በከፋ መልኩ ለፍች መ ድረስ ፤ ትዳር በመፍረሱም በሚደርሰው የቤተሰብ መበተን ለሚፈጠሩ ቀጣይ ችግሮች ስንዳረግ ይታያል ። አንባቢያን ሆይ በዚህ እርዕስ ላይ ግልጽነትን በማዳበር በወንድና በሴት ግንኙነትና በትዳር ህይወት ውስጥ ስለሚከሰቱ መልካምም ሆነ መ ጥፎ ጎኖች በግልጽ በመነጋገርና በመማማር ለውጦችን ማምጣት ይቻላል ብለን ስላመንን ፤ ይህንን ጽሁፍ ለመንደርደሪያ እ ንዲሆን አዘጋጅተናል ። ወደፊትም በነዚህ ጉዳዮች ላይ ሊያስተምሩና ሊያወያዩ ይችላሉ የምትሏቸውን ጽሁፎች ፣ ገጠመኞ ች ፣ ጥያቄዎች እና አስተያየታችሁን በመላክ እንድትሳተፉበት እንጋብዛለን ።

ትዳር ምንድን ነው? እንዴትስ ይመሰረታል? ችግሮቹና የችግሮቹ መፍቻስ ምንድን ናቸው። በርግጥ የዚህ ጽሁፍ አዘጋጅ ትዳርና ችግሮቹን በአንድ የመጽሄት የተወሰኑ ገ ጾች መተንተን ይቻላል የሚል እምነት ባይኖረኝም ፤ ከሞላ ጎደል ዋና ዋና ብ ዬ የማምንባቸውን አጠር አድርጌ ለመተንተን እሞክራለሁ። ጋብቻ ማለት እድሜ ለአቅም አዳም ሲደርስ ፤ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም ባለመሆኑ ፤ እራስን አሳልፎ በመስጠት ፤ ከሌላ ተቃራኒ ጾታ ጋር ህይወትን በመጋራት ፤ የጎደለውን ግማሽ እኛነት ፤ በአካለም ሆነ በመንፈስ ለማሟላት የሚደረግ የሁለት ተቃራኒ ጾታዎች የህይወት ውሳኔ ነው ። በም ድራችንም ላይ ከሰው ልጅ መፈጠር ጋር ተያይዞ የተመሰረተ የመጀመሪያው ና አስፈላጊ ተቋም ነው። ታዲያ ለዚህ አይነቱ አስፈላጊና ጤናማ የሆነ ቤተሰብ ምስረታና እድገት ፤ ጤናማ የሆነ ግንኙነት አስፈላጊ ነው። ጤናማ ማህበረሰብም ሆነ መንግስት ከዚሁ በአካል ፣ በመንፈስና በስነልቦና ጤናማ እና ደስተኛ ከሆነ ቤተሰብ የሚፈጠሩ ሲሆን ፤ ሀገርም በነዚሁ ጤናማ ግለሰቦችና ተቋሞች የ ምትገነባ በመሆኗ ፤ ለሁሉ የሚበጅ ጥብቅ መሰረት መጣል አስፈላጊ ነው። ይህንን ጤናማ የምንለውን ቤተሰብ ለመመስረት ደግሞ ዋነኛው መሳሪያ በ ፍቅር ላይ የተመሰረተ ጋብቻ እንደሆነ ብዙዎች ያተቱለት ጉዳይ ነው። ዋና 48

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ው ጉዳይ ያለው ግን ለፍቅር የምንሰጠው ትርጉምና መረዳት ስለሆነ ፤ ምን አይነት ፍቅር??? የሚለውን ጥያቄ መመልከት ይኖርብናል። ብዙዎች እውነ ተኛ ፍቅር ብለው ይመልሳሉ። “ይህ እውነተኛ የምንለው ፍቅር እኮ የሚያስ ታግስ ፣ የሚያስተዛዝን ፣ የማያስታብይና ማያስመካ ፣ ብቻዬን ይድላኝ የማ ያሳኝ ፣ የማያበሳጭ ፣ ክፉ ነገር የማያሳስብና ከእውነት ጋር ደስ የሚለው እ ንጂ ከአመፃ ጋር ደስ የማይለው ፣ ሁሉን የሚያምን ፣ በሁሉ ደግሞ ተስፋ የ ሚያደርግ፣ በደልን የሚሸፍንና ጽናት ያለውን ፍቅር ማለት ነው።” ይህን አ ይነቱን ፍቅር መሰረት ያደረገ ግንኙነት የሚኖረውን ጥንካሬ ፣ ጤናማነትና ውጤታማነት መገመት አያዳግትም። ያልተጋቡ ጥንዶችን ወደ ጥሩ ትዳር ሲ ወስድ ፤ የተጋቡትን ደግሞ ደስተኛ ቤተሰብ እንዲኖራቸው ያደርጋል። እንግዲህ መሰረቱ ይሄ ሆኖ ሳለ ለምን ይሆን በዚህ ዘመን ትዳሮች ችግር የ ሚበዛባቸው? ብዙዎች ወደዚህ የትዳር ህይወት የሚገቡት በችኮላ ፣ በበቂ ሳያ ጤኑበት ፣ ባልጠበቁት የህይወት አጋጣሚዎችና መስፈርቶች በመሆኑ ፤ አ ብሮ ለመኖር የሚያስችሉትን ዋና ጉዳዮች ፤ እንደ ፀባይ ፣ የጋራ ፍላጎት ፣ ባ ህሪና አመለካከት የመሳሰሉትን . . . ለማጥናት ጊዜ ባለማግኘትና ፤ እነዚህን ም ጉዳዮች ለመመልከት የሚያስችለውን ህሊና ደግሞ ፤ በአካል ማማር ፣ በ ፍትወት እርካታ ፣ በገንዘብ ወይም በቁሳቁስ (ማቴርያል) ላይ ብቻ በተመሰ


ረተ ፍላጎት . . . በመጋረድ ስለሚገቡበት ፤ ጉዟቸውን ከጅምሩ አድካሚና ስ ኬታማ እንዳይሆን ያደርጉታል። ትዳር በደመነፍስ በድንገት አንድን ነገር በ ማየት ብቻ የሚገባበት ቀላል የጥምረት ህይወት ሳይሆን ፤ የትዳር አቻን ደስ ታ ፣ እርካት ፣ እድገት በመመኘት ፤ በመተማመን ፣ በቅንነት ፣ በትህትና ፣ በመተሳሰብ ፣ በማበረታታት ፣ በመተጋገዝ ፣ በመመሰጋገን ፣ በመቻቻል ፣ ይቅርታን በመጠየቅና ትክክለኛውን ነገር በማድረግ ፣ አብሮ ለመሆን በመነ ፋፈቅ ፣ በፍትወት ነፃነት በመረካካት ፣ ባለመቀናናት ፣ አንዱ ያንዱን ፍላጎ ትና ተፈጥሮ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ጫና ባለማሳደር ፣ ስህተትን በመን ቀስ ለማሸነፍ በመሞከር ሳይሆን ፤ በበጎ መንፈስ በመተራረም ፣ በመቀባበ ል ፣ በግለኝነትና በስሜታዊነት የሚደረጉ ውሳኔዎችን በማስወገድ ፣ በትእግ ስት እና በመልካም ስነምግባር በመውያየት ፤ የጎደለውን ለማሟላት አንጀት ን ሰፋ አድረጎ ፤ በአንድነት ለመጓዝ የሚደረግ የህይወት ጥምረት ነው ። በ ርግጥ ሲዘረዘር ብዛቱ የሚያስፈራ ቢመስልም ፤ የኑሮ ዘመኑ ደግሞ ረጅም መሆኑ መዘንጋት የሌለበት ጉዳይ ነው። እነዚህ ከላይ የዘረዘርኳቸው ቱባና ቁልፍ ሀሳቦች እየተበተኑ መታየት የሚገባቸው ስለሆኑ ከፊሉን በዚህ እትም ሌሎቹን ደግሞ በሌሎች እትሞች ላይ እናያቸዋለን። በፍቅር አብሮ መኖር አስደሳች ቢሆንም ፤ ወደ አንድ ጣሪያ ከመ ገባቱ በፊት ፍጹምነት እንደሌለው ፣ ብዙ ውጣ ውረድና መሰራትን እንደ ሚጠይቅ አስቀድሞ መረዳት ያሻል። ምክንያቱም ሁለት በተለያየ ቤተሰብ እ ና የአስተዳደግ ስልት ተኮትኩተው ያደጉ ፣ የተለያየ ጾታ ፣ ዕድሜ ፣ ፍላጎት ፣ የትምህርት ደርጃ ፣ በተለያየ ባህልና የህይወት ልምዶች ያካበቷቸውን ባህ ሪዎች፣ የአመለካከት ልዩነቶችንና . . . የመሳሰሉትን በማዘላቸው ሲሆን ፤ እ ነዚህ ልዩነቶች ደግሞ በየዕለቱ በኑሯቸው ውስጥ የሚፈጥሩባዋቸው ያለመ ግባባቶችና ግጭቶች ስለሚኖሩ ነው ። አብሮ ለመኖር የሚወሰነው ውሳኔ እ ለት ተለት የሚደረግ የትምህርት ሂድት ነው። አንዱ ስለ ሌላው ጸባይ ፍላጎ ት እና የባህሪ ለውጥ በየቀኑ የሚማርበትና ፤ የሚማርበትም መንገድ የተለያ የ በመሆኑ እውነታዎችን አምኖ በጋራ የመስራቱን አስፈልጊነት መቀበል ይ ፈልጋል። እስቲ በትዳር ውስጥ ዋና ዋና የሚባሉትን ችግሮች ፣ እንዴት ሊፈ ጠሩ እንደሚችሉና መፍትሄያቸው ምን እንደሆነ እንመልከት። ጋብቻና እቅድ ሰው በህይወት ጉዞው ላይ ምን እንደሚፈልግ ፣ ወዴት መሄድና ምን ማድረግ እደሚገባው አለማወቅ ጉዞውን አድካሚ ያደርገዋል። ስለዚህ ም ለረዥም ዓመታት እራስን አሳልፎ በመስጠት ህይወትን ለመጋራት ካሰበ ው ሰው ጋር ፣ ያለውን የህይወት አንድነትና ልዩነት ማጥናት ጠቃሚ ነው። ከቤተሰብ ጋር መተዋወቅና ስለ ቤተሰቡ ታሪክና አኗኗር ማወቅ ፤ ባስተዳደ ግ የሚመጡትን ባህሪዎች ለመረዳት ይረዳል። የራስን የወደፊት የህይወት እ ቅድ ከዚያ ሰው የህይወት እቅድ ጋር ምን ያህል ሊጣጣም እንደሚችል ፤ በ ተለያዩ የቅድመ ጋብቻ መጠናናቶች መረዳት ያሻል። ለምሳሌ ፦ የመኖሪያ ቦ ታ ምርጫ ፣ የልጆች ብዛት፣ የሞያና ትምህርት እንዲሁም የአኗኗር ደረጃ ፍ ላጎቶች ፣ የእምነት ልዩነቶች ፣ በማህበራዊ ኑሮ ግንኙነቶች ላይ ያሉ ፍላጎቶ ች . . . በስምምነት በመቻቻል ወይም እንዴት ተደርገው ሊቀናጁ እንደሚገ ባ ለማሰብ ይረዳል ፤ ካልሆነም ወደ ጥምረት ከመግባት በፊት ለመወሰን ይ ረዳል። ጋብቻና ውይይት (Communication) ውይይት በቅድመ ጋብቻም ሆነ በድህረ ጋብቻ ህይወት ውስጥ ዋ ነኛና የሁሉ ነገር መፍቻ ቁልፍ ነው። ሀሳብን ለመረዳት መፈለግንና መቻልን ይጠይቃል። የሰው ልጅ ሀሳብን የመለዋወጫ ፣ የመወያያ ፣ የመልዕክት ማ ስተላለፊያ መንገዶች ፤ ከአፈጣጠር ፣ ከአስተዳደግና ከእውቀት ደረጃ ጋር የ ተያያዙ በመሆናቸው ፤ አንዱ ጾታ ስለሌላው ጾታ አፈጣጠርና ባህሪ እውቀ ት እንዲኖረውና አመለካከቱም አዎንታዊ ሊሆን ይገባዋል ። በተፈጥሮ መለ ያየታችን ለጉድለቶቻችን ማሟያ ሚስጥሮች መሆናቸውን ሁልጊዜ ሊታሰብ በት የሚገባ ጉዳይ ነው። በውይይት ጊዜ የሌላውን ስህተት ከመንቀስ ይልቅ ፣ በእለት ተለት ኑሮ መካከል አንዱ ለሌላው የሚያደርገውን መልካም ድርጊ ቶች በማድነቅና በማመስገን መጀመር የመወያየት ፍላጎትን ያጎልብታል። በ

ውይይት ጊዜ በሙሉ ላህይና በጥሞና በማዳመጥ ፣ ተናጋሪው ወገን ሊገልጽ የፈለገውን ሀሳብና ፍሬ ነገር ለመረዳት መሞከር ተገቢ ነው። በመወያየት ጊ ዜ ሌላ ስራን ትቶ አይን ለአይን በመተያየት መደማመጥ ፣ በተቻለ መጠን ዋ ናው ሃሳብ ላይ በማተኮር አጭርና ግልጽ አድርጎ ሀሳብን ለማቅረብ መሞከ ር ፣ አንዱ ሲናገር ሌላው ላለማቋረጥ መሞከር የውይይት መሰረተ ህጎች ና ቸው። በቤተሰብ ንግግር መካከል ውስጥን ሊያሻክሩ የሚችሉ አሉታዊ አባ ባሎችን አለመጠቀም ፣ ካደግንበት ማህበረሰብ በተወረሱ ልማዳዊ አመለካ ከቶችና አባባሎች ወንዶች እንዲህ ናቸው. . . ወንድ ልጅ እንዲህ ካደረጉለ ት ሌላ ምን ይፈልጋል? . . . ሴቶች እንዲህ አይደሉ እንዴ . . . አይረዱህም እኮ . . . ደግሞ ለሴት ! በማለት ለጾታው የተለየ ያስተሳሰብ ሳጥን በመስራት በጥቅል ማሰብና ፤ ከዚያ ውስጥ ወጥተው ሊያስቡ እንዳማይችሉ አድርጎ በ ማሰብ ለመወያየት የሚኖረውን ክፍት ቦታ በተሳሳተ አመለካከት መዝጋት ፤ ስህተትና ውይይቱ ውጤታማ እንዳይሆን ያደርገዋል ። አብሮ ለመኖር ሲታ ሰብ አንዱ ለሌላው አስፈልጊና ጠቃሚ ፍጡር መሆኑ ታምኖና ቃል ገብቶ የተጣመረ መሆኑን በማስታወስ ፤ ሊያግባባ የሚችል የጋራ ቋንቋን ማዳበር ጠቃሚ ነው። በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩትን ችግሮች በጋራ በመወያየት ፣ በ ቀና መንፈስ ለመፍታት እና እያንዳንዱም ከስህተቱ በመማር አለመግባባት የተፈጠሩባቸውን ጉዳዮች ለማስተካከል ፍቃደኛ መሆን በጣም አስፈላጊ ነገ ር ነው። የጋራ ኑሮ በአንዱ ብቻ ፍላጎትና ጥረት ስለማይሰራ ፤ በተለያየ ጊዜ ያት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ ያለመግባባቶች ቢፈጠሩ እና ለመፍታት የሚደረ ገው ውይይት ወደ ንትርክና በመክረርም ወደመጋጨት ቢያመራ ፤ አንዱ በ ማብረድና በማሳለፍ ፤ በሌላ ጥሩ ስሜት ባለ ቀን በዘዴ ነገሮችን አንስቶ ማ ስረዳት ወይም ለመነጋገር መሞከር አዋቂነት ነው። አንዳንዴ በውይይት መ ካከል የተፈጸሙ ስህተቶችን እያወቁ “እኔ እንዲህ ነኝ ፣ ተፈጥሮዬ ስለሆነ እ ንዳለሁ ተቀበለኝ” በሚል ሽፋን ስህተትን ላለማረም የሚደርጉ የመዝጊያ አ ባባሎችን በማስወገድ ፤ ስህተትን በመቀበል ይቅርታን መጠየቅን መልመድ ፤ በሳልነትና የአፍቃሪ ሰው መልካም ልብ ተግባር ነው። ያ! ተፈጥሮዬ ነው የ ምንለው ትክክል ያልሆነ ፀባይ አንድ ወቅት ከሌሎች የተማርነው ወይም የ ወረስነው በመሆኑ ፤ ለትዳርና ለቤተሰብ ህይወት የማያስፈልግ ከሆነ ለመቀ የር ፍቃደኛ መሆን ጥቅም ሰጪ ነው። ነገር ግን ለመቀየር የሚደረገው ሂደት ጊዜ ሊወስድና እርዳታም ሊያስፈልገው እንደሚችል በማስረዳት ፤ በመቻቻ ል መጓዝ እንዲፈጠር መንገድ መክፈት ያስፈልጋል ። ትዳር በመከባበር ፣ በመቻቻል እንጂ በመሸናነፍ የሚጓዙት ህይወት አይደለም።

ጋብቻና ፍትወት ፍትወት ለበጋብቻ መኖር ዋነኛው መሰረት ነው። ፍትወት ባይኖ ር ኖሮ ሁለቱ ጾታዎች አብረው አይኖርም ነበር። ፍትወት ከትዳር አቻ ፍቅር ን ሰጥቶ ፍቅርን የሚቀበሉበት፣ እርካታ የሚገኝበት፣ ሰላም የሚፈጠርበት፣ ልጆች የሚገኙበት ትልቅ የፀጋ ስጦታ ነው። ይህንን ታላቅ ስጦታና አስፈላጊ ነገር ለመጠቀም ፤ በሁለቱ ጾታዎች መካከል ያለውን የተፈጥሮ ልዩነት መረ ዳት ይጠይቃል። ፍትወት አካላዊ ብቻ ሳይሆን ስንልቦናዊም በመሆኑ ፤ በተ ለያዩ ችግሮች ፣ የኑሮ ውጣ-ውረድ ድካሞች ፣ የእለት-ተለት አለመግባባቶች ና . . . የተነሳ የፍላጎት መቀነስ ወይም ጭራሽ ማጣት ስለሚያስከትልና ፤ በዚ ያም የተነሳ የትዳር አቻን ወደ አልተፈለገ መንገድ ወይም ከትዳር ውጪ እን Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

49


ዲመለከትና እንዲያመራ ስለሚያደርግ ፤ ለቤተሰብ ትኩረት መስጠት ፣ በአ ኗኗር መረጋጋትና እራስን ደስተኛ ማድረግ መሞከር ዋነኛ መፍትሄና በጣም ጠቃሚ ነገር ነው። ለፍትወት መፈጽም ዋናው ግብረሥጋ ሲሆን ንጽህናን በ መጠበቅ ፣ በግልጽ በማውራት ፣ በመነካካት ፣ አንዱ የሌላውን ስሜት ሊያነ ሳሱ የሚያስችሉ ነገሮችን በመፍጠርና በማድረግ ፣ ኑሮን በፍቅር በመጋራት ፣ ጥሩ በመልበስ፣ እራስን በመጠበቅ፣ በአካላዊ እይታ ብቁና ሊበሉት የሚያ ስጎመዥ ሆኖ በማቅረብ የሚደረግ ነው። ስለ ግብረስጋ ግንኙነት በመወያየ ትም ሆነ በተለያዩ መንገዶች በቂ ግንዛቤንና እውቀትን በማግኘት ግልጽነት ን ማዳበር ፤ በመካከል የሚኖሩትን አለመግባባቶች ይፈታል። በትዳር ውስ ጥ ምንም ዓይነት ሀፍረትና የስሜት መደበቅ ሊኖር አይገባም። ጋብቻና የቤተሰብ ጊዜ በትዳር ህይወት ውስጥ ችግር ከሚፈጥሩ ዋነኛ ጉዳዮች መካከል አንዱ ሚዛናዊ የሆነ የሰዓት አጠቃቀም አለመኖር ነው። ከልክ ላለፈ ስራ ፣ ለአንዳንድ ሱሶች፣ ለጓደኛ ፣ ለማህበራዊ ህይወትና ለተለያዩ ከቤት ውጪ ለ ሚደረጉ ክንውኖች ሰፊውን ጊዜ በመስጠት ፤ በነዚህም ምክንያቶች በአካል ደክሞ በመምጣት ፤ ከትዳር ጓደኛና ከቤተሰብ ጋር በቂ ጊዜ ማጣት አለመ ተማመንን እየፈጠረ ወደ አላስፈላጊ ጭቅጭቅና ግጭት ይከታል። ለቤተሰ ብ በቂ ጊዜን መስጠት አለመቻል ፤ ከልጆች ጋር አብሮ ማሳለፍ የሚገባውን ወርቃማ ጊዜ ስለሚቀንስና ፤ ልጆችም ከቤተሰቦቻቸው በቂ ፍቅርንና የጠበ ቀ አንድነትን አጥተው እንዲያድጉ በማድረጉ ፤ ዘላቂ ህይወታቸው የተዛባና የስነልቦ ችግር እንዲኖርባቸው ያደርጋል። ከቤተሰብ ጋር አብሮ በመውጣት ፣ በመዝናናት አንዳንድ አጋጣሚዎችን በመጋራት በሚፈጠር ደስታ፤ የበለ ጠ መተሳሰብ ፣ መዋደድና መተማመንን የሚያጠናክርና ለተሻለ ግንኙነትና የፍትወት ፍላጎትም የሚጋብዝ ነው።

50

ኢትዮጵያ መጽሄት 33ኛ ኛ እትም | 2003 2004 ዓ/ም

ጋብቻና ገንዘብ በያዝነው የ21ኛው ክፍለ ዘመን ፤ ገንዘብ በሰው ልጆች ህይወት ውስጥ ያለው ቦታ ትልቅ ቢሆንም በትዳር ውስጥ ግን ከአስፈላጊዎቹ ነገሮች መካከል እንደ አንዱ ተደርጎ መወሰድ ይኖርበታል። ምክንያቱም ብቸኛ የደ ስታ አምጪ በማድረግ ሌላውን የህይውት መንገዶች ላለመዘንጋት ማስተዋ ል ላለመጋረድ ነው። ገንዘብ በየቤቱ ያለው አጠቃቀም የተለያየ በመሆኑ የ ሌሎችን ኑሮ በመመልከት ፤ እራስንም ሆነ ቤተሰብን በአካል ፣ በአእምሮም ና በማቴርያል ከሌሎች ጋር ማወዳደር ወደ አላስፈላጊ አዘቅት ይከታል ። የ ራስን የኑሮ አቅም መመጠንና ማወቅ ፣ ከፕሮግራም ውጪ በግድየለሽነት፣ በፉክክር ወይም ለታይታ በሚደረጉ አጓጉል ወጪዎች ምክንያት ቤተሰብን እዳ ውስጥ ከመዝፈቅ ያድናል። በተጨማሪም እዳው ከሚፈጠረው ጭንቀ ትና በየቀኑ ከሚያስነሳውም ንትርክ ፣ የሰላም መደፍረስና በኑሮ ደስተኛ አለ መሆንን ያድናል። የገንዘብ አያያዝ በጥንቃቄ ካልተመራ ለቤተሰብ መፍረስ ዋነኛ ምክንያት ነው። ሁለቱ ጥንዶች በራሳቸውና ከጓደኞቻቸው ጋር በሚ ኖራቸው ጊዜ ፤ ሊጠቀሙበት የሚገባ የኪስ ገንዘብን መመደብ ከጋራ ውሳ ኔ ውጪ በሚደረጉ ወጪዎች ከሚከሰቱ አለመግባባቶችና ግጭቶች ይቆጥባ ል። ከቤተሰብ ተደብቆ ለራስም ሆነ ወላጅና ቤተሰብን ለመርዳት የሚደረግ ወጪ ትዳርን ይጎዳል ፣ አለመተማመንን ይፈጥራል። እንግዲህ የትዳር ጥን ዶች አንድ አካልም ቢሆኑ ሁለት ሰዎች በመሆናቸው ፤ የሁለቱ ሰዎች ፍላጎ ትና ያኗኗር ዘይቤ ደግሞ የተለያየ በመሆኑ ፤ ሁሉንም ጉዳዮች በመመካከር ና በመቻቻል ለመፍታት መሞከር በሳልነት ነው። ለመንደርደሪያ ጥቅል በሆ ነ መልኩ ዋነኛ የሆኑትን የትዳር ችግሮችና መፍትሄዎች ተመልክተናል በሚ ቀጥሉት ህትመቶች ደግሞ ሌሎች የቤተሰብን ህይወትና ግንኙነትን ሊረዱ የ ሚችሉ ጉዳዮችን በማቅረብ አንባቢያንን ለበለጠ ግንዛቤ እንዲረዳ እናደርጋ ለን። ደህና ቆዩን። ከዝግጅት ክፍላችን


Ethiopia Magazine Issue 3 | 2011 2012

51


ማንኛውም ስራ የራሱ የሆነ ውጣ ውረድ አለው። ሁሉም የሥራ ዓይነት የተከበረ ነው። የሥራውን ዓይነት መጥፎም ሆነ ጥሩ ነው ለማለት ፤ በ ተለይም ባለሙያው ለመረጠው ሙያ በቂ ምክንያት ካለው፡ በባለሙያው እይታና አንደበት ቢደመደም ያምራልና ለባለሙያው እንተወዋለን። ነገር ግን ይህ አምዳችን ታክሲና በታክሲ ዙሪያ ያሉ ጉዳዮችን የምናቀርብበት በመሆኑ ፤ በዚህ እትማችን በሎስ አንጀለስ የሚገኘው “ዩ ሲ ኤል ኤ” ተብሎ በሚጠራው ትልቁ የትምህርት ተቋም የስራ ዘርፎችን የሚያጠናው ክፍል ፤ በዚህ የስራ ዘርፍና በስራው ላይ ስላሉ ሰዎች ካ ደረገው ጥናታዊ መረጃ ከፊሉን በመውሰድ አቅርበንላችኋል። ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ በአብዛኛው ከሌሎች ስቴቶች የታክሲ አሽከርካሪዎች ጋር ልዩ ነት የለውም። በተለይ የሚያተኩረው ታክሲን በመከራየት በሚያሽከረክሩት ላይ ነው። ጥናቱም 302 የታክሲ ሾፈሮችን ለናሙና በማሰባሰና ቃ ለ መጠይቅ በማድረግ ይህን ጥናታዊ መረጃ ሲያሰባስብ ፤ የታክሲ መስራቤቶች እና የታክሲ መቆሚዎች ፤ እንዲሁም በሎስ አንጀለስ አውሮፕ ላን ማረፊያ (ኤል. ኤ. ኤክስ) ድረስ በመገኘት ነበር። ከእነዚህም ውስጥ 21 ቃለመጠቅ በማድረግ የጠለቅ ጥናት ተደርጓል። በተጨማሪም አሰራ ርን በተመለከት 20 የታኪስ መስራቤቶችን ቃለ መጠየቅ አድርጓል።

“ረዥም ሰዓት ዝቅተኛ ክፍያ ፤ ጭንቀትና ውጥረት የበዛበት ፤ጤንነትን የሚያውክ” ስራ ነው። ይህ ጥናታዊ ጽሁፍ ከላይ የተሰመረ በትን የመግቢያ ዓረፍተ ነገር በማተት ፣ በሞያ ው ላይ ያሉትን ቃለ መጠየቅ በማድረግ የቀረበ ነው። በአብዛኛውን ጊዜ በብዙዎች አእምሮ ታክ ሲ ማሽከርከር ጊዜያዊና ለሌላ የስራ መስክ መሸ ጋገሪያ ይሆነናል ብለው እንደሚጀምሩት ይናገራ ሉ። ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያሳዩት ተጻራሪ ሆ ኖ ተገኝቷል። ብዙ አሽከርካሪዎች ወደዚህ የስ ራ ዘርፍ እንዴት እንደ ገቡም ሲጠኑ “ከሌላ ሀገ ር በመምጣታችን ሌላ ስራ ለመስራት እንደምን ችል እይታችን ውስን በመሆኑ ፣ የታክሲ ካምፓ ኒዎችም ክፍት የስራ ቦታ ሲኖራቸው ማስታወቂ ያቸውን በተለያዩ ቋንቋዎች በተለያዩ ሀገር ማህ በረሰብ ጋዜጦች ላይ በመጻፋቸው፣ ያለተቆጣጣ ሪ በራስህ ሰዓት ሰርተህ መግባትና መውጣት መ ቻል” በሚሉት ሀሳቦች በመሳብ መሆኑን ገልጸዋ ል። አብዛኛው የታክሲ አሽከርካሪዎችም ከመጡ በት ሀገር በነበራቸው የትህምርት ደረጃና በነበራ ቸው የሙያ እውቀት ፤ ስራው ከሚጠይቀው መ ስፈርት በላይ የሚያሟሉ እንደሆኑ ገልጸዋል። በጥናቱ መሰረት አብዛኛው አሽከርካ ሪ በአማካኝ በሳምንት ከ72 ሰዓታት ያላነሰ ይ ሰራል። ብዙ አሽከርካሪዎች ረዥም ሰዓት በትራ ፊክ በተጨናነቀ መንገድ ላይ መንዳት በጤንነታ ቸው ላይ ጉዳትን እንዳስከተለ ገልጸዋል። የህክ ምና ምርመራ ውጤታቸው እንዳረጋገጠው ከግ ማሽ በላይ የሚሆኑት በጀርባና በእግር ላይ የጤ ና ችግር ይታይባቸዋል ። ሌሎች ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ደግሞ ስራው በተለይ በአእምሮ ላይ 52

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ስላለው ውጥረት አስረድተዋል። በብዛቱ 12 ሰዓትና 6 ቀናት በመስራ ት ካለው ውጥረት በተጨማሪ ፤ ከሌላ ሀገር የ ፈለሱ በመሆናቸው በቋንቋ ችሎታቸው የተነሳ ዘረኛነት የተሞላበት ንግግርና ወንጀል እንደተፈ ጸመባቸው ያትታሉ። ባለፈው ዓመት ማለትም በ2010ዓ/ም ብቻ 36.5% ከመቶው በሚሆኑ ት ላይ ተሳፋሪዎች በዘራኝነት የተሞላ ስድብ ወ ይም በሀገራቸው ላይ መጥፎ አስተያየትን ሰንዝ ረውባቸውል። 25% ከመቶው የሚሆኑት ደግ ሞ የማስፈራራት ዛቻ አጋጥሟቸዋል። በአካላቸ ው ላይም ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ረዥም ሰዓታት መስራቱ ከቤተሰቦቻ ቸው ጋር የሚያሳልፉትን ጊዜ ከማሳነሱ ባሻገር ፤ ከ8 ሰዓታት በላይ ለሰሩት ስራ ተጨማሪ ክፍ ያ ሳይሆን እንደመደበኛው ሰዓት ክፍያ ተቆጥሮ መከፍሉ አግባብ እንዳልሆነ በዚሁ ጥናቲዊ ጽ ሁፍ ተተችቷል። 61% የሚሆ ኑት ማንኛውም አይነት የህክ ምና ዋስትና የላቸውም። ከእነ ዚህም 42% ለልጆቻቸው ህ ክምናን የሚያገኙት ከመንግስ ት የህክምና እርዳታ ተቋሞች ነው። በታክሲ ውስጥ እ ግርን ለማፍታት በቂ ቦታ አ ለመኖር ፣ የቀኝ እግራቸው ለ12ሰዓት ያህል በነዳጅ መስ ጫው ላይ ወይም በፍሬን ላ ይ በመጫን በመዋልና ፤ የግ

ራ እግር ደግሞ ያለ ብዙ ንቅናቄ በመቀመጡ እን ደማሸንከል ያለ የጤና መዛባት ይታይባቸዋል። አንዳንዶች በተደጋጋሚ ክፍያን ለመቀበል እና ለ መመልስ የሚያደረጉት መዞር የጀርባ ህመም እን ዳደረሰባቸው ገልጸዋል። በተጨማሪም በዚህ ረ ዥም የስራ ሰዓት ፤ ለምግብ የሚያርፉበትን ጊዜ በስራ በማሳለፍ የተሻለ ገቢን ለማስገባት ከማሰ ብ የተነሳ ፤ የሚመገቡት ምግብ አብዛኛውን ጤ ናማ ባለመሆኑና ፤ በቂ የአካል እንቅስቃሴ ባለማ ድረግ የሰውነት ክብደት መጨመር ፣ የልብ በሽ ታ ፣ እንዲሁም ለሽንት በሰዓቱ አለመሄድና ሽን ትን በመቋጠር ለኩላሊት በሽታ የተጋለጡ አድር ጓቸዋል። 61% የሚሆኑት ልጆች እንዳላቸው ሲገልጹ ፤ ከልጆቻቸውና ከቤተሰባቸው ጋር በቂ ጊዜ አለማግኘት ፤ የመኝታና የመመገቢያ ሰዓቶ ች አለመጣጣም ፤ አባት ስራ ላይ በመዋሉ እናት


ለብቻዋ ልጆችን በመንከባከብ ላይ ያለውን ተጽ ኖ አማረዋል። ሀዳድ የተባለ አሽከርካሪ ቁጭቱን ሲገልጽ “ ልጆቼን አላውቃቸውም ምክንያቱም ከእኔ ጋር ስላላደጉ . . . በአካል መኖሬ ጥቅም የ ለውም።” ሙስጠፋ የተባልው ሌላ አሽከርካሪም ቤተሰቦቹ እንደሚረዱት ተናግሮ ነገር ግን “ልጆ ቼ በፍጹም ደስተኛ አይደሉም ምክንያቱም ከእነ ርሱ ጋር ጊዜ ለማላሳልፍ ባለመቻሌ” ብሏል። ዶ ናልድ ከትዳሩ ተለያይቶ ከትልቅ ሴት ልጁ ጋር የ ሚኖር አሽከርካሪ ሲሆን ወንድ ልጁን እና ሌሎች ቤተሰቦቹን ማየት እንደተቸገረና ፤ በስራው ምክ ንያት በወንድ ልጁ ልደት ላይ እንኳን ለመሄድ ፈ ልጎ መሄድ ባለመቻሉ ማዘኑን በዚሁ ጥናታ ዊ ቃለመጠየቅ ላይ ተናግሯል። የቀረበት ም ምክንያት ከቀረ ለካምፓኒው መከ ፈል ያለበትን መክፈል ስለሚኖርበ ት ነው። ከሌሎች ጥናቶችም እንደተገኘው እነዚህ የታክሲ አሽከርካሪዎች 47 ከሚጠጉ የተለያዩ ሀገሮች የመጡ ሲሆ ኑ። 38% ከመሀከለኛው ምስ ራቅ እና ከፓኪስታን ፣ 18% ከቀድሞው ሶቪየት ህብረት ፣ 18% ከአፍሪካ ፣ 12% ከላቲ ን አሜሪካ ናቸው። አማካኝ እድ ሜያቸውም 47 ዓመት እንደሆነ ጥናቱ ይጠቅሳል። እነዚህ አሽከርካ ሪዎች ተከራይተው የሚያሽከረክሩና ኑሮአቸውም ቀኑን ሙሉ ሰርተው በሚ ያገኙት ገቢ ላይ የተወሰነ እንደሆነ ያስረዳ ል። ብዙዎች ፦ የእረፍት ጊዜ ካለኝ ወጥቼ ምግብ ከገ በያ እገዛለሁ ፤ ልብሴን አጥብበታለሁ ፤ አለበለዚ ያም ስለሚደክመኝ እተኛለሁ። ወይም ተጋድሜ ከቴለቪዥን ጋር አሳልፋለሁ ብለዋል። እንደ ብዙዎች አባባል ከቤተሰብ ጋር ስላለው ሰዓታቸው ሲናገሩ “ከስራ ስመጣ እታጠ ባለሁ ፤ ትንሽ እበላና እተኛለሁ ከእንቅልፌ ስነሳ ልጆቼ ተኝተዋል እኔም ወደ ስራ እገባለሁ። ተመ ሳሳይ የህይወት ድግግሞሽ!” ኦማር የተባለ አሽከ ርካሪ ቤተሰቦቹ ምን አይነት ሰው እንደሆነና ምን ላይ እንዳለ እንደማያውቁ ገልጾ ፤ በሳምንት አን ዷን የእረፍት ቀኑን ከቤተሰቦቹ ጋር ተገናኝተው አብረው እንደሚመገቡና ፤ በዚያን ጊዜ ብቻ እን

ደሆነ ከልጆቹ ጋር ጊዜ የሚያገኘው ፤ ያንንም ጊ ዜ በጥንቃቄና ራሱን በመቆጣጠር እንደሚያሳል ፍ ተናግሯል። “ልጆችህ በሚናገሩት ነገር ትገረ ማለህ ፣ ግራ ትጋባለህ ፣ አንዳንዴም ትበሳጫለ ህ። በቦታው ስላልነበርክ በሚናገሩትና በሚያደ ርጉት ነገር ላይ ሀሳብ መሰንዘርም ሆነ መክራከር አትፈልግም ፣ ብትፈልግም አእምሮህ በስራው ስ ለተበላ በዝምታ ታልፈዋለህ” ይላል።

በዓለም ለ መኪና አደ ጋ ዋነኛው ምክንያት የሆነው ጉዳይ ከሰውነት መ ዛልና ከአዕምሮ መዳከም ጋር የተገናኘ እንደሆነ የ መንገድ ትራንስፖርት አጥኚዎች አረጋግጠዋል። እነዚህ የታክሲ አሽከርካሪዎች በደከማቸው ጊዜ ምን እንደሚያደርጉ ሲጠየቁ ፦ አንዳንዶች አል ፎ አልፎ እንደሚያቆሙና አንድ ነገር ገዝተው እ ንደሚመገቡ ፣ የሚያነቁና ጉልበት ሰጪ መጠጦ ችን እንደሚጠጡ ፣ ወይም ከመኪናው ወጥተ ው በእግራቸው ወዲህ ወዲያ እንደሚሉ ፣ መኪ ናው ውስጥ እንደሚተኙ ወይም ቤታቸው ሄደ

ው እንደሚያርፉ ገልጸዋል። አንዳንዶች ደግሞ ከሌሎች አሽከርካሪዎች ወይም ከተሳፋሪዎቻቸ ው ጋር እንደሚነጋገሩ ሲገልጹ ሌሎች ደግሞ እን ደሚያነቡ ተናገረዋል። የሎሳንጀለስ ታክሲ አሽከርካሪዎች በ ስራው ላይ ያላቸው ቆይታ ፤ በአማካኝ 9.5 ዓ መት ሲሆን የታክሲ ባለቤት የሆኑት ደግሞ እስ ከ 12 ዓመት ሲያሽከረክሩ ፣ ታክሲውን በመከራ የት የሚሰሩ (ብዙ ጊዜ ሊዙ ለሳምንት ሲሆን) በ አማካኝ 8 ዓመታት ይሰራሉ። 23% የሚሆኑት ለሶስት ወይም ከዛ በታች የሚሆን ዓመታት አሽ ከርክረዋል። በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩ ብዙዎች ሲናገ ሩ ፤ በአጠቃላይ በስራው ላይ ሙዚቃ ወይም ሬድዮ መስማት ማስተዋላቸ ውን እንደሚወስድና ለአድጋ ሊያ ጋልጣቸው እንደሚችል በመግ ልጽ ፤ የግል ኢንሹራስ ስለሌ ላቸው የአደጋው መድረስ ደ ግሞ በተሳፋሪዎችና በራሳቸ ው ላይ የሚያስከትለውን ች ግር የከፋ ስለሚያደርገው በ ጣም በጥንቃቄ እንደሚያሽ ከረክሩ ገልጸዋል። በቂ ገቢ ባለማግኘትና የህክምና ወ ጪን መሸፍን ብቃት ማጥት የተነሳ ብዙዎቹ ሳይመረመሩ ወይም ሳይታከሙ ለብዙ ጊዜያ ት በስራው ላይ እንዲቆዩ አድርጎአ ቸዋል። ስኬትን በተመለከተ አንዳን ዶች ከተራ አሽከርካሪነት ተነስተው በማ ደግ የካምፓኒ ባለቤት እንደሆኑ ከዚያም ሌ ላ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠሩ የሪል ስቴት ባለቤ ቶች በመሆን እንደተሳካላቸውም ገልጸዋል። የእ ነዚህንም ሰዎች ስኬት እንዴት ሊሆን ቻለ? ለሚ ለው ጥያቄ ጠንክሮ በመስራት ወይም በእድል ነ ው! ከማለት ውጭ ምንም አይነት አስተየት እን ደማይሰጡም ገልጸዋል። እንግዲህ በከተማችን በላስ ቬጋስ ያለ ው የታክሲ አቀጣጠርና የአሰራር ሁኔታ ከሌሎች ከተሞች የተለየ በመሆኑ ያንን በተመለከተ በጥና ት የተደገፈ ጽሁፍ ወደፊት እናስነብባችኋለን። እ ስከዚያው ቸር ይግጠመን። ከዝግጅት ክፍላችን

Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

53


የስኳር በሽታ(ዳያቤቲስ) የሚፈጠረው በደማችን ውስጥ በቂ ኢንሱሊን ባለመኖር ወይም ሰውነታችን ለኢንሱሊን አልበገር በሚልበት ጊዜ ነ ው። ይህ በሽታ ስር-ሰደደ የዕድሜ ልክ በሽታ ነ ው። ተለይቶ የሚታወቅበትም ምልክትም በደም ውስጥ ከፍ ያለ ስኳር መጠን ሲከሰት ነው።

ሶስት ዓይነት የስኳር (የዲያቤቲስ) በሽታዎች አሉ። 1ኛው ዓይነት ፦ የኢንሱሊን ጥገኛ በ መባል ይታወቃል። ብዙውን ጊዜ የሚከሰተው በ ወጣቶች ላይ ነው። ብዙዎቹ በሽተኞች ይህ የስ ኳር በሽታ የሚገኝባቸው ከሀያ ዓመት ጥቂት ከፍ ሲሉ ነው። ይህንንም ለማስተካከል ወይም ለማከ ም ኢንሱሊን ግዴታ አስፈላጊ ነው። ለዚህ ነው የ ኢንሱሊን ጥገኛ የተባለው። በዘርም ሊመጣ ይች ላል። ይህ ዓይነቱ የዲያቤቲስ በሽታ ያለባቸው ሰ ዎች ኢንሱሊንን መወጋት ግዴታቸው ነው። የበሽ ታው ምልክቶች ፦ ድካም ድካም ማለት፣ ከመጠ ን በላይ የሆነ የውሃ ጥማት፣ ብዙና ቶሎ ቶሎ መ ሽናት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ ምንም እንኳን የ ምግብ ፍላጎት የበዛ ቢሆንም ክብደት መቀነስ ናቸ ው። እነዚህ ምልክቶች የሚከሰቱት በቶሎ ቢሆን ም ብዙውን ጊዜ የሚታወቁት በድንገተኛ አጋጣ ሚ ነው። ኢንሱሊን የሚወጋው ስብ በሆነው የአ ካላችን ክፍል ላይ ነው። ኢንሱሊን መውጊያ መር ፌዎች በጣም ቀጫጭኖች ናቸው። ብዙም ይህ ነ ው ለሚባል ህመም አይዳርጉም። ሆኖም አንድ ቦ ታ ላይ በተዳጋጋሚ ከተወጉ ቁስለትን ሊፈጥሩ ስ ለሚችሉ መርፌው በተለያዩ ቦታዎች ላይ መወጋ ት ይኖርበታል።

2ኛው ዓይነት፦ ቀለል ያለው የስኳር በሽታ ሲሆ ን ፤ የተመጣጠነ ምግብ በመመገብና አካላዊ እን ቅስቃሴን በማዘወተር ፣ በተጨማሪም የደም ስኳ ርን (ግሉኮስ) ሊቀንሱ የሚችሉ መድሃኒቶችን በ መውሰድ መቆጣጠር ይቻላል። ይህ ዓይነት ዲያ ቤትስ ያለባቸው ሰዎች ኢንሱሊን መውጋት ላይኖ ርባቸው ይችላል። ብዙውን ጊዜ የዚህ ዓይነት ስ 56

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ኳር በሽታ ሰለባ ሊሆኑ የሚችሉት ፦ ክብደት ያ ላቸው በተለይ ቦርጫቸው አካባቢ ብዙ የስብ ክ ምችት ያላቸው፣ በቂ አካላዊ እንቅስቃሴ ባለማድ ረግ፣ ከ45 ዓመት እድሜ በላይ መሆን። በቤተ ሰባቸው ውስጥ የስኳር በሽታ ያለባቸው፣ የልብ በሽተኛ የሆኑ ፣ በእርግዝና ወራት ስኳር የተያዙ ሴቶች ወይም የሚወልዱት ልጅ ከ4.5 ኪሎ በላ ይ መሆን፣ በደም ውስጥ ያለው ኮልስትሮል መጠ ን ከፍ ማለት፣ በስቴሮይድ የተነሳ ከፍ ያለ የደም ስኳር ያለባቸው ከፍተኛ የደም ግፊት ያለባቸው ፣ ብዙ ውሃ የቋጠረ የአኮረት ዕጢ (Ovaries)፣ ከመሰረቱ የተጎሳቆለ የግሉኮዝ አለመስማማ ት(Intolerance)፣ አንዳንድ የሰው ዘሮች (አፍ ሪቃ-አሜሪካኖች ፣ የአሜሪካን ተወላጆች፣ የእስያ ና የእስፓኒያን ዘሮች በተፈጥሮ ለስኳር በሽታ የተ ጋለጡ ናቸው። ለስኳር በሽታ ሊጋለጡ ይችላሉ ተብለው የሚጠረጠሩ ገና ሲወለዱ ከፍተኛ ክብ ደት ያላቸው ልጆች፤ ከአሥር ዓመት ዕድሜ ጀም ሮ በየሁለት ዓመት በመደጋገም ስኳር እንዳለባቸ ውና እንደሌለባቸው መመርመር ይኖርባቸዋል። 3ኛው ዓይነት - በእርግዝና ወቅት የሚ ከሰት ሲሆን ይህንን በሌላ እትም በስፋት እንመለ ከተዋለን። የስኳር በሽታን አመጣጥና ሂደት ለመረዳት ምግ ብ እንዴት ተፈጭቶ ኃይልና ጉልበት ሰጪ ሆኖ እንደሚያገለግል አጣርቶ ማወቁ ይረዳል። ግሉኮ ስ (በሰውነታችን ውስጥ የተቀመጠው የስኳር ስ ም ነው) ለሰውነታችን ሃይል በመፍጠር ይረዳና ል። ማንኛውም ምግብ ስንመገብ ተላምጦና ታኝ ኮ በጨጓራችን አማካኝነት ተሰልቆ ከተፈጨ በኋ ላ። በጣፊያ ውስጥ ያሉት የላንገርሃንስ ደሴቶች ስ ኳሩን ለመቆጣጠር ኢንሱሊን ያመርታሉ። እንደ ምግቡ ብዛትና ከባድነት ጣፊያ ኢንሱሊንን ለማ ምረት ከፍ ያለ ስራ መስራት ይኖርበታል። ሲደጋ ገም እና ሲበዛ ጣፊያ ስራውን መቆጣጠር ያቅተዋ ል። ምርቱም ይቀንሳል ውጤቱም አስከፊ ሊሆን ይችላል። የስኳር በሽታ ሰለባ የሚሆን ሰው በድን ገት ሁኔታዎች ይለወጡበታል። “ሰሞኑን ተቸግሬ ያለሁ፣ ምን ሆኜ ይሆን? ውሃ በጣም ይጠማኛል፣ ሽንትም በብዛት እሸናለሁ። የምጠጣው ውሃ ፈጽ

ሞ ጥማቴን ሊያረካልኝ አልቻለም፣ ሰውነቴም እ የደከመና ክብደቴም እየቀነሰ ነው በማለት ማማረ ር ይጀምራል።

ኢንሱሊን ምንድነው ለምንስ ያስፈልጋል? በ1921 ቤስታና ባፒንግ የተባሉ ሰዎ ች ስለ ኢንሱሊን አስደናቂ የሆነ ግኝት አደረጉ። ይ ኸውም ኢንሱሊን በሰውነታችን (በደማችን) ውስ ጥ የሚዘዋወረውን ስኳር ለመቆጣጠር ወይም ለ ማስተካከል ከፍ ያለ ሚና እንደሚጫወት ነው። በጣፊያ አማካይነት የሚመረቱ ዋነኞቹ ንጥረ-ነገ ሮች ኢንሱሊንና ግሉካጎን (ግሎኮዝ) ሲሆኑ፤ ዓብ ይ ሥራቸውም በመላው አካላችን ውስጥ ያለውን የደም ስኳር መጠን ማስተካከል ፣ ከደማችን ወደ ጡንቻዎቻችን፣ ስቦቻችንና ወደ ጉበታችን ማከፋ ፈል ነው። የደም ስኳር መስተካከል የውስጥ አሠ ራጭ ዕጢዎች (Endocrine ) ሥራቸውን በስ ነ-ሥርዓት እንዲሠሩ ያደርጋል። ለዚህም ሥራ ኃ ላፊውና ንጥረ-ነገሮችን አምራቹ በጣፊያ ውስጥ የ ሚገኘው ላንገርሃንስ ደሴት የሚባለው የጣፊያ አ ካል ነው። ኢንሱሊን ባይኖር ኖሮ የሰውነታችን ህ ዋሳት ይወድሙ ነበር። አንጎላችንም በሃይል ማነ ስ የተነሳ እየደከመ ስራውንም በትክክል መስራት ይሳነው ነበር።

የኢንሱሊን አልበገር ባይነት(Resistance) ለኢንሱሊን አልበገር ባይነት የሚባለው የስኳር በሽታ ሰውነታችን ውስጥ በጣፊያ አማካ ኝነት የሚመረተውን ኢንሱሊን በስርዓት ሳይጠቀ ምበት ሲቀር ነው። ሰውነታችን ለኢንሱሊን አልበ ገር በሚልበት ወቅት ጡንቻዎቻችን፣ የሰውነታች ን ስቦችና የጉበት ህዋሳት ሰውነታችን ለኢንሱሊን አልበገር በማለቱ ይደናገራሉ። በዚህ የተነሳ ሰው ነታችን ተጨማሪ ኢንሱሊን እንደሚያስፈልገው ለ ጣፊያ መልዕክት ያስተላልፋል። ጣፊያም የተቻለ ውን ያህል ተጨማሪ ኢንሱሊን ያመርታል። ጣያ ፊያችን ተጨማሪ ኢንሱሊን ማቅረብ ካልቻለ ስኳ ር በደም ውስጥ በመከማቸት ወደ 2ኛው አይነት የስኳር በሽታ ለመለወጥ ይዘጋጃል።


ከፍ ያለ የደም ስኳር (ግሉኮዝ) ክምችት በሰውነታችን ወስጥ ግሉኮዝ በሰውነታችን ውስጥ የተቀመ ጠው የስኳር ስም ነው። በሰውነታችን ውስጥ መ ከማቸት ሲጀምር ወደ መርዝነት ይለወጣል። ህዋ ሳታችንን እና አንዳንድ የአካላችንን ክፍሎች በ ማበላሸት ከስራ ውጭ ያደርጋቸዋል። ከፍ ያለ የስ ኳር (ግሉኮዝ) ክምችት እስከ ኮማ አልፎም ወደ ሞት ሊያደርስ ይችላል። ከፍ ያለ የስኳር ክምችት በሰውነታችን ውስጥ ሲኖር ውሃ በጣም ይጠማና ል፣ ቶሎ ቶሎ ያስሸናል፣ ብዙ ያልበናል። ይህም ሰ ውነታችን የተከማቸውን የሱኳር ክምችት ለመቀ ነስ የሚያደርገው ሙከራ ነው።

ዝቅ ያለ የደም ስኳር? የደም ስኳር ከ70-ሚ/ግ በታች ዝቅ ካ ለም ጥሩ አይደለም። ይህ ብዙ ጊዜ የሚከሰተው የዲያቤቲክስ እንክብካቤ ወይም ኢንሱሊን በሚ ወስዱ ሰዎች ላይ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ዝቅተ ኛ የደም ስኳር የሚከሰተው መድሃኒት ምግብና አ ካላዊ እንቅስቃሴ ባንድነት በስምምነት ሳይሰሩ ሲ ቀር ነው። ብዙ አካላዊ እንቅስቃሴ፣ በሰዓቱና በቂ ምግብ ባለመመገብ እና ብዙ መድሃኒት በመውሰ ድ የሚፈጠር ነው። ዝቅ ያለ የደም ስኳር የሚከ ተሉትን ስሜቶች ያስከትላል፦ መንቀጥቀጥ፣ ድካ ምና የእንቅልፍ ስሜት፣ ማላብ፣ መደናገር ወይም የብስጭትና የመነጫነጭ ስሜት፣ ረሃብ፣ ራስ ማ ዞር፣ ሌሊት በብዛት መወራጨት የመሳሰሉት ናቸ ው። የስኳር ማነስ ስሜት ሲሰማን በአስቸኳይ በ ደም ውስጥ ያለውን የስኳር መጠን መለካት ያስፈ ልጋል። ከትክክለኛው የስኳር መጠን በ15 ግራም ዝቅ ብሎ ከተገኘ በአስቸኳይ ሊያስተካክሉት የሚ ችሉ ከፈተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦች መ መገብ ያስፈልጋል። እነዚህም ውስጥ እንደ ግማሽ ስኒ የፍራፍሬ ጭማቂ ወይም ግማሽ ጣሳ ሶዳ አ ሊያም ሶስት የግሉኮዝ እንክብሎች ካልሆነም ሶስ ት ከረሜላዎችን መውሰድ ሊያስተካክለው ይችላ ል። ከጥቂት ቆይታም በኋላ በድጋሚ በመለካት አ ሁንም ዝቅ ያለ ከሆነ በድጋሚ ከላይ ከተጠቀሱት አንዱን መውሰድ ያስፈልጋል። ዝቅ ያለ የደም ስኳ ር ስሜት ሲሰማንና መለካት የማንችልበት አጋጣ ሚ ከተፈጠረ እራሳችንን በራሳችን መርዳት እሰከ ሚያቅተን ድረስ አለመጠበቅ የተሻለ ነው። በተቻ ለም በምን ምክንያት ዝቅ እንዳለ ለማወቅ መሞክ ር። ማለትም ብዙ የአካል እንቅስቃሴ በማድረግ? በቂ ምግብ ባለመመገብ? ትክክለኛውን ምግብ ባ ለመመገብ ወይም በምን ምክንያት እንደሆነ ለመ ረዳት መሞከር ያስፈልጋል።

የግሉኮዙ መጠን ስንት ሲሆን ነው ትክክለኛ ነው የሚባለው? የደም ስኳርን ልክ በመለካት ለመቆጣጠር የግ

ሉኮዝን ልክ ማወቅ ያስፈልጋል። ሁነኛው የደም ስኳር ልክ 60-120 ሚ/ግ ነው። ትክክለኛው የ ደም ስኳር መለኪያው ሰዓት ደግሞ ምግብ በመ መገቢያ ሰዓት ነው። ይህ ትክክለኛውን መጠን ይ ሰጠናል። ጧት በባዶ ሆድ በሚለካበት ጊዜ ከ110 ሚ/ግ/ዲሲ ሊትር ጥቂት አነስ ካለ፣ ከበሉ ከሁለት ሰዓቶች በኃላ ሲለካ ደግሞ ከ140ሚ/ግ/ዴሲ ሊት ር አነስ ሲል ነው። የስኳር በሽታ ያለባቸው ሰዎች በደማቸው ውስጥ ያለውን የስኳር ልክ ቢያንስ በ ቀን 4 ጊዜ መለካት ይኖርባቸዋል። አንድ ሰው ሁ ለት ጊዜ ተደጋግሞ በተወሰደ የደም ስኳር ምርመ ራ አማካኝነት ደጋግሞ 126 ሚ/ግ ከተገኘበት ዲያ ቤቲስ ማሊቱስ እንዳለበት ይቆጠራል።

የደም ስኳር ከፍ ሊል የሚችልባቸው ምክንያቶች ብዙ በመመገብ፣ በስራ ወይም ሌላ በኑሮ ው ስጥ ጭንቀት ሲኖር፣ መድሃኒትን በስርዓቱ ባለመ ውሰድና በመታመም። በተለይ በተወሰን የቀን ሰዓ ት የደም ስኳር ወደላይ ከናረ ሃኪምን ወይም የስ ኳር በሽታ አስተማሪን ማማከር ያስፈልጋል። በተ ጨማሪም ምን እንደሚሰማን ለሃኪም ማስረዳት ጠቃሚ ነው። ለምሳሌ፦ የድካም ስሜት ሲሰማ፣ ብዙ ሽንት ሲያሸና፣ ከመጠን በላይ ውሃ ሲያስጠ ጣ፣ አይን ብዥብዥ ሲልና በደንብ ማየት ሲሳን። ምናልባት የመድሃኒት አወሳሰዱን ወይም የአመጋ ገብን ዘዴና ሰዓት ወይም የእለታዊ ንቅናቄን ማስ ተካከል ሊያስፈልግ ይችላል።

የስኳር በሽታ በሰውነታችን ላይ የሚያስከትላቸው ችግሮች የስኳር በሽታ ከሰውነታችን ጫፍጫፍ ያሉትን ጥቃቅን የደም ቧንቧዎች ቀስበቀስ በማ ጥበብ የደም ስርጭትን ያውካል። መጀመሪያ ሰለ ባ ከሚሆኑት አካሎች መካከል የአይንና የእግር ደ ም ቧንቧዎች ናቸው። አይኖች ብዥብዥ ከማለ ት አለፈው እስከ መታወር ይደርሳሉ። በአይን ላ ይ የሚከሰተው ብዥታና የማየት ድክመት ዲያቤ ቲክ ሬቲኖፓቲ ይባላል። መኪና መንዳት ቀስ በቀ ስ ይሳናቸውል። በወቅቱ ተረድተው መኪና መን ዳት ካላቆሙ በራሳቸውም ሆነ በሌሎች ላይ አደ ጋ ፈጣሪዎች ይሆናሉ። ሌላው የእግር ጣቶች መ

ቀዝቅዝ፣ መቁሰልና እስከ መቆረጥ መድረስ ሲሆ ን። በደም ቧንቧ ውስጥ የስብ መከማቸትና እስ ከ መደፈን መድረስ (አቴሮስክሌሮዚስ)፣ የልብ መ ጋቢ ደምስሮች መታመም(ኮሮናሮፓቲ) ፣ በስኳ ር ሳቢያ የሚመጣ የላሊት በሽታ(ዲያቤቲክ ኔፍ ሮፓቲ) ፣ በስኳር ምክንያት የሚመጣ የነርቭ በሽ ታ (ዲያቤቲክ ኒውሮፓቲ)፣ ከመጠን በላይ የስብ ክምችት(ሃይፐርላይቲደሚያ)፣ ከፍተኛ የደም ግ ፊት(ሃይፐርቴንሽን) ፣ የፊኛ ኢንፌክሽን ፣ የአንጎ ል ምት(ስትሮክ) እና የቆዳ መቁሰል የተወሰኑ ጠ ባዮች ናቸው። ከፍ ያለ የደም ስኳር መጠን ለደም ቧንቧዎች ጠር ነው። በሽተኛው(Intermittent Claudication) የተባለ ሁኔታ ላይ ይወድቃል። ይህ ማለት በሽተኛው በግሩ በሚጓዝበት ወቅት ከ ሃይለኛ የእግር ህመም በሽታ የተነሳ መንገዱን አቋ ርጦ ህመሙ እስኪታገስ ድረስ ማረፍ ይገደዳል። ከጊዜ በኋላ የሚቆምበት ጊዜና እርቀቱ እያጠረ ወ ይም እየቀነሰ ይሄዳል። ቀስ እያለም ከጊዜ በኋላ የ እግሩ ጣቶች መጥቆር ይጀምራሉ፣ ይደነዝዛሉ፣ በ ድን መሆን ይጀምራሉ። ይህ ነው በኋላ እግርን ለ መቆረጥ የሚያደርሰው። ነፍሱን ይማረውና የአን ጋፋውን አርቲስት የዶክተር ጥላሁን ገሠሠን የጤ ና ታሪክ ያስታውሷል?

ኬቶን አሲዶዚስ ምንድነው? በጤነኛ ሰው ሰውነት ኬቶኖች በጉበት ውስጥ ይመረታሉ፡፡ ኬቶኖች ሰውነታችን ተጨ ማሪ ጉልበት እንድናገኝ በአሲዳዊ ስቦች መፍረስረ ስ (Metabolism ) ምክንያት የሚመረቱ ተጨ ማሪ ውጤቶች ናቸው። በሰውነታችን ውስጥ የግ ሉኮዝ መጠን ሲቀንስ ወይም ከነጭራሹ ሲጠፋ በ ግሉኮዝ ምትክ ጉልበት እንድናገኝ ሰውነታችን በ ድንገት የተፈጠረውን የስኳር እጥረት ለማሟላት ወይም ለማስተካከል ተጨማሪ ኃይል ከሌላ ምን ጭ ማምጣት ግድ ስለሚሆንበት አሲዳዊ ስቦችን እንደ ድንገተኛ ደራሽ ለሰውነታችን በጉልበት ሠ ጪነት ይጠቀምባቸዋል። ይህ የሚከሰተውም በረ ሃብ ወይም በአንደኛው ዓይነት የስኳር በሽታ ወ ቅት ነው። የተወሰነ የኬቶን መጠን የሚወገደው በ ሣንባ አማካይነት ሲሆን። ከቁጥር የማይገባ በጣ ም ጥቂት ኬቶን በሽንት አማካይነት አልፎ አልፎ ሊወገድ ይችላል። ይህም ለጉዳት አይሠጥም ወ ይም የመታመም ምልክት ሆኖ ሊወሰድ አይገባው ም። ነገር ግን ከፍተኛ የኬቶን መጠን በሽንት ውስ ጥ መገኘት ከጀመረ ግን የአደጋ ምልክት ነው። ይ ህ የሚያሳየው የግሉኮዝ እጥረት በሚከሰትበት ወ ቅት ሰውነታችን ጉልበት ለማግኘት ሙሉ በሙሉ ኬቶኖችን ብቻ እንደ ኃይል ሰጪነት ስለሚጠቀም ነው። የሽንት ምርመራ በማድረግ ነው። ውጤቶ ቹም ጥቂት፣ መጠነኛና ከፍ ያለ ተብለው ይመደባ ሉ። መካከለኛ ወይም ከፍተኛ ኬቶን በሽንት ውስ ጥ መታየት በደማችን ውስጥ ከፍተኛ የስኳር ክም Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

57


ችት እንዳለ ያሳየናል። ይኸም አስቸኳይ የሃኪም እርዳታ ያሻዋል። የዳያቤቲክ ኬቶ አሲዶዚስ የስኳር በሽ ታ ያለባቸው ሰዎች በውነስነት(ሰውነታችን ውስ ጥ ያለው ፈሣሽ በመመጠጥ ከመጠን በላይ ሲቀ ንስ ወይም መጠጥ ሲል) ሁኔታ በምንገኝበት ወ ቅት ነው፡፡ ይህን የመሰለ ውጥረት በሚፈጠርበ ት ወቅት ለዚህ ሁኔታ ምላሽ ወይም ለማስተካከል ንጥረ-ነገሮችን ይመረታሉ፡፡ንጥረ-ነገሮቹ እንደ ኢ ንሱሊን የመሰለ ሊመክታቸው የሚችል ኃይል ስለ ሌለ (ምክንያቱም ኢንሱሊን ማምረቱን ወይ ጭራ ሹን አቁሟል ወይም ምርቱን በጣም ቀንሷል)፡፡ በዚህ ወቅት እንደግሉካጎንን ፣ የዕድገት ንጥረ-ነገ ርንና አድሬናሊንን የመሳሰሉት ንጥረ-ነገሮች ሰው ነታችንን ለማንቀሳቀስ የሚፈለገውን ኃይል ለማግ ኘት ከጡንቻ፣ ከስቦች፣ ከጉበት ሕዋሳትና ከስብ አሲዶች እየፈረፈሩ መውሰድ ይጀምራሉ፡፡ እነዚ ህ የስብ አሲዶች ኦክሲዴሽን በተባለ ሂደት ወደ ኬቶንነት ይለወጡና፤ ሰውነታችን የራሱን አካል ማለትም ጡንቻዎቹን፣ ስቦቹንና የጉበት ሕዋሣት ን መመገብ ይጀምራል፡፡ ይህም ሰውነታችን ከመ ደበኛው በመፍረስረስ (Metabolism) አማካይ ነት ካርቦሃይድሬትን በሀይል ሰጪነት በመጠቀም ፋንታ ስቦችን መጠቀም ይጀምራል፡፡ የዚህ ውጤ ት ስኳሩን ሊያስተካክል ይችል የነበረው ኢንሱሊ ን ስለሌለ፤ በደማችን ውስጥ ያለው የስኳር መጠ ን ይጨምራል፡፡ የስኳሩ መጠን ሲጨምር ኩላሊ ቶች ተጨማሪ የሆነውን ስኳር መያዝ ስለማይች ሉ ቶሎ ቶሎ መሽናት ይጀምራሉ ይህም ወደ ው ነስነት (የሰውነት ፈሣሽ መመጠጥ) ደረጃ ያመራ ል፡፡ የስኳሩ በሽተኛ ቀስ በቀስ ወደ ዳያቤቲክ አ ሲዶዚስ እየተንሸራተተ በሚገባበት ወቅት ከሰው ነታችን ጠቅላላ ክብደት አሥር ከመቶው ያህል ይ ቀንሣል፡፡ ይህም ጠቃሚ የሆኑ እንደፖታሲየም የ መሳሰሉትን ንጥረ-ነገሮችና ጨዎች በሽንት አማካ ይነት በማስወገድ ለባሰ ሁኔታ ይዳረጋል፡፡ አንድ ን የስኳር ሕመምተኛ ወደ ዳያቤቲከ ኬቶ አሲዶ ዚስ ሊከቱት ከሚችሉት ምክንያቶች በጥቂቱ ከዚ ህ የሚከተሉት ናቸው፡፡ •ተቅማጥ፣ ማስታወክና ከፍ ያለ ትኩሣት •የኢን ሱሊን ማነስ ወይም ፈጽሞ አለመኖር •አዲስ ተገ ኝ የስኳር በሽታ ወይም ከዚህ በፊት ኖሮት (ኖሯ ት) ግን በበሽተኛው ያልታወቀ የስኳር በሽታና ሌ ሎችም ተጨማሪ ምክንያቶች ይገኙባቸዋል፡፡

በስኳር በሽታ የተነሣ የሚከሰት የዓይን ርገብ መታወክ (ዳያብቲክ ሬቲኖፓቲ)

የስኳር በሽታ ከዓይን ርገብ በስተጀርባ የሚገኙትን ጥቃቅን የደም ቧንቧዎች ይጎዳል። የ ዓይን ርገብ ከዓይናችን ጀርባ የተሰመረ ብርሃን ወ ደ ዓይናችን እንዲገባ የሚያደርግ አካል ነው። ጥ ቃቅኖቹ የደም ቧንቧዎች በሚጎዱበት ወቅት ደም በዓይናችን ርገብ አካባቢ በመፍሰስ እብጠትን ይ 58

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ፈጥራል። ውጤቱም የደም ቧንቧዎች መዳከም ና ማበጥን ያስከትላል። በጊዜ ሊታከሙት ካልቻ ሉ የዓይንን ርገብ በመጋረድ እስከ መታወር ያደር ሳል። ይህንን ለማስተካከል ደም ስኳርንና የደም ግፊትን በደንብ ማስተካከልና መቆጣጠር ያስፈል ጋል፡፡ ዓይንን ሊጎዳ የሚችል (ዳያቤቲክ ሬቲኖፓ ቲ) የስኳር በሽታ በደም ቧንቧዎች ውስጥ ከመጥ ን በላይ የሆነ ግሉኮዝ ሊያከማች ይችላል፡፡

በስኳር በሽታ የተነሣ የኩላሊት መታወክ

(ዳያቤቲክ ኔፍሮፓቲ) ዋነኛው የኩላሊት በሽታ ችግር ብዙው ን ጊዜ ከፍተኛ አደጋ ላይ እስኪያደርስ ድረስ ምል ክት አይሠጥም፡፡ ሆኖም አልፎ አልፎ በሽንት ው ስጥ የሚወገደውን ፕሮቲን መጠንና ቆሻሻ በመመ ርመር በሽታውን ሥር ሣይሰድና ለክፉ ሣይዳርግ ሊደረስበት ይቻላል። ኩላሊት ሊታወክ የሚችለ ው በስኳር በሽታ አጉል ምጥ የተነሣ ነው። የስኳ ር በሽታ የታወቀና የተለመደ የኩላሊት ጠር ነው። ይህም ሊሆን የሚችለው ኩላሊቶች ብዙ ሥራዎ ች አሏቸው። በሰውነታችን ውስጥ ከመጥን በላ ይ ሆነው የሚገኙትን ፕሮቲን፣ ፈሣሾችና አንዳን ድ ንጥረ-ነገሮች ማስወገድ ከሥራዎቻቸው ዋናዎ ቹ ናቸው። ታዲያ ከዕለታዊ ሥራቸው አንዱ የሆ ነውን ቆሻሻዎችን ማጣራትና ከሰውነታችን ውጭ ማስወገድ ሲሳናቸው የደም ግፊት መጠን ከፍ ይ ላል፣ የጠረጋና ቆሻሻ ማስወገድ ሥራው ይዳከማ ል። ይህም የቀይ ደም ሕዋሣት ምርትንም እንዲቀ ንስ ያደርጋል። ከፍ ያለ የስኳር መጠን ኩላሊትን ብዙ ደም እንዲያነጥር የሥራ ጫና ይሰጥዋል። በ ዚህ የተነሣ ፕሮቲንና አንዳንድ ቆሻሻዎች ወደ ሽ ንት ሠርገው መግባት ይጀምራሉ። በሽንት ውስ ጥ የሚከሠት ጥቂት ፕሮቲን (ማይክሮአልቡሚኔ ርያ) የመጀመሪያው በኩላሊት የመያዝ ምልክት ነ ው። በሽታው በዚህ ጊዜ ከተደረሰበት ጥሩ አጋጣ ሚ ነው። ምክንያቱም ወደ አስከፊ ደረጃ ከመድረ ሱ በፊት በቶሎ ማከም ስለሚቻል። ይህ በጊዜ ሊ ታወቅ ካልቻለ ወደ ሽንት የሚቀላቀለው የፕሮቲ ን መጠን በየጊዜው እየጨመረ በመሄድ ወደ ማ ክሮ አልቡሚኔርያ (ብዙ አልቡሚን ማለት ነው) ይደርሳል። በዚህ ዓይነት እስከ ዳያሊዚስና አልፎ ም ሌላ ኩላሊት እስከማስቀየር ድረስ ሊያደርስ ይ ችላል። ስለዚህ የስኳርንና የደም ግፊትን ልክ በጥ

ንቃቄ በመቆጣጠር በዚያ ሳቢያ ሊመጡ የሚችሉ ትን አሠቃቂ ተከታይ ጉዳቶች መከላከል እጅግ በ ጣም ጠቃሚ ነው፡፡

የማስታወስ ኃይል መዳከም

ከቁጥጥር ውጭ የሆነ የስኳር በሽታ የ ማስታወስ ችሎታንም ሊቀንስ ይችላል፡፡ ይህም የ ሚሆነው ዋናው የአንጎል አንቀሳቃሽ ነዳጅ ግሉኮ ዝ እንደመሆኑ መጠን፤ የግሉኮዝ ወደ አንጎል የ መግቢያው በር የሚቀናጀው በአንጎል ደም ማንጠ ሪያ አማካይነት ነው፡፡ በአንጎል ውስጥ የስኳር ክ ምችት የተወሰነ ስለሆነ ወደ አንጎል የሚተላለፈ ው የስኳር አቅርቦት የተስተካከለ መሆን አለበት፡ ፡ በአንጎል ውስጥ የስኳር ክምችት መብዛት አንጎ ልን የበለጠ ያሠራዋል ማለት አይደለም፡፡ በተቃራ ኒው በደማችን ውስጥ ያለው የስኳር መጠን መቀ ነስም ሆነ ከልክ በላይ መጨመር የአንጎልን የማስ ታወስ ኃይል እንዲዳከም ያደርገዋል፡፡ ከፍተኛ የ አንጎል የመፍረስረስ መጠን (metabolism) ተ ፈላጊውን ነዳጅ በደም መሥመር አማካይነት ወደ አስተላላፊ ነርቮች በማጓጓዝ ያጠናክራቸዋል፡፡ ለ ዚህ ነው መማርና ማስታወስ ያለ አስተላላፊ ነርቮ ች እርዳታ ሥራቸውን በትክክል መሥራት የማይ ችሉት፡፡ የደም ስኳር መጠን በደም ቧንቧዎች ው ስጥ ለረዝም ጊዜ መቀነስ ወይም መጨመር ሂፖካ ምፐስ የተባለውን የአንጎል አካል በስነ -ሠርዓት እ ንዳይሠራ ያደርገዋል፡፡ ውጤቱም የማስታወስ ኃ ይልን፣ የትኩረትን መቀነስንና ዘገምተኛነትን ሊያ ስከትል ይችላል፡፡

ቆዳን ስለመንከባከብ፣

የስኳር በሽተኞች ለቆዳቸው የተለየ ጥ ንቃቄ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ከፍ ያለ የደም ስ ኳር በሰውነታችን ውስጥ የሚዘዋወረውን የፈሣሽ ልክ ይቀንሠዋል፡፡ በዚህ የተነሣ ቆዳ ይደርቃል፡፡ እስከ መሠንጠቅም ሊደርስ ይችላል፡፡ ቀጥሎም ያ ሣክካል:: በዚህም የተነሣ ጥቃቅን ቁስለቶች ሊፈ

ጠሩ ይችላሉ፡፡ ከሰውነታችን የሚወገደውም ላብ መጠን ይቀንሣል፡፡ በተፈጥሮ ላብ ሰውነታችንን በሙቀት ጊዜ ሰውነታችንን ከማቀዝቀዝና በሰውነ ታችን ውስጥ የሚፈጠሩትንም አንዳንድ ቆሻሻ ነገ ሮች ከማስወገድ አልፎ ቆዳችን እንዲረጥብና እን ዲለሰልስም የማድረግ የሥራ ድርሻ ነው ያለው፡፡

የእግርን ንጽሕናና ጤንነት ስለመንከባከብ

ከፍ ያለ የደም ስኳር በተጨማሪ ለባክ


ቴርያዎች መፈልፈያ ወይም መራቢያ ይመቻል፡፡ የእግር ጣቶች ለማጽዳት አስቸጋሪ በቀላሉ ለመጎ ዳት ምቹዎች ናቸው፡፡ ብዙውን ጊዜ የእግር ላይ ቁስል የሚጀምረው ጥፍር በመቁረጥ ወቅት ወይ ም የመጫሚያ መጥበብ በሚፈጥረው ትንሽ አል ባሌ ቁስል ነው፡፡ ይህችን ትንሽ ቁስል ችላ በማለ ት እያደገችና ሥር እየሰደደች በመሄድ በስዕሉ ላ ይ እንደሚታየው ሁኔታ ላይ ሊያደርስ ይችላል፡፡ ይህ ነው በኋላ ወደ እግር መቆረጥ ደረጃ የሚያደ ርሰው፡፡ እስቲ አንድ ጊዜ የሆነውን ላጫውታችሁ አቶ ጎበ ና የተባሉ የ60 ዓመት አዛውንት የሁለተኛው ዓይ

ነት ዲያቤቲስ ሰለባ የሆኑ ታካሚ ነበሩ። የአመጋ ገብ ስርዓት እንዲለውጡ የተነገራቸውን የሃኪም መመሪያ አልተቀበሉትም፣ ፈጽሞም አልተዋጠላ ቸውም። በስኳር በሽታቸው የተነሳ ብዙ ጊዜ ሆስ ፒታል ገብተዋል። አሁንም የደም ስርጭት ችግር ስላለባቸው እንደገና ሆስፒታል መግባት ግድ ሆ ኖባቸው ሆስፒታል ይገባሉ። ከእኩለ ሌሊት በኋ ላ በጣም እየራባቸው ነርሷን ምግብ እንድትሰጣ ቸው ይጠይቃሉ ፤ የሚጠይቁትም ምግብ ለጤና ቸው የማይስማማ እና ሰዓቱም ሰውነታችን ለመ ፍጨት ዝግ የሚልበት በመሆኑ እንዳይመገቡ ት መክራቸዋለች። አዛውንቱም ምክሯን አሻፈረኝ በ ማለት ሚስታቸውን እያስመጡ ደብቀው ይመገባ ሉ። የሚመገቡበት ምግብና ሰዓት ልክ ባለመሆኑ ና አሻፈረኝ በማለት በመመገባቸው፤ ይህ እምቢ ተኛ ጸባያቸው ከስድስት ወራት በኋላ እግራችው ን ለመቆረጥ ይዳረጋቸዋል። በዚህ ብቻም አላበቃ ም በከፍተኛ የደም ግፊታቸው ምክንያት ከጥቂ ት ወራት በኋላ ኩላሊታቸውም ተጠቃ። በስነ-ስ ርዓት መስራትን አቆመ። ባለመጠንቀቅ በሚፈጠ ር ችግር አቶ ጎበና ዛሬ የዲያሊስስ ጥገኛ ናቸው። ሆኖም ግትርነታቸው፣ እምቢተኝነታቸውና የሃኪ

ምን ምክርና መመሪያ አለመቀበላቸውን ዛሬም እ ንደቀጠሉ ነው። አቶ ጎበና የመጀመሪያው የዲያሊ ስስ ቀን እለት “ዲያሊስስ ሶስት ሰዓት ይፈጃል ሲ ሉ ሰምቻለሁ! የእኔ እህት እውነት ነው?” ብለው ነርሷን ይጠይቃሉ። እርሷም እውነት መሆኑን አ ረጋግጣላቸው ከዚያም ለምን እንደጠየቋት ለማ ጣራት ብትሞክር “ሶስት ሰዓት ሙሉ እዚህ የም ጋደምልሽ ይመስልሻል? አይምሰልሽ” ይሏታል “ለ ኔ ብለው እኮ አይደለም የሚጋድሙት ለራስዎ ጤ ንነት መሆኑን አይዘንጉ!” በማለት ለማስረዳት ት ሞክራለች። እንግዲህ አስታውሱ ጤነኛ ህይወትን ለመምራት የአኗኗር ዘይቤን ማስተካከልና መጠን ቀቅ ይፈልጋል። ዘወትር በስሜትም ሆነ በጉልበት ላለመድከም መሞከር ፣ ነገሮችን በቀላል መውሰ ድ መልመድ ወይም ባህሪ ማድረግ ይጠይቃል። በቂ እረፍት ማድረግ፣ ከስርዓት ውጭ የሆነ አመ ጋገብን ማስወገድና ጤናማ የሆነውን መመገብን ልምድ ማድረግ፣ ሌሊት የምግብ መፍጨት ሂደት ዝግ ያለ ስለሆነና ውፍረትን ስለሚያስከትል ሌሊ ት መመገብን ማቆም። ስኳር በሽታ ያለባቸው ሰ ዎች ማወቅ ያለባቸው ምን እንደሚመገቡ ብቻ ሳ ይሆን መቼ እንደሚመገቡም ጭምር ነው። የስኳ ር በሽታ ሰለባ ለሆኑ ሰዎች ስለአመጋገብ የሚያስ ተምሩ የአመጋገብ ባለሞያዎች ስላሉ ማማከሩ ጠ ቃሚ ነው። ዛሬ ተጨማሪ መረጃዎችን በቀላሉ ከ ተለያዩ ድህረ ገጾች ማግኘትም ይቻላል። አካላዊ እንቅስቃሴን ማዘውተር፣ ጭንቀትንና ድብርትን መቆጣጠር ግዴታ ነው። ዲያቤቲስ እራሱ ድብር ትና ጭንቀት ነው። በዚህ ላይ ከቁጥጥር ውጭ የ ሆነ ከፍተኛ የስኳር በሽታ ለበለጠ ጉዳት ይዳርጋ ል። የደም ስኳር ብዛትን በጭንቀትና ባስቸጋሪ ሁ ኔታ ላይ ስትሆኑ መለካት ያስፈልጋል (ለምሳሌ በ መኪና አደጋ ጊዜ፣ በጭቅጭቅ ጊዜ፣ ከስራ በመባ ረር ጊዜ፣ ከመወዳደር በፊት፣ ለአዲስ ስራ ቃለም ልልስ በምታደርጉበት ጊዜ . . . በጠቃላይ በንዴ ትና በአንዳንድ ምክንያቶች ልብ በሚሰቀልበት ወ ቅት የደም ስኳር ሊንር ይችላል። ከሚግቧቧቸው ሰዎች ጋር መዝናናት፣ በጥልቅ መተንፈስ፣ ፊልም ማየት፣ በጭንቀት ጊዜ የሚፈጠረውን ንጥረ-ነገር (ኮርቲሶል) ከመስተካከሉ በፊት ሰውነታችን ውስ ጥ ወደ 4 ሰዓታት ያህል ስለሚቆይ ያንን ባስቸኳ ይ እንዲያዘቀዝቅና ወደ መደበኛ ቦታው እንዲመ ለስ አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ፤ መጥፎ ንጥረ-ነ ገሩ ቀንሶ ወደ ጥሩው ንጥረ-ነገር እንዲዛወር ሰው ነትም ሆነ አንጎል እንዲዝናና ያደርጋል። በመጨረ ሻም ለማንኛውም መጠንቀቅ ያስፈልጋልና ችግር ሲገጥማችሁ ወደ ሃኪማችሁ ዘንድ በመሄድ ማማ ከርና የሀኪምን ምክር ተግባራዊ ማድረጋ አዋቂነ ት መሆኑን አይዘንጉ።

ሰውነታችን እንዴት እንደሚሳራ ያውቃሉ? ሰዎች በአስተሳሰብ፣ በስልጣኔ፣ በጠ ባይ፣ በቆዳ ቀለም ብንለያይም ውስጣዊና ው ጫዊ መሰረታዊ የአካል አፈጣጠራችን፣ የሰ ውነት ክፍሎቻችን ግንባታና ስራቸው አንድ ነ ው። አንድ ሕጻን ሲወለድ 350 አጥንቶ ች ሲኖሩት፤ ካደገ በኋላ ግን ቁጥራቸው በግም ት ወደ 200 ይደርሳል ታድያ የሚቀንሰው ጠ ፍተው ፤ ሳይሆን በእድገት ጊዜ አንዱ ከሌላው ጋር ስለሚዋሀዱ ነው። የሚገርመው አጥንቶች ለሰውነታችን ቅርጽ ባይሰጡት ኖሮ የተጨማ ደደ ጆንያ እንመስል ነበር። የአጥንቶቻችን ጥንካሬ እንደ ድንጋ ይ ሲሆን። ታድያ ይህንን ጥንካሬአቸውን የሚ ያገኙት ካልሲየም ከተባለው ንጥረ-ነገር ነው። ነገር ግን ከድንጋይ የሚለዩት ህይወት ስላላቸ ውና ስለሚያድጉ ነው። አጥንቶቻችን ጠንካራ ና ለሰውነታችን ግድግዳ በመሆን እንደመከላከ ያ ይጠቅሙናል። ከውስጣዊ የሰውነት ክፍሎ ቻችን ለምሳሌ አንጎል በጣም አስፈላጊ አካል በ መሆኑ በአጥንት አጥርንርት ተከቦ ይጠበቃል። ሰዎች 12 ወይም 13 ጥንድ የጎድን አጥንቶች አሉን። እነዚህም አጥንቶች ለህይወ ታችን ዋነኛ ደጋፊ የሆኑትን ልብና ሳንባን እን ደግንብ ግድግዳ ሆነው ይከላከላሉ። ምንም እ ንኳ የራስ ቅል አጥንቶቻችን ብዙዎች ቢሆኑም እርስ በእርሳቸው የተቀጣጠሉና የተጣበቁ ናቸ ው። የአገጫችን አጥንቶች ብቻ ናቸው በ ምናኝክበትና በምንነጋገርበት ጊዜ የሚነቃነቁ ት። በሰውነታችን ውስጥ የሙዚቀኞች አጥንት የሚባል እንዳለ ያውቃሉ?

ጠናይስጥልኝ! ወንድማችሁ ዶ/ር ሰለሞን ማሞ ውቤ Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

59


ኦሎምፒክ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ኦሎምፒክ ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ከክር ስቶስ ልደት በፊት በ776 ዓ/ዓለም ኦሎምፒያ በምትባል የግሪክ ከ ትማ ሲሆን ፤ ግሪኮች ከሚያመልኳቸው አማልክቶች ዋና የሆነው ን “ዙስ” የተባለውን አምላክ ለማክበር የሚደረግ የስፓርት ውድድ ር ስራዓት ነበር። ነገር ግን በ1894ዓ/ም ዓለም አቀፋዊ የሆነ የኦሎ ምፒክ ኮሚቴ ተቋቁሞ የዛሬው ዓለም አቀፋዊ መንገዱን ጀመረ። ሀ ገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1948ዓ/ም የኦሎምፒ ክ ኮሚቴን በማቋቋም ከስምንት ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በ1956ዓ/ም ፤ በአውስትራሊያ አህጉር ሜል ቦርን በተባለ ከተማ ላ ይ በተደረገው የኦሎምፒክ ውድድር ፤ ስምንት የሩጫ አራቱ የብስክ ሌት ውድድር ተሳታፊ አትሌቶችንና አሰልጣኞችና ባጠቃላይ 18 ሉ ካንን በመላክ ተሳታፊ ለመሆን በቅታለች። በዚህም ውድድር ሩጫን ወክለው ንጉሴ ሮባ ፣ ባሻዬ ፈለቀ ፣ ገብሬ ብርቃይ ፣ ማሞ ወልዴ ፣ ሀይሉ አበበ ፣ በቀለ ሀይሌ ፣ ለገሰ በየነና ፣ በየነ አየነው ሲካፈሉ ። በ ብስክሌት ውድድድር ደግሞ ገረመው ደንቦባ ፣ መስፍን ፀሀይ ፣ ጸሀ ይ ባህታ እንዲሁም ንጉሴ መንግስቱ ተሳትፈው ነበር። ከሩጫው ቡ ድን መካከል የማይረሳ ትዝታ የነበረው ባሻዬ ፈለቀ ፤ ከሯጭነቱ በፊ ት በውትድርና ሞያው በጣሊያን ወራራ ላይ የተሳተፈ ሲሆን ፤ ወደ ሩጫው ውድድር ተሳታፊነት ወስኖ ከገባ በኋላ በድንገት በሰማው አ ንድ የግሪክ ጀግና አፈ ታሪክ ፍራቻ ራሱን ከተወዳዳሪነት አግሎል ነ በር። ይሀውም ግሪኮች ፔርዥያኖችን ድል እንደመቱ የሚያበስረውን ዜና ለመንገር ከ41 ኪሎ ሜትር በላይ ፣ ሁለት ቀን ሙሉ በመሮጥ አ ቴንስ ከደረሰ በኋላ “አሸንፍን” ብሎ እንደተናገረ ስለሞተው ሰው ታ ሪክ በመስማቱ ነበር ። ባሻዬ በኦሎምፒክ የሩጫ ውድድር ለመሳተፍ የወሰነውን ሀሳብ መሰረዙን ባሳወቀ ጊዜ ፤ ከዝግጅት ኮሚቴው ምን ም እንደማይሆን በማባበል ይነገረዋል። በኋላም ባሻዬ ቀዳማዊ ኃይ ለ ሥላሴ ሲመለስ በክብር ተጋባዥነት ከተገኙና ቢሞት እንኳን ለዚህ መሰዋዕትነት ምስክር ይሆናሉ በማለት ለመወዳደር ወስኖ ተጓዘ። ከ ውድድሩ በኋላ በህይወት እና በድል ወደ ሀገሩ በመመለሱ ከንጉሱም ስለ አሸናፊነቱ ሽልማት አግኝቷል። በ1960ዓ/ም በሮም የተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድር የ ህዝብን ትኩረት የሳቡና ብዙሃኑን ያነጋግሩ ብዙ የማይረሱ ትውስታ ዎች የታዩበት ወቅት ነበር። ከነዚህም መካከል ለእኛ ለኢትዮጵያውያ ን ፤ የአበበ ቢቂላ በባዶ እግሩ በመሮጥ የአንደኝነትን ደረጃ በመያዝ ያ ሸነፈበትና ዓለምን ድንቅ ያስባለበት ትዕይንት ነበር። በ1964ዓ/ም አበበ ቢቂላ በአራተኛው ዓመት በድጋሚ በ ጃፓን ከተማ ቶኪዮ ላይ በተደረገው የኦሎምፒክ ውድድር አንደኝነት ን በመቀዳጀት የወርቅ ሜዳሊያውን በማሸነፍ ሀገሩን በዓለም ላይ በ ድጋሚ ማስጠራቱን ቀጠለ። ከዚያ በኋላማ ሀገራችን የዓለም ሩጫ ተ ወዳዳሪዎች እናት ሆነች። በዚህ የ1964ዓ/ምህረቱ የኦሎምፒክ ውድ ድር ላይ ውሂብ ማስረሻ ከአበበ ቢቂላና ማሞ ወልዴ ጋር አብሮ በመ ወዳደር የውድድሩን ፍጥነት ተቆጣጥሮት ነበር። 1968ዓ/ም በሜክሲኮው ኦሎምፒክ ማሞ ወልዴ ወርቅና ነሀስ ያሸነፈበት ድንቅ ውድድር ሲሆን ፤ በዚህ የኦሎምፒክ ውድድር አበበ ቢቂላ በጤና መታወክ ምክንያት ደክሞ ውድድሩን አቋርጦ በወ ጣበት ወቅት ፤ ታዋቂው ጋዜጠኛ ሰለሞን ተሰማ የኢትዮጵያን ባንዲ ራ በማውለብለብ ይህን ውድድር ለማሸነፍ ብቸኛው ተስፋ ሞሞ ወል

62

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ዴ በመሆኑ ጮሆ በማበረታታ ፤ ማሞ ወልዴ ም ጠንክሮ በመሮጥ የአንደኛነት ድል የተቀዳጀ በት ታሪካዊ ትይንት ነበር። “ይፍጠር ዘ ሽፍተር” ይፍጠር ማር ሽ ቀያሪው? በ1980ዓ/ም ሞስኮ ላይ በ5ሺ እ ና በ10ሺ ሜትር ርቀት የወርቅ ተሸላሚው ም ሩጽ ለ13 ደቂቃ ያህል ከተወዳዳሪዎች ጋር አ ብሮ በመሮጥ የ5ሺውን እንዲሁም የ10ሺ ሜ ትር እርቀቱን ደግሞ በ27 ደቂቃ በመሮጥ ለመ ጨረስ 300 ሜትር ሲቀረው በቅጽበት ተወዳ ዳሪዎችን ጥሎ በማፈትለክ “ይፍጠር ዘ ሽፍተ ር” የሚለውን ስያሜ አግኝቷል። ተፎካካሪዎቹ ን በአስር ሜትር ርቀት ብልጫ ቀድሟቸው ሲ ያሸንፍ በጊዜው የነበረውንም ክብረ-ወሰን አ ሻሽሏል። ምሩጽ በ1972ዓ/ም በሙኒክ የኦሎ ምፒክ የ10ሺህ ሜትር ውድድር የነሀስ ፣ ማ ሞ ወልዴ ደግሞ በወንዶች ማራቶን ነሀስ ሲ ያገኙ ፤ ምሩጽ ይፍጠር የ10ሺሜትር ርቀት ላ ይ ተወዳድሮ የነሀስ ሽልማት በማግኘቱና በመ ክፈቻው የ5ሺ ውድድር ላይ ሳይሳተፍ በመቅ ረቱ አሳዝኝና ወደ ሀገሩ ሲመለስ እስር ቤትም ያስገባው ነበር። በወቅቱ ወደ ስታዲየሙ የሚ ያስገባው መንገድ ጠፍቶት ይሆናል በሚል ግ ምት ተነግሮ የነበረው ታሪክ ሚስጢር ፤ ምሩ ጽ ሀገሩን ከድቶ ለመጥፋት ፈልጎ ሀሳቡን እን ደቀየረ ተደርጎ ወደሀገሩ እንደተመለሰም እስር ቤት አስገብቶት ነበር። ሌላው የሚገርመው የ ምሩጽ እድሜ ለብዙ ዘጋቢዎች ምስጢር መ ሆኑ ነበረ። እኒህ ዘጋቢዎች የምሩጽን እድሜ ከ33 እስከ 42 ዓመት በማለት ነበር የሚያሰፍ ሩት። ይህም የሆነበት ምክንያት ፤ ምሩጽ እድ ሜውን ሲጠየቅ “ሰዎች ዶሮዎቼን ሊሰሩቁ ይ ችላሉ፣ በጎቼን ሊሰርቁ ይችላሉ ፤ ነገር ግን እ ድሜዬን ሊሰርቁ አይችሉም።” ብሎ በመመለ ስ እድሜውን ለመንገር ፍቃደኛ ስላልነበር ነ ው። በ1972ዓ/ም ቶሎሳ ቆቱ በሞስኮው የኦ ሎምፒክ ውድድር ተወዳድሯል። በ1980ዓ/ም በሞስኮ ኦሎምፒክ ምሩጽ በ10ሺህና በ5ሺህ ውድድር ሁለት የ ወርቅ አሸናፊ በመሆን ታላቅ አትሌት መሆኑን አሳይቷል። በዚህ የ10ሺ ሜትር ውድድር ዮ ሃንስ መሀመድ የውድድሩን ፍጥነት በመቆጣ ጠር ለምሩጽ ይፍጠር ድል ትልቅ አስተዋጾ አ ድርጓል። በዚሁ የሞስኮ ኦሎምፒክ ውድድር ም እሸቱ ቱራ በ3ሺህ ሜትር የነሀስ ሜዳሊያ አሸናፊ ሲሆን፡ መሀመድ ከድር ደግሞ በ10ሺ ህ ሜትር የነሀስ ሜዳሊያ አግኝቷል። በ1992ዓ/ም ስፔን ባርሴሎና በተ ደረገው የኦሎምፒክ ውድድር ደራርቱ ቱሉ የ10ሺ ሜትር ርቀት በመወዳደር የወርቅ ሜ ዳሊያ ተሸላሚ ስትሆን ገና የ20ዓመት ወጣ ት ነበረች። በሩጫ ውድድር ታሪክም በ10ሺ


ህ ሜትር ርቀት አሸናፊ የ መጀመሪያዋ ብቸኛ ጥቁር ሴት በመሆኗ ከብርቅዬ አ ትሌቶቻችን ከነአበበ ቢቂላ ፣ ማሞ ወልዴና ምሩጽ ይ ፍጠር ጋር በታሪክ ሰሪነቷ በ ክብር እንድትሰለፍ አድርጓ ታል። ደራርቱ ከርሷ በኋላ ለ ተፈጥሩት እንደነ ፋጡማ ሮባ ላሉ ጠንካራ ሯጮች የመሮጥ ምሳሌ የሆነች ታላቅ አትሌት ና ት። በባርሴሎናው ኦሎምፒክ አ ዲስ አበበና ፊጣ ባይሳም በ10 እ ና 5ሺህ ውድድሮች በመሳተፍ የነ ሀስ መዳሊያ አሸናፊ ሆነዋል። በኦሎምፒክ ታሪክ ኢ ትዮጵያ በ1976ዓ/ም አፓርትይድ ን በመቃውም በ1984 ደግሞ ከሞ ስኮ ጎን በመቆም በሎስ አንጀለስ የተ ካሄደውን ኦሎምፒክ በመቃወም እና በ1988ዓ/ም በኮርያ ሶል ከተደረጉት ወድድሮች እራሷን ካገለሉት ሀገሮች መ ካከል አንዷ በመሆን ሶስት ጊዜ ሳትሳተ ፍ ቀርታለች። እነዚህ አትሌቶቻችን ከኦሎም ፒክ ውጪ በሀገር አቀፍና ዓለማቀፍ ውድ ድሮች በተመሳሳይ ሁነታዎች በማሸነፍ ሌ ሎች ሜዳሊያዎችና ክብረወሰኖችን አስገኝ ተዋል። ኃይሌ ገብረስላሴ በአትላንታ በተ ኪያሄደው የ1996ዓ/ምቱ የኦሎምፒክ ውድድ ርም የ10ሺህ ሜትር ርቀቱን በማሸነፍ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ፤ በዓለም የአንደኝነት ሯጭ ማ ዕረጉን አስጠብቋል። በዚህ ውድድር ላይ የኬን ያው ፖል ተርጋት የተባለው አትሌት እስከ መጨ ረሻዋ ደቂቃ ድረስ ዋናው ተፎካካሪው ሆኖ በመ ቆየት ኃይሌ ገብረ ስላሴን በመጨረሻዋ ደቂቃ ቀድ ሞት ሲያፈተልክ በንዴት የኃይሌን ጀርባ በጡጫ በ መዶቆስ ኃይሌ ተሽቀንጥሮ በ6ሜትር ርቀት ልዩነት እንዲያሸንፍ ማድረጉ ይታወሳል። ኃይሌ የ5ሺ እና የ10ሺ ሜትር ርቀት ውድድሮችን በተከታታይና በተ ደጋጋሚ በማሸነፍ በኦሎምፒክ ታሪክ መዝገብ ከያዙ ት ኤምል ዛቶፕከ እና ለሲ ቨረን ጋር ሶስተኛው ሰው ሆ ኗል። ኃይሌ ገ/ሥላሴ ገና ተማሪ ሳለ ከቤቱ ወደ ትምህ ርት ቤት ለመሄድ የ10 ኪሎ ሜትር ርቀት በየቀኑ በመሮ ጥ ያካበተው ልምድ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅናን እንዲ ያገኝ እረድቶታል። በዚሁ 1996ዓ/ም ኦሎምፒክ ፋጡማ ሮባ በሴቶች ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ነበረች። አበ በ ቢቂላ ኢትዮጵያን ወክሎ የኦሎምፒክ ወርቅ በማምጣት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ አትሌት እንደሆነ ሁሉ ፤ ፋጡማ ሮባም የመጀመሪያውን የኦሎምፒክ የሴቶች ማራቶን ውድድ

ር አሸናፊ በመሆን ለሀገሯ የመጀመሪያውን ወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘች ኢትዮጵያዊት ና ት። ጌጤ ዋሚም በሴቶች 10ሺህ የነሀሱን አላጥችም። ሀገራችን ኢትዮጵያ በሩጫው ስፖርት ከማንኛው ሀገር ይልቅ ብዙ ምርጥና ተደናቂ ተወዳዳሪዎች ያሏት ሀገር ናት። እነዚህ አትሌቶች የዓለምን የሩጫ ክብረ ወሰ ን በማሻሻልም ሆነ አዲስ ክብረ ወሰንን በማስመዝገብና ለሩጫ ውድድር ልዩ ጣዕም የሚሰጡ ፣ ለሀገራችው ኢትዮጵያና ለህዝቧ ደግሞ ኩራት የሆኑ እጹብ ድንቅ አትሌ ቶች ናቸው። በ2000ዓ/ም ኦሎምፒክ ደግሞ ገዛኽኝ አበራ በወንዶች ማራቶን በብዙ የር ቀት ልዩነት የወርቅ ሜዳሊያ ለማሸነፍ ሲበቃ ፤ የዓለም የአሸንፊዎች አሸናፊ ው ድድር ላይም የወርቅ አሸናፊ በመሆን በዓለም ሁለቱን ውድድር በተመሳሳይ ጊዜ በተከታታይ በማሸነፍ የመጀመሪያው ሯጭ ሆኗል። በዚህ የ2000ዓ/ም ኦሎም ፒክ ሚልዮን ወልዴ በ5ሺህ፣ ኃይሌ ግ/ሥላሴ በ10ሺ፣ ደራርቱ ቱሉ በሴቶች 10ሺህ ሀገራችንን የወርቅ ሜዳሊያ ያንበሸበሹበት ነበር። ለሀገራችን አትሌቶች ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ክብረ ወሰን ማሻሻል ወይም አዲስ ውሰን መፍጠር የተለ መደ ክስተት ነው። በዚሁ የ2000ዓ/ም ኦሎምፒክ ውድድር ጌጤ ዋሚ የብ ርና የነሀስ፣ አሰፋ መዝገቡ በ10ሺ ሜትር የነሀስና ተስፋዬ ቶላ ደግሞ በማራ ቶን የነሀስ መዳሊያ አሸናፊ ለመሆን በቅተዋል። በ2000 የሲድኒ ኦሎምፒክ ጥሩነሽ በ5ሺህና በ10ሺህ ሜትር ወርቅ በማሸነፍ በኦሎምፒክ ታሪክ በአን ድ ጊዜ ሁለት ወርቅ ያስገኘች የመጀምሪያዋ ሴት በመሆን ታሪክ ሰርታለች። ቀነኒሳም ከምሩጽ ቀጥሎ በኦሎምፒክ ታሪክ በአንድ ጊዜ ሶስት የወርቅ በ ማሸነፍ ታሪካዊነቱን አስመዝግቧል። ቀነኒሳ በ2004 በኦሎምፒክ ውድድር ጀማሪዋ ግሪክ በተዘጋጀ ው የአቴንስ ኦሎምፒክ ውድድር የ10ሺህ ሜትር የወርቅና የ5ሺ ሜትር ርቀት የብር ሜዳሊየ ተሸላሚ ሆኗል። በዚሁ ኦሎምፒክ መሰረት ደፋር ገና በ23 ዓመቷ በ5ሺ ሜትር ርቀትና የ1500 ሜትር ርቀት ጥሎ ማለ ፍ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ስትሆን ስድስት የዓለም ክብረ ወሰን (ሪኮርድን) የያዘች አትሌት ናት። ከነዚህም መካከል በአሁን ጊ ዜ አራቱ ገና አልተደረሰባቸውም። በተጨማሪም ስለሺ ስህን የብር ፣ እጅጋየሁ ዲባባ በ10ሺህ ብር እና ጥሩነሽ ዲባባ በ5ሺህ ነሀስ ደራር ቱ ቱሉም በ10ሺሁ የነሀስ አግኝተዋል። እንዲሁም ሌሎች አትሌቶ ቻችን ቢሳተፉም በቤጂንጉ የ2008ዓ/ም ኦሎምፒክ ቀነኒሳ አዲስ የዓለም ክብረ ወ ሰን በማስመዝገብ በ10ሺህ ሜትር የወርቅ ፣ በ5ሺሁ እንደዚሁ የወርቅ ሲያገኝ ፤ ጥሩነሽ ዲባባም የ5ሺ እና የ10ሺ ሜትር ርቀት በማሸነፍ የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ሀገራቸውን አ ስጠርተዋል። በዚህ ውድድር ስለሺ ስህን የብር በ10ሺህ ፣ መ ሰረት ደፋር በ5ሺህ የነሀስ፣ ጸጋዬ ከበደም በማራቶን የነሀስ በ ማሸነፍ በሩጫው ያለንን ታሪክ ለማደስ በቅተውል። ይህንን የረዥም ዓመታት ጠንካራ የሩጫ ስፖርት ታ ሪክ ስናወሳ ፤ ከተወዳዳሪዎቹ ጀርባ በተለያዩ ጊዜያት ለእነ ዚህ አትሌቶች ውጤታማ መሆን አስተዋጾ ያደረጉትን እን ደ ንጉሴ ሮባ ፣ ዶ/ር ወልደመስቀል ኮስትሬ ፣ እሸቱ ቱራ ፣ ቶሎሳ ቆቱ. . . ያሉትን ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ሳናወድስ አናልፍም። በሩጫው ስፖርት ዛሬ አትሌቶቻችን ወደው ጪ ሀገር ተጉዘው በመወዳደር ከሚያገኙት ዝናና እውቅ ና በተጨማሪ በሚያገኙት ከፍተኛ ገንዘብ ኑሯቸው የተ ቀየረ ሲሆን ፤ በሚከፍቷቸው አዳዲስ የንግድ ተቋማት ና የእርዳታ ድርጅቶች ደግሞ ወገናቸውን በመጥቀም ላይ ይገኛሉ። በአሁኑ ጊዜም በመጪው የ2012ዓ/ም በለንደን በምካሄደው ኦሎምፒክ ላይ ታሪክ ለመስራ ት በዝግጅት ላይ ይገኛሉ።

Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

63


ባለፉት ወራት ከአረቡ ሀገር ከቱኒሲያ የተነሳው “የአረብ ስፕሪን ግ” በመባል የሚታወቀው ንቅናቄ በከፊል ያመጣውን ለውጥ እነሙባረክን ና ጋዳፊን በመጣል አሳይቷል። አምባ-ገነኖች የህዝብን ለውጥ ፍለጋ በማናና ቅ “በውጪ ሀይሎች በሚደረግ ጣልቃ ገብነት የሚደረግ ንቅናቄ ነው” በሚ ል ተንኮል በማፈን በህዝብ ላይ የሚወስዱት ጭፍጨፋ ፤ እያደረሰባቸው ያ ለውን ውድቀት እየተመለከትን ነው። ይህ በሰሜን አፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ በወጣቱ ህይወት መስዋዕትነት እየተከፈለ ያለው ንቅናቄ በሶርያ ፣ በየመን . . . እንደቀጠለ ነው። አሁንም አንዳንድ ስልጣንን መልቀቅ በማይፈ ልጉ ጥመኛ መሪዎች ፤ በተመሳሳይ መልኩ ለማፈን ከመሞከር አልተቆጠቡ ም ። አይማሩም እንጂ! ሳይዘገይ ቢማሩ ሀገራቸውን ከውድቀትና ትውልድ ን ከእልቂት ያድኑ ነበር። ታዲያ ይህ በአመጽ የተቀየረው ህዝብ የወደፊት ህ ይወት አቅጣጫውን መተንበይ ግን አስቸጋሪ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከተጀመረ ከሶስት ወራት በላይ ያስቆጠረው “ኦኩፓይ ዎልስትሪት” የተባለው የሰሜን አሜሪካን ንቅናቄ ፤ አሁንም በተለ ያዩ የአሜሪካን ግዛት መቀጣጠሉን አላቆመም። ሲጀመር በኒው ዩርክ ስቴት “ዎል ስትሪት” ተብሎ በሚጠራው በማንሃተን ጎዳና የተጀመረው የህዝብ አ መጽ ፤ አነሳስ 99% የሚሆነውን የአሜሪካን ህዝብ በመወከል ፤ 1% የሚ ሆኑት ባለሀብቶች በስግብግብነት በሚፈጽሙት ድርጊት በሀገሪቱ ላይ የደረ ሰውን የኢኮኖሚ ቀውስ በመቃወም እንደሆነ ይታወቃል። በሴምተበር 17, 2011 የተጀመረው ይህ የህዝብ ንቅናቄ የተለየ ዘር ፣ ቀለም ፣ ሀይማኖት እና የፖለቲካ አመለካከትን ባለመጠየቁ ቀስ በቀስ እያደገ መጣ። ዛሬ 99% የሚሆነው የአሜሪካ ህዝብ ፤ በቤንዚን ዋጋ መናር ፣ በቤት ዋጋ መውደቅና ፣ የስራ ምንጩ የነበሩት ትልልቅ ኢንደስትሪዎች ፤ በእነዚህ ባለሃብቶች የሀብት ማካበት ፍላጎት እንደቻይና ወዳሉ የርካሽ ጉል በት በርካሽ ክፍያ ወደሚገኝባቸው ሀገሮች በመውሰድ ፤ የሥራ አጡ ቁጥር እንዲጨምር በማድረጋቸው . . . ይህም የህዝቡን ኑሮ ወደ አልተጠበቀ አዘ ቅት በመጣሉ ፤ ህዝብ የተቃውሞ ጩሀቱን ማሰማት መርጦ በአንድነት ተሰ ባስቦ መትመም ቀጠለ። በዚህም እንቅስቅሴ ምክንያት ብዙ ሰልፎች በያሉበ ት ተደረጉ ፤ አልፎ ተርፎም በየአደባባዩ ተሰብስቦ በመቀመጥ ለቀናት በው ጪ ማደርንና የረሀብ አድማውን ተያያዘው ፣ በአንድነት ሊቆም እንደሚችል አሳየ፣ አቤቱታውንም ማሰማት ጀመረ። በስልጣን ላይ ያሉ የየከተማው አስ ተዳደሮች የተለያየ እርምጃ ለመውሰድ ሞከሩ ፤ አንዳንድ የባለሀብቱ አቀን ቃኞችና ሚዲያዎች ፤ በጥቂት ሶሻሊስታዊ አስተሳሰብ ባላቸው ሰዎች የሚካ ሄድ እንቅስቃሴ እንደሆነ አድርገው ለማቅረብ ሞከሩ። ነገር ግን በየስቴቱ የ ተነሳውን የህዝብ ጩኽት በቀላሉ በተለመደ የሚዲያ ፖለቲካቸው ሊያግዱ ት እንደማይችሉ አሳየ። ይህ በሰሜን አሜሪካ የኢኮኖሚ ቀውስ ምክንያት ከሺህ በማይበ ልጡ ሰዎች ተጀምሮ አሜሪካንን ያጥለቀለቀው የህዝብ ንቅናቄ ፤ “በግሎባላ ይዜሽን” የኢኮኖሚ ትስስር የተጣመረውን የዓለም ህዝብ በተመሳሳይ መንገ ድ ህይወቱን ያወከው በመሆኑ ፤ ከአሜሪካን አልፎ የሌሎች የአውሮፓ ህዝ ቦችንም አስነሳ ፣ ዓለማችንን ማመሱንም ቀጠለ። ታዲያ ዛሬ በፖለቲካውም ሆነ በኢኮኖሚው ዓለማችንን የሚያም ሳት ችግር ምንጭ ፤ እነዚህ ዓለም አቀፍዊ በሆኑ ጥቂት ባለሀብቶች ባለቤ ትነት እጅ የሚነቃነቁ ታላላቅ የኢንቨስትመንት ኩባንያዎች ፤ ባንኮች ፣ የቤ ት እና የህንጻ ግንባታ ድርጅቶችና የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች በሞኖፖል በመ ያዛቸው። የጦር መሳሪያዎቻቸውን ለመሸጥ ጦርነትን በገንዘባቸው በማስነሳ 64

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

ትም ሆነ በመደገፍ ፣ በጦርነቶች ለተጎዳው ህዝብ መድሃኒቶቻቸውን በመሸ ጥ ፣ በጦርነት የፈረሱትን ከተሞች ኮንትራት ወስዶ በመገንባት ፣ አልፎ ተር ፎም በአገዛዝ ስልጣን ላይ የተቀመጡትን መሪዎችና ህግ አርቃቂዎች ፣ በገን ዘብ በመግዛት የህብረተሰቡን የአኗኗር ዘይቤ ወደ ፈለጉት አቅጣጫ ለመቀየ ር እንዲያስችላቸው በማድረግ ፣ በተለያዩ የፋይናስ ተቋሞቻቸው የተጭበረ በረ አሰራር ፤ ተጠቃሚው ህዝብ ሊረዳው በማይችለውና አስቸጋሪ በሆኑ አ ባባሎች በረቀቁ ውሎቻቸው ህዝብን እዳ ውስጥ በመዝፈቅ ወደ ድህነት በ ረንዳ ሲወረውሩት ኖረዋል። የህዝብን ሰባዊነት በማሳነስ ፣ በኑሮው ላይ ጫ ናን በማሳደር ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ትርፋማ ለመሆንና የራሳ ቸውን ኪስ ለመሙላት ሲሉ የብዙሀኑን ህይወት አጥፍተዋል። ታዲያ ይህን ስር የሰደደ ችግር ለመንቀል የተለያዩ ሀገራት መሪዎች በመሰባብሰብ እቅዶ ችን ቢነድፉም ፤ ዓለማችንን ከዚህ ቀውስ በፊት ወደነበረችበት ሁኔታ ለመ መለስ አስቸጋሪና ዓመታት የሚፈጅ ጉዳይ መሆኑ እየታየ ነው። በርግጥ ይ ህ ጉዞ ወዴትና ምን ይሆን ይሆን የሚለውን ሁኔታዎች በሂደት የሚመለስ በመሆኑ ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለመድረስ በጉግት እንጠብቃለን። የኛና እኛን መሰል የአፍሪካ ሀገሮች መንግስታት አገዛዝና የህዝብ ኑሮና ንቅና ቄውስ ምን ይመስላል የወደፊት እጣውስ ምን ይሆን? በሚቀጥለው እትም።


የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ 28ኛው ዓመታዊ የስፖርት እና የባህል ዝግጅት ከሙሉ ዓመት ውዝግብ፣ የአዘጋጅ ኮሚቴ የውስጥ ሽኩቻና መከፋፈል በኋላ ፤ በዓሉ በአትላንታ ሲካሄድ በህዝብ በኩል የነበርው እይታ ይህንን ይመስል ነበር። መጽሄታችን በመሃል አንድ እትም በመዝለሉ በወቅቱ ለማቅረብ ባለመቻላችንና ፤ ቢዘገይም በየዓመቱ የሚካሄድ ዝግጅት በመሆኑና ነፃ የሆነውን የህዝብ አስተያየት ማስነበቡ ጠቀሜታ እንዳለው የዝግጅት ክፍላችን ስለ አመነበት አቅርበነዋል። መጽሄታችንን በማሳየት የኢትዮጵያ መጽሄት አዘጋጆች መሆናች ንን በመግለጽ ከየት እንደመጡና ስለዚህ ዝግጅቱ አጠቃላይ ሁኔታ የተሰ ማዎን ስሜት አጠር አድርገው ቢገልጹልን? በማለት ለብዙ ሰዎች ላቀረብነ ው ጥያቄ ከተሰጠን ምላሽ መካከል ጥቂቱ። D መላኩ እባላለሁ የመጣሁት ከቦስተን ነው። ይገርምሀል የሚ ያሳዝን ነው! በየዓመቱ የእድገት ለውጥ የሌለው፣ እየወደቀና እየጫጨ የ መጣ ዝግጅት ነው። የህዝቡን ፍላጎት አጥንተው የተሻለ ነገር መፍጠር ሲ ችሉ በህዝብ ይቀልዳሉ። ካልቻሉ ደግሞ መልቀቅ ነው። ምን ይደረግ መገነ ጣጠል ለመደብን። በሀገር ፣ በፖለቲካው ፣ በቤተክርስትያኑ . . . አሁን ደግ ሞ በኳሱ ምን ይቀጥል ይሆን? D ስሜ ቤቲ ነው እድሜዬ 21 ነው። ከኖርዝ ካሮላይና ነኝ የመ ጀመሪያዬ ነው። እኔ የነርሱን ኳስ ላይ እይደለም የመጣሁት። እንደኔ ያሉ ኢትዮጵያዊ ወጣቶች ከተለያዩ ከተሞችና ሀገሮች ስለሚመጡ ያው ከተለያ የ ሰው ትተዋወቃለህ እና ያው ኩል! ነው። በዓመት አንዴ ሶስት አራት ቀን ከከተማህ ወጥተህ የኢትዮጵያ የሆነ ነገር የምታገኘው ይህ ስለሆነ ነው። D የወንድወሰን ነኝ ከሚኒሶታ፦ ያው ድሮ የማውቃቸውን ሰዎ ች ባገኝ ብዬ ነበር የመጣሁት እስካሁን ያገኘሁት የለም። በየቀኑ እዚህ እየ ገባሁ እግሬን አደክማለሁ። በርግጥ ዛሬ የምትፈልገውን ሰው ፌስ ቡክ ላ ይ ታገኘዋለህ። የት/ቤት ወይም የጓደኛ . . . ማህበር አድርጎ መገናኘት ተጀ ምሯል . . . ስለዚህ ይሄ ነገር በኔ በኩል አይቀጥልም። ከምታጠፋው ጋር የ ምታገኘው ነገር አይመጣጠንም። ቀድመውህ ኤክሳይትድ ሊያደርግህ የሚ ችል ነገር ካልፈጠሩ እና ከትውልድ ጋር ካልሄዱ አንድ ቀን ይቆምላቸዋል። ይኸው እንደምታየው በየዓመቱ የሚመጣውን ስታወዳድረው ሰው የለም። D አጥናፉ እባላለሁ ባለቤቴና ሶስት ልጆቼ ናቸው። የመጣነው ከዳላስ እየነዳን ነው። ቀላል አይደለም ወደ 12ሰዓት ፈጅቶብናል። በዛሬ ው የኑሮ ውድነት ነዳጁ ፣ የሆቴሉ ፣ የምግቡ ፣ ከዚያ ደግሞ ሜዳ ስትመ ጣ በየቀኑ በሰው ከ$12 ብር በላይ ለእያንዳንዳችን መክፈሉ፣ በየምሽቱ ስ ትሄድም ለዝግጅቶች የሚወጥው፣ በየሀበሻ ቤቱ ለመመገብ የምትጠብቀው ሰዓት ፣ ወረፋና አጠቃላይ ሁኔታ ስታየው ለመምጣት የሚጋብዝ አይደለ ም። አምስት ሆኖ ወደ ሀገር ቤት ለመሄድ አቅሙ ከባድ ስለሆነ እንደው ል ጆቹ የሀገራቸውን ነገር እንዳይረሱ ፣ እንዲቀላቀሉ ብለን ነው እንጂ መጥተ ህ የምታየው ነገር ያንያህል የሚያጓጓ አይደለም። ዘፋኞቹ እንደሆነ በየከተ

ማህ ይመጣሉ፣ ቲሸርቱንም ሲዲውንም በየኪዎስኩ ታገኘዋለህ ፤ ኳሱን እ ንኳ ተወውና! ታዲያ ምን አለ ብለህ ነው የምትመጣው። ጊዜህን አልውሰ ድብህ ብዙ ማለት ይቻላል እንደው ልጆቼም ፊት ብዙ ጥሩ ያልሆነ ነገር ማለት አልፈልግም። D ቆንጂት፣ ቅድስትና ሀና እንባላለን ኦ ማይ ጋድ! መጽሄት ላይ ልታወጣን ነው? ፎቶአችንም ይወጣል? አይ አይወጣም። ከሲያትል ነን። ዊ አር ሂር ጀስት ፎር ፈን። ገባህ አይደል? ያው! አለ አይደ ል አንተ ደግሞ ስንት ነገር አለ። ቂቂቂቂቂ . . . ይገባሀል አይደል . . . ነገሩ ቢገባኝም ግልጽ እንዲያደርጉት በመፈለግ ያው ዳንሱ፣ መ ጠጡ፣ ሺሻው ፣ ጠበሳውንም ይጨምራል አይደል ብዬ ሳልጨርስ አሀሀሀ! ቂቂቂ . . . ኦ! ያ! ዩ ጋት ኢት! አሉኝ። D ሽመልስ እባላለሁ ከቬጋስ። ይገርምሃል ሼኩ ሊገዛው ነው የ ሚባለው እውነት መሰለኝ። ያረፍኩት አዘጋጅ ኮሚቴዎቹ ያረፉበት ሆቴል ነበር። የሼኩ ሰዎችና ኮሚቴው ብዙ ጊዜ ስብሰባ ያደርጉ እንደነበር አይቻለ ሁ። ሀገር ከተሸጠ ኳስማ ማንም ሊቸረችረው ዝግጁ ይመስለኛል። ምን ባ ክህ ይሉኝታችንን ገንዘብ ከገዛው ቆይተናል። ያሳዝናል! D ታዲዮስ ከአትላንታ ፦ የወ/ሮ ብርቱካን ጉዳይ የፖለቲካ ሰ ው በመሆኗ አለመጋበዟ የሚሻል ነበር። ያ ማለት ግን ያለው መንግስት ደጋ ፊ ነህ የሚያሰኝ አይደለም። የሚገርመው ግን ከዲሲዎቹ አዘጋጆች ጋር የተ ለያዩት ባለመጋበዟ ከነበር ለምን አሁን እንደገና መጋበዟና የክብር እንግዳ መሆኗ አስፈለገ? ሰዎቹ አቋም የላቸውም ማለት ነው። ሌላው የገረመኝ ሰ ዎቹ አሁንም ፕሮግራሙን መምራት አልቻሉም። የሚገርመው ግን ብዙ ነገ ር ሊሰራበትና ሊፈጠርበት የሚችል ዝግጅት ሆኖ ፤ የኮሚቴው አባላት አን ድ ቦታ የቆሙ ይመስላል። ስታዲዮም መከራየትና ገበያ ማዘጋጀት ብቻ ሆ ኗል! ምን ይደረግ ትላለህ የገንዘብ ነገር ልቀቅ አያሰኝም። የሚገርመው ይብ ሉ ግን ሰርተው የተሻለ አድርገውት ቢበሉ ምንም አልነበር። የተለያየ ስብሰ ባዎች፣ ድርጊቶችንና ህዝቡን ሊያስደስቱ የሚችሉ ነገሮችን . . . የሚፈጥሩ ሰዎችንም አያበረታቱም ቢሆን ቢበሉአይቆጭም። ግን ሁልጊዜም የኛ ችግ ር ይኼው ነው። ከዝግጅት ክፍላችን Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

65


The fi rst step is to seek professional tax, legal and business advice. The second is to have your business “registered” as the correct entity type within the state you are operating. This is absolutely necessary. The third step is to establish a record keeping system in place no matter how simple to keep track of business income, operating expenses, sales and possibly customers. Finally you must set up a business baking account to keep your business and personal fi nances separate. Missing any of these elements for a period of time can lead you down the road to business closure. Although you might want to take a do it yourself (D.I.Y.) approach to your business in order to save a dollar, it is often the worse thing you can do. It has been said that every dollar you save up front, not seeking professional advice, can cost you $10 to correct later because you were ill informed. Talking to a CPA or lawyer up front may be a very wise decision. Check out their references or get a recommended from a friend. Fortunately for you there are organizations set up to help out new businesses which cost no money. One of these organizations is S.C.O.R.E. (www.score.org) which often schedules workshops at local public libraries. They will give you information on business start up as well as 66

ኢትዮጵያ መጽሄት 3ኛ እትም | 2004 ዓ/ም

sources of funding. If you call them you can get free mentoring. Registering your business within your state is as simple as choosing a form, fi lling it out and paying any necessary fees. Easy, right? Filling out the form, yes. Choosing the right entity (business type), not so much. There are certain legal implications, benefi ts and disadvantages to each type of business and again it is best to talk to a CPA and/or attorney who can advise you as to the best choice. At minimum spend a few hours reading about it on your own so you can talk to them as an informed person. They will respect you more. Under certain situations you may not have to fi ll out more than an exemption form (state of Nevada). It all depends on your specifi c situation. If a friend runs a convenience store and chooses a “Sole Proprietorship” this may not be the best choose for you or even for them. Another form of business such as an LLC might be better but it all depends on your own personal situation. Record keeping is not an option when running a business. It is something you must do and there is one golden rule you must never forget. Never mix your personal fi nances and records with your business records. Get a separate business banking account. You must keep track of purchases no matter


how small. You must keep track of inventory, cash on hand and things such as the mileage driven on your car for your business. Why, do you ask? There are many reasons but most important are taxes. Why would you throw away money that is owed to you? Did I just mention taxes? You must also report your earnings to the Internal Revenue Service (I.R.S.) also known as “Uncle Sam”. This is required by federal law and failing to do so can result in fi nes and in extreme cases jail and confi scation of property. If you have a business and have never done so please contact the IRS and they will guide you for fi ling retroactively. It is advised that you to keep your tax related records for seven years. Your options for record keeping are almost limitless these days. Record the date and amount and fi le the original away safely. Outside of pen and paper the cheapest alternative is to use a spreadsheet. I would recommend Google Docs (docs.google.com) or Zoho Work Online(www.zoho.com) which have the benefi t of being free, accessible anywhere and protected from any physical damage. Accounting software is the ideal solution but you must back up your data frequently.

The downside is that it may take a week of your entire evening just to get the basics and set you back about $200. At the end of the fi scal year (a tax business year that does not match up to our calendar year) you can give this to your accountant and it will reduce their bill to you signifi cantly. Further information can be obtained from the Nevada state website (www.nvsos.gov) by looking under the Business Center menu. There you will see options such as: State Business License, Start a Business, Resources and others. Selecting Resources will lead you to “Frequently Asked Questions” also known as a FAQ. It is a necessary read. Forms can be printed or fi lled out online as well. Don’t forget to check out other online resources, the library and your local bookstore which will allow you to read books for free. The bookstore has the advantage of having many current books on popular business software. Trial versions of these applications are available for download, so bring your laptop and buy a very large cup of coffee to begin your journey to fi nancial independence. Good luck!

በከተማችን የቤት ግዥ ሲከናወን ወደ ፍጻሜ ከሚካሄዱት የመጀ መሪያ ዙር ድርጊቶች ውስጥ ቤቱን ማስመርመር ነው። ይህንንም ስንል በቤ ቱ ውስጥ ተገጥመው ስለሚገኙ በዓይን የሚታዬና የማይታዪ ቛሚ ንብረቶ ች፡ ለምሳሌ ያህል አየር ማቀዝቀዣዎች፤ማሞቅያዎች፤ቤት ውስጥ የተቀበሩ የውሃ ቱቦዎች፤የመብራት መስመሮችና ሶኬቶች፤የውስጥ በቤት ጣራዎች፤የ ጋዝ መስመሮች፤ዕቃና ልብስ ማጠብያዎችን ፤እንዲሁም ሌሎች ሌሎችን የ ሚያጠቃልል በቤቱ ዙሪያ ላይ ብቻ ያጠነጠነ፡ እየገዛን ያለው ቤት ሥራና ወ ጪ ይጠይቃል ወይንስ በመልካም ይዞታ የሚገኝ ቤት ነው ብለን ለመወሰን እንዲረዳን በግል ፍላጎት ተነሳሽነት የሚካሄዱ የማረጋገጫ ፍተሻ ነው። ይህንንም ለማድረግ ገዢ በራሱ ወጭ ከፍሎ የማስመርመር ምር ጫ ይጠበቅበታል። በዚህ አጋጣሚ የማስመርመር ምርጫ ይጠበቅበታል ያ ልኩት በውሉ ውስጥ ተፈፃሚነት እንዲኖረው ገዥን የሚያስገድድ አንቀፅ ባ ለመኖሩና በፍላጎት ላይ የተመሠረተ መሆኑን አጥብቆ ለማሳሰብ ያህል ነው። ይህንን ካልን ዘንዳ ገዢው የቤቱን ግዢ ከማጠናቀቁ በፊት ማስ መርመር እፈልጋለሁ በማለት በውል ሰነድ ውስጥ አስቀድሞ በማካተት ለሻ ጭ ካሳወቀ ፤ ቢያንስ በ10 ቀናት ወይም በተዋዋሉት የቀናት ገደቦች ውስጥ ቤቱን አስመርምሮ ግኝቱን ለሻጭ የማስወቅ ግዴታ ይጠበቅበታል። ከዚህ በማያያዝ ስለቤቱ ተጨባጭ ግንዛቤ ለማግኘት ገዢ ቤቱን በባለሙያዎች ማስመርመር ግዴታው ነው። እነዚህ ባለሙያዎች በሙያው

ትምህርት የወሰዱና ከመንግሥት ዕውቅናና ፈቃድ ያላቸው እንዲሆኑ ህግና ደንቡ ያዛል። በቤቱ ዙሪያ በምርመራው ላይ የተለያዩ ግድፈቶች ቢገኙ በባ ለሙያዎች ያልተመረመር ከሆነ ሻጭ ቤቱ ላይ የታዩትን ግድፈቶች የማረም ግዴታ የለበትም። በሌላ በኩል ቤቱን በባለሙያው ስናስገምት ፤ በዋነኛነት ደረጃ መረዳት ያለብን ጉዳይ ቢኖር እየተመረመረ ያለው የቤቱ ጠቅላይ ሁና ቴ ፤ ቤቱ በተመረመረበት ዕለት ያለውን የቤቱን አጠቃላይ ግኝት የሚያስረ ዳ እንጂ ለቀጣይ ቀናቶች ፣ ወራቶች ወይም ዓመታት የሚሆነውን ለመተንበ ይ ወይም የዋስትና ማረጋገጫ ለመስጠት የሚደረግ ምርመራ አለመሆኑን ነ ው። ይህንንም ለመጥቀስ ያስፈለገው አንዳንድ ገዢዎች ቤታቸውን በተረከ ቡ ማግሥት ወይም ጥቂት ወራት እንደኖሩበት ያልጠበቁት የቤት ውስጥ ብ ልሽቶች ሲያጋጥማቸው ፤ ሳስመረምረው ግን ይሠራ ነበር በማለት ቅሬታቸ ውን ሲገልጡ መታየቱ ነው። ይህም የዋህነትን የተከናነበና የማስመረመሩን ሂደትና ዓላማ ጠንቅቆ ያለመገንዘብን ያንፀባርቃል። ለመሆኑ ቤቱን ገዢ ካስመረመረና ቤቱ ላይ እንዳንድ ጉድለቶች ቢገኙበት አሁን ባለው ያልተረጋጋ የቤት ግዥ ትርምስ በምን መልክ ጉድለቶ ችን ዕልባት ሊያገኙ ይችላሉ? ይህንንና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በሚቀጥ ለው እትም የምናየው ይሆናል። በዚህ አጋጣሚ በዚህ ጽሑፍ ዙሪያ ወይም በማንኛውም የቤት ጉዳይ ላይ ጥያቄ ካልዎት አቶ ዮሐንስ በላይን በስልክ ቁ ጥር 702- 526-5487 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ። እስከዛው ቸር ያቆየን።

Brian Joseph

Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

67


As your teen matures, they are becoming adults, discovering themselves, and deciding who they want to be. They are struggling to move away from their parents, toward their own future, and they are trying to establish more mature relationships. This can be a very turbulent time for you and your teen. However, watching your teen blossom into a responsible adult can also be a source of great pride. You may find that you have to shift from treating your teen as a child to knowing him as a young adult. In order to make this adjustment, you need to be able to effectively and positively communicate with your teenager. If you can maintain a personal, positive, and loving relationship with your teen, then the two of you can address most of problems together without damaging consequences. To accomplish this, you have to change the way you interact with your teen. The key to a good relationship The key to having a good relationship with your teen is open and honest communication. Teenagers may give the impression that they do not need their parents help as they get older, but most really want it. A teenager who is trying establish his identity and autonomy will probably be offended by anything that seems like nagging or lecturing. So, how do you give your teen the guidance they need while letting them have their autonomy? Be flexible when guiding your child through this phase of his life. Let him know that you care about him, and develop a bond with your teenager so he knows you understand him. When your teen feels connected to you, he will be less likely to shut you out. You may have to be willing to give your teen some space, but ultimately communicate your expectations. Let him know that you are there to offer help anytime your child needs it. A parent as a confidant Your teen should be able to confide in you. He should feel comfortable sharing his dilemmas, fears, and apprehensions. Know who his friends are, what he is going through at school, what he is reading, watching on TV and which web sites he is visiting. Knowing these kinds of things can give you insight into his personality, and you may discover proactive ways to bring issues into the open. If your teen confides in you that she’s having trouble making friends or that she thinks she’s too heavy, try to offer solutions to her problems rather than dismissing them as something that happens to everybody. Try to make positive comments about your teen, and find constructive ways to offer help. Being someone your teen can relate to Your teen should be able to relate to you. Today’s, adolescents and their parents are very different from those of fifteen or twenty years ago, yet their primary needs to

be respected, accepted, understood and trusted are the same. Think about all the wonderful qualities your teenager possesses, and let them know how much you admire these qualities. Show them that you respect them and their opinions. Watch your teenager brighten up when you talk about what he loves doing. His interests essentially describe who he is, and when you take an active part in those interests you are becoming an active part in your teen’s life. The essence of all communication is the need to be understood. One of the best things that you can do as a parent, and a confidant, is be an active listener. • Listen carefully and try to understand their points of view. • Use your instinct to pick out their underlying fears and apprehensions. • Communicate openly to connect on a deeper level with them. Whether she is talking about a field trip to the museum or talking about a sports team, you can learn a great deal about your child by actively listening. When your child knows that you are listening and remembering what he says, he will want to talk to you even more. Encourage responsible behavior through trust not lectures Adolescents are eager to take on responsibilities, because they want to prove to their parents that they are trustworthy and mature. When you indicate to your teenager that you trust them, you can encourage responsibility in their actions. It can be very tempting to criticize your teen when you get home from work and their sports gear, books, CDs, and clothes are strewn all over the place or when they are devoting more time to sports than they should be, but avoid that temptation. Let your child know that you care about his interests and appreciate that he works hard at school and in other activities, but that you also work hard and would appreciate him doing his part to clean the house. Approach the subject with him as you would with another adult. Don’t get emotional or discipline him. Treating him like an adult will make him more receptive to helping. To maintain a positive relationship with your teen as they make the transition into young adulthood, it is important to reevaluate your thinking and perceptions. Your teen is searching for his individuality, and as a parent you can support that search by being his friend and confidant as well as parent. You will find that your relationship with your teen, even during difficult times, will be one of the most heartwarming and enriching times for you as a parent. Ethiopia Magazine Issue 3 | 2012

69


Mukera  

first try or test