Page 1

ዘኢትዮጵያ

Zethiopia, Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

2ኛውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ የመቅረጽ ሽኩቻ ገጽ 4 የኢንደስትሪው ፖሊሲ በትግራይ! ገጽ 3

ሌላኛው “ቁጥር መቀቀያ” ኤርምያስ ለገሠ ገጽ6 የዲሲ ታክሲ ባለቤት ማን ይሁን? ገጽስ 3

እነዚ ህወጣቶች እኔም አንዳርጋቸው ነኝ ቢሉ ያምርባቸዋል። ልክም ይሁን አይሁን ቢያንስ የትግል አቅጣጫን በተግባር ተጋርተዋል። ሰሞኑን የግንቦት ሰባትና የአርበኞች ግምባር ውህደት የመሰማቱ ዜና በሥፍራው የተገኙ የኢሳት ጋዜጠኞች ፋሲል የኔ አለምና ከሠራዊቱ

አባላት ጋር በፎቶ ግራፉ ላይ ከመሃል የሚታየው መሳይ መኮንን ከሚልኩት ዘገባ ጋር ስንከታተል ቆይተናል። በምድር ያለውን የትጥቅ ትግል ዝግጅት እንስቃሴ እንዲሁም የአካባቢውን ሁኔታና የወደፊቱን የኤርትራውያንና የኢትዮጵያውያንን የግንኙነ አቅጣጫ

የእነዚህ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ጭቅጭቅ ስናይ ምናልባትም “ቦንድና ሉአላዊነት በኢትዮጵያ” የሚል መጽሐፍ በክፍፍል አፈንግጦ በሚወጣ ሌላ ባለሥልጣን እናነብ ይሆናል። ገጽ2 የሚያሳስቡ ዘገባዎችን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በሚሰማው ነገር ብቻ ሳይሆን በሚታይ ነገርም ላይ መወያየት ለደጋፊዎች ተስፋን ለተቃዋሚዎች ስጋትን ጥርጣሬዎች ላሏቸው ደግሞ ወደፊት ከሚሆኑት ነገሮች ጋር መልስን እየሰጡና ሁኔታዎችን እየገለጡ እንደሚመጡ ተስፋ ይደረጋል። ባለው ጎሰኛ ስርዓት ቅጥ ያጣ ግፍ የተማረሩ ኢትዮጵያውያን ግን የት ድረስ ሊሄዱ እንደሚችሉ ያሳያል። ያን የሚፎከርበት ጠመንጃን ይኸው ልጆች ሳይቀሩ አንግተውታል። ሰላማዊው የትግልና የምርጫ መንገድም እንደሚታየው እየሆነ መሆኑ አማራጮችን እያጠበበ መጥቷል። የሚበጀውን መፍትሔ መንገድ ማመላከቱ ላይ አገር ፈጥኖ መምከር ካልያዘ ወይ ጉልበት ሁልጊዜ የገለልተኞች ሳትሆን የተሳታፊዎች ናት! ከኢሳት የተገኘውን የውህደት ዜና በገጽ 9 ይመልከቱ

የቀድሞ በሐንጋሪ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ጓደኞቻቸው

ከ200ሺ ዶላር በላይ የሚገመት መጽሐፍትና ኮምፒውተሮችን ገጽ 7

የቦብ ማርሌይ ሐውልት በአዲስ አበባ ሊቆም ነው 7

አቶ መለስ ዜናዊ ሞልተውን ለሄዱት የውድቀትም ሆነ የእድገት ሰሌዳ፣ እንደርስ ዘንድ ምን ያህል ጊዜ ይቀረናል? በራዕይ የተገለጠላቸውን የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ምልክቱን እናይ ዘንድ ምን ያህል መጓዝ ይኖርብናል? ወይስ ደርሰናል ? ወይስ አቅጣጫውን ስተን ሌላ መንገድ ይዘናል? ከእድገቱ ወይስ ከቁልቁልቱ አፋፍ ላይ ነን? በፈጣኑ እድገታችን ፋፍተን እንደ ጽጌረዳ ፈንድተን እንፈካለን ወይስ እንደ ፈንጂው እንጠፋለን? ወዴት እየሄድን ነው? ገጽ 2

ያቃጠለው የጣይቱ ሆቴል ቃጠሎ

ወደ ኢትዮጵያ ላኩ

አንድነት መግለጫ አውጥቷል ሰልፍ ጠርቷል “ታጋይና ምስማር ሲመቱት ይጠብቃል” የሰላማዊ ትግሉ በር ሙሉ ለሙሉ እየተዘጋ መጥቷል!

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ /አንድነት/ የ2007 አገር አቀፍ ምርጫን በአሸናፊነት ለመወጣት የተለየ ስትራቴጂ በመንደፍ በሙሉ ኃይሉ ወደ እንቅስቃሴ መግባቱን ገልጾ በድርጅቱ ላይ የተቀነባበረ ዘመቻ፣ አሉታዊ ቅስቀሳና ወከባ እየተደረገበት መሆኑን አስታውቋል። አንድነት በጥር 14 ቀን 2007 መግለጫው “ የምርጫ ውድድር የይስሙላ ሳይሆን የምር መሬት ላይ በሚታይ ደረጃ መሆን እንዳለበት ወስኖ፤ የተንቀሳቀሰበት ሁኔታ በገዥው ፓርቲ የተወደደ ባለመሆኑ፤ በምርጫ ቦርድ፣ በሬዲዮ ፋና፣

712-432-7777

በቀድሞ ኢቲቪ በአሁኑ በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፓሬሽን እና የአንድነት አባል ነን በሚሉ በተግባር ለአፍራሽ ተልዕኮ በተሰለፉ ወገኖች የተቀነባበረ ዘመቻ ከተጀመረ ወራት ተቆጥረዋል፡፡” ብሏል። ይህም ግልጽ ዓላማ ያለው መሆኑን ገልጾ “ ህዝቡ በተቃዋሚዎች በተለይም በአንድነት ላይ እምነት እንዳይኖረው እና ተስፋ እንዲቆርጥ በማድረግ አሉታዊ የምርጫ ቅስቀሳ በፓርቲያችን ላይ በማሳደር ለገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ መንገድ እየጠረጉ ...........ወደ ገጽ 15 ዞሯል

ላይ እስካሁን የሚያስተማምን ማብራሪያ አልተሰጠም። ይህም በመሆኑ የህዝብ አመኔታ በሌለው በዚያ ላይ ደግሞ የታሪክ ጠላት ተደርጎ በሚታየው መንግሥት ላይ የሚደረገው ነቀፋ የቃጠሎው ዜና በተነሳ ቁጥር አካራካሪ እየሆነ ይመጣል። ለምሳሌ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለጉዳቱ መባባስ የ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከያና መቆጣጠሪያን ተጠያቂ አድገዋል የሚል ዜና በአገር ውስጥ የመገናኛ ብዙኃን ተስርቷል። ፖሊስ ቃጠሎው የተነሳው ከጃዝ አምባ ነው ብሎ ቢናገርም የጃዝ አምባው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤርምያስ ፋንቱ ጨርሶ ቅጥፍት አድርግውታል። የጃዝ አምባ የኤሌክትሪክ ሲስተም

አዲስ የቋንቋ ፖሊሲ ረቀቀ - ለምን? “ባለፉት ስርዓቶች ተጨቁነው ለአደጋ የተጋለጡ ቋንቋዎች እንዲለሙና መልሰው እንዲያንሰራሩ የሚያስችል በኢትዮጵያ በዓይነቱ የመጀመሪያው ነው” የተባለለት አዲስ የቋቋ ፖሊሲ መረቀቁን መንግሥት አስታወቀ። የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ጥር 7 ለኢዜአ እንደገለጹት ፖሊሲው በተያዘው ዓመት የሕግ ማእቀፍ ሆኖ ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።ፖሊሲው ሁሉም ቋንቋዎች በእኩል ሁኔታ ለመንግስታዊ ስራዎችና ለትምህርት መስጪያነት ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ ያለመና ከ47 በላይ ቋንቋዎች ሥርዓተ ትምህርት ተቀርፆላቸውና መምህራን ተመድቦላቸው ዜጎች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው እየተማሩ መሆናቸውን

202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com dereje@zethiopia.com

አዲስና ደረጃውን የጠበቀ የጣይቱ ሆቴል ቃጠሎ በመሆኑ ለእንዲህ አይነት አደጋ መንስኤው አልታወቀም የሚጋለጥበት ምንም ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው እንደሌለና ላለፉት አራት ዓመታት ሆቴል የሆነውና በ1888 ዓ.ም ምንም ዓይነት ችግር አጋጥሞ የተገነባው ታሪካዊው የእቴጌ እንደማያውቅ ለአዲስ አድማስ ጣይቱ ሆቴል በቅርቡ በደረሰው የተናገሩት አቶ ኤርሚያስ፤ ፖሊስ ቃጠሎ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት እሳቱ የተነሳው ከጃዝ አምባ ነው በመሆኑ ሲዘገብ ሰንብቷል። ማለቱ እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡ በቃጠሎው አነሳስና አከላከል ፡ “ከሙዚቃ መሳሪያ ጋር በተገናኘ

ባለሥልጣኑ ገልጸዋል። መንግሥት ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በአፍ መፍቻ ቋንቋቸው የሚማሩበትን ፊደላትና ሌሎች አስፈላጊ መሳሪያዎችን እንደሚያዘጋጅ ዳይሬክተሩ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ቋንቋዎች ያላት መሆኑን የገለጸው መንግስት ምኑን ከምኑ አድርጎ ሁሉንም ቋንቋዎች ፊደል እንደሚቀርጽላቸው እኩል አድርጎ ከዘመኑ ቴክኖሎጂ እንደሚያዋሃዳቸው አላብራራም። ጥናቱ አልቆ ፖሊሲው ተረቆ ለረጀም ጊዜ የቆየ መሆኑ ቢገለጽም ዛሬ ብድግ ብሎ የሰነበተ ሰነድ አቧራውን አራግፎ ማንሳት የፈለገበት ምክያት ግልጽ አይደለም። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የቋንቋ ጥናትና ምርምር ተቋማትንና ፕሮግራሞቻቸውን በመዝጋት

የታወቀው መንግሥት፣ በአፍ መፍቻ ቋንቋ አጠቃቀም ውዝግብ ብዙ ግጭቶችን አስተናግዶ ያለፈ መንግሥት፣ ብሎ ብሎ ወዳቃተው ፖለቲካ እንደገና ለምን መግባት እንደፈለገ ግልጽ አይደለም። ያውም ዛሬ? ብቸኝነት የተሰማው መንግሥት ድጋፍ ማሰባሰቢያ ሊያደርገው የፈለገ ይመስላል። ድጋፉም ባይገኝ መተረማመሱ ይገኛል። ከዚያ ትርምስ ስጋት፣ ከስጋቱ ደግሞ አንተው ቆይልን የሚለው የሥልጣንና የህልውና ጥያቄ ይመነጫል። ይኸው ነው። "አማርኛ" የሚለውን አስተያየት በገጽ 14 ይመልከቱ!

የዕንቁ መጽሔት ማኔጂኒግ ዳይሬክተር ፍቃዱ ማህተመወርቅ ታሰረ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መ/ቤት መክፍል የሚገባውን ግብር አልከፈለም በሚል ሰበብ ቂርቆስ ክ/ከተማ የሀገር ውስጥ ገቢ ጊዚያዊ ማቆያ እስር ቤት ከታሰረ በኋላ ጥር 14 ቀን 2007 በአራዳ የመጀመሪያው ፍርድ ቤት ቀርቧል። ጉዳዩን የያዘው የአገር ውስጥ መርማሪ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመጠየቁ የጠየቀው የዋስትና ጥያቄው ወድቅ ሆኖ ተጨማሪ የሰባት ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆበታል። እሳቱ ተነስቷል እንዳይባል እንኳን እሁድ ጠዋት የጃዝ አምባ ሰራተኛ የሆነው ልጅ ገብቶ መድረኩን ለቴአትር ዝግጁ ለማድረግ ሁሉንም የሙዚቃ መሳሪያ አነሳስቶ ነበር” ብለዋል፡ ፡፡ ታዲያ እሳቱ ከየት መጣ? የእሳት አደጋ ሠራተኞች ፈጥነው አልደረሱም ከደረሱም በኋላ በቸልተኝነት ጊዜ ፈጅተዋል ተብሎ መወቀሳቸው የተገለጸላቸው የ እሳት አደጋው የኮሙዩሚኬሽን ኢፊሰር በሁለት ደቂቃዎች ውስጥ መድረሳቸውን በመግለስ ሠራተኞቹ ምንም አይነት ቸልተኝነት አላሣዩም ያሉት አቶ ንጋቱ፤” እሣት እንደ ሻማ እፍ ተብሎ የማይጠፋ በመሆኑና ህዝብ የማይረዳቸው ብዙ ቴክኒካል ነገሮች በመኖራቸው እነሱ እስከሚስተካከሉ ድረስ ደቂቃዎች ማለፋቸው አይቀሬ ነው” ብለዋል፡፡ እሳት እፍ ተብሎ እንደሻማ የማይጠፋ ገጽ 15

በኢትዮጵያ ከባድ ዕቃዎችን የማንሳት ሥራ የሚሰራ

ክሬን ማምረቻ ፋብሪካ ተመረቀ

በኢትዮጵያ ከባድ ዕቃዎችን የማንሳት ሥራ የሚሰራ ኬ.አይ.ጂ የተባለ የክሬን ማምረቻ ፋብሪካ ተገንብቶ ተመረቀ። ፋብሪካው በሃገሪቱ ለሚከናወኑ የኮንስትራክሽን ግንባታ የሚያገለግሉ ማሽኖችንና የገዘፉ እቃዎችን ለማንሳትና ለማውረድ እንደሚረዳ ተገልጿል። የ400 ሚሊዮን ብር ካፒታል ያለው የፋብሪካ ባለቤት የሆኑት አቶ ካህሳይ ገ/እግዚአብሔር እንደተናገሩት ይህኛውን ፋብሪካ ህንጻ ብቻ ለማቋቋም ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎበታል። 150 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ ትላልቅ የክሬን መፈብረኪያ ማሽኖች ሲገጠሙለት ፋብሪካው ለሥራ ዝግጁ ይሆናል። የሚመረቱት ክሬኖች እስከ 80 ቶን የሚደርስ ክብደት ያለው ዕቃ የማንሳት አቅም እንዳላቸው አቶ ካኽሳይ ገብረ እግዚአብሔር ገልጸዋል።

የአቶ ካኽሳይ ድርጅት ንብረትነቱ የመከላከያ ሠራዊት ከሆነው የሜቴክ የብረታ ብረት እና ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ጋር አብሮ እንደሚሠራ ተገልጿል። ፋብሪካው ለጊዜው ከ10 እስከ 50 ቶን ሊያነሱ የሚችሉ ማንሻ ክሬኖችን ለመስራት ሲያቅድ እያንዳንዳቸውን ክሬኖች ከ3-22 ሚሊዮን ብር እንደሚሸጣቸው አስታውቋል። ከወዲሁ ከሜትክ (የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን) 10 ክሬኖችን ለመግዛት ትዕዛዝ መቀበሉን አቶ ካኽሳይ አስታውቀዋል። ከዲሴምበር 13/2014 ጀምሮ በቃሊቲ አካባቢ 6ሺ ስክዬር ኪሎሜትር ላይ የገነባውን ፋብሪካ የኢንደስትሪ ሚኒስትሩ ደኤታ አቶ ታደሰ ኃይሌ በተገኙበት ማስመረቁን ሚኒስትሩ ባወጣው ዘገባ ገልጿል።


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

2

ምን ያህል ይቀረናል? ትራንስፎርሜሽን

መወቃቀስ መያዛቸው ይሰማል። ቀጣዩ አቅጣጫ ይህ ሊሆን ይገባል አይገባም መባባላቸው እየተሰማ ነው። ክርክሩ ንትርክ ከንትርክም አልፎ የተካረረ መስመር እየያዘ መምጣቱ ይሰማል። ይህ ወደ ፖለቲካው ሽኩቻ አድጎ ወይም ሰበብ ሆኖ እንደ ኤርትራው ጦርነት ክፍፍል ዘመን ኢህአዴጎችን ለሁለት እንዳይከፍላቸው አስግቷል። ወይም አስጎምዥቷል። በሌላ አነጋገር አቶ መለስ ልክ ነበሩ ወይስ አልነበሩም ይከለሱ ወይስ አይከለሱ የሚል ትርጓሜ እየፈጠረ ይመስላል። የመለስ ራዕይ ወይም አስተምህሮ አራማጆችና አስጠባቂዎች ባንድ በኩል ከላሾችና ምንትስ ሊብራሎች የተባሉት ደግሞ በሌላ በኩል ሆነው ለመወጋገዝ በተጠንቀቅ ሆነዋል። የክፍፍል ዓይነቱ ብዙ ነው። ፓርቲ ውስጥ ያሉትን የመንግሥት ሰዎች በአንድ በኩል መንግሥት ውስጥ የሌሉ የፓርቲ ሰዎችን ደግሞ በሌላ በኩል ማሰለፉም እየተሰማ ነው። ለዚህ ሁሉ የልማትና የትንራንስፎርሜሽን እቅዱ ዋነኛው መነጋገሪያ ወይም የመዋጊያ ሜዳ መስሏል።

በአንድ የቅርብ ስብሰባ ላይ አቶ አዲሱ ለገሠ አቶ አርከበን ሲነቅፉ “ ቆይ ቆይ አርከበ እኔ እዚህችጋር አንድ ጥያቄ አለችኝ። እስኪ ይሄ ያዘጋጀኸው ዶክመንት ከመለስ አስተምህሮ ጋር እንዴት እንደሚሄድ አስረዳኝ......” አቶ አዲሱ በኢህአዴግ ድርጅታዊ መዋቅር ውስጥ እንጂ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሉም። አቶ አርከበ ደግሞ በመንግሥት እንጂ በድርጅቱ መዋቅር ውስጥ የሉም። መዋቅር የማያገናኛውቸው ከሆነ ሁለቱን ከአንድ ስብሰባ ምን አስቀመጣቸው? የመከራከሪያቸው ፍሬ ነገርስ ስለምን የመለስ አስተምህሮ ሆነ? የመለስ አስተምህሮ ራዕይና ሌጋሲ የአገሪቱ አቅጣጫ መመሪያ ማስፈራሪያ እየሆነ ዋነኞቹን ባለሥልጣናት ሳይቀር እያከራከረ ይመስላል። ወደታች ወረድ ብለን እንመለከተዋለን። ለማናኛውም አቶ መለስ ዜናዊ ሞልተውን ለሄዱት የውድቀትም ሆነ የእድገት ሰሌዳ፣ ከአንዳቸው እንደርስ ዘንድ ምን ያህል ጊዜ ይቀረናል? በራዕይ የተገለጠላቸውን የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ምልክቱን እናይ ዘንድ ምን ያህል መጓዝ ይኖርብናል? ወይስ ደርሰናል ? ወይስ አቅጣጫውን ስተን ሌላ መንገድ ይዘናል? ከእድገቱ ወይስ ከቁልቁልቱ አፋፍ ላይ ነን? በፈጣኑ እድገታችን ፋፍተን እንደ ጽጌረዳ ፈንድተን እንፈካለን ወይስ እንደ ፈንጂው እንጠፋለን? ወዴት እየሄድን ነው?

2015 እና ኢህዴግ! የአቶ መለስ ራዕይ ወራሽች የእሳቸውን ሌጋሲ እናስጠብቃለን ህልማቸው እንፈጽማለን አገሪቱ ከመልካም ጎዳና ላይ ናት ሲሉን ደጋገመን ሰምተናል። እሳቸው የሞቱ እንደሆን ማን ይተካቸዋል የተባሉትን አቶ መለስ ዜናዊን በደቂቃ የተኩት አቶ ኃይለማያርም ደሳለኝ መለስ “በኔ አድረው ይቀጥላሉ እኔ የሳቸው ህልምና ትልም አስፈጻሚ ነኝ…” በማለት ምለው ተገዝተው ሲነግሩንም ሰምተናል። አሁን አሁን ግን በርግጥ እንደሱ ማለቴ አልነበረም ከአቶ መለስ ህልማቸውን እንጂ ግብራቸውን ልወርስ አልፈልግም፤ የሳቸው መንገድና የኔ መንገድ የተለያየ ነው ማለት ጀማምረዋል የሚል ነገር መኖሩን ብንሰማ “አሄሄ!” ብለን ከማሾፍ አናልፍ ይሆናል። ምክናያቱም አቶ ኃይለማርያምን እንደ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ እንደ አቶ መለስ ዜናዊ ፈላጭ ቆራጭ አድርገን አለመቀበላችን አንዱ ማጣጣያችን ሊሆን ይችላል። አቶ ኃይለማርያም የመለስን ራዕይ አላስፈጽምም ቢሉ ታዲያ የማንን ሊያስፈጽሙ ፈለጉ ብለን እንጠይቃቸዋለን እንጂ መቸም በራሳቸው ራዕይ ባለቤትነት አንጠረጥራቸውም። አሁን የጨነቀን ኢትዮጵያ በመለስ ራዕይ የማታድር ከሆነ ታዲያ በማን ራዕይ ማደሩን ወደደች ወይም ተገደደች ብለን ማሰቡ ላይ ነው። “የመለስ ራዕይ የሚባል ነገር የለም፤ ያለው የኢህአዴግ ራዕይ ነው” ያሉንን እነ አቦይ ስብሐትን እናስታውሳለን። ከዲጃ ሄደች ፋጤ መጣች መለስ ሞተ ተነሳ ብለን አቋማችንን አንቀይርም እኛ ድርጅት ነን በድርጅታዊ መርህ እናድራለን ሲሉንም አድምጠናል። ያልሰማነው ነገር እንደ ከዲጃ የተቆጠሩት አቶ መለስ ዜናዊ የሌጋሲያቸው እጣ ፈንታው ምን ሆነ የሚለውን ነው። የግል ሥልጣን ያከማቹት አቶ መለስ “ድርጅቱን ገድለውት ሄደዋል” ሲሉ የነበሩት ጓዶቻቸው በተራቸው፣ አሁን ደግሞ “ድርጅቱ አቶ መለስን ሊገድል ይገባል” የሚሉ መስለዋል እየተባለ ነው። መቸም በዚህ እነ አቶ አርከበ እቁባይን መጠርጠር አይገባም። የሆኖ ሆኖ መለስ አቅደውታል የተባለው ነገር ሁሉ አንዱም አልሠራም። ከዚያም አልፎ በመሄድ ሠርቶም አያውቅ

የሚሉም ተነስተዋል። ለመሆኑ መለስ ያቀዱት ነገር ምንድን ነበር ቢባል የአምስት ዓመቱ የልማትና የትንራንስፎርሜሽን እቅዱ ዋነኛው ሆኖ ይጠቀሳል።

የእቅዱ እውነታና የኢህአዴግ ግምገማ ኢህአዴጎችን በምርጫ የሚሞግታቸው ቢኖር አሁን በራሳቸው ቋንቋና በራሳቸው እቅድ በቀላሉ ሊረታቸው ይችላል። ምክንያቱንም እንሰራዋለን ያሉትን አልፈጸሙም። እናሟላለን ያሉትን አላሟሉም። ለዚህም ማስረጃው የራሳቸውን አብይ እቅድ የሆነው የ5 ዓመቱ የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድና ግምገማ ነው። ኢህአዴጎች እንደቀድሞ ቢሆን የሚያወጡትን ግብ ስኬት የሚያወጡት በመቶኛ ነበር። ይህን ያህል አቅደን ይህን ያህሉን ፐርሰንት/መቶኛ ፈጽመናል በማለት ተሳክቶልናል ይላሉ። አሁን ግን ያን ሊሉ የሚችሉበት ሁኔታ የለም። ምክንያቱም አሁን በትራንስፎርሜሽኑ እንሰራለን እናሳያለን ያሉት በኪሎሜትር የሚለካ በቁጥር የሚሰፈር በመገንባትና ባለመንገባት የሚረጋገጥ እቅድ ነው። አንዳንዶች እንደሚሉት በዚህ የተነሳ ኢህአዴጎቹ በራሳቸው ላይ ገመድ አንጥልጥለዋል። እንደ ድሮ ቁጥር ማስላት በመቶኛ መከራከር የለም። ጨበጣው ቀርቷል። አሁን እንሰራለን ያላችሁት መንገድ የታለ? እንዘረጋለን ያላችሁት የኮረንቲ ገመድስ ወዴት ነው? ቃል የገባችሁት የባቡር ሐዲድ ታዲያ የታለ?.... የሚል ቀላል ጥያቄ ማቅረብ በቂ ሆኗል። እቅዱ እንኳን ሌላው እነሱም ሊክዱ ያልቻሉት መጋለጥን አምጥቶባቸዋል። በ5 ዓመት ውስጥ ይህን ይህን እንደርጋለን ብለው የተዘረዘረ የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አውጥተዋል። ውጤቱ ግን አይገናኝም። ካቀዱት አለመገናኘቱ ግን የሁለተኛውን የ5 ዓመት የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማውጣት ከመዘጋጀት አላገዳቸውም። ብናሳካም ባናሳካም ብንችልም ባንችልም ያለነው እኛው ነንና እንደገና እንቀጥላለን ባዮች ሆነዋል። ይሁን እንጂ ከውጭ የሚሞግታቸው ባይኖርም ከውስጥ ግን እርስ በርሳቸው በዚህ ክሽፈት ዙሪያ

በወቅቱ እንደተዘገበው 8ኛው የኢህ አዴግ ጉባዔ የተካሄደው ከመስከረም 5-7/2003 ዓ.ም አዳማ የኦሮምያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነበር። ጉባዔውን በመምራት ላይ የነበሩት አቶ መለስ፣ የአምስት- ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ የተደረገው ውይይት በቂ እንደሆነ ገልፀው፣ ‹‹የቀረበውን ሪፖርት መፅደቁን የምትደግፉ፣ ያደረጋችሁትን ባጅ ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ›› ሲሉ ጠየቁ። ጉባዔተኛው በሙሉ አንገታቸው ላይ ያንጠለጠሉትን ሰማያዊ የጉባዔ ተሳታፊነት መለያ ወደ ሰማይ ቀሰሩ። ‹‹እቅዱን የምትቃወሙና ድምፅ የማትሰጡ?›› ማንም የለም።

ሰበብ ሆኖ የሚያነጋግረው ይሄ የ 5 ዓመት እቅዱ ዋነኛው ይሁን እንጂ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ እያደገ የመጣው መናናቅና ዓይን የሚሞላ ሰው በድርጅቱ አመራር ውስጥ አለመገኘት መሆኑም ይወራል። ሥልጣን የባለ ራዕዮች ስለሆነ የነበረውን ማስቀጠል ወይም አዲስ ራዕይ መውለድ ወቅቱ የጠየቀው ጥያቄ መስሏል። ይህ ሁሉ ተደማምሮ የመጀመሪያውን እቅድ አፈጻጸምን በመገምገምና በሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን አስተቃቀድ ላይ አለመግባባት ደንቅሯል። በዚህ ጽሑፍ የምናየው እነዚህን ይሆናል። ወደ ገጽ 6

እቅዱ ይፋ የተደረገበት መስከረም 4 ቀን 2003 እዚያው የኢህአዴግ 8ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ አዳራሽ ውስጥ የነበረው አትሌት ባለሀብት ኃይሌ ገብረሰሥላሴ ጉባኤውንና እነ አቶ መለስን እንዲህ ሲል መከረ “አደራ የምላችሁ እቅድ አውጥተናል 5 ዓመት! ይህ አምስት ዓመት እንደ አያያዙ ነው። በዓመታት ከወሰናችሁ ይከብዳል። መሆን ያለበት በቀንም አይደለም በወራትም አይደለም በደቂቃም አይለም በሴኮንድ ነው። ... እኔ በሴኮንድ 10 ሚሊዮን ብር አግኝቻለሁ በሴኮንድ 10 ሚሊዮን ብር አጥቻለሁሴኮንድ ዋጋ ኣላት... እቅዳችንን ለሴኮንዶች ዋጋ በመስጠት መጀመር እንዳለበት አሳስባለሁ። “ በማለት ለኢህአዴግ ያለውን ድጋፍ ምክር ገለፀ። አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ። አሁን አቶ መለስ ሞተዋል.. እቅዳቸውስ? ወደ ገጽ 4

“የአምስት- ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጸድቋል።” አሉ። አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ። የአቶ መለስ በዚህ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር እንዲህ አሉ bxND wQT yxg‰CN xþ÷ñ¸ kðýÄlþZM wdXZ ኢþ÷ñ¸ XNdtSfn«rý hùlù# kXZ xþ÷ñ¸ wdnþ× lþb‰L ygbà xK‰¶nT ymSfN«„N xdU tÌqÜmN kxg‰CN hùn¤¬ UR ytÈÈm L¥¬êE mNGST mF«RN ¥:kL Ãdrg yL¥T xQÈÅ lmqyS bmÒ§CN Xnç b¬¶µCN ¬Yè b¥Y¬wQ xµ*ºN lsÆT tk¬¬Y xm¬T fÈN FT¦êE L¥TN ¥rUg_ ClÂL”” DHnTN btúµ hùn¤¬ têGtN XùnFN ÄGM bSLÈn¤ ¯Ä mr¥mD jMrÂL”” kîST xm¬T bðT ytjmrý xÄþsù yxg‰CN ¸l¤NyM bRG_M yxþT×eà yHÄs¤ zmN XNd¸çN xm§KaL”” kxND ¹þ xmT b§Y yöyý yºlþT gùø tqLBî bXDgT ¯Ä bF_nT mr¥mD jMrÂL”” bÃZný F_nT kq«LN b¸q_lùT xm¬T kkÍ DHnT t§qN mµkl¾ gbþ çcýN xgéC ¯‰ XNdMNq§qL GLI Xyçn m_aL”” bzþhù xµ*ºN kq«LN lzmÂT wDqNbT knbrý xSkð xrNÌ w_tN kBzù ¹þ xm¬T bðT XNdnbrý hùlù kxMú xm¬T ÆLbl« gþz¤ ysl«nù xgéCN ¯‰ XNdMNq§qL lmgmT y¸ÒLbT dr© §Y dRsÂL”” gùÆx¤ÃCN bmÀãcÜ xMST xm¬T ytlmdýN 11 bmè b§Y XDgT l¥Sq«L# kzþÃM xLæ btÒl m«N b¸q_lùT xMST xm¬T Bÿ‰êE gbþÃCNN bX_F y¥údG tLX÷ Ãlý XQD XNd¸Ã{DQ Y«bÝL”” 8¾ DRJ¬êE gùÆx¤ÃCN bfÈN XDgtÜ £dT xg‰CN mµkl¾ gbþ çcýN xgéC ¯‰ yMTq§qLbTN QDm ZGJT y¥«ÂqQ tL:÷ yt¹km gùÆx¤ ný”” እቅቀአቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ ግን ድርጅታቸው ዛሬ ላይ ቆሞ ሲያየው የአቶ መለስ እቅድ ያለቅጥ የተለጠጠ ነበር። ምክንያቱም አልተሳካም። የማይሳካው ነገርም የታቀደው ሆን ተብሎ ነው። አቶ መለስን ልክ አልነበሩም በማለትና እሳቸውን በማምለክ መካከል በመንገላታት ላይ የሚገኘው ድርጅታቸው በጣም የሚያስቅ መግለጫ ይዞ ወጥቷል። የአቶ መለስን ስህተት እንኳ እንድ ራዕይ አይቶት ከሰማይ ከዋክብትን ከማርገፍ ጋር አመሳስሎታል። በሌላ በኩል ደግሞ አቶ መለስ ከላይ በንግግራቸው "wdnþ× lþb‰L ygbà xK‰¶nT ymSfN«„N xdU tÌqÜmN" ያ ያሉትን አደጋ ዛሬ መልሶ የሚያመጣ ወይም ድላቸውን የሚቀለብስ አደጋ በገዛ ጓዶቻቸው መጥቶባቸዋል። በቦንድ ሽያጩ ትላልቅ ኢንደስትሪ ዞኖችን በማቋቋም ስም ትላልቅ የውጭ ኢንቨስተሮችን ጓዶቻቸው ወደ አገር ውስጥ እየጋበዙላቸው ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ ያሉት እድገት አልመጣም። አገሪቷ በኢኮኖሚ ቀውስ ተዘፍቃ ከሌሎች ችግሮቿ ጋር አብጣ ልትፈነዳ ሰከንድ የምትቆጥር መስላለች.... በኢህአዲግ አመራሮች መካከል ይቅር እንጂ አቶ መለስም ድርጅታቸውንና አገሪቱን ከማይሆን ነገር ውስጥ ዘፍቀዋት ሄደዋል....

"እቅዳችን ከዋክብትን ከሰማይ ተኩሶ የመጣል ያህል ነው - የአቶ መለስ እቅድ የተለጠጠው ለዚህ ነው" የኢህአዴግ ርዕዮተ ዓለም መጽሔት የሆነው አዲስ ራዕይ ከሁለት ወራት በፊት በወጣው የመስከረም 2007 እትሙ ስላልተሳካው የ 5 ዓመቱ የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ማስተባበያ ሰጥቷል። እቅዱ ያለቅጥ መለጠጡን አምኖ ይህ እንዲሆን የተደረገው ግን ሆን ተብሎ መሆኑን ተንትኖና አመኻኝቶ ጽፏል። ኢኮኖሚያችን በዓመት ከ11 ከመቶ በላይ በማደጉ፣ ድሆች በመሆናችን ፈጥነን ለማደግ ካለን ቀና ጉጉት፣ በ2010 ምርጫ ሳላሸነፍንና ህዝቡ አዎንታውን ስለሰጠን፣ በቂ የሰው ኃይልና እምቅ ሀብት ስላለን እነሱን መነሻ በማድረግ ያን መሳይ እቅድ አውጥተናል ብሏል። በየዓመቱም “ከተቻለ የ15 በመቶ ከፍተኛ የዕድገት ምጣኔ ለማምጣት አልመን የተነሳንበት ዕቅድ ነበር።” በማለት መነሻው አንዳንዶች እንደሚያጣጥሉት አይደለም ብሏል። የድርጅቱ የኢህአዴግ ጽሑፍ ተቆጥቶ እንደዚህ ብሏል“የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን ሲነደፍ የተለጠጡ ግቦችን እያለምን እንድንሰራ የተፈለገው... አንዳንዶች እንደሚሉት የተለጠጡ ግቦች የሚፈለጉት ህዝብን በባዶ ተስፋ ለመሸንገልና በምናባቸው ከፈጠሩት ውጥረት በአልባሌ ስልቶች ታግዞ ለማምለጥ አይደለም፡፡ የምንኖረው በቻይና የፈጣን ዕድገት ማዕከል የሆነችውና ከሞላ ጎደል የኢትዮጵያን ያክል ህዝብ ያላት ጓንዶንግ ክፍለ ሃገር ከሰላሳ ዓመት በላይ ለሆነ ጊዜ በአማካይ የሃያ ሰባት በመቶ ዓመታዊ ዕድገት እያስመዘገበች የመጓዝ ልምድ ባዳበረችበት ዓለም ነው፡፡ ስለሆነም ድርጅታችንና ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስታችን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን በሚያዘጋጁበት ጊዜ ከዋክብትን ከሰማይ ላይ ተኩሶ የመጣልን ያህል የላቀ ግብ አንግበው መነሳታቸው አማራጭ የሌለው ነበረ፡፡” በስኬቱ ብቻ ሳይሆን በውድቀቱም ለመጽናናት የማይበገር የሚመስለው ድርጅት በመኩራራት “በእርግጥም ድርጅታችንና በእርሱ የሚመራው ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ መንግስት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱን የተለጠጠ ግብ አስይዘው ማዘጋጀታቸው ፍፁም ትክክል እንደነበር በድጋሚ ለማረጋገጥ ይቻላል።” ብሏል። በራሳችን ተነሳሽነት ለጥጠን ያስቀመጥነው ግብ ላይ ባለመድረሳችን ዛሬም የምንቆጭና ለነገ በእልህና የላቀ ወኔ መነሳሳት እንዳለብን የምንገነዘብ ቢሆንም በአራቱ ዓመታት ርብርብ ያስመዘገብነው ውጤት የአገራችን፣ የህዝባችንና የድርጅታችን ኩራት ምንጭ ከመሆኑም በተጨማሪ ለቀጣይ መሻሻል ብዙ ትምህርቶች የገበየንበት ነው፡፡ ስለዚህ አገሪቱ ያቀደቻቸውን ተግባራዊ ያደረገችባቸው ሳይሆን መሬት ያስነካችባቸው ሆኖ አርፎታል። ኮከቡን ከሰማይ የሚጥለው ህልም ገና ከመሬት አልተነሳም። ስለዚህ ምን ይታቀድ ወደ ገጽ 6

የእቅዳቸው መክሸፍ ግን የሁለተኛውን የ5 ዓመት የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማውጣት ከመዘጋጀት አላገዳቸውም። ብናሳካም ባናሳካም፣ ብንችልም ባንችልም ያለነው እኛው ነንና እንደገና እንቀጥላለን ባዮች ሆነዋል። ይሁን እንጂ ከውጭ የሚሞግታቸው ባይኖርም ከውስጥ ግን መናናቁ ስልጣንና ገንዘብ ፍለጋው ተጨምሮበት እርስ በርሳቸው ስለውጥረቱ መወቃቀስ መያዛቸው ይሰማል። ቀጣዩ አቅጣጫ ይህ ሊሆን ይገባል አይገባም የመባባላቸው ጉዳይ የተካረረ መስመር እየያዘ መምጣቱም ይታያል። ይህ ወደ ፖለቲካው ሽኩቻ አድጎ ወይም ሰበብ ሆኖ እንደ ኤርትራው ጦርነት ክፍፍል ዘመን ኢህአዴጎችን ለሁለት እንዳይከፍላቸው አስግቷል። ወይም አስጎምዥቷል።


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

“ተንጠራርተን ከምናወርደው ፍሬ ይልቅ መጀመሪያ በእጃችን ያለው ይበልጣል-

ትግራይ ኢንደስትሪን እንጂ የገጠር ልማት ፖሊሲን አልተከተለችም ። ይህን ፤ ከፌዴሬሽን ም/ቤት የበጀት ቀመር እና ከ2010 የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት መረዳት ይቻላል ሁሉም ዳታዎች የ2010 ናቸው

አንድ እግር በመሬት” የአቶ መለስ ዜናዊ የገጠር ፖሊሲ

የኢንደስትሪው ፖሊሲ በትግራይ! አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከስድስት ወራት በኋላ ባለቤትና ልጆቻቸውን ካሉበት ሆነው በስልክ ማነጋገራቸው ተነግሯል። ባለቤታቸውን ጠቅሶ ኢሳት እንደዘገበው አቶ አንዳርጋቸው ወደ ቤተሰባቸው የደወሉት በድንገት ነው። “ድምጹን ድንገት ስንሰማ ደስታም ድንጋጤም የተቀላቀለበት፣እንዲሁም ምንም ልናደርለት ባለመቻላችን ቁጭት ንዴት እና አቅም ማጣት ስሜት” ተሰምቶናል ብለዋል ባለቤታቸው ወ/ሮ የምስራች። አቶ አንዳርጋቸው በጤነነታቸው አንጻር “በደህና ጤንነት”ላይ መሆናቸውን እንደለገለጹ ተዘግቧል። የእንግሊዝ ፓርላማ አባላትና የጠበቆች ማህበር ተወካይ ወደ ኢትዮጵያ የማቅናታቸው ዜና ተስፋ እንዳሳደረባቸውም ወይዘሮ የምስራች መናገራቸው ተገልጿል።

የዕንቁ መጽሔት ማኔጂኒግ ዳይሬክተር ፍቃዱ ማህተመወርቅ ታሰረ ለገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን መ/ቤት መክፍል የሚገባውን ግብር አልከፈለም በሚል ሰበብ ቂርቆስ ክ/ ከተማ የሀገር ውስጥ ገቢ ጊዚያዊ ማቆያ እስር ቤት ከታሰረ በኋላ ጥር 14 ቀን 2007 በአራዳ የመጀመሪያው ፍርድ ቤት ቀርቧል። ጉዳዩን የያዘው የአገር ውስጥ መርማሪ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመጠየቁ የጠየቀው የዋስትና ጥያቄው ወድቅ ሆኖ ተጨማሪ የሰባት ቀናት ቀጠሮ ተጠይቆበታል።

የቀድሞ የኢትዮጵያ የኮሙዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሚኒስትር ደኤታ እና የመለስ ትሩፋቶች መጽሐፍ ጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ለገሠ የአምስት ዓመቱ የልማትና የትራንስፎርሜሽን ማጠንጠኛ ነው በተባለው የኢንደስትሪ ግንባታ ላይ ልምዳቸውን መሠረት በማድረግ አስተያየታቸውን ለዘኢትዮጵያ ሰጥተዋል። እንደሳቸው እምነት ፖሊሲው

ራሱ የወጣው ድንገተኛ በሆነ እወጃ እንጂ በቂ ጥናትና ዝግጅት አልተደረገበትም። ትራንስፎርሜሽን የተባለውም ከአነስተኛና የነፍስ ወከፍ የገጠር ልማት ወደ ትልቅ ኢንደትስትሪ ወይም መሠረት ልማት ወደ ተሟላበት ወደ ከተማ ልማት የሚደረገው የአኗኗር ሽግግር ጭርም ነው። ይህ አልታየም። ምክንያቱም ከመነሻውም ቢሆን የትላልቅ ፕሮጀክቶች ሀሳብ ወይም የትንራንስፍሮሜሽን ሀሳብ

3

የመጣው የአቶ መለስ የቀደመው ፖሊሲ ያልሠራ መሆኑን ለራሳቸው ለአቶ መለስ ጭምር ከድርጅታቸው ቅሬታና ሂስ መቅረብ በመጀመሩ የተነሳ ነው። አቶ ኤርምያስ እንደሚከተለው አብራርተዋል። ከትራንስፍሮሜሽኑ በፊት አቶ መለስ ይሉት የነበረው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተመሠረተው እርሻ ላይ ስለሆነ ትኩረታች በሙሉ እዚያ ነው መሆን ያለበት። በእጃችን ያለው የአርሶ አደሩ መሬትና የሰው ጉልበት ነው። ያለንን ትተንት ሌላ ነገር ውስጥ እንዳንገባ ዋናው ትኩረታችንን በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ማድረግ አለብን። በዚህ የተነሳ ዋነኛ ሥራችን በመሬት ላያ ያለው ሥራ ነው ተብሎ ተነገረ። አርሶ አደሩ በእጁ ያለውን ትናንሽ ማሳ እንዲያለማ የሚፈልገው ሁሉ ይቅረብለት ተባለ። ጥቃቅን የመስኖ ልማት ጥቃቅን የግብርና ልማት ሁሉ ነገር ጥቃቅን ሆነ። ይህ አስተሳሰብ ከ1993 እስከ 2002 ለ9 ዓመታት ይህል ተለፈፈ። ካድሬዎች ይህን ይዘን ጮኽን። ወደ ኋላው ላይ ምንም ውጤት አላስገኝ አለ።

ትግራይ

አማራ

ደቡብ

የትልልቅና መካከለኛ ኢንደስትሪዎች ምርት ሽያጭ

3.5 ቢሊዮን

1.2 ቢሊዮን

1.2 ቢሊዮን

የመካከለኛና ትላልቅ ኢንደስትሪዎች ብዛት

199

233 ፋብሪካዎች

292 ፋብሪካዎች

የንግድ ተቋማት ገቢ

92 ሚሊዮን

92.8 ሚሊዮን

38 ሚሊዮን

የጅምላ ንግድ(የማ ዕከላዊ ስታስትስቲክስ ኤጀንሲ የጅምላና ችግርቻሮ ናሙና ጥናት 2010)

719 ሚሊዮን

605 ሚሊዮን

198 ሚሊዮን

የሞተር ተሽከርካሪዎች ሽያጭ

64 ሚሊዮን

7 ሚሊዮን

14 ሚሊዮን

ፋብሪካዎች

ወደ ገጽ 5

የትልልቅና መካከለኛ ኢንደስትሪዎች ምርት ሽያጭ

ትግራይ አማራ

ደቡብ

የመካከለኛና ትላልቅ ኢንደስትሪዎች ብዛት

ትግራይ አማራ

የ2ኛ ደረጃ ሽፋን የአገሪቱ አማካይ 16.4 % ነው

ትግራይ አማራ ደቡብ ኦሮምያ

ደቡብ

የመጠጥ ውሃ ሽፋን የአገሪቱ ከተማ አማካይ 51%

ትግራይ አማራ

ደቡብ

እነዚህ ዳታዎች የተገኙት 89 ገጾች ካሉት ከፌዴሬሽን ም/ቤት የበጀት ቀመር 2005-2009 ዶክመንት ነው። ሌሎችም እንዲሁ ከ2010 ማዕካላዊ ስታትስቲክስ የተገኙ ናቸው። ዳታዎቹን ከአገሪቱ የክልሎችና አጠቃላይ የህዝብ ብዛት አናጻር መመልከት ይቻላል።

የዲሲ ታክሲ ባለቤት ማን ይሁን? በዓለሜ ታደሰ ዋሽንግተን

ዲሲና

ታክሲ!

የዲሲ ታክሲ አገልግሎት መጀመሪያውኑ ሲጀመር ጥቁር አሜሪካውያን በትንሽ ወጪ የራሳቸው ቢዝነስ እንዲኖራቸው ታስቦ የተደረገ ነበር። የታክሲ መንጃ ፈቃድ ያወጣ ማንኛውም ሰው፣ ባለ አራት በር መኪና ገዝቶ፣ የራሱ ታክሲ ኖሮት፣ የራሱ አለቃ በመሆን የፈለገውን ሰዓት መርጦ እንዲሰራ ሆነ። ሥራውን ቀድሞውንም ነጭ አሜሪካውያን የማይፈልጉት በመሆኑ በተለይ ከጦርነቱ የተመለሱ ጥቁር የአሜሪካ ወታደሮች በስፋት ያዙት። በጡረታ የሚተዳደሩ አዛውንቶችም ዋና ሥራ ኖሯቸው በትርፍ ጊዜ እየሠሩ ሲጠቀሙበት ቆዩ። በ1970ዎቹና 80ዎቹ መጀመሪያ ተማሪዎች በትርፍ ጊዜ የሚነዱት ሥራ ሲሆን ቀስ በቀስም የውጭ አገር ተወላጆች ኢራኖች ናይጄራውያን፣ ህንዶች አብዛኛዎቹ የዲሲ ታክሲ ነጂ ነበሩ። ወደ 80ዎቹ አጋማሽ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ ለትምህርት የመጡት ዜጎችም በትርፍ ጊዚያቸው ታክሲ ማሽከርከር ጀመሩ። የኢትዮጵያ ፖለቲካና ኑሮ እየከፋ ሲመጣም እጅግ ብዙ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ታሪክ እናት አገራቸውን ትተው የተሰደዱበት ጊዜ ሆኖ ነበር። ከእነዚህ ስደተኞች አብዛኞቹ ወደ አሜሪካ ሲሰደዱ፣ አሜሪካ ከመጣው ደግሞ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ኑሮውን በዲሲና አካባቢው መመሥረት ጀመረ። በዚህም ምክንያት የዲሲ ታክሲ በኢትዮጵያውያንና ከኢትዮጵያ አካባቢ በመጡ የታክሲ ነጂዎች ቁጥር እየጨመረ ሄደ። በጊዜው ብዙዎች ታክሲ መንዳትን ለሚቀጥለው ኢላማና ዓላማቸው ማደሻ በማድረግ ጠንክረው በመስራት ሥራ የያዙ ጥቂት አይደሉም። ሌሎችም የራሳቸን ህይወት በማቃናት ቤተሰብ በመርዳትና በመመስረት የኮሙዩኒቲውም ምሶሶ መሆን ጀመሩ። እንደልባቸው የሚያዙበትን ጊዜያቸውንም ለቤተሰብ በመመደብ፣ ለወግ ለማዕረግ የበቁ ልጆችን በማሳደግ አንጻራዊ ነጻነታቸውን ጠብቀው የቆዩ በርካታዎች ሆነው መታየት ጀመሩ።

የዲሲ ከተማ የዲሲ ከተማ የሚኖሩት በአብዛኛው ጥቁር አሜሪካውያን ነበሩ። ይሁን እንጂ በአሜሪካ የዘር መድልዎ ስለነበር፣ ነጮች ጥቊሮችን ይጨቁኑ ነበር። ወቅቱ ነጭ እና ጥቁር ውሃ የሚጠጡበት ቧንቧ እንኳ የተለየበት፣ ወይም ጥቁሮች የመምረጥ መብት ተነፍጓቸው ለመሠረታዊ መብት ሲታገሉ የነበረበት ወቅት ነበር። ትግሉ በርትቶ በጊዜው የነበረው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆንሰን የዋሽንግተን ዲሲ ነዋሪዎች የራሳቸው አስተዳደር መስርተው ቢኖሩ ይሻላል ብሎ እንዲመክር ተገዶ ነበር። ያ በወቅቱ የተሟላም ባይሆን ከጥቂት ጊዜ በኋላ የዲሲ ከተማ አስተዳደር ቀስ በቀስ በጥቁሮች ሥር ሆኖ መቆየት ጀመረ። በዚህም

ምክንያት ጥቁሮች የበዙበት የታክሲ ሥራ እጅግ ሳይነካ ቆየ። በየጊዜው ግን የታክሲን ሥራ ወደ ራሳቸው ጠቅልለው የግለሰቦችን ባለቤትነት ለመንጠቅ የሞከሩ አልጠፉም፡፡ አዛውንት ጥቁር አሜሪካውያን እየተሟገቱ መሠረታዊ የሆነውን የግል ባለቤትነት ሲያስጠብቁ ኖረዋል። እነሱ ባስጠበቁት መብት በታክሲ ነጂነትና በታክሲ ባለቤትነት የውጭ አገር ዜጋው እየተጠቀመ አነሰም በዛም እስካሁን በዚህ መልኩ ቆይቷል።

ዘመነ ሜየር ፌንቲ ከ2007-11 በሜየር ፌንቲ ዘመን ጀምሮ መልካም ሆኖ የቆየው የታክሲ አገልግሎት ችግሮች ማሳየት ጀመረ። ፌንቲ የቀድሞ የፖሊስ አባል የነበረውን ሊዮን ስዌን (Leon Swain) የሚባል ሰው የታክሲ ኮሚሽን አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመው። በዲሲ ታሪክም በታክሲ ዘርፍ ዋና ዋና ለውጥ የነበረበት ጊዜ ሆነ። ሜየር ፌንቲም ባሳየው ትዕቢት ከአዛውንት ጥቁር አሜሪካውን ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባት ያዘ። የውዝግቡም ምክንያት ከዞን ሲስተም ወደ ሜትር ሲስተም የመቀየሩ ውሳኔ ሆነ። ጥቁር አሜሪካውያኑ እኛን በደንብ ሳታማክር እንዲህ ያለ ለውጥ ለማድረግ ለምን ተነሳሳህ በሚል ቁጣቸውን መግለጽ ጀመሩ። ሜየር ፌንቲ እልህ ገብቶ ቆይ እንዲያውም የታክሲ ነጂዎችን አሳያቸዋለሁ በሚል ሜትሩ የሚጀምርበትን 4 ዶላር ወደ 3 ዶላር ዝቅ አደረገ። ሜሪላንድና ቨንርጂያ የሚኖሩ ታክሲ ነጂዎች በካምፓኒ ሥር ካልሆኑ ባለቤትነታቸውን እነጥቃለሁ የሚል ነገር አመጣ። በዚህ ጊዜ ኢትዮጵያውያን ታክሲ ነጂዎች ተሯሩጠው የራሳቸውን የታክሲ ካምፓኒ በፍጥነት አቋቋሙ።

በፌንቲ ጊዜ የታክሲ ካብ ኮሚሽን ሁኔታ በ2008 ዓ.ም ፌንቲ አገልግሎት አሰጣጡን ከዞን ሲስተም ወደ ሜትር ሲስተም ሲቀይር ከታክሲ ነጂዎች ጋር የነበረው ጭቅጭቅ አላማከርከንም፣ ገቢያችንም ያለ አግባብ ይቀንሳል የሚል ቢሆንም ሜየሩ ግን ለህዝቡ የሚገልጸው ሌላ ነበር። ባለታክሲዎች ላይም ስም የማጥፋት ዘመቻውን ጀመረ። ባለታክሲዎች ለታክሲ ተጠቃሚዎች ወይም ለህዝቡ ያሰብኩትን መልካም ለውጥ አንቀበልም ብለው አሻፈረኝ አሉ የሚል ክስ አመጣ። በተጫማሪም ኮሚሽነር ስዌይን ለኤፍ ቢ አይ ሰዎች ባለታክሲዎች ጉቦ ሊሰጡኝ እየሞከሩ ነው በሚል ክስ በተደረገው የስውር ክትትል ሶስት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉ። በሁለት ዓመት ጊዜ 300ሺ ብር ጉቦ በመስጠት ማስረጃ ቀርቦ ሲከሰሱ

አንድ የከተማው ተቀጣሪ ሠራተኛ ጉቦ በመቀበል ሲታሰር 39 ሰዎች የታክሲ መንጃ ፈቃድ በጉቦ ለማውጣት ሞክረዋል በሚል ተከሰው ፍ/ቤት ቀርበው ቅጣታቸውን ተቀብለዋል። እነዚህ ከላይ የዘርዘኳቸው ሁኔታዎች በሙሉ የዲሲ ታክሲ ኢንዱስትሪ ከከተማው አልፎ በፌደራልና በህዝቡ ዘንድ ትልቅ ትኩረት እንዲያገኝ አደረገው። ውዝግቡ መሻሻል እንደሚገባው በሁሉም ዘንድ ስምምነት ሆነ። ወዲያውም ሜየር ፌንቴ በምርጫ ተሸንፎ ሜየር ግሬይ በታክሲ ነጂዎች ድጋፍ ጭምር ተመረጠ። (ግሬይ ከ2011-14)።

እውን ለማድረግ ወጪውን የከተማው አስተዳደር ታክሲ ተጠቃሚውና ታክሲ ነጂው ይካፈለዋል የሚል አሳብ አቀረበ። አብዛኛውን የከተማው አስተዳደር እንደሚከፍል፣ በተለይም የታክሲ መኪናዎች በከባቢ አየር ኢንቫይሮመንት ተስማሚ እንዲሆኑ ለታክሲ ነጂዎች እርዳታ ይደረጋል የሚል ቃል ገባ።

የሜየር ግሬይ ዘመንና የዲሲ ታክሲ

ሊንተን ሥራው በቋሚነት ኮሚሽነር ቢሆንም ከታክሲ አስተዳዳሪነት ይልቅ ልክ የራሱ ካምፓኒ ዓይነት አስተዳዳሪ መሆን ጀመረ። እንደቀድሞ ሁሉ ከታክሲ ነጂዎች ተቃውሞ ቢግጥመውም ታክሲ ነጂዎች ከመቸውም ይበልጥ የተከፋፈሉበት ጊዜ ነበር። ቀድሞ የሚታገሉለት ጥቁር አሜሪካውንያንም ተዳክመዋል። ከሁሉም በላይ በፊት የገለጽኩት የቀድሞ ኮሚሽነር የታክሲ ኢንደስትሪው የሚንቀሳቀሰው በጉቦ ነው በማለቱ ትላልቅ ባለሥልጣናት ትኩረት ያደረጉበትና የታክሲ ተጠቃሚዎችም ለውጥ የሚፈልጉበት ጊዜ ነበር። አጋጣሚውን በመጠቀም ሮሊንተን የፈለገውን እንደልቡ ለማድረግ ተመቸው። እንዲያውም ለኮሚሽኑ መተዳደሪያ የሚሰጠው ገንዘብ ስለ ማይበቃ ከህዝቡ 0.25 ሳንቲም እየሰሰበብኩ የታክሲ ኢንደስሪን ላሻሽል ብሎ ተነሳ። ለመጀመሪያ ጊዜ በዋሽንግተን ታሪክ አንድ መ/ቤት ገንዘብ ሰብስቦ ራሱን እንዲያስተዳደር ተፈቀደለት። ዶም ላይትና ክሬዲት ካርድ መቀበያ በአስቸኳይ ይግባ በሚል ሽፋን PSP (payment system provider) ገንዘቡን የሚሰበስቡለትን አዘጋጀ። ዶም ላይቱን በ480 ብር ለመሸጥ ተነሳ። ሁሉም ክርከር ሳይደረግበት በአስቸኳያ ስብሰባ ውሳኔ መሰጠቱ አግባብ አይደለም በሚል አምስት የፖኪስታን ተወላጆች ወደ ፌደራል ፍ/ቤት በመሄድ ክስ መሰረቱበት። ክሱም ወደማሸነፍ ስላዘነበለ የዋሽንግተን ከተማ እንደራደር ማለት ጀመረ።ይሁን እንጂ 5ቱ ዋና ከሳሾች እርስ በርስ መጣላት ብቻ ሳይሆን ከጠበቃውም ጋር በመጋጨታቸው የጠበቃ ክፍያ ሳይከፈል ቀረ።ተከራካሪ በመጥፋቱም በፌደራል ፍ/ቤት የቀረበው ክስ ሁሉ ውድቅ ሆነ።

ሜየር ግሬይ ሥልጣን እንደያዘ የታክሲ ኮሚሽነሩን ሊዮን ስዌይን ወዲያኑ አባረረ። በምትኩ ዲና ሪድ (Dena Reed) የምትባለውን የኮሚሽኑ ጠበቃ የኮሚሽኑ ኃላፊ አድርጎ በጊዚያዊነት ሾማት። ግሬይ ከታክሲ ነጂዎች ጋር አብሮ መስራት የፈለገ መሰለ። የተለያዩ ታክሲ ነጂዎችም የተለያዩ ሀሳቦችን ይዘው እየመጡ ሜየር ግሬይን ማስቸገር ያዙ። በዚህ የተማረረው ግሬይ “እኔ አንድ በር ስላለኝ አንድ ሆኗችሁ ኑ!” ብሎ ታክሲ ነጂዎችን አሳወቀ። በኮሚሽነርነት የሾማት ዲና ሪድ የምትመች አልሆነችም። የባሰችው አምባገነን ሆነች። የምታደርገው ነገር ሁሉ አጨቃጫቂ መሆኑ ሳይበቃ የፓርክ ፖሊስ ጠርታ ከህዝባዊ ስብሰባው ውስጥ ሁለት ጋዜጠኞች እስከማሳሰር ደረሰች። ሶስተኛውን ጋዜጠኛ ወደ ስብሰባ እንዳይገባ አሳገደችው።ዜናው ከዲሲ አልፎ “በዲሲ ታክሲ ህዝባዊ ስብሰባ ጋዜጠኞች ታሰሩ” የሚለው በመላው አሜሪካ ትልቅ ዜና ሆኖ ቀረበ። በዚህ መካከል ግን በዲስ ታክሲ ተጠቃሚዎችም በኩል የሚቀርቡ ጥያቄዎች መሰማት የጀመሩበት ጊዜ ነበር። ለምሳሌ ተጠቃሚዎች በካሽ ብቻ በሚለው አከፋፍል የተጉላሉበት፣ መ/ቤቶች ለትራንስፖር የሚሆን ክሬዲት ካርድ የሰጡበትና ሁሉም መንገደኛ ክሬዲት ካርድ ውሰዱልን የሚልበት ጊዜ ብቅ ማለት ጀመረ። በዚህ የተነሳ ሜየር ግሬይ ከየአቅጣጫው ትልቅ ጫና በዛበት። ዲና በተሾመች በሶስት ወሯ አባሮ አዲስና ጠንካራ ኮሚሽነር ይሆናል በሚል የ82 ዓመቱን ሽማግሌ ራን ሊንተንን (Ron Linton) ሾመ። ራን ሊንተንን ከአዳዲስ ስርነቀል ሀሳቦቹ ጋር ብቅ አለ። የዲሲ ታክሲን ወደ 21ኛው ክ/ዘመን አሸጋግረዋለሁ በማለት አንደኛ ሁሉም ታክሲ ክሬዲት ካርድ እንዲቀበል፣ ሁለተኛ ሁሉም ታክሲ አንድ ዓይነት ቀለም እንዲቀባ፣ ሶስት ሁሉም ዓይነት ታክሲ አንድ ዓይነት ዶም ላይት እንዲኖረው፣ አራተኛ የታክሲ ኮሚሽን ቢሮ አሰራር ማሻሻል፣ የሚል አዋጅ አወጀ። ይህንን

የሊንተን አስተዳደር (ኦገስት 2011- 2014)

ዶም ላይትና ክሬዲት መቀበያ ከተገጠመ በኋላ ታክሲ ነጂዎች ብዙ የሥራ ሰዓት አባክነው፣ ያለአግባብ ብዙ ገንዘብ ካወጡ በኋላ፣ ቀን ሲሰሩት የዋሉት ገንዘብ ወደ PSP ይሄዳል። ከዚያም የሚቆራረጠው ገንዘባቸው ወደ ገጽ 9 ተቆራርጦ የነሱን ድርሻ ከሶስት ቀን


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

4

የእነዚህ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ጭቅጭቅ ስናይ ምናልባትም “ቦንድና ሉአላዊነት በኢትዮጵያ” የሚል መጽሐፍ በክፍፍል አፈንግጦ በሚወጣ ሌላ ባለሥልጣን እናነብ ይሆናል። ከገጽ2......

ምን ይታቀድ?

(ሪቪዥኒስት) ናችሁ.... ባዮች ናቸው።

የገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በየዓመቱ የአገሪቱን አጠቃላይ የፖለቲካና ኢኮኖሚ አቅጣጫና ግብ አስመልክቶ ግምገማ ያደርጋሉ። በተለይ የአምስት ዓመቱን የልማትና የትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ይቃኛሉ። አሁን የአምስት ዓመቱ እቅድ ሰኔ ላይ አልቆ ሁለተኛው የአምስት ዓመት የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ይፋ መደረግ ይጀምራል። በዚህም መሠረት ከወራት በፊት በጥቅምት 2007/ ኖቨምበር 2014 ላይ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። በዚሁ ስብሰባ የመጀመሪያውን እቅድ ጉድለቶችና ችግሮች ገምግሞ በሁለተኛው የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መነሻ ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲመጣ አዟል፡፡ የእቅዱ ዋናው ማጠንጠኛ አቅጣጫ የኢንዱስትሪያላዜሽን ትራንስፎርሜሽን ማረጋገጥ እንደሚሆን አስምሮበታል፡፡

ከሱ ይልቅ በትንናሽ መንደሮች (ሳተላይት) መካከለኛ ኢንደስትሪ ማቋቋም እንደሚሻል ይከራከራሉ። በየተወሰነው ትናንሽ ከተማ ትናንሽ የጎጆ ኢንደስትሪዎችን ብንቋቁም ይሻላል። ያቺ ለአካባቢው ነዋሪ የሥራ እድል ትፈጥራለች። አካባቢውም ለኢንደስትሪው የሚሆን ግብአት (ጥሬ እቃና የሰው ኃይል) በመስጠት ይደግፋል። ስለዚህ መደጋገፍ ይኖራል፡ ፡ ለትንንሽ መንደሮችና ከተሞች እንዲሁም ለገበሬዎች ትንሽ ትንሽ እየሰጡ ከተሠራ እነሱ እያደጉ ይመጡና በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ራሳቸውን ወደ ትላልቅ ኢንደስትሪዎች ማሳደግ ይችላሉ ባዮች ናቸው።

ይሄ የኢንደስትሪያላዜሽን ትራንስፎርሜሽን ወይም የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ጉዳይ “ዋነኛ” ሆኖ መውጣቱ በአቶ መለስ ብዙም የማይደገፍ አካሄድ መሆኑና አፈጻጸሙም ላይ ልዩነት መኖሩ ይታወቃል። የትራንስፎርሜሽኑ ምሶሶ ኢንደስትሪ መሆኑ በመርህ ደረጃ ተቀባይነት ቢኖረውም በኢንደስትሪ ዞን አመሠራረት ፖሊሲ ዙሪያ አሁን ያለው የኢህአዴግ አመራር ለሁለት ተከፍሏል። የኢንዱስትሪ ዞኖቹ የት የት አካባቢ ነው መቋቋም ያለባቸው መጠናቸውና አገልግሎታቸው እንዴት ይሆናል የፋይናንስ ድጋፉንስ ከየት ያገኛሉ በየትኞቹ የምርት ዓይነቶች ላይ ማተኮር አለባቸው እነዚህ ሁሉ ኢህአዴጎቹን ያስማሙ አልሆኑም። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ኢንደስትሪያል ዞን (ፓርክ) ላይ ማተኮር አለብን ባዮች ናቸው። የሆነ አካባቢ ትልቅ ቦታ ተከልሎ የተንጣለለ መሬት ይሰጣል። ገንዘብ ይቀርባል። ባንኩ ታክሱ ሁሉ ነገር እዚያው ይጠናቀቃል። ልክ ሞጆ ላይ ለቻይኖቹ እንደሆነው ትልቅ ኢንደስትሪ ዞን ማለት ነው። እዚህኛው ላይ ጥያቄ የሚያነሱት አመራሮች እንደዚያ ያለ ትልቅ ዞን ሲቋቋም የአገር ባለሀብቶች አቅሙ አይኖራቸውም። እንደዚያ ያለ ካፒታል የሚኖራቸው የውጭ ኩባንያዎች ስለሆኑ አገር ቤት ያለው ባለሀብት እየቀነሰ ይመጣል። ያ ደግሞ እንደ ኬንያና መሰል አገሮች ኢንቨስትመንቱን የሚቆጣጠሩት የውጭ ኢንቨስተሮች ይሆናሉ። ይህ አገሪቱን አሳልፎ ለውጭ ባለሀብቶች የመክፈት ስለሆነ የኒዮ ሊብራሎች አስተሳሰብ ነው። ይህ ከኢህአዴግ መርህ፣ ከመለስ አስተምህሮ ጋር ይቃረናል። ስለዚህ እናንተ ካላሾች በራዦች

ትራንስፎርሜሽን አብይ ዓላማው ገጠሬን ወደ ከተማ መለወጥ ግብርናን ወደ ኢንደስትሪ መቀየር ኤክስፖርት ላይ የተመሠረተ ምርት በማፍራት የአገሪቱን ገቢና የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል የሚለው ሲናገሩት ቢጣፍጥም አብረው ሊሄዱ የሚችሉ የአመራርና የአስተዳደር ብቃት በቦታው አልተገኘም። የግል ባለሀብቱም ሚናው በግልጽ አልተመለከተም። አንደኛ ይህንን ህልም ሊደግፍ የሚችለው የግል ባለሀብቱ የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ የሚችልበት የብድርም ሆነ የፋይናንስ ምንጭ የለም። የአገር ውስጥ ባንኮች እንዳይበድሩ በመመሪያ ታስረዋል። እያንዳንዱ ባንክ የሚያበድረውን ብድር 27% ቦንድ እንዲገዛ ይገደዳል። ይህ ማለት ለግል ባለሀብቱ ሊያበድር ከሚችለው ገንዘብ ለቦንዱ ይከፍላል ማለት ነው። ስለዚህ ባንኮች ብዙ ባበደሩ ቁጥር ክፍያቸው እየመጨረ ይሄዳል፡፡ በመካከሉ ባለሀብቱ ገንዘብ አያገኝም። ለዚሁ ተብለው የተቋቋሙት እንደ ልማት ባንክ ያሉት የመንግሥት አበዳሪዎችም ቢሆኑ የባንኩ ኃላፊ ሰሞኑን እንደገለጹት ከሆነ መስፈርቱ ቀላል አይደለም። ለተመረጡ ዘርፎች ያውም ተበዳሪዎች ቢያንስ 30 ከመቶ የማዋጣት ኃላፊነት ይኖርባቸዋል። ከውጭ ባለሀብቶች ይልቅ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር ሲስተያይ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ከባንኩ ብድር የማግኘት ተጠቃሚነታቸው ከመቶ ፐርሰንት ወደ 75 በመቶ እየወረደ መምጣቱም ተገልጿል። ይህም እያደገ ሄዶ ወደፊት አብዛኛውን የባንኩን ብድር የውጭ ባለሀብቶች ጠቅልለው ሊወስዱ የሚችሉበት አቅጣጫ ይታያል። ሌሎቹ ደግሞ ሲከራከሩ የፋይናንስ ምንጫችንን ከውጭ ቢሆን አፈላልገን እናገኛለን። ለዚህም መፍትሔ የተለያዩ የፋይናንስ ምንጮችን አፈላልጎ ማግኘት ነው እንጂ እንዲሁ በር ዘግቶ መቀመጥ አያዋጣንም ባዮች ናቸው። የቦንድ ሽያጩ ነገር የመጣው እዚህጋ ይመስላል።።

መለስ ቢኖሩ ቦንዱ አይኖርም! መለስ እየሞቱ ነው! የመለስ ሌጋሲ አስጠባቂዎቹ አመራሮች እነ አቶ በረከት እና አባይ ፀሐዬ ቦንዱን በጥብቅ ተቃውመውታል። የቦንዱ ሽያጭ የፓርቲው ዶክመንት ከሚፈቅደው ውጭ አገሪቱን ለውጭ ኃይሎች በርግዶ መስጠት ነው። ለትላልቅ ፕሮጀክቶቻችን የአገር ውስጥ የፋይናንስ አማራጮችን ገና ተጠቅመንና ፈልገን አልጨረስንም። በኒዮ ሊብራሎች ኃይልና ግፊት ነው እዚህ ውስጥ የገባነው ብለው ያምናሉ። ቦንዱ ከኢህአዴግ እምነት ውጭ የተደረገ ፣ ሁሉንም ነገር ከፍቶ የመስጠት ኢኮኖሚውን ለውጭ ኃይላት የመክፈት የመጀመሪያው ዝንባሌና ምዕራፍ ነው። ነገ መለስ ተሟግቶ ያቆየውን ቴሌ ይሸጥ፣ ባንኮች ለውጭ ባለሀብቶች ባለቤትነት ክፍት ይሆኑ...የሚለው ክርክር ጅማሬ ነው ባዮች ናቸው። የእነዚህ ከፍተኛ አመራሮች ምሬት ስናይ ምናልባትም ወደፊት “ቦንድና ሉአላዊነት በኢትዮጵያ” የሚል መጽሐፍ በክፍፍል አፈንግጦ በሚወጣ ሌላ ባለሥልጣን እናነብ ይሆናል። ምክንያቱም ጨዋታውና መወነጃጀሉ ሁሉ እንደ ኢትዮ ኤርትራ ወቅት ክፍፍል ከላሽና ተቸካይ መባባልን እያመጣ ነው። ሌሎች ተንበርካኪ ይሏቸው የነበሩ ባለሥልጣናት አሁን ደግሞ በተራቸው ተንበርካኪ የሚባሉበት ሁኔታ የተፈጠረ ይመስላል። የክፍፍሉን ደረጃ አስገራሚ የሚያደርገው ሌላው ነገር ደግሞ የቦንዱ ሽያጭ ውሳኔ የተወሰነበትና ለህዝብ ይፋ የተደረገበት መንገድ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃ/ማርያም (ከአማካሪያቸው አቶ አርከበ ጋር) ቦንድ ሽያጭ የመግባቱን ውሳኔ ሲወስኑ የኢህአዴግን ሥራ አስፈጻሚ አልተነጋገረበትም። በመጀመሪያ በሚኒስትሮች ም/ቤት ተወሰነ። ከዚያ ወደ ፓርላማ ሄደ። ከፓርላማውም በፓርላማው ጠቅላላ (በአዳራሹ) ሳይሆን በኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ብቻ ነው የታየው።

ይህን የሰሙት የፓርቲው የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ተቆጡ። እነ ኃ/ማርያም ሥራ አስፈጻሚውን ሳታስፈቅዱ ለምን ገባችሁበት ተብለው ሲጠየቁ ፍርጥም ያለ ምላሽ ሰጡ። 1ኛ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሊነጋገር የሚገባበት ጉዳይ አይደለም። ሁለተኛ የመንግሥት ሚኒስትሮችና ፓርላማው ተነጋግሮበት ወስኗል። 3ኛ በዚያ ላይ የሚኒስትር ም/ቤት አባላትም ውስጥ ቢሆን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት አሉ። ሁሉም የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚዎች የሚኒስትሮች ም/ቤት አባል ባይሆኑም ከሞላ ጎደል ሁሉም ሚኒስትሮች ግን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት ናቸው። የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት 60 ሲሆኑ የሚንስትሮች ም/ቤት አባላት ደግሞ 30 ናቸው። እዚህ ላይ አቶ ኃ/ማርያም ሥር የተጠለሉ የፓርቲው አንጃዎች (ከአቶ መለስ የተማሩትን) ጨዋታውን በሚገባ አውቀውታል። እንዲያውም ይባስ ብለው እንዴ ምን ማለት ነው? ምንስ ቢሆን እኛን እንዴት አታምኑንም? እዚያ ቦታ ስታስቀምጡን ከድርጅታችን ውጭ እንዴት ልንወስን እንችላለን በማለት ተቆጡ። ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ሆነና እነዚያም እንዲሁ ይተዋወቃሉና ውስጣቸው እያረረ በሉ ላሁኑ ይሁን አሉ። እንደዚህ ዓይነት ነገር ግን ለወደፊቱ መደገም የለበትም ይህ ቀላል ውሳኔ አይደለም የድርጅቱን መርሆ የታላቁ መሪያችንን አስተምህሮ የሚቃቀረን ነው አባሎቻችንን ማረጋጋት ይኖርብናል ዓይነት ነገር ብለው ሂስ አስውጠው እንዳይደገም ማስጠንቃቂያ ሰጡ። ለዚህም ይመስላል አቶ ሱፍያን ወዲያው አደባባይ ወጡና ስለቦንዱ ስለሶቭሪን ቦንዱ መግለጫ ሰጡ። “ሶቭሪን ቦንድ መሸጥ ማለት የኢኮኖሚ ፖሊሲያችንን ቀይረናል ማለት አይደለም። ለሚቀጥለው ሶስትና አራት ዓመት ሌላ የቦንድ ሽያጭ አናወጣም” ብለው ተናገሩ። እዚህ ላይ ፖሊሲ ስለመቀየር አለመቀየር መናገርን ምን አመጣው? ቦንዱንስ የማይሸጡት ለምንድነው? ያቀርብነው ቦንድ የ1 ቢሊዮን ቢሆንም ያገኘነው ግን 2.5 ቢሊዮን ለመግዛት ፈቃደኛ የሆነ ገበያ ነው። ያህን ያህል ገበያ ካገኙ፣ ቦንዱም ያን ያህል ተፈላጊ ከሆነ፣ ለሚቀጥሉት ዓመታት አንሸጥም ማለትን ምን አመጣው? አይለመደንም እንደማለት ይመስላል።

ምርጫ እና ድርጅታዊ ጉባኤ አሁን ያለው አመራር ይቀጥላል አቶ መለስ ያለሰብሳቢ በትነዋቸው የሄዱትና በዓይነ ቁራኛ የሚጠበባቁት የኢህአዴግ ባለሥልጣናት የሚተማመኑበት ድርጅት ሳያውቁት ፈርሷልና መክቶ የሚያድናቸው አይመስልም። ለምሳሌ እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲፈጠር ተቃዋሚዎቻቸውን ማራገፍ የሚችሉበት የፓርቲው መዋቅር አካል የሆነው አንዱ መሣሪያ ድርጅታዊ ጉባኤና ምርጫ ነው። በዚህ ወቅት መተማመን ስለጠፋና ከመበላላት መሰንበት ስለተመረጠ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ድርጅታዊ ጉባኤያቸው ከምርጫው በኋላ እንዲደረግ ተወስኗል። ባለፈው ከተደረገው 9ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ በኋላ 10ኛው መደረግ የነበረበት ከምርጫው በፊት ነበር። አሁን ግን መች እንደሚደረግ የት እንደሚደረግ ሳይገለጽ በእንጥልጥል እንዲቀጥሉ ተደርጓል። የኢህአዴግ ጉባኤ በየሁለት ዓመቱ ይደረጋል። ሁልጊዜ የሚደረገው ከምርጫው በፊት ነው። ድሮ ቢሆን አቶ መለስ ስላሉ በፊት ይሁን በኋላ ምንም ችግር አልነበረውም። ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት እሳቸው መሆናቸው ግልጽ ነበረ። አሁን ግን የኢህአዴግ ጉባኤ ከምርጫው በኋላ መደረጉ ከወዲሁ የሚገልጸው ነገር አለ። ይሄ ማለት አሁን ያለው አመራር እንዳለ ይቀጥላል ማለት ነው። ኃ/ማርያም ባሉበት ይጸናሉ። በርግጥ ፓርቲው ከፈለገ በጉባኤው የድርጅቱን ሊቀመንበር መቀየር ይችላል። ለጠቅላይ ሚንስትርነት ግን የሚወሰነው በምርጫ ውጤት ላይ ተመርኩዞ ነው። ኃ/ማርያም ምናልባት የፓርቲው ሊቀመንበር ላይሆኑ ይችላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ግን እሳቸው ሆነው የመቀጠላቸው ሁኔታ በግልጽ እየታየ ነው። አቶ ኃ/ማርያም (ወይም በሳቸው የተጠለሉት) አሁን ሊቀመበርነቱንም ጠቅላይ ሚኒስትርነቱንም ተጠቅመው እየሠሩ ነው። ይህ ማለት ግን ሥልጣን ወደ ድርጅቱ ሊሄድ አይችልም ማለት አይደለም። ለምሳሌ በአቶ መለስ ጊዜ ከክፍፍሉ በፊት ድርጅቱን ይመሩ የነበሩት አቶ ተወልደ ነበሩ። መንግሥቱን መለስ፣ ድርጅቱን ተወልደ ሲመሩ ድርጅቱ ከፍተኛ ሥልጣን እንደነበረው ይታወቃል። ወደ ኋላው ላይ ግን በክፍፍሉ ጊዜ፣ ያ ችግር ማምጣቱን የተገነዘቡት አቶ መለስ፣ የድርጅቱን አቅም አሽመድምደው፣ የመንግሥቱን መዋቅር ለማጠናከር ሁለቱንም

ይህ ዓይነት ልዩነትና መቀበጣጠር የኖረው ሁሉም መሪያችን ነው ብለው የሚያከበሩት ሰው ባለመኖሩ ነው። ሁሉም የሚያከበሩት መሪ (ግለሰብና) ድርጅት የሌለበት ሁኔታ ነው የሚታየው። አንዱ ላንዱ ያለው አክብሮት ጤነኛ አይመስልም። መጥፎ ስሜትም እያሳደሩ ነው። ይህ ከኢኮኖሚ ወጥቶ የፖለቲካ ጉዳይ የማይሆንበት ምክንያት የለም። እነዚህ ሰዎች ልዩነታቸውን ምን ያህል በሰለጠነ መንገድ ይፈታሉ? ከዚህ ገፍተው የሞትና የሽረት ትንቅንቅ (የሰርቫይቫል) ቢያደርጉና ቢሞክሩ ሁሉም ነገር ሌላ መልክ ይኖረዋል። እነ አርከበ/ኃይለማይርም የቦንዱን ውሳኔ ለብቻቸው ሲወስኑ ምክንያት ነበራቸው። ለምሳሌ ከአቶ መለስ ራዕይ የተለየው የኢንደስትሪያል ዞኑ ፖሊሲ ጉዳይ ሁለቴ ተጥሏል። ቦንዱን በራሳቸው ከወሰኑ በኋላ ለፓርቲው ማስረዳት የመረጡት በዚህ ምክንያት ነው። ይህንም ብናቀርብ ይጥሉብናል። ሰለዚህ ለራሳችን ለምን አናደርገውም የሚል ብልጠት መኖሩ ተነግሯል። በሌላ በኩል ከአቶ መለስ ራዕይ ጋር በተቸከሉትና በቻልነው ፍጥነት ተጠዳድፈን ካፈጠጠብን ቀውስ እውንጣ በሚሉት አባላት መካከል ፍትጊያ ቢርኖም ችግሩ በአንድና በሁለት የመከፈል ሳይሆን ቢያንስ ወደ ሶስት የሚጠጋ ቡድን መፈጠሩም ይሰማል። በረከት አዲሱ አባይ ፀሐዬ የመለስ ሌጋሲ እናስጠብቅ ባዮች ሆነው አንድ ቡድን ናቸው። አርከበ ዋነኛው ሆኖ ኃይለማርያም ሱፍያን ተክለወልድና ደብረፅዮን ደግሞ ሌላኛው ቡድን ሲሆኑ የማሻሻያ ለውጥ ያስፈልጋል ባዮች ናቸው። ጄኔራል የተባሉት እነ ሳሞራ የመለስ ራዕይ ከሚለው ውጭ ጉዳዩ ብዙም ስለማይገባቸው አገሪቱን በሥልጣን እያሳደረ ነው የሚባለው ሠራዊታቸው ከማንኛቸው ጋር እንደሚቆም ለመገመት ሳያዳግት አልቀረም። ገና እጅ ያልሰጡት እነወይዘሮ አዜብና ቀሪዎቹ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚዎች ከሠራዊቱ ጋር ማንዣበባቸው ይሰማል።

ጠቅልሎ መያዛቸው ይታወሳል። መለስ ያ አደጋ በትክክል ገብቶታቸው አስተካክለዋል። አሁን ግን ኃ/ማርያም መለስን አይደሉም። ስለዚህ ኃ/ ማርያምን ወይም በሳቸው የተጠለሉትን ለመካለከል የተገደበ ሥልጣን የመስጠት ሙከራ ሊኖር ይችላል።

ህወሓት ምን ያስባል? አሁን ያሉት ህወሓቶች ምን እንደሚያስቡ ለማወቅ በዚያ ደረጃ ማሰብ የሚችል ሰው ከመካከላቸው አለ ብሎ ማመንን ይጠይቃል። አሁን ቀላል የሚሆነው አንድ ለናቱ ጭንቅላታቸው የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊ ምን አስበው ነበር ማለቱ ይሻላል። ምክንያቱም አሁን ያለውን ህወሓት እንደገና ጠፍጥፈው የሠሩት እሳቸው ናቸው። ስለዚህ ስላሁኑ ህወሃቶች ስናወራ ስለ አቶ መለስ እያወራን መሆኑን እያሰብን ነው። ህወሓቶች አሁን ያላቸው ሥልጣን እንዳይጠፋ ይሰጋሉ። እንደ አስተሳሰባቸው በቁጥርም ጠባብ በመሆናቸው የባለብዙ ቁጥር ህዝብና ድርጅት ውክልና ሁሌም ያባንናቸዋል። ስለዚህ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ የሚሰጡት ሰው ከኦሮሞው ወይም ከአማራው እንዲሆን አይፈልጉም። ኦህዴድ ያው ኦነግነት አለበት ብለው ይጠረጥራሉ። አማራውም ላይ ግልጽ የሆነ የጥርጣሬና የጠላትነት ስሜት አላቸው። ሌሎቹም የድርጅት ቢሆኑ አንዳቸው ላንዳቸው ይጠባበቃሉ። ስለዚህ ማንም ሰው ከደቡብ የመጣ ሰው ላይ የጠነከረ ፍቅርም ሆነ የመረረ ጥላቻ እንደሌለው ያውቃሉ። ደቡብ የመገንጠል ጥያቄ የለውም። በኢትዮጵያዊነቱም ላይ ጥያቄ አያነሳም። በዚያ ላይ 53 የተለያዩ ብሔረሰቦች የሚኖሩበት ጥሩ የፌደራሊዝም አስኳል ነው። የክልሉ ቋንቋም አማርኛ ስለሆነ ጥሩ ነው። አቶ መለስ ይህን በማሰብ ነው ከደቡብ የተወሰኑ ሰዎች መርጠው ከዚያ ውስጥ ነው ኃ/ለማርያን ያሰለጠኑት። እንደሚባለው በሚኒስትርነት ሥልጣን አንድ አስር ሰዎች ከደቡብ ለአቶ መለስ ቀርበው ነበር። ከእነዚያ ውስጥ ነው ኃ/ማርያም የተመረጡት። ችሎታ ያለው ታማኝ የሆነ አምጡልኝና ላሰልጥን ብለው አሰልጠነዋቸዋል ይባላል። አቶ መለስ ከሥጣልን ወርደርው በኃ/ማርያም አማካይነት ሊመሩ ህልም ነበራቸው። ሞት ቀደማቸው። አቶ ኃ/ማርያምም መቸም ሰው ከሆኑ ያቺን ቂም ሳይቋጥሩ አይቀሩም። የመለስን ሌጋሲን ክደው ከባላንጣቸው ከአቶ አርከበ ጋር ሽር ጉድ ማለታቸው የት እንደሚያደርሳቸው ግን ይታያል።

ሁለተኛውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ የመቅረጽ ሽኩቻ በሚኒስትሮች ም/ቤት በኩል ያለው ዝግጅት የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ከመነጋገሩ በፊት አስቀድሞ የተጀመረ ነው። ካለፈው ጁላይ 2013 ጀምሮ ዝግጅት ሲደረግበት እንደነበር ይታወቃል። ለምሳሌ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በጁላይ 2013 ላይ ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፍሮሜሽን እቅድ እንዲቀርጽ መታዘዙ በወቅቱ ተዘግቧል። ይሄ ማምን ማለት ነው? አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ከአማካሪዎቻቸው ጋር ካቢኔያቸውን የመሰረቱት ወይም “የተመሠረተላቸው” ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ ሹመት ከሰጧቸው ሰዎች መካከል አቶ መኮንን ማንያዘዋል ይገኙበታል። አቶ መኮንን በአቶ መለስ ጊዜ ለረዥም ዓመታት በከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ላይ ቆይተዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው ከማገልገላቸውም በላይ የመጀመሪያውን የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን ማሰናዳታቸው ተነግሯል። እንደ መለስ ራዕይ ተደርጎ የተገለጸው እቅድ እሳቸው ያዘጋጁት መሆኑ ነው። አቶ መኮንን በቀድሞ የደርግ መንግሥት አንስቶ በፕላን ጽ/ቤት....የቆየ የረጅም ጊዜ የሥራ ልምድ አላቸው። የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ አባል ባለመሆናቸው ከፓርቲው ይልቅ ከመንግሥት አካላት ጋር ግንኙነታቸው የጠበቀ ነው። የድርጅት አባል ሳይሆኑ በሥልጣን ላይ ከቀሩት ጥቂት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት መካከል እንደ አቶ ተቀዳ ዓለሙ፣ ኃይሌ አሰግዴ ከመሳሰሉት ውስጥ አሁን ሥልጣን ላይ የሚገኙት እሳቸው ብቻ ናቸው። ሌሎቹ

ከአቶ መለስ ሞት ጋር ሄደዋል። ስለሆነም አቶ መኮንን የፓርቲና የመንግሥት ሥልጣንን በማራራቅ የተካኑት አቶ መለስ ዜናዊ ካቀረቧቸው ሰዎች አንዱ ነበሩ። አሁንም በፓርቲውና በመንግሥት መካከል ልዩነት ፈጣሪ ሆኖ በተገኘው የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ ከፍተኛውን ድርሻ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ኃላፊነት ተመልሶ የተሰጣቸው ይመስላል። ከአቶ መለስ ሞት በኋላ አዲስ የተቋቋመው ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል። ኮሚሽኑ ደግሞ ቀጣዩን የዕድትና ትራንስሮሜሽን እቅድን እንዲቀርጽ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ታዟል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ለራሱ ተጠሪ የሆነ የፕላን ኮሚሽን እንዲያቋቋም መደረጉ በፖሊሲ አማካሪነት ኃ/ማርያምን የከበቧቸውን የአቶ መለስ ቱባ ቱባ ባለሥልጣናት ለመከላከል ይሆን የሚል ግምት ማሳደሩ አይቀርም። ምክንያቱም አማካሪዎቹ የፓርቲ እንጂ የመንግሥትነት ሥልጣን የላቸውም።

ፕላን ያስፈልገናል ብለው ተነሱ። ለዚህም ኃላፊነት አቶ መኮንን ማን ያዘዋልንን መርጠው የአምስት ዓመት የልማትና የትራንስፎርሜሽን ፕላን እንዲዘጋጅ አዘዟቸው። አቶ መኮንን ቢሯቸውን ዘግተው ሶስት ወር ያህል ከቀመጡ በኋላ የአገሪቱ መነጋገሪያ የሆነውን ፕላን ይዘው ወጡ። አቶ መለስ ዜናዊ እሱን ተቀብለውና ቀባብተው የአገሪቱ ፕላን አድርገው በይፋ አወጁ። ባለ ራዕይ ያሰኛቸው ይህ ፕላን መሆኑ ይገመታል። መቸም የአቶ መኮንን ማንያዘዋል ራዕይ አይባልም።

ለመሆኑ የ5 ዓመት የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሀሳብ እንዴት መጣ?

ስለትራንስፍሮሜሽኑ አወጣጥ ሌሎች ደግሞ የተለየ አመለካከት አላቸው። የአቶ ኤርምያስን አስተያየት ያንብቡት።

የእቅዱ ሀሳብ ተጸንሶ የተወለደው በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘመኑ 2010 ነው። በ2010 የተደረገውን ምርጫ ማሸነፉን ከልቡ ያመነው ወይም በፈለገው ሁኔታ በመጠናቀቁ የተደሰተው ኢህዴግ መሪ የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ያመጡት ሀሳብ ነው። አቶ መለስ የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶቻቸውን ድል ነስተው ሲደላደሉ ካሁን በኋላ እዚህም እዚያም ቁጥ ቁጥ የሆነ ፕላን ሳይሆን ሁለገብና አብይ (ግራንድ) የሆነ

አቶ መኮንን በቀድሞው የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርና በኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር በተለያዩ ኃላፊነቶችና በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ አገልግለዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በዴቨሎፕመንት ማኔጅመንት ሲያገኙ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተቀበሉት ደግሞ በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ ነው፡፡

አሁን ታዲይ ሁለተኛውን ልማትና ትራንስፎርሜሽን ለመቅረጽ ምን እየተደረገ ነው? አቶ ኃ/ርያም የተሰየሙበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ ቤት አቶ መኮንን ማንያዘዋልን ከሾመ በኋላ አዲስ የተቋቋመው ብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን ራሱን በተቋም ደረጃ እንዲያዋቅር ተደርጓል። በተለይ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ወደ ገጽ 6

አቶ መለስ ለዚህም ኃላፊነት አቶ መኮንን ማን ያዘዋልን መርጠው የአምስት ዓመት የልማትና የትራንስፎርሜሽን ፕላን እንዲዘጋጅ አዘዟቸው። አቶ መኮንን ቢሯቸውን ዘግተው ሶስት ወር ያህል ከተቀመጡ በኋላ የአገሪቱ መነጋገሪያ የሆነውን ፕላን ይዘው ወጡ። አቶ መለስ ዜናዊ እሱን ተቀብለውና ቀባብተው የአገሪቱ ፕላን አድርገው በይፋ አወጁ። ባለ ራዕይ ያሰኛቸው አንድም ይህ ፕላን መሆኑ ይገመታል። መቸም የአቶ መኮንን ማንያዘዋል ራዕይ አይባልም።


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ በሰሜን አሜሪካ በተለይም ዋሽንግተን ሜሪላንድና ቨርጂኒያ ነዋሪ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ከጁላይ 2002 ጀምሮ የሚታተም፣

Zethiopia Newspaper Editor - Dereje Desta

አዘጋጅ ደረጀ ደስታ

202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com dereje@zethiopia.com

"የደኸዩት ደኽይተዋል" ዓለም ባንክ ሰሞኑን የዓለም ባንክ ኢትዮጵያን አስመልከቶ አንድ ጥናት ይፋ ማድረጉ ሲዘገብ ሰንብቷል። ጃንዋሪ 21 ይፋ ያደረገው ሪፖርት እንደሚገልጸው ክ2002-2011 ባሉት ዓመታት በኢትዮጵያ ያለው የድህነት መጠን ከነበረበት 55 በመቶ ወደ 30 በመቶ መቀነሱን አመልክቷል። ይሁን እንጂ በአገሪቱ በአስከፊ ድህነት ውስጥ የሚገኙ 25 ሚሊዮን ያህል ኢትዮጵያውያን ወደ ተባባሰ ድህነት መግባታቸውን አስታውቋል። የሚሆኑ ኢትዮጵያውያንም በከፋ ድህነት ውስጥ እንደሚገኙ አስታውቋል። በባንኩ የአፍሪካ ቀጣና የድህነት ቅነሳና የኢኮኖሚ

የኢንደስትሪው... ከገጽ 3 ምርት ቁልቁል ወረደ እንጂ አልጨመረም። የዋጋ ንረት ሰማይ ወጣ። እንዲያውም አገሪቱ ስንዴ የምታስመጣ አገር ሆነች። የከተሞች ድህነት ከድህነት ወለል በታች ደረሰ። አርሶ አደሩ በማዳበሪያና ብድር እዳ ባሪያ ሆነ። ብዙ ቦታ በማዳበሪያ ምክንያት መሬቱ ተራቁቷል። እንዲያውም አንዳንድ ቦታ ከቀረበው ምርጥ ዘር የተመረተው ምርት ያንሳል። ገበሬ ባለችው የበሬ ግንባር በምታህል ቦታ ላይ እርሻን ማስፋፋት አልተቻለም። በዚህ የተነሳ ኢህዴጎች ጥያቄ ማቅረብ ጀመሩ። ለምንድነው ወደ ትላልቅ ሜካናይዜሽንና የመስኖ እርሻዎች የማንሄደው ሲባል አቶ መለስ አበዱ። እንዲያውም ባንድ ወቅት የጋምቤላና የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልሎች በደርግ ጊዜ በመስኖ

ማኔጅመንት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያዋ ሩት ቫርጋስ ሒል ለሪፖርተር እንደገለጹት እ.ኤ.አ. በ2005 ከነበሩት ድሆች ይልቅ እ.ኤ.አ. በ2011 የነበሩት ድሆች የበለጠ ደህይተዋል፡፡‹‹እጅግ ዝቅተኛ በሆነ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ደሃ ቤተሰቦች እ.ኤ.አ. ከ2005 ጀምሮ የኑሮ መሻሻል አላሳዩም፣ እንዲያውም አንዳንዶቹ በፊት ከነበሩበት በባሰ ድህነት ውስጥ ይገኛሉ፤›› በማለት የገለጹት ሩት፣ ከዓለም ድህነት መስመር ውጪ ያሉት 12 በመቶ ተጋላጮችም መልሰው ወደ ድህነት አዘቅት ውስጥ የመግባት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን አሳስበዋል፡፡

ብቻዋን ወደ ኢንደስትሪ ግንባታ ተሸጋግራ ነበር። ትግራይ የገጠር ልማት ፖሊሲን አልተከተለችም ። ይህን በማስረጃ ፤በ2010 ላይ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት መሠረት የመካከለኛና ትላልቅ ኢንደስትሪዎች ብዛት መመልከት ይቻላል። በአጠቃአላይ ትራንስፎርሜሽን አርሶ አደሩን ወደ ኢንደስትሪ ማሽጋገር ከገጠር ወደ ከተሜነት መለወጥ ጭምር ነው። የደቡብ የአማራና የኦሮሞ የ3ቱ 83% ህዝብ በገጠር ይኖራል። የትግራይ 81 % ደርሷል። የኢንደስትሪ ሽግግር የተማረ ሰው ኃይል ማፍራትን ይጠይቃል። ቢያንስ ኃይስኩል የደረሰ ማፍራት ያስፈልጋል። በዚህ ረገድ ትግራይ ከክልሉና ከአጠቃላይ ያገሪቱ ህዝብ ብዛት አንጻር ፍትሐዊ

የትምህርት ሽፋን

የገጠሩ ህዝብ ብዛት

ትግራይ አማራ ደቡብ ኦሮምያ

3.6 ሚሊዮን 15.7 ሚሊዮን 14.6 ሚሊዮን 25.7 ሚሊዮን

ተጠቃሚ ስለነበሩ እሱ ፕሮጀክት እንደገና ለምን አይንቀሳቀስልንም ማለት ጀመሩ። የቤንሻንጉል ፕሬዚዳንት የነበረው አቶ ያረጋል አቶ መለስን ለምንድነው ቤንሻንጉል ላይ ትላልቅ መስኖ የማናካሂደው ብሎ ሲጠይቁ ይሄ ኪራይ ሰብሳቢ አስተሳሰብ ነው ብሎ አቶ መለስ እንደጮሁባቸው እናስታውሳለን። አሁን ግን ስለትላልቅ መስኖ እየተወራ ነው። የልማትና ትራንስፎርሜሽን የሚባል ነገር ያኔ አይታወቅም። እሱ ኋላ ድንገት በግብታዊነት የተከሰተ ነገር ነው። የኢንደስትሪውም ነገር እንዲሁ ጨርሶ የሚታሰብ አልነበረም። እሱ ላይ ይልቅ በጣም የሚገርመው ነገር ሌሎቹ ክልሎች በሙሉ በጥቃቅን የእርሻ ሥራዎችና በገጠር ልማት ላይ ሲያተኩሩ ትግራይ ክልል ግን

የሚኖር አንድ ሰው በቀን 30 ሊትር ውሃ በ500 ሜትር ርቀት ውስጥ በገጠር የሚኖረው ደግሞ 15 ሊትር በ1.5 ኪሎሜርት ርቀት ውስጥ ማግኘት ሲችል ነው። በሠንጠረዡ የሚታየው በዚህ መሠረት የተሰላ ነው። የአገሪቷ ጠቅላላ ሽፋን በከተማ 92% ገጠር 41% በድምሩ 51% ነው። እነዚህ ለናሙናነት የቀረቡት የሚገልጹት ነገር ይኖራል። አንዳንዶች እንደሚከራከሩት በአብዛኛው ትግራይ ክልል ባዶ ቦታዎች ሰዎች የተፈናቁሉባቸው አካባቢዎች መታየታቸው አንድም የኢንዲስትሪ መስፋፋት ምልክቶች ናቸው። ምክንያቱም ኢንደስትሪ በውስን ቦታዎች እንጂ ሁሉም ቦታ ሊስፋፋ አይችልም። የገጠር ሰዎች አካባቢያቸውን እየተው ወደ ተሰሩላቸው ኢንደስትሪ አካባቢዎች ሥራ ፍለጋ ይሄዳሉ። የከተሞች እድገት ያንን ተክትሎ ይመጣል።

የመጠጥ ውሃ ሽፋን የአገሪቱ ከተማ 92 ገጠር 41 አማካ 51%

የ2ኛ ደረጃ ሽፋን የአገሪቱ አማካይ 16.4 % ነው 28%

ቴክኒክና ሙያ የአገሪቱ አማካይ 2.4% ነው።

ከተማ

4.2%

98%

58%

66%

15.9

2.5%

93%

44%

53%

94%

38%

44%

18.5% 15%

1.8%

ገጠር

አማካይ

92%

ያልሆነ ተጠቃሚነት ማግኘቷ ይታያል። አቶ መለስን ጠቅሰው ወ/ሮ አዜብም የገለጹት የትግራይ ኢንደስትሪ ራ ዕይም ከሜዳ የሚጣል አይደለም። መቸም በዚያ ላይ ይህ መረጃ የተገኘው 89 ገጾች ካሉት ከፌዴሬሽን ም/ቤት የበጀት ቀመር 20052009 ዶክመንት ነው። ሌሎችም እንዲሁ ከማዕካላዊ ስታትስቲክስ የተገኙ ናቸው። ሁሉም በራሱ በመንግሥት የተዘጋጀ ጥናት ነው። የኢንደስትሪው ትራንስፎርሜሽኑ የመጠጥ ውሃ ሽፋንም እንዲሁ ነው። ጤንነቱ ማህበራዊ ህይወቱ የተጠበቀ ትውልድ ለልማት የተጋ ይሆናል። ከመሠረት ልማት ግንባታዎችም መሠረታዊና ቀዳሚው ነው። የመጠጥ ውሃ ሽፋን ስሌቱ (ማለት) በከተማ

ሁለተኛ አብዛኛው የትግራይ አካባቢዎች የተፈጥሮ ጥሪታቸውን የጨረሱ በመሆናቸው ድንጋይ ላይ ውሃ እንደማፈሰስ ነው። በፎቅና ህንጻ የተደለሉት ሌሎች ከተሞች መሠረታዊ ከሆኑ የኢንደስትሪ መሰረቶች ወደ ኋላ ቀርተዋል። አቶ መለስና ጓዶቻቸው በእጃችን ያለ የአርሶ አደሩ ያለው መሬት ነው ይበሉ እንጂ በሌሌች ክልሎች ግን የአርሶአደሩን መሬት ቀምተው ሸጣዋል። መሬቱን የተቀማ አርሶ አደር ደግሞ የሌለውን መሬት የሚያለማው ከየት አምጥቶ ነው። መሬታቸውን ይዘው የተቀመጡትም በማዳበሪያ እዳ ብድር ታስረዋል። እነዚህን ሁሉ ነገሮች ማየት መጪውን የኢትዮጵያ እጣ ፈንታ አመዛዝኖ ለማቀድና ፍትሃዊነት ለማረጋገጥ ይረዳሉ። ዝምብሎ ማጣጣል ይጥላል።

አቶ መለስ ዜና በሞቱ ማግስት አካባቢ ስለባለቤታቸው ራዕይ የተጠየቁት ወ/ሮ አዜብ አንድ መግለጫ ሰጥተው ነበር። አቶ መለስ ሞት ባይቀድማቸው ኖሮ ትግራይን በአምስት ዓመት ውስጥ የኢንደስትሪ መዲና ለማድረግ ልዩ እቅድ እንደነበራቸው ተናግረዋል። በሌላም በኩል ወ/ሮ አዜብ አሁን ድረስ በእሳቸው አመራር ስር ስለሚገኘው የኤፈርት የንግድና የኢንደስትሪ ድርጅቶች ወይንም የኤፈርትን የ2011/2005 አንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸም አስመልክተው ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸው እነዚህ ነጥቦች ይገኙበታል። •

ኤፈርት ባሳለፍነው ዓመት ከ376 ሚሊዮን በላይ የትርፍ ግብር ለመንግሥት ገቢ አድርጓል።

በዚህ ዓመት 16.57 ቢሊዮን ብር ምርትንና አገልግሎት ወደ ገበያ ያቀርባል።

መሶበ ሲምንቶ አሁን ከነበረበት በሶስት እጥፍ ያድጋል። ምርቱም በአምስት እጥፍ ያድጋል።

ትእምት 17 ሺ ሠራተኛ ቀጥሮ ያሠራል።

እያንዳንዱ ኩባንያ ከአንድሺ በላይ ሠራተኛ አለው።

ሱር አሁን በያዘው ፕሮጀከት ከአስርሺ በላይ ሠራተኛ ለማስተፍቅ እቅድ አለው።

5

ርዕሰ አንቀጽ

የአገር ፖለቲካን አስመልክቶ “ምን አዲስ ነገር አለ?” መባባል የተለመደ ነው። መንግሥትም ተቃዋሚም አይረባምና እግዚአብሔር የሚያመጣውን መጠበቅ ይበጃል ማለትም አለ። ያለኛ ምንም መዳኛ የላችሁምና አብራችሁን ዝለቁ የሚያስብል ጉራም አለ። ወይ ጉድ እኔኮ ምንም አልሰማሁም መንግሥት እንደዚህ ጭራቅ ነው እንዴ ብሎ ገና ከእንቅልፉ የሚነቃም አልጠፋም። ልማቱን አጧጥፏልና ፎቅ መንገድ ሠርቶልናልና አዲስ አበባን አታውቋትም ማለትም ይሰማል። እየመጣን ነውና ታግሳችሁ ጠብቁን የሚል ነገርም ከበስተ ሰሜን አለ። እንዴ ህዝቡ ምን ያድርግ ህዝቡኮ ብሎ ብሎ አቃተው የሚሉም አሉ። እንደሁልጊዜው አሁንስ በቅቶታል አልቆለታል የሚሉም አሉ። ቢሆንም እኛ ውሾች ገዢው ግመል በተባልንበት አገር እኛ እየጮህን ግመሉ ጉዞውን ቀጥሏል። በመሆኑም የሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አሁን ያሉት ገዢዎች እንዲቀጥሉ የሚያስችል የወግ ሥነሥርዓት በምርጫ መልክ ይካሄዳል።እንደወትሮው ሁሉ በምርጫው አዲስ ውጤት እንደማይጠበቅ እየታወቀ ወግ ነውና ምርጫው ይካሄዳል። ምርጫውን ዴሞክራሲያዊና አጓጊ የሚያደርግ ምንም ነገር ባይኖርበትም ቦርድ ተቋቁሞለት፣ ህግ ወጥቶለት፣ ታዛቢ ተመድቦለት፣ የምርጫ ክልል ተከልሎ እጩ ተደልድሎ የሚታወቀው ውጤት ይቆጠራል። ሴል ላይ እንደዋለ ሸቀጥ 99.9 ከመቶ መቀመጫ እየተባለ አፍ ያመጣው ቁጥር ይጠራል። አገር በጊዜ፣ አገር በገንዘብ፣ አገር በገዛ ፖለቲካውና የወደፊት ተስፋው የሚያፌዝበት ክስተት፣ ለወራት ያህል ሌት ተቀን ይለፈፋል። የምርጫውን ምርጫነት ከልቡ አምኖ የሚቀበል አንድም ትውልድ በሌለበት አገር ማን ማንን ፈርቶ እንደሚያደርገው ማሰቡ ያስገርማል። ጥንቅር ብሎ ቢቀር የሚቆጣ የሚከፋ ያለ ይመስል በዚህ ሁሉ ኪሳራ መደረጉ፣ ምን ዓይነት መንግሥትና ምን ዓይነት ህዝብ ምን ዓይነት አገር ነው ማስባሉ አይቀርም። ከዚያም አልፎ መንግሥት ምርጫውን ፈርቶታል ሲባል መደመጡ ህዝቡም ይሄ ምርጫ ወዲያ አልፎልን በተገላገልን በሚል የፍርሃት ምጥ ውስጥ መማቀቁ ሲታይ ምነው ዛሬውኑ አድርገው ቢገላገሉት ያስብላል። ሂደቱም ውጤቱም ያልተወደደ ምርጫ ምን ያደርጋል? ከዚህ የምርጫ ሂደት ይገኛል የሚል ጥቅም ቢኖር መንግሥትን ለመናገሪያ፣ ስለበደሉ ለመከራከሪያ፣ ምክንያትና ሽፋን ይሰጣል ተብሎ ሊሆን ይችላል። ወይም እንዲሁ ምርጫውን እየተለማመዱ ቢቆዩ የመንግሥት ወንበዴ የህዝብ ነጋዴ መሆኑ ቀርቶ መንግሥት ለአገሩ ህዝብ ለክብሩ መቆም ሲጀምር ጥሩ መሣሪያ ይሆናል ተብሎም ይታሰባል። ምርጫ ጠቃሚ ነገር ነው። አማራጭ ይሰጣል፣ ሥልጣን ይገድባል፣ ለውጥ ያመጣል አገር ያረጋጋል። እንዲህ እንዲሆን ግን ምርጫው ትክክለኛ ምርጫ መሆን ይኖርበታል። ትክክለኛ ምርጫ በራሱ ሥርዓት ነው። ያን ሥርዓት ደግሞ ከሁሉ ቀድሞ የሚያመጣው የሚያረጋግጠው ህዝብ ነው። የትኛውም መንግሥት በባህርይው አምባገነን በመሆኑ ምርጫን አይፈቅድም። ምርጫ ማለት ህዝብ አስገድዶ መንግሥት ተገዶ የሚፈጽመው ነገር ነው። የትም አገር ያለ መንግሥት እንደሆነ እንኳን የምርጫ ሥርዓትን ከመሠረቱ ሀ ብሎ ለመንገባት ይቅርና ለዘመናት የቆየውን የምርጫ ሥርዓት እንኳ ቢችል ለማፍረስ ካልሆነም ከማጭበርበር አይመለስም። ስለዚህ ትክክለኛውን የምርጫ ሥርዓት የሚያመጣው ህዝብ እንጂ መንግሥት አይደለም። በእኛም አገር መፍትሔው ይህ ነው። ህዝቡም መንግስትም በዚህ ምርጫ ፈርተዋል ማለቱ ግን ትንሽ ያጫውታል። የመንግሥቱን ፍርሃት እናቆየውና የህዝቡን እንመርምረው። ህዝቡ “አሁንስ ይሄ ምርጫ ወዲያ አልፎልኝ ሰላሜን ባገኘሁ” ብሎ የሚጨነቅ ህዝብ መሆኑ እውነት ይሆን? ሆኖ ከሆነ ይገርማል። እርግጥ ነው በዘንድሮ ምርጫ አሸንፌ 99 ከመቶ ወንበር ጠቀለልኩልህ እየተባለ የሚቀለድበት ህዝብ፣ ትክክለኛ ምርጫን መቸም አይወልድም። እኔን ብቻ ምረጥ ሲባል ዝም የሚል ህዝብ፣ እንደምንም ብሎ የመረጠው ድምጽ እንኳ ሲገለበጥበት ሰዎች ሲገደሉ ሲታሰሩበት ዝም የሚል ህዝብ፣ በገዛ መብቱ የቀለደ በፍርሃቱ የነገደ ነውና አይታዘንለትም። 2005 ላይ ተገድሏልና 2015 ላይ ይፍራ አይባልም። ህዝብና ፍርሃት የሚዋህዱበት ጨዋታ ደስ አይልም። እንዴት ነው ነገሩ ህዝብ ማለትኮ ራሱን በራሱ ማስተዳደር የሚችል ነገር ነው። ህዝብ ማለትኮ ሲነካ ሲደለል ሲቀለድበት ዝም የማይል ህዝብ ነው። ህዝብ ማለት ኃያል ነው። ስለራሱ እንኳ መናገር የማይችል አይደለም። ግን ሆኖ እንደምናየው በአገራችን ስለ ህዝቡ የሚናገሩት ሌሎች ናቸው። “ህዝብ ያውቃል” መሆኑ ቀርቶ ስለህዝብ የሚያውቁለት ሌሎች ናቸው። ህዝብ የሚናቀው በገዥው ህዝብ ብቻ ሳይሆን በተቃዋሚ ጠበቆቹ አማካይነት ነው። ህዝብን እሹሩሩ በሉት፣ አትናገሩት፣ አክብሩት አንግሡት ይባላል። ምን ያድርግ ህዝቡ ስለራሱ መናገር አይችልምና እኛ እንናገርለት ማለት ጥሩ ነው። ይህን ብለው የሞቱ የታሰሩም አሁንም በመታሰር ላይ በመሰደድ ላይ ያሉ ብዙ ናቸው። ከህዝብ ህዝብነትና ቁጥር አንጻር ሲታዩ ግን እዚህ ግባ የማይባሉ ጥቂቶች ናቸው። ለውጥ የሚመጣው በጥቂቶች ተነሳሽነት ሞትና መሥዋዕትነት መሆኑ ግልጽ ቢሆንም አንዳንዱ ንቁ ህዝብ ፣ እየሞቱ እየታሰሩለት ያሉ ሰዎች መኖራቸውን ፈጥኖ ይገነዘባል። እንደ አገሬ ህዝብ 20 እና 30 ዓመት ዝምብሎ አይታዘብም። ህዝብ ውለታ ያውቃል። ዝም ብሎ ከንፈር እየመጠጠ ስለባርነቱ እያላገጠ እንደ አጋሰስ አይመርሰመስም። የተጨቆነ የተጠማ የተሰደደ ህዝብ ማምሻም እድሜ ነው ብሎ ራሱን አይደልልም። ለውጥ ሊመጣ የሚችለው በመንግሥት ሳይሆን በህዝብ ነው። ጥቂት ሰዎችና መሪዎች ህዝብን አነሳስተውና መርተው ለለውጥ እንደሚያዘጋጁት የታወቀ ነው። ህዝብን ማነሳሳት አስከትሎም ለለውጥ ማብቃት የመሪዎችና የድርጅቶች ኃላፊነት ችሎታና ብቃት መሆኑም እርግጥ ነው። ስለተቃዋሚ ድርጅቶች ድክመት መሽቶ እስኪነጋ አውርተናል። መሪ ስለመጥፋቱም ብዙ ብዙ ብለናል። ያ እንደተጠበቀ ሆኖ የህዝቡስ ህዝብነት፣ የህዝቡስ ተከታይነት፣ የህዝቡስ ተመሪነት ምን ያህል ተወርቷል? ወይስ ጭቆናም አፈናም በደልም የለም። ህዝብ ምንም አልሆነም፣ ዝምብለን ነው የምናወራው? ይህን አጥርቶ ማወቅ ይረዳናል። ለነገሩ የተቃዋሚዎች የተቃውሞ መሠረት መንግሥት ብቻ አይደለም። የዴሞክራሲ ሥርዓት፣ ፍትህ፣ ድንቁርና፣ ድህነት፣ ጎሰኝነትና አድሎኝነት፣ የግለሰቦች ነጻነትና የመሳሰሉት የመርህ ጥያቄዎች የተቃውሞና የለውጥ ፈላጊዎች መሠረት ናቸው። በደንብ ከፈተሹት አንዳንዴም በነዚህ ችግሮች አፈጣጠር ላይ ህዝብም የራሱን ድርሻ የሚጫወትበት ቦታ አለው። መንግሥትን ብቻ ሳይሆን ህዝብንም መቃወም የለውጥ ፈላጊ ግለሰቦች ድርሻ ሆኖ መገኘቱም ለዚህ ነው። አንዳንድ ጊዜም ህዝብ ታይቶ መንግሥት ይሰጠዋል የሚለውን ተረት ማድመጡ ጠቃሚ የሚሆንበት አጋጣሚም አለ። አምባገነን መንግሥት እንዳለ ሁሉ አምባገነንነት በህዝቡም አድሮ ልናየው እንችላለን። መንግሥት ትችትን እንደማይፈልግ ሁሉ ህዝቡም መነካትን መተቸትን ላይፈቅድ ይችላል። በፍርሃት ታጅሎ የኖረ እውነት ተገልጦ ሲነገር መንግሥት ያስራል ህዝብ ያድማል። ህዝባችን ዝምብሎ ይከፋፈላል። ስለሚከፋፍሉት አካላት ብዙ ውግዘት ብዙ ነቀፋ አሰምተናል። አንድ ኮሜቴ እንኳ መዳኘት አቅቶት በየፖለቲካ ድርጅቱ በየቤተ እምነቱ እዚህም እዚያም እንክሽ ፍርክሽ ማለቱ ለምንድነው? ከብት ይመስል ያም ይሄም የሚነዳው ምንሆኖ ነው? ዳሩ ምን ያደርጋል፣ ህዝብ አምላክ ሆኖ ያለ አቅሙ ይመለካል። ህዝብን እንዲህ ልትል የቻልክበትን ምክንያት አቅርብ የማለት ርሃርሄ (ዴሞክራሲ) የማይታሰብ ሲሆን ቀድሞ ነገርስ ህዝቡን እንዴት ደፈረ ተብሎ በሰከንድ ብልጭታ መደፍጠጥም ያለ ነው። እያጨበጨበ እየቀለበ የሚያደለባቸው ደናቁርት አምባገነኖቹ ያዘው ፍለጠው ቁረጠው ባሉት ቁጥር ለገዛ ጥቅሙ እንኳ ተቆጭተው የሚጩኽለትን ሰዎች በጭካኔ አድሞ ይቀረጣጥፋቸዋል። ማን በኔ ማን ለኔ ቆመ ብሎ አያስተውልም። ሆይ ሆይታ ይወዳል። ህዝብኮ ሥርዓት ተቋም ርትዕ ፍትዕ ነው እንጂ ቁጥር አይደለም። ህዝብኮ አገር ነው። አገር ደግሞ የሚኖሩበት የሚኮሩበት እንጂ ተጠይፈው የሚሸሹት እዚህስ ከምኖር ባህር ውቂያኖሱ ይብላኝ የሚሉበት ምድረ በዳ አይደለም። የአገር ጥራት በህዝብ ጥራት ያስታውቃል። በጥቂቶች ጀግንነትና ታሪክ እየነገደ ክብርን ከራሱ ሳይሆን ከታሪክ እየተዋሰ የሚኖር ህዝብ ባይፈጠር ይሻለዋል። ህዝብን አትናገሩት የሚለው ቁጣ መሠረቱ ይህ ባዶነት ነው። ስለዚህ አምባገነኑ ህዝቤ ያይን ሞራውን ገልጦ የሚያሳየው ምናምን ቸልሶበት ከተኛ ከፈዘዘበት የሚያነቃው ነገር ያስፈልገዋል ብሎ መጸለይ ያስፈልግ ይሆናል። መፍራት የለመደ ያገኘውን ነገር ሁሉ ይፈራል። በአገራችን ፍርሃት ባህል ከመሆኑ ብዛት ህዝብ ለህዝብ እንኳ መፈራራት መኖሩ እየተሰማ ነው። ካሉት ስጋቶች አንዱ ህዝብ ህዝብን ፈርቶ ማደሩ ነው። ያኛው ህዝብ ይቀየማል ብሎ ይህኛው ህዝብ ፈርቶ ያድራል። እንጨራረሳለን እንጂ እንነጋገራለን የሚል እምነት ስለሌለው ሀቅን አቅፎ ይተኛል።ሁሉም የመነጨው ግን ከህዝብ ነው። ጎሰኛው የራሱ ቢጤ ከሌለው ብቻውን ጎሰኛ አይሆንም። ጎሰኛ ባለበት ቦታ ሁሉ ጎሰኞች አሉ። ጎሰኞች ደግሞ መቶም ሺም ሚሊዮንም ሊሆኑ ይችላሉ። ህዝብ የሚወጣቸው ቁጥራቸው ስንት ሲደርስ ነው የሚለውን ቆጥሮ ያሰላው ባይኖርም ችግሩ ግን ከግለሰቦች በላይ መሆኑ ግልጽ ነው። ስለሆነም ነው በጎሳ እና በሀይማኖት የተከፋፈለ ህዝብ መፈራራቱ መጠባበቁ አይቀርም። የእነገሌ መንግሥት የወረደ እንደሁ እንተላለቃለን የሚል ህዝብ፣ ወይም የሚቀጥለው ማነው እያለ ሲፈራ የሚኖር ከሆነ እሱ ራሱ አስፈሪ ነው። ስጋቱ ተገቢ ቢሆንም ማንትስ የወረደ እንደሆነ “ማን ይተካዋል?” ብሎ መጨነቁ ዘለዓለማዊ ሲሆን ያሳፍራል። በተለይ ተቃዋሚ ድርጅቶችን ጨምሮ ይህ ሲነገር መሰማቱ የኃላፊነት መሆኑ ቢታመንም እንዲህ እየተባለ ያለመፍትሔ ዘመን ሲያስቆጥር ያሳፍራል። ምድነው ዝምብሎ ማን ይተካዋል ብሎ ነገር! እንዴ እኔ እኮ ህዝብ ነኝ “እኔ እተካዋለኋ!” ወይም “እኔ እፈጥረዋለኋ” እማይባለው ለምንድነው? ፥መገዳደልን ምን አመጣው? ምንም ጎሰኛ ቢሆን፣ እኔ ወንድሜን እገድላለሁ እንዴ የኢየሱስ የአላህ ሰው አይደለሁ! ለምን አይባልም? አንተ ትበቃለህ፣ አንቺ ትመሪያለሽ፣ እማይባለሁ እንኳን ከአገር ከመንደር ሰው ጠፍቶ ነው? ከጠፋ ከጠፋ እኔ አለሁ የሚል በራስ መተማመን የት ገብቷል? ወይስ ተተኪ ህዝብና ድርጅት ከቱንዚያና ከቡርኪናፋሶ ልናስመጣ ነው? እርግጥ ነው እነዚህ ነቀዞችና የበታችነት ስሜት ያወራቸው ደናቁርት የቻሉትን እኛ ምን ያቅተናል ብሎ ነገር ማቅለል መልሶ ያቀል ይሆናል። ግን ዶክተሮቹንም የህግ ባለሙያዎቹም የፖለቲካ ሳይንቲስቶቹንም ኢኮኖሚስቶቹን የጦር ባለሟሎቹን ጋዜጠኞቹንም አርቲስቶቹንም ወጣቶቹንም ሴቶቹንም ሁሉ ይዘን እነዚህን ምናምንቴዎች መተካት እንዴት ያቅተናል? ለዚህስ ዝግጅት ምን ያህል ጊዜ ያስፈልገናል? ችግሩ የሁላችንም ነው። ከዚህ መውጫ ብቸኛው መፍትሄ ያኛውን ምርጫ ብንንቀው የራሳችንን ምርጫ የምናካሄድበት ዝግጅት መፍጠር ነው። ከሁሉ በላይ የየራሳችን ንዑስ ህዝብ እየሆነ ቀስፎ ከያዘን “የኛ እና የነሱ” ከሚያሰኝን ተላቀን ትልቁን ህዝብ መሆን ስንችል ነው። ካለበለዚያ አሁንም መልሶ የጠሉት ይደርሳል የፈሩት ይነግሳል መሆኑ አይቀርም! ወይም ህዝብ ይጮኻል ግመሎቹ....


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ ቤትዎ እንዲላክልዎ ከፈለጉ ከዚህ ቅጽ ጋር የዓመት ደምበኝነት ሞልተው 40 ዶላር ይላኩልን

6

Yes I want to subscribe Zethiopia Newspaper Name-----------------------------------------------Address----------------------------------------------City................................................................................ State...................Zipcode............................................ Phone,...........................................................................

Zethiopia Newspaper

Email................................................................................. Starting date...................................................................

For only $40.00

Ze Ethiopia Corp.

P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com dereje@zethiopia.com

ምርጫ ቦርድ

ሌላኛው “ቁጥር መቀቀያ” 1.

መዋቅራዊ ችግሮች

1.1 ገዥው መደብ በምርጫ 97 ውጤት ምክንያት ከወሰዳቸው እርምጃዎች አንዱ የምርጫ ቦርድን እለታዊ እንቅስቃሴ መቆጣጠር ነው። ከምርጫ 97 በፊት ስማዊም ቢሆን እንደ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን፣ እንባ ጠባቂ፣ ምርጫ ቦርድ ...ወዘተ በቀጥታ ተጠሪነታቸው ለፓርላማ ነበር። ይህ በአዋጅ ደረጃ ያልተቀየረ ቢሆንም በተዘዋዋሪ መንገድ በኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት አማካይነት በአስፈጻሚው እጅ ወድቋል። የኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት በተቋቋመበት አዋጅ መሠረት የሁሉም ተቋማት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊዎች ተጠሪነት ለኮሙዪኒኬሽን ጽ/ቤት እንዲሆን ተደርጓል። በዚህም መሠረት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው የሚሾመውና የሚሻረው በጽ/ቤቱ ነው። የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው በየተቋማቱ የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ በመሆኑ በተቋማት ውስጥ ያለው ሥልጣን ሁሉንም የሚያስከነዳ ነው። ይህ ኃላፊ በየዕለቱ ከኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ትዕዛዝ እየተቀበለ ለተቋማት ያስተላልፋል። በዚህ የኮሙዩኒኬሽን አዋጅ መሠረት የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት መዋቅር የተደራጀው በዚሁ ጽ/ቤት ነው እያንዳንዷን የምርጫ ቦርዱን እንቅስቃሴ ሪፖርት የማድረግ ግዴት አለበት። ከአስፈጻሚው አካል ትዕዛዝ እየተቀበለ ተፈጻሚ ያደርጋል። 1.2 በምርጫ ቦርድ ስም የሚመደቡት የምርጫ አስፈጻሚዎች የሚመለመሉት በየደረጃው ባሉ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ካድሬዎች ነው። በወረዳና በቀበሌ ደረጃ ምርጫውን የሚያስፈጽሙ ሰዎች በማዕከል (በሁሉም የብሔር ድርጅቶች ጽ/ቤት እንዲመለመሉ ያደርጋል። በቀጠና (ምርጫ ጣቢያ) ደረጃ ያሉት በቀበሌ ካድሬዎች ይመለመላሉ። በማስከተልም ሁሉም በደህንነት መዋቅሩ እንዲያልፉ ይደረጋል። በዚህም መሠረት ህዝቡን የመመዝገብ ሥራ የሚሠሩት፣ የምርጫ ገለጻ የሚሰጡትና ከምርጫ ኮሮች ጋር የሚንቀሳቀሱት እነዚህ የኢህአዴግ ካድሬዎች ናቸው 1.3 የምርጫ ማስፈጸሚያ ጣቢያዎች ብዛት የሚወሰነው በምርጫ ባርድ ሳይሆን በየደረጃው ባሉ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ኃላፊዎች ነው። የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች በበዙ ቁጥር ገዥው መደብ የማታለል እድሉ ይጨምራል። በመጀመሪያ እስከ 30-40ሺ የሚጠጉ ምርጫ ጣቢያው ውስጥ ተቃዋሚዎች ታዛቢ መመደብ አይችሉም። የህዝብ ታዛቢ ተብለው የተመረጡትም ከውስጥ የለበሱት ካናቴራ የንብ አርማ ያለበት ነው። ከሁሉም በላይ እጅግ በጣም አስደንጋጭና ምርጫ የማይቻልበት ደረጃ ያደረሰው “የመንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አዋጅ” የሚጫወተው ሚና ነው። በአዋጁ መሠረት መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት (መያድ) ሆኖ የገቢውን ከ10 ከመቶ በላይ ከውጭ የሚያገኝ ከሆነ በማንኛውም የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ (ምርጫን ጨምሮ) መሳተፍ አይችልም። ከመንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ኤጄንሲ ድህረ ገጽ ባገኘሁት መረጃ መሰረት በ2006 (2014) ብቻ ከ3000 በላይ መያዶች ተመዝግበዋል። ከእነዚህ ውስጥ 400 ብቻ የሚሆኑት

የመታዘብ መብት አላቸው። ከ2600 በላይ የሚሆኑት በምንም መንገድ በዲሞክራሲ እንቅስቃሴ ውስጥ አይሳተፉም። በምርጫ ሂደቱም አያሳተፉም። የተቀሩት 400 ያህሉም ቢሆን የወጣት፣ ሴት፣ኮሮችና ፎረሞች ኢህአዴግ ያደራጃቸው ሌላኛው ክንፎች ናቸው። 1.4 በምርጫ ጣቢያዎች የሚመደቡ ፖሊሶች፣ ሚሊሺያና ሌሎች የፀጥታ ኃይሎች በየደረጃው ባለው የኢህአዴግ መዋቅር ነው። የ እነዚህ ታጣቂዎች የጎላ ሚና የሚጫወቱት ምርጫ ኮሮጆ በመለዋወጥ ሂደት ላይ ሲሆን ከዚህም በተጨማሪ የተቃዋሚ ታዛቢዎች ላይ የመዛትና የማስፈራራት ሚና አላቸው። በገጠሩ አካባቢ የሚገኙት ታጣቂ የሚሊሻ ኃይሎች ከፖሊሶቹ በተለየ በግልጽ የኢህ አዴግ ድርጅቶች አባል እንዲሆኑ ይደረጋል። 1.5 ምርጫ ቦርድ መዘገብኳቸው፣መረጡ፣ ይህን ያህል ድምጽ አገኙ ብሎ የሚያቀርባቸውን ተመዝጋቢዎች/መራጮች ድምር የሚያገኘው በየደረጃው ባሉ የኢህአዴግ መዋቅሮች አማካኝነት መሆኑ ግልጽ ነው።፡ምርጫ ቦርድ እያንዳንዱ የኢትዮጵያ ገጠር የመድረስ አቅም ስለሌለው ከፓርቲው የመጣውን በአንድ በኩል በራሱ የደረሰበትን በሌላ በኩል ሳያጣጥም ሪፖርት ያደርጋል። ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው በፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም ምርጫ በሚል በ2003 ዓ.ም የታተመውና ስለ2002 ምርጫ የሚያነሳውን መመልከት ተገቢ ይሆናል።

አቶ ኤምርያስ ለገሠ የቀድሞ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳይ ም/ሚ/ር እና የመመለስ ትሩፋቶች የሚል መጽሐፍ ጸሐፊ ናቸው። (ፎቶ ኢሳት)

ፕሮፌሰር መስፍን በመጽሐፋቸው ገጽ 157-158 ላይ አስገራሚ ውጤቶች ያሏቸውን 25 የፓርላማ አባላት በስም፣ በምርጫ ክልልና በድምጽ ብዛት በናሙናነት ለማሳየት ሞክረዋል። ከ25 ውስጥ የአራቱን ብቻ ለይተን እንመልከት (ከታች ያለውን ሠንጠረዥ ይመልከቱ)

የተመራጭ ስም አሊ ኡመር ኢላሌ አብዱልፈታ አብዱላሂ ዴቅ ሼህ አብዲ ኡስማን አለ መላ

ቦታ ጅጅጋ ጅጅጋ

የድምጽ ብዛት 213288 246782

ፊቅ ፊልቱ

135484 368211

1.5.1 ለምርጫ የተመዘገቡ በምርጫ ቦርድ ዶክመንት መሠረት በምርጫው የተመዘገቡ ሰዎች አንድ ቦታ 31 926520 ይላል። ሌላ ቦታ ደግሞ 29170867 ይላል። ልዩነቱ 2755653 ያህል ይሆናል። ፕሮፈሰር እውነቱ የትኛው ነው ብለው ይጠይቃሉ። እናም እውነቱ የትኛው ነው? 1.5.2 የህዝብ አጠቃላይ ብዛትና የተመዝጋቢ ብዛት በ2002 የተመዘገቡትን ሰዎች በክልሉ ስለሚኖረው አጠቃላይ ህዝብ ብዛት ሲታይ ሌላ አስቂኝ ነገር ያጋጥማል። ለምሳሌ በድሬዳዋ ከአጠቃላይ ህዝቡ 80.2፣ በአፋር 71.1% እንዲሁም በጋምቤላ 59% ይላል። እንግዲህ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ መረጃ መሠረት ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች የሚሆኑት 45.2% ያህል ይሆናሉ። ስለዚህ ከላይ የተጠቀሱት ክልሎች እነዚህን ህጻናት መዝግበዋል። ወይ እቤታቸው ቁጭ ብለው ዳታውን ሞልተውታል ወይ ከጎረቤት አገሮች ተበድረዋል። አሊያም ፕሮፌሰር እንደሚጠረጥሩት ልዩ ፍጥሮች መዝግበዋል። 1.5.3 አስገራሚ የምርጫ ውጤቶች

በምርጫ ህጉ መሠረት አንድ የምርጫ ክልል የሚዋቀረው አጠቃላይ የህዝብ ብዛቱ እስከ 100ሺ ያለው ከሆነ ነው። ከዚህ ውስጥ ለመራጭነት የሚመዘገበው ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ እስከ 50 በመቶ ቢገመትና ሙሉ ለሙሉ ተመዝግቧል ተብሎ ቢታሰብ ተመዝጋቢው ህዝብ 50ሺ ይሆናል። ታዲያ እነ ኡስማን ከ300ሺ በላይ ህዝብ የመረጣቸው ከየት የመጣ ህዝብ ነው? 1.1.1 ተመዝግቦ ባለመምረጥ በመለስ ትሩፋቶች መጽሐፍ የአዲስ አበባ ህዝብ ለሶስት ተከታታይ ምርጫዎች ኢህአዴግን እንደማይፈልግ ለማሳየት ተሞክሯል። የፕሮፌሰር መስፍንን መጽሐፍ በጥሞና ለተመለከተ ይህ ህዝብ በ2002 አቋሙን ሳይቀይር መቀጠሉን ያስተውላል። ለዚህ እንዲረዳ ከአዲስ አበባ ህዝብ ለምርጫ ተመዝገበ የተባለው 1289369 ቢሆንም ወጥቶ የመረጠው 564982 ያህል ነው። ይህ ማለት 56.2% የአዲስ አበባ ህዝብ ወጥቶ አልመረጠም። ወጥቶ መረጠ ከተባለው 43.8% ውስጥ ግማሽ ያህሉ ኢህዴግን መረጠ ቢባል እንኳን፣ 750000 ያህሉ ኢህአዴግን እንደማይፈልግ ያመላክታል።

ሁለተኛውን የትራንስፎርሜሽን... ከገጽ 4 መምሪያ እንዳለ ወደ ብሔራዊው ፕላን ኮሚሽን በመውሰድ በመደራጀት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መንደፍ መጀመሩም ተመልክቷል። እቅዱ ገና ሳይጠናቀቅ ግን በፓርቲው ባለሥልጣናት በኩል እክል የገጠመው መስሏል። በፓርቲው ውስጥ ያሉት ሰዎች በመንግሥትነት ያስቀመጧቸው ጓዶቻቸው የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ከፓርቲው መርህ ውጭ እየሆነ ነው በማለት ጭቅጭቅ ማሰማት ጀምረዋል። ፖሊሲውን ማን ይቅረጽ የሚል ጥያቄው የሥልጣን መገለጫ እየመሰለ ሲያነታርክም ሰንብቷል። ለዚህ ንትርክ እልባት ለመስጠት ይመስላል የሁለተኛውን የትንራንስፎርሜሽን እቅድ በሚመለከት መንግሥት ያቋቋመው የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን አልበቃ ብሎ ሌላ ተደራቢ ኮሚቴ መቋቋሙን ሰሞኑን ሰምተናል። ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ጃንዋሪ1 8/2015 እትሙ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገውን ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ዘግቧል። እንደጋዜጣው ዘገባ የአምስት ዓመቱ ዕቅድ በስምንት ዘርፎችና ኮሚቴዎች ተከፍሎ እየተዘጋጀ ነው። እቅዱ እንደ ቀድሞው በጠቅላይ ሚኒስትሩ (አቶ መለስ) ራዕይና ትእዛዝ ብቻ መቀረጹና መዘጋጀቱ ቀርቶ አሁን ሁሉም ባለስልጣናት የየራሳቸውን ራዕይ የሚያኖሩበት እየመሰለ ነው። በተቋም ደረጃ በብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን

ደረጃ እንኳ እንዲዘጋጅ አልተፈለገም። በመሆኑም ፕላኑ በሚቀጥሉት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሆኖ የኮሚቴ ሰብሳቢዎች ተመድበውለታል። •

የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የዕቃዎችና የአገልግሎቶች ኤክስፖርት-የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ የግብርናና የገጠር ትራንስፎርሜሽን- የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በረከት ሰምዖን -

የኢንዱስትሪ ልማትና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥበጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ

ዘመናዊ የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ዘርፍ አቅም ግንባታን- በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ዓባይ ፀሐዬ

የሰው ሀብት ካፒታል ማሳደግና የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታን - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን

ወሳኝ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችና የማስፈጸም አቅም ግንባታ- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና

የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል •

ልማታዊ መልካም አስተዳደር፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ከም ንጩ በማድረቅ ተወዳዳሪነትን ማጎልበት ወ/ሮ አስቴር ማሞ ዴሞክራሲን ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባት መፍጠርና የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራን የመተለከተ- አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ

በእነዚህ ኮሚቴዎች የታቀደው አገራዊ ዕቅድ ውይይት ከተደረገበት በኋላ አገሪቱ ለአምስት ዓመታት የምትመራበት ብሔራዊ ሰነድ እንደሚሆን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሁለተኛው የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የሚጠበቀው ምንድነው? -የአቶ መለስ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የታሰበውን መዋቅራዊ ለውጥ አላማምጣቱ በግልጽ እየተነገረ መሆኑ ይታወቃል። ሪፖተር ቀደም ሲል ስለ እቅዱ አፈጻጸም ጥናት ያደረጉና በጉዳዩ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊና አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ጋር ጭምር የተወያዩና በአማካሪነት የሠሩ ሁለት ጃፓናዊ ባለሙያዎችን ፕሮፌሰር

ኪኒቺ ኦህኖ እና ፕሮፌሰር ኢዙሚ ኦህኖን ጠቅሶ እንደዘገበው በትራንስፎርሜሽኑ ይፋ የተደረገው የኢንዱስትሪ ፖሊሲ የሚፈለገውን ለውጥ አላመጣም። ለኢንዱስትሪ የሚመች ምንም መዋቅር ቀድሞ ባለመዘርጋቱ ነው። ዕቅዶቹን ሊያስተገበሩ የሚችሉ ተቋማትና ባለሙያዎች በሚያስፈልገው መጠን አልተሟሉም። በወዲህም በኩል ብቁ የሆኑ ኢንዱስትሪዎች ባለመኖራቸው የታቀዱት የወጪ ንግድ ግቦች አልተሳኩም። መንግሥት በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ለውጥ ይመጣል ብሎ ተስፋ ካደረገባቸው መካከል ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች መምጣታቸው ዋናው ነው፡፡ የቻይና፣ የህንድ፣ የቱርክና የኮሪያ አምራቾችን ጨምሮ ከቅርብ ጊዜ በኋላ የጃፓን ትልልቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት ሊያደርጉ ማሰባቸው ለለውጡ ታሳቢ የተደረጉ ተስፋዎች ናቸው፡፡

ያለፈው እቅድ ተሳክቷል? አቶ መለስ የአገሪቱን አጠቃላይ ገቢ በእጥፍ እናሳድጋለን ብለው ነበር። አልተሳካም። ያኔ 37 ቢሊዮን አካባቢ ነበር አሁን 40 ቢሊዮን ነውአላጠፈም። እንደ ኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የአዲስ ዓመት ንግግር ከሆነ አልተሳካም። ፕሬዚዳንቱ በሰፕቴምበር 2014 በአራተኛው የህዝብ ተወካዮችና

የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አምስተኛ የሥራ ዘመን የመጀመሪያ የጋራ ስብሰባ ላይ ያደረጉት የመክፈቻ ንግግር ይህን አያረጋግጥም። የ እቅዱ መለያ ባህርያት ተደርገው ከተወሰዱት ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀከቶች መካከል ብቸኛው ተቀዋሚ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት (ፓርላማ) አባል ግርማ ሰይፉ ይህንን የ እቅዱን አለመሳካት ለፓርላማው አባላት የደረሰውን ሪፖርት አጣቅሰው ጽፈዋል። የጽሑፋቸው ፍሬ ነገር የአምስት ዓመቱን የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ያወጣው ኢህ አዴግ እቅዱን ማሳካት አልቻለም። ምክንያቱም ራሱ ያወጣውን እቅድ እንኳ ማሳካት የሚችል ድርጅት አይደለም በማለት የእቅዱን ውጤት አብጠልጥለውታል። የእቅዱን ዋና ዋና ትልሞች ለምሳሌ የአስፋልት መንገድ ሳይጨምር የገጠር ቀበሌዎችን ከዋና መንገድ ጋር የሚያገናኙ ከ71 ሺ ኪሎ ሜትር ክረምት ከበጋ የሚያገለግሉ መንገዶች ግንባታ አለመሳካቱን፣ 10 ሺ ሜጋ ዋት የሚደርስ የኢነርጂ ልማት ተግባራዊ አለመደረጉን፣ በማዳበሪያ ምርት ከፊል የሀገር ውስጥ ፍጆታን ይሸፈናል የተባለው አለመፈጸሙን ወዘተ እየጠቀሱ ነቅፈዋል። የ እቅዱ ዋነኛ ማጠንጠኛ የሆነው የኢንደስትሪ ሴክተሩንም አንስተው “የማኑፋክቸሪንግ ሴክተሩ የተጣለወን ሃያ በመቶ እድገት ለማሳካት የሚያስችል የግል ሴክተር ተነሳሽነት አይታይም፤ ቢመጣም ማነቆ ብዙ ነው፡፡” ብለዋል።


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

7

የቀድሞ በሐንጋሪ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ጓደኞቻቸው

ከ200ሺ ዶላር በላይ የሚገመት መጽሐፍትና ኮምፒውተሮችን ወደ ኢትዮጵያ ላኩ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ የቀድሞ በሐንጋሪ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችና ወዳጆቻቸው ከ220ሺ ዶላር በላይ የተገመተ የትምህርት መጻሕፍትና መርጃ መሳሪዎችን ወደ ኢትዮጵያ መላከቸውን ገለጹ። አስተባባሪዎቹ አቶ ፍቅረ ሥላሴ ጽጌና ዶ/ር ፀሐዩ ታደሰ ለዘኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደተናገሩት ወደ 22ሺ የሚጠጉ የመማሪያ

ዘርፍ የሚሸፍኑ መሆኑን አቶ ፍቅረሥላሴ ገልጸዋል። መጽሐፍቱ አስፈላጊነታቸውን መሠረት አድርጎ በተሰናዳ ዝርዝርና ከአንኮበር ወረዳ የትምህርት አስተዳደር እውቅና የተላኩ መሆኑንን አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል። አንድ ኮንቴየነር ሙሉ የሚደርሰውን ቁሳቁስና የመጓጓዣ ወጪው ወደ $14,040.00 ዶላር

ታዋቂው የሬጌ ድምጻዊ ቦብ ማርሌይ ሐውልት በአዲስ አበባ ሊቆም ነው መጽሐፍት ኮምፒውተሮችና ሶፍት ዌሮች የተላኩት በሰሜን ሸዋ አንኮበር አካባቢ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ነው። ይህንኑ ተግባር ሥራዬ ብሎ በሚያከናውነው በቡክ ፎር አፍሪካ አማካይነት የተላኩት የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችና የመማሪያ መጻሕፍቱ ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ሀይስኩል ላሉ ተማሪዎች የሚያገለግሉ ሲሆን የሳይንስ የሂሳብ የቋንቋ የኮምፒውተር ና የተለያዩ

የፈጀ መሆኑ ሲገለጽ 62 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ወጪውን አዋጥተው መሸፈናቸውን ዶ/ር ፀሐዩ ገልጸዋል። የተረፈውን ገንዘብ ለተመሳሳይ ፕሮጀክት ለማዋል እቅድ መኖሩንም አመልክተዋል። ለበጎ አድራጎቱ ሥራ ያነሳሳቸው በኢትዮጵያ የሚገኙት የትምህርት ቤት ጓደኛቸው ዶክተር ካሣሁን አሰፋ መሆናቸውን አቶ ፍቅረ ሥላሴ ተናግረዋል። “አንኮበር ያሉት ትምህርት ቤቶችን ለመርዳት

በሚሠራው በጎ ሥራ ተደስቼ እኛስ ምን እንድናደርግልህ ትፈልጋለህ ብዬ ጠየቅኩት ፟- መጻሕፍት ላኩልኝ” ሲል መለሰለኝ” ብለዋል፡፡ በተመሳሳይም ዶ/ር ፀሐዩ “ጓደኛችን ለብቻው የሚችለውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ስለተረዳን እኛስ ለምን የድርሻችንን አንረዳውም በሚል ተነሳስተናል” ብለዋል። በዚህ መሠረት በሜሪላንድ አቢሲኒያ ሬስቶራት የቀድሞ የሐንጋሪ

ተማሪዎችና ወዳጆቻቸው ጁላይ 27 በመሰባሰብ መምከራቸውና ገንዘብ ማሰበሳባቸውን ገልጸዋል። የሰቨን ኢሊቨን ባለቤቶች፣ የህክምና፣ የህግና በተለዩ የሥራና የሙያ ዘርፍ የተሰማሩት የቀድሞ ተማሪዎቹ ወደፊትም ተመሳሳይ የበጎ አድራጎት ሥራ ሊያከናውኑ እንደሚችሉ አስታውቀዋል። (ዘኢትዮጵያ)

ያስተውሉ

የኦባማ ኬር በሰጠው የኢንሹራንስ ማነጻጸሪያ(market place) በመጠቀም ማንኛውም የአሜሪካ ነዋሪ የጤና ሽፋን እንዲኖረው ያስገድዳል። እርስዎም ይህንን እድል ተጠቅመዉ እስከ ፌብሩዋሪ 15/2015 ካልተመዘገቡ በቅርቡ ስራ ላይ በዋለው የሃገሪቱ ህግ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ይጣልብዎታል:: ቅጣቱ የሚሰላው ዓመታዊ ግብርዎን (tax return) በሚያሰሩበት ወቅት ሲሆን በሰዓቱ ተመዝግበው ቢሆን ኖሮ ሊያገኙ የሚችሏቸውን በርካታ የቅናሽ እድልዎች በሙሉ ያሳጣዎታል::

ታዋቂው የሬጌ ድምጻዊ ቦብ ማርሌይ ሐውልት በአዲስ አበባ ሊቆም መሆኑን አስተባባሪዎቹ ገለጹ። የሐውልቱ ተከላ አስተባባሪዎች አዲስ አበባው ውስጥ ለታዲያስ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም እንደገለጹት ሐውልቱ ከዓመታት ቆይታ በኋላ ልክ በልደቱ ቀን የቦብ ማርሌይ ሙዚየም በኪንግስተን ጃማይካ ፌብሩዋሪ 6/2015 በአዲስ አበባ ይፋ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት እስካሁን ይደረጋል። በአርቲስት ብዙነህ ሳይሰራ ቆይቶ አሁን ሁኔታዎች ቀራጭነት የተሠራ ሐውልት እንዲመቻቹ መቻቸታቸውን አዲስ ኢምፔሪያል ሆቴል አካባቢ አርቲስት አዲስ አስረድቷል። ቦብ እንደሚተከል አርቲስት አዲስ ማርሊይ የንጉሠ ነገሥቱ ቀድማዊ ገሠሠ አስታውቋል። ከአስር ኃ/ሥላሴ አክባሪና በአለባበሱም ዓመት በፊት የቦብ ማርሌይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ 60ኛ ዓመት ልደት በአዲስ አበባ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የሚያዘወትር በተከበረበት እለት ሐውልቱ በዜማዎቹም የኢትዮጵያን ስም የሚሠራበትን ቦታ በመጠቆም ከቅድስናና ፍቅር ጋር አይይዞ ጭምር የመንግሥትን ፈቃደኝነት የሚጠራ በዓለም ዝናው የናኘ የገለጹት የቀድሞ ከንቲባ አቶ ድምጻዊ ነበር። አርከበ እቁባይ እንደነበሩም ተገልጿል። ይሁን እንጂ ሐውልቱ

በኢት. ለእግርኳስ ተጫዋቾች ሽያጭ አዲስ መማሪያ ወጣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በክለቦች ላይ የሚታየው የተጨዋቾች የዝውውር በፌዴሬሽኑ እውቅና ሊኖረው እንደሚገባና የዝውውር ጊዜውም ፌዴሬሽኑ ባስቀመጠው ቀን ብቻ ሊወሰን መንግስት ተጨዋቹ ከሚያገኘው ገቢ ግብር ማግኘት እንደሚገባ በአዲሱ መመሪያ ይገልጻል። ሰነዱ ከጥር 25 ቀን ጀምሮ ተግባራዊ እንዲሆነም ፌዴሬሽኑ ወስኗል። በሰነዱ ላይ በሰፈረው መረጃ መሰረት ክለቦች ልምድ ያላቸውን የውጭ አገራት ፕሮፌሽናል ተጨዋቾች ቁጥር ከሶስት ሊበልጥ አይገባም ይላል። ከዚህ ቀደም የኮንትራት ውላቸውን ያልጨረሱና በሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ክለቦች ሊያደርጉት ስለሚገባው አሰራር ፌዴሬሽኑ በቅርቡ መግለጫ ይሰጣለ ተብሎ ይጠበቃል። ኢዜአ

ይህ እንዳይሆን የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ማእከል በሜሪላንድ አጫጭር የትምህርት የምክርና የምዝገባ ፕሮግራሞችን ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ጋር በመተባበር አዘጋጅቷል በመሆኑም 8120 Fenton street, Silver Spring ,MD 20910 ቢሮ ቁጥር 201 (B) በአካል በመምጣት ወይንም ደግሞ በስልክ ቁጥሮች (240) 859 7805 / (240) 429 1215 ዛሬዉኑ በመደወል አስፈላጊውን ትብብር እንዲያገኙ በአክብሮት እንጋብዝዎታለን። ለምዝገባው የሚያስፈልግዎትን ቅድም ሁኔታ ያለ ስህተት እንዲያከናውኑ መረጃ በመስጠት የሚያግዙዎት ለዚሁ የተዘጋጁ ባለሙያዎች መኖራቸውን እንገልጻለን:: አስቀድመው በመደወል ለተመዘገቡት በተለይ ማክሰኞ ጃንዋሪ 27 ከ4:30-7:30 ሰዓት ምዝገባውን በአማርኛ ቋንቋ የሚያግዝዎት ወገንዎን ያገኛሉ።

የዓመት ደንበኛችን ይሁኑ ስለ ድጋፍዎ እናመሰግናለን ፎርሙን ዌብ ሳይታችን ላይ ያገኙታል www.zethiopia com

202-518-0245


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

8

Connect To Your Favorite Amharic Programs By Phone ከእነዚህ ሬዲዮ ጣቢያዎች የፈለጉትን ደውለው በስልክዎ መስማት ይችላሉ

Dial these US numbers from your mobile phone and listen to the following stations for free!

Admas Radio

712.432.8435

ESAT

712.432.7777

AWR Amharic

712.432.9970

Ethiopiawinet

832.225.5387

BBN Our Voice

857.232.0104

Fana FM Radio

712.432.9944

Bereka Broadcasting

712.432.8427

FM Addis 97.1

231.460.1971

Bilal Communication 712.432.6826

Helina Radio Las Vegas 712.432.8498

Dallas Ethiopian Community Radio

Hiber Radio Las Vegas 712.432.8451

DireTube Radio DW Amharic

712.432.8435 716.274.2515 712.432.2900

ETHIO Diaspora Radio 832.999.5222 Ethiopia Rise and Shine 857.232.0135

Calls only use mobile minutes. powered by

NOW ®

1334 9th Street NW, Washington, DC 20001

Tel 202.299.9703

712.432.6885

SBS Amharic

712.432.7701

VOA Afaan Oromo

213.992.4245

VOA Amharic

213.493.0122

VOA Tigrigna

213.493.0272

WENTC

213.992.4363

For more information, email: zradiophone@gmail.com

202 518 0245 የኢትዮጵያ ሬስቶራንትና ገበያ

Sheger 102.1 FM


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

አርበኞች- ግንቦት 7 ለ አንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ

ድርጅቶች፣ በምንም ዓይነት ሁኔታ በሀገርና በሕዝብ ደረጃ ትርጉም ያለው ሥራ በጋራ መስራት አይቻሉም’ የሚለውን፣ አስከፊ ተመክሮና አመለካካት ለመስበርም ጭምር ነው።” ብሏል።

ለኢትዮጰያ ህዝብ፣ ለመከላከያ ሰራዊቱና ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ አቀረበ።

<<ከትናናሽ ድርጅቶች ዙሪያ ከሚሽከረከሩ ሀሳቦችና ስሜቶች ለመውጣትና ሀገራዊና ሕዝባዊ የሆነውን ጉዳይ ለማስቀደም የወሰነ ማንኛውም ድርጅት፣ አርበኞችና ግንቦት7፣ እንደደረሱበት የውህደት ውሳኔ ፤ወይም በሌሎች በጋራ ሊያሰሩ በሚችሉ ስምምነቶች አብሮ ለመስራት መወሰን የማይችልበት ምንም ምክንያት አይታየንም።>>ብሏል ንቅናቄው።

(ከኢሳት የተገኘ ዜና) ንቅናቄው በግንቦት 7 እና በ አርበኞች ግንባር መካከል የተደረገውን ውህደት አስመልክቶስ በቅርቡ ባወጣው መግለጫ፤ << እኛ መዋሃድ መወሰናችንን ስንገልጽ፤ በተናጠል ከሚደረጉት – በጋራ የሚደረጉ የትግል ጥረቶች ውጤታማ ይሆናሉ በሚል ብቻ ሳይሆን፣፡”የተቃዋሚ

ንቅናቄው ለተቃዋሚ ድርጅቶች ባስተላለፈው መልእክት <<ዛሬ በአርበኞችና በግንቦት 7፣ የተጀመረው ጉዞ ውጤታማ በመሆን ሀገራዊና ታሪካዊ ትርጉም እንዲኖረው፣ ሌሎችም በተግባር የምትንቀሳቀሱ ተቃዋሚ ድርጅቶች፣ ወያኔን የማስወገድንና ብሎም ሀገር የማረጋጋቱን ሀላፊነት በጋራ

<<በወያኔ አድሎ ስርዓት የተንገፈገፈና ትግሉን ለመቀላቀል የቆረጠ ማንኛውም ዜጋ፣ የተገኘውን አጋጣሚ በመጠቀም ትግሉን መቀላቀል ይችላል>>ያለው አርበኞች-ግንቦት 7፤ <<የኢትዮያ ሕዝብ በአንድነት የተነሳ ቀን ደግሞ፣ የወያኔ ግብዓተ መሬት ይፈጸማል ብለን ከልብ እናምናለን።>> ሲል የመተባበርን አንድነት በአጽንኦት ገልጿል።

እንድንወጣ የሚያስችል መቀራረብ እንድናደርግ ፣ በውህደት በመሰረትነውበአርበኞች ግንቦት 7፣ ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ፣ ሥም፣ ጥሪያችንን እናቀርባለን።>> ብሏል። ንቅናቄው ለወታደራዊና የፖሊስ ሠራዊት አባላት ባስተላለፈው መልእክት ደግሞ፤<<የወያኔን ዘረኛና አምባገነን ቡድንን ዕድሜ ለማሳጠርና ሁላችንንም በእኩልነት የምታስተናግድ ሀገር እንድትኖር፣ የሰሞኑን ቆራጥ የዓየር ሃይል መኮንንኖች ያሳዩትን ዓርያነት በመከተልና በኤርትራ የሠራዊቱን እንቅስቃሴ ለመዘገብ በስፍራው የተገኘው የኢሳት ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን በተገኘው አጋጣሚና ሁኔታ በመጠቀም አይተሄው ለማታውቀው ውርደት፣ ክፋት፣ እንድታደርግ፣ በአርበኞች ግንቦት 7፣ በየቦታው የሚደረገውን ትግል እንድትቀላቀሉ የመከፋፈልና የመጋጨት አደጋ የዳረገህን እና ለአንድነትና ዴሞክራሲ፣ ንቅናቄ ሥም፣ በውህዱ ድርጅታችን ሥም፣ ጥሪያችንን ሀገርና ሕዝብን የማራከስና የመሸጥ ዕኩይ ጥሪያችንን እናቀርባለን።>> ሲል መግለጫውን እናቀርባለን።>>ብሏል። ተግባር የተጠናወተውን አገዛዝ ከነግብር ቋጭቷል። (ምንጭ ኢሳት) አበሮቹ ጠራርጎ ለማስወገድ በተጀመረው ንቅናቄው በመጨረሻም፦<<የተከበርከው የጋራ ትግል ውስጥ በቀጥታ እንድትሳተፍ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ፣በረጅም ታሪክህ አለያም በምትችለው ቀዳዳ ሁሉ ድጋፍ

የዲሲ ታክሲ..ከገጽ 3 እስከ ሳምንት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ ሊቀመንበር ሊንተን ታክሲ ነጂው ላይ በከፈተው ጦርነት የአሰራር ሥርዓቱን ባልጠበቀ ሁኔታ ሥብሰባዎችን ያደጋል። ውሳኔዎች ሲወስን አጀንዳዎችን እየደበቀ ተካራካሪ እንዳይኖረው ያደርጋል። ለሁሉ ነገር ውድ ገንዘብ ሲያስከፍል ይህ አልበቃ ብሎት ተጨማሪ 2ሺ ታክሲዎችን

በስምሪቱ ላይ ጨመረ። መጨመር ብቻ ሳይሆን ማንኛውም የዲሲን ታክሲ ለመንዳት ለሚፈልግ ሰው በ5 ቀናት ውስጥ ፈቃድ እንደሚሰጥ አስታወቀ። በዚህ ሁሉ ምክንያት የዲሲ ታክሲ አሽከርካሪዎች ገቢ በመቀነሱ ብዙ ተጨማሪ ሰዓት መስራት የግድ ሆነ። ለቤተሰብ የሚሰጠው ጊዜም መቀነስ ጀመረ። ከዚህም በተጨማሪ

በህጋዊ መንገድ ኢች ታግ - ታርጋቸውን በዲሜምቪ ያስቀመጡ የታክሲ ነጂዎችን ታርጋ አልሰጥም በማለት ተከራይ አደረጋቸው። ቀድሞ የኢንስፔክሽን ደህንነት ያለፈ መኪና የሚሰጠውን ጊዚያዊ ስቲከር ከለከለ። እነዚህ ሁሉ ጥቂቶቹ በደሎች ሲሆኑ በኪምስተር ዘገባ መሠረት 700 ያህል ታርጋ ለሰዎች የሰጡ መሆኑ

Skin & Laser Surgery Center

ንቅሳት እናጠፋለን GENERAL DERMATOLOGY ·

ACNE

·

WARTS

·

SCARS

·

KELOIDS

·

MELASMA

·

OTHERS

We will help you with your skin problems

COSMETIC PROCEDURES

TO OUR LOCATIONS:

·

LASER TATTOO REMOVAL

MCLEAN, VA

·

LASER HAIR REMOVAL

WOODBRIDGE, VA 703.492.4140

·

CHEMICAL PEELS

·

BOTOX

website http://bderm.com/

·

9

703.893.1114

FREE CONSULTATION WITH THIS AD

ሲታወቅ ለማን እንደሰጡ ምንም መረጃ አልተገኘም። ለካምፓኒዎች ሰጥቶ ካምፓኒዎች ለአዳዲስ ታክሲ ነጂዎች እያከራዩት እንደሆነ ይጠረጠራል።

የሜየር ግሬይ መሸነፍና የሊንተን መሻር ሜየር ግሬይ በወ/ሮ ባውዘር በምርጫ ሲሸነፍ ሰው ሁሉ አዲሷ ሜየር ኮሚሽነሩን እንደምትቀይር ቢያውቅም ኮሚሽነሩ ግን ትንሽ የምታቆየው መስሎት ነበር። ወደፊት እንደምናየው ከቦታ እንዲነሳ ሆነ። ኮሚሽነሩ ከመውጣቱ ከሁለት ወር ተኩል በፊት አንድ አፕ (applications) ለጠቅላላ ዲሲ ታክሲዎች አሰራለሁ፣ ለታክሲ ነጂዎች የጡረታ ማስከበር መብትና የጤና ዋስትና ኢንሹራንስ አመቻቻለሁ ሲል አወጀ። ይህ ሀሳብ መልካም ቢሆንም የታክሲ ካብ ኮሚሽን ሥራ አይደለም። የታክሲ ኮሚሽን ሥራ ደንብ ማስከበር ብቻ ነው በሚል ተቃውሞ ተነሳበት። ይህንንም አስመልክቶ በጠራው ህዝባዊ ስብሰባ አፕሌክሽኑን ሌላ አካል በነጻ አበርክቶልኛል ያለው ማንን እንደሆነ እንዲናገር ሲጠየቅ መናገር አልፈለገም። በአፕሊኬሽኑ ተጠቅሞ ሰው ያላነሳ ታክሲ በመጀመሪያው 200 ብር ይቀጣል፣ የደገመ ደግሞ ወደ 300 ቅጣቱ ከፍ ይልበታል የሚል ህግ አሰናድቶ ነበር። መጀመሪያ አፕሊኬሽኑን ሳይኖርህ ለምን ስለቅጣት ታስባለህ ሲባል መልስ ግን አላገኘም። ይህ በእንዲህ እንዳል በታክሲ ነጂዎች ዘንድ ኮሚሽነሩ አንድ አፕሊኬሽን ይሰራልናል፣ ከኡበር ጋርም እንድንወዳደር ያስችለናል በሚል ተስፋና ደስታ ሲንጸባረቅ ሰነበተ። ኮሚሽነሩ ባለፈው አራት ዓመት ታክሲ ነጂውን የሚጠቅም ምንም ነገር እንዳልሰራ የተረሳ ቢመስልም ከአፕሊኬሽኑ ጋር ምን እንደሚመጣ አለማወቅ ግን የዋህነት ነበር። በኮሚሽነሩ መሠረት እያንዳንዱ ታክሲ ነጂ ለአፕሊክሹን መጀመሪያ መቶ መቶ ብር መክፈል ሲኖርበት አፕሊክሼኑን የሚያስተዳድረው አካል ደግሞ ወርሃዊ ወይም ሳምንታዊውን የክፍያ ውል ይወስናል። ለጊዜው ማን እንደሚያስተዳደረውም የታወቀ ነገር የለም። ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሚሽነር ሊንተን ቀኑ ደርሶ ጃንዋሪ 7/20015 ተነስቷል። አዲሱ ሜየር ባውዘር ኤሪክ ሮጀርስ (Eric Rogers) የሚባል የዲፓርመትን ኦፍ ኮንሲሙየር ኤንድ ሪጉላቶሪ አፌር አስተዳዳሪ የነበረውን የ41 ዓመት ሰው ሾማለች።

አዲሱ ጊዚያዊ ኮሚሽነር ኤሪክ

FILLERS

ሮጀር ኤሪክ ሮጀርስ ቃለ ምልልስ ለማድረግ ተቃጥረን ለዚህ እትም አልደረሰም። ሆኖም የመጀመሪያው ስብሰባ ከታክሲ ነጂዎች ባደረገበት ወቅት እኔም ሌሎችም ታክሲ ነጂዎች ስለ ወደፊቱ አስተዳደር ጠይቀውት በሥራው ላይ ገና 9 ቀን በመቆየቴ ብዙ የማላውቀው ነገር አለ። “ዋናው ነገር የናንተ ንግድ በመሆኑ እናንተ ገንዘብ እንድትሰሩ የእኔ ሥራ ህግ ማስከበር ብቻ በመሆኑ እኔም ህጉን እንዳሰክብር አብረን እሰራለን። እናንተ ደግግሞ የከተማውን ነዋሪዎችና ጎብኚዎች ጥሩ አገልግሎት በመስጠት እንዳልወቀስ አግዙኝ ፣ እናንተም እርዱኝ እኔም እረዳችኋለሁ” ብሏል።

መደመደሚያ እስካሁ ባለፉት አራት ዓመታተ በአጭር በአጭሩ በኮሚሽኑና በታክሲ ኢንደስትሪው የሆነውን ገልጫለሁ። በታክሲ ነጂው በኩል የነበረው መፎካከር እንደማያገባው በዝምታ መቀመጥ ለማንም እንዳልጠቀመ ሁሉም ታክሲ ነጂ አይቶታል። በፌንቲ ጊዜ በታክሲ ነጂዎች ባለቤትነት ካምፓኒዎች ሲቋቋሙ ሁሉም ሳይሆን ብዙዎቹ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ይዘት ተከትለው በመቋቋማቸው በሁሉም ታክሲ ነጂ ላይ አንድ ላይ የመጣውን አንድ ላይ ለመከላከል አልተቻለም። አሁን ግን ችግሩ ስለታየ በተለይም ባለቤትነት አደጋ ላይ በመሆኑ ሁሉም ይተባበራል ለመብቱም ይከራከራል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። በቅርቡ ከአዲሱ ኮምሽነር ጋር በነበረው ስብሰባ የቲምስተር ታክሲ አባል ታክሲ ነጂዎች ተወካይ 2ሺ ታክሲ ነጂዎችን እወክላለሁ የሚል ትክክል ያልሆነ መረጃ ሲያቀርብ ሰምቻለሁ። የዚህም አደጋ ከዚህ በፊት የስሞል ቢዝነስ አሶስዬሽን ተወካዮች በየስብሰባው መጀመሪያ 3ሺ ታክሲ ነጂ እንወክላለን እያሉ በመናገራቸው ቼርማን ሊንተን የነሱን ቃል እየያዘ ነበር ታክሲ ነጂዎች ይደግፉኛል በማለት አግባብ ያልሆነ ነገር ለመፈጸም ያስቻለው። አሁንም ችግሩ የሁሉንም በር ስላንኳኳ፣ ትክክለኛ ተወካይ ማስቀመጥ፣ የባለቤትነትን መብት ማስከበር፣ ወጪ የሚቀነስበት መንገድ መፈለግ፣ የሁለት ሺ አስራ አምስት ዋነኛው አጀንዳችን ሊሆን ይገባል። አዲሱ ኮሚሽነርና አዲሱ የከንቲባ ቢሮ የምትፈልጉትን ሁሉ በጽሁፍ አስታውቁን ያሉትን አጋጣሚ መጠቀም ያስታውሳል። ጸሐፊውን በኢሜይል ለማግኘት - catchaleme@ g m a i l . c o m

የሌዘርና የቀዶ ጥገና ማዕከል

ማንኛውንም የቆዳ ችግሮዎን እንረዳዎታለን ይህንን ማስታወቂያ ይዘው ለሚመጡ የነጻ ምክር እንሰጣለን

202-518-0245


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

ኮሙዩኒቲ

10

የዘረ ኢትዮጵያውያን የሰሜን አሜሪካ የማህበራዊ ተቋማት ማስተባበሪያ ማእክል

የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድ- Ethiopian Community Trust Fund (ECTF) 1- ዳራ (Background) በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው የምንገኝ ዘረ-ኢትዮጵያዊያን በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካና በሌሎች ልዩነቶች ሊገደብ የማይገባው እሴት፣ ባህል ፣ልማድ፣ ወግና ቅርስ ያለን ማህበረሰብ እንደመሆናችን፤ በሃገረ አሜሪካ ተገቢውን ክብርና ጥቅም አስጠብቀን ለዚህና ለቀጣይ ትውልድ ለማሸጋገር በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢ የዘረ-ኢትዮጵያዊያን ማህበራዊ ተቋማት ማስተባበሪያ ማእከል መኖር ፈርጀብዙ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ ለዚህ ማእከል እውን መሆን የማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድ (Community Trust Fund) ተመራጭና ለተጨማሪ ሀብት ማሰባሰብ ወሳኝ መሆኑን ከስኬታማ ተሞክሮዎችና በመስኩ ከተሰማሩ ባለሙያወች ለመረዳት ይቻላል፡፡ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢ የዘረ-ኢትዮጵያዊያን ማህበራዊ ተቋማት ማስተባበሪያ ማእከልም በየደረጃው ለሚያቋቁማቸው የአረጋውያን፣ የወጣቶች፣ የባህል፣ የሳይንስ፣ ትምህርትና ማህበራዊ አገልግሎት ማእከላት ህልውና የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድ ( Ethiopian Community Trust Fund) መኖር ወሳኝና ሂደቱን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያፋጥን በጽኑ ይታመናል፡ ፡ ለዚህም በአካባቢያችን የሚገኙ ጠንካራ የማህበረሰብ ክፍሎች ተሞክሮ እንደ አመላካች አብነት ሊወሰድ ይችላል፡፡ ዘረኢትዮጰያዊ የማህበረሰቡ አባላትን በማስተባባረና በማቀራረብ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ለሚገኙ ተማሪዎች፣ ባለሙያወች፣ በየሙያቸው ለመሰማራት ለተዘጋጁና ድጋፍ ለሚሹ የህብረተሰባችን ክፍሎች ለመድረስ፤ አንዱ ሃብትን የማቀናጃ ዘዴ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድ እንዲኖር ማድረግ ነው፡ ፡ ፈንዱ የዘረኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ክብርና ጥቅም እንዲከበር ልዩ ልዩ በበጉ ፈቃደኛነት የሚከናወኑ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶችን ይደግፋል፡፡ በተለይም በዘለቄታው የማህበረሰባችን እድገት ሊያፋጥኑ ለሚችሉ ከወጣቱና ከትምህርት ጋር ለተያያዙ የሰው ሃብት ልማት ስራወች ልዩ ትኩረትን ያደርጋል፡፡

2- የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድ (ECTF) አስፈላጊነት

የቢዝነስ ትስስር፣ በሳይንስ ክህሎትና የእውቀት ሽግግር መስክ፣ በሰሜን አሜሪካ በምንኖር ዘረ-ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው ውህደት ማነስ ማሳያዎች ናቸው፡ ፡ ከዚህ አልፈን የትምህርትና የጤና አገልግሎትን ጨምሮ የህብረተሰብን እድገትና ፍላጎት እውን ለማድረግ አዳዲስ እስትራቴጅና ሃሳቦችን እውን የሚያደረግ ማህበራዊ ሂደትን መተግበር አሰፈላጊነቱ የጎላበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡

ፈጥረው ልዩነቶቻችን የመቻቻልና የመተጋገዝ ባህላችንን የሚያጎለብትበትን መድረክ የሚፈጥር ይሆናል፡፡ ማዕከሉ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ሙዚየምን፣ የኪነጥበብና የታሪክ መዘክርን እንዲሁም በዕላትና ትእይንቶችን ማስተናግድ የሚችል ደረጃውን የጠበቀ አዳራሽ ያካተተ ህንፃ እንዲኖረው ይደረጋል፡፡ ማዕከሉ ለዘረኢትዮጵያዊያ እንዲሁም ሌሎች ጎብኞች አመቱን ሙሉ ለጉብኝት ክፍት ይሆናል፡፡

ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ደግሞ የማህበራዊ ተቋማትና የሙያ ማህበራት ቁርኝት ጥንካሬ ጉልህ ሚና ይኖረዋል፡፡ ከዚህ ጋር በማዛመድ በዋሽንግተን ዲሲና

ለ. የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አረጋዊያን ማዕከል

ሐ. የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ የወጣቶች ልማት ማዕከለ በልጅነትና በጎልማሳነት መካከል የሚገኘው የአንድ ማህበረሰብ ወሳኝ ሃይል ወጣቱ ሲሆን፤ በዚህ የእደሜ ክልል የምትገኝ ወይም የሚገኝን ትውልድ ብቁና ተወዳዳሪ አድረጎ ማፍራት የጠንካራ ማህበረሰብን ድጋፍ፣ ክትትልና ያላሰለሰ ጥረት ይጠይቃል፡፡ ይህ በእቅድና በተግባር

የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድ (ECTF) የፋይናንስ ግብ በጊዜ ሰሌዳ ሲታይ የፋይናንስ ምንጭ

በመጀመሪያ ዓመት

ከአንድ ሽህ አባላት ይሰበሰባል ተብሎ የሚጠበቅ የቦንድ ዋጋ (Estimated Bond value per member $1000.00)

$1,000,000.00

ከመዋጮና ብድር ይሰበሰባል ተብሎ የሚጠበቅ

$1,000,000.00

ከአገልግሎት ይሰበሰባል ተብሎ የሚጠበቅ በድምሩ የሚጠበቅ የገቢ መጠን

$2,000,000.00

በሁለተኛ ዓመት

በአምስተኛ ዓመት

$1,000,000.00

$1,000,000.00

$1,000,000.00

$1,000,000.00

$3,000,000.00

$5,000,000.00

$5,000,000.00

$8,000,000.00

የትምህርትና የሳይንስ ማዕከለ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ የትምህርትና የሳይንስ ማዕከለን ማቋቋም ይህን ትውልድና ቀጣዩን የዘረ-ኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ተተኪ ትውልድ የሳይንስ፣ የሂሳብ፣ የቴክኖሎጂ፣ የአዳዲስ ግኝቶችና ፈጠራዎች ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል፡ ፡ ለዚህም ተቋሙ በንግድ ትርፋማነት ላይ የለተመሰረተ (not-for-profit) አላማ ስለሚኖረው ለሰፊው የማህበረሰብ ክፍላችን ተደራሽነት ይኖረዋል፡፡ ይህ ማዕከል በዲሲና አካባቢው ለሚገኙ የዘረኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ፈርጀብዙ የሳይንስ፣ የምርምርና የትምህርት ስራዎችን ለማከናወን፣ በዚህ ሂደትም ሰፊውን የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚና አሳታፊ ለማድረግ የጎላ ጠቀሜታ ይኖረዋል፡ ፡ የሚካሄዱት የትምህርትና የምርምር ስራዎች በቀዳሚነት የማህበረሰባችን ችግር ለመቅረፍ ትኩረት ይሰጡ ዘንድ ተማሪዎችን፣ የቤተሰብ ሃላፊዎች እና ተመራማሪዎች በሰፊው እንዲያሳትፍ ትኩረት ይደረጋል፡፡ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድን ከሌሎች ተመራጭ የአቅም ማሰባሰቢያ ስልቶች ጋር በማቀናጀት በተጠናከረ የባለሙያዎች ጥረት ይህን ተግባራዊ ለማድረግ በአካባቢዋ ሰፊ የዘረኢትዮጵያዊያን እምቅ የባለሙያ ሃይል መኖሩ ሌላው የማህበረሰባችን ምቹ እድል ሆኖ ሊወሰድ ይችላል፡፡ 4-

አካባቢው የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድ (ECTF) መቋቋም በራሱ ከሚፈጥረው የፋይናንስ አቅም በተጨማሪ ሌሎች የፋይናንስ ምንጮችን በማሰከተል የአገልግሎት ተደራሽነትን ያሰፋል፣ ማህበረሰባችን ለበለጠ እድገትና ተወዳዳሪነት ያነሳሳል ያቀራርባል፣ ለችግሮች የጋራ መፍትሄ ለማፈላለግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድን (ECTF) ማቋቋም እጅግ አስፈላጊና አዋጭ ነው፡፡

በኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ፈንድ (ECTF) ምን ይሰራል? 3-

ሀ. የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ የባህል ማዕከል

በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ለረዥም አመታት በተለያዩ ማህበራዊ ተቋማትና የሙያ ማህበራት እንደየፍላጎታችን ስንደራጅ መቆየታችን ይታወቃል፡፡ ይሁንና ከተቋሞቹ የቁጥር ብዛት አንጻር ሲታይ ቀጣይነት ያለው የሁለንትናዊ ሀብት እጥረት መኖርና በትብብር መስራት አለመቻል ብዙ ተቋሞች የሚጠበቀውን ያህል እድገት ሊያሳዩ አልቻሉም፡፡ ለዚህም በሚከተሉት ተቋማትና የትበብር መስኮች ከሚጠበቀው በታች የሆነ ግንኙነት መኖሩ እንደ አብነት መጥቀስ ይችላል፡፡ በኢትዮጵያዊያን በማህበራዊ አገልግሎት መስጫዎች፣ በሰሜን አሜሪካና በሃገር ቤት ያለው

ይህ ማዕከል በኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ በተለይም የአረጋዊያን ማህበረዊ ግንኙነትና

የንግድ ድርጅቶች፣ ከተጠቃሚዎች ክፍያ፣ ከአይነት እርዳታና በጎድራጊዎች ነጻ አገልግሎና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተፈላጊውን ሃብተና አቅም ለማሰባሰብ ሰፊ ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያዊያን የራስን ባህል፣ ወግ፣ ማንነት፣ እምነት፣ ታሪክና እሴቶች ማክበር የብዙ ክስተቶችና እውነታዎች ውጤት ናቸው፡፡ ለዚህም ኢትዮጵያ ለዘመናት የብዙ ቋንቋዎች፣ የራስ ብሄራዊ ቋንቋና የፊደል ሥርዓት ፣ የሃማኖትና ፍልስፍና፣ የስነምግባርና ንድፈሃሰብ፣ የተከበሩ እሴቶች፣ ነጻነትና ክብር፣ የራስ ማንነት፣ ሃገር ወዳድነትና አርበኝነት ባለቤት ሆና መቆየቷ ተጠቃሽ እውነታዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም የሚቋቋመው የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ የባህል ማዕከል በረካታ ገጽታዎችን ያካተተ፣ የኢትዮጵያ የኪነ ጥበብ፣ የትምህርትና የመዝናኛ አገልግሎቶችን በመስጠት በዘረኢትዮጵያዊያን ቤተሰብና ማህበረሰብ መካከል የበለጠ መተሳሰብ፣ መቀራረብን

ጓደኝነት፣ ለአረጋዊያን የሚሰጠውን ክብር፣ ከአረጋዊያን ሊተላለፍ የሚገባውን የህይወትና የትምህርት ተሞክሮ፣ አረጋዊያን ለራሳቸው የሚሰጡት ግምትና ክብር እንዲጠናከርና በውጤቱም የብቸኝነትና የመገለል ስሜት በአካልና በአዕምሮ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ለመከላከል የበኩሉን ሚና የሚጫወት ይሆናል፡፡ ማዕከሉ በተለያዩ ምክንያቶች ራሳቸውን የመደገፍ አቅም ላጠራቸው አረጋውያን በርካታ አገልግሎቶችን በማቅረብ ቀሪው የእድሜ ዘመናቸው ሰላማዊ እንዲሆን እድል የሚፈጥር ይሆናል፡፡ የጤና፣ የትምህርት፣የመዝናኛና ሊሎች የማህበረዊ ግንኙነት አገልግሎቶች በተሳታፊ የበጎ አድራጎት አገልጋዮች በመደገፍ የማህበረሰቡን ተሳታፊነት ማጎልበትና የተጠቃሚዎችን ክብርና በራስ መተማመን ማጎልበት በማዕከሉ ሊሰጡ ከታሰቡ አገልግሎቶች ውስጥ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በተጨማሪም የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አረጋዊያን ማዕከለ በዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ የእድሜ ባለጸጎችን ለሚንከባከቡና ለሚረዱ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አባላት አገልግሎትና መረጃን በመስጠት የሚንቀሳቀስ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ማዕከሉ ምቹና የተቀናጀ ድጋፍ ለአረጋዊያንና ለአረጋዊያን አገልግሎት ሠጪ ባለድርሻዎች በማዳረስ ማህበረሰባችን ተጠቃሚ ለማድረግ ከየፊዴራል፣ ከአገርና የአካባቢ መንግስታት፣ ከልዩ ልዩ ዝግጅቶች፣ከግልና ከማህበራዊ ተቋማት፣

ሲደገፍ ወጣቶች ተገቢውን ክህሎት፣ እውቀት፣ ተወዳደሪነትና አመለካካት ይዘው ለዘላቂ ስኬት ይበቃሉ፡፡ ይህ ሳይሆን ሲቀር የወጣቶች የወደፊት ተወዳደሪነትና ተስፋ የጨለመና ወዳልተፈለገ ጎዳና ያመራ ይሆናል፡፡ ለዚህ ነው በወጣትነት እደሜ የሚወሰዱ አማራጮችና ውሳኔዎች በግለሰብም ሆነ በማህበረሰብ ስኬት ላይ የጎላ አንድምታ የሚኖራቸው፡፡ ወጣቶች ፈተናን ተቋቁመው ለአሸናፊነት እንዲበቁ በግላቸውና በቤተሰባቸው ከሚደረግ ጥረት ጎን ለጎን የማህበረሰብ እገዛ የጎላ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ የዘረ-ኢትዮጵያዊያን ማህበራዊ ተቋማት ማስተባበሪያ ማዕከልም ለዚህ ጉዳይ ትኩረት በመስጠት፤ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ የወጣቶች ልማት ማዕከልን ለማቋቋም ወስኗል፡፡ ይህም ወጣቶች ለተወዳዳሪነትና ስኬታማነት የሚያበቁ እውቀትና ተሞክሮን የሚጋሩበትን መድረክ ይፈጥራል፡፡ ጠቃሚ ውሳኔዎችን መውሰድ እንዲለማመዱና ገንቢ ግንኙነትን እነዲለማማዱ ማዕከሉ ከራሱ የማህበረሰብ ተወካዮችና ከሌሎች የማህበረሰብ መዕከላት፣ ከበጎ አድራጎት ተቋማት፣ ከአካባቢ ኮሚሽነሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት በመመስረት ማዕከሉን ያቋቁማል ያሳድጋልም፡፡ ማንኛውም የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አባል ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ በአፈፃፀምና ግምገማ ተሳታፊ እንድንሆን ለሁላችንም የአባልነት ጥሪን ያቀርባል፡፡ መ.

የኢትዮጵያዊያን

ማህበረሰብ

ረቂቅ የፋይናስ ምንጪ እቅድ

በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢ የሚደረጉ የማህበረሰብ ልማት ስራዎች ከልዮ ልዮ የፋናንስ ምንጪ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያስችል አሰራር በፌዴራልና በከአካባቢ መንግስታት፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች፣ በበጎ አድራጎት ተቋማት፣ በታላላቅ የንግድ ድርጅቶችና መስሪያቤቶች ውስጥ መኖሩ ይታወቃል፡ ፡ አንድን ማህበረሰብ የዚህ አሰራር የበለጠ ተጠቃሚ ከሚያደርጉት ቅድመ ሆኔታዎች አንዱ የማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድን ያቋቋመ ሆኖ መገኘት ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ አስተማማኝ ፈንድ መቋቋም በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢ የሚገኙ የዘረ-ኢትዮጵያዊያን ማህበረሰብ ለሚያከናውናቸው የማህበረሰብ የልማት ስራዎች አስተማማኝ አሴትን ከመፍጠሩ በላይ ተጨማሪ የገንዘብ አቅምና ልገሳዎችን ከሌሎች ባለድርሻዎች ለማግኘት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ይህ የማህበረሰብ ልማት ፈንድ የንግድ ትርፍ ለማግኘት አገልግሎት የማይውል ቢሆንም በማዕከላቱ ከሚሰጡ አገልግሎቶች አስተማማኝ የገቢ ምንጪን እውን በማድረጉ ረገድ የጎላ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ በዚህም ማህረሰባችን በሂደት ዘላቂ የልማትና የእድገት ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የኢንቨስትመንት አቅም ባለቤት ይሆናል ማለት ነው፡ ፡ በማጠቃለል የዘረ-ኢትዮጵያዊያን ማህበራዊ ተቋማት ማስተባበሪያ ማዕከልም የፋይናስ ምንጪ ከመንግስት፣ ከማህበረሰብ የሚገኝ ልገሳና ከማዕከላቱ ገቢ ይሆናል ማለት ነው፡፡

ቤተሰብ ሐምራዊት ተስፋ አንድ ልንክደው የማንችለው እውነት አለ። ያም ልጆቻችን የሚሄዱበት ትምህርት ቤት፣ የትምህርት አሰጣጣቸውን እንደሚወስን ነው፤ስለዚህም ለምጥቀታቸው ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል። ይህንን እውነት ተረድተን፣ በተቻለን መጠን የትምህርት አሰጣጥ ጥራቱ የተሻለ ትምህርት ቤት እንዲሄዱ እንጣር። እውነት ነው፤ ብዙዎቻችን፣ ልጆቻችንን የግል ትምህርት ቤት ለመላክ፣ አቅሙ ላይኖረን ይችላል፤ ስለዚህም ያለን ብቸኛ አማራጭ፣ በአካባቢያችን ያለ ትምህርት ቤት ልጆቻችንን ማስገባት ብቻ እንደ ሆነ ሊሰማን ይችላል። ነገር ግን፣ ከዛ ያለፉ የተለያዩ ምርጫዎች አሉ። ከስር የምናያቸው ፕሮግራሞች በእርስዎ ወረዳ ውስጥ እንዳሉ ያጣሩ። የትምህርት ቤት ምርጫን አስመልክቶ ያሉ የተለያዩ ፕሮግራሞች Open enrollment፤ በዚህ ፕሮግራም ስር፣ ከመኖርያዎ አቅራቢያ ባለ ትምህርት ቤት

የልጆቻችን ትምህርት ቤት አይወሰኑም። በእርስዎ ወረዳም ያሉ ሌሎች ትምህርት ቤቶች ሆኑ በሌሎች ወረዳዎች፤ ለልጅዎ ትምህርት ቤቶችን መምረጥ ይችላሉ። Charter school፤ እነዚህ በህዝብ የተመሰረቱ (የሚደገፉ) አንደኛ ደረጃ ፤ ሁለተኛ ደረጃና አጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ናቸው። የህዝብ ትምህርት ቤት ቢሆኑም፣ ሌሎች የህዝብ ትምህርት ቤቶች በሚተዳደሩበት ህግ ሁሉ አይተዳደሩም። ብዙ ጊዜ ቻርተር ስኩልስ ልጆችን የሚቀበሉት በዕጣ መልክ ነው። ቻርተር ስኩልሰ ክፍያ እንዲያሰከፍሉ አየፈቀድላቸውም። አንዳንድ የቻርተር ትምህርት ቤቶች በተወሰኑ የትምህርተ መስኮች ብቻ ስርአተ ትምህርተ አላቸው። ለምሳሌ ስነ ጥበብ፣ ሂሳብ። ሌሎች ደግሞ፣ የተሻለና ከሌሎች የህዝብ ትምህርት ቤቶች በጠራ ሁኔታ ሁሉንም ትምህርት ይሰጣሉ። Magnet schools፤ የህዝብ ትምህርት ቤት አካል ናቸው።

ማግኔት ስኩል የተለየ ችሎታ ወይም ምርጫ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የተዘጋጀ ፕሮግራም አለው። ብዙ ጊዜ ትምህርት አሰጣጣቸው ጥራት ባለው መልኩ ነው። ትምህርት ቤቱ አመልካቾችን የሚመርጥበት የራሱ መስፈርት አለው። Voucher፤ ወላጆች የህዝብን ድጎማ (ፓብሊክ ፈንድ) ተጠቅመው የመረጡት ትምህርት ቤት ልጆቻቸውን ለማስገባት የሚረዳቸው ሰርተፊኬት ነው። አሪዞና፣ ፍሎሪዳ፣ ኦሀዮ፣ ኦታዋ ዊስከንሰንና ዋሽንግተን ዲሲ የቫውቸር ፕሮግራም አላቸው። Alternative schools በትምህርት በጣም ዝቅ ያለ ውጤት እያመጡ ያሉና በመውደቅ አደጋ ውስጥ ላሉ ተማሪዎች የተሻለ አካባቢ ለመፍጠር የተቋቋሙ ትምህርት ቤቶች ናቸው (በኢንተርኔት የበለጠ ገለጻን ማግኘት ይችላሉ) No Child left behind (NCLB) የሚለው ህግ

ይህን ይመስላል፤ የልጅዎ ትምህርት ቤት ከፌደራል የተለየ ድጎማ የሚቀበል (title 1) ትምህርት ቤት ከሆነ እና ለ2 ተከታታይ አመታት የሚጠበቅበትን ግብ ካልመታ፣ በዚያው ወረዳ (district) ላይ ልጅዎን ወደ ሌላ ት/ቤት የማዛወር መብት አለዎት። የፌዴራል ድጎማ የዚህ አይነቱን ዝውውር ወጭ ይሸፍናል። ልጅዎ ከነበረበት ት/ቤት ለተሻለ ለውጥ እሰከተዘዋወረ ድረስ የወረዳው ትምህርት ቤት ለልጅዎ መጓጓዣ ወደ አዲሱ ትምህርት ቤት ያቀርባል። ከላይ እንዳየነው፣ የትምህርት ቤት ምርጫን በተመለከተ፣ የተለያዩ አማራጮች አሉ። ልጅዎ የምትማርበት ትምህርት ቤት ሄደው ስለእነዚህ ፕሮግራሞች መጠየቅ ይችላሉ። በምንኖርበት ወረዳ (ዲስትሪክት) ውስጥ ትምህርት ቤትን በተመለከተ፣ የቱ አማራጭ እንዳለ ለማወቅ መሞከር በጣም አስፈላጊ ምርጫ ነው። በርስዎ ወረዳ

(district) ምን አይነት ፕሮግራም እንዳለ ለማወቅ፣ ወደ ወረዳዎ ቢሮ ደውለው ማወቅ ወይም ዌብ ሳይታቸው ውስጥ ገብተው መመልከት ይችላሉ። ሌላው፣ የምንችል ከሆነ ያለን አማራጭ፣ የተሻለ የትምህርት አሰጣጥ ያለበት ወረዳ መግባት (ሰፈራችንን መለወጥ ነው)። በአካባቢያችን ያሉ የግል ትምህርት ቤቶች፣ ለልጆቻችን ስኮላርሺፕ ሊሰጡ የሚችሉበት አማራጭ ካለም ሄዶ መጠየቅ ሌላ ጥሩ አማራጭ ነው። በአካባቢዎ ያሉትን ወላጆች መጠየቅና ከእነሱ እይታ እና ምርጫ አንጻር ሁኔታውን ለመረዳት መሞከርም ይጠቅማል። (ስለእነዚህ ፕሮግራሞች የበለጠ እውቀት ለማግኘት ከገጾቹ ስር ያሉትን ድህረ ገጾች (ዌብ ሳይት) ይመልከቱ) ማጠቃለያ የልጆች በትምህርት መምጠቅ ላይ፣ ወላጅ ትልቅ ቦታ እንዳለው ተረድተን፣ ከልጅነታቸው እንገንባt’å።

ጠንክሮ መሥራት፣ ትልቅ ነገር ማለምን፣ አደርገዋለሁ ብሎ ማመን፣ተስፋ አለመቁረጥ፤ በልጆቻችን ውስጥ እንዲቀረጽ ጠንክረን እንስራ፤ በራሳቸው በተጠሩበት ነገር አብበው ይወጣሉ። Charter School; በአካባቢዎ ያለ ቻርተር ስኩል ለማግኘት ቢፈልጉ (www. ederform.com) ብለው ይዩ Charterschoolcenter. org ብለው ቢገቡ ስለቻርተር ስኩል የበለጠ ገለጻ ማግኘት ይችላሉ። Magnet schools; (ስለዚህ ፕሮግራም የበለጠ ለማወቅ ኢንተርኔት ገብተው magnet.edu ብለው ይመልከቱ የበለጠ እርዳታ ለማግኘት 202-824-0672 ይደውሉ) ስለ ቫዎቸር ፕሮግራም የበለጠ ለማወቅ ከፈለጉ Schoolchoices.org/ voucher w w w . allianceforschoolchoice.org


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

11

Clamp down on Ethiopia’s independent media The Ethiopian government’s systematic repression of independent media has created a bleak landscape for free expression ahead of their May elections. In a report released this week, Human Rights Watch details how the Ethiopian government has curtailed independent reporting since 2010, and says legal and policy reforms are crucial in Ethiopia prior to the May 2015 elections. In the past year, six privately owned publications closed after government harassment; at least 22 journalists, bloggers and publishers were criminally charged, and more than 30 journalists fled the country in fear of being arrested under repressive laws. HRW interviewed more than 70 current and exiled journalists between May 2013 and December 2014, and found patterns of government abuse against journalists that resulted in 19 being imprisoned for exercising their right to free expression, and that have forced at least 60 others into exile since 2010. Most of Ethiopia’s print, television and radio outlets are state-controlled, and the few

Horrific Car Accident on Ethiopia’s New Expressway Left Eleven Dead An early morning major car accident on Sunday January 18th on the newly opened Addis-Adama expressway has left eleven people dead on impact and nine people wounded. Five of the wounded have received life threatening wounds and are in critical conditions, an investigating officer told Addis

private print media agencies often self-censor their coverage of politically sensitive issues for fear of being shut down. Social media is also heavily restricted, and many blog sites and websites run by Ethiopians in the diaspora are blocked inside Ethiopia. It is reported that journalists who publish critical articles may receive threatening telephone calls, text messages, and visits from security officials and ruling party cadres. Some said they received hundreds of these threats. If this does not silence them or intimidate them into self-censorship, then the threats intensify and arrests often follow. The courts have shown little or no independence in criminal cases against journalists who have been convicted after unfair trials and sentenced to lengthy prison terms, often on terrorism-related charges. “Muzzling independent voices through trumped-up criminal charges and harassment is making Ethiopia one of the world’s biggest jailers of journalists,” deputy Africa director at HRW Leslie Lefkow said. “The government should immediately release those wrongly imprisoned and reform laws to protect media freedom.” Most radio and television stations in Ethiopia are government-affiliated, rarely stray from the government position, and tend to promote government policies and tout development successes. Control of radio is crucial politically given that more than 80%

Standard. The accident happened early at around 6:00 am when a driver of a Sinotruk coming from Adama, the capital of Oromia regional state 100 kms South of Addis Abeba, lost its track and derailed into the separation fence of the six lane expressway. The Sinotruck then hit a minivan carrying 16 people and was speeding from Addis Abeba to Adama, reducing the minivan to a quarter of its original size and killing the eleven people on board on impact. “We have no idea how this could possibly happen,” an investigating officer on the spot told Addis Standard, “we are unable to know whether the driver of the truck is amongst the dead or has left the accident scene.”

of Ethiopia’s population lives in rural areas, where radio is still the main medium for news and information. The few private radio stations that cover political events are subjected to editing and approval requirements by local government officials. The government has also used a variety of subtle but effective administrative and regulatory restrictions, such as hampering efforts to form journalist associations, delaying permits and renewals of private publications, putting pressure on the few printing presses and distributors, and linking employment in state media to ruling party membership. The increased media repression will clearly affect the media landscape for the May elections, HRW said. “The government still has time to make significant reforms that would improve media freedoms before the May elections,” Lefkow said. “Amending oppressive laws and freeing jailed journalists do not require significant time or resources, but only the political will for reform.”

The driver and the assistant on the minivan were among the dead. Most of the passengers on the minivan were people going to celebrate the Epiphany celebrations of the Ethiopian Orthodox Church with their loved ones, the investigating office who wants to remain anonymous told us. Due to massive construction works throughout the country, Ethiopia has seen a sharp increase in the numbers of the Chinese made Sinotruks. However, many Ethiopians complain of horrific car accidents caused by these tucks as most of them are operated by poorly trained drivers. The 84.5 km Addis-Adama expressway, the first for the country, opened for traffic on Sep. 14th 2014. The six-lane expressway

was built by China Communications and Construction Co. (CCCC) and financed by the government in Ethiopia and Exim Bank of china, which provided a US$800 million.

Heineken’s new Ethiopia brewery hits full capacity

ELEVEN CHILDREN HURT AFTER SCHOOL FENCE COLLAPSE Elven children were hurt, two critically, when the school fence caved in while the children were out playing during a snack break this morning, according information from the Addis Abeba Fire and Emergency Prevention and Rescue Agency (AAFEPRA). Frehiwot elementary school is located at Nefas Silk Lafto K. K, near Kadisco Paint Factory and adjacent the construction site for the city’s light rail project. According to AAFEPRA the concrete fence might have caved in due to a deep drilling happening next to it for a power house intended for the light rail project. The students were at a snack break playing in the compound when the fence collapsed. Two of the eleven were admitted to a hospital and are said to be in critical condition. (Addis Standard)

Heineken’s new EUR110m (US$129m) brewery in Ethiopia is up to full capacity six months after it was completed. The Kilinto factory, near capital Addis Ababa, is Heineken’s third brewery in the country and was inaugurated last week in a ceremony led by Heineken CEO Jean-François van Boxmeer. The ceremony marked the formal finish of the project, but brewing started in the last week of July. The spokesperson said the brewery is now at “full planned capacity and running as required”. Construction on the project, part of Heineken’s EUR310m investment in Ethiopia, started in March 2013. The plant’s main focus is the local brand Walia beer, which was launched in August, as well as Bedele, Harar and Sofi Malt. Brand Heineken will also be brewed at The brewery will the plant “in due course”, the spokesperson said. mainly produce Walia beer Capacity outstrips Heineken’s other two Ethiopian breweries at 1.5m hectolitres a year. (Just-drinks)

The expressway has seven toll stations between Tulu Dimtu on the outskirts of Addis Abeba, and the last point in the western part of Adama.

“Islamic Revolution” Seminar Planned in Ethiopia The Iranian Cultural Center in Ethiopia plans to hold a seminar on the Islamic Revolution later this month. Slated for January 31, the event will also feature Islamic Awakening in the sub-Saharan region. A number of university scholars and Muslim and Christian figures will be present in the seminar, planned on the occasion of the victory anniversary of Iran’s 1979 Islamic Revolution. Iranian Deputy Foreign Minister for Arab and African Affairs Hossein Amir Abdollahian is expected to present a paper in the seminar. Iranian Islamic Revolution’s victory, seen as the most important milestone in Iran’s recent history, liberated the country from the yoke of the hegemonic powers --with the ousted Shah as their stooge-- and established a new political system based upon Islamic values and democracy. The Iranian nation toppled the West-backed Pahlavi regime in February 1979, ending 2,500 years of monarchic rule in the country. (Source : IQNA)

Experts Rank Ethiopia’s Coffee Among Best (VOA) Ethiopia’s coffee has been ranked as the best in the world by an international group of coffee connoisseurs. Not surprisingly, coffee is a top export for the country. But at home it is a source of pride. International coffee experts travel the world to find the best tasting cup. They keep coming back to Ethiopia, where importers like Morton Wennersgaard say the climate produces quality coffee beans. “You have different ancient varieties referred to as Ethiopian heirdom. They are grown in places with perfect soil, perfect altitude, and

micro climates that are really suitable for coffee processing, such as drying and things like that,” he explains. Finding the best beans is a matter of taste, literally. The intense process is known as cupping - tasting and comparing coffee from different roasted beans, grading and then pricing them.

“When the coffee comes to the lab, we assess the coffee quality first by recording the details. Then we weigh the moisture level and we screen the beans for analysis. After that we grind the coffee beans and taste the samples. At the end we check for defective beans,” Assefa explains.

Coffee labs

And that screening is a very difficult and lengthy process, says lab worker Mubarik Abaoli.

But before international experts come to taste, coffee beans go through analysis in small coffee labs, where Helen Assefa describes the process.

“We sort out the defects manually, by hand. And we sort out the defect according to the defect types. The types are immature, paste

damage, foxy, black - all has to be sorted out according to the severity of the defects,” Mubarik Abaoli says. Cashing in abroad Nevertheless, Ethiopia is cashing in on its coffee reputation with consumers in more than 120 countries and a yearly export revenue of more than $840 million. But not all the best coffee leaves Ethiopia. With 40 percent of the coffee production consumed at home, it remains an important part of everyday life at work, at home and at ceremonies just to celebrate that special cup.


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

አንዳንድ ነገሮች ስለሕግ ዶ/ር ፍፁም አቻምየለህ ዶ/ር ፍጹም አቻምለህ ዓለሙ ከሃገንጋሪ ቡዳፔስት በህግ የመጀመሪያ ዲግሪውን ያገኘው እ.ኤ.አ. በ1988 ነበር። ከኢትዮጵያ ለትምህርት ከሄደበት ሃንጋሪ ትምህርቱን እንደደረስ ለተደማሪ ትምህርት በቡዳፔስት ከሚሰራበት የሰብዓዊ መብት ድርጅት ስኮላርሺፕ አግኝቶ ወደ አሜሪካ መጥቷል። እንደገና ወደ አውሮፓ ቡዳፔስት በመመለስ በሃንጋሪ ታዋቂ ለሆነ አንድ ሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት ጠበቃና የፕሮጀክት ማኔጀር ሆኖ ሠርቷል። ከ1996 ጀምሮ ወደ አሜሪካ በምመጣት በተለያዩ ቦታዎች ሲሠራ ከቆየ በኋላ ከዲሴምበር 2003 ጀምሮ የራሱን የፍጹም አቻምየለህ የጥብቅና ድርጅት አቋቁሞ እየሠራ ነው።

አስገድዶ መድፈር -R a p e አስገድድሞ መድፈርን 50ዎቹ ክፍለ ሀገሮችም ሆኑ የፈደራሉ መንግስት እንደከባድ ወንጀል ነው የሚቆጥሩት። እንዲህ ዓይነቱ ወንጀል በቨርጂኒያ ከ5 ዓመት እስከ እድሜ ልክ፣ ለዲሲ ደግሞ 50ሺ ብር ቅጣትና አምስት ዓመት፣ በአካል ላይ ጉዳት ከደረሰ ደግሞ እስከ እድሜ ልክ ሊያሳስር ይችላል። ወንጀሉ ከ14 ዓመት በታች በሆነ ሕጻን ላይ ከተፈጸመ ግን፣ ከ20 እስከ 30 ዓመት እስር ሊያስከትል ይችላል። አስገድዶ መድፈር ማለት፣ ያለ ውዴታ በማስገደድ፣ በማስፈራራት፣ ኃይል በመጠቀም ወይንም በመጠጥ፣ በመድኃኒት፣ በአልኮል፣ ብሎ ም በአደንዛዥ እጽ ምክንያት የመስማማት አቅም ከሎለው ወይም ከደከመ ሰው ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም ማለት ነው። እድሜያቸው ለአቅመ አዳም ካልደረሱ ህጻናት ጋር ( እንደየክፍለ አገሩ 13 ወይም 14 ዓመት ካልሞላቸው ህጻናት ጋር) የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም በራሱ እንደ አስገድዶ መድፈር ይቆጠራል (Statutory Rape) ። ይህ የሆነበት ምክንያት ህጻናቱ የመስማማት ችሎታ የላቸውም ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። ብዙዎቹ ክፍለ አገሮች ባልተጋቡ ሰዎች መካከል ብቻ ሳይሆን በተጋቡ ሰዎች መካከልም አስገድዶ መድፍረን ይከለክላሉ። ይቀጣሉ። የአስገድዶ መድፈር ህጎች ታሪክ እንደሚያሳየው ህጎቹ ሲወጡ ሴቶችን ከጥቃት ለመከላከል ነበር የወጡት። የዛሬ ህጎች ግን ሁለቱም ጾታዎች ላይ ልዩነት አያሳዩም። ከዚያም አልፎ አዳዲስ ህጎች በጋብቻ ውስጥ የሚፈጸመውን አስገድዶ መድፈርንም አጥብቀው ይከለክላሉ። ቀደም ያሉት ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ የአስገድዶ መድፈር 83 ፐርሰንቱ የሚፈጸመው በሚተዋወቁ ሰዎች መካከል ነው። የድርጊቱ 36 ከመቶ ደግሞ የሚፈጸመው በተደፋሪው ቤት ነው። ድርጊቱም የሚፈጸምበት ሰዓት በብዛት ከ6 ፔም እስከ 6 ኤ ኤም ባለው ሰዓት ውስጥ ነው። ጥናቶቹ እንደሚያሳዩት መጠጥ፣ አደንዛዥ እጽ መውሰድ ለእንዲህ ዓይነት ድርጊት ፈጻሚም ሆነ ሰለባ ለመሆን ትልቅ ሚና ይጫወታል። ማቲው ሴል እንዳለው “ በአስገድዶ መድፈር አንድን ሰው ለመክሰስ ቀላል ነው። ተከሳሽን ጥፋተኛ ለማሰኘት ከባድ ነው። ተከሳሽን ለመከላከልና ነጻ ለማውጣት ደግሞ በጣም ከባድ ነው።” ይህ ማለት በአጠቃላይ አስገድዶ መድፈር ለከሳሽም ለተከሳሽም፣ ለፍርድ ቤትም አስቸጋሪና ውስብስብ ከሚባሉት ወንጀሎች አንዱ ነው። ፖሊስና አቃቢ ሕግ ተከሳሽን ጥፋተኛ ለማሰኘት ዋነኛ መረጃቸው የህክምና የምርመራ ውጤቶች፣ የምስክርነት ቃሎች፣ ፎቶ ግራፎች፣ ቪዲዮዎች፣የስልክ ልውውጦች፣ የፈጻሚ እና የተፈጸመበት ግለሰብ የግንኙነት ታሪክ፣ የትውውቅ ጊዜ እና ለአቅመ አዳም ካልደረሱ ጋር ደግሞ ከተፈጸመ የህጻኑ ወይም የህጻኒቷ “ በአስገድዶ መድፈር የልደት ሰርትፍኬት አንድን ሰው ለመክሰስ ሊሆኑ ይችላሉ። ቀላል ነው። ተከሳሽን ተከሳሽ በበኩሉ ጥፋተኛ ለማሰኘት ወይም በበኩሏ ከባድ ነው። ተከሳሽን ደግሞ ስምምነት ለመከላከልና ነጻ መኖሩንና ምንም ለማውጣት ደግሞ በጣም ዓይነት ኃይል ከባድ ነው።” አለመጠቀሙን ወይም አለመጠቀሟን ብሎም ተጠቂዋ ወይም ተጠቂው የመስማማት ሙሉ ችሎታ እንደነበራት ወይም እንደነበረው ማሳየት ይኖርበታል ወይም ይኖርባታል። ተጠቂው ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ሰው ወይም ህጻን ከሆነ ግን የህጻኑን እድሜ አለማወቅ በራሱ መከላከያ ሊሆን አይችልም። ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው አስገድዶ መድፈር ከባድ ወንጀል ነው። ለብዙ ዓመት ከማሳሰሩም በላይ እስከ ሕይወት መጨረሻ ድረስ የሚኖሩበትን አድራሻ ማስመዝገብ እንደ ግዴታ ይሆናል (requires a sex offender registration) ። አሜሪካዊ ዜጋ ካልሆኑ ደግሞ ከዚህ አገር መባረርን ያስከትላል። ስለዚህ በሥራ አጋጣሚ፣ ወይንም በምንዝናናበት ጊዜ የሚያጋጥሙንን እድሎች እንጠቀም በሚል ሰበብ የመስማማት ችሎታ የሌላቸው ወይም በመጠጥም ሆነ በአደንዛዥ እጽ ምክንያት የመስማማት ችሎታቸው የደከመባቸው ሰዎች ጋር የሚፈጸም የግብረ ሥጋ ግኙነት እንደ መድፈር ስለሚቆጠር፣ ብዙ ዓመት እስር ብሎም ሎሎች ሕይወትን የሚያውኩ ነገሮች ስለሚያስከትል ከእንደዚያ ዓይነት ድርጊት መቆጠብ ያስፈልጋል።

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ 202 518 0245

P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

12

ታሪክና ሥነፅሁፍ ዓለማየሁ ገ/ሕይወት

በሞት ጉዞ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋራ የሚነበብ አዲስ መፅሐፍ ደራሲ፣ ሃራልድ ናይስተሮም (Harald Nystrom) ተርጓሚዎች፣ ገበየሁ ተፈሪና ደስአለኝ አለሙ

(ክፍል ሁለት)

ምጥን ዳሰሳ - በዓለማየሁ ገ/ሕይወት በክፍል አንድ ዳሰሳችን ስዊድናዊው የህክምና ባለሙያ ዶ/ር ሃራልድ ናይስትሮም በተወልን ታሪካዊ ሰነድ ላይ ተመርኩዘን አንዳንድ ሃሳቦችን ለመሰንዘር ሞክረናል። በዚህም ደራሲው የአይን ምስክርነት የሰጠባቸውን ሁነቶች አንስተናል። በተጨማሪም በመፅሐፉ ውስጥ ጎልተው የወጡትን የደጃዝማች አያሌው ብሩን የቀደመ ታሪክ በአጭሩ ቃኝተናል። በዚህ አጋጣሚ ክፍል አንድን ያነበቡ አንድ የታሪክ ባለሙያ፣ የጠቀስነው ግጥም በዘመኑ “አያሌው ሞኙ፣ ሸዋ አማኙ” ተብሎ የተገጠመ እንደነበርና “ሰው አማኙ” ወደሚለው የተለወጠው ከጊዜ በኋላ መሆኑን ጠቁመውናል። ስለአስተያየታቸው እናመሰግናቸዋለን። ቀደም ባሉ ፅሁፎችም የሸዋ መኳንንት፣ የጎንደር መኳንንት፣ ወዘተ የሚሉ አገላለጾችን መመልከት የተለመደ ነው። ከዚህ ቀጥሎ ወደ ቀሪው የመፅሐፉ ዳሰሳችን እናልፋለን። ደራሲው በክፍል አንድ እንደጠቀስነው ሁሉ በርካታ ጉዳዮችን በእግረመንገድ እያነሳ እሱ የተመለከታቸውን አስገራሚም ሆኑ አሳዛኝ ነገሮች እንድናያቸው ያደርገናል። ለምሳሌ ያህል ስለሰሜን ተራሮችና የተፈጥሮ ገፅታ ከፃፈው፦ “ስለሰሜን ተራሮችና ገደሎች ብዙ ሰምቻለሁ። ነገር ግን በአይን ሲታይ እንደሚሆነው አይደለም። የተራሮቹ አናቶች ጠፍጠፍ ያሉ ሆነው አንድ ሺህ ሜትር ወይም ከዛ በላይ ቁመት ባላቸው ገደሎች ይከፋፈላሉ። የተዘበራረቀ ግን አስገራሚ የሆነ እይታ አላቸው። ያለው ንፁህና ድንግል የተፈጥሮ ውበት ሰውነቴን ወረር እስከሚያደርገኝ ድረስ በአድናቆት ተመለከትኩ። ወደግራ በኩል በግምት ወደ መቶ ኪሎ ሜትር ርቀት በፀሃይ ግባቱ ምክንያት ጠቆር ብሎ 3500 ሜትር ከፍታ ያለው የሚያስፈራው የጠገዴ ተራራ ሰንሰለት ይገኛል። ... በቀኝ በኩል በምትጠልቀው ፀሃይ የመጨረሻ ጮራ ፍንጣቂ ብርሃን ሲመለከቱ የትልቁ የሰሜን ተራራ ጉብታዎች በበረዶ ተሸፍነው ይታያሉ። ሁሉም ነገር የሚያስደንቅ ታላቅ ግርማ ሞገስ አለው። በተፈጥሮ ታላቅነት ምክንያት የትንሽነት ስሜት ተሰማኝ” (ገፅ 18) የሚለው ይገኝበታል። ከዚህም በተጨማሪ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ የመሣሪያ (የጠመንጃ) ባህልና ፍቅር፣ በጦርነቱ ዋዜማ ይደረጉ ስለነበሩት ሺለላና ቀረርቶዎችና ከእምነት ጋር ስለተያያዙ አንዳንድ ጉዳዮችም የታዘበውን ያካፍለናል። ለምሳሌ አንድ ወታደር (አርበኛ) ጠዋት ካደረበት ዛፍ ሥር ሲነቃ በዛፉ ቅርንጫፍ ላይ የተጠመጠመ ነገር ይመለከታል። ከዚያ በኋላ ያለውን ታሪክ ዶክተር ናይስትሮም እንዲህ ያጫውተናል። “... ምን እንደሆነ ለማወቅ ጠጋ ብሎ ሲያይ የተጠመጠመው ነገር መንቀሳቀስ ይጀምራል። ሰውየው ወዲያው ገባውና ከመቅፅበት ጠመንጃውን አንስቶ ዘንዶው ላይ ካርታውን እንዳለ ጨረሰበት። የሞተው ዘንዶ ቁመት ሲለካ ሰባት ሜትር ነበር። በግንድ ላይ አንጠልጥሎ ዘንዶውን ወደ ደጃዝማች ለመውሰድ ስድስት ሰዎች መሸከም ነበረባቸው። የቀኑ ጀግና የተኮሰው ጥይት መጠን ተተክቶለት የሃምሳ ብር ሽልማት ተሰጠው። በተጨማሪም ጥሩ ንግድ ቀናው። የዘንዶውን የጎን አጥንት በአስር ብር ሸጠ። ይህ አጥንት መድሃኒትነት አለው ስለሚባል በጣም ተፈላጊ ነበር። ከመድሃኒትነት በተጨማሪ ደግሞ ለአስማት ይሆናል

ፍቅር ያስይዛል ተብሎ ይታመናል። (ገፅ 64) ደራሲው የሃኪምነት ሥራውን ለመጀመር ወደ ዋናው የጦር ካምፕ ከደረሰ በኋላ አካባቢውን ከመቃኘት በተጨማሪ ህግና ደምቡንም ለማጤን ይሞክራል። ቀን ቀን ሁሉም በየድንኳኑና በየጎጆው ውስጥ እንደሚቀመጥ ከአስራ አንድ ሰዓት በኋላ ግን የጣሊያኖች የአውሮፕላን ድብደባ ስለማያሰጋ እያንዳንዱ ሰው እግሩን ለማፍታታትና የየስራ ድርሻውን ለመወጣት ደፋ ቀና እንደሚል ይናገራል። እንጨት መልቀም፣ ውሃ መቅዳት፣ ለከብቶች ሳር ማጨድ፣ ለሚቀጥለው ቀን የሚሆነውን ምግብ ማዘጋጀትና የመሳሰሉት ተግባራት ማምሻውን መፈፀም አለባቸው። በዚህ የተደራጀ እንቅስቃሴ የተገረመው ሃኪምም ይህን ሁሉ ጥበብ ማን እንዳስተማራቸው ይጠይቃል። “ጀግናው ጌታችን ደጃዝማች አያሌው” የሚል መልስ ተሰጠኝ። “እኛ የምናውቀው ነገር የለም። አውሮፕላን የሚባል ነገር እንኳን ገና አላየንም። ነገር ግን አለቃችን እንደሚያውቁ ስለምናውቅ የታዘዝነውን መፈፀም ነው” (ገፅ 27)። ከራሳቸው ከደጃዝማች አያሌው ጋር ተገናኝቶ ከተወያየ በኋላ ደግሞ ይበልጥ እየወደዳቸውና እያከበራቸው ይሄዳል። ጤንነታቸው በየዕለቱ እየተሻሻለ መሄዱ ያስደስተዋል። የሚመሩትን ጦር ስንቅና ስምሪት በማደራጀትም ረገድ የነበራቸውን ብቃትና ያስገኘላቸውን ተቀባይነት ደጋግሞ ሲያደንቅ እናያለን። “በእኛ ግንባር ምስጋና ለደጃች አያሌው አርቆ ማሰብና ድርጅት ይሁንና ጦሩ የአስፈላጊ ነገሮች እጥረት አላጋጠመውም። ለአምስት አመታት እህል እየሰበሰቡ ተከዜ ወንዝ ጥግ ድረስ ከዝነዋል ... የሳቸው ጦር ከእነዚህ የእህል ካዝናዎች በየሶስት ቀናት ሌላ ዙር ስንቅ ይታደለዋል። የኛ ካምፕ ባለበት አካባቢ ያሉ ገበሬዎች ምንም አይነት ረብሻ እንደማያደርስባቸው ደጃዝማቹ ቃል ገብተውላቸዋል። ... ገበሬዎቹ በጣም ተደሰቱ ... ነገር ግን ደስታቸው ለአጭር ጊዜ ነበር። የራስ እምሩ ጦር ይዞት የመጣውን ስንቅ ጨርሷል። ደጃች አያሌው ደግሞ ከተከዜ ማዶ ካከማቹት እህል እንዲወስዱ ቢጋብዟቸውም ተከዜ ማዶ ሄደው ለመውሰድ ሰንፈው ነበር። በዛ ፋንታ ... የአካባቢውን ገበሬ ቤት መውረርና መመዝበር ጀመረ። ብዙ ጊዜ በገበሬውና በሠራዊቱ መሃል ውጊያ ተደርጎ ብዙ ሰዎች አለቁ። ገበሬዎቹ ግንባር ፈጥረው ንብረታቸውን ከእንዳባጉና በወሰዱዋቸው ጠመንጃዎችና በቀላል አውቶማቲክ መሳሪያዎች ለመከላከል ወስነዋል። ሰላሳ የሚሆኑ የራስ እምሩ ወታደሮች ከሞቱ በሁዋላ ገበሬዎቹ ሰላም አገኙ።” (ገፅ 116) የጣሊያኖቹን የአውሮፕላን ድብደባና የመርዝ ጋዝ ለመቋቋም ያልቻለው ጦር ማፈግፈግ በጀመረበት ጊዜም በበርካታ ቦታዎች ከገበሬዎቹ የበቀል በትር እንደተሰነዘረበት ጨምሮ ገልጾታል። በሌላ በኩል ከእንዳባጉና ድል በኋላ ደጃዝማች አያሌው ወደ ፊት እንዳይገፉ የተደረገባቸው ጫና ስህተት ነበር ብሎ ያምናል፡ ፡ ከንጉሠ ነገሥቱ የተላከላቸው የ’የምሥራች’ ቴሌግራም አዲስ ጥቃት እንዳይሰነዝሩም ያዛል። ይህን ሁኔታ ደራሲው እንዲህ ይገልፀዋል። “ንጉሠ ነገሥቱ ጠቅላላው ምዕራብ ትግራይ በእንዳባጉና ጦርነት ምክንያት

ነፃ እንደወጣ መረጃ ደርሷቸዋል። ሁሉም የጠላት ምሽጎች ተወስደዋል። ኢታሊያኖችም ወደ አክሱም ሸሽተዋል። ያ ሁሉ ሆኖ ባለህበት ቆይ የሚል ትእዛዝ ተላልፏል። ደዳች አያሌው የተረበሹ ይመስላሉ። “የአዲስ አበባ ገዥዎች ምን ማለታቸው ነው?” ይህንን ትእዛዝ ለወታደሮቹ ቢናገሩ አመፅ ይፈጠራል። ባገኙት ድል የተደሰቱት ወታደሮች ወደአክሱምና አድዋ መገስገስ ነው የሚፈልጉት።...ለምንስ አሁን ካውያው እንደጋለ በትኩሱ ጥቃቱ አይቀጥልም? ምን ማለት እችላለሁ? በዚያን ጊዜ ደጃዝማቹ ትክክል እንደነበሩ አውቃለሁ። ዛሬም ቢሆን ሰውየው ትክክል እንደነበሩ በተሻለ ሁኔታ አውቃለሁ። ... እነዚያ ሰዎች ከጦርነቱ ርቀው መናገሻው ከተማው ነው የተቀመጡት። በደንብ መረጃ እያላቸው ነገር ግን በጦር ግንባሩ ተሰልፈው የራሳቸውንም ሆነ የጠላትን አሰላለፍ በደንብ የሚያውቁ ሰዎችን አስተያየት ሳይቀበሉ ትእዛዝ ማስተላለፍ እንችላለን ብለው ያስባሉ። ... ያለምንም ርህራሄ በአፍሪካ የመጨረሻዋን ነፃ ሃገር እጣ ፈንታ ወሰኑ።” በዚህ አጋጣሚ ስለእንዳባጉናው ድል፣ ስለኢትዮጵያውያን ጀግንነትና መስዋዕትነት ደራሲው ከተወልን ማስታወሻ አለፍ አለፍ ብለን ለማቅረብ እንሞክራለን። በደጃዝማች አያሌው የሚታዘዙት ፊታውራሪ ሺፈራው የግንባሩ መሪ ነበሩ። ከአክሱም ርዳታ የመጣለት የጣሊያን ሃይል አስር ታንኮች፣ ሃያ አምስት መትረየሶች፣ አራት የጭነት መኪኖች፣ አንድ አውቶሞቢል፣ መቶ ያህል የጭነት ከብቶች፣ ሰላሳ ግመሎች፣ አንድ ሺህ አምስት መቶ ከኤርትራ የመጡ ባንዶችና አንድ መቶ ሃምሳ ነጮች እንዳሉት መረጃ ይደርሳቸዋል። እናም የጠላትን መንገድ በመዝጋት ምሽጉን ከቦ መያዝ እንደሚገባ ያምናሉ። ታንክ ላይ ዘለው የሚወጡ ቅብጥብጥና ችኩል ሠራዊት የሚመሩት ፊታውራሪ ሺፈራው በጀግንነት እስከወደቁበት ጊዜ ድረስ በጠላት ላይ ከባድ ጉዳት አድርሰውበታል። ደራሲው ስለውጊያው ሂደት ከገለፀበት የሚከተለው ይገኝበታል። “ኢታሊያኖች እንደገና በሁለት ተኩስ መሃከል ተከበቡ። አቢሲኒያኖቹ ከፍታውን ጥሰው ገብተው የተደበቁ ኢታሊያኖችን በሙሉ ገደሉ። ብዙ መኮንኖች አብረው ተገደሉ። የውሃ ጥሙ አስቸጋሪ ሆኖባቸው ወኔያቸው ወደቀ። ሁሉም ጦር ጋራው ላይ ተሰበሰበ። መሳሪያቸውን ጥለው እጃቸውን ወደላይ አነሱ። ይህንን ማድረግ አልነበረባቸውም። ያልሰለጠኑት የእኛ ጀግኖች የእጅ ወደላይ ማንሳት ምልክቱ አልገባቸውም። እንዳውም ጠላትን ለመምታት አጋጣሚ ፈጠረላቸው። የጠፋው ህይወት ትልቅ ነው። በተለይም ፊታውራሪ ሺፈራው ሶስት መቶ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ከፍታ ላይ ከወጡ በኋላ ተኩሱን ያቀልጡት ጀመር። የያዙትን ቀላል አውቶማቲክ መሳሪያ ሲተኩሱ ጥይቱ በተንጣጣ ቁጥር ጎፈሬያቸው ይወዛወዝ ነበር። ኢታሊያኖቹ የፈፀሙት ስህተት ... ገባቸው። ወዲያውኑ ሰንደቅ አላማቸውን አንስተው ከመኮንኖቻቸው ጋራ በመሆን መጮኽ ጀመሩ።” ከፊታውራሪ ሺፈራው ሞት በኋላ የተፈጠረውን ቁጭትና የበቀል ስሜት ደግሞ ደራሲው እንዲህ ይተርከዋል። “በዚህ ጊዜ ፊታውራሪ ነጋሽ እየሮጡ ወረዱ። ከእድሜያቸው ጋራና በንዴት

የሚንቀጠቀጠውን ጎራዴ የያዘውን እጃቸውን ከፍ አድርገው ወደ ላይ አነሱ። “ልጆች!” አሉ በሚንቀጠቀጥ ድምፅ። ሺፈራው አልሞተም! ጠላት እንዳያመልጥ አዟችኋል። ተከተሉኝ” ሰዎች መሰብሰብ ሲጀምሩ አይኑን ጨፍኖ እንደሚሄድ ሰው ወደፊት ገሰገሱ። አምልጠናል ብለው ማሰብ የጀመሩት ኢታልያኖች ከጀርባቸው የጭነት መኪናና ሁለት ታንኮች በያዘ እግረኛ ካምፖኒ የኋላ ጦር ሽፋን አግኝተዋል። ነገር ግን በንዴት እየከነፉ የመጡት አቢሲኒያውያን ደረሱባቸው። መኪናው ወዲያውኑ ተወረረ። በጥቂት ደቂቃዎችም ውስጥ ከጥቅም ውጭ ሆነ፡፡ መኪናው ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ለማዳን ተስፋ በማድረግ ታንኩ ዞሮ መጣ። ወዲያውኑ ፊት ለፊት የነበሩ ሰዎች ታንኩ አናት ላይ ዘለው በመውጣት የታንኩን ሰዎችና ታንኩን ከትቅም ውጭ አደረጓቸው። ሌላኛው ታንክ ራቅ ብሎ ሄዶ ወንዙን ለማቋረጥ በመሞከር ላይ እያለ መሻገሪያው ላይ ሲደርስ ተገለበጠ። ከታንኩ ስር እየተንፏቀቁ ከወጡ በኋላ ለማምለጥ የሞከሩት ሁለት ኢታልያኖች በጥይት ወደቁ።” (ገፅ 85) በአጠቃላይ ሰባት ታንኮችና አራት መኪኖች ሲደመሰሱ አንድ ሌላ መኪና ከነሙሉ ጭነቱ ይማረካል። አንደኛው ታንክ ሲሸሽ የገደል ስንጥቅ ውስጥ በመግባቱ ውስጡ የነበሩት ሁለት ጣሊያኖች ከሁለት ቀናት በኋላ ህይወታቸው ሊተርፍ የቻለው በኢትዮጵያውያን ርዳታ ነበር። ደራሲው ኢትዮጵያውያን ጀግኖች በጦር ግንባር ስለፈፀሟቸው ጀብዱዎች በብዛት ያስነበበን ሲሆን የበለሳው ፊታውራሪ ነጋሽን ቆራጥነትና ወኔ እዚህ ላይ መጥቀስ ይገባል። ብዙ የተታኮሱበት መውዜር ጠመንጃ ከመጋሉ ተነሳ የነከሰባቸውና የአርበኞቻቸው ጥይትም እየተገባደደ መሆኑን የተገነዘቡት ፊታውራሪ የወሰዱት ርምጃ ይህን ይመስላል። “ከዚያም ፊታውራሪ በጩኸት “ልጆች! ከዛፉ ስር የቆመውን ያን ከፍተኛ መኮንን ታያላችሁ? የኔ ነው እንዳትነኩት።” ጠመንጃቸውን ወርውረውና ጎራዴያቸውን መዘው ከወታደሮቻቸው ፊት ለፊት ወደ መኮንኑ ገሰገሱ። ጥይት በዙሪያቸው ይከንፋል፣ ግን ከጉዳይ አልቆጠሩትም። አይናቸው የተተከለው ዛፉ ስር የቆመው ጣልያናዊ ሰው ላይ ነበር። ነጋሽ ለራሳቸው ምንም ሳያስቡ በጠላት ወታደሮች መሃል ሮጡ። አስር ሜትር ብቻ ይቀራቸው ነበር። የጦርነት ጥማቸውን በተመረጠው ሰውየ ደም ሊያረኩ ይሆን? የራሳቸው ወታደሮች ተስፋ የለውም ብለው አሰቡ። ነገር ግን ነጋሽ የነበረውን ችግር አልተቀበሉትም። በዚያች ወቅት ለሳቸው የጠላት ወታደር ሆነ የጠላት ጥይት አልነበረም ሰውየው ብቻ ነው የታያቸው። ጥይቶችም ሊነኩዋቸው የፈለጉ አይመስልም ነበር። ተልኮአቸውን እስኪፈፅሙ ድረስ ሕይወታቸውን ሊጠብቁ የፈለጉ ይመስል ነበር። “ከአላማቸው ትንሽ እስኪቀሩ ድረስ ባለ ጉልበታቸው

እርምጃዎች

ወደ ገጽ 15


13

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

Health Whiplash Matthew J. De Gaetano, DC and John Doe, DC Certified in Personal Injury

Part 1 1. What

is whiplash?

The term “whiplash” is used to describe a variety of neck injuries that often occur in rear-end crashes. The most common of these are mild muscle strain and minor tearing of soft tissue. Other injuries include nerve damage, disk damage and, in the most severe cases, ruptures of ligaments in the neck and fractures of the cervical vertebrae. Nerve damage, which can occur even when other injuries are mild, is probably responsible

for long-term symptoms, such as headaches, dizziness and ringing in the ears. Neck distortion resulting from sudden movement of the head relative to the torso is believed to explain most whiplash. Specifically, hyperextension of the neck, or rearward bending beyond its normal range of motion, likely causes many injuries. People can experience severe crashes with no neck injury if there is little or no movement of the head relative to the torso.

DC This article is sponsored by Painfree Chiropractic & Rehab (Dr. Eden Wubante) 6121 Lincolnia Road, Suite 106 Alexandria, VA 22312 703.270.9020

NHTSA estimated that 272,464 occurred as a result of a rear impact. 4 A 1999 Institute study found that 26 percent of drivers of rear-struck vehicles reported neck injuries to their insurance company. 5 This was about the same as the 24 percent neck injury rate reported in a 1972 Institute study. 6 Estimates of neck injury rates in other studies have ranged from 7 to 37 percent, depending on whether police or motorists reported the information. 7, 8, 9 3. How do head restraints help prevent neck injuries? What many motorists refer to as a headrest is actually a head restraint. These aren’t comfort features, but rather essential safety components like safety belts and airbags. When a vehicle is struck

from the rear it is accelerated forward, causing the seatback to push against the occupant’s torso and propel it forward. An unsupported head lags behind the torso until the neck reaches its limit of distortion. Then the head is suddenly accelerated by the neck much like the tip of a whip; hence the term whiplash. Effective head restraints help move an occupant’s head forward with the body in a rear-end crash and decrease the likelihood of a whiplash injury.

However, experimental and field studies suggest that even slight neck bending that falls well short of hyperextension can cause nerve damage. One hypothesis is that such damage is caused by motion of adjacent neck vertebrae during a crash. 1 Another hypothesis is that it is caused by fluctuation in spinal fluid pressure arising from neck distortions.

As the vehicle accelerates forward from the starting position, the seatback pushes the occupant forward. If the head is unsupported (top sequence), then the neck bends rearward. Eventually the seatback springs forward, pushing the body ahead of the neck during rebound.

2. How common are neck injuries? What kinds of crashes do they occur in?

The majority of studies on whiplash have focused on adult front-seat occupants. Unless otherwise noted, the following facts pertain to people sitting in front.

Neck sprains and strains are the most frequently reported injuries in U.S. insurance claims. In 2007, an estimated 66 percent of all insurance claimants under bodily injury liability coverage and 57 percent under personal injury protection coverage — two important insurance injury coverages — reported minor neck injuries. 3 For 43 and 34 percent of bodily injury liability and personal injury protection claimants, respectively, neck sprains or strains were the most serious injuries reported. The cost of the claims in which neck pain was the most serious injury was about $8.8 billion, representing approximately 25 percent of the total dollars paid for all crash injuries combined. Whiplash injuries can be sustained in any type of crash but occur most often in rear-end collisions. Based on National Automotive Sampling System data, the National Highway Traffic Safety Administration (NHTSA) estimated that there were 805,581 whiplash injuries occurring annually between 1988 and 1996. Of these injuries,

4. What factors influence the severity of neck injury?

Height: According to German research, height is a risk factor for neck injury, particularly among females. 10 Shorter people often are protected by unadjusted head restraints. Stature may not play as big a role in the severity of injuries among males because many head restraints are too low to protect even shorter males. Taller motorists who do not adjust their head restraints are more likely to sustain whiplash injuries. Gender: The same German report found females to be 1.8 to 2.2 times more at risk of neck injury in all types of collisions, a finding consistent with research by the Institute and other organizations. A Swedish study found that females with whiplash injuries were more likely to develop long-term symptoms. 11 Fifty-five percent of females who sustained whiplash injuries went on to develop longterm symptoms compared with 38 percent of males. The risk of disability for drivers has been shown to be 3 times as high for females as for males; in rear seats,

females’ risk is 4 times as high. 12 One possible explanation is that males have more neck musculature than females for about the same size head. The Institute studied insurance data and found female drivers in a rear-end crash were more likely than male drivers to report a neck injury. 5, 13 Seating position: It is uncertain which seating position exposes an occupant to the greatest chance of neck injury. One study concluded that drivers have a higher risk of injury than passengers. 14 It was hypothesized that drivers are prone to move forward and away from the seatback as they reach for the steering wheel and observe traffic around them, whereas passengers usually are more relaxed and lean further back in

their seats, with their heads closer to the restraint. Research studies are inconsistent in their findings of neck injury risk for front and rear seat passengers. One study found that rear-seat passengers are less likely than front-seat occupants to sustain neck injuries. 14 Another study found that the risk of neck injury among females was lowest in the front passenger seat and significantly higher in the rear. 12 The same study found that injury risk for males was higher in the front seat than in the rear seat. Vehicle size/weight: The size and weight of the struck and striking vehicles may influence neck injury risk. A study of insurance claims found that drivers struck by vehicles heavier than the one they were driving were more likely to claim neck injuries than drivers struck by vehicles of approximately equal or lesser weight. 13 Drivers of rear-struck cars were more likely to claim a neck injury than drivers of rear-struck SUVs. Seat/head restraint geometry: Restraints can be classified into one of four geometric zones defined by their height and backset (distance from the back of the head to the front of the restraint). Based on these factors, the Institute assigns ratings of good, acceptable, marginal or poor. Institute research has shown that vehicles with geometric head restraints rated good have 24 percent lower driver neck injury rates than vehicles with restraints rated poor.

Mamadou Samba was appointed by Mayor Muriel Bowser in January 2015 to serve as the Director of the Mayor’s Office of African Affairs (OAA). Originally

from Dakar, Senegal, Mamadou was a former Commissioner of the DC Commission on African Affairs, a role in which he served as a strong advocate for diverse African diaspora communities. Mamadou, has extensive experience in addressing challenges faced by African immigrants in the District and nationwide. He played a significant role in securing grants for African nonprofit organizations, highlighting issues impacting Africanborn residents in the United States. He also partnered with community groups to develop capacity building, provide cultural sensitivity training, and facilitate education outreach programs to illuminate complex issues, including the negative impact of stereotypes and social stigma. In 2011 Mamadou was one of six out of nearly 100 candidates selected to join the Capital City Fellows program a mayoral initiative to attract and recruit graduate students to work for the District. As a Fellow, he rotated among several agencies, including the Office of the Chief Financial Officer, the Department of General Services, and the Office on African Affairs, where he served as the agency’s Public

Mamadou Samba, Director, Office on African Affairs

Information Officer. While at OAA, he researched and compiled the District’s first-ever report highlighting African immigrant population growth since the 1960s, highlighting accomplishments and socio-economic challenges and proposing policy recommendations based on the needs of diverse African communities. Prior to his appointment, Mamadou worked as a Capital Budget Administration Analyst in the Office of the Chief Financial Officer, where he was primarily responsible for the formulation and execution of the District’s seven billion dollar Capital Improvements Plan. He specifically oversaw the District Department of Transportation’s (DDOT) capital budget in excess of three hundred million dollars annually, including local and highway trust funds. Mamadou earned a Master of Public Administration degree from Kennesaw State University, and a Bachelor Degree in Political Science from the University of South Carolina Aiken, where he was awarded an NCAA athletic scholarship. He is fluent in French and Wolof. (Source OAA).

Eritrean Catholics to get their own Church in break with Ethiopians Pope Francis has established a new Eastern Catholic Church for Eritrea, the first since the early 20th century, in what may be a move to ease the position of Catholics in the country. Roman Catholicism is one of the four religions tolerated in Eritrea, along with the Eritrean Orthodox Tewahedo Church, the Evangelical Lutheran church and Islam. Until now, the four Eritrean ‘eparchies’, or dioceses, have been part of the Ethiopian Catholic Church. However, the Vatican announced on last week that they will now come under the authority of an Eritrean metropolitan archbishop, the present Bishop of Asmara, Menghesteab Tesfamariam.

Ethiopian icon exhibit in Clinton "The Vibrant Art and Storied History of Ethiopian Icons" is a new exhibition at The Museum of Russian Icons, 203 Union St., Clinton, that features 60 icons and artifacts from a private European collection. The dates of the icons and objects, which will be on view Jan. 23 through April 18, range from the 16th century to the present. Ethiopian iconography is closely related to the simplified Coptic version of Late Antique and Byzantine Christian art. It is typified by stylized, graphically bold figures with large, almond-shaped eyes. Colors are usually bright and vivid. The majority of paintings are religious in nature, often decorating church walls and Bibles. The museum's own collection of Ethiopian icons, stone-carved triptychs and sacred objects will also be on display. Free to members and with museum admission ($10; seniors $7; students $5; children $5; children younger than 3, free). www.museumofrussianicons.org

in the next issues 5. Do head restraints have to meet government standards? 6. How should my head restraint be positioned? 7. Where do I find information about which vehicles have better head restraints? 8. Do newer vehicles have better head restraints than older ones? 9. Are the Institute's head restraint ratings reflected in realworld crashes?

Ethiopian court jails three Britons over terror charges An Ethiopian court last week handed down prison terms to three British citizens convicted on terrorism-related charges.

Sources at the ministry of justice told Sudan Tribune on Monday that the three Britons were conspiring to carry out terrorist attacks and to eventually overthrow the government in collaboration with the Oromo Liberation Front (OLF), an exiled Ethiopian rebel group designated by Addis Ababa as a terrorist entity. According to the federal

high court, the trio had links to local members of a jihadist group seeking to turn the Horn of Africa nation into an Islamic state. The court sentenced Ali Adorus to four-and— half years in jail, while Mohammed Sharif and Mohamad Ahmed each received jail terms of six years and eight months. (ST)


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

አማርኛና ብሔር ብሔረ ጠቦች! ዝምታ ይሻላል መጻፍ??? ከጻፉ ደግሞ እንደወረደ ቢለቁት ግሩም ነበር..... ሰው ከሰውጋር ሲቀመጥ ነው እንጂ ከራሱ ጋር ሲቀመጥ ደስ ይላል። ሰው የመሆን ትርፏ ይቺ ናት! አቤት አማርኛ! እንደምን ደስ ይላል። ይቺ ኢትዮጵያ የምትባል ባልቴት አማርኛን ባትሰጠኝ ምን ይውጠኝ ነበር። “ሰው ያለውን ነው የሚሰጠው ..”...ትላለች ባማርኛ! አማርኛ ጥሩ ነገር ነው። “አማራ አለ ወይስ የለም?” የሚያስብል የመከራከሪያ ቋንቋ ነው። እኛ እነገሌዎችም አማሮች እንዴት እንደጨቆኑን የምንናገረው በአማርኛ ነው። እኛ ጎንደሮች ከጎጃሞች ስለመሻላችን ጎጃሞችም ከጎንደሮች ስለመብለጣችን የምናወራው በአማርኛ ነው። ሸዋ “ምነው ሸዋ!” የሚለው በአማርኛ ነው። ጉራጌም አማራን የሚያቄለው በአማርኛ ነው። ኦሮሞው ደራሲ በአማርኛ የጻፈው ሥነጸሁፍና የተቀኘው ቅኔ ለአማራው አማርኛ ማስተማሪያ ይሆናል። የትግሬውና ኤርትሬው መለስ ዜናዊ “ራዕይ” የተገለጠው በአማርኛ ነው። መለስ ከጠመንጃቸው በላይ ኢትዮጵያን የገዙት በአማርኛቸው ጭምር መሆኑን በአማርኛ መከራከር ይቻላል። በትግርኛ ሞተው በአማርኛ ተለቀሰላቸው። ኤርትሬዎቹም ከአማርኛ ቢገነጠሉም አማርኛ ከነሱ አልተገነጠለም። ይኸው ቴዲ አፍሮ አዲስ አበባ ተቀምጦ አስመራ ላይ ይዘፍናል። አማራ ይጠላሉ የሚባሉት ስብሐት ነጋ እንኳ “አማራ ገዢ መደብ” የሚሉትን ለመዋጋትና አከርካሪውን ለመስበር፣ ጫካ ከመሄዳቸው በፊት ሸዋ ወርደው፣ ሰላሌና ደብረብርሃን ላይ የአማርኛ አስተማሪ ነበሩ። አስተማሪው ትግሬ፣ ተማሪው ኦሮሞ፣ ትምህርቱ አማርኛ። ድንቅ አገር....! እርግጥ አማርኛ የሁሉም የአፍ መፍቻ ቋንቋ ቢሆን ኖሮ፣ ማይሙም ማይም፣ ሊቁም ሊቅ መሆኑ ይለይ ነበር። አማርኛ አስተካክሎ መናገር የማይችል የማንትስ ብሔረሰብ ተወላጅ የሆነ ፕሮፈሰር፣ አፉን በአማርኛ ካልፈታ ማይም መስሎ ይታያል። አማርኛን የሚያቀለጣጥፈውና በአማርኛ ጥበብን ሳይሆን አፉን ብቻ የፈታ ጉግማንጉግ ሁሉ እየተነሳ፣ ተኮፍሶ ሊቅ መምሰሉም ስለ አማርኛው ነው። የአማርኛ ሙት ጎኑ ይህ ነው። የሌላው ብሔረሰብ ሰው በቋንቋው በመናገሩ ብቻ ጎሰኛ መስሎ ሲታይ፣ አማርኛ ስር የተሸሸገው ምድረ መንደርተኛ ጎሰኛና ክፍለሀገርተኛ ግን አማርኛው ደብቆለት አያስታውቅበትም። ልክ በዘመናችን ትግሬነት ብቻውን ፕሮፌሽን ሆኖ እንጀራ የሆናቸው፣ ማዕረግ ሆኖ ጄኔራል ያደረጋቸው፣ ቀፎዎች እንዳሉ ሁሉ፣ አማራና አማርኛ ብቻውን ኢትዮጵያዊነት የመሰላቸው ግብዞችም አሉ። ሌላው ቋንቋ ባዕድ ያደረጋቸው ሰለዜግነታቸው የተጠረጠሩ ኢትዮጵያውያንም የሉም ማለት አይቻልም። ይቺ ስቃይ ኢትዮጵያ ውስጥ መኖሯን አማርኛ አይሸሽግም። አንድ ምሁር ከየትኛውም ዩኒቨርስቲ ዲግሪ ቢኖረው የትኛውንም ችሎታና ተሰጥኦው ቢቸረው፣ አማርኛ ከጎደለው ምናምኒት እንደጎደለው ተደርጎ መወሰዱ ግልጽና አለመታደል ነው። አማርኛኮ በራሱ ቋንቋ ነው እንጂ እውቀትና ዜግነት አይደለም። ዛሬ እንዲህ ጥንቡን ሊጥል “አቤት እገሌ እንዴት ያለ አዋቂ ነው ፣የሚናገረው እንግሊዝኛ እኮ..!” ይባል ነበር ድሮ። እንግሊዝኛ ብቻውን እውቀት በመሰለበት ዘመን ስንት ሰው በእንግሊዝኛ ለመናደድ ይጣደፍ ነበር። አማርኛም ብቻውን እውቀት፣ አንዳንዴም አልፎ ተርፎ ኢትዮጵያዊነት እየመሰለ ስንቱን አጃጅሏል። አሜሪካን አገር እንግሊዝኛ መልመድ ግዴታ ባይሆን እንኳ አስፈላጊ ነገር ነው። የእንግሊዝኛው እንግሊዝኝነት ግን እንደ ቋንቋ እንጂ እንደ አሜሪካዊነት አይታሰብም። አማርኛም እንደ ቋንቋነት እንጂ እንደ ኢትዮጵያዊነት መታሰብ አልነበረበትም። በእንግሊዝኛ አፉን ያልፈታ አሜሪካዊ ብዙ ነው። ወላጆቹ ከሜክስኮ ከቻይና ወይ ኮሪያና ሶሪያ ሊሆኑ ይችላሉ። ጥልያንም ህንድም አይሁድም ቢሆኑም ያው ነው። አሜሪካዊነታቸው ላይ አይደራደሩም። እንግሊዝኛ እንደሚያስፈልጋቸው ያውቁታል። ቋንቋው አስተሳሳሪያቸው ነው። ስለዚህ ራሳቸው የልጆቻቸው አፍ መፍቻ ያደርጉታል። ምነው ለኛም እንዲሁ በሆነ! አማርኛ አለመቻል የነጻ አውጭ

አማርኛ ብዛት ሲቀፈቅፍብን ከሚያድር በአንድ ስሙ ሁሉም አፉን ቢፈታበት የታሰርነበት ገመድ ይፈታ ነበር።

አማራው በሌለበት ትግሬውና ሶማሌው ተቀምጠው አማራውን የሚያሙበት ቋንቋ መሆኑ የግድ ከሆነ፣ በአንድ ስሙ አማርኛን ከዳር እስከዳር የኢትዮጵያ ቋንቋ አድርጎ (ለነገሩ አሁንም ድርቅና ነው እንጂ አይተናነስም) የሚገላገሉትን ወዲያ መገላገል ነበር። ምንም አይሰራም ይሄ ሁሉ የቋንቋ ብዛት የአሳብ ጥራት አያመጣም። ሁለት አማሮች እንኳ በአንድ አማርኛ እየተነጋገሩ መግባባት አልቻሉም። ትግርኛም አገዳደለ፣ አነቃቀለ እንጂ ትግራይ ትግርኞችን ሀማሴንና አጋሜን እየሆነ አላስማም። ብሔራዊ ቋንቋችንም ራሱ ወይ ይዘነው አልያዝነው ወይ ጥለነው አልጣነው ነገር ሆኖብን ይሄው እየተግባባንበት አይደለም። ስለዚህ 70ና 80 ቋንቋ ኮተት ነው። የማንነት ኮተት! ለአንዲት ድሃ አገር ይህ ሁሉ ኮተት መዘዙ ብዙ ነው። ሁሉንም ላበልጽገው ቢሉት ብዙ ነገርና ብዙ ገንዘብ ይመዘዝበታል። የበላይነትና የበታችነት ስሜት እየፈጠረ ገዛሁ፣ ተገዛሁ፣ ኮራሁ፣ ተናቅሁ.. የሚል ንጭንጭ ያበዛል። ሳር ቅጠሉ እየተነሳ ነጻ አውጪ ይሆንበታል። ኢትዮጵያኮ ከምትሰጠው ነጻነት ስጪኝ የምትባለው ነጻነት ይበልጣል። የገንዘብ ደሃ ብቻ ሳትሆን የነጻነትም ድሃ ናት። የማትሰጠውኮ ስላልፈለገች ብቻ ሳይሆን

ስለሌላት ነው። ለስንቱ ስጥታ ትችላለች። አንዱ ቋንቋዬን፣ አንዱ ሃይማኖቴን፣ አንዱ ጎሳዬን፣ አንዱ ጾታዬን፣ አንዱ ክልሌን.... አቤት የተነጫናጩ ብዛት! ምነው እነ መንግሥቱ፣ እነ መለስ፣ አምባገነን መሆናቸው ካልቀረ ይህን ውለታ የጣሉልን አምባገነኖች ቢሆኑ ጥሩ ነበር። ወዲያ ሁልሽንም ጠራርጎ ወይ ከትልቁ አማርኛን፣ ወይም ኦሮምኛን ትግርኛን ወይ ከትንሹ ጎርባጎኛን፣ ወይ አዶርባኛን ብቻ አንዱን ቋንቋ ወዲያ መርጦ የኢትዮጵያ ቋንቋ አድርጎ፣ በቃ አዳሜ አርፈሽ አንድ ቋንቋ ተናገሪ! አንድ ባንዲራ ስቀዪ፣ ካሁን በኋላ ፊትሽን ወደ ሚጠቅምሽ ድህነት ምናምንሽ አዙሪ ነጭናጫ ሁላ!... ማለት ቢችሉ ደግ ነበር። ብሄር ብሄረ ጸብ ፣ ጎሳ ጉስጎሳ፣ ሺ ቢያሰማምሩት ሲያወሩት ያምራል እንጂ ሲያደርጉት ያስጠላል። ያገዳድላል። በየአገሩ በዝቶ የምናየው ይኸው ነው። ተጨቆንኩ ባሉ ጊዜ የሚያራምዱት ሀሳብ ገዢ በሆኑ ጊዜ ይቃወሙታል። ጫካ ሲሆኑ መንገንጠል መተርተር ከተማ ሲገቡ አንድነት ባንዲራ ህብረ ብሔር ድህነት ልማት ያስብላል። መብትነቱ ግን መብት ይሁን። ማንም ያሻውን ይናገር። ቢፈልግ ኢትዮጵያችሁ ገደል ትግባ ማለት መብት ነው። የዚያኑ ያህልም ጎሰኝነታችሁም የድንቁርና ነው ማለትም መብት ነው። ስለጎሎባላይዜሽን ሲያስተምር የዋለ የሓርቫርድ ፕሮፌሰር ማታ ቤቱ ገብቶ ስለጎሳው ነጻነት ብቻ ኢንተርኔት ላይ የሚጽፍ ከሆነ ችግር ነው። ምኒልክ ለሠሩት የአማራው ገበሬ ተጠያቂ ነው ካለ ምኑን ተማረው? ከክርስቶስ ልደት በፊት የተሠራብኝ ግፍ ይርመርልኝ ማለት ሥራ መፍታት ብቻ ሳይሆን እውቀት መፍታትም ነው። የቅድም አያቶቼ ቋንቋ ምነው አማርኛ ባልሆነ ተብሎ ማልቀስ እስኪያምር ድረስ የነጋ ጠባው ንዝንዝ ይሰለቻል። አማራና አማርኛ እኔን ከስደት፣ ቻላቸውን ከውርደት፣ አምባቸውን ከግብርና፣ አስናቁን ከግርድና፣ ያስቀረ ይመስል ይሄም ያም እየተነሳ ጥራዝ ነጠቅ አገር ነጠቅ እየሆነ... ፌደራሊዝም ገዢ መደብ... ምንትስ እያለ....

ምነ ጃል! አማርኛኮ በደቡብ ብሄራዊ ቋንቋ ነው። አዋሶቹ ከተሞች እያማሩበት፣ አማሮቹ ገበሬዎች ግን ከደቡብ ተባረው እየወጡበት ነው። ጓንጉል ከቤንሻንጉል ተባሮ ሲነቀል ትዕዛዙ የተሰጠው በአማርኛ ነው። አማርኛን ወዶ አማራውን መጥላት በአማርኛ እንዴት ተብሎ ይገለጻል? ብልጦቹ ጎሰኞች ግን አሁን ገብቷቸዋል። አማራን በአማርኛ እየተዋጉ፣ አማራ ይመካበታል የሚሉትን መገለጫዎቹን እየወሰዱ ቀዳዳዎቻቸውን እየደፈኑበት ነው። አንድነታውያን የሚሏቸውን በሽብርተኝነት እያወገዙ እነሱ አንድነታውያን፣ ባንዲራውያን፣ ዳር ድንበራውያን፣ አባይና ግድባውያን እየመሰሉበት ነው። ፣ አማርኛ ጫካ ሆነው የሚዋጉት፣ ቤተመንግሥት ሲገቡ ደግሞ የሚሞቱለት ቋንቋ መሆኑም እየታየ ይመስላል። ኦነግ እንኳ የሽግግሩና መንግሥት አባል በሆነ ጊዜ አማርኛን ሊሠራበት ከተመቸም ሊበላበት ከማዕድ ተቀምጦ ነበር። ኦሮምኛን በአማርኛ ነጻ ሊያወጣ ማለት ነው። እግዜር አልፈቅድ አለ እንጂ ሥልጣኒቱን መጠቅለል ችሎ ቢሆን ኖሮ የሶማሌውና የሐዲያው ነገር ኦነግን ራሱ አማርኛ ተናጋሪ ያደርገው ነበር። በምን ይግባባቸዋል? የኦሮሞ ልጆች ፌደራል ቋንቋን ትተው ከፌዴራል ሥራ ሲነጠሉ ማየት በደል እንጂ ድል አይደለም። አገር ሁሉ ገና ለገና ቅቤና ቁቤ ጠጥቶ ለውጥ አምጥቶ ኦሮምያ ኦሮምሽክን

ኦሮሚቲ ተገንብቶ እናያለን ማለት ሲያልሙት ይጣፍጣል። እንዲህ የሚሉትን ኦሮሞዎች ሁሉ አስረን ወይም በፀረ ኢትዮጵያዊነት ወንጅለን አንገት አስደፍተን በነሱ መቃብር ላይ ኢትዮጵያን እንገነባለን ማለትም ሲያስቡት ይጣፍጣል። ምናለ እብድና ዘመናይ ያሻውን ይናገራል እያሉ ዝም ነው። ገዳይ አገዳዳይ ሀሳብ ሁሌም ደንቡ ነው እየጣፈጠ ይወስዳል። ኦሮምያ መፎከሪያ- ትግራዋይ መበቀያኢትዮጵያነት ማስፈራሪያ እየሆነ ዝምበል አትናገር በአድማ ትደፈጣጠለህ በፍረጃ ትፈጠፈጣለህ ከተባለ ግን ዝም ነው እንጂ ምን ይባላል? ይልቅ ይህን የማንነት ጅልነት ወዲያ ትቶ 80ውን ቋንቋ ወዲያ ጨፋላልቆና አቅልጦ አንድ አለት የሚወጣው ወርቅ ማውጣት ፈውስ በሆነ ነበር። ቢቻልማ የግድ አማርኛ መሆን አይገባውም። ሸከቾም ሞርቾም ጋጎም ዳዳም... ይሁን ብቻ ኢትዮጵያውያንን አንድ የሚያደርገን አንድ ቋንቋ ተጠንቶና ተመርጦ ቢወጣ ሁሉም ሰው እሱን አጥንቶ አገር አንድ ልሳን ይኖራት ነበር። ካልሆነ ግን አማርኛን እየወደዱ አማሮችን እየጠሉ ፖለቲካ ለገዢም ሆነ ተገዢ ማስቸገሩ አይቀርም። ቋንቋ ሁሉ እኮ ዝምብሎ አፍ ስለተፈታበት ወንዝ አያሻግርም። ጥበብ፣ እውቀት፣ ሳይንስ፣ ታሪክ፣ ፖለቲካና ነገረ መለኮት ካልተፈታበት አንደኛ ክፍል ላይ የተፈታው አፍ፣ ሶስተኛ ክፍል ላይ መልሶ መያዝ መለጎሙ አይቀርም። ሆኖም እያየነው ነው። ስለሆነም ሁሉም ሰው አፉን በአማርኛ ቢፈታ፣ ይሄ ሁሉም እየተነሳ የሚነጫነጭበት አማራም እረፍት ያገኝ ነበር። እባክህ አማርኛ ሌሎችም አፋቸውን ይፍቱብህና አንተም አገርም ዳኑ! እንኳን የፈቱብህ ያልፈቱብህ ይተኩሱህ! ተነሳ ታጠቅ ዝመት ተዋጋ አማርኛ! ስንጽሑፍህን ምዘዘው፣ ቅኔንህ ለስሜት ዝረፈው! በሙዚቃህ አገርን አርገፈው! ጥላሁን ገሠሠ ያዚምህ፣ ሳህሌ ደጋጎ ይሞዝቅህ፣ መሀሙድ አህሙድ አቻ ገዳዎ ይበልብህ! ተው አማርኛ ሆይ አማልደኝ እባክህ! የአማርኛ ታሪክ ጸሐፊዎችን እነ ላጲሶን ጋዴቦን እነ ኢጆሌ አምቦ ሎሬት ባለቅኔዎችን እነ ጸጋዬ ገ/መድህን

ቀዊሳን አፋቸውን በኦሮምኛ የፈቱትን እነ በዓሉ ግርማን ጥራቸው። ለመጀመሪያ ጊዜ “ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚል ቃል ፈጣሪ የሆኑ አባት ጋዜጠኞችን እነ ከበደ አኒሳን አንሳቸው፣ የጦርና የጥበብ ፊታውራሪዎችን እነ አባመላ ሀ/ጊዮርጊስ ዲነግዴን እነ ባልቻ አባ ነፍሶን አንድ በአንድ ዘርዝራቸው! እነ አብዲሣ አጋን አምጣቸው! ወደ አበደው ዘመንም ደግሞ ከፈለግክ ምጣ። የመለስ ዜናዊን የእብሪትና እብለት አንደበት እንኳ ያጣፈጥክ አማርኛ፣ የአባዱላን በፓርላማ መዶሻ ያስቀወርክ አማርኛ፣ ኃይለማርያም ሰለጠቅላይ ሚኒስትርነቴ “ደስ አለኝ” ያለበት አማርኛ፣ ብርሃኑ ነጋ አንቺ ወያኔ መንጋጋ መንጋጋሽን እላለሁ ያለበት አማርኛ፣ ነጋሦ በቤተመንግሥት ነግሦ የታየበት አማርኛ፣ ገብሩ አስራት የትግራዮችን ታሪክ የጻፈበት አማርኛ ድንቅ ነው። ወጣቱ ጁሃር አማርኛን በአማርኛ ሲዋጋ፣ ሜጫውን ዋሽንት አስመስሎ ጩኸቱን ሲያጣፍጠው ተመልከተው! አፈንዲ ሙተቂ የሚባል ጣፋጭ ብላቴና፣ ያለ እድሜው በስሎ አገር ለማስታረቅ ሽማግሌዎቹን ሲሸመግል፣ ሙስሊሙን ክርስቲያን ክርስቲያኑን ሙስሊም ሲያደርግ አማርኛውን ፍቅር አድርጎት ነው። የስንቱን ገጣሚና ባለቅኔ እውቀት አማርኛም ጭምር እንጂ ፊዚክስ ብቻውን አልወለደውም። እንኳን ስታፋቅር ስታጣላ ስታባላ ስታጋድል እንኳ

አማርኛዬ ደስ ትላለህ። አማርኛ! አማርኛ! አማርኛ! አማርኛ! አገር ማለት አንተ ነህ። በፌስቡኩ ዓለም እንኳ እንዳሻህ ትርመሰመሳለህ። በመለስ ዜናዊም፣ በኃ/ማርያም ደሳለኝም፣ በብርሃኑ ነጋም፣ በሌንጮ ለታም በገብሩ አስራትም በብርቱካን ሚደቅሳም በኦባንግ ሳይቀር በሁላቸውም አንደበት ሰማንህ ከእነዚህ አንዳቸውም ቢሆኑ አማራ አይደሉም። ከቤንሻንጉል ከተፈናቀለው አማራው ጓንጉል ጋር የሥጋ ዝምድና የላቸውም! ለነገሩኮ ልዩነታቸው ቋንቋ ነው እንጂ ደም አይደለም። ኢትዮጵያዊነት ደግሞ ከደም በላይ ነው። የባራክ ኦባማ አባት ኬንያዊ መሆኑ ለዚህ ዘመን የተላከ ታላቅ ትምህርት ነው። የማንዴላ ሞት ክብረቱ ከጎጥና ጎሳ አልፎ ዘርና ቀለም ሳይቀር ተዋህደው የሚኖሩባት አገር መፍጠሩ ነው። አንድ እንሁን የሚለውን ሀሳብ ዝምብሎ ጨፍልቆ ማናናቅ ደግ አይደለም። ኦሮሞችን ትግሮችን ህዳጣኖችን ማንትሶችን ተንከባከቧቸው እንደ እንቁላል ያዟቸው መባልም ሲበዛ ይሰለቻል። አገርና ህይወት የማንነት ቁስለኞችን ሲንከባከቡ ተወልዶ አድጎ መሞት ብቻ ከሆነ ይሰለቻል። ኤጭ አሁንስ በዛ የማንነት ጥያቄ ጥንቡን ጣለ ለማለትም ጊዜ አለው! መነገጃም መሸወጃም አንገት ማስደፊያም ማስፈራሪያም ሆነ ለማለት ጊዜ አለው። በቃ ጎሰኛ የሆንክ ሁሉ ገደል ግባ ብሎ ምን አባክ ላድርግህ ለማለትም ጊዜ አለው። ስድብ ፍራቻ ስድብ ጥላቻ ስድብ እየጠጡ ንቀት እየገመጡ መኖርም የሚመርበት ቀን አለው። አገራችን አማርኛችን ከሆነ ይህን ሊገልጸው ይገባል። አማርኛምኮ አንዳንዴ ያበዛዋል! ይሉኝታም ያጠቃዋል መሰል አፍርጦ አፍረጥርጦ አይናገርም። አካፋን አካፋ አይልም። ጎሰኝነት ጎሰኝነት ነው። አንዱ ላይ አስጠልቶ ሌላው ላይ አያምርም። ሌላው ላይ ካማረ ሁሉም ላይ ማማር ይኖርበታል። አንድ አገር ውስጥ አንድ ሺ ቋንቋ ሊኖር ይችላል። መብት ዴሞክራሲ ፍልስፍና ቲዮሪ ማንነት ቅብጥርስ እያሉም አርባውን ምክንያት መደረደር ይቻላል። ያንን ሀሳብ የሚያራምዱ ሰዎች ያለማንም

14

ፈቅድ በራሳቸው ፍላጎትና ትግል ሊኖሩ ይችላሉ። እነሱን መከልከል አይቻልም። አይቻልም ብቻ ሳይሆን ክልከላውም መታሰብ የለበትም። የማይከለከለው ግን ልክና መብት ስለሆነ ብቻ ሳይሆን ክልከላ ራሱ በመሠረቱ ልክ ስላልሆነ ነው። ይሄ ነገር ልክ አይደለም የምንል ወገኖች ግን ሀሳባችንን በአማርኛችን የማቅረብ መብት እንዳለን መግለጽ ይኖርብናል። አማርኛ ለኛ የጋራ ማንነት አስተሳሳሪያችን ብቻ ሳይሆን ኢኮኖሚክስ ነው። ታሪክ ነው። ፖለቲካችን ዜማችን ዜናችን ስነጽሑፋችን ነው! ተዘምቶበት ያልጠፋ፣ ቢያሰተኙት ያላንቀላፋ፣ ቢያቀጭጩት የፋፋ እንዲያውም ከሌላውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ እየሆነ የመጣ ነገር ነው! .... ተሞክሮ- ተግዳሮት- ዘውግ- ሙስናልማታዊ....ይባልልኛል! እንደ ፕሮፌሰር መስፍን አማርኛን ሲችሉበት ሀሳብን እንደ ሸማኔ ፈትል ያደሩበታል፣ እውቀትን እንደ ጠጅ ያንደቀድቁበታል፣ ንዴትን እንደ ብራቅ ያጩኹበታል፣ታሪክ ፍልስፍናን እንደማር ያጣፍጡበታል። ወልደ ማርያሙ መስፍን እንደ ወልደ ማያርሙ ድምጹን በምድረ በዳ ከፍ አድርጎ ይጮኻል። ኢትዮጵያዊነት ቀርባለችና ንሰሃ ግቡ ይላል። አማራ የለም ብሎ ኢትዮጵያዊነትን አብርቶ አማራነትን በአማርኛ የማጥፋቱ ሚስጥር ይኸው ነው። ቋንቋው ውስጥ የተሸሸገው ሚስጥር ተገልጦለት ይሆናል። ስለዚህ አማራው ቢጠፋ እንኳ አማርኛው አለ። ምክንያቱም አማራው የለም የተባለው በአማርኛ ነው። የለም አማሮችማ አሉ የተባለውም በአማርኛ ነው። “አዎ አለን እንጂ ያውም እየተሰደድንም እየተፈናቀልንም ቢሆን አለን!” ተብሎ የተደራጁትም በአማርኛ ነው። ግን መአህድ ብለው ይጀምሩና መኢአድ ሆነው ያልቃሉ። ለአንድነቶች እንደመታደልም ለጎሰኞች እንዳለመታደልም ሆኖ አማራና ኢትዮጵያዊነት ተጣብቆ መታየቱም ለዚህ ነው። እንኳን አማራው ወላይታው ኃይለማርያም፣ ትግሬው ደብረጽዮን፣ ኦሮሞዋ አስቴር ማሞ የሚያወሩት በአማርኛ ነው። ያውም በዚህ ነጻ ወጥተናል ብለው በሚፈነጩበት ዘመን ተገደው ሳይሆን መርጠው የሚያደርጉት ነው። አማርኛ መናገርኮ ለአማሮች የተዋለ ውለታ አይደለም። አማራ በሌለበት ቦታ ሁሉ ሰዎች ለገዛ ጥቅማቸው ሲሉ የሚገለገሉበት ቋንቋ ሆኗል። ይህን ጥቅም በግዴታ የጫነብኝ ማነው? ይህን ያደረገው ለፍርድ ይቅረብ፣ ሐውልቱም ይነቀል ማለት መብት ሊሆን ይችላል። መብት ሁሉ ያምራል ያለ ግን ማነው? በራሴ ቋንቋ ላውራ ማለቱም ቢሆን ብቻውን አያምርም። ቁምነገሩ ከቋንቋው ሳይሆን ከሀሳቡ ነው። ማንነትኮ ቋንቋ ብቻ አይደለም አስተሳሰብም ጭምር ነው። እንግሊዝኛውን በእሳተ ገሞራ አክሰንት እያስኬድነው ተቀንባረን በምንኖርበት አገር ምን እየተማርን ነው? የአንዳችን አፍ ላንዳችን በመኮለታተፉ ምክንያት መገዳደል አለብን? ያንተ ሆድ ይከፋል የኔ ይሰፋል እኔ አፌን በአማርኛ ልፍታ እንጂ ሌላው እንዲገደድ አላደረግኩም። ይህ እንዴት እንደሆነም አላውቅም። እንዴ አሁንስ ቢሆን ምን አውቃለሁ? በምንጅላት እንጃላት... ቅድመ አያት አያቶቼ አዳምና ሔዋን ጥፋት መቀጣቴ አንሶ፣ ደግሞ ዳግማዊ ቀዳማዊ የሚባልብኝ ለምንድነው? ምን ይፈጠር ነው? አማራን ጨምሮ ኢትዮጵያዊ ውስጥ ካሉት 80 ብሔር ብሔረ ጠቦች ካንዱም አይደለሁም። ባባቴ ደረጀ በናቴ ደስታኝ ! አፌን ብቻ ሳይሆን ዜግነቴንም የፈታሁት ግን በኢትዮጵያዊነት ነው። ለየብቻችሁ እንደፍርጥርጣችሁ ሁኑ እኔጋ ስትመጡ ግን ዘብሔረ ኢትዮጵያ ነኝ። ዘኢትዮጵያ! ደ.ደ

ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ 202 518 0245

P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

በሞት ጉዞ ከገጽ 12 ወደፊት ተወረወሩ። አሁን ግን ዛፉ ስር ያለው ሰው ወደሱ የመጣውን ጥቃት ተመልክቷል። ወዲያውኑ ሽጉጡን መዘዘ። ነገር ግን ዘግይቷል። በድንጋጤ የፈዘዙት ጣቶቹ የሽጉጡን ምላጭ ሙሉ በሙሉ ከመሳባቸው በፊት በጀግና እጅ የሚወዛወዝ ደም የጠማው ጎራዴ አንገቱ ላይ ወረደበት። የመኮንኑ ሰውነት ከመውደቁ በፊት ጭንቅላቱ እግሩ ስር ዘፍ አለ። ነገር ግን ሽጉጡ ... ጥይት ተኩሶ ስለነበር የተተኮሰው ጥይት የነጋሽ ልብ ውስጥ ተቀረቀረ። በዚያን ሰአት ግን ሌሎች አስር ጥይቶች በጎናቸው መቷቸው። ... ከመውደቃቸው በፊት እስከመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ አሌ የማይባል ጀግና መሆናቸውን አስመሰከሩ። ለሁልጊዜም ጀግና እንደሆኑ ይኖራሉ።” (ገፅ 123) የህክምና ባለሙያው ዶ/ር ናይስትሮም ግዴታውን በተወጣባቸው ጊዜያት እንደማንኛውም ተዋጊ ህይወቱን ለአደጋ አጋልጦ ተንቀሳቅሷል። ታዲያ አደጋው ከጣሊያኖቹ ቦንብና ጥይት ብቻ ሳይሆን ከወገን ጦርም ጭምር ነበር። በብዙ አጋጣሚዎች በነጭነቱ ምክንያት -ጣሊያናዊ እየመሰላቸውሊያጠቁት የሞከሩ ተዋጊዎች ነበሩ። ከነዚህ አጋጣሚዎች ባንዱ የሆነውን ደራሲው እንዲህ ይገልፀዋል። “... ወደ ደቡብ አቅጣጫ መንገዳችን ቀይረን የቆሰሉ ወታደሮች ወዳሉበት ካምፕ ሄድን። ቦታው ልንደርስ ትንሽ ሲቀረን ከጫካው መሃል ድንገት ጎራዴ የያዘ ሰው እየሮጠ ወደኛ መጣ። “አሃ! እኛ በእግራችን እየሄድን ይሄ አሳማ በፈረስ ይሄዳል? አሳየዋለሁ! አሳየዋለሁ!” ጣሊያናዊ ነው የመሰልኩት፣ ከዛም በላይ እስረኛ። ወዲያውኑ ሽጉጤን መዘዝኩ። “የታጠቀ እስረኛ ነው እንዴ ይዛችሁ የምትዞሩት?” አለ በመገረም። ቀናዝማች ንጋቱ በመሃላችን ገቡና ማን እንደሆንኩ ነገሩት። ሰውየውም ጉልበቴን ሳመና ይቅርታ እንዳደርግለት ጠየቀ። (ገፅ 89) ደጃዝማች አያሌውም የሃኪሙን ውለታ አልረሱም። ጦሩ ከተፈታና በያቅጣጫው መበታተን ከጀመረ በኋላ ዶ/ር ናይስትሮም ወደ አዲስ አበባ ታጅቦ ከሚሄድ አንድ ባለሥልጣን ጋር ለመጓዝ ተነሳስቶ ነበር። እናም ጥያቄውን ለደጃዝማች ያቀርባል። እሳቸው ግን አይፈቅዱለትም። “ደጃች አያሌው ግን እኔን እንዳልሄድ ከለከሉኝ። አያሌው ‘ሁኔታው በጣም አደገኛ ነው፣ ያሰቡት ቦታም አይደርሱም’ አሉ። ለመንኩ ፀለይኩ ቢከለክሉኝም እሄዳለሁ ብዬ አስፈራራሁ። “የራሴ አለቃ ራሴ አይደለሁም እንዴ?” አይሆንም! እሄዳለሁ ብዬ ከሞከርኩ እንደሚያስሩኝ ነገሩኝ። ምክንያቱም በመንገድ

የኢትዮጵያ ሬስቶራንትና ገበያ

ጣይቱ ..ከገጽ 1 የዞረ ላይ እንድገደል አልፈለጉም። ስለዚህ ሌሎቹ ጥለውኝ ሄዱ። በመቅረቴ ተፀፅቼ አላውቅም። በአንድ ሳምንት ውስጥ ሁሉም ተገደሉ” (ገፅ 163) ይለናል። በመፅሐፉ የመጨረሻ ገጾች ደግሞ ደራሲው ‘የውድቀቱ መንስኤ’ ናቸው ያላቸውንና በታሪክ ባለሙያዎች በወጉ ሊታዩ የሚገባቸውን ጉዳዮች ያካፍለናል። ተርጓሚዎቹ ይህን ጠቃሚ የታሪክ ሰነድ ወደ እንግሊዝኛ በተተረጎመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደአማርኛ ቋንቋ መልሰው ለአንባቢያን ማቅረባቸው የሚያስመሰግናቸው ነው። መፅሐፉ የታሪክ መፃሕፍትን ለሚወዱ ወገኖች ብቻ ሳይሆን ለታሪክ ተመራማሪዎችም ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው አያጠራጥርም። በመጨረሻ ምናልባት ሁለተኛ እትም የማዘጋጀት ሃሳብ ቢኖራቸው በማለት የተመለከትናቸውን አንዳንድ ነጥቦች ልናጋራቸው ወደድን። 1) ‘ጣሊያን’ ወይም ‘ጣሊያኖች’ የሚለው የሃገርና የዜጎች ስያሜ በአማርኛችን የተለመደ ሆኖ ሳለ ‘ኢታሊያን’ ወይም ‘ኢታሊያኖች’ ብሎ ደጋግሞ መጠቀሙ ተገቢነት ያለው አይመስልም። 2) ከሌሊቱ ወይም ከንጋቱ አሥር ሰዓት ተኩል ማለት ሲገባ የፈረንጆቹን አባባል ተከትሎ “ከጠዋቱ አሥር ሰኣት ተኩል” (ገፅ 12) መባሉ አደናጋሪ ያደርገዋል። በገፅ 91 ላይም እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር ይታያል። ጎላ ብሎ የሚታየውን የሥርዓተ ነጥብ ግድፈትም ትኩረት ሰጥቶ ማስተካከል ይገባል። 3) በገፅ 22 ላይ ደራሲው ከአገሬው ሰዎች ጋር ስለመሣሪያ ጉዳይ ሲወያይ “... እናንተ ደደቦች እኔ ሃኪም እንጂ ወታደር መሆኔን አታውቁም ወይ?” ማለቱ ተገልጿል። ነገሩ “ወታደር አለመሆኔን” ለማለት የፈለገ ነው የሚመስለው። ዋናው ልናነሳው የወደድነው ነጥብ ግን በ”ደደቦች” ተገቢነት ላይ ነው። ከሰውየው ባህርይና አቀራረብ ስንነሳ መጠነኛ የሆነ የነጭነት/የሥልጡንነት ስሜት ቢታይበትም እንኳ የተናገረበትን አውድ ወስዶ ለተመለከተው ከ”ደደቦች” ይልቅ “ጅሎች” የበለጠ የሚቀርብ ይመስላል። 4) “ስለ ቡጀሌ ከተነሳ” አይቀር በሚል ተርጓሚዎቹ የጨመሯቸው ሥነቃሎች (ገፅ 119) አስፈላጊነታቸው ባያጠራጥርም እንኳ የዋናው ታሪክ አካል ሆነው ሳይሆን በ’ግርጌ ማስታወሻነት ሊቀርቡ ይገባ ነበር እንላለን። ደራሲውንና ተርጓሚዎቹን ለዚህ ታሪካዊ ሥራ እንደገና እናመሰግናቸዋለን።

መሆኑን በማያውቅ ህዝብ የተበሳጩ ይመስላሉ። ለጥያቄ ክፍት የሆኑ ቢያንስ ሁለት መሠረታዊ ነጥቦች አሁንም አልተመለሱም። እሳቱ እንዴት ተነሳ? እሳቱን ለማጣፋት የተደረገው ጥረት ምድንነበር? መንግስቶቹ ለጣይቱና ለሚኒልክ ያላቸውን ጥላቻን በማሰብ እነሱን ነጻ ሊያደርግ ይችላል ለሚባል ምርመራ እንኳ የሚጨንቁ መሆናቸውን እምነት ማሳደር አይቻልም። ያን ያህል ግድ የላቸውም። በቃጠሎው ላይ የመንግሥት እጅ ላይኖርበት ይችላል። ከቃጠሎው በኋላ ያሳየው ግድየለሽነት

አንድነት... ከገጽ 1

15

1334 9th Street NW, Washington, DC 20001

Tel 202.299.9703

ነው፡፡ ” ሲል

ከሷል። “አሁን ባለው ሁኔታ ከምንጊዜውም በላይ ባፈጠጠ እና ባገጠጠ መልኩ በኢትዮጵያ የመድብለ ፓርቲ ዲሞክራሲ ፈተና ላይ ወድቋል፡ ፡ ሰላማዊ ትግሉ በሩ ሙሉ ለሙሉ እየተዘጋ መጥቷል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ ሌሎች ትልልቅ በሮችን ይከፍታል፡፡ በዚህ መንገድ አገሪቱን ለከፋ ችግር እየተጋለጠች መሆኑ ግልፅ ጉዳይ ሆኗል፡፡” በማለት ፓርቲው ያለውን ስጋት ገልጧል። አንድነት “በፓርቲያችን በኩል ለሰላማዊ ትግል መጐልበት፤ ለዘላቂ ሰላምና መረጋጋት የቻልነውን ብናደርግም ህዝብ በሚከፍለው ታክስ የሚተዳደሩት የመገናኛ ብዙኃን እና የግል ተቋም ነኝ የሚለው፤ በተግባር ግን የገዥው ፓርቲ ልሳን የሆነው ሬዲዮ ፋና በፓርቲያችን ላይ ከምን ጊዜውም በላይ አፍራሽ

ዘመቻቸውን አጠናክረው ገፍተውበታል፡ ፡ የዚሁ ተልዕኮ አካል የሆነ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፓሬሽን ከ3 ወር በፊት ያስተላለፈውን ፕሮግራም አቧራውን አራግፎ እንደ አዲስ ሐሙስ ጥር 14 ቀን 2007 ዓ.ም ምሽት ፕሮግራም እንዳዘጋጀ ተከታትለናል፡፡” ካለ በኋላ “ሕዝቡ በቀድሞ ኢቲቪ በአሁኑ ኢቢሲ የሚተላለፉ ዘገባዎች ላይ ያለውን ዕምነት ብናውቅም በፓርተያችን በኩል ማለት የምንፈልገው፤ ፕሮግራሙ የተለያዩ አካላት የፓርቲው አባላት ነን ከሚሉት ጋር በመሆን የተቀነባበረ ቀጣይ አፍራሽ ድራማ መሆኑን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳው ነው፡፡” በማለት ህዝቡ ለአፍራሽ ቅስቀሳዎቹ ቦታ እንዳይሰጠው ጠይቋል። “የመንግስት ኃላፊነት እና ልዩ ልዩ ስልጣኖች ያልፋሉ አገር እና ሕዝብ ግን ህያው ናቸው፡፡” ያለው መግለጫው “ዛሬ በአንድት ፓርቲ ላይ የተቀነባበረው ዘመቻ ለአባላቱና ለደጋፊው ጥንካሬን ይሰጠዋል “ታጋይና ምስማር ሲመቱት ይጠብቃል” እንደሚባለው ነው፡ ፡ ሕዝብ ደግሞ በግልፅ እየታዘበ ነው፡፡ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ ሬዲዮ ፋና የቀድሞ ኢቲቪ የአሁኑ ኢብኮን ተባባሪዎቻቸውን ታሪክ እና ጊዜ ይፈረዳቸዋል፡፡ ፓርቲያችን አይጠፋም፡፡ ምንም ጥርጥር የለውም ሊያጠፉት የሚቅነዘነዙት ይጠፋሉ፡ ፡ የሕዝብ ፓርቲ ሁሌም ዘላለም ይኖራል፡፡” በማለት የድርጅቱን ጽናት ገልጧል። በሌላም

በኩል

አንድነት

ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ለእሁድ ጥር 17 2007 በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ ፓርቲውን ለማፍረስ የሚያደርጉትን በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ጠርቷል። ሰልፉ የሚደረግባቸው አካባቢዎችንም ገልጧል። በጥሪውም ላይ “ፈፅሞ የማይቀሩበት ሰልፍ ነው ነው ስለሀገራችን ድምፃችን እናሰማ! የአንድነት አባለት፣ ደጋፊዎች በጠቅላላ በኢትዮጵያ የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ የምንፈልግ ሁሉ በዚህ በአጭር ጊዜ ሰልፎቹ የተሳኩ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ርብርብ ታደርጉ ዘንድ ሀገራዊ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።” ብሏል። በተያየዘ ዜናም ከድርጅቱ ተለይተውና የኢህ አዴግና የምርጫ ቦርድ መሳሪያ ሆነው የነበሩ አባላቱ ይቅርታ እየጠየቁ ወደ ድርጅታቸው መመለሳቸውን አስታውቋል። በግንባር ቀደምትነት የተጠቀሱት አቶ አየለ ስሜ ናቸው። “ ምርጫ ቦርድ ለአቶ አየለ ስሜ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲጠራ ደብዳቤ መስጠቱን የምርጫ ቦርድ ምክትል ሀላፊ አቶ አዲሱ ገ/እግዚአብሄር ከዚህ ቀደም መናገራቸው አይዘነጋም፡፡ ዛሬ በምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ተሰጥቷቸው የነበሩት አቶ አየለ ስሜና አቶ ኢሳይያስ ቱሉ እናት ፓርቲያቸውን ይቅርታ በመጠየቅ ተመልሰዋል፡፡ ከእነ አቶ አየለ ቀደም ብለው የተወሰኑ ወጣቶች ከፓርቲው ውጪ ይሰበስቧቸው የነበሩ ሰዎችን የጥፋት ተልዕኮ በመረዳት መመለሳቸው አይዘነጋም፡፡” በማለት “የኢህአዴግና የምርጫ ቦርድ ድራማ ተዋናይ እያጣ ነው” ብሏል።


ዘኢትዮጵያ ጋዜጣ Zethiopia Ethiopian American Community News NO.89 Jan 2015 202 518 0245 P.o.box 2049, Fairfax, VA 22031 www.zethiopia com

16

Ze 89  

Zethiopia Newspaper, Washington DC

Ze 89  

Zethiopia Newspaper, Washington DC

Advertisement