Page 1

ግብር አዳዲስ የንግድ ስራ ባለቤቶች ስለ ግብር ክፍያ ምን ማወቅ ይጠበቅባቸዋል? 

የንግድ ስራ ወይስ ልማድ ነው?

የአገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት ግብር ከፋዮች የንግድ ስራቸው ልማድ መሆኑን ወይም አለመሆኑን ወይም ለትርፍ እንደሚሰሩት ለመወሰን አግባብነት ያላቸው መመሪያዎች እንዲከተሉ ያስታውሳል፡፡ የግዴታዎች ምስረታን አስመልክቶ ግብር ከፋዮችን ለማስተማር፣ ይህ የፍሬ ነገር ቅጽ 11ኛ ክፍል አንድ ተግባር እንደ ንግድ ስራ ብቁ የሚያስብሉትን እና ተግባሩ የንግድ ስራ ካልሆነ ምን አይነት መወሰኛዎች ሊኖሩበት እንደሚችሉ ለመወሰን ደንቦቹን ያብራራል፡፡ ከመጠን በላይ የተጠቀሱ ማስተካከያዎች፣ ቅናሾች፣ ከግብር ነጻ መብቶች እና ገቢዎች በድምሩ በየአመቱ ባልተከፈሉ ግብሮች ላይ እስከ 30ቢሊዮን ዶላር የሚደርሱት ትክክለኛ ያልሆኑ የልማዳዊ ወጪዎች ተቀናሽ ሂሳብ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ ግብር ከፋዮች አንድን ንግድ ወይም ስራ ለማካሄድ መደበኛ እና አስፈላጊ ጪዎች ለመቀነስ ይችላሉ፡፡ መደበኛ ወጪ የግብር ከፋዩ ንግድ ስራ የሚያስከትላቸው በተለምዶ ተቀባይነት ያላቸው ወጪዎች ናቸው፡፡ አስፈላጊ ወጪ ደግሞ ለንግድ ስራው ተገቢ የሆነ ወጪ ነው፡፡ ይህንን መወሰኛ ለማድረግ፣ ግብር ከፋዩ የሚከተሉትን ሁኔታዎች መወሰን አለበት፡        

በስራ ውስጥ የተጠቀሰው ጊዜ እና ጥረት ትርፍ የማስገኘት አላማን ያመላክታል? ግብር ከፋዩ ከስራው በሚገኘው ገቢ ላይ ይመሰረታል? ኪሳራዎች ከደረሱ፣ ከግብር ከፋዩ ቁጥጥር ውጪ በሆኑ ሁኔታዎች ወይም ከግብር ከፋዩ የንግድ ስራ የመጀመሪያ ደረጃ የተከሰቱ ናቸውን? ግብር ከፋዩ ትርፋማነቱን ለማሻሻል የአሰራር ዘዴዎቹን ለውጧልን? ግብር ከፋዩ ወይም አማካሪዎቹ በስራው ላይ ስኬታማ እንዲሆን የሚያስፈልገው እውቀት አላቸውን? ግብር ከፋዩ ባለፉት ጊዜያት በተመሳሳይ ተግባራት ተመሳሳይ ትርፍ አግኝቷልን? በአንዳንድ ጊዜያት ስራው ትርፍ አስገኝቷልን? ግብር ከፋዩ ለወደፊቱ በስራው ላይ በጥቅም ላይ የዋሉትን ትርፎች በመጠቀም ትርፍ እንደሚያገኝ ይጠብቃልን?

አይአርኤስ አንድ ስራ ባለፉት 5 ዓመታት ጊዜያት ቢያንስ በ3ቱ፣ የዘመኑን አመት አካቶ ቢያንስ ባለፉት 3 ዓመታት ባካሄዳቸው ተግባራት ከብት ማርባት፣ ትርዒት ስልጠና ወይም የፈረስ ውድድር አካትቶ ትርፍ ለማስገኘት ዓላማ እንደተካሄደ የተመታል፡፡ ስራው ለትርፍ የተካሄደ ካልሆነ፣ ከስራው የሚገኙት ኪሳራዎች ሌሎች ገቢዎችን ለማጣጣት ላይውሉ ይችላሉ፡፡ አንድ ተግባር ተዛማጅ ወጪዎች ከገቢው ከበለጡ እንደ ኪሳራ


እንደሚቆጠር ግልጽ ነው፡፡ በግለሰቦች በማህበራት በቤቶች ልማት፣ በአደራ እና በኤስ ኮርፖሬሽኖ ላይ ተግባራዊ የሚሆኑ ለትርፍ ያልተመሰረቱ ኪሳራዎች ወሰን ከኤስ ኮርፖሬሽኖች ውጪ ባሉ ድርጅቶች ላይ ተግባራዊ አይሆኑም፡፡

የልማዳዊ ተግባራት ተቀናሾች በሰንጠረዥ ሀ (ቅጽ 1040) ላይ በተለዩ ተቀናሾች ይወሳሉ፡፡ እነዚህ የሚከተሉትን ስርዓቶች መውሰድ እና በእያንዳንዱ ሶስት ምድቦች ውስጥ እስከተጠቀሰው መጠን ድረስ ብቻ ተግባራዊ መሆን አለባቸው፡ 

አንድ ግብር ከፋይ ለግሉ ወይም ለንግድ ስራ ተግባራቱ እንደ ቤት እዳ፣ ወለድ እና ግብር ሊወስዳቸው የሚችላቸው ቅናሾች ሙሉ በሙሉ ሊተገበሩ ይችላሉ፡፡ በማስተካከያ መሰረት ሊከሰቱ የሚችሉ ቅናሾች እንደ ማስታወቂያ፣ መድን፣ አረቦን እና የቀን ክፍያ በመጀመሪያው ምድብ ከተጠቀሱት ተቀናሾች በላይ አጠቃላይ ከስራው ከሚገኘው ገቢ ድረስ ሊወሰድ ይችላል፡፡ የንብረቱን መሰረት የሚቀንሱ የንግድ ስራ ተቀናሾች እንደ እርጅና ተቀናሽ እና አሞርታዜሽን በመጨረሻ የሚወሰዱ፣ ግን ስራው በመጀመሪያው ሁለት ምድቦች ከተወሰዱት ተቀናሾች በላይ ከሆነ እስከ አጠቃላይ ገቢው ድረስ ይሆናል፡፡

የንግድ ስራ ግብር የትኛዎቹን ግብሮች የንግድ ስራውን አይነት ለማንቀሳቀስ መጠቀም እንዳለብዎትና እንዴት መክፈል እንዳለብዎት ለመወሰን የሚከተሉትን አራት አጠቃላይ የንግድ ስራ ግብሮች ከግምት ውስይ ውሰድ     

የገቢ ግብር ግምታዊ ግብር የራስ-ስራ ግብር የስራ ቅጥር ግብር ኤክሳይስ ታክስ

የገቢ ግብር ሁሉም የንግድ ስራ ከማህበራት በስተቀር አመታዊ የገቢ ግብር ተመላሽ ማመልከት ግድ ይላል፡፡ ማህበራት የግብር ተመላሽ መረጃ ይመሰርታሉ፡፡ በዚህ ረገድ የሚጠቀሙት ቅጽ የንግድ ስራዎ እንዴት ተደራጀ በሚለው እውነታ ላይ ይመሰረታል፡፡ የትኛዎቹ የግብር ተመላሾች በንግድ አካልነት በተቋቋመው ድርጅት መከፈል ያለበትን ተመላሽ አስመልክቶ የንግድ አወቃቀሮችን ያጣቅሱ፡፡ የፌደራል ገቢ ግብር በሚሰሩት ተጨባጭ የንግድ ስራ ላይ እንደሚከፈለው በአመት ውስጥ ገቢን ሲያገኙ ወይም ሲቀበሉ ግብር መክፈል አለብዎት፡፡ አንድ ሰራተና በተለምዶ ከክፍያው ላይ የሚያዝ ግብር ይኖርበታል፡፡ በሚያዘው መጠን ላይ በመመስረት ግብርዎን ካልከፈሉ ወይም በዚህ መንገድ በቂ ግብር ካልከፈሉ፣ ግምታዊ ግብር ሊከፍሉ ይችላሉ፡፡


ይህንን ግብር እንዲከፍሉ ካልተጠየቁ፣ የግብር ተመላሽዎን ሲመሰርቱ ማንኛውንም ግብር እንዲከፍሉ ሊጠየቁ ይችላሉ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ሕትመት 583ን ያጣቅሱ፡፡ ግምታዊ ግብር በአጠቃላይ በገቢዎ ላይ የራስ-ስራ ቅጥርን አካትቶ (በሚቀጥለው በአመቱ ግምታዊ ግብር ላይ መደበኛ ክፍያዎችን በማድረግ ይኖርቦዎታል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ግምታዊ ግብሮችን ያጣቅሱ

እንደምንወያየው) ግብር መክፈል

የራስ - ስራ ቅጥር ግብር ይህ ለራሳቸው የሚሰሩ ግልሰቦች ለማህበራዊ ዋስትና እና ለህክምና እንክብካቤ ግብር የሚውሉት ነው፡፡ የኤስኢ ግብር ክፍያዎች በማህበራዊ ዋስትና ስርዓት ስር ለሽፋኑ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡ ይህም የጡረታ ጥቅማጥቅሞች፣ የአካል ጉዳተኛ ጥቅማጥቅም እና በህይወት ያሉ ሰዎች ጥቅማጥቅሞች እንዲሁም የሆስፒታል መድን ጥቅማጥቅሞች ይሆናሉ፡፡ የኤስኢ ግብር እና ሰንጠረዥ ኤስኢ (ቅጽ 10) ከሚከተሉት በአንዳቸው ላይ ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡  

ከራስ የስራ ቅጥር የሚያገኟቸው ገቢዎች 400 ዶላር ወይም ከዚያ በላይ ከሆኑ ለቤተክርስቲያን ወይም ብቁት ላለው በቤተክርስቲያን ቁጥጥር ስር ባለ ድርጅት (የኃይማኖታዊ ስርዓት አገልጋይ ወይም አባል ውጭ) ከማህበራዊ ዋስትና እና የህክምና እንክብካቤ ግብር ነጻ ሆኖ ከተመረጠ፣ ከመቶ 2.28 ወይም ከዚያ በላይ የቀን ክፍያ ከቤተክርስቲያን ወይም ከድርጅቱ የሚያገኙ ከሆነ በኤስኢ ግብር ይገዛሉ፡፡

ማስታወሻ: ለውጭ አገር ዜጎች፣ ለአሳ አጥማጅ ቡድን አባላት ለህዝብ ጉዳይ አዋዋይ ለክልል ወይም የአካባቢያዊ መንግስት ሰራተኞች፣ ለውጭ አገር መንግስታት ወይም ለአለም አቀፍ ድርጅት ሰራተኞች ወዘተ… ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡

የስራ ቅጥር ግብሮች ሰራተኞች ሲኖርዎት አሳውቀው መክፈል የሚገባዎት የስራ ቅጥር ግብር ኃላፊነቶች አሉ፡፡ የስራ ቅጥር ግብር የሚያካትተው የሚከተሉትን ነው፡፡   

የማህበራዊ ዋስትናና የህክምና እንክብካቤ ግብር የፌዴራል ገቢ ግብር ተያዥ የፌዴራል የስራ አጥነት ግብር

ለተጨማሪ መረጃ የአነስተኛ የንግድ ስራዎችን የስራ ቅጥር ግብር ይመልከቱ


ኤክሳይስ ግብር ይህ ክፍል ከሚከተሉት አንዳቸውን የሚያካሂዱ ከሆነ አሳውቀው መክፈል የሚገባዎትን ግብር ይመለከታል፡፡    

የተወሰኑ ምርቶችን ማምረት ወይም መሸጥ የተወሰኑ የንግድ ስራ አይነቶችን ማንቀሳቀስ መሳሪያዎች፣ አቅርቦቶች ወይም ምርቶችን መገልገል የተወሰኑ አገልግሎቶችን መቀበል

ቅጽ 720 - የፌዴራል ኤክስአይስ ታክስ ግብር በቅጽ 720 ላ ሪፖርት እንደሚደረገው የሚከተሉትን አካትቶ በጣም ብዙ ሰፋፊ ምድቦችን ይይዛል፡፡     

የአካባቢያዊ ግብር የግንኙነትና የአየር መጓጓዣ ግብር የነዳጅ ግብር የከባድ መኪናዎች ተሳቢዎች እና ትራክተሮች የመጀመሪያ መሸጫ ዋጋ ግብር በተለያዩ እቃዎች ላይ ተከፋይ የሚሆን የሽያጭ ወይም የአገልግሎት ግብር

ቅጽ 2290 - በተወሰኑ ገልባጮች ከባባድ ትራክተሮች እና አውቶቡሶች ላይ የሚከፈል የፌዴራል ኤክሳይስ ታክስ ነው፡፡ ይህ ግብር ከ55,000 ፓውንድ ወይም ከዚያ በላይ አጠቃላይ ክብደት ባላቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ግብሮን በቅጽ 2290 ሪፖርት ያድርጉ ፡፡ ለበለጠ መረጃ ቅጽ 2290 ይመልከቱ፡፡ ቅጽ 730 - የቀን ክፍያ ወይም በአንድ ላይ የሚከፈሉ ድርጎዎች ወይም ከሎተሪ ያገኙ ከሆነ፣ በፊዴራል የኤክሳይስ ታክስ ይገዛሉ፡፡ ቅጽ 730፣ በሚያገኙት የቀን ክፍያ ላይ ተግባራዊ የሚሆን የግብር አሃዝ፡፡ ቅጽ 11-ሐ - ይገልገሉ፣ የስራ ግብር እና የምዝገባ ተመላሽ የቀን ክፍያ ዓላማ፣ ማንኛውንም የቀን ክፍያ ለማስመዝገብ እና በቀን ክፍያው ላይ ማንናውንም የፌዴራል ግብር ይገልገሉ፡፡ የኤክሳይስ ግብር እጅግ በጣም ብዙ አጠቃላይ የኤክሳይዝ ግብር ፕሮግራሞች አሉት ከእነዚህ ዋና ዋናዎቹ የሞተር ነዳጅ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ የኤክሳይስ ግብርን ያጣቅሱ፡፡

የመዝገብ አጠባበቅ 1 ለምን መዛግብትን እንጠብቃለን? ጥሩ መዛግብር የንግድ ስራውን ግስጋሴ ለመቆጣጠር፣ የገንዘብ መግለጫዎች ለማዘጋጀት፣ የሀብት ምንጮችን ለመለየት የተቀናሽ ሂሳቦችን ለመፈለግ፣ የግብር ተመላሾችን


ለማዘጋጀት እና ረፖርት የሚደረጉ ተቀናሽ ግብሮች፣ የግብር ተመላሾች እና የሪፖርት ድጋፍ ክፍሎች ናቸው፡ የንግድ ስራው በእያንዳንዱ ሰው መዝገብ መጠበቅ አለበት፡፡ ይህም ለንግድ ስራዎ በጣም ጠቃሚ ነው፡፡ የእቃዎች መዝገብ እንደሚከተለው ድጋፍ ጠያቀርባል፡     

የንግድ ስራውን ግስጋሴ ለመቆጣጠር የገንዘብ መግለጫዎችን ለማዘጋጀት የሀብት ምንጭን ማሳወቅ የተቀናሽ ወጪዎችን በቀጣይነት ለመከታተል የግብር ተመላሾችን ለማዘጋጀት በግብር ተመላሾች ላይ ያሉ ክፍሎትን ለመደገፍ

የንግድ ስራውን ግስጋሴ ለመቆጣጠር የንግድ ስራውን ግስጋሴ ለመቆጣጠር መዝገብ መጠበቅ ያስፈልግዎታል፡፡ መዛግብቱ የንግድ ስራው እየተሻሻለ መሆኑን፣ የትኛዎቹን እቃዎች እንደሚሸጡ ለመቆጣጠር ያስፈልጋል፡፡ የእቃዎች መዛግብት የንግድ ስራ ስኬታማነትን ለማሳደግ ያስችላል፡፡

የገንዘብ መግለጫዎችን ለማዘጋጀት የገንዘብ መግለጫዎችን ለማዘጋጀት ትክክለኛ መዛግብት ቢኖርዎት ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም የሚያካትተው ገቢ (ትርፍና ኪሳራ) መግለጫዎች እና ወጪ ቀሪ ቅጾች ናቸው፡፡ እነዚህም የባንክ ወይም የአበዳሪዎችን ጉዳዮች ለማስተናገድ እንዲሁም የንግድ ስራዎን በተገቢው መልኩ ለማስተዳደር ያግዛሉ፡፡  

የገቢ መግለጫ የንግድ ስራ ገቢዎ ለተወሰነ ጊዜ ትርፋማ መሆኑን ለመወሰን ያገለግላል፡፡ የወጪ ቀሪ ቅጽ በንግድ ስራው ላይ ለተወሰነ ጊዜ የንግድ ስራውን ሀብት እዳ እና ድርሻ ያሳያል፡፡

የሀብት ምንጭን ማሳወቅ ገንዘብ ወይም ንብረት ከብዙ ምንጮች ሊያገኙ ይችላሉ፡፡ እነዚህ መዛግብት ምንጮችዎን ይለያሉ፡፡ የንግድ ስራዎን ከሌሎች የንግድ ስራዎች ለመለየት የተናጠለ መረጃ ያስፈልግዎታል፡፡

የተቀናሽ ወጪዎችን በቀጣይነት ለመከታተል ገቢዎችዎ ሲከሰቱ በመዝገብ ካልጠበቋቸው የግብር ተመላሽዎን ሲሞሉ ችግሮች ያጋጥምዎታል፡፡


የግብር ተመላሾችን ለማዘጋጀት የግብር ተመላሽዎን ለማዘጋጀት መዝገብ ቢኖርዎት አስፈላጊ ነው፡፡ እነዚህ መዛግብት ገቢ ወጪዎችዎንና ዱቤዎችን ሪፖርት ለማድረግ ያስችላሉ፡፡ በአጠቃላይ የንግድ ስራዎን ለመቆጣጠር ተመሳሳይ መዛግብትን መጠበቅ እና የፋይናንስ መግለጫ ማዘጋጀት ይኖርብዎታል፡፡

በግብር ተመላሾች ላይ ያሉ ክፍሎትን ለመደገፍ አይአርኤስ ለሚያካሂዳቸው ፍተሻዎች በሁሉም ጊዜያት የንግድ ስራ መዛግብት መጠበቅ አለበብዎት፡፡ አይአርኤስ የግብር ተመላሽዎን ከመረመረ፣ ሪፖርት የተደረጉትን ክፍሎች እንዲያብራሩ ይጠየቃሉ፡፡ የተሟላ የመዝገብ ስብስብ ምርመራውን ያፋጥነዋል፡፡

2ምን ምን አይነት መዛግብት መጠበቅ ያስፈልገኛል? ለንግድ ስራዎ ምቹ የሆነ ማንኛውንም የመዝገብ አጠባበቅ ስርዓት መምረጥ ገቢዎን እና ወጪዎችዎን በግልጽ ለማሳየት ምቹ ነው፡፡ ከጥቂት ሁኔታዎች በስተቀር ህጉ ልዩ መዝገብ እንዲጠብቁ አያስገድድዎትም፡፡ ቢሆንም ግን የንግድ ስራዎ የፌዴራል ግብር አላማዎችን የመጠበቅ አስፈላጊነት የሚነኩ የመዝገብ አይነቶችን አይወስንም፡፡ ይህ ማጠቃለያ በመደበኛነት በንግድ መዛግብትዎ (ለምሳሌ የሂሳብ ጆርናሎች እና ባህር መዝገቦች) የሚዘጋጅ ነው፡፡ መጻህፍቶ አጠቃላይ ገቢዎን እንዲሁም ቅናሽና ዱቤዎችን ማሳየት አለባቸው፡፡ አብዛኛዎቹ አነስተኛ የንግድ ስራዎች፣ የንግድ ስራው ማረገገጫ ደብተር ለገቢዎቹ ዋነኛ ምንጭ ነው፡፡ አንዳንድ የንግድ ስራዎች መዝገባቸውን ለመያዝ እና ለማረጋገጥ ኤሌክትሮኒክ የሂሳብ አያያዝ ሶፍትዌር ፕሮግራሞችን ለመገልገል ይመርጣሉ፡፡ በነአንድ ሁኔታዎች ግን የተወሰኑ ክፍሎን በሰነድ መጠበቅ ያስፈልግዎታል፡፡ የሶፍትዌር ፕሮግራ ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ዋና ዋና መሰረታዊ የመዝገብ አጠባበቆችን ያሟላል፡፡

የንግድ ሰነዶች ግዢዎች፣ ሽያጭ ደመወዝ ክፍያ እና ሌሎች ግብይቶች በንግድ ስራ ውስጥ እንደ ደረሰኞች እና ኢንቮይሶች ያሉ ደጋፊ ሰነዶችን ያመነጫሉ፡፡ ደጋፊ ሰነዶቹ የሽያጭ ደረሰኞች፣ ክፍያ የተፈፀመባቸው ደረሰኞች፣ ኢንቮይሶች፣ ተቀማጭ ደረሰኞች እና የተሰረዙ ቼኮችን ያካትቱ፡፡ እነዚህ ሰነዶች የሚያካትቷቸው በመዝገብዎ ውስጥ የጠበቋቸውን መረጃዎች ይሆናል፡፡ እነዚህ ሰነዶች ጠቃሚ ከመሆናቸው የተነሳ በመዝገብዎ እና በግብር ተመላሽዎ ውስጥ ያስገቧቸውን መረጃዎች ይደግፋሉ፡፡ እነዚህን ስርዓት ባለው አኳኋን እና


አስተማማን ሁኔታ መጠበቅ አለበት፡፡ ለምሳሌ በአመት እና በገቢዎ አይነት ወይም ወጪዎች ማደራጀት፡፡ ለበለጠ መረጃ Publication 583, Starting a Business and Keeping Records.

የሚከተሉት መጠበቅ የሚያስፈልግዎ አንዳንድ የመዛግብት አይነቶች ናቸው 

ጠቅላላ ደረሰኞች ያገኟቸው ጠቅላላ ገቢዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ደጋፊ ሰነዶች የጠቅላላ ገቢዎችዎን ምንጭ እና መጠን ይደግፋሉ፡፡ አጠቃላይ ደረሰኞች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡o የገንዘብ ምዝገባ ቴፖች o የባንክ ተቀማጭ ደረሰኞች o የተሰበሰቡ ሂሳብ መዛግብት o ደረሰኞች o የዱቤ ካርድ ክፍያ ደረሰኞች o ቅጽ 1099-ኤምአይኤስሲ

ግዢዎች የሚገዟቸው እና ለደንበኞች መልሰው የሚሸጧቸው እቃዎች ናቸው፡፡ እርስዎ አምራች ከሆኑ ይህ የሚያካትታቸው የጥሬ እቃዎች ወይም ክፍሎች ወይም የተጠናቀቁ እቃዎች ዋጋን ይሆናል፡፡ ደጋፊ ሰነዶችዎ የተከፈለውን መጠን ማሳየት እና የግዢውን መጠን ማመላከት አለበት፡፡ እነዚህም የሚያካትቷቸው፡o የተሰረዙ ቼኮች o የገንዘብ ምዝገባ ቴፕ ደረሰኞች o የዱቤ ካርድ ሽያጭ ደረሰኞች o ደረሰኞች

ወጪዎች እርስዎ ለንግድ ስራዎ ማካሄጃ የገቧቸው ከግዢዎች ውጪ ያሉ ሂሳቦች ናቸው፡፡ ደጋፊ ሰነዶችዎ የከፈሉትን መጠን እና የአንድን የንግድ ስራ ወጪ ማመላከት አለበት፡፡ እነዚህም የሚያካትቷቸው o የገንዘብ ምዝገባ ቴፕ ደረሰኞች o የዱቤ ካርድ ሽያጭ ደረሰኞች o ደረሰኞች o የፔቲ ካሽ ደረሰኞች ለአነስተኛ ገንዘብ ክፍያዎች

ጉዞ መጓጓዣ፣ መዝናኛ እና የስጦታ ወጪዎች እነዚህን የተወሰኑ የወጪ አካላት በማስረጃ መደገፍ ይኖርብዎታል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ፣ Publication 463, Travel, Entertainment, Gift, and Car Expenses ያጣቅሱ፡፡

ሀብት እንደ ማሽን እና የቢሮ እቃዎች ያሉ ንብረቶች ናቸው፡፡ እነዚህም ለንግድ ስራው በእርስዎ ባለቤትነት የተያዙ ናቸው፡፡ እነዚህን ለማረጋገጥ የተወሰነ መረጃ መጠበቅ ያስፈልግዎታል፡፡ አመታዊ የእርጅታ ተቀናሽ እና ገቢ ወይም ኪሳራ ለማስላት መዝገብ ያስፈልግዎታል፡፡ እነዚህም የሚያካትቷቸው፡o አስፈላጊ ሀብቶችን መቼ እና እንዴት እንዳገኟቸው o የግዢ ዋጋ


o o o o o o o o

የማንኛውም ማሻሻያዎች ወጪ ክፍል 179 የተወሰዱ ተቀናሾች በእርጅና ተቀናሽ ላይ የተወሰዱ ተቀናሾች በአደጋ ኪሳራዎች የደረሱ ተቀናሾች እንደ ከእሳት ወይም ከማእበል የተነሳ የሚከሰቱ ሀብትዎት እንዴት መጠቀም እንዳለብዎ ሀብትዎን እንዴት እና መቼ ማስተላለፍ እንዳለብዎት የሽያች ወጪ የሽያጭ ዋጋ

የሚከተሉት ሰነዶች ይህንን መረጃ ያሳያሉ o o o 

ግዢአ እና የሽጭ ደረሰኞች የማይንቀሳቀስ ሀብት መዝጊያ መግለጫዎች የተሰረዙ ቼኮች

የስራ ቅጥር ግብሮች እነዚህ በመዝገብ መጠብ የሚያስፈልግዎት ልዩ ልዩ የስራ ቅጥር ግብር መዛግብት ናቸው፡፡ ቢያንስ ለአራት አመታት እነዚህን መዛግብት በሙሉ መጠበቅ ይኖርብዎታል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ Recordkeeping for Employers እና Publication 15, Circular E Employers Tax Guide ያጣቅሱ፡፡

መዛግብትን ለምን ያህል ጊዜ መጠበቅ ያስፈልገኛል? መዛግብትን የመጠበቅ ርዝማኔ በሰነድ መዛግብት ላይ ባሉት እርምጃዎች ወጪዎች ዌም ክስተት ላይ ይመሰረታል፡፡ እነዚህ መዛግብት በግብር ተመላሽዎ ላይ ገቢዎን ወይም ተቀናሽዎን ለማረጋገጥ ሊያስፈልጉ ይችላሉ፡፡ በአጠቃላይ ለግብር ተመላሽዎ የተወሰነው ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ የገቢዎን ወይም ተቀናሽዎን ክፍል ለመደገፍ ያስፈልጋል፡፡ ይህ የመወሰኛ ጊዜ የግብር ተመላሽዎን ይገባኛል ለማለት ሊያሻሽሉት የሚችሉት ቆይታ ነው፡፡ ከዚህ በታች ያለው መረጃ በገቢ ግብር ተመላሽ ላይ ተግባራዊ የሚሆነው ጊዜ ነው፡፡ በሌላ አኳኋን ካልተጠቀሰ በስተቀር፣ ይህ ተመላሽ ከተመለሰ በኋላ ያለውን የቆይታ ጊዜ አመታት የመለከታሉ፡፡ ከመክፈያው ቀን በፊት የቀረቡ ማመልከቻዎች በትክክለኛ መክፈያው ቀን ላይ ይመሰረታሉ፡፡ ማስታወሻ: የእርስዎ የግብር ተመላሽ ማመልከቻ ቅጂዎችን ያግኙ የወደፊት የግብር ተመላሽዎን ለማስላት እና ተመላሹን ካሻሻሉ ስመሌቶችን ለማካሄድ አላማ ይደግፋል፡፡ 1. ተጨማሪ ግብር እና ሁኔታዎች (2), (3), እና (4), ከዚህ በታች፣ በእርስዎ ላይ ተግባራዊ አይሆኑም፤ ለሶስት አመታት ይጠብቁ፣ 2. ሪፖርት ማድረግ ያለብዎትን ገቢ ሪፖርት ሳያደርጉ ከቀሩ፣ እና ከግብር ተመላሽዎ ጠቅላላ ገቢ 25 በመቶ በላይ ከሆነ፤ መዛግብቱን ለ6 ዓመታት ለስድስት አመታት ይጠብቁ፡፡ 3. የተጭበረበረ የግብር ተመላሽ አመልክተው ከሆነ፤ መዛግብትዎን ላልተወሰነ ጊዜ ይጠብቁ፡፡ 4. የግብር ተመላሽ ካላመለከቱ፣ መዛግብትዎን ላልተወሰነ ጊዜ ይጠብቁ፡፡ 5. ለግብር ተመላሽ ይገባኛል አቅርበው ከሆነ የግብር ተመላሽ ካቀረቡ በኋላ፤ መዛግብቱን ዋና የግብር ተመላሽዎን ካቀረቡበት ጊዜ ጀምሮ ለሶስት አመታት ወይም የግብር ተመላሽዎን ከከፈሉበት ጊዜ ጀምሮ ማናቸውም ቀድመው የተከሰተቱት ይጠብቁ፡፡


6. ዋጋ የሌላቸው መተማመኛዎችን ወይም ሳይሰበሰቡ የቀሩ እዳዎችን ተቀባሽ ይገባኛል ይጠብቁ፤ መዛግብትዎን ለሰባት አመታት ይጠብቁ፡፡ 7. ግብርዎ መከፈል ካለበት ወይም ከተከፈለበት ቀን ጀምሮ ማናቸውም ቀድመው የተከሱት ሁሉንም የስራ ቅጥር ግብር መዛግብት ይጠብቁ፡፡

የሚከተሉት ጥያቄዎች ሰነዱን ቢጠብቁም ወይም አርቀው ቢጥሉት በእያንዳንዱ መዝገብ ላይ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡

መዛግብቱ ከሀብቶችዎ ጋር የተገናኙ ናቸውን? ንብረቱን ግብር በሚከፈልበት አኳኋን እስከሚያስተላልፉበት አመት ድረስ ከንብረቱ ጋር በተገናኘ የተወሰነው የቆይታ ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ እነዚህን መዛግብት የእርጅና ተቀናሽ፣ አሞርታይዜሽን ወይም ግሽበት ተቀናሽ ለመጠበቅ በቀጣይነት ማኖር ወይም በሌላ አኳኋን ንብረቱን ማስተላለፍ ይገባዎታል፡፡ በአጠቃላይ ግብር በማይከፈልበት ተለዋጭ መንገድ ንብረቱን ከተረከቡ፣ በንብረቱ ላይ ያለዎት መሰረት ንብረቱን ከተዉበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ ነው፣ የከፈሉት ማንኛውም ገንዘብ በተጨማሪነት የሚያገለግል ይሆናል፡፡ እንዲሁም በድሮው ንብረት ላይ መዛግብቱን መጠበቅ እና በተባለው አመት አዲሱን ንብረትዎን ግብር በሚከፈልበት አኳኋን እስኪያዘዋውሩበት ድረስ ያለው ጊዜ እስኪያበቃ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

ግብር ለማይከፈልባቸው አላማዎች መዛግብቶችን ምን ማድረግ አለበት? ለግብር አላማዎች ምንም አይነት መዝገብ የማይጠበቁ ከሆነ ለተባሉት አላማዎች እንደማይገለገሉባቸው እርግጠኛ እስኪሆኑ ድረስ ሰነዶቹን እንዳያስወዷቸው ለምሳሌ የመድን ኩባንያው ወይም አበዳሪዎች አይአርኤስ ከሚጠበቅብዎ ጊዜ በላይ ሊፈልጓቸው ይችላሉ፡፡

የስራ ቅጥር ግብር መዛግብትን ለምን ያህል ርዝማኔ መጠበቅ አለብኝ? ሁሉንም መዛግብቶችዎን እስከሚያስፈልገው ርዝማኔ ድረስ መጠበቅ አለብዎት ቢያንስ ለአራት አመታት የስራ ቅጥር መዛግብቶችዎን መጠበቅ አለብዎት፡፡ በአመቱ አራተኛ ሩብ አመት በኋላ ቢያንስ ለአራት አመታት የስራ ቅጥር መዛግብቶችዎን መጠበቅ አለብዎት፡፡ መዛግብቱ የሚያካትቷቸው፡     

የአሰሪ የመታወቂያ ቁጥር የሁሉም የቀን ክፍያ ጥቅማጥቅም እና የጡረታ ክፍያዎ መጠንና ቀናት ሪፖርት የተደረጉ ጉርሻዎች መጠን በአይነት ለተከፈሉ የቀን ክፍያዎች ፍትሐዊ የገበያ ዋጋ የሰራተኞች እና ተቀባዮች ስም፣ አድራሻ ማ/ዋ/ቁ. እና ስራ ለእርስዎ ሳይረከቡ ተመልሰው የነበሩ የቅረጽ W-2 ቅጂዎች


      

የስራ ቅጥር ቀናት ሰራተኞች እና ተቀባዮች በህመም ወይም በጉዳት ምክንያት ሲቀሩ ያልተከፈሏቸው ክፍያዎች እና ለእርስዎ ወይም ለ3ማ ወገን የተፈፀሙ ሳምንታዊ የክፍያ ተመኖች፡፡ የሰራተኖች እና ተቀባዮች የገቢ ግብር ተያያዥ አበል ምስክር ወረቀቶች፣ ቅጆዎች (ቅጽ W-4, W-4P, W-4S, እና W-4V). የግብር ተቀማጭ ሂሳቦች ቀናትና መጠን ያመለከቱት የግብር ተመላሽ ቅጂዎቸው የተመደቡ ጉርሻዎች መዛግብት የቀረቡት ጥቅማጥቅሞች ማጠናከሪያን አካትቶ መዛግብትን መጠበቅ

የንግድ ግብይቶቼን መዛግብት እንዴት መጠበቅ አለብኝ? የንግድ ስራዎ የሚያስገኟቸውን ግዢዎች፣ ሽያጭ፣ የደመወዝ መክፈያ እና ሌሎች ግብይቶች፣ ደጋፊ ሰነዶችን በመዛግብትዎ ውስጥ ማካተት ያስፈልግዎታል፡፡ ጥሩ የመዝገብ አጠባበቅ ስርዓት የንግድ ግብይቶች ማጠቃለያን ያካትታል፡፡ እነዚህም ጆርናሎችና የባህር መዛግብት ተብለው የሚታወቁት መደበኛ ማጠቃለያ መዛግብት ናቸው፡፡ ጆርናል ደጋፊ ሰነዶችን በማሳየት የንግድ ስራ ግብይት በእያንዳንዱ ሁኔታ የሚጠብቁበት ደብተር ነው፡፡

ሌጀር ሁሉንም ጆርናሎችዎን የሚያካትት ነው፡፡ ጆርናሎችን እና ሌጀሮችን በመጠበቅዎ ወይም ባለመጠበቅዎ ሁኔታ ላይ ሳይመሰረት የንግድ ስራ ተግባራት አይነትዎን እንዴት መጠበቅ እንዳለብዎት ለምሳሌ ለአነስተኛ የንግድ ስራዎች የመዝገብ አጠባበቅ ስርዓት የሚከተሉትን ክፍሎች ያካትታል፡፡      

የንግድ ስራ ማረጋገጫ ደብተር የቀን ተቀን የገንዘብ መቀበያ ማጠቃለያ የወርሃዊ የገንዘብ መቀበያ ማጠቃለያ የቼክ መክፈያ የጆርናል የእርጅና ተቀናሽ ቅጽ የሰራተኛ ካሳ መዛግብት

ማስታወሻ: ለንግድ ግብይትዎ ምዝገባ አላማ የሚጠቀሙት ስርዓት እጅግ በጣም አስተማማኝ ስኬትን ያጎናጽፍዎታል፡፡ ለምሳሌ ወጪዎች ሲከሰቱ እና የተመዘገቡትን ደረሰኞች ምንጭ ለመለየት በአጠቃላይ በየቀኑ ግብይቶቹን ለመመዝገብ አዋጭ ነው፡፡ ለተጨማሪ መረጃ እንዴት የንግድ ስራ ግብይትዎን መመዝገብ እንዳለብዎት አስመልክቶ Publication 583, Starting a Business and Keeping Records ያጣቅሱ፡፡


የማስረዳት ሸክም ምንድን ነው? በግብር ተመላሽዎ ላይ የተገበሯቸውን ገቢዎች ተቀናሾች እና መግለጫዎች የማረጋገጥ ኃላፊነት የማስረዳት ሸክም ተብሎ ይታወቃል፡፡ ስለዚህ የተወሰኑ ወጪዎችን ለመቀነስ አላማ የማስረዳት/የማረጋገጥ ኃላፊነት ይኖርብዎታል፡፡ በአጠቃላይ ግብር ከፋዮች ለወጪዎቻቸው መረጃ እና ደረሰኞችን (እንደ አስፈላጊነቱ በማሟላት በቂ መዛግብት መጠበቅ አለባቸው፡፡ እርስዎ በአጠቃላይ የሰነድ ማስረጀዎች እንደ ደረሰኞች፣ የተሰረዙ ቼኮች ወይም ሂሳቦች ወጪዎችዎን ለመደገፍ ሊኖርዎት ይገባል)፡፡ ተጨማሪ ማስረጃ ለጉዞ ለመዝናኛ ለስጦታ እና ለተሽከርካሪ ወጪዎች ያስፈልጋሉ፡፡

Tax  
Read more
Read more
Similar to
Popular now
Just for you