Page 1

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ሐበሻዊ ቃና

ሐበሻዊቃና

በእዚህ ዕትም m የእኛ ሰው በሲድኒ m ኢትዮጵያዊቷ በኒውዮርክ m የ“3ቱ ወፎች” ኮከብ በካምፓላ m “የዘር ግንዳችን ከኢትዮጵያ ነው”

m“አለምዬ ሶራ”በካባካ ቤተመንግስት

7/11

አንደኛ ዓመት ቁጥር 003

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

1

ዩጋንዳ 1,500 ሺልንግ / ኬንያ 60 ሺልንግ / ደቡብ ሱዳን 3 ፓውንድ

አንደኛ ዓመት መታሰቢያ (ልዩ ዘገባ)

ገጽ 4- 8

ነፃነትን በኡጋንዳ ፈለጋት ግና... የኢትዮጵያን ቪሌጅ ባለቤት ምን ይላሉ? ሞትን ማምለጥ ማን ይናገር… ፎቶዎች


ሐበሻዊ ቃና

2

ዜና

በታንዛንያ የታሰሩ 600 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ሊመለሱ ነው

ደቡብ ሱዳን

በስመኝሽ ይቆዬ በጄፍሪ ጌትልማን

በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

ና እየጨፈሩ የጁባን በጣት የሚቆጠሩ የአስፋልት መንገዶች አድምቀዋት አንግ ተዋል። ከአፋቸው የማይጠፋው አንድ ቃል ነበር። “ነጻነት”። ደቡብ ሱዳንውያ ን ነጻነታቸውን ከማግኘታቸው በፊት ለ አምስት አስርት ዓመታት ከሱዳን መንግ ስት ጋር ተዋግተዋል። በውጤቱም ሁለ ት ሚሊዮን የሚጠጉ ደቡብ ሱዳንውያ ን ህይወታቸውን አጥተዋል። የቅዳሜውን በዓል ለማክበር ወደ አደ ባባይ ከወጡት ብዙዎቹ ቢያንስ አንድ የቤተሰብ አባላቸውን በጦርነቱ ያጡ ና ቸው። ለዚህም ይመስላል ስለበዓሉ ሲ ጠየቁ በስሜት የሚሞሉት። የአረብ ዝር ያ ባላቸው ሱዳንውያን ከተሞላው ሰሜ ን ሱዳን ራሳቸውን ለመገንጠል ባደረጉ ት ትግል አባቶቻቸው፣ እናቶቻቸው አ ሊያም ልጆቻቸውን ገብረዋል:፡ እንግሊ ዘኛ አስተማሪ የሆነው ጆርጅ ጋራንግ አ ባቱን ወንድ አያቱን እና 11 ወንድሞቹን በጦርነቱ አጥቷል። በደቡብ ሱዳን የ“ል ደት ቀን” የተሰማውን ለ በ “ኒውዮርክ ታይምስ” ጋዜጣ አጋርቷል። “መላ ሰው ነቴ በደስታ ተሞልቷል”ይላል ጋራንግ። ከጋራንግ የደስታ ስሜት ከፍ ባለ ስሜ ት ውስጥ የገቡ አንዳንድ የኦፊሴሊያዊ በዓሉ ታዳሚዎች ገና የሀገሪቱ ነጻነት ሳ ይታወጅ ራሳቸውን ስተው ሲወድቁ ተ ስተውለዋል። የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜ

ኒውዮርክ ታይምስ ለዓመታት በታንዛንያ እስር ቤት ውስ ጥ ታስረው የቆዩ ወደ 600 የሚጠጉ ኢ ትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው እንዲመ ለሱ ለማድረግ የሁለቱ ሀገራት መንግስ ታት እየተደራደሩ ነው። ኢትዮጵያዊኑ ለእስር የበቁት ወደ ታ ንዛኒያ በህገወጥ መንገድ ለመግባት ሞ ክሯችኋል ተብለው ነው። በርካታ ኢት ዮጵያውያን ከኬንያ በመነሳት በታንዛኒ ያ በኩል አድርገው ወደ ማላዊ በመግ ባት የመጨረሻ መድረሻቸው ወደ ሆነ ው ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ ይሞክራሉ። ስደተኞቹ በደቡብ አፍሪካ የተሻለ ስራ እና ገንዘብ እናገኛለን የሚል እምነት አ ላቸው። ደቡብ አፍሪካ ለመግባት በአ ጓጓዥ “ኤጀንሲዎች” የሚጠየቀው ገንዘ ብ ከፍተኛ በመሆኑ አንዳንዶች ንብረቶ ቻቸውን ሸጠው ነው ለጉዞ የሚነሱት። ለስደተኞች መጠለያ የማትሰጠው ታን ዛኒያ በበኩሏ እንደዚህ ዓይነት ድንበር ተሻጋሪ የውጭ ዜጎችን ያለ ህጋዊ መረ ጃ ስታገኝ በቀጥታ ወደ እስር ቤት ነው የምትልከው። በዚህ ዓይነት ሁኔታ የታሰሩት ኢትዮ ጵያውያን ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎ ች የመጡ ናቸው። በታንዛኒያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙ ወ

ገኖቻቸውን ገንዘብ በማዋጣት ሲረዱ ቆይተዋል። ለአንዳንዶቹም የትራንስፖ ርት ወጪያቸውን በመሸፈን ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ አድርገዋል። የታንዛኒ ያን ድንበር ሲያቋርጡ የሚያዙ ኢትዮ ጵያውያን ቁጥር በመበርከቱ ምክንያት የስደተኞቹን የትራንስፖርት ወጪ ሸፍ ኖ ወደ አገር ቤት መመለስ አዳጋች ሆ ኗል። የስደተኞቹ ጉዳይ በዚህ ሁኔታ ላይ እ ንዳለ ናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤ ምባሲ ከታንዛኒያ መንግስት ጋር መደራ ደር ይጀምራል። እንደ ኤምባሲው ም ንጭ ከሆነ ድርድሩ ተሳክቶ ከታንዛኒያ መንግስት ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷ ል። የታንዛኒያ መንግስት 600 የሚጠ ጉትን ስደተኞች ለመልቀቅ የተስማማ ሲሆን የዓለም የስደተኞች ድርጅት (አ ይ.ኦ.ኤም) የትራንስፖርት ወጪ ለመሸ ፈን ቃል ገብቷል። የስደተኞች ጉዳይ ያስመረረው የታንዛ ኒያ መንግስት ኢትዮጵያ በሀገሪቱ ለም ን ኤምባሲ እንደማትከፍት በተደጋጋ ሚ ሲጠይቅ ቆይቷል። የኢትዮጵያ መ ንግስት ግን በአሁኑ ወቅት አዲስ ኤምባ ሲ ለመክፈት በጀቱ የለኝም የሚል ምላ ሽ ያቀርባል።

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

በጥብቅ የጸጥታ ቁጥጥር ምክንያት ከቀናት በፊት ጭርታ ይስተዋልባት የነበረችው የደቡብ ሱዳን ዋና ከተማ የሆነችው ጁባ ቅዳሜ ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም መተንፈሻ አጥታ ውላለ ች። የሀገሪቱ አባት የሚባሉት ጆን ጋ ራንግ መካነ መቃብር የሚገኝበት በተ ለምዶ “ከስተምስ” ተብሎ የሚጠራ ው ቦታ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አ ጥልቅለቅውት ነበር። ፊታቸው ላይ ደስታ እና እፎይታ የ ሚነበብባቸው ደቡብ ሱዳንውያን የ አዲሰቱ አገራቸውን ውልደት ለማክ በር ማልደው ነበር በዓሉ ወደሚከበ ርበት ቦታ መትመም የጀመሩት። በ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሌሎች ደቡብ ሱ ዳናውያን ግን በዓሉን አስቀድመው ነ በር የጀመሩት:፡ ደስታቸውን ለመግለ ጽ ንጋትን አልጠበቁም። አርብ እኩለ ለሊት ላይ የተተኮሰውን የደስታ ርች ት ተከትለው በርካቶች አቧራማ በሆ ኑት የጁባ መንገዶች ላይ ደስታቸው ን ለመግለጽ ወጥተዋል። የሰሜን ሱዳን ግልባጭ የሆነውን ባ ንዲራቸውን እያውለበለቡ፣ በየመኪ ናው ላይ እየተንጠላጠሉ፣ እየዘፈኑ እ

ጠኛ ጄፍሪ ጌትልማን አንዲት ሴት ከጠ ዋቱ ሶስት አካባቢ ራሷን ስታ ከወደቀ ች በኋላ ስትወስድ ተመልክቷል። ረፋ ድ ሆኖም የገገረውን ጸሀይ ያስተዋለው ጋዜጠኛ ከታዳሚዎቹ መካከል አንዱን ምን ሆና እንደሆነ ይጠይቀዋል። “ራሷ ን ያሳተችው በደስታ ነው። ዛሬ ሌሎች በርካቶች ይኖራሉ” ሲል መልሶለታል። ልክ ከቀኑ ሰባት ሰዓት 20 ሲል ደቡ ብ ሱዳንውያን በጉጉት ሲጠብቁት የነበ ረ ነገር ሆነ። ደቡብ ሱዳን ሪፐብሊክ የ ሚል ስያሜ ስያሜ የያዘችው ሀገራቸው በይፋ ተወለደች። የሀገሪቱ የህግም መ ወሰኛ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የሆኑት ጄ ምስ ዋኒ ኢጋ “ረጅሙን እና ጀግንነት የ ተሞላበትን የህዝባችንን ትግል በማስታ ወስ” ሲሉ ስነስርዓቱን አስጀመሩ። ጥቂ ት ደቂቃዎች ቆይቶ የሱዳን ባንዲራ ወ ርዶ የደቡብ ሱዳን ባንዲራ ተሰቀለ። የ ደቡብ ሱዳን ባንዲራ እንደ ሱዳን አቻ ው ተመሳሳይ ቀለማት ያለው ሲሆን የ ሚለየው በአደራደሩ ነው። ጥቁር አፍ ሪካውያን እንጂ አረብ አይደለንም የሚ ሉት ደቡብ ሱዳንውያን በሱዳን ባንዲ ራ ከታች ያለውን ጥቁር ቀለም ወደ ላ ይ አምጥተውታል። የሱዳን ባንዲራ ከ ታች ወደ ላይ ከመገልበጡ ሌላ ኮከብ ም ታክሎበታል። የባንዲራ መስቀል ስነስርዓት ሲካሄድ

ታዳሚው አካባቢውን በደስታ ጩኸት አናጋው። “መብሩክ ጃኑብ ሱዳን” ሲሉ ም ከሰሜን ሱዳን በወረሱት አረብኛ ቋ ንቋ ከፍ አድርገው ጮኹ። “ደቡብ ሱዳ ን እንኳን ደስ ያለሽ”። የሚታወቁበትን ባርኔጣ ያደረጉት የደቡብ ሱዳን ፕሬዝ ዳንት ሳልቫ ኪየር የሽግግር ጊዜ ሕገ መ ንግስቱ ላይ ፈረሙ። ከዚያ ረጃጅሞቹ ንግግሮች ተከተሉ። “ዛሬ ለአፍሪካ ውብ ቀን ነው። ረጅም ጊዜ የወሰደው ግጭት መቆሙ ትልቅ ስ ኬት ነው” የተባበሩት መንግስታት ጠ ቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት የሆኑት ጆሴፍ ዴይሲስ በሚያዩት ነገር ተደስተው ተ ናግረዋል። የ54ኛዋ የአፍሪካ አገር አፈ ጣጠር በእርግጥም ለብዙዎች እንደተአ ምር የሚታይ ነው። ትላንት ሲጋደሉ የ ነበሩት የሰሜን ሱዳን መንግስት ሰዎች እና የደቡብ ሱዳን አማጽያን ዛሬ በፕሬ ዝዳንቶቻቸው ተወክለው በዓል እያከበ ሩ ነው። ትላንት ከደቡብ ሱዳን ጋር ጦ ርነት ገጥመው የዛሬው ቀን እንዳይመያ ጣ ሲከላከሉ የነበሩት ፕሬዝዳት ኦማር ሀሰን አልበሽር ዛሬ የሀገሪቱን ነጻነት ተ ቀብለው የክብር እንግዳ ሆነው ጁባ ተ ገኝተዋል። እንደእርሳቸው ሁሉ አሉ የተባሉ የአ ፍሪካ መሪዎች የበዓሉ ተካፋዮች ሆነዋ ል። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር መለ

የካምፓላ መድኃኒያለም ቤተክርስቲያን ጠቅላላ ጉባኤ ሊያካሂድ ነው በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ሐበሻዊ

ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

ከተመሰረተ ከአስር ዓመታት በላይ ያ ስቆጠረው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋ ህዶ የኡጋንዳ መካነ መድሃኒአለም ቤተ ክርስቲያን በካምፓላ ጠቅላላ ጉባኤ ሊ ያካሂድ ነው፡፡ እሁድ ሐምሌ 3 ቀን 2003 ዓ.ም ይካ ሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው ጠቅላላ ጉባ ኤ ከተያዙት አጀንዳዎች መካከል በተሻ ሻለው የቤተክርስቲያኒቱ ረቂቅ መተዳደ ሪያ ደንብ ላይ መወያየትና ማጽደቅ እን ደዚሁም ለአዳዲስ የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ ይ ገኝበታል፡፡ የቤተክርስቲያኒቱ መተዳደሪያ ደንብ ተሻሽሎ እንዲዘጋጅ የተደረገው ስልጣ ንና ኃላፊነትን በመለየት አንዳንድ ጉድ ለቶች አሉበት፣ ከዘመኑ ጋርም የሚጣ ጣም ሆኖ አልተገኘም በሚል ነው። አ ሁን በስራ ላይ ያለው ደንብ ቤተክርስ ቲያኒቱ ከተመሰረተች ጀምሮ ሲሰራበት የቆየ ነው። ከደንብ ማሻሻል በተጨማሪ እንደ አጀ ንዳ የቀረበው የስራ አስፈጻሚዎች ምር ጫ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ “መተዳደሪ ያ ደንቡ ከሚፈቅደው ውጪ ስልጣን ላ ይ ቆይተዋል” በሚል ነው፡፡ “ለረጅም ጊ ዜ ቦታው ላይ ከመቆየታቸው የተነሳም መሰላቸት ይታይባቸዋል” በሚል ቅሬታ ነው አዲስ ስራ አስፈጻሚ ለመምረጥ ሀ

የኡጋንዳ መካነ መድሃኒአለም ቤተክርስቲያን በካምፓላ

ቃና

በሐበሻ ኮሚዩኒኬሽን ሊትድ በየ15 ቀኑ የሚታተም ጋዜጣ

ዋና አዘጋጅ- ተስፋለም ወልደየስ

ሳብ የቀረበው፡፡ በጠቅላላ ጉባኤው እንደሚመረጥ የሚ ጠበቀው አስመራጭ ኮሚቴ በአንድ ወ ር ጊዜ ውስጥ ለስራ አስፈጻሚነት ብቁ ናቸው ያላቸውን እጩዎች በማቅረብ በ ጠቅላላ ጉባኤው እንደሚያስመርጥ ይ ጠበቃል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቤተክርስቲያኒቱ አስተዳዳሪ በአባ ኃይለእየሱስ እማኘው ና በስራ አስፈጻሚው መካከል የተፈጠ ሩ አለመግባባቶችን ተከትሎ ከ15 ቀን በ ፊት የህዝብ አስተያየት መሰብሰቢያ መ ድረክ በባለአደራ ቦርዱ አማካኝነት ተጠ ርቶ ነበር። መድረኩን የመሩት የቦርዱ ሰ ብሳቢ አቶ ባንቲሁን ኃይሌ አሉ ያሏቸ ውን ችግሮች አቅርበው ምዕመኑ እንዲ ወያይባቸው አድርገዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ሁለቱም ወገን (ስ ራ አስፈጻሚውና የቤተክርስቲያኒቱ አስ ተዳዳሪ) ተከስተዋል ያሏቸውን ችግሮች ና ለችግሮቹም መንስኤ ሆነዋል ያሏቸው ን ጉዳዮች ለተሰብሳቢው አሰምተዋል፡፡ የስራ አስፈጻሚውን በመወከል ንግግር ያደረጉት የመቶ አለቃ አባተ በቤተክርሰ ቲያኗ ውስጥ ለተከሰተው ችግር አስተዳ ዳደሪውን ተጠያቂ ያደረጉ ሲሆን ከስራ አስፈጻሚው ጋር ተባብረው አይሰሩም፣ ህግም አያከብሩም የቤተክርሰቲያኒቱ ን ብረትም እየተመዘበረ ነው በማለት ቅሬ ታቸውን አቅርበዋል፡፡ የስራ አስፈጻሚውን ንግግር ተከትሎ

ምላሽ የሰጡት የቤተክርስቲያኒቱ አስተ ደዳሪ አባ ኃይለእየሱስ እማኘው በበኩ ላቸው ህግ ያፈረስኩት እኔ ሳልሆን ስራ አስፈጻሚው ነው በማለት ምላሽ የሰጡ ሲሆን “ህግን ጥሶ ህጋዊ መሆን አይቻል ም” ብለዋል፡፡ አስተዳዳሪው እንዳሉት በቤተክርስቲያኒቱ እየተፈጠረ ላለው ች ግር መንስኤ አንዳንድ ካህናት ለህዝበ ክ ርስቲያን አለማሰብና የስራ አስፈጻሚው ለህግ ተገዥ አለመሆን ናቸው፡፡ በእለቱ የተሰበሰበው ቁጥሩ ከፍ ያለ ህ ዝበ ክርስቲያም ከሁለቱም ወገን የቀረቡ ሀሳቦችን መነሻ በማድረግ ለችግሩ መን ስኤ ያላቸውንና መፍትሄዎቻቸውን ጠ ቁሟል፡፡ ተሳታፊዎቹ እንዳሉት የቤተክ ርስቲያን አገልጋዮች ችግር ሲፈጠር እር ስ በእርሳቸው በመነጋገር ሊፈቱት ይገ ባል፡፡ ይህ ካልሆነ ሁሉም የቤተክርስቲ ያኒቱን ህግ እንዲያከብሩ አሳስበዋል፡፡ በሁለቱ ወገኖች መካከል የተከሰተውን አለመግባባት ተከትሎ አስተዳዳሪው ከ ስልጣናቸው መነሳታቸውን የሚገልጽ ደ ብዳቤ ከአውሮፓና ምስራቅ አፍሪካ ሊ ቀ ጳጳስ አቡነ ኤሊያስ የደረሳቸው ሲሆ ን በስብሰባው ላይ አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት አስተዳዳሪው ከስልጣን መነ ሳት ህግን ያልተከተለና አግባብነት የሌለ ው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአስተዳዳሪው ን ከስልጣን መነሳት እንቃወማለን ያሉ ምዕመናንም የአቤቱታ ፊርማ በማሰባሰ ብ ለባለአደራ ቦርዱ አቅርበዋል፡፡

የዝግጅት ክፍሉ አድራሻ ዩጋንዳ ካምፓላ ጋባ ሮድ-ካንሳንጋ ዲዲስ ወርልድ አጠገብ ባለው የናይል ቢራ ማከፋፈያ ህንጻ አንደኛ ፎቅ ቁጥር 6

የባለአደራ ቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ባንቲሁ ንም ከሁለቱም ወገን አሉ የተባሉት ች ግሮች ለህዝብ መቅረባቸውና ውይይት መደረጉ ለቤተክርስቲያንቱ ሰላም የሚበ ጅ መሆኑን ገልጸው በጠቅላላ ጉባኤው ወቅትም መምረጥና መመረጥ መብት ባ ላቸው የሰበካ ጉባኤው አባላት የህዝበ ክርስቲያኑ ጥያቄ ምላሽ እንደሚያገኝ ተ ናግረዋል፡፡ ይሁን እንጂ ብዙው ምዕመን የሰበካ ጉ ባኤው አባል ባለመሆኑና አባል የሆነው ም ጠቅላላ ጉባኤ ሲጠራ ስለማይገኝ ኮ ሚቴና የተለያዩ ኃላፊዎችን በመምረጡ ሂደት ችግር እየተፈጠረ መሆኑን ሰብሳ ቢው ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም ምዕመኑ ችግር ሲፈጠር ከመማረር የሰበካ ጉባኤ ው አባል እንዲሆንና በስብሰባዎችም እ የተሳተፈ መብቱን እንዲያስከብር አሳስ በዋል፡፡ እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ አንዳንድ ተሰብሳቢዎች ግን አባል ለመሆን ጥያቄ አቅርበው መከልከላቸውን በመድረኩ ላ ይ ገልጸዋል፡፡ ይህንን ተከትሎም ሁለት አስተባባሪዎች ከስራአስፈጻሚ ኮሚቴ ው ጋር ሆነው እስከ ጠቅላላ ጉባኤው ድረስ አዳዲስ አባላትን እንዲመዘግቡ ከ ስምምነት ተደርሷል፡፡ ጠቅላላ ጉባኤው እስከ አሁን ሲንከባለ ሉ ለመጡት ችግሮች መፍትሄ እንደሚ ሰጥና የቤተክርስቲያኗን ቀጣይ አካሄድ እንደሚጠቁም ይጠበቃል፡፡

ስልክ +256-778-693669 ፖ.ሳ.ቁ-28268 ካምፓላ-ኡጋንዳ

ኢሜይል habeshawikana@gmail.com


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

3

ዜና

ፎቶ- ኤ ኤፍ ፒ

ስ ዜናዊን ጨምሮ የኡጋንዳ ፕሬዝዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ፣ የኬንያው ሞዋይ ኪባ ኪ፣ የደቡብ አፍሪካው ጃኮብ ዞማ፣ የዚ ምባቤው ሮበርት ሙጋቤ አልቀሩም። እነዚህ ሁሉ የሀገር መሪዎች በበዓሉ ስፍ ራ ሲደርሱ ያልተደረገው ነበር ለአልበሽ ር የተደረገላቸው። የበዓሉ ታዳሚ በደ ማቅ ጭብጨባ ነበር የተቀበላቸው። ዳ ንኤል አቴም የተባለ ደቡብ ሱዳናዊ ጭ ብጨባው እና ሞቅ ያለው አቀባበል “የ ደስታ አይደለም” ባይ ነው። ለበዓሉ ሱ ፉን ግጥም አድርጎ እና አነስተኛ ባንዲ ራ የያዘው ዳንኤል “ጠላትህን ስታነጋግ ር አንተ እኮ መጥፎ ነህ እያልክ አይደለ ም። በልብህ ያለውን አንተ ታውቃለህ” ሲል ደቡብ ሱዳናውያን ለአልበሽር አሁ ንም ድረስ ያልተለወጠ አመለካከት እን ዳላቸው አስረድቷል። (ይህ ዘገባ መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል)

ፎቶ- ሮይተርስ

የዓለም 193ኛ አገር ሆነች የደቡብ ሱዳን ባንዲራ እንደ ሱዳን አቻው ተመሳሳይ ቀለማት ያለው ሲሆን የሚለየው በአደራደሩ ነው

ፎቶ- ሮይተርስ

(በስተግራ ከታች) ትላንት ሲጋደሉ የነበሩት የሰሜን ሱዳን መንግስት ሰዎች እና የደቡብ ሱዳን አማጽያን ዛሬ በፕሬዝዳንቶቻቸው በኦማር ሀሰን አልበሽር እና ሳልቫ ኪር ተወክለው የነጻነት በዓል አክብረዋል

ፎቶ- ኤ ኤፍ ፒ

ፎቶዎች(በስተግራ ከላይ) በሺህዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳናውያን ደስታቸውን ለመግለጽ በእኩለ ለሊት በጁባ መንገዶች ወጥተዋል።

በሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ ሱዳንውያን በሀገራቸው ውልደት ላይ ለማክበር የሀገሪቱ አባት በሚባሉት ጆን ጋራንግ መካነ መቃብር ተገኝተው ነበር

አስተያየት q ጸሁፍ q ጥቆማ…

q

በሐበሻዊ ቃና ፖስታ አድራሻ ፖ.ሳ.ቁ 28268 ካምፓላ-ኡጋንዳ ብለው ይጻፉልን።

ወይም በኢሜይል habeshawikana@gmail.com አድርሱን። በ+256-778-693669 ይደውሉልን።


ሐበሻዊ ቃና

4

ልዩ

የማይረሳው ዕለት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ዘገባ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ነፃነትን በኡጋንዳ ፈለጋት ግና ሕማምን አገኘ! ዕለታዊው የኡጋንዳ ጋዜጣ “ዴይሊ ሞኒተር” ከዓመት በፊት በካምፓላ የደረሰውን የቦምብ አደጋ ለማስታወስ የጥቃቱ ሰለባ ሰዎችን ታሪክ ለአንድ ወር ያህል በተከታታይ አትሟል። እ.ኤ.አ በጁን 21 ቀን 2011 በወጣው እትሙ ነፃነትን እና ሠላምን ፈልጎ ወደ ኡጋንዳ ስለመጣ ነገር ግን በአደጋው ምክንያት ከቆሰለ በኋላ እስካሁንም ድረስ በጀርባ አጥንት ህመም የሚሰቃይ ኢትዮጵያዊ ታሪክ አውጥቷል። የጋዜጣው ዘጋቢ ፍላቪያ ላኜሮ የጻፈችውን እንደሚከተለው አቅርበነዋል።

ጌታ ያውቃል ተሰማ

ቶ ዮሐንስ ምህረት ከአገሩ ከኢትዮጵያ የመጣው ሠላምን እና ነፃነትን ፈልጎ ሲኾን ለሦስት ዓመታትም ይ ህንኑ የሚፈልገውን ነገር ከኡጋንዳ አግኝቷል። ይህ ግን በሽብርተኞች እንደተፈጸመ በተጠረጠረው የቦ ምብ ፍንዳታ ሰበብ 76 ሰዎች ሞተው በመቶ የሚቆጠሩ ሌሎችን ቁስለኛ እስከኾኑበት እስከ ጁላይ 11 ቀ ን 2010 ድረስ ብቻ ነበር የቀጠለው። በዚያች ሰንበት ዩሐንስ እና ጓደኞቹ የዓለም ዋንጫውን ፍፃሜ በማስመልከት መዝናናት የጀመሩት ጨዋታው ከሚ ተላለፍበት ቀደም ብለው ነው። ከአንዱ ቡና ቤት ወደሌላው ሲሉ ይቆዩ እና በመጨረሻ ካባላጋላ በሚገኘው የኢት ዮጵያን ቪሌጅ ሬስቶራንት ማረፊያቸውን አደረጉ። ከቆይታ በኋላ በዚያ ቦታ መልአከ ሞት መቅሰፍቱን አወረደ። ዩሐንስ በጣም ከባድ ፍንዳታ እንደሰማ እና ግርግር እንደተፈጠረ ያስታውሳል። የመጨረሻው ቆጠራ ሲደረግ 15 ሰ ዎች መሞታቸው ተረጋገጠ። እንደመታደል ኾኖ ዮሐንስ እና አምስት ጓደኞቹ ተረፉ። ነገር ግን ጠባሳው አልቀረላቸ ውም። አካል ጉዳተኝነትን ፍራቻ! “በጣም አስቀያሚ ቀን ነበር፤ ማውራትም አልፈልግም” ያለው ስለጉዳዩ የበለጠ እንዲነግረኝ ስጎተጉተው ነበር። ከአደጋው በፊት ዮሐንስ ባለቤቱን እና ልጁን በከባድ መኪና ሾፌርነት ተቀጥሮ በሚያገኘው ገቢ ያስተዳድር ነበር፤ ያ ሁሉ አሁን ቀርቷል። ፍንዳታዎቹ ሕብለ ሰረሰሩን (ስፓይናል ኮርዱን) ጎድቶታል። ጀርባውን ስለሚያመውም ለረጅም ሰዓት ቀጥ ብሎ መቀመጥ አይችልም። ከአደጋው በኋላ በሦስት ወር ውስጥ ቀዶ ሕክምና ሊደረግለት ይገባ ነበር። ነገ ር ግን ከአንድ ዓመት በኋላም ቀዶ ህክምናውን አሁንም እየጠበቀ ይገኛል። “አንዳንድ ዶክተሮች ጉዳቱ ከፍ ያለ ስለኾነ እዚህ ቀዶ ሕክምናው ሊደረግልኝ እንደማይችል ተናግረዋል። እኔም እዚ ህ ማድረግ እንደሌለብኝ ይሰማኛል። አለበለዚያ አካል ጉዳተኛ ኾኜ መቅረቴ ነው” ይላል። “አንዳንዶች ግን እዚሁ ቀ ዶ ህክምናውን ማድረግ እንደምችል ይነግሩኛል ” ሲል ጨምሮ ይናገራል። የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች መርጃ ድርጅት (ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር) ቀዶ ሕክምናው የትም ይደረግ የት “ስፖን ሰር” ሊያደርገው ፈቃደኛ ነው። ይህን ሊያደርግ የሚችለው ግን ከሙላጎ ሆስፒታል በሚያገኘው ይሁንታ ብቻ ነው። ዩሐንስ ይህን ይሁንታ ለማግኘት በተደጋጋሚ በሐኪም ቢታይም ሊሳካለት እንዳልቻለ ይናገራል። “ዶክተር አይደለሁም ግን አንድ ሐኪም ሕክምናውን እዚህ ማድረግ አደገኛ ነው ካለ ጥሩ ምክር ይመስለኛል፤ ለሕ ይወቴም የሰጋሁት በዚህ ምክንያት ነው” ይላል ዮሐንስ። የዩሐንስ ባለቤትም የራሷ ስጋቶች አሏት። ፍንዳታውን ተከትሎ ባለቤቷ በካምፓላ ኢንተርናሽናል ሆስፒታል እንዲተ ኛ ሲደረግ ለሦስት ቀናት የህክምና ክትትል የሚያደርግለት አልነበርም። ምክንያቱ ደግሞ ጥንዶቹ ለህክምናው የሚከ ፍሉት ገንዘብ ስላልነበራቸው ነው። “በጣም ተጎድቶ ነበር። የምንከፍለው ስለሌለን አንዳንድ ዶክተሮች ወደ ቤቱ እን ድንወስደው ነግረውን ነበር። ነገር ግን ከሦስት ቀናት በኋላ የፖሊሱ አዛዥ ሜጀር ጀነራል ካሌ ካዩሁራ በመምጣታቸ ው ሕክምናው ተጀመረ” ትላለች። እንደ እርሷ አባባል ጄኔራል ካዩሁራ ቁስለኞቹ ክፍያ ከመፈጸማቸው በፊት መታከ ም እንዲጀምሩ መመሪያ በመስጠታቸው ምክንያት በብዙ ታማሚዎች ዘንድ ተወድደዋል። መዝሙር እና መብራት ዮሐንስ በሆዱ፣ በደረቱ እና በአንጀቱ ውስጥ ያሉ የቦምብ ቁርጥራጮችን ለማውጣት ያኔ ቀዶ ሕክምና ማድረጉን እና ውጤታማም እንደነበረ ይናገራል። ተጨማሪ ቀዶ ሕክምና እንዲረግለት የሚጠብቀው ዮሐንስ አእምሮውን ዕረፍት ከ ሚነሱት ፍርሃቶች ጋር እየታገለ ይገኛል። “ሕዝብ የሚሰበሰብበት ማንኛውም ቦታ መሔድ አልችልም” ይላል ዮሐንስ። “ብዙ ሰውም አጠገቤ ሲሰበሰብ እረበሻለሁ፣ እፈራለሁ። ሆቴል እና ካፍቴሪያም መሔድ አልፈልግም።” ከአደጋው በኋላ የተፈጠረው ለጨለማ ያለው ፍርሃት እስካለፈው ወር ድረስ ቆይቷል። መብራት ከጠፋ መተኛት ይ ቸገርም ነበር። ሰዎች ተሰብስበው ኳስ ጨዋታ ሲመለከቱም ይረበሻል። በራሱ ወጪ ለረጅም ጊዜ የቆየ የ“ሳይኮሎጂ” ሕክምና ካደረገ በኋላ ግን ወደ ጤናማ ኑሮው ለመመለስ እየሞከረ ነው። ባለቤቱ “ሌሊቱን ሙሉ መዝሙር እየሰማን ነው የምናድረው” ትላለች። “ሲነቃ መብራት ጠፍቶ ካገኘ ወይም መዝ ሙር ከሌለ በጣም ይፈራል” ስትል የዮሐንስን ጭንቀት ታስረዳለች። ዮሐንስ በበኩሉ ጀርባው ላይ በሚሰማው የማቃ ጠል ስሜት ከእንቅልፉ እንደሚባንን እና አንዳንድ ጊዜም አንድ እግሩ እንደሚደነዝዝ ይናገራል። አንዳንድ ምሽቶችም የማይመቹ እንደሚኾኑበት ይናገራል። “ምንም አይነት ቀዶ ህክምና ስላላደረግሁ ዝም ብዬ አምላኬን የሚያመጣውን እየጠበቅሁ ነኝ። ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም” ሲል ያለበትን አስቸጋሪ ሁኔታ ያስረዳል።

ኤፍሬም ተስፋገርጊስ

ሃብቶም ግርማይ

ፎቶ- ፍላቪያ ላኜሮ

ስምዖን የማነ

ዩሐንስ ምህረት ከባለቤቱ እና ልጁ ጋር

ኤፍሬም ንዋይ

ካሌብ ተከስተ

ናርዶስ መብራሃቱ የሚጠበቀው ስልክ ቤተሰቡን ለመርዳት ሲል መኪና ለማሽከርከር ይሞክራል። ነገር ግን ቀኑን ሙሉ መንዳት አይችልም። ቤተሰቡ ኑሮን እየገፋ ያለው በጎረቤቶች እና በበጎ አድራጊዎች ድጋፍ ነው። ዮሐንስ ምንም እንኳን በዚህ አሳዛኝ አደጋ ውስጥ ቢያልፍም አሁ ንም ለኡጋንዳውያን ያለው ክብር ትልቅ ነው። እነርሱን ሲገልጻቸ ውም “ደግ እና ሰላማዊ ናቸው” እያለ ነው። “በእኔ አገር ሰዎች ሲ ጠጡ ይጣላሉ። ብዙውን ጊዜም ረብሻ አይጠፋም” ይላል ሰላማ ዊነታቸውን ለማጠየቅ። “ኡጋንዳን እወዳታለሁ። የኡጋንዳን መን ግሥትም አመሰግናለሁ” ይላል። ዮሐንስ ወደ ሬስቶራንት እና ካፌዎች መሄድ ቢያስፈራውም አሁ ንም አልፎ አልፎ አደጋው ወደ ደረሰበት የ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ ሬ ስቶራንት” ጎራ ይላል። በምግብ ቤቱ የተሰራው መታሰቢያ በተመ ረቀበት ቀን እዚያው ነበር። የኢትዮጵያ በዓላት ሲከበሩም ወደ ም ግብ ቤቱ ይሔዳል። በእግዚአብሔር እና ከአማኞች ጋር ባለው ግንኙነት የሚጽናናው ዮሐንስ አሁንም ቢሆን መረጋጋት አልቻለም። ከዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር እስኪደወልለት እና እንዴት እንደሚኾን እስከሚነገረው ልቡ እን ደተንጠለጠለ አለ።


ሐበሻዊ ቃና

ልዩ

የማይረሳው ዕለት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

5

ዘገ

ማሜ መንገሻ “የኢትዮጵያውያን ገጠር ምግብ ቤት” (ኢትዮጵያን ቪሌጅ ሬስቶራንት) ባለቤት እና ዋና ስራ አስኪያጅ ናት። የዛሬ ዓመት ግድም በምግብ ቤቷ ስለተከሰተው እና ለ15 ሰዎች ሞት ምክንያት ስለሆነው የቦምብ ፍንዳታ፣ ከአደጋው በኋላ ስለነበረው ሁኔታ እና ስለ ወደፊት አቅዷ ከ“ሐበሻዊ ቃናው” ተስፋለም ወልደየስ ጋር ቆይታ አድርጋለች።

ማሜ እና “ቪሌጅ” ከዓመት በኋላ

አደጋው የተከሰተበትን ቅጽበት መለስ ብ ለሽ አስታውሽን? ትንሽ ደቂቃ ነበር የቀረው። በዚያን ሰዓት በጣ ም ብዙ እንግዳ ስለነበር ምግብ እየሰራን፣ ሰው እ ያስተናገድን፣ መቀመጫ ጠፍቶ ነበር። እኔ ራሴ ነ ኝ የመጨረሻውን መስተንግዶ ያደረግኩት። አም ስት ኢትዮጵያኖች ነበሩ። ገንዘብ ሰጥተውኝ ታዘ ዝኳቸው። ለእነሱ ቢራ ከፈትኩላቸው። ቢራ እ ንድቀይርላቸው ጠይቀውኝ ነበርና ቅያሬውን ተ መልሼ ይዤ ሄድኩኝ። ከዚያ ሁለት ደቂቃ አይ ሞላም። በጣም ኃይለኛ ድምጽ ተሰማ። እኔ ፕሮ ጀክተሩ ነበር የመሰለኝ። “ማናጀሩን” ጮኼ ተጣ ርቼ “ምንድነው? ፕሮጀክተሩ ነው?” አልኩት። ማናጀሩ እየሮጠ ወደዚያ ሲሄድ እኔም ተከትየው ሮጥኩ። “አይ ማሜ! አይዞሽ በርቺ። አደጋ ነው” አለኝ። “ምን?” ብዬ ስሮጥ እነዚያ ያስተናገድኳቸ ው ልጆች ከወንበር ላይ ወድቀው አየኋቸው። ወ ድቀው “አይዞሽ ማሜ፣ አይዞሽ” ሲሉኝ በቃ መ ፈጠሬን ጠላሁት። በሀገራችንም ባህል ወደ አንተ የመጣን እንግዳ አስተናግደህ በሰላም ከቤትህ ሲሄድ ነው ደስ የ ሚለው። እንኳንስ እንደዚህ ዓይነት መጥፎ አደ ጋ ቀርቶ ሰው ትን እንዲለው እንኳ አትፈልግም። ውሃ ለመስጠት እንኳ ትሯሯጣለህ። እና የተከሰ ተው ነገር በጣም ነው ያስደነገጠኝ። በዚያ ድንጋጤ ውስጥም ሆነሽ ሰዎችን ለመርዳት ትሞክሪ ነበር…. ሁኔታው ሲከሰት እጅግ በጣም ያሳዝናል። ሆኖ ም ግን እጅግ ቢያስደነግጥም ወዲያውኑ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው የሚደሙ “እርዱን” የሚሉ ሰ ዎች ስለነበሩ መፍትሄው ከማልቀስ ይልቅ መርዳ ት ነው። ፈረንጆች በጣም ተጎድተው እየደሙ ነ በር። ቆሜ ሳስበው ደግሞ ከመርዳት ሌላ ምንም ዓይነት ምርጫ የለም። እና የ“ሬስቶራንቱም” ባ ለቤት ስለሆንኩኝ ከመሸበር ተቆጥቤ ሰራተኞቹ ን ማስተባበር፣ የመንግስት አካላት ጋር ደውሎ እ ርዳታ መጠየቅ፣ የተጎዱትን ሰዎች ወደ ሆስፒታ ል ማድረስ፣ የሞቱትን ደግሞ አስክሬናቸው ወደ ሆስፒታል እንዲሄድ ማድረግ ነበረብኝ። ያን ቀን መቼም አልተኛንም። በሚቀጥለው ቀን ከባልደረቦቼ ጋር በሆስፒታል የተኙትን ቁስለኞ ች በየቦታው፣ በየክፍላቸው ሄደን በግል አይተና ቸዋል። የህክምና እርዳታ እንዲሰጣቸው መንግ ስትን ጠይቀን ተፈቅዶልናል። ሰው ሲሞት፣ ሰው ደም በደም ሆኖ አይቼ አላ ውቅም። እንደዚህ ዓይነት ነገር ለመጀመሪያ ጊ ዜ ሳይ ነው። እኔ ምግብ ማቅረብ፣ ሰው ማስተ

ናገድ፣ አገልግሎት መስጠት ነው እንጂ አንደዚ ህ ዓይነት ነገር አይቼ አላወቅም። እንደውም ጎበ ዝ ነበርኩ። ሴት ልጅ ሆኜ እንደዚህ ዓይነት ሁኔ ታ ሲከሰት ከባድ ነው። አንኳን ለእኔ ለማንም ሰ ው የሚያስደነግጥ ነውና። ከባድ ነው። በጣም ከ ባድ ነው። በቃላት አይገለጽም። ያን ሁሉ ሰው አ ስተናግዳለሁ ብለህ ከቤትህ አስክሬን ሲወጣ በ ጣም ከባድ ነው። ውሎ ሲያድር ነገሩ እየረገበ ይሄዳል። ግን በጣ ም ነው የሚያሳዝነው። አሁንም ቢሆን ከህሊናዬ የማይጠፋው የ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” አፍቃሪ የሆ ኑ ደንበኞች እዚህ መጥተው ይህ አደጋ ተከስቶ ባቸው በማየቴ ህመሙ እስካሁንም አለ። የሚረ ሳ ነገር አይደለም። አደጋው በአልሻባብ አሸባሪዎች አጥፍቶ ጠፊዎ ች እንደተፈጸመ ተነግሯል። ግን እንዴት እንደተ ከሰተ በዝርዝር የሚታወቅ ነገር አለ? እኔ በእውነት ለመናገር በዚያን ጊዜ ይሄኛው ነ ው ይዞ የገባው፣ ያኛው ነው የሚባል አይደለም። ከ350 እስከ 400 ሰው ለማየት በጣም አስቸጋ ሪ ነው። ሁሉም ደንበኛ ነው። እኛ ማስተናገድ ነው። እያንዳንዱ ጠረጴዛ እየሄድን አስተናግደና ል። በጣም ደስ የሚል ሆኖ ፍጻሜው ግን በአደጋ ው ምክንያት አሳዛኝ ሆኗል። ማንም ይሁን ያደረ ገው ማን፤ እኔ በዜና ላይ ሰማሁ እንጂ ይኼኛው ን ነው ብሎ ለመናገር በእኔ በኩል በጣም አስቸ ጋሪ ነው። እኔ የ“ቢዝነስ” ሰው ነኝ። እንደዚህ ዓ ይነት ነገር ተከስቶ አያውቅም። በሬስቶራንት ው ስጥ በሃያ ዓመት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያ ነው። አደጋው በደረሰ በሁለተኛው ቀን ፕሬዝዳንት ሙሴቬኒ መጥተው ቤቱን ጎብኝተዋል። ካንቺ ጋርም ተነጋግረዋል። እንዴት ነበር ያን ቀን የነበረው ሁኔታ? ፕሬዝዳንቱም ባለስልጣኖችም ነበሩ። “አይዞሽ፤ ብቻሽን አይደለሽም፤ በርቺ፤ ቢዝነሱ ወደ ነበረበ ት ይመለሳል፤ የምንችለውን ሁሉ ደግሞ እንረዳ ለን” የሚል ቃል ከአንድ ፕሬዝዳንት ሲሰማ በጣ ም ያስደስታል። በተከሰተው ሁኔታ በጣም ደን ግጬ ነበርና እንደዚህ ዓይነት ድጋፍ በዚያ ሰዓ ት ሲሰማ እጅግ በጣም ያስደስታል። ከመንግስት ባለስልጣኖች ጋር የደረሰውን ሁኔታ ተነጋግረን እጅግ በጣም ረድተውናል። ተረባርበውልናል። በዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው የልጆቼ አባ ት በሶስተኛው ቀን ከውጭ መጥቶ የደረሰው። የ መጀመሪያ እርዳታ ያደረገልን እርሱ ነው። በዚህ በአደጋው አጠገቤ ለቆሙት እና በሁለት እግሬ እ ንድቆም ላደረጉኝ ቤተሰቦቼ፣ ወንድሞቼ፣ ዘመዶ ቼ እና ጓደኞቼ አመሰግናለሁ።

አደጋው በግል ህይወትሽ ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ አላሳደረብሽም? አደጋው ከባድ ነው። ግን ከአደጋው በፊት በጣ ም የምወዳት ልጄ የምላት እህቴ ስለሞተች፣ ከዚ ያ ይሄ አደጋ ሲጨመር፣ ደግሞም ወንድሜ ስለ ሞተ ሁሉም ነገር ተደራራበና ትንሽ ከባድ ነበር። እና አሁን ግን ሁሉንም ተቀብየዋለሁ። የመጣው ን ነገር ተቀብዬ እኔ ጎበዝ ሆኜ ባልደረቦቼን ካል መራሁ ቢዝነሱም መስመሩን ስለሚስት፣ ስራዬ ም ስለሆነ እየሰራሁ ነው። የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱም እየተቀየረ ነው። እዚህ ካምፓላ ውስ ጥ የሚመጣ ማንኛውም ሰው፣ ለስራም የመጣ “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ሳያይ አይሄድም። እግዚያ ብሔር ይመሰገን።

ከአደጋው በኋላ የነበሩት ሳምንታት ለአ ንቺ በጣም አስቸጋሪ ነበሩ። ከሀዘኑ ለመ ጽናናት በጣም ከባድ አንደሆነብሽ አይቻ ለሁ። የቆሰሉትን በሆስፒታል ሄደሽ ጠይ ቀሻል። አስክሬን ወደየሀገራቱ ሲሸኝ በ ሁለቱም ቦታዎች ነበርሽ። በጣም ጥል ቅ የሀዘን ስሜት ውስጥ እንደነበርሽ አስ ታውሳለሁ። የሞቱት ልጆች ደንበኞቼ ናቸው። አውቃቸዋለ ሁ። በዚያ ላይ ደግሞ ወጣቶች ናቸው። ይሄ ለ እነሱ አይገባም። ኳስ አይተው ተዝናንተው ሊሄ ዱ ሲሉ ይሄ መሆኑ ያሳዝናል። ፎቶግራፋቸውን ስመለከት መቋቋም ያቅተኛል። እኔ ምንም ዓይነ ት አደጋ ቢደርስብኝ ከዚህ የበለጠ ሊሆን አይች ልም። ሀዘን ላይ የሰው ልጅ ስጋህ ወይም ወንድ ምህ መሆን የለበትም። በእኔ ቤተሰብ ላይ አንደ ዚህ ዓይነት አደጋ ቢደርስብኝ ከዚህ የበለጠ ላዝ ን አልችልም። የሚቀየር ቢሆን በእነሱ ፋንታ እኔ ብሆን ቅንጣት ታህል አይሰማኝም።

ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

ፎቶ- ሬድዬ ኔዘርላንድስ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ለደንበኞቼ ምን ልስጣቸው? አደጋ ሲደርስባቸው አልቅሻለሁ፣ አዝኛለሁ። አንድ መታሰቢያ ማድረግ እንጂ ሌላ አቅም የለኝም።

አሁን ድሮ የነበሩት ደንበኞቼ ተመልሰ ውልኛል ትያለሽ? ይሄ ቤት ለሐበሻው መሰባሰቢያ ቦታው፣ አመት በዓሎችን የ ሚያከብርበት ነበር። ከስሙ ጀምሮ ብዙ ሰው ስለ ኢትዮጵያ ሬስቶራንት ሲያስብ መጀመሪያ የሚመጣለት “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ነውና እንደቀድሞው ሆኗል። ፈረንጆችስ እንደድሮው ይመጣሉ? እኔ ምንም አላስብም። እኔ እኮ ደንበኞቼ ላይ ያ ደረግኩትም ምንም ዓይነት ነገር የለም። እኔም ደ ንበኞቼም የደረሰብን አብረን ነው። እርግጥ እኔ አልሞትኩም እንጂ በቀላሉ አይደለም የተጎዳሁ ት። አንድ ቢዝነሴ ተመትቷል። ሁለተኛ ደግሞ ንብረቴ እና ገንዘቤ ወድሟል። ነገር ግን ከሰው ህይወት አይበልጥም። አንድ ሚዛን ላይ ቢቀመ ጥ የአንድን ነፍስ ዋጋ ሩብ አይሆንም። ከህይወ ት ጋር የሚነጻጸር ጉዳይ አይደለም። ህይወት ስለ ሚበልጥ፤ የእኔ ቢዝነስ ቢበላሽም፤ ምንም ነገር ቢሆን፤ በአደጋው ሰዓት ምንም የሚሰማ ነገር አ ይደለም። ግን ሲቆይ…እንግዲህ የሞተውም ይቀ በራል፣ የቆሰለውም ይታከማል። የእኔ ቁስል ደግ ሞ ከባድ ነው። የእኔ ደግሞ ሃያ ዓመት የተለፋ ድ ካም ነው። እንደዚህ የኮራሁባቸው ደንበኞቼ ጎኔ ባይቆሙ ኖሮ የሚመጣውን አደጋ እንግዲህ የዓ ለም ህዝብ መፍረድ ይችላል። ግን እጅግ በጣም የሚያኮሩ ናቸው። ወደፊት ደግሞ ጠንክሬ እንደ ሰራ የሚያደርግ ግፊት አለው። ስራዬን ብቻ ሳይሆን በደንበኞቼ ተማምኜ ምን ም እንደማልሆን፣ ቤቱ ቢከፈት ቅንጣት ታህል ከድሮው ሁኔታ እንደማይበላሽ በመተማመን ል ክ በሁለተኛው ወር ተከፈተ። እርግጥ ነው አስደ ንጋጭ ነው። ቀላል አይደለም። አንድ ወር፣ ሁለ ት ወር፣ ሶስት ወር እያለ ቀስ በቀስ ቢዝነሱ እየተ ነሳ አሁን ባለበት ደርሷል።

አንዳንድ ደንበኞች ግን ቤቱ የሰው ህ ይወት ያለፈበት ከመሆኑ አንጻር አንቺ ም ሁልጊዜ ባየሽው ቁጥር የምታስታ ውሽው ስለሚሆን ለምንድነው ወደ ሌ ላ ቢዝነስ ያልቀየረችው የሚሉ አሉ? መሬቱን የገዛሽው እንደመሆኑ ወይ ህ ንጻ ብትገነባበት አሊያም ሌላ ቢዝነስ ብትቀየር ይሻል ነበር ይላሉ። ብዙ አስተያየት ትሰማለህ። ጓደኞቼ ሳይቀ ሩ “ስሙን ብትቀይሪው” ብለውኛል። ቢዝነ ስ እንግዲህ የራስህ አቋም ነው። ሰው የሚያ ዋጣውን ነው የሚይዘው። እኔ አለቃዬ ስራዬ ነው። ደንበኞዬ ደግሞ ህዝብ ነው። የእኔ ደንበ ኛ ይመጣል የሚል ሙሉ እምነት ካለኝ “ኢት ዮጵያን ቪሌጅ” ምን አደረገ? “ኢትዮጵያን ቪ ሌጅ” ማለት እኔ ነኝ ባለቤቷ። እንደገና ይታ ደሳል። ማንም ሰው አደጋ ያጋጥመዋል። መኪና ይጋ ጫል። ይጠገናል፤ ይሄዳል። ሰው አባቱ ይሞታ ል፤ አባቱ የሞተበትን ቤት ጥሎ አይሮጥም። እ ናቱ የሞተችበትን ቤት ጥሎ አይሄድም። አባቴ ስለሞተ በአባቴ ስም አልጠራም አይባልም። እ ና ለምንድነው ስሙ የሚቀየረው? ስሙ አይደ ለም ጥፋቱ። አደጋ በመጣ ቁጥር ሰው የአባቱ ን ስም እንደማይቀይር ሁሉ እኔም ደግሞ “ኢ ትዮጵያን ቪሌጅ” ልክ እንደዚያ ነው የሚሰማ ኝ። ብቅይረው ደግሞ ልክ እንደዚህ አይመጣ ም። ሃያ ዓመት ያሳደግሁት ልጅ ስሙ ሲቀየር ማለት ተቀበረ ማለት ነው። በአዲስ አንደገና ለ መጀመር ከባድ ነው። ቦታ መለወጥ ላይ ያለሽ አቋምም ተ መሳሳይ ነው? አዎ ቦታውም ለምን ይቀየራል? ስሙም እን ዳለ ሆኖ ቦታውም ላይ እንዳለ ሆኖ አካባቢው ን ሌላ አይነት ማድረግ ነው። የአደጋው አካባ ቢ ለምሳሌ ተቀይሯል። አደጋ የደረሰበት አይ መስልም። አሁን ፈረንጆች ሲመጡ “የቱ ጋር ነ ው አደጋ የደረሰው?” ይላሉ። ምግብ ቤቱ አገልግሎቱን እንደገና ሲጀምር ለሟቾች ያሰራሽውም መታሰቢያ ለዕይታ በ ቅቷል መታሰቢያ የተዘጋጀበት ምክንያት ደንብ ነ ው። በዓለም ላይ እንደዚህ አይነት ነገር ሲከሰ ት መታሰቢያ ይደረጋል። እኔ ለደንበኞቼ የም ሰጣቸው ስጦታ ባጣ በድርጅቱ ስም ግቢ ው ስጥ መታሰቢያ አድርጌያለሁ። ለደንበኞቼ ምን ልስጣቸው? አደጋ ሲደርስባቸው አልቅሻለሁ፣

ወደ ገጽ 21 ዞሯል


ሐበሻዊ ቃና

6

ልዩ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

የማይረሳው ዕለት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ዘገባ

ሞትን ማምለጥ

ይህ ጹሁፍ የዛሬ ዓመት አዲስ አበባ በሚታተመው “ፎርቹን” ሳምንታዊ የእንግሊዘኛ ጋዜጣ ላይ ታትሞ የወጣ ነበር። በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለማስታወስ መጠነኛ ማሻሻያ በማድረግ ወደ አማርኛ መልሰን አትመነዋል። “ሕይወት አጭር ናት” የሚለውን አባባል ከ ልብ አማኝ ብሆንም ከሁለት ደቂቃም ባነሰ ሊያጥር እንደሚችል ግን መቼውንም አስቤ አላውቅም። ኡጋንዳ ካምፓላ ካባላጋላ በሚገኘው የ“ኢት ዮጵያን ቪሌጅ” ምግብ ቤት በሰፊው በግድግ ዳ ላይ የተዘረጋው ነጩ አቡጀዲ ስክሪን ሁለ ት ደቂቃዎች መጨመራቸውን እያመላከተ ነ ው። ጭማሪው ደቂቃ የተሰጠው ለዓለም እግ ር ኳስ ዋንጫ የመዝጊያ ጨዋታ እየተፋለሙ ለሚገኙት ስፔን እና ኔዘርላንድስ ነበር። የጨ ዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ እየተገባደደ ነ ው። እደግፈው የነበረው የሆላንድ ቡድን ለእ ረፍት ከመውጣቱ በፊት አንድ ጎል ቢያስቆጥ ር የጨዋታውን አካሄድ ይቀይረዋል እያልኩ ማሰብ ይዤአለሁ። ከጥቂት ሰከንዶች በኋላ የ ሚሆነው ግን የህይወቴን አካሄድ እንደሚቀይ ረው ግን የማውቅበት መንገድ አልነበረኝም። “ቡም”!!! ይህንን ነበር በሰከንዶች ልዩነት ው ስጥ የሰማሁት። ጨዋታውን ያስተላልፍ የነበ ረው ስክሪን ወዲያውኑ ወደ ጥቁርነት ተለወ ጠ። አደንቋሪውን ድምጽ ተከትሎ በተቀመ ጥኩበት ደንዝዤ ቀረሁ። ጩኸት አየሩን ሞ ላው። መጀመሪያ የመሰለኝ ጆሮ አሳማሚ ድ ምጽ የወጣው የጋለው ፕሮጀክተር ሲቃጠ ል የፈጠረው መስሎኝ ነበር። “ዚንንንንንንን ንን….” የሚለው እና ጆሮዬ ላይ የቀረው ድም ጽ ግን የቦምብ ፍንዳታ እንደሆነ እንድደመድ ም አደረገኝ። ራሴን አረጋግቼ እርምጃ ከመውሰዴ በፊት ግን ሰዎች ወደእኔ ሲንጋጉ ተመለከትኩ። የተ ቀመጥኩት በመተላለፊያ አጠገብ ነበር። ፊት ለፊታቸው በነበሩ የፕላስቲክ ወንበሮች ላይ እየዘለሉ ነፍሳቸውን ለማዳን የሚሯሯጡ ሰዎ ችን ፈዝዤ እመለከታለሁ። ይሄኔ እኔም ከለላ መያዝ እንዳለብኝ ተረዳሁ እና ወደ ሽንት ቤ ት ወደ ሚወስደው መተላለፊያ ሮጥኩ። መተላለፊያው ጋር ቆሜ ዙሪያ ገባውን በቅ ጡ መመልከት ጀመርኩ። የቆሰሉ ሰዎች ይታ ዩኛል። የምግብ ቤቱን ውጭ ሞልተው የነበሩ ት ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች እዚህና እዚያ ወ ድቀው ይታያሉ። ፊት ለፊቴ የተዝረከረኩትን ወንበሮች ወደ ጎን እያደረግኩ አብረውኝ ወደ ምግቤቱ የመጡ ጓደኞቼን መፈለግ ጀመርኩ። ሶስቱ ጓደኞቼ ጨዋታውን ይከታተሉ የነበ ረው ከእኔ በስተቀኝ በኩል ባለው አነስተኛ ክ ፍል ውስጥ ነበር። ከጓደኞቼ መካከል ይበል ጥ የሰጋሁት ግን ከሳምንት በፊት ለስራ ጉዳይ ወደ ካምፓላ ለመጣችውን ጓደኛዬ ህሊና አለ ሙ ነበር። በሙያዋ ጋዜጠኛ የሆነችው ህሊና ን ወደ ምግብ ቤቱ ይዤያት የመጣሁት እኔ ነ በርኩ። እርሷንም ሆነ ጓደኞቼን በህይወት ማ ግኘቴ የፈጠረበኝን ስሜት በቃላት መግለጽ ይከብደኛል። ህሊናን ከሌሎች ጓደኞቼ ጋር ካ ገናኘሁ በኋላ እንደገና አደጋው ወደደረሰበት ቦታ ተመለስኩ። አሁን ለሌሎች ሰዎች እርዳታ የመስጪያ ጊ ዜ ነው። ጓደኞቼ ጨዋታውን ይከታተሉበት ወደነበረው ክፍል እየተመለስኩ እያለ በጣም ከመጎዳቱ የተነሳ መራመድ እንኳን ያቃተው አንድ ሐበሻ ተመለከትኩ። ሁለት ጓደኞቹ ከ ግራ እና ቀኝ ተሸክመውት በተዝረከረኩት ወ ንበሮች መሃል ለመራመድ ተቸግረዋል። ሌላ የሐበሻ ሴት እያለቀሰች እነርሱን ለመርዳት ት ሞክራለች። የሚያዩትን ማመን ያቃታቸው ጓ ደኞቹ ተጎጂውን ወዲያውኑ ለህክምና መውሰ ድ አቅቷቸዋል። “እሺ…አሁን አንድ ነገር ማድረግ አለብኝ” አ ልኩ ለራሴ። ሰዎቹን አላስኬድ ብሏቸው ያስ

ቸገራቸውን ወንበር እያነሳሁ መወርወር ጀመር ኩ። ጓደኞቹ ይዘውት ከግቢ ውጭ ሲወጡ ጓደ ኞቼ ተቀምጠውበት ክፍል ወደነበረው ክፍል ገ ባሁ። ሶስት ነጮች ወለሉ ላይ ተኝተው ተመ ለከትኩ። ሁሉም በደም ተሸፍነዋል። ሁለቱ ወ ንዶች ናቸው። ሰዎቹን እየተመለከትኩ አንድ ኡ ጋንዳዊ ሰውን ለማረጋጋት ይናገር የነበረውን አ ስታወስኩ። “ስክሪኑ ነው…ቦምብ አይደለም…ተ ረጋጉ…ተረጋጉ”። እነዚህን የውጭ ዜጎች ከተመ ለከትኩ በኋላ ግን የጠረጠርኩትን አረጋገጥኩ። “ወይኔ ቦምብ ነው…..” ከተጎዱት ነጮች ፊት ከአነጋገሩ ዘዬ አሜሪካ ዊ የሚመስል ሰው ተረጋግቶ ቆሞ ሊረዳቸው ይ ሞክራል። ተጎጂዎቹን ጮክ ብሎ ሊያነጋግር ይ ሞክራል። ሶስቱ ነጮች አይመልሱም። አሜሪካ ዊ መሳዩ አጠገቡ ያለውን ወንበር ጎትቶ በጣም የተጎዳውን አንዱን በጥንቃቄ አንስቶ ወንበር ላ ይ አስቀመጠው። እንዲሁ ሌላ ወንበር ጎትቶ የ ተጎጂውን እግሮች አስቀመጠባቸው። ይሄ ሁ ሉ ሲደረግ ግን ተጎጂው ምንም ዓይነት እንቅስ

ይህን በቅጡ ከማገናዘቤ በፊት መንገድ ዳር ጓ ደኞቹ አጠገብ በጀርባው የተዘረጋ ሐበሻ ተመለ ከትኩ። በካባዱ የቆሰለው ይህ ወጣት አተነፋፈ ሱ ልክ አይደለም። ደረቱም ባልተለመደ ሁኔታ ከፍ እና ዝቅ ይላል። በሁኔታው የተረበሹት የሚ መስሉት ሶስቱ ጓደኞቹ አጠገቡ ሆነው ሁኔታው ን ያስተውላሉ። ጓደኛቸውን ወደ ህክምና ለመ ውሰድ መኪና መጣታቸውን ከሁኔታቸው ተረ ዳሁ። በስተኋላ ላይ ጓደኞቹ መኪና አግኝተው ወደ ሙላጎ ሆስፒታል ቢወስዱትም ብዙም ሳይ ቆይ መሞቱን ሰማሁ። ፖሊስ ሲመጣ ከአካባቢው ጨርሶ መራቅ አል ሆነልንምና ከጓደኞቼ ጋር ሆነን ወደ “ፈንቅል” ምግብ ቤት ሄድን። በከተማዋ እንዳሉ ሌሎች ምግበ ቤቶች እና ቡና ቤቶች ሁሉ እዚህም በርካ ቶች ስክሪን ላይ አፍጥጠው የመጨረሻው ጨዋ ታ ሁለተኛውን አጋማሽ በጉጉት እየተከታተሉ ነ ው። በጥቂት ሜትሮች ርቀት ላይ ካለ ቦታ አደን ቋሪ ጩኸት ቢሰሙም ምንም አንዳልተከሰተ ሁ ሉ ጨዋታቸውን መመልከት ቀጥለዋል። ስክሪኑ

አደጋው በደረሰ ማግስት የወጡ ጋዜጦች የፊት ለፊት ገጽ ይህንን ይመስል ነበር

ቃሴ አያሳይም ነበር። የተቃጠሉት እግሮቹ በደ ም ተሸፍነዋል። አሜሪካዊ መሳዩ ሌላኛዋን ተጎጂ መርዳት ጀመ ረ። ወንበር ላይ ሲያስቀምጣት አገዝኩት። እር ሱ ሲያደርግ እንዳየሁት ወንበር ጎትቼ እግሮቿን ወንበር ላይ ለማስቀመጥ አናግራት ጀመር። ምን ም አትመልስም። ደጋግሜ ሞከርኩ። አይኖቿ እ ንደቦዘዙ ናቸው። ምንም የምትሰማ አትመስል ም። እግሮቿን ወንበር ላይ አስቀምጬ ወደ ሌላ ው ተጎጂ ሄድኩ። እንደሌሎቹ ተጎጂዎች ይሄኛውም ያደረገው ቁ ምጣ ነው። ስጠጋው ጉልበት ላዩ ትልቅ ቁስል እ ንዳለ ተመለከትኩ። እግሮቹ በደም በደም ሆነዋ ል። “እርዱኝ” አለ። እርሱን እየረዳሁ እያለሁ ፕ ሮጀክተሩ አጠገብ መሬት ላይ እየተንፈራፈረች በስቃይ የትጮኽ ተጎጂ ተመለከትኩ። “የጀመር ከውን ጨርስ” አልኩ ለራሴ። ከአንድ አስተናጋጅ ጋር ተባብረን የተጎዳውን ሰ ው ወንበር ላይ አስቀመጥነው። ተጎጂው ቦርሳ ውን እንድናመጣለት ጠየቀ። ጓደኛዬ አመጣለ ት። ክፍት የነበረውን ቦርሳ ለመዝጋት መታገል ጀመርኩ። ቦርሳውን ብዘጋውም ትርጉም አልነበ ረውም። በፍንዳታው ምክንያት በአንድ ወገኑ ተ ቦትርፏል። ቁስለኞቹን ወደ ህክምና ቦታ ለመው ሰድ መኪና መጠየቅ ጀመርን። ይሄኔ የምግብ ቤ ቱ ባለቤት የሆነችው ማሜ መንገሻ እርዳታችንን ፍለጋ መማጸን የጀመረችው። “እባካችሁ ትታችሁኝ አትሂዱ….እባካችሁ እር ዱኝ” ትላለች እያለቀሰች። ለመርዳት መኪና እን ደሚያስፈልግ ነገርናት።

“እባካችሁ የእኔን መኪና ውሰዱ እና ወደ ሆስ ፒታል ውሰዱልኝ” አለች በእንባ የምትታጠበው ማሜ። በምግብ ቤቱ አቅራቢያ ወዳለው ሆስፒ ታል ቁስለኞችን ለመውሰድ ስንዘጋጅ ሀሳባችን ን የሚያስለውጥ ማስጠንቀቂያ ሰማን። “ወረቀት የሌላችሁ ሐበሾች አሁኑኑ ውጡ” የሚለው በአ ማርኛ የተነገረው ማስጠንቀቂያ የመጣው ከወደ በር አካባቢ ነበር። ይሄኔ ትዝ ሲለኝ መታወቂያም ሆነ ፓስፖርት አልያዝኩም። በሰባት ወር ገደማ የኡጋንዳ ቆይ ታዬ መታወቂያ የተጠየቅኩት ሁለት ጊዜ ብቻ ነ ው የተጠየቅኩት እያልኩ የማዳንቅ ነበርኩ። ም ናልባትም ያ ይሆናል ያለምንም መታወቂያ ከቤ ት እንደወጣ ያደረገኝ። ወዲያውኑ አንድ ጓደኛ ዬ ደወሎ ከአካባቢው በአስቸኳይ እንድርቅ አስ ጠነቀቀኝ። ፖሊስ በአካባቢው ከደረሰ በኋላ ነገ ሮች ጥሩ እንደማይሆኑ ጨምሮ ነገረኝ። ምክሩን ተቀብዬ የምግብ ቤቱን ግቢ ከጓደኞቼ ጋር ወዲ ያውኑ ለቅቄ ወጣሁ። ከወጣን በኋላ ግን ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለ ብን ግራ ተጋባን። ምግብ ቤቱ አጠገብ ቆምን እ ያለ እጄ ላይ የሚያሙለጨልጭ ነገር ተሰማኝ። የሚሙለጨለጨውን ነገር በሌባ እና በአውራ ጣቴ አጣብቄ ይዤ ምንነቱን ለማወቅ ወደ ብር ሃን ተጠጋሁ። “ኦህህህህህህህህ…”። ለካንስ የሚ ሙለጨልጨው ነገር የሰው ስጋ እና ደም ቅይጥ ነው። ክንዶቼን ፈተሽኩ። በተበጣጠሰ የሰው ስ ጋ ተሸፍኗል። የለበስኩትን ቲ-ሸርት ስነካ ሻከረ ኝ። ቲ-ሸርቴም በተበጣጠሱ ስጋዎች ተሸፍኖ ነበ ር። “ኦ….እግዚያብሔር….”

ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

ን ወደማይታይበት በረንዳ ወጥተን ከተቀመጥን በኋላ ስለሆነው ነገር መረጃ ለማግኘት ሞከረን። ብዙም ሳይቆይ በቻይዶንዶ የራግቢ መጫወቻ ሜዳ ተስብሰበው ጨዋታውን በመመልከት ላይ ባሉ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች መሃል ሌላ ቦምብ መፈንዳቱን ሰማን። ያኔ ነው ነገርየው የአሸባሪ ዎች ጥቃት መሆኑን የተረዳሁት። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ከ“ኢትዮጵያን ቪሌ ጅ” እንድንወጣ ደውሎ ያስጠነቀቀኝ ጓደኛዬ በ ድጋሚ ደውሎ ከተማ ውስጥ የሚወራውን አረ ዳኝ። ከቻይዶንዶ ሌላ ንቲንዳ በተሰኘው ቦታ ሌላ ቦምብ ፈንድቷል መባሉን ነገረኝ። “ኦ….እግ ዚያብሔር….”። ከዚህ በላይስ አልችልም። እንባ ጉንጮቼን አቋርጦ መውረድ ጀመረ። ከጓደኛዬ ጋር ስለአደጋው ይበልጥ መረጃ በተቀበልኩ ቁ ጥር ተጨማሪ እንባ በፊቴ ላይ መፍሰሱን አላቋ ርጥ አለ። ሀዘኔን ያበዛው ደግሞ በአደጋው ወቅ ት አብረውኝ የነበሩትን ጓደኞቼን ወደ ቦታው እ ንዲመጡ እና አብረን ኳስ እንድንመለከት ሀሳብ ያቀረብኩት እኔ በመሆኔ ነበር። ወደ ምግብ ቤቱ የደረሰነው በጣም አርፈደን ነ በር። ቤቱ ግጥም ብሎ ከመሙላቱ የተነሳ ብቸ ኛ ክፍት ቦታ የነበረው ከስክሪኑ ስር ነበር። ስክሪ ኑ አጠገብ የነበሩ ሰዎች ክፉኛ መጎዳታቸውን ሳ ስታውስ ህይወታችንን ያተረፈውን አንድ አስተ ናጋጅ እንደነበር ትዝ አለ። አስተናጋጁን ስክሪኑ ፊት ወንበር እንዲያስቀመጥልን ስንጠይቀው በነ በረው ክፍት ቦታ ወደ ስክሪኑ በጣም ስለምንቀ ርብ ጨዋታውን በትክክል መመልከት እንደማ ንችል አስረድቶን ሌላ አማራጭ አቀረበልን። ከ

ስክሪኑ ጎን ያለችውን አነስተኛ ክፍል እያሳየን እ ዚያ ውስጥ እንድንገባ እና ወንበር ከቢሮም ቢሆ ን ፈልጎ እንደሚያመጣ ቃል ገባልን። እንዳለው አደረግን። እርሱም ቃሉን ጠብቆ ወንበሮች ይ ዞልን መጣ። ጨዋታው ከተጀመረ በኋላ ወንበ ር ለውጬ መተላለፊያ አጠገብ ተመልካቹ መሃ ል ተቀመጥኩ። ከፊቴ የተቀመጠች ሴት የያዘችውን ቢጫ “ቩ ቩዜላ” በድጋድ ስሜት በተደጋጋሚ ስትነፋ እን ደነበር አስታውሳለሁ። ግቢውን ግጥም አድርገ ው እንደሞሉት አብዛኞቹ ተመልካቾች እርሷም የኔዘርላንድስ ደጋፊ ነበረች። ተመልካቹ ለመላወ ሻ የተተውን ቦታ ሁሉ በመያዙ ቦታው ሁሉ ተ ጨናንቆ ነበር። በ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” እንደዚህ ህዝብ ጢም ብሎ ሞልቶ የሚታየው በበዓላት ቀ ን ብቻ ነው። ያኔም ልክ እንደአሁኑ የአብዛኛው ዓይን ከስክሪኑ አይነቀልም። ስክሪኑም የኢትዮጵ ያ እና ኤርትራ የሙዚቃ ክሊፖችን እያከታተለ ያስኮመኮማል። ምግብ ቤቱ የአገር ቤት ማስታወሻ ነው። በግ ቢው ውስጥ የሚገኙት በሳር የተሸፈኑት ጎጆዎ ች የአገራችንን ገጠር ያስታውሰናል። በ“ኢትዮ ጵያን ቪሌጅ” በኩራት የሚውለበለበው የኢት ዮጵያ ባንዲራም ከቤቱ ጋር ያለንን ቁርኝት ይበ ልጥ የሚያጠብቅ ነው። አሁን ሁሉም ነገር እንዳ ልነበር ሆኗል። ከ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” አቅራቢያ እስከ እኩለ ለሊት ቆየን። ግን እስከዚያን ሰዓት ድረስም ቢ ሆን አደጋውን እንዴት ሊደርስ እንደቻለ በቅጡ መረዳት አልቻልንም። የመረጃ ረሃብ ላይ ነበር ን። ወደ ቤት ተመልሰን ቴሌቪዥን ላይ አፈጠ ጥን። ያሉትን ጣቢያዎች በሙሉ እያቀያየርን ተ መለከትን። ሁሉም ጣቢያዎች ስፔን የዓለም ዋ ንጫ አሸናፊ መሆኗን ነው የሚያበስሩት። ዘግየ ት ብሎ “አል ጀዚራ” ዜናውን ይዞ መጣ። ጣቢ ያው “ሰበር ዜና” ከሚለው በትልልቁ ከተጻፈው ጽሁፍ ስር 26 ሰዎች ካምፓላ ላይ የዓለም ዋን ጫ ፍጻሜን በመመልከት ላይ እያሉ መሞታቸ ውን አወጀ። የኡጋንዳው ኤንቲቪ ተከተለ። የኤንቲቪው ዘ ገባ እንደ አልጀዚራ አጭር እና ምስል አልባ አል ነበረም። አደጋው በደረሰባቸው በሁለቱም ቦታ ዎች ያለውን ሁኔታ የሚያሳይ ምስል በተደጋጋ ሚ ማስተላለፍ ያዘ። ከፊት ለፊቴ የነበረችው ሴ ት ይዛው የነበረውን ቢጫ “ቩቩዜላ” አሁን በ ፖሊስ እጅ ላይ ተመለከትኩት። ጣቢያው የፖ ሊስ ኢንስፔክተር ጄነራል የሆኑት ካሌ ካይሁራ “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ፊት ለፊት ከሚዲያዎች ጋ ር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ማሳየት ጀመረ። ኤን ስፒክተር ጀነራሉ በ“ኢትዮጵያን ቪሌጅ” በደረ ሰው የቦምብ ፍንዳታ 11 ሰዎች መሞታቸውን ተ ናገሩ። አደጋውን ያደረሰውም የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን የሆነው አልሻባብ እንደሆነ ለብዙሃን መገ ናኛዎች ገለጹ። ምንም ዓይነት አርትኦት ሳያደርግ ምስሎችን እ ንደመጡለት ያስተላለፍ የነበረው ኤንቲቪ ከደቂ ቃዎች በኋላ በቻይዶንዶ ራግቢ ሜዳ የሆነውን ድርጊት እንደወረደ ማሳየት ጀመረ። ምስሎቹ ዘ ግናኝ የሚለው ቋንቋ ብቻ አይገልጻቸውም። ተ ቆርጦ የወደቀ አንገት የቴሌቭዥኑን ስክሪኑን ሞ ላው። በተቀመጡበት በዚያው የሞትን ጽዋ የቀ መሱ ሰዎችንም ተመለከትን። እንባዬ በድጋሚ መውረድ ጀመረ። እስከ ለሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጣ ቢያዎችን እየቀያየርን ስንመለከት ቆየን እና ጎና ችንን ለማሳረፍ ወደ አልጋዎች አመራን። እንቅል ፍ ግን ከየት ይምጣ። ከዚያን የመሰለ አደጋ በኋ ላ እንቅልፍ….? ማልጄ ነበር የተነሳሁት። መታጠቢያ ቤት ደር ሼ ፊቴን ስመለከት የዓይን መነጽሬ በነጠብጣቦ


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ልዩ

የማይረሳው ዕለት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ዘገ

ማን ይናገር የነበረ…

አቶ ካሳ መንግስተዓብ ጁላይ 11 ምሽት በኢትዮጵያ ገጠር ምግብ ቤት (ኢትዮጵያን ቪሌጅ) የዓለም ዋንጫን የፍጻሜ ውድድር በሚመለከቱ ወገኖች ላይ ከደረሰው የቦምብ አደጋ በህይወት ተርፈው ክስተቱን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ መመልከት ከቻሉት መካከል አንዱ ናቸው፡፡ ማን ይናገር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ ነውና አቶ ካሳ ‹‹አንድ ዓመት ሊሞላው ቀርቶ ወር ሁለት ወር እንኳን የሆነው አይመስልም›› የሚሉትንና አስከሬን እንደ ቅርጫ ስጋ ከየቦታው የሰበሰቡበትን አሳዛኝ ክስተት እንደሚከተለው ይተርኩታል፡፡

ቀን አያውቁ ቀኑ እሁድ ነው፡፡ እናም ዘወትር በዚሁ እለት እንደምናደርገው ወደ ሜዳ ወርደናል፡፡ በእግር ኳስ ሰበብ ፍቅርና ጨዋታን ልንገዛ መተጋጋዝና መተሳሰብን ልናጠናክር፡፡ በሁለት ወገን ተከፍለ ን ኳስን ከወዲያ ወዲህ፣ ሰውነታችንንም ከላይ ታች ስናንቀሳቀስ አርፍደን አሁን ወደማብቂያው ደርሰናል፡፡ የዛሬው ቀን በተለይ እግር ኳስ እንደ ነፍሳችን ለምንወደው ለእኛ ቡድን (ግሩፕ) የተ ለየ ነው፡፡ ምክንያቱም የውድድሮች ሁሉ ንጉስ የ ሆነው የዓለም ዋንጫ ፍጻሜ የሚያገኝበት እለት በመሆኑ፡፡ ሁላችንም የዓለም ዋንጫን ፍጻሜ ለ ማየት ጓጉተናል፡፡ ስፔንና ሆላንድ በእግራቸው ቅ ልጥፍናና ጥበብ ስሜታችንን እንዲያረኩት የፈለ ግንበትም ጊዜ እየተቃረበ ነው፡፡ በተለይ ለእኔ የዘንድሮው የዓለም ዋንጫ እንደ ወትሮዎቹ አይደለም፡፡ አለም አቀፍ የእግር ኳ ስ ውድድሮችን ማየት ከጀመርኩበት ጊዜ አንስ ቶ እንደ የደቡብ አፍሪካው የአለም ዋንጫ በደ ንብ የተከታተልኩት የለም፡፡ ከመክፈቻው እስ ከ ፍጻሜው አንድም ሳይቀረኝ ስራዬንም ቤተሰ ቤንም እየተውኩ ሁሉንም ጨዋታዎች ተመልክ ቼያለሁ፡፡ ከማለዳ ጀምሮ ካረፍድንበት የእግር ኳስ ሜዳ ወጥተን ዘወትር እንደምናደርገው ለምሳ “ሳሚ ምግብ ቤት”ተሰባሰብን፡፡ ትዝ ይለኛል አብነት የሚባለው ወዳጃችን ለመጀመሪያ ቀን ዶሮ ወጥ መሸጥ የጀመረበት ቀን ስለነበር እሱኑ ለማስተዋ ወቅ በሚል እኛም ምሳችንን ዶሮ ወጥ ነበር ተሰ ባስበን የበላነው፡፡ ማዕዱ ቀርቦ ከፍ እስኪልም ሳ ቅና ጨዋታ ከመካከላችን አልጠፋም ነበር፡፡ በእ ለቱ ከናይሮቢ በእንግድነት የመጣውና ኳስ አፍ ቃሪው ኤፍሬምም ከሜዳ ጀምሮ አብሮን ነበር፡ ፡ በዚህ መልኩ ምሳ ከበላን በኋላ የጓጓንለትን የ ዓለም ዋንጫ የፍጻሜ ውድድር ለማየት ተቀጣጥ ረን ተለያየን፡፡ ምሽት ሆነ፡፡ ዛሬም ድረስ በጥቁረቱ የማልረሳ ው ለዘላለም የሚኖር የሚመስል ጨለማ፡፡ ስፔ ንና ሆላንድን በቴሌቪዥን መስኮት እያየን ለመ ደገፍ በቡድን ተከፋፍለናል፡፡ ዘላለምና ዘድንግ ል ከሚባሉት ጓደኞቼ ጋር ጨዋታውን ለማየት በሚል መጀመሪያ ያመራነው “መቹቼ” የሚባል የ ስዊዝ ሬስቶራንት ነበር፡፡ እዚያ ሄድን ከተቀመጥ ን የምንጠጣውንም ካዘዝን በኋላ ግን ‹‹የለም ኢ ትዮጵያን ቪሌጅ ሄደን እንይ›› የሚል ሀሳብ ተሰነ ዘረ፡፡ ሀሳቡ ተነስቶ ብዙም ሳይቆይ ሳይረፍድብ ን እንሂድ ተባባልንና ወዲው ወደ ኢትዮጵያን ቪ ሌጅ ምግብ ቤት አመራን፡፡ እኔ የሆላንድ ቡድን ደጋፊ ነበርኩ፡፡ የ45 ደቂቃው ዓለም በእርግጥ ከዚህም በፊት ብዙውን ጊዜ ጨዋታ ዎችን የምንመለከተው በቡድን እየተሰባሰብን ነ በር፡፡ በዚህ የፍጻሜ ጨዋታ ቀን ግን አይቻቸ ው ከማላውቃቸው ልጆች ጋር ጭምር ኳስ አብ ረን ለማየት የተገባበዝንበት በመሆኑ የተለየ ያደ ርገዋል፡፡ ከእኛ ጋር የነበረው ዘላለም መቼም የኳስ ፍቅ ሩ የተለየ ነው፡፡ እኛ ቁጭ ብለን ስናይ እሱ ግን ዘጠናውንም ደቂቃ ከእንቅስቃሴና ከንግግር ጋር ነው የሚያሳልፈው፡፡ በዚህም ከሰዎች ጋር ሊጋ ጭ ይችላል እያልን እንሳቀቅ ነበር፡፡ ያን ቀንም በ ዚሁ ምክንያት ከሰዎች ጋር እንዳይጋጭ በሚል “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ከገባን በኋላ ከፊት ይልቅ

ፎቶ-ቪኦኤ

ች ተሞልቶ ተመለከትኩ። መነጽሬን አውልቄ አ ስጠግቼ አየሁት። በመነጽሩ መስታወት ላይ ያ ሉ ነቁጦች የተበጣጠሰ የሰው ስጋ መሆኑን ስረ ዳ ክፉኛ አዘንኩ። ቀናት ቢያልፉም ይህ ነገር እ ንደማይለቀኝ ተሰማኝ። ከሰዓታት በኋላ የኡጋን ዳ ፖሊስ ስለአደጋው ለማብራራት በጠራው ጋ ዜጣዊ መግለጫ ላይ ተገኝቼም ይሄው ስሜት አ ብሮኝ ነበር። አንደተከፋሁ ነበር። ውስጤም መ ረበሹን አላቆመም። በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የሚነገሩት ነገሮች ደግሞ ይህንን ስሜት የሚያባ ብሱ እንጂ የሚያረጋጉ አልነበሩም። በመግለጫ ው ከተባሉት ነገሮች አንዱ ደግሞ እስካሁን ያላ ሰብኩትን አሳወቀኝና ውስጤን ይበልጥ አተራ መሰው። ጥቃቱ የተፈጸመው በአጥፍቶ ጠፊዎች እንደሆነ ፍንጮችን ማግኘቱን ፖሊስ ማሳወቁ ነ በር የረበሸኝ። “እኔም የተረፍኩት ከአጥፍቶ ጠ ፊዎች ነው ማለት ነው?”። ጥያቄዬ በጆሮዬ ደጋ ግሞ አስተጋባ። እያንዳንዱ ደቂቃ ባለፈ ቁጥር አደጋውን አስመ ልክቶ የሚደርሰኝ መረጃ ባገናዘብኩ ቁጥር ነገርየ ውን በፊልም የተመለከትኩት እንጂ በራሴ የደረ ሰ አልመስልህ አለኝ። ከአደጋው በኋላ ያሉት ቀ ናት ድንገት በሚገነፍሉ ስሜቶች የተሞሉ ነበሩ። በአደጋው ቦታ እንደምኖር የጠረጠሩ ጓደኞቼ ደ ህነቴ አስግቷቸው መልዕክቶችን ያጎርፋሉ። እነር ሱን ለማረጋጋት በ“ፌስ ቡክ” ላይ “አለሁ…አልሞ ትኩም….ተርፌአለሁ” ማለት ነበረብኝ። ከዚህች አጭር መልዕክቴ ስር ያለው ቦታ በጓደኞቼ አጽ ናኝ መልዕክቶች ተጨናነቀ። እያንዳንዱን መልዕ ክት ባነበብኩ ቁጥር ጥንካሬ እንደሚሰጠኝ ሁሉ እንባዬንም ያመጣው ነበር። “እንዴ! ምን ሆኜ ነው ማልቀስ ማቆም ያቃተ ኝ?” ስል ራሴን በተደጋጋሚ ጠይቄአለሁ። መል ስ ግን ማግኘት አልቻልኩም። በጋዜጠኝነት ሙ ያዬ ውስጥ የቦምብ ፍንዳታን ጨምሮ ብዙ አደ ጋዎችን ተመልክቼአለሁ። የሞቱ፣ የቆሰሉ ሰዎች ንም አይቼአለሁ። እንዲህ አይነት ልምድ ስለነበ ረኝም ምንም ነገር ቢመጣ ስሜቶቼን መቆጣጠ ር እችላለሁ ብዬ አስብ ነበር። ግን አልሆነም። ጥቂት ቆይቼ ራሴን የማገኘው ሳለቅስ ነው። ኢ ትዮጵያዊት በቲቪ ቀርባ የጠፋ ወንድሟን እን ዲያፈላልጓት እያለቀሰች ስትጠይቅ ስመለከት እ ኔም እርሷን እከተላለሁ። ለሟቾች በተዘጋጀ የ ሽኝት ስነስርዓት ላይ ስታደም እንባዬ ይቀድማ ል። የሟቾችን ፎቶ ተመለከትኩ ቁጥር በጣም አዝናለሁ። ከአደጋው በኋላ የነበረው ጊዜ በስሜት መለዋ ወጦች ብቻ የቆመ አልበረም። የስደተኞችን ሰላ ማዊ ህይወት እስከማናጋት ድረስ ሄዷል። ኢት ዮጵያውያን እና ኤርትራውያን አደጋውን አድር ሰዋል ተብለው የተጠረጠሩተን ሶማሌዎችን ይ መስላሉ በሚል ጥቃት እና መገለል ደርሶባቸዋ ል። እንደጋዜጦች ዘገባ ከሆነ የተወሰኑ ኢትዮጵ ያውያን እና ኤርትራውያን በአደጋው ተጠርጥ ረው ታስረዋል። በፖሊስ ጣቢያ ለቀናት ታስረ ው፣ ኃይል የተቀላቀለበት ምርመራ ተደርጎባቸ ው የተለቀቁም ነበሩ። ህዝብ በሚበዛባቸው ቦ ታዎች ቦምቦች ተገኙ እየተባለ ከተማይቱ ስት ታመስ ሰንብታለች። ምን ማድረግ እንዳለባቸ ው ግራ የገባቸው በርካታ ሐበሾች በር ዘግተው ቆይተዋል። ከዚህ ሁሉ በኋላ ግን በእርግጠኝነት አንድ ነገ ር ማለት ይቻላል። ጁላይ 11 ብዙ ነገሮች ለዋው ጧል። ብዙዎች 13 ቁጥርን ከመጥፎ እድል ጋር ያይዛሉ። ለኡጋንዳውያን፣ ለአሜሪካኖች እና ለ እኔ ግን 11 ቁጥር ሌላ ትርጉም አለው። እ.ኤ.አ በ ሴፕቴምበር 11 2009 በካምፓላ በተቀሰቀሰ ብጥ ብጥ በአስራዎቹ የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን ሞተ ዋል። በዚያኑ ቀን ከስምንት ዓመት፤ ኢትዮጵያ ኖች አዲስ አመታቸውን በሚያከብሩበት ዕለት፤ በኒው ዮርክ የአለም የንግድ ማዕከል መንትያ ህ ንጻዎች ላይ ደግሞ የሆነውን ሁላችንም እናስታ ውሳለን። አሁን ደግሞ ጁላይ 11 በኡጋንዳ ታሪክ “አሰቃቂ የአሸባሪዎች ጥቃት የደረሰበት” በሚል ተመዝግቧል። ለእኔ ግን ጁላይ 11 የማንቂያ ደውል ነበር…. ንቃ…..ህይወት አጭር ናት….ከሁለት ደቂቃም ያጠረች…… q በተስፋለም ወልደየስ

7

ኢትዮጵያን ቪሌጅ ምግብ ቤት ከአደጋው በኋላ

d

c

በህይወቴ ካየኋቸው አደጋዎች ሁሉ እጅግ አሰቃቂውና አሳዛኙ ነበር፡፡ በተለይ ከሐበሾች መካከል ሁለት ልጆች አሟሟታቸው አሁንም ድረስ አይረሳኝም፡፡ ምክንያቱም የፈነዳው ቦምብ ከአንደኛው ጫፍ ወርውሮ ወደሌላኛው ስለወሰዳቸው እጅግ ተጎድተው ነበር፡፡

a

b

ወደኋላ መቀመጡን መረጥን፡፡ ኢትዮጵያን ቪሌ ጅ የደረስነው ብዙ ሰው ከመግባቱ በፊት ነበር፡ ፡ ከእኛ በፊት የገቡ ዘጠኝ ያህል ነጮች ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል፡፡ እኛም ለሶስታችን የሚሆ ን መቀመጫ አዘጋጅተን ተቀመጥን፡፡ በዚህ ሁ ሉ ጊዜ ዘላለም ከፊት ካልተቀመጥን እያለ ይጎተ ጉተን ነበር፡፡ እኔ ግን “ለንፋሱም ይሄው ይሻላል” በሚል ለማግባባት ሞክሬ እዚያው ተቀመጥን፡፡ ኳሱ ሊጀመር ሲል ሰውም ቀስ በቀስ እየበዛ መ ጣ፡፡ ትዝ ይለኛል ዘላለም ከእኔ በተቃራኒው የስ ፔን ደጋፊ ነበር፡፡ ጨዋታው እየሞቀ የተመልካ ቹም ስሜት ከወዲያ ወዲህ መንጸባረቅ ቀጠለ፡፡ በእለቱ እኔ የምደግፈው የሆላንድ ቡድን ጉልበት የተሞላበት አጨዋወት ይከተል ስለነበር ብዙም አልተደሰትኩበትም፡፡ መሸነፉ እንደማይቀር ስለ ገመትኩ ስሜቴም መቀያር ጀምሮ ነበር፡፡ እንዲ ህ እየሆነ “ቪሌጅ” ከመጠን በላይ እየሞላ፣ ቦታ እየጠፋ መጣ፡፡ ጠረጴዛ ከመጥፋቱ የተነሳ የሚገቡት ሰዎች ወን በር እየተሰጣቸው ወደፊት እየሄዱ ይቀመጣሉ፡ ፡ በዚያ መልኩ ቦታ ጠፍቶ እኛ የተቀመጥንበት አጠገብ ግን አንድ ባዶ ወይም ትርፍ መቀመጫ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ አብሮን ኳስ ይጫወት የነበረ ው ካሌብ ከሌሎች ሁለት ጓደኞቹ ጋር ሲገባ አየ ሁት፡፡ ልጠራው አሰብኩና ያለው አንድ ቦታ ብ ቻ ስለነበር ‹‹እሱን ጠርቼ ሌሎችን ልተዋቸው አ ይደል›› በሚል እሱንም ዝም አልኩትና ከፊት ሄ ዶ ተቀመጠ፡፡ ኳስ ማየቱ በዚህ መልኩ ቀጥሎ ልክ የመጀመሪ ያው 45 ደቂቃ አልቆ የዕረፍት ፊሽካ ሊነፋ ሲል ሽንቴን ለመሽናት ብድግ ስል ሀይለኛ ፍንዳታ ግ ቢውን አናወጠው፡፡ በመጀመሪያ ፈንጂ ነው የ ሚል ምንም ግምት አልነበረኝም፡፡ እንዲያውም እኔ በግሌ ኳስ የሚታይበት ፕሮጄክተር የተቃጠ ለ ነበር የመሰለኝ፡፡ ምክንያቱም ከፕሮጄክተሩ ፊ ት ለፊት የተሰቀለው ስክሪን መሀሉ ተቀዷል፡፡ ቴ ሌቪዥኖቹ ይሰራሉ፡፡ መብራት አለ፡፡ ስለዚህ ቴ

ሌቪዥኖች ከሰሩ ፕሮጄክተሩ ፈንድቶ ነው አ ልኩ፡፡ ግምቴን ለሌሎች እያካፈልኩ ማረጋጋ ት ስሞክር ወዲያው ከፈነዳበት አካባቢ ደም በደም የሆኑ ሰዎች እየመጡ ከፊታችን መው ደቅ ጀመሩ፡፡ አስከሬን እንደ ቅርጫ ስጋ ነገር ይሸታል አመድ ነገር ደግሞ ላያችን ላ ይ ተበታትኗል፡፡ የዚያን ጊዜ በእጅጉ ደነገጥኩ፡ ፡ ወይ ወደውጪ አልሸሸሁ ወይ ወደ ፊት አል ተጠጋሁ የቆምኩበት ደርቄ ቀረሁ፡፡ አስታውሳ ለሁ ሶስት አራት ደቂቃ ያህል ከቆምኩበት አል ተንቀሳቀስኩም፡፡ ከዚያ በኋላ ተነስተን ወደ ሰ ዎቹ መሀል ገባን፡፡ ትንሽ እንደቆየ የደህንነት ኃ ይሎች ወዲያው መጡና ሰዎችን ማስወጣት የ ተጎዱትንም በመኪና እየጫኑ መውስድ ሲጀም ሩ እኔ፤ ማሜ (የኢትዮጵያን ቪሌጅ ባለቤት)ና ማኔጀሩ ብቻ ቀረን፡፡ መጀመሪያ የደረሱት ፖሊሶች ነበሩ፡፡ እነሱ የ እጅ ጓንት ለእኛ ሰጡንና ለጥበቃ በዙሪያው ተ ሰማሩ፡፡ በዚህ ጊዜ እኛ አስከሬን ማንሳት ጀመ ርን፡፡ በአደጋው የተሰባበሩ አሉ፡፡ እግራቸው የተቆረጠ አሉ፡፡ ሁሉም በድንጋጤ የሚያወራ ውን አያውቅም፡፡ ግማሾቹ ነጮች ‹‹ትታችሁን አትሂዱ ሀገራችን ስላልሆነ ነው ወይ›› ይላሉ፡፡ ህይወታቸው ያለፈ አሉ፡፡ የትኛውን ቅድሚያ ሰጥተን እንደምንረዳ ግራ ተጋባን፡፡ ስለራስ ደህንነት መጠንቀቅ የማይታሰብ ነበ ር፡፡ ከፊታችን ያገኘነውን አንዱን ስናነሳ ሌላ ውን ወደመኪና ስናደርስ በሌላ በኩል ህይወቱ ያለፈውን ማንነት ለመለየት በምናደርገው ጥረ ት መዋከብ ሆነ፡፡ አንዳንዶቹ ያንቀላፉ እንጂ የ ሞቱ አይመስልም ነበር፡፡ ለምሳሌ ጌታ ያውቃ ል የሚባለው ወዳጃችን እንደሞተ ማንም አላ ወቀም ነበር፡፡ እኔም ሰው ህይወቱ ሲያልፍ አ ይኑ አካባቢ የሚስተዋለውን ለውጥ አይቼ ነው ህይወቱ ማለፉን ያወቅሁት፡፡ በጥቅሉ በህይወቴ ካየኋቸው አደጋዎች ሁሉ እጅግ አሰቃቂውና አሳዛኙ ነበር፡፡ በተለይ ከሐ በሾች መካከል ሁለት ልጆች አሟሟታቸው አ ሁንም ድረስ አይረሳኝም፡፡ ምክንያቱም የፈነዳ ው ቦምብ ከአንደኛው ጫፍ ወርውሮ ወደሌላ ኛው ስለወሰዳቸው እጅግ ተጎድተው ነበር፡፡ የ ሟቾቹን አስከሬን በምናነሳበት ወቅት የሰውነት አካላቸውን ለየብቻ ነበር ያገኘነው፡፡ እንዲህ እ ያደረግን ነበር የሰበሰብነው፡፡ አንዱን የሰውነት አካል እንዲያውም አሞራ ይዞት ወጥቶ የቤቱ ጣራ ላይ ተገኝቷል፡፡ ይሄም በዚያን ሰሞን በታ ተሙ ጋዜጦች በአንደኛው ላይ በፎቶ መውጣ ቱን አስታውሳለሁ፡፡ እንዲህ እያደረግን የተጎዱትን እየረዳን ህይወ ታቸው ያለፈውን አስከሬን እየሰበሰብን እያለ የፖሊስ አዛዡ መጥቶ በአካባቢው የነበሩትን ማረጋጋት ሲጀምር ሌሎችም እኛን ማገዝ ጀመ ሩ፡፡ እስከዚያ ድረስ ግን እኔና የምግብ ቤቱ ማ ኔጀር ብቻ ነበር እያነሳን ወደመኪና የምንወስደ ው፡፡ በወቅቱ አምቡላንስ እንኳን ባለመምጣቱ ፖሊሶች በራሳቸው መኪና ወዲያው ወዲያው እየተቀበሉ ወደ ሆስፒታል እየያዙ ይሄዳሉ፡፡ የጉድ ሌሊት አይነጋም ተረቱ የጉድ ቀን አይመሽም ነበር፡፡ ለእኛ ግን አሰቃቂው ሌሊት የሚነጋ ሁሉ እስከማይመስ ል ረዝሞብን ነበር፡፡ ይሁንና እንዳያልፍ የለም

ወደ ገጽ 21 ዞሯል


ሐበሻዊ ቃና

8

ልዩ

ዘገባ

የማይረሳው ዕለት አንደኛ ዓመት መታሰቢያ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

9

የስደት ዓለም

መስፍን ገብረስላሴ ይባላል። አርባ አንደኛ ዓመቱን ያከበረው በቅርቡ ነው። ከአንድ ዓመት ከ10 ወር በፊት ወደ አውስትራልያ ከመሄዱ በፊት ካምፓላ ኡጋንዳ ውስጥ ለበርካታ አመታት ኖሯል። አሁን የሚኖረው ሲድኒ አውስትራልያ ነው። ሲድኒ ባለው ዩኒቨርስቲ ኦፍ ቴክኖሎጂ በአካውንቲንግ እና ፋይናንስ በአንድ ጊዜ ሁለት ዲግሪ ለማግኘት እየተማረ ይገኛል። ወደ ካምፓላ ለዕረፍት በመጣበት ወቅት ከ “ሐበሻዊ ቃናው” ጋር ተስፋለም ወልደየስ ጋር ቆይታ አድርጓል።

ፎቶ- ፎቶ ኤቭሪዌር

የእኛ ሰው በሲድኒ እንዴት ነው ወደ አውስትራሊያ የሄድ ከው? በግል ስፖንሰር ነው የሄድኩት። እንደተለመደ ው ፎርም ተሞላ። በጉዳይ (በኬዝ) ከማለት ይል ቅ በአጋጣሚ ነው። ከአንድ ዓመት ከ 10 ወር በፊ ት እዚህ ካምፓላ ላይ አውስትራልያ ያመለከትን ሰዎች ጥሩ እድል አጋጥሞን ነበርና በዚያ ወቅት ነ ው የእዚያ ዕድል ተጠቃሚ ሆኜ ነው የሄድኩት።

በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደ አውስት ራልያ ያሉ ሀገሮች ሲሄዱ ኑሮን ለማሸ ነፍ ላይ ታች መሮጥ ነው እንጂ ትምህ ርት ቤት አይገቡም። አንተ እንዴት ተ ሳካልህ? ከሰው ሰው ፍላጎቱ ይለያያል። እዚህ ሆነን ብ ዙ ጊዜ ስናስብ በውጭው ዓለም ሄደን፣ ቶሎ ስ ራ አግኘተን፣ ትንሽ ሳንቲም ይዘን፣ ቤተሰብ ረድ ተን የሚሉ ነገሮች ናቸው አእምሮአችን ውስጥ የ ሚመጡት። ከዚህም ስሄድ “ከስደት ዓለም አን ድ ነገር ማትረፍ አለብኝ” ብየ ነው የሄድኩት። ያ ነገር ገንዘብ ሊሆን አይገባውም። የምሰራ ከሆ ነ አዎ አገኛለሁ፣ እጠቀማለሁ። ነገር ግን ከዚያ ያለፈ ነገር መኖር አለበት የሚል ዕምነት ነው የ ነበረኝ። እዚህ ያሉ ወዳጆቼ ያውቃሉ። እማራለ ሁ ቢያንስ ቢያንስ እሷን ለማግኘት ነው የምሄደ ው ነው ያልኩት። እንደወሰንኩትም የመጀመሪያ ስራዬ የነበረው በየዩኒቨርስቲዎቹ እየዞሩ መረጃዎችን ማሰባሰብ ነበር። ጊዜው የመረጃ ዘመን ነው። “ጎግል አድር ገህ” ስለእያንዳንዱ ዩኒቨርስቲ አስፈላጊ ነገር መፈ ለግ ትችላለህ። በዚህ አይነት የሁሉንም ዩኒቨርስ ቲዎች ሁኔታ ካወቅሁና አካባቢውን እና የአገሩን ሁኔታ ካጠናሁ በኋላ የምፈልጋቸውን የትምህር ት ዓይነቶች መረጥኩ።

ፎቶ- ተስፋለም ወልደየስ

እንደሄድክ በቀጥታ ሲድኒ ነው ያረፍከ ው ወይስ ሌሎች ቦታዎችን የመመልከት እድል አጋጥሞሃል? እንደሄድኩኝ ሲድኒ ነው ያረፍኩት። ኑሮዬ እስ ካሁንም ሲድኒ ነው። ወደ ትምህርት ቤት ከመግ ባቴ በፊት ግን “ኩዊንስላንድ” የሚባል ስቴት አ ለ። እዚያ ሄጄ ነበር። አውስትራሊያ ውስጥ በቱ ሪስት መስብህነቷ በይበልጥ የምትታወቅ፣ እንደ “ጎልድ ኮስት”፣ “ሰንሻይን ኮስት” የሚባሉ ጥሩ የ መዝናኛ ቦታዎች ያሉባት፣ “ብሪስበን” የምትባል ከተማን የማየት ዕድል አጋጥሞኛል። ይህ ቦታ ከ ዓለም ቱሪስቶች እየመጡ ጊዜያቸውን የሚያሳል ፉበት ነው። በጣም የወደድኩት ቦታ ነው። ብዙ ጊዜ አንድ ቦታ ስሄድ አካባቢን የማወቅ፣ የተሻሉ ቦታዎችን የማየት፣ በአንደዚህ ዓይነት ነገሮች የ መደሰት ባህሪው አለኝ። በዚያ ምክንያት ነው እነ ዚህን ቦታዎች ያየሁት።

“ሂዩማንቴሪያን ቪዛ አግኝተህ ወደ አውስትራልያ ከሄድክ ከወለድ ነጻ የሆነ 86 ሺህ ዶላር ያህል የመማር መብት አለህ ”

የመማር ዕድሉ ግን አለ? ብዙ ሰው ዕ ድሉ የለም፣ ከባድም ነው ብሎ ስለሚ ያስብ ይመስለኛል ወደ ትምህርቱ ዓለም የማይገባው። ገንዘብ ኖሮህ አይደለም ትምህርት የምትማረ ው። መንግስት ይደጉመሃል። የምትበላው፣ የም ትጠጣውን ለመሸፈን፣ መጠለያ እንዳያስቸግር ህ፣ መንግስት በየ14 ቀኑ የተወሰነ ገንዘብ ይሰጣ ል። በዚያ ላይ “ሂዩማንቴሪያን ቪዛ” አግኝተህ ከ ሄድክ ከወለድ ነጻ የሆነ 86 ሺህ ዶላር ያህል የመ ማር መብት አለህ። እንደዚህ የተመቻቹ ሁኔታዎ ች ካሉ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ካልተማርን መቼ እ ና የት ልንማር እንችላለን? አውስትራልያ እንድት ማር በጣም የሚገፋ ስርዓት ያለበት ሀገር ነው። ምን ያህሎቻችን በዚህ እድል ተጠቅመናል የሚ ለው ግን ጥያቄ ምልክት ውስጥ የሚወድቅ ነው። ብዙዎቻችን ገንዘብ ያሸንፈናል። ገንዘብ አግኝ ተን እዚያ ኑሮ እንጀምራለን። እዚያ እንግዲህ ኑ ሮ በተለያዩ ወጪዎች የተሞላ ነው። “ቢል” ይመ ጣል። ቤት በ“ሞርጌጅ” መግባት ይኖራል። አን ዴ እዚያ ውስጥ ከገባህ በኋላ ወጥተህ ወደ ትም

ስደተኞች ማወቅ የሚገባቸው 1.

ስደተኞች በሁለት ዓይነት መንገድ ወደ አውስትራልያ መግባት ይችላሉ። አንደኛው ጉዳያቸውን ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር አይቶ ወደ አውስ ትራልያ እንዲሄዱ ከመራላቸው “ክላስ 200” የሚባል ቪዛ ያገኛሉ። መንግስት በሚያዘጋጀው ቦታ ለአንድ ወር ከተቀመጡ በኋላ ቤት እን ዲፈልጉ ይደረጋል። ሁለተኛው መንገድ የግል ስፖንሰር አግኝቶ መሄ ድ ሲሆን “ክላስ 202” ነው። በኩል ለመሄድ መሞከር እንደ ፖሊሲ ያቸው ሁኔታ የሚጠብ የሚሰፋ ስለሆነ ከባድ ነው።

2.

5

ህርቱ ዓለም መመለስ በጣም አስቸጋሪ ነው። ብ ዙዎቻችን የመታለል ነገር አለብን። በገንዘብ መ ልኩም ካየነው ትምህርት ኢንቨስትመንት ነው። የተሻለ ክፍያ ታገኛለህ። ከመማር በኋላ በሚኖረ ው ህይወትህ ቢያንስ ቢያንስ ጉልበትህን ትቆጥባ ለህ። በደንብ ከተማርክ፣ ጊዜህን በደንብ ሰጥተህ የምትፈልገው ውጤት የምታስመዘግብ ከሆነ፤ እ ድሉ አለ፣ ስራው አለ። አብዛኞቹ እንደዚህ የትምህርት ዕድሎችን አይዳ ፈሩትም። በተለይ በእድሜ የገፋ ሰው የነበረው የኋላ የትምህርት ታሪክ ጥሩ ካልነበረ እዚያ ሄዶ በትምህርት የሚያሳልፈውን ጊዜ ሲያስበው የመ ዘግየት ነገር ይሰማውና የእኔን ሁኔታ በምሳሌነት መውሰድ ትችላለህ። በእኔ እድሜ ትምህርት ቤ ት መግባት በጣም ደፋርነት ነው። መቼ ተምሮ፣ መቼ አግኝቶ፣ መቼ ሊኖር ነው የሚል ጥያቄ ያስነ ሳል። ለእኔ ግን ገንዘቡ አይደለም የሚቀድመው። አንድ የሆነ ነገር ባውቅ ብዬ ነው። መቼም እዚህ የሌሉ መልካምና የተሻሉ ነገሮች እዚያ አሉ። እዚ ያ የሌሉ ነገሮች ደግሞ እዚህ ሊኖሩ ይችላሉ። የ እዚህን ልምድ ወደዚያ የዚያን ተሞክሮዎች ደግ

ነጥቦች

“ክላስ 200” ሆነ “ክላስ 202” የ“ሂ ዩማኒቴርያን ቪዛ” በመባል በጥቅሉ ይታወ ቃሉ። “ሂዩማኒቴርያን ቪዛ” ያገኘ ሰው ከ መምረጥ መመረጥ መብት ውጭ ማንኛው ም አውስትራልያዊ የሚያገኘውን ጥቅማ ጥቅም የማግኘት መብት አለው።

3.

ሞ ወደእዚህ ማምጣት ያስፈልጋል። መቼም በስ ደት ህይወቴን እስከመጨረሻው እገፋለሁ ብዬ አ ላምንም። በአንድ ወቅት ሁኔታዎች ሲመቻቹ ወ ደ አገር ቤት እመለሳለሁ ብዬ አስባለሁ። እና ባ ዶ እጄን መመለስ አልፈልግም። ምንድነው ይዤ ልገባ የምችለው ነገር? ይህን ዕድል ሳገኝ ሁኔታዎ ችን አይቼአለሁ። ፍላጎቴን እና የትምህርት ታሪኬን አውቃለሁ። የሚገባኝን የሙያ መስክ የመረጥኩኝ ይመስለኛ ል። በዚያ ዙሪያ ስኬታማ ብሆንና አንድ ቀን ወ ደ አገሬ የተወሰነ እውቀት ይዤ ብገባ ምናልባት በዚያ ዙሪያ ዕውቀታቸውን ይዘው ከገቡ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር አንድ ነገር በጋራ መስራት ነ ው የማስበው። የነበረውን ማሻሻል ሊሆን ይችላ ል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ የሌለ ነገር ካለ ያንን አሰራ ር አገር ቤት ወስዶ ተግባራዊ ማድረግ ሊኖር ይገ ባል ብዬ አምናለሁ። በነገራችን ላይ የትኛውንም የትምህርት ዓይነት ብትማር ፍላጎቱ ካለህ እና ከተማርክ በጥሩ ሁ ኔታ ትጨርሳለህ። በጥሩ ሁኔታ ከጨረስክ ደግ ሞ ምንም የምታጣው ነገር የለም። ይህንን ከጓ

“ስኪልድ ማይግራንት” የሚባ ል በርካታ ኢትዮጵያውያን የማይጠቀ ሙበት የቪዛ ዓይነት አለ። በዚህ ቪዛ ወደ አውስትራልያ የሚገቡ ሰዎች በተ ለያየ ሙያ ተመረቁ ባለሙያዎች ሲሆ ኑ በሙያቸው ስራ እንዲሰሩ የሚፈቀ ድላቸው ናቸው። ስደተኞች አይደሉ ም። ጥቂት ኢትዮጵያውያን ይህንን ቪ ዛ ማግኘት ተሳክቶላቸው በአውስትራ ልያ ይሰራሉ።

4.

ደኞቼ ተሞክሮ አይቼዋለሁ። ብዙዎቻችን ግን ያ ንን አለመዳፈር፣ ከእነሱ ጋር ተወዳድሬ ምን ያህ ል ውጤት ነው የማመጣው? የቋንቋ ችሎታዬ እ ያልን ብዙ ገደቦችን በራሳችን ላይ እንጥላለን። በ እርግጥ ብዙ መሰናክሎች አሉብን ነገር ግን እነዚ ያን ሁሉ አልፎ ከሚፈለገው ቦታ መድረስ ይቻላ ል ብዬ አምናለሁ። ማንኛውም ሰው ራሱን ከዚህ አዘጋጅቶ ከሄደ፣ መማር እንዳለበት አስቦ ከሄደ ቋንቋ እንደ ምክን ያት መነሳት የለበትም። በተለይ ከፍተኛ ትምህ ርት መማር የሚችሉ ሰዎች እዚህ ያላቸውን ጊዜ ቋንቋ ቢማሩበት፣ የመናገር እና የመጻፍ ችሎታቸ ውን ቢያዳብሩ እና የትምህርት ማስረጃዎችን ቢ ሰበስቡ እና ቢያዘጋጁ እዚያ በሚሄዱበት ጊዜ ነገ ሮችን ያቀልላቸዋል። ከሄዱ በኋላ መረጃ መፈለግ አለባቸው። የትኞቹ የትምህርት ዓይነቶች መልካ ም ናቸው? የእኔ ፍላጎት ምንድነው? የትኛው ቦታ ላይ ስኬታማ እሆናለሁ? ከዚያስ በኋላ ቀጣዩ ነገ ር ምን ይመስላል? የሚለውን ማየት አለባቸው። እዚያ ሲደርሱ ወደዚህም ወደዚያም ሳይሉ በቀጥ ታ ትምህርት ቤት ቢገቡ ይመረጣል። የትምህርት ማስረጃቸውን በቅርብ ማግኘት የ ማይችሉ ወይም የጠፋባቸውስ? እኔ ለምሳሌ የትምህርት ማስረጃ አልነበረኝም። የትምህርት ማስረጃ ለማምጣት ጥረት አድርጌ ነ በር። ሊሳካልኝ አልቻለም። የትምህርት ማስረ ጃ ስሌለኝ የነበረኝ አማራጭ “እንዲህ ነበርኩ” ብ ዬ መናገር ነበር። አገሩ፣ ስርዓቱ ጥሩ ነው። እዚያ “ጀስቲስ ኦፊስ” ውስጥ የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎ ች አሉ። እነሱ ፊት እንዲህ “እንዲህ ነበርኩኝ” የ ሚል ቃሌን ጽፌ ይህ እውነተኛ ታሪኬ ነው ብዬ ፈረምኩኝ። እኔ በዚያ መልክ ነው ትምህርት ቤ ት የገባሁት። ያለ ትምህርት ማስረጃ። የትምህር ት ማስረጃ ለማምጣት አንድ ሴሚስቴር አቃጥያ ለሁ። ግን ማምጣት አልቻልኩም። አንድ ሴሜስ ቴር ማባከን ቀላል ነገር አይደለም። በውጭው ዓለም አንድ ሴሚስቴር ማለት ብዙ ጊዜ ነው። የትምህርት ማስረጃችሁን ማግኘት ባትች ሉ ችግር የለም፣ ገንዘቡንም ቢሆን መ ጨነቅ አይገባችሁም አልክ። መማር ጀ መርክ እንበል። አውስትራልያ ከምትከ ተለው የትምህርት ስርዓት በተለየ ሁኔ ታ ነው የተማርከው። በዚያ ላይ የዕድ ሜ ጉዳይም አለ። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ቋንቋውን አቀላጥፈው ከሚናገሩት ወጣ ት አውስትራልያውያን ጋርም ሆነ ከሌ ሎች ሀገር ዜጎች ጋር መወዳደር አይከ ብድም? አንድ እውነት አለ። እንደ እኔ አይነቱ በኢትዮጵ ያ የተወለደ በሌሎች ቋንቋዎች አፉን የፈታ በእን ግሊዘኛ አፉን ከፈታ ሰው ጋር በንግግር ቅላጼው ም ሆነ በቋንቋ ክህሎት እኩል ሊሆን አይችልም። ይሄ ግልጽ ነው። አውስትራልያ ያለው በሙሉ ቋ ንቋውን በደንብ ይናገራል ማለት ግን አይደለም። እዚያ የተወለደው የሀገሩ ተወላጅ በመሆኑ ቋንቋ ውን በደንብ ሊናገር ይችላል። እንደኛው ግን ከ ተለያዩ አገሮች የመጡ አሉ። እኔ ከማውቀው ተ ነስቼ እንኳ ብነግርህ ጎረቤት አገሮች ከሆኑት ፊ ጂ፣ የሰሎሞን ደሴቶች፣ በጠቅላላው የፖለኔዥያ ን ደሴቶች ተብለው ከሚጠሩ ሀገሮች የሚመጡ አሉ። ከኮሪያ እና ከጃፓንም ጭምር የመጡት ይ ማራሉ። ክፍል ውስጥ ስትገባ እነዚህ ሁሉ አሉ። ግን በራስ መተማመነህ ይወስነዋል። ከእነሱ ጋር ቁጭ ብለህ ትማራለህ። ትፎካከራለህ። ቋንቋ ማወቅህ በራሱ የዕውቀት መመዘኛ ሆኖ መታየት የለበትም። የምትማረውን በደንብ ጠን ቅቀህ ካወቀኸው ያወቁትን ነገር መናገር ቀላል ነ ው። የሆነ ነገር ብትጠይቅ ስለዚያ ነገር እውቀቱ

ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር ወደ ሶስተኛ ሀገ ር የመስፈር እድሉን የሚሰጠው አንድ ስደ ተኛ ባለበት ሀገር ለህይወቱ የሚያሰጋ የደ ህንነት ችግር አለበት ብሎ ካመነ ብቻ እነደ ሆነ ይታወቃል። ይህ በ ዩ. ኤን. ኤች.ሲ.አ ር በኩል የሚገኘውን ዕድል ጠባብ ያደርገ ዋል። አሳማኝ “ኬዝ” ያላቸው ሰዎች ሌት ተቀን መጎትጎት አለባቸው። በተለይ በ “ኮ ሚዩኒቲ” ደረጃ ተደራጅተው ድምጻቸውን ማሰማት ይኖርባቸዋል።

ወደ ገጽ 22 ዞሯል

5.

የተለያዩ ሀገራት ስፖንሰር አ ግኝተው የሚጠብቁ ሰዎች ማመል ከቻቸውን ካስገቡ በኋላ በዩ.ኤን.ኤ ች.ሲ.አር ላይ ግፊት ከማድረግ በ ዘለለ “አፋጥኑልን” ለማለት ጉልበ ት አይኖራቸውም። ስለዚህ ውጤ ታችውን እስኪያውቁ ድረስ እዚያ ሲሄዱ ለሚጠብቃቸው ህይወት መ ማር እና መዘጋጀት አለባቸው።


ሐበሻዊ ቃና

10

ጥበብ የጁባ ስታር ሆቴል የሙዚቃ ቡድን ሽኝት ተደረገለት ላለፉት ዘጠኝ ወራት ጁባ በሚገኘው ስታር ሆቴል ውስጥ የሙዚቃ ዝግጅቶችን ሲያቀርብ የቆየው የሙ ዚቃ ቡድን ባለፈው ሳምንት ሽኝት ተደረገለት። ለሙ ዚቃ ቡድኑ ሽኝቱን ያደረገላቸው የሆቴሉ አስተዳደር ነው። በሽኝቱ ስነስርዓት ላይ የሆቴሉ ባለቤቶች እና አ ጠቃላይ ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን ለቡድኑ የምግብ እ ና መጠጥ ግብዣ ተደርጎለታል። የሙዚቃ ቡድኑ ወንድ እና ሴት ድምጻውያን እንደዚ ሁም አምስት ሴት እና አንድ ወንድ ተወዛዋዥን ያካተ ተ ነው። ቡድኑ ከስታር ሆቴል ጋር የሶሰት ወር ኮንት ራንት ተፈራርሞ ከአዲስ አበባ ወደ ጁባ የመጣው የዛ ሬ ዘጠኝ ወር ግድም ነበር። በሙዚቃ ቡድኑ እንቅስቃ ሴ የተደሰተው የሆቴሉ አስተዳደር ሁለት ጊዜ ኮንትራ ቱን በማደሱ ተጨማሪ ስድስት ወር ቆይቷል። ቡድኑ ከማክሰኞ በስተቀር ሳምንቱን ሙሉ የኢትዮጵያ፣ የኤ ርትራ እና ሱዳን ሙዚቃዎችን ከውዝዋዜ ጋር ለተመ ልካች ያቀርብ ነበር። በጁባ ስታርን ጨምሮ “ጁባ ብሪጅ” እና “ኩዊን ኦፍ ሼባ” የተሰኙት ሆቴሎች የሙዚቃ ቡድኖችን ከኢትዮ ጵያ በማስመጣት በዚያ ያለውን የሐበሻ ማህብረሰብ እና ደቡብ ሱዳንውያንን እያዝናኑ ይገኛሉ። አሁን ያቆ ሙ እንጂ “ኒውዮርክ” እና “ሄሮን” የተሰኙት ሆቴሎች ም ከኢትዮጵያ ያስመጧቸው የየራሳቸው የሙዚቃ ቡ ድን ነበራቸው።

የዳዊቴ መኮንን አዲስ አልበም በካናዳ ሊመረቅ ነው የታዋቂው ኦሮምኛ ዘፋኝ ዳዊቴ መኮንን አዲስ አልበም በካ ናዳ በድጋሚ ሊመረቅ ነው። “አኒ ዱፌን ጂራ” በተሰኘው ዘ ፈኑ ይበልጥ የሚታወቀው ዳዊቴ በቅርቡ የለቀቀው አዲሱ አ ልበሙ “ሶለኔ” ይሰኛል። ይህንኑ አልበም በግንቦት ወር መ ጨረሻ ላይ በሚኒሶታ አሜሪካ በይፋ ያስመረቀ ሲሆን ሐም ሌ 9 እና 10 በቶሮንቶ ካናዳ ይካሄዳል ተብሎ በሚጠበቀው የሙዚቃ ዝግጅት በድጋሚ ያስመርቃል ተብሎ ይጠበቃል። የዳዊቴ አልበም በኦሮምኛ ሙዚቃ አድማጮች ዘንድ በከፍ ተኛ ሁኔታ ይጠበቅ እንደነበር በኦሮሞ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያ ተኩሩ ድረገጾች በተደጋጋሚ ዘግበዋል። ለአልበሙ መጠበቅ አንድ ምክንያት የነበረው አስቀድሞ የተለቀቀው ነጠላ ዜማ ነበር። “ኦሮሚያዊነቴን እወደዋለሁ” የተሰኘው እና በአማርኛ ና ኦሮምኛ ቅይጥ የተሰራው ዜማ ጠንከር ያሉ መልዕክቶችን ያዘለ ነበር። ዳዊቴ በዚህ ዘፈኑ “ሊነጋጋ ሲል ይጠቁራል ሰማ ይ” ይላል። በዚሁ ስንኝ “ንጉስ እና ዝናብ” ከላይ እንደሚወር ድ ይጠቅስና “ያን ጊዜ ብሔር ከብሔር ጋር ተፋቅሮ” እንደሚ ኖር እና “አማረን ከጫላ መለየት ይቀራል” ሲል ይተነብያል። ይህ ነጠላ ዜማ ዳዊቴ ሚኒሶታ ከሚታተመው “ዘ ሐበሻ” ጋ ር ባለፈው ዓመት ባደረገው ቃለ መጠይቅ ምክንያት ለደረሰ በት ትችት የተሰጠ ምላሽ እንደሆነ ኦሮሞሲስ የተሰኘው ድረ ገጽ ዘግቧል። በቃለ መጠየቁ ድምጻዊው የኦነግ ደጋፊ እንደ ሆነ በግልጽ ተናግሯል። ስለ ኦሮሚያ መገንጠል ጉዳይ በቃለ ምልልሱ የተጠየቀው ዳዊቴ “ኦሮሚያ ከየት ነው የምትገነጠ ለው? መገንጠል ለሚፈልጉት ነጻነት እንሰጣለን እንጂ” የሚ ል ምላሽ ሰጥቶ ነበር።

በየዓመቱ በአሜሪካ የሚከበረውን የኢትዮጵያውያን የእግር ኳስ ውድድር ምክንያት በማድረግ ከኤፍሬም ታምሩ ጋር በአንድ መድረክ እንዲያቀንቅን ተጋብዞ የነበረው ጎሳዬ ተስፋዬ በሐዝን ምክንያት በሙዚቃ ዝግጅቱ ላይ ሳይገኝ ቀረ። ጎሳዬን የሙዚቃ ዝግጅቱን እንዲሰርዝ ያስገደደው ከሁለት ዓመቱ ጀምሮ እንደ እናት ተንከባክበው ያሳደጉት አያቱ ሞት ነው። ጎሳዬ ለአያቱ ከፍ ተኛ ፍቅር እንደነበረው በቅርብ የሚያውቀው የ“ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮግራም አዘጋጅ ተወልደ በየነ (ተቦርነ) ይገልጻል። እ ንደተቦርነ አባባል ከሆነ ጎሳዬ የመጨረሻ አልበሙ በሆነው “ሳታማኻኝ ብላ” ላይ የተጫወተውን “እናትዬ” የተሰኘውን ዘፈን መ ታሰቢያ ያደረገው ለእኚሁ አያቱ ነው። የጎሳዬ ድንገተኛ ሀዘን አትላንታ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ መነጋገሪያ ሆኖ እንደሰነበተ በቦታው ላይ የሚገኘው የ“ታዲያስ አዲሱ” ሰይፉ ፋንታሁን ይናገራል። በሁኔታው የተደናገጡት የሙዚቃ ዝግጅቱ አዘጋጆች ነገርየውን ሲያስተባብሉ ቢቆዩም በስ ተመጨረሻ ጎሳዬ ከኤፍሬም ጋር መዝፈን እንደማይችል ለአፍቃሪዎቹ አስረድተዋል። ጎሳዬ ከኤፍሬም ጋር ዝግጀቱን ለማቅረብ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ለእሁድ ሰኔ 26 ቀን 2003 ዓ.ም ነበር።

የጥላሁን ገሰሰ የ“ሆድ ይፍጀው” ቅኔ ሊፈታ ይሆን?

ላሁን ገሰሰ አዲስ አበባ ነው የተወለድኩት ይ በል እንጂ አዲስ አበባ አለመወለዱን፣ ለም ን እንደዋሸ የሚናገር መጻሕፍት በቅርቡ ታ ትሞ ለገበያ ሊውል ነው፡፡ በቅርቡ ለሕዝብ እንደሚቀር ብ የተነገረለት ይህ መጽሐፍ ከ450-500 ገጾች እንደሚ ኖሩት “ኢትዮፒካሊንክ” የሬድዬ ፕሮግራምን ጠቅሶ አዲ ስ ነገር ኦንላይን ዘግቧል። ይህ ብዙ ሚስጥር የሚገልጥ መጽሕፍ የጥላሁንን ጉዶች ዘክዝኳቸዋል ነው የተባለው፡ ፡ ለሕዝብ እስከዛሬም እንቆቅልሽ ሆኖ የቆየው “ሆድ ይፍ ጀው” በዚህ መጻሕፍ በስፋት ይተነተናል፡፡ ከጥላሁን ገ ሰሰ የቅርብ ቤተሰብ አንዱ ጥላሁን ገና የአንድ ዓመት ል ጅ እያለ ማስታወሻ መያዝ ጀምሮ ነበር፡፡ ይህ ከቤተሰብ የተገኘ ማስታወሻ ለዚህ መጽሕፍ መነሻ እንደሆነ ተዘግ ቧል፡፡ በእጅ የተጻፈው ይኸው መረጃ በመጽሐፉ ውስ ጥ እንደሚካተት ተነግሯል፡፡ ከዚህ መረጃ ባሻገር እስከ ዛሬ ህዝብ ያላያቸው አስገራሚ የጥላሁን ፎቶዎችም ይ ካተታሉ ተብሏል፡፡

የግጥም ጥግ ተይው እንተወው ተይው እንተወው፤ … የዘመን ቃፊሩን ማለፍ አልቻልንና ይህ ዓለም ጥበቱ አልመጠነንና፤ ተይው እንተወው፣… ውጥኑ ግብ ይሁን ጅማሬው ፍጻሜ፣ ቅጽበቷ ሙሉ ዕድሜሽ ወቅቷ ዘላለሜ።

ደበበ ሰይፉ u

u

u

ስማኝ አንተ ዳኛ እኔ የአንተ ወዳጅ የምድሩ ምሶሶ፤ የአድባሩ መከታ የባድማው ግርማ የፍትህ መሰረት የቀየው መከታ እኔ ታዛዥ ባሪያህ የፍጡራን ንጉስ ልዑል ዘ አናብስት አጥንቷ የላላ ቀንዷ ያልጠነከረ ክፉ ደግ ያላየች ስጋዋ ያልገረረ ዱሩን ያላወቀች ፤ ጥርስ የማታስቸግር አንድ ጭቅላ አጋዘን፤

ድምጻዊት አቢ ላቀው በፊልም ልትመጣ ነው

ጎሳዬ ከኤፍሬም ታምሩ ጋር የነበረውን ኮንሰርት በሐዘን ምክንያት ሰረዘ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ነዋሪነቷን ቴክሳስ አሜሪካ ያደረገችው ድምጻዊት አቢ ላቀው የኢትዮጵያ የገጠር ህይወት የሚያሳይ ፊልም ሰራ ች። ወደ መጣሁበት (ባክ ቱ ማይ ሩትስ) የተሰኘው ይሄ ው ፊልም በስንታየሁ አበበ ዳይሬክተርነት የተሰራ ሲሆን በቅርቡ ለዕይታ ይበቃል ተብሎ ይጠበቃል። አቢ ለዚህ ፊልም ወደ 150 ሺህ ብር ገደማ እንደተከፈላት ምንጮች ከአዲስ አበባ ለ “ሐበሻዊ ቃና” ገልጸዋል። ፊልሙ አንድ የከተማ ልጅ ገጠር በሄደበት ወቅት በተ መለከታት እንስት ሲማርክ እና እርሱን ተከትሎ የሚደር ስበትን የሚያሳይ ነው። አቢ በዚህ ፊልም ላይ በገጠር ያ ለች ሴት ሆና ስትጫወት የከተማ ልጅነቱን ሚና ደግሞ ሳ ሙኤል በየነ ወስዷል። በሙያ ሳሙኤል እንደ አቢ ዘፋኝ ነው። የኤፍሬም ታምሩን ዘፈኖች አስመስሎ በመጫወት የሚታወቀው ሳሙኤል የራሱ ነጠላ ዜማዎችም አሉት። አቢ ለዚህ ፊልም ማጀቢያ የሚሆን ነጠላ ዜማ ከሶስ ት ሳምንት በፊት ለቃለች። እንደ ፊልሙ ሁሉ “ወደ መ ጣሁበት” የሚል ስያሜ ያለው ነጠላ ዜማ አዲስ አበባ በ ሚገኙ የኤፍ. ኤም ሬድዬ ጣቢያዎች እየተደመጠ ቢሆን ም “እንደተጠበቀው አይደለም” እንዳልሆነ ምንጮች ይ ናገራሉ። አቢ በዚህ ነጠላ ዜማ ከምትታወቅበት ዘመናዊ አዘፋፈን ወጣ ብላ “ችክችካ” ተብሎ በሚታወቀው በዘ መናዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች የተቀናበረ ባህላዊ ስልት ያለ ው ዘፈን ሰርታለች።

አግኝቼ ካልበላሁ፤ ውስጤ ላለው ጌታ መስዋ’ት ካላቀረብሁ እንዴት በምድሪቱ ፍትህ ይበየናል ሰላምስ ይሰፍናል? ግርማ ተስፋው u

u

u

እምጷ…!? ነጋዴ ደብቆት፣ ዋጋው ጣሪያ ደርሶ የደሜ ስኳርም፣ ጤናዬን አቃውሶ ምስኪኑ ምላሴ ከላሰው ቆይቷል እስኪ አስታውሽኝ ውዴ… ስኳር ምን ምን ይላል?

ዮሐንስ ሞላ u

u

u

ርሃብ ርሃብ ምን ይመስላል? ችግርስ? ብላችሁ እንዳትጠይቁኝ ለኔ ለመልሳችሁ ጥጋብን ጠይቁኝ እነግራችኋለሁ ሲመጣ እንዳይጠፋኝ ሳጠናው ኖሬአለሁ።

በዕውቀት ላቀው [“ድንጋይ ይጣፍጣል” በሚል በቅርብ ከወጣው የግጥም መድብል] u

u

u

ቲፎዞ አንበሳው ጅቡን አሸንፎ ስላዩት አንበሳው አንበሳው አሉት፣ አንበሳው ባይቀናው ኖሮ እኮ ጅቡ ጅቡ ነበር የሚሉት፣ ጅቡንም ነበር አንበሳ ግቢ የሚያስገቡት።

አባ አደራው u

u

u

ግማሽ ሌሊት ሆነ ልቤ ቅር እንዳለው ልቤ እንደተዘጋ ልቤ ሲፈልግሽ ዝምታ ወርቅ ሆነ ዝምታ ራት ሆነ ምንም ሳናወራ ግማሽ ሌሊት ሆነ ።

ሮጀር ሚላ- ካምፓላ


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ጣዕመ ዳግም ወደካምፓላ መጣ

ለ2010 አዲስ ዓመት ወደ ኡጋንዳ በመምጣት የሙዚቃ ዝግጅቱን ያቀረበው ዝነኛው ኤርትራዊ ድም ጻዊ ጣዕመ ወልደሚካኤል ወደ ካምፓላ ተመልሷል። የሙዚቃ ዝግጅቱን እሁድ ሐምሌ 2 ቀን 2003 ዓ.ም (ጁላይ 10) ቡጋንዳ ሮድ በሚገኘው ኦፕን ሀውስ ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል። ጣዕመ ይህንን የ ሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ ከሚኖርበት አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ነው የሚመጣው። በዝግጅቱ ላይም የዛሬ ዓመት ገደማ ካወጣው አዲሱ አልበም ዘፈኖችን ይጫወታል ተብሎ ይጠበቃል። የጣዕመ የመጨረሻ አልበም “ይኩንለኪ” የሚሰኝ ሲሆን በኤርትራ ሙዚቃ ሀያስያን ዘንድ “ለረጅም ጊዜ በሙዚቃ ውስጥ የመቆየቱን ኃይል” ያስመሰከረበት ነው ተብሎለታል። በዚህ አልበም ውስጥ 12 ዘ ፈኖች የተካተቱ ሲሆን በ“ጓይላ” እና ዘመናዊ ሙዚቃ ስልቶች የተሰሩ ናቸው። ጣዕመ የባህላዊ ትግርኛ ስልት በሆነው “ጓይላ” የተጫወታቸውን ዘፈኖች በኤርትራ እንዲዘጋጁ ያደረገ ሲሆን ዘመናዊ የ “ፖፕ” ስልት የተከተሉትን ዘፈኖች ደግሞ በአሜሪካ እንዲቀናበሩ አድርጓል። ይህ የመጨረሻ አልበሙ በአብዛ ኛው ያካተተው የፍቅር ዘፈኖችን ነው። ኤርትራውያን ለአመታት ጋብቻዎቻቸውን ያደምቁበት የነበረ ው “ሩሁስ ጋማ” የተሰኘው የሰርግ ዘፈንም የአልበሙ አካል ነው። ጣዕመ ለዚህ ዘፈን “አዲስ ህይወት” ነው የሰጠው ተብሎ ተወድሷል። ይህንን አልበም የገመገመው ቢኒያም ተክሌ የተባለ የሙዚቃ ሀያሲ “ጣዕመ እንደገና ተሳክቶለታል” ብ ሎታል። “አልበሙ ከውስጡ ለብቻ ተነጥሎ የሚወጣ ዘፈን አላቀረበም። ነገር ግን አድማጭን የሚያስደ ስቱ ዘፈኖች በውስጡ የሞሉበት ነው” ብሎ ነበር። ስለ ጣዕመ ደግሞ ይህን ተናግሮ ነበር። “አንድ ድም ጻዊ የተዋጣላት ድምጽ ቢኖረውም እንዴት ወደ አድማጭ ዘንድ እንደሚያደርሰው ካላወቀ ተፈጥሮ የ ሰጠችው ጸጋ ጥቅም የለሽ ነው የሚሆነው። በተቃራኒው አንድ ድምጻዊ የማይረባ ድምጽ ይዞ ነገር ግን እንዴት ማዋሃድ እንዳለበት ካወቀ ኮከብ ሊሆን ይችላል። ጣዕመ የተዋጣለት ድምጽ የለውም ግን አይ ረቤም አይደለም። በጊዜ ሂደትም እየተሻሻለ የመጣ ዘፋኝ ነው። ድምጹን ለማሻሻል ጠንክሮ የሚሰራ ነ ው። ልክ እንደ ቆየ ወይን ጠጅ ዕድሜው በጨመረ ቁጥር ምርጥ እየሆነ የመጣ ነው።”

የኢትዮጵያ ድምጻውያን አትላንታ ላይ ከትመዋል በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን አዘጋጅነ ት በየዓመቱ በሚካሄደው የእግር ኳስ እና ባህል ዝግጅት ላ ይ ለመገኘት በርካታ ድምጻውያን አትላንታ ላይ ከትመዋ ል። ከሰኔ 26 ቀን ጀምሮ ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሚካ ሄደው በዚህ ፌስቲቫል ላይ ዝግጅቶቻችን ለማቅረብ ከተ ገኙት ድምጻውያን መካከል ብርሃኑ ተዘራ፣ ታደለ ገመቹ፣ ታደለ ሮባ፣ ብዙአየሁ ደምሴ፣ ሳያት ደምሴ፣ ይርዳው ጤ ናው፣ እዮብ መኮንን፣ ቀመር ዩሱፍ፣ አበባ ደሳለኝ፣ አስቴር አወቀ እና ሄለን በርሄ ይገኙበታል። ነዋሪነታቸውን አሜሪካ ያደረጉት እንደ ኤፍሬም ታምሩ፣ ሳምቮድ እና ናቲ ሐይሌ ም ከቦታው አልቀሩም። የዚህን ዓመት የእግር ኳስ እና የባህል ዝግጅት ላይ ለመታ ደም ወደ 10 ሺህ ኢትዮጵያውያን ወደ አትላንታ ይተማሉ ተብሎ ቅድሚያ ግምት ተሰጥቶ ነበር። ይህንን ከፍተኛ ቁ ጥር ያለውን ኢትዮጵያዊ ለማዝናናት የሙዚቃ አዘጋጅ ፕ ሮሞተሮች ቁጥሩ ከፍ ያለ ገንዘብ ከፍለው ዘፋኞችን ከኢ ትዮጵያ በየዓመቱ ያስመጣሉ። በአሜሪካ የሚኖሩትንም ጠ ርተው ያሰራሉ። በዓመታዊው ዝግጅት ላይ ሙዚቃቸውን እንዲያቀርቡ የሚጋበዙ ድምጻውያን ታዲያ ወቅታዊ ዝናቸ ው ከፍ ያለ አሊያም የምንግዜም ተወዳጅ የሆኑ ዘፋኞች ና ቸው። በዚህ ዓመት ግን ነገሮች የተለዋወጡ ይመስላል። የ “ታዲያስ አዲስ” የሬድዬ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነውና በቦ ታው የሚገኘው ሰይፉ ፋንታሁን ለባልደረቦቹ እንደተናገረ ው ከሆነ ለስራ ያልተጋበዙ ድምጻውያን ሳይቀር በአትላንታ ስራ ፍለጋ ታይተዋል። “ዘፋኝ ክብር ነበረው። ዘፋኞች ተጠይቀው ነበር የሙዚቃ ኮንሰርት የሚሰሩት። አሁን ግን አንዳንድ ዘፋኞች ፕሮሞተ ሮች ጋር እየደወሉ ልሰራ እሰከማለት ድረስ ደርሰዋል” ብሏ ል ሰይፉ በሬድዬ ፕሮግራሙ ላይ በስልክ በሰጠው ቃለ ም ልልስ። እንደ እርሱ አባባል ከሆነ ሌላውን ዜጋ የሸነቆጠው የኑሮ ውድነት የድምጻውያንንም በር አንኳኩቷል። “የበፊቱ የኮንሰርት ክብር እና ግርማ ሞገስ እየቀረ መጥቷል” ሲልም የተመለከተውን ተናግሯል። ድምጻውያን ከኮንሰርት ይልቅ ፈጠራ ላይ ቢያተኩሩ ይሻል ነበር የሚለው ሰይፉ የኑሮ ች ግሩንም ለመፍታት ማድረግ ያለባቸውን ጠቁሟል። “ቁጭ ብለው በር ዘግተው ኮፒራይቱ እንዲስተካከል ስራ ቢሰራ እነሱም እዚህ ደረጃ ላይ የሚደርሱ አይመስለኝም” ይላል።

በዚህ ጋዜጣ ማስታወቂያ ለማውጣት ከፈለጉ

በ+256-778-693669 ይደውሉልን

11

ጥበብ ሰሞነኛ ፊልሞች ዱካ ተዋንያን፦ ምኦን ጸጋዬ፣ ካሌብ ዋለልኝ፣ ሜሮን ጌትነት እና ሌሎች ዳይሬክተር፦ ተገኝ ሳሙኤል የፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ 46 ደቂቃ

በፋና ኤፍ ኤም በሚተላለፈው የ“ኢትዮፒካሊንክ” የሬድዮ ፕሮግራም ላይ የሚሰራው ስምኦን ጸጋዬ በዚህ ፊልም ላይም የወከለው ገጸ ባህርይ ከሙያው ጋር ይመሳሰላል። የምርመራ ጋዜጠኝነትን (ኢንቨስትጌቲቭ ጆርናሊዝም) ለመስራት የት ድረስ እንደሚኬድ ይህ ፊልም ያሳያል። ዋና ገጸ ባህርይው የመረጃ ዱካዎችን ለመከተል ራሱን ወደ ሴትነት ይቀይራል። ከዚያስ? ፊልሙ ምላሽ አለው።

ላውንደሪ ቦይ ተዋንያን፦ ሳያት ደምሴ፣ ታሪኩ ብርሃኑ፣ ጌታቸው ስለሺ፣ መቅደስ መለሰ እና ሌሎች ዳይሬክተር፦ ጸጋ ዩሐንስ እና ልዑል ሰለሞን የፊልሙ ዘውግ፦ አስቂኝ የፍቅር ፊልም የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ ባባ እና ሊያድ በገጠር አብረው ያደጉ ናቸው። ወደከተማም ከመጡ በኋላ የማይነጣጠሉ ጓደኛሞች ሆነዋል። አንድ ቤት እየኖሩ በአንድ ላውንድሪ ቤት አብረው እየሰሩ እንድ እህት እና ወንድም ይኖራሉ። ጓደኛ ለማፍራት ወደ ምሽት ክለብ ሲሄዱ እንኳ አብረው ነው። ሳያት ደምሴ የምትጫወታት ሊያድ ባባን እንዴት ሴቶችን አንደሚያጠምድ የምትመክር ናት። ጨዋታ ወዳድ የሆነው ባባ ሴቶችን የሚያሳድድ ነው። ሊያድ ከባባ ጋር ያደገችበትን መንደር እንደገና ስትጎበኝ ግን በሁለቱ መካከል ያለው ትስስር ከጓደኝነትም በላይ እንደሆነ ትረዳለች። ከዚህ በኋላ በሁለቱም መካከል እያደገ የሚመጣው እንግዳ ስሜት የፊልሙ ማጠንጠኛ ነው።

ትዝታህ ተዋንያን፦ ግሩም ኤርሚያስ፣ አንተነህ አስረስ፣ ሙሀመድ ሚፍታህ፣ ሜላት አሰፋ እና ሌሎች ዳይሬክተር፦ ሀብታሙ ህብረወርቅ የፊልሙ ዘውግ፦ ድራማ የፊልሙ ርዝመት፦ 1 ሰዓት ከ35 ደቂቃ ይህ ፊልም በ19 60ዎቹ የነበረውን ሁኔታ በምልሰት የሚተርክ ነው። በኬንያ የከፍተኛ ተቋም ትምህርቱን ያጠናቀቀው ወጣቱ መብራቱ ከብቶችን የሚያጠቃውን የደስታ በሽታ ለማጥፋት ወደ ሲዳሞ ይወርዳል። በሲዳሞ ጉዞው ስራውን ብቻ ሳይሆን የወደፊት ህይወቱን ሙሉ ለሙሉ የሚለውጥ ክስተት ያጋጥመዋል። መብራቱ በሲዳሞ ቆይታው አብራው ከምትሰራው ጽጌረዳ ጋር ፍቅር ይጀምራል። በስራው ላይ ባሳየው ትጋትም ሹመት ያገኛል። በመብራቱ ስኬት የተበሳጩት ሁለት የስራ ባልደረቦቹ ሊበቀሉት ይወጥናሉ። ውጥናቸው የታሰበለትን ኢላማ ቢስትም መብራቱ ልጅ ወልዶ እና ጎልማሳ ለመርሳት ያልቻለውን ሀዘን ያሸክመዋል።


ሐበሻዊ ቃና

12

ጥበብ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ኢትዮጵያዊቷ ፋሽን ዲዛይነር ለኒውዮርክ

“ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የፋሽን ስታይል አለ። የእኛ የሆኑት አልባሳት ደግሞ አሉ። እኔ ያደረግኩት ለራሳችን ባህላዊ ልብስ መስሪያ የምንጠቀምባቸውን ጥሬ ዕቃዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ‘ስታይል’ መስጠት ነው”

ሪስ፣ ለንደን፣ ሚላን እና ኒው ዮርክ። እዚህ አራት የአለማች ን ድንቅ ከተሞ ች የየራሳቸው መለያ ቢኖራቸውም አን ድ የሚያደርጋቸው ነገር ግን አለ። ፋሽ ን። አራቱም ከተሞች በፋሽን ከተማነታ ቸው ይታወቃሉ። ፓሪስ ከጥበብ እና ፋ ሽን ጋር በነበራት የረጅም ጊዜ የታሪክ ት ስስር እና አሁንም ድረስ መቀመጫቸው ን በእርሷ ባደረጉ የፋሽን ቤቶች ትታወ ቃለች። ለንደን የክብር እና ማራኪ ፋሽን ከተማ ነች ይሏታል። ከከተማይቱ የሚ ወጡት ፋሽኖች ከገበያ ስኬት እና በብዙ ሰዎች እንዲለበሱ ከመሰራት ይልቅ ክብ ር እና የሚያተኩሩ ናቸው። ሚላን እና ኒውዮርክ ግን ከለንደን በተ ቃራኒ ጠርዝ የተቀመጡ ናቸው። የሁለ ቱም ከተማዎች ፋሽኖች ገበያ ላይ ባላቸ ው ውጤታማነትም ሆነ በብዙሃን መገ ናኛ በሚያገኙት ሽፋን የገነኑ ናቸው። የ ሚላንም ሆነ የኒውዮርክ ፋሽኖች በው በታቸው እና ማራኪነታቸው የሚታሙ አይደሉም። አሰራራቸውም ጥንቅቅ ያለ ነው። እንዲያም ሆኖ ወዲያውኑ ተገዝ ተው የሚለበሱ አይነት ልብሶች የሞሉ ባችው ናቸው። ከነዚህን አራት የፋሽን ከተሞች ቆንጮ ማን እንደሆነ ለመለየት በየጊዜው ው ድድር ይደረጋል። እንደ “ግሎባል ላን ጉዌጅ ሞኒተር” ዘገባ ኒውዮርክ እ.ኤ.አ ከ2004 ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ አ መታት የበላይነት ክብሩን ተጎናጽፋለ ች። እ.ኤ.አ በ2009 የኢጣሊያኗ ሚላን ክብሯን ብትነጥቃትም ባለፈው ዓመት ግን መልሳ አምጥታዋለች። ኒውዮርክ በ ፋሽኑ ዓለም ያላትን ይህን ደረጃ የሚያ ውቁ የዘወትር ህልማቸው በከተማይቱ በሚካሄዱ ዝግጅቶች በአንዱ መካፈል ነ ው። የ30 ዓመቷ ኢትዮጵያዊት ዲዛይነ ር ፍቅርተ አዲስ ግን ወደ ፋሽኑ ዓለም ጠቅላላ በገባች በሁለተኛ ዓመቷ ይህን ን እድል አግኝታለች።

የሞሪሸሷ “ንግስት” ፍቅርተ ከሐምሌ ሰባት እስከ ዘጠኝ በ ኒውዮርክ በሚካሄደው “አፍሪካን ፋሽን ዊክ” እንዲሳተፉ ከተመረጡ 21 ዲዛየነ

ሮች አንዷ ሆናለች። በየዓመቱ በሚካሄ ደው፣ እውቅና ባለው እና ሰፊ መገናኛ ብዙሃን ሽፋን በሚያገኘው በዚህ ዝግጅ ት ላይ እንድትሳተፍ የተመረጠችው ግን አለ ምክንያት አልነበረም። ባለፈው መ ጋቢት ላይ በአፍረካዊቷ ሞሪሸስ ላይ ተ ካሄዶ በነበረው “ኦሪጅን አፍሪካ- ፋይበ ር ቱ ፋሽን” በተሰኘው ዓመታዊ ውድ ድር ካሸነፈች በኋላ ነበር በኒውዮርኩ የ ፋሽን ሳምንት አዘጋጆች አይን ውስጥ የ ገባችው። ኢትዮጵያዊቷ ዲዛይነር በሞሪሽሱ ው ድድር ለአሸናፊነት የበቃችው ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገሮች ከተውጣጡ 12 ዲዛየነ ሮች ጋር ተወዳድራ ነበር። የውድድሩ ዓ ላማ አፍሪካን በአልባሳት እና ዲዛይን ዘ ርፍ አዳዲስ ሀሳቦች የሚፈልቁባት አህጉ ር ማድረግ ነው። በውድድሩ ላይ አሸና ፊው የሚመረጠው የሚቀርቡት ዲዛይ ኖች በተለያዩ መስፈርቶች ከተመዘኑ በ ኋላ ነው። አልባሳቱ ሊሸጡ የሚችሉ ዓ ይነት መሆናቸው እና በየጊዜው መለበስ መቻላቸው በመመዘኛ መስፈርትነት ከ ተካተቱት መካከል ነው። የዲዛየነሩ የፈ ጠራ ብቃት፣ ቴክኒካዊ ችሎታው እና የ ሀገሩን ጥሬ ዕቃ የሚጠቀም መሆኑም ከ ግምት ውስጥ ይገባል። የሀገር ባህል አልባሳትን በዘመናዊ መን ገድ ዲዛይን ማድረግ የሚያስደስታት ፍ ቅርተ በአወዳዳሪዎቹ የሚጠየቁትን መ ስፈርቶች ሳይጠየቅ ያሟላች ነበር። ፍቅ ርተ ለዚህ ወድድር ስምንት ያህል ስራ ዎቿን ነበር ይዛ የቀረበችው። ሞሪሸስ በ ሚገኙ ሞዴሎች አማካኝነት ለዕይታ የ ቀረቡት ቀሚሶቿ በተለይ ባህላዊን የሐ በሻ ቀሚስ ከዘመናዊ ጋር በሚገባ የቀየ ጡ ነበሩ። ለወንዶች ያዘጋጀቻቸው አል ባሳትም ቢሆን ኢትዮጵያ ቀለም ያላቸ ው ነበሩ። “እኛ ጋር ሁሌም ቢሆን የትኛው ነው ባ ህላዊ? ወይ የትኛው ነው ዘመናዊ? የሚ ለው ክርክር አለ። በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የፋሽን ስታይል አለ። የእኛ የሆኑት አልባሳት ደግሞ አሉ። እኔ ያደረግኩት ለራሳችን ባህላዊ ልብስ መ ስሪያ የምንጠቀምባቸውን ጥሬ ዕቃዎች ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ‘ስታይ ል’ መስጠት ነው” ስትል ለሪፖርተር ጋ

ዜጣ ተናግራለች። በሌላው ዓለም ያልተለመዱ ግን ዓ ይን የሚገቡ ስራዎችን ይዛ በውድድ ሩ ላይ ብትገኝም አሸንፋለሁ የሚል ቅድሚያ ግምት እንዳልነበራት ግን ትናገራለች። “እኔ እንዲህ አልጠብ ቅም ነበር። “አሸንፋለሁ ብዬ አላስ ብኩም” ስትል ለታዲያስ አዲስ የሬ ድዬ ፕሮግራም ተናግራለች። በው ድድሩ በርካታ ነገር መማሯንም ትና ገራለች። “ከባድ እና አስደሳች ውድ ድር ነበር። ሁሉም አገራት የየራሳቸ ውን የሚስብ ባህል እና ስታይል ይ ዘው ነበር የመጡት። ለእኔ እንኳ አ ንዱን ከአንዱ ለመምረጥ ከባድ ነበ ር። ምክንያቱም ሁሉም ቆንጆዎች ነ በሩ” ስትል ለውድድሯ የነበራትን ስ ሜት ለ “ኒውዮርክ ፋሽን ዊክ” ድረ ገጽ አካፍላለች።

የእናቴ ስፌት መኪና ፍቅርተ ለሞሪሸሱ ወድድር ስምንት ያህል ስራዎቿን ይዛ ነበር የቀረበችው

ፍቅርተ በሞሪሽሱ ውድድር ለአሸናፊነት የበቃችው ከ12 ዲዛየነሮች ጋር ተወዳድራ ነበር

ፍቅርተ ሞሪሸስ ከመጓዟ፣ ለኒውዩ ርክም ለመታጨት ከመብቃቷ ሁለ ት ዓመት በፊት ፋሽን የትርፍ ጊዜ ስ ራዋ ነበር። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሳይኮሎጂ ትምህርቷን ያጠናቀቀች ው እና እስከ ማስተርስ የተማረችው ፍቅርተ በተማረችበት ሙያ የተለያ ዩ ቦታዎች ሰርታለች። የዛሬ ሁለት ዓመት ግድም ግን ወደ ፋሽኑ ስራ ጠቅላላ ለመግባት በመወሰን የራሷን ሱቅ ከፍታለች። አሁን “የፍቅር” በ ሚል ስያሜ የአልባሳት ዲዛይኖቿን አዲስ አበባ ቦሌ ኤድና ሞል አካባቢ በሚገኘው ሱቋ ለገበያ ታቀርባለች። ወደ ፋሽኑ ስራ ሙሉ ለሙሉ ከመ ግባቷ በፊት ለዲዛይን ስራ መነሻ የ ሚሆኑ ነገሮችን ሁለተኛ ደረጃ ተማ ሪ እያለች ጀምሮ ታደርግ ነበር። የ ሚገዛላትን ልብስ ወደ እናቷ የስፌት መኪና በመውሰድ በሚጥማት እና እርሷ ጥሩ ነው ብላ በምታስበው “ስ ታይል” መልክ ታስተካክላች። “ሁለ ተኛ ደረጃ እያለሁ ሀሳቦቼን በስዕል አስፍራለሁ። ልብስ ተገዝቶልኝ ዲዛ ይኑን እለወጣለዋሁ። ሙከራዎች አ ድርግ ነበር” ስትል ለ“ታዲያስ አዲ ስ” የሬድዬ ፕሮግራም ተናግራለች። እንዲህ በአልባሷቷ ላይ ሙከራ ስ

ፎቶዎች- የፍቅርተ ፌስ ቡክ ገጽ፣ “አፍሪካን ፋሽን ዊክ”፣ ማይቤኑካፌ ድረ ገጽ ፣ ዩ ኤስ አይድ

ታደርግ ትቆይ እንጂ የመጀመሪያ ሙሉ የዲዛይን ስራ የሰራችው ግን በራሷ ልብ ስ ሳይሆን በእናቷ ቀሚስ ላይ ነበር። “በ ጣም የምታምር የእናቴ ቀሚስ ነበረች። ሰርቼው ለብሼ ወጣሁ” ትላለች ወደ ኋ ላ መለስ ብላ ስታስታውስ። ያቺ ቀሚ ስ አሁንም ድረስ በክብር ተቀምጣለች። በእናቷ ቀሚስ የጀመረችው የዲዛይን ስ ራ አሁን ባህር ማዶ ተሻግሯል። ኢትዮ ጵያንም በዓለም አቀፉ የኒውዮርክ ፋሽ ን ሳምንት ለመወከል የመጀመሪያው ሆ ናለች።

“የፍቅር” ኒውዮርክ ፍቅርተ በ“ኒውዮርክ ፋሽን ዊክ” 15 አ ልባሳቶቿን ይዛ ትቀርባለች። አልባሳቶቹ ጥንቃቄ በሚያስፈልጋቸው የባህላዊ አ ልባሳት ጥሬ ዕቃዎች የተሰሩ ስለሆኑ ጥ ቂት ችግር ቢያጋጥማቸው የሚበላሹ ዓ ይነቶች ናቸው። የዚህ ዝግጅት ኦፌሲሊ ያዊ አጋር ከሆኑት አንዱ የሆነው “ዲ ኤ ች ኤል” ታዲያ ይህንን ችግር ለመፍታ ት መላ ይዞ መጣ። አንድን ልብስ ሳይተ ጣጠፍ በቁመናው ማጓጓዝ የሚያስችል እና ልዩ ትዕዛዝ የሚመጣ “ሀርበር ቦክ ስ” አዘጋጃላት። ለዚህም የፍቅርተም ኤ ፌሲሊያዊ የጉዞ አጋር ለመሆን መስማ ማቱን ለመግለጽ ሰኔ 23 ቀን በሸራተን አዲስ ሆቴል ግብዣ አሰድቶ ነበር። ፍ ቅርተ ለቅድመ ዝግጅት በሚል ሁለት አ ልባሳትን በዚህ ድርጅት በኩል አስቀድ ማ ልካ ነበር። አሁን ልብሶቹም ተዘጋጅተዋል። የቀረ ነገር ቢኖር ሐምሌ 8 ቀን ከ17 ሌሎች ዲ ዛይነሮች ጋር ስራዎቿን ማቅረብ ነው። በዚህ ዝግጅት ከኡጋንዳ፣ ካሜሮን፣ ጋ ና፣ ጃማይካ፣ ናይጄሪያ፣ ቱኒዚያ፣ ሴኔጋ ል፣ ሴራሊዮን፣ ደቡብ አፍሪካ እና ታን ዛኒያ እንዲሳተፉ የተመረጡ እና የተጋበ ዙ ዲዛይነሮች ይገኙበታል። አልባሳቱን ለብሰው ሰበር ሰካ እንዲሉ ደግሞ ከጥቁ ር እስከ ሂስፓኒክ፣ ከነጭ እስከ እስያዊ ያሉ ሞዴሎች ተዘጋጅተዋል። ከኒውዮርኩ ከንቲባ ብሉምበርግ በየዓ መቱ እንዲካሄድ ኦፊሲሊያዊ እውቅና የ ተሰጠው ይሄው ዝግጅት ባለፈው ዓመ ት ብቻ በፋሽን ኢንዱስትሪ ውስጥ አሉ የተባሉ ወደ 1500 ሰዎችን በአንድ ቦታ ማሰባሰብ ችሎ ነበር።


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

13

ጥበብ

ስት ሴት ጓደኛሞች ናቸ ው። አንዷ የለየላት “አራ ዳ” የምትባል አይነት ነች። ሁለተኛዋ አራዳዋ የምታደ ርጋችው ነገሮች ሁሉ አጋር ነች። ሶስተኛ ዋ ግን ሁለቱ በሚያደርጉት ሁሉ ብታካ ፈልም የሚሰሩት “ጥሩ እንዳይደለ” እን ደሆነ ታስባለች። ሶስቱ ወፎች ማለት እ ንግዲህ እነዚህ ናቸው። እንዲህ እንደዛሬው በሀገሪቱ ሌላ ነገር የሌለ እስኪመስል ድረስ አንድ የቴሌቪ ዥን ድራማ የወራት መነጋገሪያ ከመሆኑ በፊት ነበር “ሶስቱ ወፎች” የተሰራው። የ ቴሌቪዥን ድራማ አሰራርን ቀይረውታ ል የተባለላቸው “ገመና” እና “ሰው ለሰ ው” ከመምጣታቸውም በፊት ነበር ለዕ ይታ የበቃው። ሆኖም ዘወትር እሁድ ይ ቀርብ በነበረው የ“120” የቴሌቪዥን ፕ ሮግራም ላይ መታየት ሲጀመር ግን የወ ቅቱ ተወዳጅ ድራማ ሆኖ ነበር። ከተሰራ ከዓመታቶች በኋላ በተለያየ ጊዜ በታየበ ት ወቅትም በድራማ ተከታታዮች ዘንድ ተወዳጅነቱ አልደበዘዘም። ድራማው ተወዳጅነት ማትረፉን ተከት ሎ የተወደደባቸውን ምክንያቶች በወቅ ቱ በነበሩ ብዙሃን መገናኛዎች የዘረዘሩ ነ በሩ። የመጀመሪያው ምክንያት ተደርጎ የ ተወሰደው መንግስታዊው እና ብቸኛው የቴሌቪዥን ጣቢያ ለድራማው የመደበ ው ገንዘብ ነበር። የኢትዮጵያ ቴሌቪዥ ን ለድራማ መስሪያ ይመድብ ከነበረው በብዙ እጥፍ በላቀ ለዚህ ድራማ ገንዘብ እንዳፈሰሰ ተዘግቧል። በድራማዎች ላ ይ ባልተመለደ መልኩም በ“ሶስቱ ወፎ ች” የእያንዳንዱ ክፍል ማለቂያ ላይ የአካ ውንታንት ስም ከተዋንያን እና አዘጋጆች ዝርዝር ቀጥሎ ይነበብ ነበር። ለድራማው ተወዳጅነት በሁለተኛ ምክ ንያት የሚጠቀሰው ድራማው ይዞት የተ ነሳው ጭብጥ በፊት ከነበሩት ለየት ያለ መሆኑ እና ቀረጻው በተለያዩ ቦታዎች ቀ ን እና ማታ ሳይመርጥ የተከናወነ መሆ ኑ ነበር። ሶስተኛውና ብዙዎችን የሚያስ ማማው ምክንያት ግን የተዋናዮቹ የትወ ና ብቃት ነበር። የድራማው መሪ ተዋንያ ኖች ሶስት እንስቶች ቢሆንም ቹቹ የተሰ ኘችውን የ“አራዳ ገጸ ባህርይ” ወክላ የተ ጫወተችው ላምሮት ገብረሰንበት ይበል ጥ እውቅና አግኝታበታለች።

ቹቹ “እንዲህ ይሆናል ብዬ አይደለም የሰራ ሁት” ትላለች ላምሮት ከድራማው ቀረጻ በፊት ስለነበራት ስሜት ስታስታውስ። ከዚህ ቀደም የቴሌቪዥን ድራማ ሰርታ የማታውቀው ላምሮት በልምምድ ወቅ ት ለ“ሶስቱ ወፎች” የነበራት ስሜት እም ብዛም ነበር። “ትያትር (ድራማ) ልምም ድ ላይ እንደምታስበው አይደለም። ስት ዋሃድ ነው ስሜት የሚመጣልህ” ትላለ ች። ስድስት ወር በፈጀው ልምምድ ያል ታየው መዋሃድ በአንድ ወሩ የድራማ ቀ ረጻ ወቅት መጣ። ቀረጻው ሲጀመር ላምሮት ሌላ ሰው ሆ ነች። የተሰጠቻትን ደፋር፣ አታላይ እና አጭበርባሪ ገጸ ባህርይ በአሳማኝ ሁኔታ ተጫወተቻት። ገጸ ባህሪዋን በብዙዎች ልቦና ውስጥ እንድትቀር አደረገች። እስ ካሁንም ድረስ ሰዎች ሲያገኟት በገጸ ባህ ሪይዋ ስም ቹቹ እያሉ መጥራታቸው ም ስክር ይሆናል። ላምሮትን ቹቹን በቃለ ተውኔቱ እንደተጻፈችው አድርጋ ለማም ጣት ብዙ ደክማለች። የድራማው ዳይሬ ክተር የሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥኑ ተ ስፋዬ ስንቄም አስተዋጽኦው ከፍተኛ ነ ው። “ቤትሽ ገብተሽ በመስታወት ራስሽ ን እያየሽ ስሪው ይለኝ ነበር” ትላለች ተስ ፋዬ እንዴት ገጸ ባህሪዋን በትክክል እን ድታመጣ እንደረዳት ስትናገር። ላምሮት “ሶስቱ ወፎች” ተወዳጅ እንደ ሚሆን ያወቅሁት “ቀረጻ ላይ እያለን” ነበ ር ትላለች። “ቀረጻ ላይ እያለን ፕሮዳክሽ ኑ የተሳካ እንደሆነ ገባኝ። እነርሱም ሲቀ ረጽ ደስተኞች ነበሩ” ትላለች ከቀረጻው ጀርባ የነበሩትን ባለሙያዎች ስታስታው ስ። ድራማው የተሰራው በኢትዮጵያ ቴ

ብዙዎች የሚያውቋት “ሶስቱ ወፎች” በተሰኘው ተከታታይ የቴሌቪዥን ድራማ ነው። ይህንን ድራማ ከመጫወቷ በፊት ግን “የልደት ጧፍ” በተሰኘ ተከታታይ ድራማ መሪ ተዋናይ ሆና በሬድዬ አድማጮች ዘንድ አድናቆትን አትርፋለች። በትወና መነሻዋም ቢሆን በወቅቱ አነጋጋሪ በሆኑ ትያትሮች ላይ ዋና ገጸባህሪ ወክላ በመጫወት የጥበብ አፍቃሪያን ልብ የገባች ነች። ይህቺ ተዋናይት ላምሮት ገብረሰንበት ትባላለች። በቅርቡ በምትሰናበታት ካምፓላ ላይ ለሁለት ዓመት ግድም ቆይታለች። የ“ሐበሻዊ ቃናው” ተስፋለም ወልደየስ ስለስራዎቿ እና የትወና ህይወቷ አነጋግሯት ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

ፎቶዎች- ተስፋለም ወልደየስ

የ“3ቱ ወፎች” ኮከብ በካምፓላ ሌቪዥን አማካኝነት እንደመሆኑ ባለሙ ያዎቹ በሙሉ የመጡትም ከዚያው ነበ ር። ብዙዎቹ ታዲያ ወደ ቴሌቪዥን ጣ ቢያው ከመምጣታቸው በፊት ባለ 35 ሚሊ ሜትር ጭምር ፊልሞችን ይሰራ በ ነበረው የቀድሞው የኢትዮጵያ ፊልም ኮ ርፖሬሽን ሰራተኞች ነበሩ። ይህም ድራ ማው የፊልም ዓይነት ገጽታ እንዲላበስ አድርጎታል። “አሁን እንደምናያቸው ፊ ልሞች እንደ ፊልም ተቀርጾ ገበያ ላይ ቢ ውል ኖሮ በወቅቱ ትልቅ ገቢ ይኖረው ነበር” ስትል ላምሮትም ምስክርነቷን ት ሰጣለች።

የአጋጣሚዎች ብዛት ላምሮት “ከብዙ ስራዎቼ የገነነ ስለነበር እስካሁንም ይዞኝ ቆይቷል” የምትልለት ን “ሶስቱ ወፎችን” እንድትሰራ የተመረ ጠችው በአጋጣሚ ነበር። ያን ጊዜ ሀገ ር በቀል በሆነው “ፕሮ ፕራይድ” በተሰ ኘ መንግስታዊ ባልሆነ ድርጅት ውስጥ መደበኛ ሰራተኛ ነበረች። በዚሁ ድርጅ ት ውስጥ ባለው “የባህል ማዕከል” አብ ራት ድራማዎችን የምትሰራው ሶፊያ መ ሐመድ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሰዎች ጋ ር ትግባባ ነበርና ዳይሬክተር ተስፋዬ ሊ ሰራ ላሰበው ድራማ ዋና ተዋናይ ሲፈል ግ ትሰማለች። ወደ ሶፊያም ይመጣና “የ ምታውቂው ሰው ካለ ይዘሽ ነይ”ይላታ ል። ሶፊያ ላምሮትን ይዛ ወደ ኢቲቪ ት ሄዳለች። ተስፋዬ ይመለከታት እና ለስራ ው ትመረጣለች። ይህ በአጋጣሚ ተመ ርጦ ዋና ተዋናይ የመሆን ነገር በላምሮት ላይ ተደጋግሞ ተከስቷል። በትያትር መ ድረክም ሆነ በሬድዬ ያሳወቋት ስራዎች ን የሰራችው እንዲሁ በአጋጣሚ ነው። “የልደት ጧፍ” የተሰኘውን ተከታታይ የሬድዬ ድራማ እንድትሰራ የሆነው በጓ ደኞቿ ጠቋሚነት ነበር። የድራማው ደራ ሲ የ“ቀን ቅኝት” የተሰኘውን ረጅም የሬ ድዬ ድራማ ከጻፉት ሶስት ደራሲያን መ ካከል አንዱ የሆነው መስፍን ጌታቸው ነ ው። ሴተኛ አዳሪ የሆነችውን ዋና ገጸ ባ

ህሪይ በሚፈልግበት ወቅት ጓደኞቹ ላም ሮትን ያመጡለታል። የድራማው መቼ ት የሚካሄድበትን ቦታ እንኳ የማታው ቀው ላምሮት “ትሰራው” ይባልና ቃለ ተ ውኔቱ ይሰጣታል። መስፍን ላምሮት ድ ራማውን እርሱ እንደሚፈልገው ትጫወ ተው እንደሆነ ጥርጣሬ ገብቶታል። ዝግ ጅቱ አልቆ፣ ድራማው ተቀርጾ፣ በእሁድ ጠዋት የመዝናኛ ፕሮግራም አማካኝነት አየር ላይ ዋለ። ምላሹ ደግሞ ያልተጠበ ቀ እና አስገራሚ ነበር። ድራማው የአንዲት ሴተኛ አዳሪን ህይ ወት የሚያሳይ ሲሆን የዩኒቨርስቲ ተማሪ የሆነች ጓደኛዋ ህይወት እንዳይበላሽ ስለ መትከፍላቸው መስዋዕትነቶች የሚተር ክ ነው። የድራማው መቼት ደግሞ ሐረ

ር አቅራቢያ የምትገኝ ትንሽ ከተማ ነች። ጉርሱም ትባላለች። ላምሮት ድራማውን ስትስራ ያንን ቦታ አታውቀውም። እስካ ሁንም ድረስ አላየችውም። “ፍላጎት ካለ ህ ቦታውን ትሰለዋለህ። ስለ ጎርሱም ሳስ ብ ጭል ጭል የሚል ወንዝ ለራሴ ይታ የኛል”ትላለች በምናብ ርቃ ሄዳ። “በት ያትር ስራዬ ብዙ ክፍለ ሀገር ሄጃለሁ። እስከድሬዳዋ ድረስ ሁሉ። እንደ እድል ሆኖ ግን ሐረር (ጉርሱምን) አላየሁም።”

ራስን መፍጠር እንደ “ሶስቱ ወፎች” እና የ“ልደት ጧ ፍ” ሁሉ “ድሃ አደግ” የተሰኘውን ትያት ር እንድትሰራ የተመረጠችውም በአጋጣ ሚ ነው። ላምሮት “ራሴን የፈጠርኩበት” እያለች የምትጠራው “ድሃ አደግ” መጀ

በአጋጣሚ ተመርጦ ዋና ተዋናይ የመሆን ነገር በላምሮት ላይ ተደጋግሞ ተከስቷል

መሪያ ወደ መድረክ የመጣችበት ነበር። ትያትሩን እንድትሰራ የተመረጠችው በአ ዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ባህል ማዕከል “ል ምምድ” ላድርግ ብላ በገባችበት ወቅት ነ በር። እናቷ ዩኒቨርስቲ ይሰሩ ነበርና በባ ህል ማዕከል ውስጥ የሚሰሩ ጓደኛቸው ን ጠይቃ በምርቃት ወቅት የሚዘመረው ን “እንኳን ደስ ያላችሁ” የሚለውን ዘፈ ን መለማመድ ተጀምራለች። ይሄኔ ጸሀፌ ተውኔት እና ገጣሚ አያልነህ ሙላት የባ ህል ማዕከሉ ዳይሬክተር ሆነው ተሾመ ው ይመጣሉ። አቶ አያልነህ እጃቸው ላይ ያለቀ ትያት ር ነበር። “ድሃ አደግ”። በባህል ማዕከሉ ለሚሰሩት “ልጅ የሆነች፣ የ17 ዓመት ካ ራክተር የምትሸፍን እፈልጋለሁ” ይሏቸ ዋል። ከላምሮት ጋር አብረው መዝሙር የሚያጠኑት እርሷን ይጠቁማሉ። የወቅ ቱ “ትኩሳት” የነበረውን የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጉዳይ ለሚዳስሰው ትያትር ዋ ና ተዋናይ ሆና ትመረጣለች። “ያኔ ትያ ትር ሰርቼ የማላወቅ “ሀ”ን ከ “ለ” የማላ ገናኝ ነበርኩ።” ትያትሩ መታየት እንደጀመረ አቶ አያ ልነህ ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ ይደረጋ ል። ጸሀፌ ተውኔቱ ከዩኒቨርስቲው ቢወ ጡም “ድሃ አደግ”ን በግላቸው መስራት ቀጠሉ። ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ በባህ ል ማዕከል ይሰሩ የነበሩትን ወጣት ተዋ ንያን ሰብስቦ ቀንዲል ቤተ ተውኔትን አ ቋቋሙ። በዚሁ ቤተ ተውኔት ስር ሆና ውርስ ትርጉም በሆነው “ጥበበኛዋ ጋለ ሞታ” ላይ እና “ከድጃ” ላይ ተጫውታ ለች። “ፕሮ ፕራይድ” እየሰራች ያጠናች ው የአቶ አያልነህ ሌላ ፖለቲካ ቀመስ ት ያትርም ነበር። “ሾተላይ” ይሰኛል። “የአ ቶ አያልነህ ትያትሮች ፖለቲካ አያጡም። ዳሰስ እያደረገ ነው የሚያልፈው” ትላለ ች። ላምሮት “ሾተላይ” ላይ አልተወነች ም። ዘነበች ታደሰ (ጭራ ቀረሽ) እንድ ትሰራው ሲደረግ “ላለመሻማት” በሚል ተወችው።

ከዚህ በኋላ ከመድረክ ትያትሮች ራቀ ች። ሆኖም ከጥበቡ አለም አልወጣች ም። ለሰባት ዓመታት ያህል በ“ፕሮፕራ ይድ” የባህል ማዕከል በሚዘጋጁ ድራማ ዎች ላይ ስትሰራ ቆይታለች። “ብዙ ስ ፖንሰሮች ስለነበሩን በየክፍላተ ሀገሩ ሁ ሉ እየሄድን ህብረተሰቡን በድራማ እ ናስተማር ነበር” ትላለች። “ፕሮ ፕራይ ድ” በኤፍ ኤም ሬድዬ ያስተላልፈው በ ነበረው “ይበቃል” በተሰኘ ፕሮግራም ላ ይም አጫጭር የሬድዬ ድራማዎች ትሰ ራ ነበር።

“ህይወት ለየቅል ነው” “ፕሮ ፕራይድ” እየሰራች በጎን ትምህር ቷንም ትማር ነበር። ማርኬቲንግ ለመማ ር በገባችበት ዩኒቲ ኮሌጅ ሶስት ዓመት ከተማረች በኋላ ወደ እንግሊዝ የምትሄ ድበት ዕድል ስላገኘች አቋረጠችው። ለን ደን ከሚገኙ ቤተሰቦቿ ጋር ለሶስት ዓመ ት ያህል ብትቆይም እንግሊዝ ብዙም አ ልተመቻትም። ወደ አዲስ አበባ ተመለሰ ች። ባለቤቷ ወደ ኡጋንዳ ካምፓላ ለስራ ጉዳይ ሲመጣ ሸገር እንደገና ደህና ሰንብ ች አለች። የልጅ እናት ለመሆን ቀናት እ የቆጠረች የምትገኘው ላምሮት ወንድ ይ ሁን ሴት ገና አላወቀችም። “እሱ ያመጣ ውን…” ባይ ነች። ወደ ካምፓላ የመጣች ሰሞን ወደ ትም ህርቱ አለም መግባት ፈልጋ የነበረ ቢሆ ንም በባለቤቷ የስራ ጸባይ ምክንያት ተረ ጋግታ ተቀምጣ መማር እንዳልቻለች ት ናገራለች። “የባለቤቴ ስራ አንድ ቦታ ላ ይ አይደለም። የተለያየ ቦታዎች ያስኬደ ዋል። በቅርቡ ኬንያ እንሄዳለን። አንድ ነ ገር ለመስራት፤ አንድ ቦታ ላይ መርጋት አለብህ” ትላለች። ከእናትነት በኋላ ወደ ጥበብ ትመለስ እ ንደሆን ስትጠየቅ “ከጥበብ ጋር መለያየ ት አልፈልግም” ስትል ትመልሳለች። ግ ን ደግሞ “ሌላም ስራ መጨመር እፈልጋ ለሁ” ስትል ምናልባት ወደ ንግድ አለም ልትገባ እንደምትችል ጥቆማ ትሰጣለች።


ሐበሻዊ ቃና

14

ትረካ

ላንድ እንደገባሁ በሁለተኛ ወሬ የቋንቋ ትምህር ት ጀመርኩ። የ ኢኮኖሚ ችግር አልነበረብንም። እኔና መቅደስ እየተላ መድን ወደ ድሮው ፍቅራችን ተመለስ ን። ደንሀግ መልካም ከተማ ናት። አን ዳንዱ እዚህ የማየው ሀበሻ ከሰፈሬ ት ቼው የመጣሁት ልጅ እየመሰለኝ ሆዴ እየተረበሸ ሰላምታ እሰጣለሁ። ሁሉን ወደ ቤቴ እንዲመጣ እጋብዛለሁ። ስል ክ እለወዋወጣለሁ። አምስተርዳም ድ ረስ እየሄድኩ ወደ ኢትዮጵያ ማሕበር ጎራ እያልኩ፣ በኢትዮጵያ ስለሚሆነው ነገር ለመስማት እሞክራለሁ። የምበሳጨው ቴሌቪዥን ሳይ ነው። ቋንቋው ገና ባይገባኝም መቅደስ እየ ተረጎመችልኝ እከታተላለሁ። አንዳን ዱ ፕሮግራም ወደ ስድብ የተጠጋ ነ ው። ኢትዮጵያን የሚመለከት ፕሮግ ራም ከተላለፈ፣ የሚተላለፈው ስለኢ ትዮጵያ ድህነት ነው። የሚደግፉትን መንግስት እንኳን አይምሩም። ሁልጊ ዜ የሚራብ አበሻ አያለሁ። ቀስ ብዬ ቲ ቪ ከማየት ወደ አለማየት ዞርኩ። አን ዳንዴም ኢትዮጵያን በጣም ከመውደ ዳቸው የተነሳ ሊረዷት ቆርጠው የተነ ሱ ይመስላል። ከስራ መባረሬን አልሰ ሙም? ልመና ልወድቅ ትንሽ እንደቀ ረኝ አልሰሙም? ኋላ ግራ ይገባኝ ጀመር። በየቦታው የሚሰበስቡን ሺህ ዓይነት የሀበሻ ፖለቲከኞች ጥያቄውን ኢትዮ ጵያን ሰበብ እንጂ ማዕከል አድርገው አንስተዋት አያውቁም። ማለት ስለኢ ትዮጵያ ያወራሉ ግን በልባቸው ያለው በማን እንደሚተዳደር የማይታወቅ ድ ርጅታቸው ነው። ሁሉም ‘እኔ አሪፍ ነ ኝ’ ሲሉ እሰማለሁ፣ ግን ለምን እንዲ ያ እንደሚሉ አልገባኝ አለ። በዕድሜ ዬ ማነስ ያልሰረስኩባቸው ድሮ የማደ ንቃቸው ፖለቲከኞች አስገረሙኝ። አ ንዳንዴ ምናልባት ልፎአቸው በስነስር ዓት መሬት ተቀብሮ ዛፍ ስላልተተከለ በት ነው ብዬ ለራሴ ነግሬው እስቃለ ሁ። አሾፍባችው ጀመርኩ። ለስብሰባ የምሄደው አንዳንድ በቅርብ ያወቅሁ ዋቸውን ሰዎች ለማግኘትና ለማውራ ት ብቻ ነበር። ከሰው ጋር በተገናኘሁ ቁጥር ግን ‘ይኼ ሰው ማነው?’ የሚባ ል ጥያቄ ተነሳ መሰል። አለነገር ያ ሰው አለምዘውድ የሚባል፣ ሄልቨርሱም የ ተባለ ከተማ የሚኖረው፣ የሆነ የፖለ ቲካ ድርጅት አባል እንዲህ አላለኝም፡ “ማነህ አንተ ለመሆኑ?” የፍልስፍና ጥያቄ አልነበረም። “ስወለድ እነዚህ ሁሉ ድርጅቶች አል ነበሩም። ለአንድ አገርና ለአንድ ችግር ይሄ ሁሉ ፓርቲ ምን ያስፈልጋል?” አ ልኩት። በየዋሕነት ነበር እንዲህ ያል ኩት። አዲስአባ ድራፍት እየለጠጡ የ ሚተዋወቁት ሰው አካባቢ መንጌን እ ንደ መተረብ ቀላል መስሎኝ ነበር። እ ንዲህ ማለቴ ቀላል ሀሳብ መስሎኝ ነበ ር። የመሃይም ነገር። መቅደስ ላይ የሚነዛው አሉባልታ የ መጣው ይሄን ከተናገርኩ በኋላ ነው። ምናልባት ሲወራ ኖሮ ወደ እኔ የመጣ ልኝ። ደሞም እላለሁ። ስለ እኔ የሚያ ወሩት ነገር መጥፎ ነገር ስላጡ መቅደ ስን መውረር የጀመሩ። * * * አንድ ቀን አምስተርዳም የእንቁጣጣ ሽን በዓል ምክንያት በማድረግ የመዝ ናኛ ፓርቲ ተደርጎ፣ ከሶስት ከማውቃ ቸው ልጆች (አንዱን አዲስአባ አውቀ ዋለሁ) ጋር ቆመን ቢራ እየጠጣን በሞ ቅታ መሃል (ወይስ ይሄ ማሳሰቢያ ሊ ሆን እንጃ) አንዱ፡ “መቅደስ ደህና ናት?” አለኝ። ደህና መሆኗን እንደነገርኩት “አንተ ባህሬይን ነበረች እንዴ?” “እንጃ አይመስለኝም”

“እርግጠኛ አይደለህም? እንዴት አታ ውቅም?” ሌላው ቀጠለ። ተማክረው ይ መስላል። አለማወቄ አላሳፈረኝም። አረብ አረብ ነው ለእኔ። “ባህሬይን የአገራችንን ሴቶች የሚሰሯ ቸው ተንኮል የሚደርስባቸው ጣጣ” ከዚህ በላይ አልሄዱም። የማውቀው አ ጠቃላይ ነገር ተወራ። የሰማሁትን ደግ ሜ መስማቱ ጥቅም አልታየኝም። እነሱ ም የጀመሩትን ወሬ ያቋረጡት ምንም እ ንዳልተሰማኝ ገምተው መሰለኝ። ከወር ምናምን በኋላ አንድ ሰው ታሞ ልጠይቅ ደንሀግ ሆስፒታል ስሄድ ነው ዝርዝሩ እንዲገባኝ ያህል ሰፋ ተደርጎ በ አሽሙር የተነገረኝ። በሽተኛው እዚህ ነው። በጀርባው ተን ጋሎ ያምጣል፣ እና ከአገሩ ተደብቆ የመ ጣ ተስቦ ተከስቶበት ያመዋል። እኔ በግ ራ በኩል ጤንነቱን ጠይቄ ወደ ቤቴ ለ መሄድ አኮበኩቤአለሁ። ታች በግርጌ በ ኩል ሁለት ሰዎች ወንበር ስበው ተቀም ጠዋል። “ኸረ ባክህ?” አለ አንዱ ድምጹን ከፍ አድርጎ “እዛ ነበረች” “አረብ ኤሚሬትስ ሴተኛ አዳሪ ምናም ን ነበረች?” ከዛ ቀና ብለው አዩኝና እንደፈሩኝ፣ ል ክ ለስእኔ ሃፍረት ያወሩ እንደነበሩ ሁ ሉ፣ እና እንዳልቃወማቸው የፈሩ ዓይነ ት አስመስለው ተያይተው በፍጥነት ዝ ም አሉ። ልናገር አልናገር እያልኩ ሳመነታ በሽተ ኛው በድንገት ዳነ መሰለኝ፡ “አንተ ባለ ቤትህ መቅደስ አቅለያስን ታውቃት ይ ሆን?” አለ “ማን ናት አቅለያስ?” አልኩ “እንዴት አታውቃትም?” አለ አንዱ ማለቴ መቅደስ ባህሬይን ሴተኛ አዳሪ እንደነበረች እንድጠራጠርላቸው ነበር? እኔን በኢትዮጵያዊነቴ ከመውደድ ይል ቅ ለፖለቲካ ድርጅቱ ስላቃጠርኩ ሲያ ጣጥለኝ ነው? በየስብሰባው አሰልቺ ጥ ሩንባቸው ‘መንግስት እህቶቻችንን ወደ ዓረብ አገር እየሰደደ አስጠቃቸው’ ይላ ሉ። ለመንግስቱ ሐይለማርያም ጊዜ ‘ጁ ንታው የመጓጓዝ ነጻነት ዜጋውን ነፈገ’ ሲሉ የነበሩ ይሆናሉ። የመዘባረቅ ከያኒ ያን። የተበወዙ። በማን አፍ እንደሚናገ ሩ አልገባኝም። በአንድ ራስ አስራ ሰባ ት ምላስ። የመቅደስ ውርደት የእሱ ው ርደት አይደለም? በየመግለጫቸው ስለ እህቶቻችን እዬዬ ይሉና፣ እዚህ ቂጣች ን ስር መውደቃቸውን መንግስት ማብ ሸቂያ ሊያደርጉት ይለፋሉ። ደቻሳ ምን አለ?ምን አለ ያ የአራተኛ ክፍለጦር ሰካ ራም? ኢልም ሃጠራው። እዚህ አንዱ የ ምወዳት ሚስቴ እንድትቀፈኝ ይለፋል። ምናልባትም እኔ ከመምጣቴ በፊት በዚ ህ ድክመቷ እያስፈራራ አውጥቷት ይሆ ናል። ብዙ አሰብኩ። መናገር አልቻልኩ ም። ብዙ ብዙ አይነት እርግማን ነገር አ እምሮዬን ደፈነው። እንዲህ የመሳሰለ፡ ‘እዚህ አልጋህ ላይ በበሽታው ተጣብ ቀህ ቅር’ ‘እናንተ ያልረባ ፖለቲከኛ ሆናችሁ አር ጅታችሁ ሙቱ’ ‘ቀድሞ የሸረሞጠ፣ ሚስቴን ሸርሙጣ ያለ የበሰበሰ ተልካሻ’ ‘ጥሩንባ ሁሉ’ መከራከሪያ ፍልስፍና ሳይሆን በአእም ሮዬ አስፋልቶች ላይ የሚመላለሰው የስ ድብ ዚታዎ ነበር። ስድብን በስድብ መ ቃወም ደንብ አይደለም? አንገቴን ደፍ ቼ እቆምኩበት በቁጭት ወለል በእግሬ እየመታሁ ዓመታት ለመሰሉ ደቂቃዎች ያህል ቆምኩ። ቀና ብዬ ሳያቸው በእርግ ጥ ሊያሳምሙኝ እንደፈለጉ ገባኝ። ታላ ቅ ዕውቀትም አገኘሁ። ማታ ቤት እንደገባሁ መቅደስ ወደ ተኛ ችበት ሄጄ የሆንኩትን ነገርኳት። “አቅለስያን አውቃታለሁ” አለችኝ “ለምን ባህሬይን እንደነበርሽ አልነገር

* ልፎ በአዳም ረታ (ክፍል ሁለት)

ሽኝም?” “ምን ያደርግልሃል? ብነግርህ ባልነግር ህ ምን ትለውጣለህ? ባልሄድስ ኖሮ? ም ኑ ደስ የሚል ነገር አለው? ላስታውሰው ም አልፈልግም” “ምን አለበት ብትነግሪኝ?” “ምነው ያለጸባይህ ምርመራ አደረግህ ብኝ?” “እንዴት ያለ ጸባይህ?” “ቸልተኛ ነበርክ፣ ወሬ አትወድም ነበ ር” “እወዳለሁ፤ ግድ የለም” “ደስ አይልም በእግዚአብሔር” “ንገሪኝ። ሰው ስላሽሟጠጠኝ ነው” “ሰው? መጣባት እንደፈራችው? እሷ ክ ሮኒንገን አይደለ ያለችው?” “ምን መጣባት?” “ምን አወሩህ?” “አላወሩኝም። አሽሟጠጡኝ” “የዞረበት ሕዝብ እኮ ነው። ፍቅር ልታ መጣ ሄደህ ደበሩህ” አለችና ሳቀች “ስለ አንቺ” “ምን?” “ስለ አንቺ። ስለ እኔ ምን ያውቃሉ? ቢ ያሙኝ ጠጪ ዱርዬ ነበር ነው፣ ካልፈ ጠሩ” “ምን አሉህ?” “አንቺ ንገሪኝ” “ይደብረኛል ልረሳው እፈልጋለሁ። በ እናትህ” “ሴተኛ አዳሪ ነበርሽ አሉ” “ምን”አለች ከተጋደመችበት ቀና ብላ። “በቀጥታ አላሉኝም። አቅለስያ ስለም ትባል ልጅ አንስተው……ሴተኛ ኣሪ እ ንደነበረች…….ከዛ በሆነ አስተያየት አዩ ኝ……አለ አይደለ ሚስትህም ነበረች ለ ማለት…….” “ጉድ! ገረድ ነበርኩ። በቃ” “ሸርሙጣን ከየት አመጡት?” “ቃሉ እኮ በየቦታው አለ። አንዱ ጋ መ ለጠፍ ነው። እኔ ገረድ መሆኔ እስከዛሬ ቁስል ነው። በአገሬ አነጅቤ መማር ስች ል ዕድሌን ሁሉ አበላሽቼ……ለአረብ ገረ ድ መሆን ቀላል አይደለም። አረብ ፈረ ንጅ አይደለም። ብዙ አለ። ተወኝ። እኔ ነኝ የኖርኩት። እዚህ ሆላንድ ሰላም አገ ር ተቀምጠው ይነጅሱናል። ምን ፈለጉ? ከሰው መግጠም የማልፈልገው ለዚህ ነ ው። በመጀመሪያ ቆንጆም አይደለሁም ለሸርሙጣነት ማን ይፈልገኛል። ሂሂሂ። ሁለተኛ ለተሻለ ኑሮ ነው ከአገሬ የወጣ ሁት። ግን ባርነት አጋጠመኝ። ተምረና ል ተሻሽለናል ብለው፣ ውድ ውድ መኪ ና ይነዳሉ ግን ይገርማል፣ አንጎላቸው ገ ና ነው። ለመጀመሪያ የእቃ ስልጣኔና የ መንፈስ ስልጣኔ እንደሚለያይ የገባኝ አ ረብ አገር ነው። ያገሬ ልጅ ዝተት ለብሶ አልደፈረኝም። በአፍ ብለከፍ፣ መልሼ የ ምለክፈው የምስድበው ያገሬ ወንድ ናፈ ቀኝ። ወንድ መስደብ ናፈቀኝ። ከወንድ መሰዳደብ ናፈቀኝ። አንዳንዴ 12 ጂ ይና ፍቀኛል። የማታ ሽፍት። ጥቁር አንበሳ ፣ መንገድ እያቋረጥን ከክላስሜቴ ወንዶች ጋር ስሰዳደብ። ሌላ ነገር ሳይሆን በቃ አ ፋቸውና ተረባቸው ናፈቀኝ። አረብ አገ ር አንዲህ አይታሰብም። አንገትህን ደፍ ተህ ነው። ስንት ልጆች ራሳቸውን እን

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ደገደሉ ታውቃለህ? ቤት ይቁጠረው ል በልህ። እንዳንሰማ አድርገው ስለሚቆጥ ሩት ነው እንጂ ይደፈራሉ። አልለመድ ንም። ተድፍሬ አላውቅም አገሬ። የአበ ሻ ሴቶች ለሚያውቃቸው ሂያጅ ናቸው ግን መደፈር አይወዱም። ደግ ወንድ አ ቀራረብ ሳይገባው ቢደፍር ይቅር ይባላ ል። በጥላቻ አይደለም። እኛ አገር ያለ ው መድፈር ያ ነው። የሚንቀኝ የሚጠ ላኝ ሲደፍረኝ እሱ ሌላ ነው” አለችና አ ተኩራ በዝምታ አየችኝ። ‘ተደፍሬአለሁ’ ልትል መሰለኝ። “ሸርሙጣ አልነበርኩም። እመነኝ። ተ ገርጄአለሁ። ገርድ መሆኔ ሳይሆን አብ ሮት መአት መከራ ይመጣል። ምን ብ ዬ ልንገርህ?” በሃዘን ቀና ብላ አየችኝ። ልቤ ላይ ውጋት ተሰማኝ። የእውነት። የአራዳ ልጅ ነኝና ተንኮል የሰራሁባቸው ጊዜያት ነበሩ። የሰው ሕልውና ግን አጥ ቁሬ አላውቅም። አላስፎግርም። ከማብ ሸቅ አያልፍም። እኔም ጓደኞቼም ‘ደባሪ’ መባልን እንጠላ ነበር። ከተቀመጥኩበት ተነሳሁና ለማሰብ ሞከርኩ። ይሄ ግድግ ዳ ነበር። ለማሰብ እንቅፋቶች መነሳት አ ለባቸው። ይሄ እንቅፋት ነው። የስደት ስነ ልቡና የት ጋ እንደሚጠመዘዝ አላ ውቅም። ሰንጋ ተራ የማውቀው አራዳ የ መሰለኝ የእኔ ቢጤ ጠጪ ድንገት ‘ኢ-አ ራዳ’ ይሆናል ብዬ አልጠበቅሁም። መቅ ደስ እንዳልዋሸችኝ ይገባኛል። ምክንያቱ ም አይኖቿ ውስጥ ሳትደፈር እንዳልቀረ ች ነገሩን ተናግራ ካሳየችኝ እንግዳ ትኩረ ት መገንዘብ አልከበደኝም። ይሄ ነገር ለ እኔ ውርደት መሰለኝ። የውርደቱ ጽንሰ ሀሳብ የመጣው ባልገባኝ ምክንያት ከው ስጤ ኃላፊነቱ የእኔ ስለመሰለኝ ነው። ለ ምን እንደሆነ አለማወቄ ደሞ የባሰ ረበሸ ኝ። ማሰብ አለመቻሌ። ሲጋራ ጠማኝ። ልክ እንደ ውሃ። “አመንከኝ” “አዎ” “እውነቱ ይሄ ነው” “ለምን ይሄን አለኝ? ለምን ዝም አልኩ ት?” “ምን ልታደርገው? ምን ልትል?” “ምን እለዋለሁ?” “እንዲህ አድነው ሊያሳፍሩህ ሲፈልጉ ለምን ይመስልሃል?” “እሱ እኮ ነው። እሱን እያሰብኩ ነው። ለምን ወደ እኔ አመጡት?” “ስራ ሊያስፈቱህ ነዋ። ስንት ዓመቱ ነ ው ሆላንድ ሲኖር። በዳች ቋንቋ የልጆ ች ፕሮግራም በቲቪ ማየት እንኳን አይ ችልም። አይገባውም። ቀንቶ ነው። አር ፈህ መቀመጥህ ሊያበሳጨውና ሊቀና ይችላል። የተለየ ፖለቲካ ያስብ ይሆና ል። የማይፈልጉትን ሃሳብ እየዞርክ እን ዳታወራ ስም በማጥፋት ያገሉሃል። ሌ ላ ምንድነው ታዲያ። ፈሪዎች ናቸው። ናቃቸው።” አልጋ ላይ እንደተቀመጠች ትቼአት በ ረንዳ ላይ ወጣሁ። ቀዝቃዛው ማታ ው ስጥ የፖታት (በዘይት የተጠበሰ ድንች) ጠረን አለ። ግራና ቀኝ ጀርባዬ ላይ ሁ ለት እጆቿን አስቀመጠች። ገና ያልወረ ደ እርግዝናዋ ሲቀርበኝ ይሰማኛል። ል ክ ማታ አዲስአባ በቅሎ ቤት ከቤተሰቤ ስሰናበት የሆነውን ነገር ይመስላል። ጭ ንቀት ሲመጣ፤ ሰዓትና የአየር ጸባይ አይ ቶ መሰለኝ። የደንሀግ ሰማይ ላይ በብር ሃን የተተኮሰ ጉም ምናምን የመሰለ ቢ ጫ ውጋጋን አለ። ለስ ያለ አየር ከባህር ይመጣል። “ስልክ ተደወለ” አለችና ትታኝ ወደ ቤ ት ገባች። ዞር ብዬ ላቅፋት ነበር። ያሳሰበኝ እሷ የተናገረችው ነገር አልነበ ረም። ያሳሰበኝ በዚህ የጣጣ ካርታ መሃ ል የሚፈሰው ስም ያልተሰጠው አንዱ ወንዝ። አንዳንዴ ሲቸግረኝና ከአሁኑ ወ ጣ ገባ ጋር ስፋጠጥ መንግስት የነጠቀኝ ቸልተኛነት ይናፍቀኛል። ሲጋራ ለኮስኩ ና ባንኮኒ ተደግፌ ልረሳ እየሞከርኩ ቆ ምኩ። ከምኖርበት ሕንጻ ስር የማይታይ

ሰው የወረወረው የቸኮላታ ከረሜላ ል ባስ በነፋስ እየተገፋ፣ በለስላሳው አስ ፋልት ላይ ያልፋል። ብዙ ጊዜ ግን አረ ፍ ብሎ በጸጥታ እስኪጠረግ ነገን የሚ ጠብቅ ይመስላል። ባለጌ ሰው መሆን አለበት ንጹህ ደንግሀግ መሃል ቆሻሻ እ ንዲህ የሚጥል። በስልክ ስታወራ እሰማታለሁ። ምን እንደምትል ግን ግልጽ አይደለም። ይሄን አገር እወደዋለሁ። ግን ሰላም እ ንዳለገኝ የሚፈልግ ሰው አለ። ይሄ ማ ለት አሁን ሰላም አለኝ ማለት ነው። ስ ትስቅ እሰማታለሁ። ውበቷ የሚወጣ ው ስትስቅ ነበር። ሌላ ነገሯ ሳይሆን ስትስቅ ‘ደስ አትልም?’ ነበር የሚባለ ው። ይከፋኝ ነበር። ለምን ሌላ አልተ ባለችም? ለእሷ ቆንጆ መሆን አለመሆ ን አስቤ ሳይሆን በብዙ አቅጣጫ ያል ተሞካሸች ልጅ ገርል ፍሬንዴ በመሆ ኗ። ሰላም እንደነበረኝ የማውቀው ስ ለከፍ ነው? ‘ምቀኛ አታሳጣኝ’ ምናም ን የሚሉት ለዚህ ይሆን? ከአገር ውጭ ከአገሬ ጋር የምሆነው እንዲህ ነው? እ ነዚህ አገራቸውን የዕውነት የሚወዱ ናቸው? ስልክ ዘግታ መጣችና ከኋላዬ አቀፈ ችኝ። እንድትናገር እጠብቃታለሁ። አልተ ናገረችም። “ለምንድነው አንድ ሰው ሌላ ሰውን ለመደበር የሚነሳው?” “እግዜር ያውቃል። የተፈጥሮ ስጦ ታ? ልክ እንደ ድምጻዊ” “ቆንጆ ነኝ?” “ምን?” “ቆንጆ ነኝ ወይ? ያልሰማህ አትምሰ ል” “ሰምቼአለሁ። ምን አመጣው ብዬ ግ ራ ገብቶኝ ነው” “አሁን አንዷ ስትደውልልኝ ምን አለ ችኝ መሰለህ? ‘እከሌ ታች ዳውን ታው ን አይታሽ ‘ኢትዮጵያዊ ነች ወይ?’ ብ ላ አለች’ አለችኝ” “ምን ማለቷ ነው?” “‘ባርያ ነሽ ምናምን’ ልትለኝ ነዋ። ‘አ ትመስልም? ምናምን’ የሚሉት ነገር አ ላቸው” “አዲስአባ አላጋጠመሽም?” “እዚህ ግን ተስተካከልን። አይገርም ም? ይሄኔ እናቶቻቸውና አባቶቻቸው እኩለ ሌሊት የሚመስሉ ናቸው። እነ ዚህ ጥቃቅን ነገሮች ናቸው። ቢያንስ ለእኛ ጥቃቅን ነገሮች መሆን ነበረባቸ ው። አለ አይደለ” “በቃ አየሽ ለወሬ የሚሆን መልካም ነገር ጠፋ” “አንተስ?” “ምኑን?” “አልመለስክልኝም” ትንፋሿ ጀርባዬ ላይ ለአፍታ ጸጥ አ ለ። መልስ እየጠበቀች፡፡ ዞር ብዬ ግዙ ፍነቷን አቀፍኩት። አይኖቿ ጮልጯ ና ደካማ ናቸው። ትልቅ አፏ ላይ ሳም ኳት። የሚጣፍጥ ጠረን አለው። መል ሴን ትጠብቃለች። “ስትስቂ አንጀት ታርሺያለሽ” እጇን ከትከሻዬ ላይ አንስታ እንደመ ሽኮርመም አፏን ያዘች። “እውነት ነው? ይበቃኛል” “እውነት ነው” የእሷ እንዳልሆኑ ሁሉ ወንድ የሚመ ስሉ የቆረፈዱ ትንንሽ እጆቿን ለመጀ መሪያ ጊዜ ያየቻቸው አይነት ለአፍታ ስታጠናቸው ቆየችና በማፈር ቀና ብ ላ አየችኝ። እንዳልገባኝ ትቼአት ለመ ሄድ፡ “ሻይ ላፍላ?” አልኳት “ውሃ አምጣልኝ” “ልጁ እንዴት ነው። ብዙ ይፈራገጣ ል?” ፈገግ ብላ አየችኝ። ሚስቴ ናት። በማ ንም የማልለውጣት ሚስቴ ናት። ‘በ እናት አገርና በሚስት የለም ዋዛ’ ይላ

ወደ ገጽ 22 ዞሯል


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

15

መጽሐፍ

የአለቃ ለማ ትዝታ በደማሙ ብእረኛ “ተደርጎ ያውቃል ወይ እንግዳ ሥርዓት፣ እግር አዲስ አባ ልቡና መቄት።” አስገራሚ የልጅነት ቀዬ ናፍቆት፤ መናፈቅማ ሁ ሉም ይናፍቅ የለ ግን አንዳንድ ሰው ናፍቆቱን ሲ ጽፈውም ሲናገረውም ውበት አለው። “ተሰጥዎ ነው!” ይሉን ይኾን የግጥሙ ባለቤት አለቃ ለማ በትዝታቸው ውስጥ ስለ ቅኔ በምሳሌ እንደተናገ ሩት? “ዳቦው በሴትዮዋ ያምራል ይከፋል እንጂ፤ አንድ ስንዴ አደለም? ልባም ሴት ብትይዘው ያም ራል፤ ሰነፍ ሴት ብትይዘው ይጨማለቃል… ተሰ ጥዎ ነው፤ ከግዜሃር የተሰጠው ነው ዋናው…” የ መጽሐፈ ትዝታቸው መዝጊያ በኾነው የግዕዝ ቅ ኔም እንዲሁ አስገራሚ ናፍቆታቸውን ገልጸዋል። “አነ ወዝናም እንዘ ንጹሐን እምነውር ወእንዘ በ ቀል አልብነ አሮን እምበዊአ ቤቱ በከንቱ ከልዓነ። እስመ እመ ዐረግነ ላዕለ ወእመ ታሕተ ወረድነ ዘምስለ አቡነ አሮን ያስተሳልመነ አረጋዊ ኢተረከብነ ለነ” በራሳቸው አንደበት ቅኔው ሲተረጎምም እንዲሁ የሚያስደስት ለዛ አለው የአቡነ አሮን ገዳምን ዝ ና ለሚያውቅ ሰው፤ “እኔና ዝናብ ኸነውር ንጹሐን ስንሆን፤ ቂም በቀል ሳይኖርብ ን፤ አሮን ወደቤቱ ከመግባት በከንቱ ከለከለን። ወደላይ ብንወጣ ወደታችም ብንወርድ ካባታችን ካሮን ጋር የሚያስታርቀን ሽማግሌ አልተገኘልንምና።” አለቃ ለማ ስለ ልጅነት አገራቸው ታቦት ስለ አ ቡነ አሮን ገዳም ያለውን እምነት በገለጹበት ስፍ ራ “ይህ ያቡነ አሮን እንዲያ ው ዋሻ ነው። ውስ ጡ ነው የተጠረበ እንጂ፤ ላዩ ዋሻ ነው። አቡነ አ ሮን በእጃቸው ነው የጠረቡት። … ገደል ሲናድ የ ተቀደደው ቀዳዳ ኸመንበሩ አጠገብ ኸቅኔ ማኅ ሌቱ ላይ ነው ጣራው ላይ። ጠሐይ ብልጭ ሲ ል ብርሃኑ ገብቶ ወለል ይላል። ዝናብ ጠብ አ

የመጽሐፍ ዳሰሳ

መዝገቡ ኃይሉ- አዲስ ነገር ኦንላይን

ተራኪ፦ አለቃ ለማ ኃይሉ ጸሀፊ፦ መንግስቱ ለማ አሳታሚ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬስ የታተመበት ዓመት፦ 2003 ዓ.ም ይልም፣ ምን በረዶ ቢወርድ ጠብ አይልም።” ይ ህ እንግዲህ “ነገር ሲመጣ” አንዳንድ ቀን ከሚዘ ንበው ውጪ መኾኑ ነው። ነገር መጣ የሚባለው ም ረሀብ፣ ጦርነት፣ መቅሰፍት እና የመሳሰለው ሲመጣ ነው። አለቃ ለማ እንግዲህ ራሳቸውን በዚህ የአቡነ አ ሮን ዋሻ እንዳይገባ በተከለከለው ውኀ መስለው ታል። ያውም ንጹህ እና ነውር በሌለበት የዝናም ውኀ። እራሳቸውንም እንዲሁ ነውር የሌለባቸው እንደኾኑ ይናገራሉ “ቂም በቀል የሌለባቸው” ን ጹህ። ነገር ግን እንደዝናሙ ውኀ ሁሉ እርሳቸው ም ተመልሰው ያገራቸውን ታቦት ለመሳለም ወደ አጥቢያቸው መሔድ አልቻሉም፤ መቄትን እንደ ናፈቋት ቀርተዋል። ያውም “በከንቱ”! እንዲያው አወጣጣቸው እና አኪያሔዳቸው በ ልጅነታቸው አንድ አዋቂ ስለ እርሳቸው የተናገረ ውን ንግር በጣሙን ይመስላል። ስለ ቤተሰቡ ሁ ሉ መጻኢ እድል ፈንታ ሲተነብይ የነበረው እንግ ዳ ነብይ አለቃ ለማን ዘነጋቸው። በድጋሚ ከተለ መነ እና ተጨማሪ ስጦታን ከተቀበለ በኋላ ግን ሰ

ውየው ለመናገር የከበደውን ያንን ትንቢት ተነፈ ሰው ምሬት ከሚመስል ጭማሪ ጋር “ምን አድር ግ ትሉኛሉችሁ ወደ ፀሐይ መውጫ ብቻ ሲሔድ አየዋለሁ፤ የሚያርፍበትን አላወቅሁትም፤ ሲያር ፍ አይታየኝም። እንዲያው ክንፍ አውጥቶ እንዳ ሞራ ወደ ምሥራቅ ሲሄድ አየዋለሁ።” አለቃም ራ ሳቸው ይህን የመሰለ ህልም ደጋግመው እንዳዩ ይናገራሉ። ፍቺውንም ያወቁት ይመስላሉ፤ “አረ ርጌ አይደለም? አረርጌ ነው” በስተመጨረሻ መኖ ሪያቸው የነበረችዋን ሐረርጌን የሚያመለክት ትን ቢት እንደነበረ ያምናሉ። አለቃ ለማ የደራሲው መንግሥቱ ለማ አባት ና ቸው። ምናልባትም የመንግሥቱ አባት መኾናቸ ው ከሌሎች እሳቸውን መሰል ሊቃውንት በተለ የ ትዝታቸው በዚህ መልክ እንዲጻፍ ምክንያት ሰይኾን አልቀረም። ከእርሳቸውም በፊት ከእር ሳቸውም በኋላ እንዲህ ቃል በቃል የተጻፈ ታሪ ክ ያላቸው ኢትዮጵያውን ያሉ አይመስሉም። ም ሥጋና ለልጃቸው ለደማሙ ብእረኛ! የአዲስ አበ ባው ዩኒቨርሲቲ ፕሬስም የሦስት ምሁራንን መ

ግቢያ በመጨመር በድጋሚ እንዲታተም አድር ጎታል። ዩኒቨርስቲ ፕሬሱ እንዲህ አይነት ድንቅ መጽሐፎችን እያሳተመ የአንባብያንን የንባብ ጥ ም ለመቁረጥ የተነሳ ይመስላል። ምሥጋና ለዩኒ ቨርስቲ ፕሬስ! መንግሥቱ ለማ የአባታቸውን ትዝታ እንዲህ ባ ለ ኹኔታ በማሳተማቸው የራሳቸውን ታሪክ ጨ ምሮ ስንት የአገሪቱን ታሪክ እንዳዳኑ ለመረዳት አ ይቸግርም። ተራኪው አዛውንት ከልጅነት ቀዬአ ቸው ከመቄት አንስተው እስከ አዲስ አበባ እና ሐ ረር ያደረጉት ጉዞ ከግለሰቡ ታሪክ ባሻገር የአገሪቱ ንም፣ የጥንታዊቱን ቤተክርስቲያንም ታሪክ ይተ ርካሉ። የጊዜውም ርዝመት የሚደንቅ ነው፤ ከአ ፄ ቴዎድሮስ ጀምሮ እስከ አፄ ኀይለሥላሴ ድረስ የነበረውን የታሪክ ዘመን አንዳንዶቹን ከዐይን ም ስክሮች እንደሰሟቸው አንዳንዶቹንም ራሳቸው እንዳለፉባቸው ታሪኮች ስለሚያስታውሷቸው ይ ህን ትረካ መከተል እንዴት ያለ ደስታ እንደሚፈ ጥር አንባቢው ብቻ ነው የሚረዳው። በዚህም ላይ ተራኪው ራሳቸው ያላቸው ባህላ

ዊው የሥነጽሁፍ እና የታሪክ ትምህርት ተሞክ ሮ ትረካውን ጣፋጭ አድርጎታል። ተራኪው አዛ ውንት በየመሀሉ የሚጠቅሷቸው የግዕዝ ቅኔዎች እና የአማርኛ ግጥሞች ትረካውን ሙዚቃዊ ቃና አድሎታል። መንግሥቱ ለማን ከሎንዶን የኢኮኖ ሚ ትምህርት ቤት ወደ ቅኔ እና የጥበብ ዓለም ያ ስሸፈታቸውም ቆሌ ለካንስ ድንገት የተከሰተ አል ነበረም የኖረ የአያት የቅድመ አያት እንጂ። ተራ ኪው አለቃ ለማ ስለ እናታቸው (ስለ መንግሥቱ አያት) በሚናገሩ ጊዜም ይህ የቅኔ ውርስ በግልጽ የሚታይ ነው። እኚህ ሴት በእድሜ ከገፉ በኋላ የ ገጠሙትን ግጥም አለቃ ለማ እንደሚሉት “መቄ ት ውስጥ ያላጠናው የለም”። ቢጠናም አይደንቅ ም የሚገርም የጥበብ ልቡና ተንጸባርቆበታልና። “ጆሮ ቀለቡን ተሰፈረ ዐይን እንደራበው ቀረ” ተራኪው አለቃ ለማ የሚያጫውቱን ወግ አንዳ ንድ ጊዜ ተረት ብቻ የሚመስሉንን ግለሰቦችም በ ቅርበት እና ባላየንበት ማንነታቸው የሚያሳየን ነ ው። አፄ ቴዎድሮስን ስናውቃቸው ቁጡ እና በየ አቅጣጫው የሚሸፍተውን ግዛታቸውን ለማስገ በር ፋታ የሌላቸው ባተሌ ነበሩ። በአለቃ ለማ ት ረካ ውስጥ ግን ቴዎድሮስ በቆሎ ትምህርት ቤት የሚዘምር አንድ ድምፀ መልካም ተማሪ ለማዳመ ጥ ሲሉ ድንኳናቸውን በቆሎ ትምህርት ቤቱ አ ጠገብ አስተክለው ሦስት ቀን በዚያው ሲከርሙ ይታያሉ። የፍቅር እስከ መቃብሩ ጉዱ ካሣ እዚያ ው ዲማ ጊዮርጊስ አድራጊ ፈጣሪ ኾኖ አለቃ ለማ ቅኔ እንዲቀኙ ሲያደርግ ይታያል፤ በቅኔ ላይ ባሳየ ው ድክመቱ ምክንያትም የተዘረፈበትንም ቅኔ ያ ስታውሱታል። በዚቀኝነታቸው ብቻ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቁትም አለቃ ገብረሃና የታወቁ የዝ ማሜ እና የአቋቋም ሊቅ ኾነው ነገር ግን በብብታ ቸው የትምባሆ ቅል ደብቀው ቤተ መቅደስ ውስ ጥ እንደተገኙ ያሳዩናል። አፄ ዮሐንስ፣ አፄ ምኒል ክ፣ ንጉሥ ሚካኤል ሁሉንም እንደገና በአዲስ ማ ንነታቸው እና በተራኪው ዕይታ እንድናያቸው ያ ደርጉናል። በዚህ ግሩም መጽሐፍ!

ሐበሻዊ ቃና habeshawi kana ብላችሁ ፈልጉን

“ላይክ” () የሚለውን ምልክት ተጫኑ

ወቅታዊ ዘገባዎች፣ “ሊንኮች”ን እና ፎቶዎች ያገኛሉ ባለፉ የጋዜጣው እትሞች ላይ የወጡ ጽሁፎችን ያገኛሉ


ሐበሻዊ ቃና

16

የከተማ ቧልት

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ስኳር + ዘይት + ቤንዚን = ቦምብ ሒሳብ የቁጥር ጉዳይ ነው

ሰሞኑን በተለያዩ የቴክኒክ እና የሙያ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚማሩ ወጣ ቶች የየራሳቸውን የፈጠራ ውጤቶች በ ኤግዚቢሽን ማዕከል አቅርበው ነበር፡፡ ይህንን የወጣቶችን ፈጠራ ያስተዋለ አን ድ የሠፈሬ ወጣት ቀልብ የሚስብ የፈጠ ራ ሥራውን ለእኛ መንደር ሰዎች ይዞ ቀ ርቦ ነበር፡፡ ወጣቱ ስኳር፣ የምግብ ዘይ ት፣ ቤንዚን፣ ውሃ እና የተለያዩ ነገሮችን ከፊት ለፊቱ አስቀምጧል፡፡ ከዚህ ወጣ ት ጋር ያደረግኩትን ቆይታ እነሆ፤ “ስምህ ማን ይባላል?” ወጣቱ ተናገረ፡፡ “ለመንደራችን ነዋሪዎች ይዘህ የቀረብ

ከው የፈጠራ ውጤት ምንድነው?” “በእነዚህ ንጥረ ነገሮች ቦምብ መሥራ ት!” “እሺ ከስኳር፣ ከምግብ ዘይት፣ ከቤንዚ ን፣ ከውሃ እና ኅብረተሰቡ በጥብቅ ከሚ ፈልጋቸው ከእነዚህ ነገሮች የሠራኸው ቦ ምብ አጠቃቀሙ እንዴት ነው? ማለቴ ተግባራዊ የሚደረገው?” “እነዚህ ንጥረ ነገሮች ውህደት ፈጥረው አይደለም ቦምብ የሚሆኑት፡፡” “እና?” “ራሳቸውን ከአገሪቱ በማጥፋት እንደ ቦምብ መጠቀም ብቻ ነው፡፡” እግዚኦ! የምቀኛ ጆሮ ይደፈን!

“ቡና ገበያ አደገኛ!” ሌላው ሰሞነኛ ጉዳይ ሆኖ የሰነበተው ጉዳይ በእግር ኳሱ፣ የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ስፖርት ክለብ የዘንድሮው ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑ ነው፡ ፡ ሊጉ ከመጠናቀቁ በፊት ባሉት አራት እና አምስት ጨዋታዎች ስቴዲየሙ የተለየ ድባብ ነበረው፡፡ በተለይ ሻምፒዮኑ ኢትዮጵያ ቡና ጨዋታ ካለው፡፡ በስቴዲየም ውስጥም ሆነ ከስቴዲየም ውጪ “ጨምሯል ቡና ጨምሯል፤ ቡና ገበያ አደገኛ!” ዓይነት የኑሮ ውድነትን የመቃወሚያ የሚመስሉ መዝሙሮችን መስማት ለከተማችን ነዋሪ እንግዳ አልነበረም፡፡ በተለይ ለስፖርቱ እንግዳ የሆኑ አንዳንድ ነዋሪዎች፣ “ጨምሯል ቡና ጨምሯል፤ ቡና ገበያ አደገኛ!” የሚለውን መዝሙር ሲሰሙ፣ “እናውቀዋለን፤ ቡና ተረት በሆነበት ጊዜ ሱሳችንን አትቀስቅሱብን!” በማለት ሲቀልዱ ተደምጠዋል፡፡

ሌሎች ደግሞ “ቡና ገበያ አደገኛ!” የሚለውን መዝሙር ሲሰሙ “እንዴ! ምን ቡናው ብቻ የስኳሩ ገበያስ ቢሆን! ኧረ የየዘይቱ፣ የጤፉ፣ የሽሮውም ቢሆን መች ይቀመስና…!” ማለታቸው ተሰምቷል፡፡ ለማንኛውም፣ “የሕዝብ ብሶት የወለደው ጀግናው የኢትዮጵያ ቡና ሠራዊት ቅ/ጊዮርጊስ ሲጠቀምበት የነበረውን ዋንጫ ተቆጣጥሮታል!” ቅ/ ጊዮርጊስ ከአሥራ ሦስቱ የሊጉ ዕድሜ ዘጠኝ ጊዜ ሻምፒዮን መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ ቡና ለዋንጫው እየቀረበ ሲመጣ እንዲህ የሚል ልማታዊ መዝሙር መጣ፤ “አባይ ይገደባል፤ ቡና ዋንጫ ይበላል!” ዋንጫው ተበላ፡፡ እነሆ የሚከተለው ዜማ ደግሞ ተከተለ፤ “መሰናበቻ መሰናበቻ! ያሆ! መሰናበቻ፤ አሁን የቀረው ግድቡ ብቻ!”

የ“ፌስ ቡክ” ስላቅ

ና?

ዝና ን እ ን ደ ሄ የት

ንግሥታችን ለተፈጥሮ ሳይንስ፣ ለቴክኖሎጂ እና ለሒሳብ የትም ህርት ዘርፍ ትኩረት መስጠቱ ሰሞኑን በየሚዲያው እንደ ጉድ እ የተዘገበ ነው፡፡ እንደውም ለዘርፉ መምህራንና ተማሪዎች እንዲ ሁም አዳዲስ የፈጠራ ስራዎቻቸውን ላቀረቡ ግለሰቦች ሽልማቶችን በመስጠት ምን ያህል ትኩረት እንደሰጠ አሳይቶበታል፡፡ በተለይ የሒሳቡ ነገር ከየትኛውም ዘርፍ በላይ መንግሥታችን ትኩረት እንደተ ሰጠው ውስጠ አዋቂዎች ይናገራሉ፡፡ ለምን ቢሉ መንግሥት እና የሒሳብ እው ቀት ባሌ እና ቦሌ ናቸውና፡፡ ይህንን ክፍተት ለመሙላት ታዲያ፣ “የሒሳብ ሊቃ ውንት ሆይ ወዲህ ኑ!” እያለ ነው አሉ መንግሥት፡፡ ሒሳብ የቁጥር ጉዳይ ነው፡፡ የቁጥር ጉዳይ ደግሞ መንግስትን እና ተቃዋሚ ኃ ይሎችን፣ መንግሥትን እና የውጪ ኃይሎችን፣ መንግስትን እና የሰብአዊ መብ ት ተከራካሪዎችን፣ መንግስትን እና የኢኮኖሚ ባለሙያዎችን ያወዛገበ፣ አሁንም እያወዛገበ ያለ ጉዳይ ነው፡፡ እስኪ ባለፉት ሃያ አመታት መንግሥታችንን ካወዛ ገቡት ቁጥር ነክ ጉዳዮች ዋና ዋናዎቹን እንመልከት፤ ሀ. የራሷ የኢትዮጵያ ዕድሜ የታሪክ ምሁራንንና መንግስትን አወዛገበ፤ ለ. የኢትዮጵያ ሕዝብ ብዛት አወዛገበ፤ ሐ. ባለፉት ምርጫዎች /በተለይ 1997 ዓ.ም/ የተገኙት የድምፅ ቆጠራዎች ው ጤት መንግሥትንና ተቃዋሚ ፓርቲዎችን አወዛገበ፤ መ. “እንደ ሾላ ሕገ መንግሥቱን በድንጋይ ለማውረድ ግርግር የፈጠሩ ፀረ ዴ ሞክራሲ ኃይሎችን ለማስቆም ወደ ሰማይ በተተኮሰ ጥይት የሞቱ ሰዎች” ቁጥ ር አለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪ ተቋማትንና መንግሥትን አወዛገበ፤ ሠ. በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በተከፈለው መስዋዕትነት ያጣነው የሰው ሕይወትና የገንዘብ መጠን ሲሰላ መንግሥትን እና ተቆርቋሪ ወገኖችን አወዛገበ፤ ረ. በየዓመቱ የምናስመዘግበውና እያስመዘገብን ያለነው “ፈጣን የኢኮኖሚ ዕ ድገት” በመቶኛ ተሰልቶ ሲቀመጥ የኢኮኖሚ ባለሞያዎችን እና መንግሥትን አ ወዛገበ፤ ሰ. በየጊዜው በሚነሳው ረሃብ የሚጎዳውና እያለቀ ያለው ህዝባችን ቁጥር መን ግሥታችንን እና የውጪ መገናኛ ብዙኃንን አወዛገበ፤ አሁንም እያወዛገበ ነው፡፡

ዩጋንዳ ፊልም

የጀርመን ፊልም በ4 ሺህ ሽልንግ

መቼ፦ ሐምሌ 6 ቀን 2003 ዓ.ም የት፦ ሲኒፕሌክስ - ጋርደን ሲቲ- ከኡቹሚ ሞል በላይ ሶስተኛ ፎቅ ሰዓት፦ ከምሽቱ አንድ ሰዓት የመግቢያ ዋጋ፦ አራት ሺህ ሽልንግ ብቻ

የደስታ በሽታ እና “ቶክ ፉትቦል” “የቴሊቪዥን የአገልግሎት ክፍያ ክፈ ሉ! ክፈሉ! ክፈሉ!” የሚለው የኢቲቪ የ ዘወትር ውትወታ እቤት በተገኘሁበት ሰ ዓት ሁሉ ቴሌቪዥኔ ላይ እንድጣድ ም ክንያት ሆኖኛል፡፡ “ኢቲቪ እንዲህ ማለ ቱ ረብ ያለው መረጃ እና ቀልብ የሚስ

ብ ፕሮግራም ቢኖረው ነው” የሚል ተ ስፋ በመሰነቅ፡፡ ታዲያ በባለፈው ሳምን ት ባንዱ ቀን ክፉና ደጉን ለመስማት የከ ፈትኩት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዲህ የሚል ዜና ጆሮዬ ድረስ ይዞልኝ መጣ፡፡ “የደስታ በሽታ ከዓለም ላይ መጥፋቱ ተ ገለፀ፡፡” ዜናው ራሱ ደስታ የሚፈጥር ነ በርና ደስ ተሰኘሁ፡፡ በተለይ ይህ በሽታ ወደ አፍሪካ የገባው በ19ኛው ክ/ዘመን መሆኑን ስሰማማ ለ ጠቅላላ እውቀት የሚሆን ጥሩ መረጃ በ ማግኘቴ ደስታዬ ወደር አጣ፡፡ አይታወ ቅም እኮ በየኤፍኤሙ በገፍ የአየር ሰዓ ት ከተሰጣቸው ከ”ቶክ ፉት ቦል” ፕሮግ ራም አዘጋጆች መካከል አንዱ የሚከተለ ውን የሞባይል ካርድ የሚያሸልም ጥያቄ ይጠይቅ ይሆናል፡፡ /ዘንድሮ በአገራችን ከፍተኛውን ሚዲያ ሽፋን የያዘው የቦን ዱ ሽያጭ እና የእግር ኳስ ስፖርት ጉዳ ይ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ ሌላ ብርቱ ጉ ዳይ አለብን እንዴ!? እኔ እንጃ! የሚያቀ ርቡልኝን ከመስማት እና ከማንበብ በስ ተቀር እኔ ምን አውቃለሁ!?/ “የደስታ በሽታ ወደ አፍሪካ የገባው መ ቼ ነው?” እኔ ሆዬ ሚስድ ኮል ለማድረጊ ያ ከቆጠብኳት ሣንቲም ላይ ቀንሼ ቁጥ ሮቹን ጠቅ፣ ጠቅ አድርጌ፣ “ሃሎ የቶክ ፉትቦል አዘጋጆች!?” ማለ ት ብቻ፡፡ “አዎ! ማን እንበል?” “እኔ ኤስ ነኝ፤ ከአዲሱ ሰፈር፤ የቅድሙ ን ጥያቄ ለመመለስ ነበር፡፡” “እሺ ይቀጥሉ!” “የደስታ በሽታ ወደ አፍሪካ የገባው በ19ኛው ክፍለ ዘመን ነው!” እላለኋ! የከሳቴ ብርሃን የአማርኛ መዝገበ ቃላት “ደስታ” የሚለውን ቃል ሲፈታው፣ “የ ልቡና መደሰት፣ ኀዘን በሌለው ስሜት መሆን፣ የፊት መፍካት” ይለዋል፡፡ የደስ ታ በሽታን የሚያውቀው ደስታን የሚያ ውቅ ሕዝብ ነው ብዬ አጉረምርሜ ሳል ጨርስ ግን የደስታ በሽታ የከብቶች በሽ ታ መሆኑን ማብራሪያ ተሰጠበት፡፡ አዎ! ጠንቁ ለሰዎችም የሚተርፍ በሽታ ሆነ እ ንጂ “የደስታ በሽታ” እንኳን የከብቶች በ ሽታ ሆነ አልኩ፡፡

ከላይ የቀረቡትን አራቱንም ጽሁፎች ከአዲስ አበባ ያደረሰን አምደኛችን የአራት ኪሎው በእግዜር ነው

እ.ኤ.አ በ2002 የኦስካርን ሽልማት በምርጥ የውጭ ሀገር ፊልም ዘርፍ ያሸነፈ ነ ው። “ኖ ዌር ኢን አፍሪካ” ስቴፈን ዝዌግ የተሰኘ ደራሲ በራሱ ታሪክ ላይ ተመስርቶ ከጻፈው ልቦለድ መጽሐፍ ወደ ፊልም የተቀየረ ነው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ከናዚዎች በመሸሽ ወደ ኬንያ ስለተሰደደ ቤተሰብ የሚተርክ ነው።

በሲኒማ ቤት

ፊልም

መቼ፦ ከሰኞ እስከ እሁድ የት፦ ሲኒፕሌክስ - ጋርደን ሲቲ- ከኡቹሚ ሞል በላይ ሶስተኛ ፎቅ ሰዓት፦ ከቀኑ አምስት፣ ስምንት፣ አስር ሰዓት እንደዚሁም ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል፣ ሶስት ሰዓት ተኩል የመግቢያ ዋጋ፦ 16ሺህ ሽልንግ ( ዘወትር ማክሰኞ ስምንት ሺህ) በሶስት የተለያዩ አዳራሾቹ የአሜሪካ እና የህንድ ፊልሞችን ሳምንቱን ሙሉ ለተመልካች የሚያቀርበው ሲኒፕሌክስ በሚቀጥሉት ሳምንታት ለዕይታ የሚያበቃቸው ፊልሞች የ“ሀሪ ፖተር” ተከታታይ ፊልም የመጨረሻ ክፍል፣ የ“ትራንስፎርመር” ተከታይ ፊልም እና “ብራይድስ ሜይድን” ነው።

ፌስቲቫል

የጣፋጭ ኬክ

መቼ፦ ቅዳሜ ሐምሌ 9 ቀን 2003 ዓ.ም የት፦ ኤሚን ፓሻ ሆቴል ሰዓት፦ ከቀኑ አራትሰዓት ጀምሮ ዋጋ፦ 20ሺህ ሽልንግ ለአዋቂዎች (ለህጻናት አምስት ሺህ) የኬክ አፍቃሪ ለሆኑ እና ልጆቻቸውን ለማስደሰት ለሚፈልጉ ወላጆች ሁነኛ አጋጣሚ ነው። ብዙ ሀበሾች የኡጋንዳውያን ኬክ እንደ አገር ቤት አይደለም ሲሉ ይደመጣሉ። በፌስቲቫል ደረጃ የሚዘጋጁት ኬኮች ግን ለየት እንደሚሉ ይገመታል። በቦታው ሄዶ ማረጋገጥ ነው።

ኬንያ ዳንስ

የአርጀንቲና ታንጎ

መቼ፦ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የት፦ ኢጣሊያ ባህል ማዕከል- ዌስትላንድ- ከጃካራንዳ ሆቴል በተቃራኒ- ግሬንዳየር

ታወር- አምስተኛ ፎቅ ሰዓት፦ ከጠዋቱ አራት ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት ተኩል ዋጋ፦ በእያንዳንዱ የመማሪያ ቀን 500 ሽልንግ

የበጎ ፍቃደኞች ስብስብ የሆነ ፓታማንጎ የተባለ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት የአርጀ ንቲናንን ታንጎ ዳንስ ወደ ናይሮቢ አምጥቷል። ድርጅቱ ለጀማሪዎች የዳንስ ትምህ ርት ይሰጣል።


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

አሮን ፀሐዬ

አዲስ ነገር ኦንላይን

ጥ ረጭ ያለ ሰፈር፤ በግ ራ እና በቀኝ የተሰደሩት ቪላ ቤቶች ግዙፍ የጋራ በር አላቸው ፤ ቦሌ ሚ ካኤል አካባቢ። አንድ የ ጥበቃ አባል በእነዚሁ የ ቪላ ቤቶች የወል በር ላይ ቆሞ ገቢ ወጪ መኪናዎችን ይቃኛል። ፀጉረ ልውጥ መኪ ና እንዳይገባ በንቃት የሚከታተል ይመስላ ል። የጥበቃው ነገር በዚህ አያበቃም። ይባ ስ ብሎ እያንዳንዱ ቪላ ቤት በተናጥል የራ ሱ በርና በረኛ ተመድቦለታል። “የተሳካላ ቸው” ብቻ የሚኖሩበት መንደር መኾኑን ከአካባቢው የሚተነው ዝምታ የዋጠው አ የር ያሳብቃል። በስተግራ አራተኛዋ ቪላ ቤት ግን የተለ የ ባሕርይ ይታይበታል። የቪላ ቤቱ በር ገ ርበብ ተደርጎ የተተወ ነው። ደጅ ላይ ጥቂ ት መኪናዎች ተኮልኩለዋል። ይህ ቤት የ ሚታይ፣ የሚዳሰስ በረኛ የለውም። በውስ ጡ ግን ብዙ ዳሳሽ መዳፎች አሉበት። ለም ሳሌ የጀሚላ ተዐምረኛ መዳፍ አንዱ ነው!

17

የአገር ቤት ጨዋታ

የጀሚላ መዳፎች

ፎቶ - ኢዚ ላይፍ ድረ ገጽ

ከሌሊቱ ስምንት ሰዓት . . .

ሷ፣ በዐይኗ እንዲሁም በፀጉሯ መንከባከብ ን ታውቅበታለች። ሥራ የሚፈታ የሰውነት ክፍል የላትም፤ ዳሌዋን ጨምሮ። “ይቅርታ ሂሳብ ቅድሚያ ነው! በሰው 250 ብር!” የማሳረጊያ ንግግሯ ነበር።

የተውኔቱ ጡዘት እና ፍጻሜ

ዛው ክሬም ጀርባዬን ካሸችኝ በኋላ ከማ ጅራቴ ጀምሮ ቁልቁል በጥፍሮቿ እንደመ ቧጨር፣ እንደመቧጠጥ አደረገችኝ። ሰው ነቴ ምላሽ ሰጠ። ትዕይንቱ በጀርባ ወደ መጋደም ተዛወረ። የመሀል ጣቷን ጆሮዬ ውስጥ በመጨመር የተለየ ትርጉም ያለው መልእክት ልታስተ ላልፍልኝ ሞከረች። አንገቴ አካባቢ ጥሩ ስ ሜት የፈጠረብኝን አንዳች ነገር አድርጋ ወ ደ ደረቴ ተንደረደረች። ተመልሳ ደግሞ የ መሀል ጣቷን በጆሮዎቼ በመጨመር ቀድ ሞ እንዳደረገችው ስሜቴን ለማናር ጣረ ች። የደረቴን ጡንቻዎች በስሜት ታሻቸው ጀመር። ከክሬሙ በቄንጥ በጣቷ ትጠነቁል ና የደረቴ ጡቶች ላይ በማሳረፍ በጥፍሮቿ ጫፉን ብቻ እየነካካች ንዝረት ለመፍጠር ታተረች፤ ተሳካላት። ከዚህ በኋላ እኔን ፍ ፁም ረስታ ከደረቴ ጡቶች ጋር ጨዋታዋን አደራችው። ይህን ረዘም ላለ ደቂቃ ከቆየች

ጀሚላ በመዳፎቿ ካልኾነ ብዙ አታወራ ም። ለጥያቄዎቼ ግን በሹክሹክታ አጠር ያ ሉ ምላሾችን ትሰጠኛለች። ብዙ ከማውራ ት ብዙ መሥራት ትመርጣለች። ለብር ሳይ ኾን ለሞያ ፍቅር የምትሥራ ነው የምትመ ስለው። ትኩረቷ ሰውነቴን ማናዘዙ ላይ ነ ው። ሥራውን ተክናበታለች፤ ዱባይ አንድ ዓመት ተኩል በግሏ ይህን አገልግሎት ትሰ ጥ እንደነበር ነገረችኝ። ከዚህ በላይ ስለራ ሷ ከመናገር ተቆጠበች። የእግሮቼን ጡንቻ ዎች በክሬም በማሸት እና በማሳሳብ ዘና ካ ደረገቻቸው በኋላ የእግር ጣቶቼ መሀል በ መሀል ጣቷ እየገባች መልእክት ለማስተላለ ፍ ሞከረች። ዐይኖቼን በመጨፈን ምላሽ ለ መስጠት ሞከርኩ። “መሳዥ ታደርገኛለህ?” “ማንን?” “እኔን!” ‘እ!’ ቤቱን ከጠቆሙኝ ሰዎች ይህ እንዳለ አል ተነገረኝም ነበር፡፡ “አልችልበትም ግን … ልሞክር?” “ሂሳብ ያስጨምርኻል” “ኸረ? ስንት?” “200 ብር…ለኔ ነው የምትሰጠኝ! ድርጅ ቱ አያገባውም” ተስማማሁ። በነበርኹበት ኹኔታ አለመ ስማማት አማራጭ አልነበረም። ሻሽ ላይነ ን ከመሰለ ጨርቅ የተሰራውን ስስ ጋውኗ

Jumanne ጁማኢኔ - ማክሰኞ Jumatano ጁማታኖ - ረቡዕ Alhamisi አልሃሚሲ - ሐሙስ Ijumaa ኢጁማአ - አርብ Miezi za Mwaka ሚኤዚ ዛ ሙዋካ n n n የዓመቱ ወራት Januari ጃኑአሪ - ጥር Februari ፌብሩአሪ - የካቲት Machi ማቺ - መጋቢት Aprili አፕሪሊ - ሚያዝያ Mei ሜኢ - ግንቦት Juni ጁኒ - ሰኔ Julai ጁላኢ - ሐምሌ Agosti አጎስቲ - ነሐሴ Septemba ሴፕቴምባ - መስከረም Oktoba ኦክቶባ - ጥቅምት Novemba ኖቬምባ - ህዳር Desemba ዲሴምባ - ታህሳስ

Vielezi vya wakati ቪኤሌዚ ቪያ- ዋካቲ የጊዜ ገላጮች Hivi punde ሂቪ ፑንዴ - በጣም በቅርቡ (ወደፊት ጊዜን አመልካች ነው) Sasa hivi ሳሳ ሂቪ - ልክ አሁን Leo ሌኦ - ዛሬ Jana ጃና - ትናንት Juzi ጁዚ - ከትናንት ወዲያ Juzi juzi ጁዚ ጁዚ - በቅርቡ (የአለፈ ጊዜን አመልካች ነው) Kesho ኬሾ - ነገ Kesho kutwa ኬሾ ኩቱዋ - ከነገ ወዲያ Mtondo ndogo ሙቶንዶ ንዶጎ ከሶስት ቀናት በኋላ Mtondo ሙቶንዶ - ከአራት ቀናት በኋላ Zamani ዛማኒ - ከረጅም ጊዜ በፊት (የቆየ ጊዜን ለማመልከት)

በሻማ ብርሃን “ማይም ተውኔት” ሻወር በቅጡ መውሰዴ ትዝ አይለኝም። ኾኖም ቀጥሎ ለሚኾነው ነገር ጉጉት ያደረ ብኝ እንዳይመስል በሻወር ቤት ጥቂት ፀና ሁ። ያውም ሥራ ፈትቼ። ወደ ተመደበልኝ ክፍል ስመለስ ጭልጭ ል የሚል የሻማ ብርሃን፣ በጭልጭል የሻ ማ ብርሃን ውስጥ ደግሞ ለግላጋ ሴት፣ ከር ሷ ሥር በአየር የተወጠረ እና ያበጠ የላስቲ ክ ፍራሽ ጠበቀኝ። መደናገጤን ዐይታ ነው መሰለኝ በከፊል ፈገግ አለች። ወይም ፈገግ ያለች መሰለኝ። “ሃይ! ጀሚላ እባላለሁ። ለምሽቱ አስተናጋ ጅህ ነኝ” ቄንጠኛ ናት። “አመሰግናለሁ!” እያልኩ በነበረበት ቅጽበ ት የሻወር ጋውኔን ገፈፈችው” በምትኩ መ ለመላዬን እንዳልቀር የማጣፋው ስስ ፎጣ ሰጠችኝ። ከሰከንዶች በኋላ “ፎጣውን ካ ልወደድከው መተው ትችላለህ” ስትል አ በሰረችኝ። ኾኖም ፎጣው እንዲቆየኝ መ ረጥኩ። በሆዴ በአየር በተወጠረው የላስቲክ ፍራ ሽ ላይ እንድጋደም ካዘዘችኝ በኋላ የተወሰ ኑ ሻማዎችን በማክሰም የክፍሉን ስልምል ም ብርሃን ይበልጥ አደበዘዘችው። አሁን በ ዐይን ቋንቋ መግባባት ችግር ውስጥ ወድቋ

ፎቶ - ከድርጅቱ ድረገጽ

ወደ ውስጥ ሲዘለቅ ከሳሎኑ በራፍ ላይ የ ተሰቀለው የእንግሊዝኛ ማስታወቅያ በደ ብዛዛ የአምፖል ብርሃን ውስጥ እንዲህ ይ ነበባል። “Close the door please! It is cold these days!” ሰሞኑን ይበርዳል! እባ ክዎ በሩን ይዝጉት! እንደማለት። በትንሹ ገ ርበብ ያለው የሳሎን በር ሲከፈት ቀጭኗ ኮ ሪደር “ሪሰፕሽን” የሚል ጽሑፍ ከአናቷ ወ ደተሰቀለባት ጠባብ ክፍል ታደርሳለች። በ ዚች ቀጭን ክፍል ደግሞ ሸንቀጥ ዘለግ ያለ ች ቆንጆ ተሰይማለች፤ ሕይወት ባለው ፈገ ግታ ተቀበለችን። “ምን ልታዘዝ?” ለደንቡ ነው እንጂ የምንፈልገውን ጠንቅ ቃ ታውቀዋለች። አጠያየቋ በመረጃ እንደ መጣን ለማረጋገጥ ያህል ነው። በዚህ ው ድቅት መቼስ ማኅሌት ለመቆም እንዳልመ ጣን እኛም፤ እርሷም፤ ሰይጣንም እናውቃ ለን። ሻወር አስቀድመን መውሰድ እንደም ንፈልግ ከጠየቀችን በኋላ ክፍሎቻችንን አ መላከተችን። በቂ ፎጣዎች፣ የሻወር ጋውን እና ሌሎች የንጽሕና መጠብቂያ ቁሳቁሶች ን የተሟሉ መኾናቸውን ዐሳየችን። “ሻወር ወስዳችሁ ስትጨርሱ አስተናጋጆ ቻችሁ በየክፍላችሁ ይጠብቋችኋል! መል ካም ምሽት!” የበረራ አስተናጋጆችን ዐይነት ቅልጥፍና ይታይባታል። የሚዘናፈለው ፀጉሯ ወደ ፊት እየመጣ ሲያስቸግራት አንገቷን ወዝ ወዝ አድርጋ ትመልሰዋለች። ሌላ ጊዜ ደ ግሞ በጣቶቿ ሰብሰብ አድርጋ በጆሮዎቿ የኋሊት ትሰበስበዋለች። ከአፍታ በኋላ ፀ ጉሯ መልሶ ወደፊት ብትን ይልባታል። ዳ ግም ከአንገቷ ወዝወዝ ትልና ጆሮዎቿን ለ ሚበተነው ፀጉሯ እንደ ታኮ ትጠቀምበታ ለች፤ ዘንፋላው ፀጉሯ በጄ አይላትም። ዳግ ም አደብ ልታሲዘው ትሞክራለች። እንግዶችን በአንደበቷ ብቻ ሳይኾን በጥር

በአዲስ አበባ እንዲህ 24 ሰዓት የማሳጅ አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች እየተስፋፉ ነው

ል፤ የመግባቢያ ቋንቋው ወደ መዳፍ ተቀየ ረ። ጀሚላ በመዳፎቿ ታናግረኝ ጀመር። የ ማይም ድራማው ፊሽካ ተነፋ። እጅግ በስሱ የሚንቆረቆረው በመሣርያ ብ ቻ የተቀነባበረ የሩቅ ምሥራቅ ሙዚቃ በም ታቃስት የሴት ድምፅ ታጅቦ ከክፍሉ አንድ ጥግ ላይ በተገጠመ አነስተኛ “ስፒከር” እየ ተሞዘቀ ነው። ደብቅ ካሜራ በክፍሉ ው ስጥ እንዳልተገጠመ በምን ርግጠኛ መዀ ን ይቻላል? የዚህ ቀስቃሽ ሙዚቃ የድምፅ ምጣኔ እውነትም ከሩቅ ምሥራቅ ከተከፈ ተ ቴፕ የሚሰማ ነው የሚመስለው። እጅግ ዝቅ ተደርጎ የተከፈተ ሙዚቃ! ልዩ መዓዛ ባለው የክሬም ቅባት በስሱ ት ዳብሰኝ ጀመር። አስተሸሸቷ መታሸት ከሚ ለው ቃል ይልቅ መነካካት፣ መፈታተን እ ና መዳራት ለሚሉት ቃላት በጣሙን ይቀ ርባል። ቀጥላ የውስጥ እግሬን በረዣዥም ጥፍሮቿ መጠነቋቆል ጀመረች። በባለ መዐ

ቋንቋ በየፈርጁ የስዋሂሊ ቋንቋ ዳሰሳችንን ቀጥለናል። በመጀመሪያው እትማችን የመግባቢያ እና የሰላምታ ቋንቋዎችን ተመልክተናል። በሁለተኛው እትማችን ደግሞ የቁጥሮችን አጠቃቀም አይተናል። ለዛሬ ደግሞ ስዋሂሊ ተናጋሪዎች ጊዜን እንዴት እንሚቆጥሩ እን መለከትና እረፍት እናደርጋለን። ከሚቀጥለው እትም ጀምሮ በማዕከላዊ ኡጋንዳ በስፋት ስለሚነገረው የሉጋንዳ ቋንቋ ያጠናቀርነውን እናቀርባለን።

ስዋሂሊ ተናጋሪዎች ዘንድ የሰዓት አቆጣጠሩ ከአማርኛው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ለምሳሌ ማለዳ ላይ እነሱም የሚጀምሩት አንድ ሰዓት ብለው ነው፡ ፡ የሳምንቱ ቀን ግን አንድ ተብሎ የሚጀምረው ከቅዳሜ ነው፡፡ ወሩ ደግሞ ከፈረንጆቹ ጋር በተመሳሳይ መልኩ ከጥር ነው የሚጀምረው፡፡ በመሆኑም አዲስ ዓመታቸው ከጥር ይጀምራል ማለት ነው፡፡ በዚህ መሰረት የጊዜ አቆጣጠሩን ከመመልከታችን በፊት ለቆጠራው የሚያገለግሉትን ቃላትና ትርጉማቸውን እናስቀድም፡፡

Asubuhi አሱቡሂ -ማለዳ Mchana ሙቻና - ቀን (ጊዜው ቀን መሆኑን ለማመልከት) Adhuhuri አዙሁሪ - እኩለ ቀን (ቀትር) Alasiri አላሲሪ - ከሰዓት በኋላ (ከስምንት እስከ ዘጠኝ ሰዓት) Jioni ጂኦኒ - ምሽት Usiku ኡሲኩ - ማታ Usiku wa manane ኡሲኩ ዋ ማናኔ - ከእኩለ ሌሊት በኋላ ያለው ጊዜ Alfajiri አልፋጂሪ -ንጋት (አጠባብ) Mapambuzuko ማፓሙቡዙኮ ንጋት

በት በኋላ ድንገት ቁልቁል ተንደረደረች። ስሷ ፎጣዬ ደጀንነቷ አከተመ። በፈቃዷ ተንሸራተተች። ሽምቅቅ አልኩኝ። “ታፍራለህ እንዴ!” እ . .!? “ታፍራለህ? የመጀመርያህ ነው?” “ኖ! ኖ !” ሽምጥጥ አድርጌ ዋሸኋት “ሻማ ትፈልጋለህ?” “አይ ይቅርብኝ!” በልቤ ግን የሻማውን ጥቅም ሳላውቀው ለ ምን ተግደረደርሁ እያልሁ ነበር። ሻማ በዚህ ምስጢረኛ ቤት ሳሙና ኾኖ እንደሚያገለግል አጫወተችኝ። “እየቀለጠ ያለ ሻማ የወንድ ሰውነት ላይ ሲፈስ መል ካም ስሜት ይፈጥራል እኮ” አለችኝ። በቅ ላጩ የሻማ ጠብታ ስቃይ ውስጥ መልካም ስሜትን ለመፍጠር የሚደረግ ጥበብ ነው፡ ፡ እንደ ጀሚላ ማብራሪያ ብዙዎቹ የውጭ ዜጎች “የሻማ ስቃይ” ነፍሳቸው ነው። እነዚ ህ ደንበኞቿ፣ ላያቸው ላይ በሚቀልጠው የ ሻማ ስቃይ ውስጥ ደስታቸውን ያበራሉ። የውጭ ዜጎች ብቻ አይደሉም የዚህ አገል ግሎት ተጠቃሚዎች፤ በስም ልትጠራቸው ያልፈቀደቻቸው ጥቂት ታዋቂ ሰዎችም የጀ ሚላ እና የሻማዋ ቋሚ ደንበኞች ናቸው። “አንዴ ከለመድከው ሻማ ሱስ ይኾናል” “እውነትሽን ነው?” ጭንቅላቷን በመነቅነቅ አዎንታዋን ገለ ጸች ከተሰጠኝ አጭር የሻማ ገለጻ በኋላ ነገሩ ን መሞከር ፈለግኩ፤ ኾኖም አንዴ ይቅር ብኝ ስላልኳት ዳግም ለመጠየቅ ኩራት ተ ናነቀኝ።

Dakika ዳኪካ - ደቂቃ Saa ሳአ - ሰዓት Kasoro ካሶሮ - ሩብ ለሰዓት(ሩብ ጉዳይ፣ ከሩብ ለማለት) Siku ሲኩ - ቀን Juma /wiki ጁማ/ ዊኪ - ሳምንት Mwezi ሙዌዚ - ወር Miezi ሚኤዚ - ወራት Mwaka ሙዋካ- ዓመት Siku za wiki ሲኩ ዛ ዊኪ n n n የሳምንቱ ቀናት Jumamosi ጁማሞሲ- ቅዳሜ Jumapili ጁማፒሊ - እሁድ Jumatatu ጁማታቱ - ሰኞ

ን ጨምሮ ልብሶቿን አንድ በአንድ እያወለ ቀች በቄንጥ መስቀያው ላይ አንጠለጠለቻ ቸው። ጡት ማስያዣዋ እና የውስጥ ሱሪ ዋ እኔ እንዳወልቃቸው የተተው ናቸው። በዮጋ ዐይነት አቀማመጥ እግሮቿን አነባ ብራ ተቀመጠች። በተራዬ ክሬሙን በስሱ እየጠነቆልኩ ከጀርባዋ ጀመርኋት። ጡት መያዣዋን እንድፈታላት ቀጠን ያለ ትዕዛ ዝ ሰጠችኝ። በጀርባዋም ኾነ በሆዷ ፍራ ሹ ላይ እንድትጋደም ያቀረብኩላትን ጥያቄ ውድቅ አደረገችው። በሌላ አገላለጽ እርሷ ን ማሳጅ ማድረግ የምችለው ከወገቧ በታ ች ያለውን የሰውነቷን ክፍል ብቻ ነው። የ ውስጥ ሱሪዋም የማይደፈር ግዛቷን የሚያ ስከብር ዘብ እንደኾነ ተረዳኹ። ከዚያ ዉ ጭ ባለው ሰውነቷ መዳፌ እንደልቡ ጋለበ በት። በተጣደፍኩ ቁጥር ዝግ እንድል ታስ ጠነቅቀኛለች። ኾኖም መዳፎቼ የተቀዳጁ ት ጊዜያዊ ሐሴት እጅግ ለአጭር ጊዜ የቆ የ ነበር። ተስፈንጥራ በመነሳት የጡት መያ ዣዋን ትታ ጋውኗን ብቻ በመልበስ ከወገ ቡ አካባቢ ባለው መቀነት ሸብ አድርጋ አ ሰረችው። “ከዚህ በላይ መቆየት አይፈቀድም፡፡” ለአንድ ሰዓት ያህል የቆየው ጫዎታችን እ የተጠናቀቀ መኾኑን አረዳችኝ። ኾኖም አንድ የማሳረግያ ትዕይንት እንደ ቀረ ገብቶኛል። እየናረ ለነበረው ወንድነቴ መፍትሄ እንድትሰጠኝ ተማፀንዃት። “ያስጨምርኻል!” “ኸረ! ስንት!” “መቶ ብር! ድርጅቱ አያገባውም ለኔ ነው የምትሰጠኝ፡፡” ለድርድር የሚበቃ አቅም አልነበረኝም። የጀሚላ መዳፎቿ የደረሱበትን የመጨረሻ ው የዳሰሳ ጥበብ ተጠቅመው ለስሜቴ ጊዜ ያዊ ምላሽ ሰጡ። ለጥቂት ደቂቃዎች ዝም አልን! ሻወር ቤት ስገባ ቆሻሻ ውስጥ የምጥላቸ ውን የሶፍት ወረቀቶች ሰብስባ የሻወር ጋ ውኔ ኪስ ውስጥ ሞጀረቻቸው። የሶፍት ወ ረቀቶቹን መታጠብያ ቤት መጣል እንዳል ረሳ ባልጠበቅኹት ኹኔታ አጥብቃ አስጠ ነቀቀችኝ። ለምን ይህን ያህል አሳሰባት!? ልብሶቿን ከመስቀያው አውርዳ በጥድፊ ያ ከለባበሰች በኋላ ድርጅቱ አይመለከታቸ ውም ያለችኝን ለእርሷ የሚገቡ ክፍያዎች እንድፈጽም የኪስ ቦርሳዬን አቀበለችኝ። ሦ ስት የመቶ ብር ኖቶችን ሰጠኋት። “ደንበኛ እንኾናለን! ሌላ ጊዜ ስትመጣ ለ ሪሴፕሽኖቹ ጀሚላ ብለህ ንገራቸው።” በሩን ከፍታ ከመውጣቷ በፊት ልብሶቿ እ ንዳልተዛነፉ ለመጨረሻ ጊዜ ርግጠኛ ለመ ኾን ሞከረች። “እኔ ምልሽ?” “አቤት!” “ጀሚላ ምን ማለት ነው?” “ቆንጆ ወይዘሪት . . .” ክፍሉ ውስጥ ብቻዬን ቀረሁ። ስሜት ቀስ ቃሹ ሙዚቃ አልተቋረጠም። ክፉኛ የጥፋ ተኝነት ስሜት ኅሊናዬን ሲበረቅሰው ተሰ ማኝ። ክፍሉን ለባለተረኛ ዳሳሽና ተዳሳሽ መልቀቅ ነበረብኝ . . .

ምራቂ asi) on

(ቦናሲ-B

q Sikukuu likizo ሲኩኡ ሊኪዞየእረፍት ቀን q Krismasi ክሪስማሲ-ገና q Pasaka ፓሳካ- ፋሲካ q Mwaka Mpaya ሙዋካ ሙፓያ- አዲስ ዓመት q Siku ya kazi ሲኩ ያ ካዚ የስራ ቀን q Liochelewa ሊኦቼልዋማርፈድ q Wakati upasao/siochelewa ዋካቲ ኡፓሳኦ/ሲኦቼሌዋ- ቀጠሮ ማክበር(አለማርፈድ) q Kutokuwako ኩቶኩዋኮ መቅረት q kuja ኩጃ - መምጣት


ሐበሻዊ ቃና

18

ፎቶ- መዝገቡ ኃይሉ

ትዝታ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ፎቶ- መዝገቡ ኃይሉ

አንድ ሺህ የሚጠጉ ባጋንዳውያን የተገደሉበትን ቀን ሜይ 24 ለማሰብ የባጋንዳ ብሔር አባላት በሀዘን ጊዜ እንደሚያደርጉት ሁሉ ከዛፍ ቅርፊት የተሰራ ልብስ ጭምር ለብሰው በካባካ ቤተመንግስት ተሰባስበው ነበር

ሐረር የተማሩት ሻለቃ አብርሃም ወደ ሀገራቸው ከተመለሱ ጊዜ ጀምሮ የካባካ የክብር ዘብ ሆነው በቤተመንግስት ውስጥ ይሰራሉ ባጋንዳዎች “ኦሉቢሪ ዋካባካ” እያሉ የሚጠሩት ነጩ የካባካ ቤተመንግስት ከእነ ግርማ ሞገስ በካምፓላ ሜንጎ ተንጣሎ ይገኛል

በመዝገቡ ኃይሉ በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

ምፓላ ሜንጎ የሚገኘው የባጋንዳ ብሔር ንጉስ (ካባካ) ነጭ ቤተመንግ ስት በተለምዶ የሚያረብ በት ጸጥታ ዛሬ የለም። ን ጉሳቸውን የወንዶች ሁሉ የበላይ (ሳባሳጃ) ብለው ለሚጠሩት ባጋንዳዎች ዛሬ የሀዘን ቀን ነው። ሜይ 24። በዚህ ቀን ነበር የቀድ ሞው የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሚልተን ኦቦቴ በባጋንዳ ታሪክ መዝገብ ላይ በሀዘን የሰፈረ ጭፍጨፋ ያከናወኑት። ከልጅ ል ጅ ለሚወራረሰው የባጋንዳ ንጉሳዊ ስርዓት ወደ ሃይማኖታዊ አምልኮ የሚጠጋ አመለ ካከት ያላቸው ባጋንዳውያን ከ45 ዓመት በፊት ያኔ ዙፋን ላይ የነበሩትን የአሁኑን ካ ባካ አባት ከሞት ለማዳን መስዋዕትነት የከ ፈሉበት ቀን ነው። አንድ ሺህ የሚጠጉ ባጋንዳውያን የተገደ ሉበትን ያን ቀን ለማሰብ የባጋንዳ ብሔር አባላት በባለ ግርማ ሞገሱ ነጭ ቤተመንግ ስት ተሰባስበዋል። በሀዘን ጊዜ እንደሚያደ ርጉት ሁሉ ከዛፍ ቅርፊት የተሰራ (ባርክ ክ ሎዝ) ልብስ ለብሰዋል። ቀኑን ለመዘከር በ ቤተመንግሥቱ ደጃፍ የተሰባሰቡት ሰልፈ ኞች የኀዘን ሙዚቃ በሚያሰሙ አዳጊዎች አጃቢነት በካምፓላ ጎዳናዎች ለመዘዋወር እስኪነሱ ድረስ ወደ ቤተመንግሥቱ ለመ ግባት የማይሞከር ነበር። ባጋንዳዎች “ኦሉ ቢሪ ዋካባካ” እያሉ የሚጠሩት ቤተመንግ ስት በር በሰዎች ታጥሯል። ከቤተመንግስቱ ቀጠሮ አለኝ። ቀጠሮዬ ጭፍጨፋው ሲካሄድ በቦታው ከነበሩ እና ካባካውን በህይወት ከአገር እንዲሸሹ በማ ድረግ ከፍተኛ ሚና ከተጫወቱ ሰው ጋር ነ ው። ሻለቃ አብርሃም ሳንኮማ ይባላሉ። የ

ከሐረር ጦር አካዳሚ ካባካው የክብር ዘብ አባል እንደነበሩ ተ ነግሮኛል። ታሪክ ለመስማት ጓጉቼያለሁ። በስተመጨረሻ ወደባለግርማው ግቢ ዘለቅ ሁ። ሻለቃ አብርሃም ወዳሉበት ክፍል ጠ ቆሙኝ። ከውጭ ቆሜ በር ስቆረቁር በባሕ ላችን እንግዳን ወደ ቤታችን እንዲገባ የም ንጋብዝበት አስደሳች ቃል ወደ እኔ ሲወረ ወር ሰማሁ። “ይግቡ! እንኳን ደኅና መጣ ህ”። ‘የሰማሁት የአማርኛ አረፍተ ነገር ነ ው አይደል?’ ራሴን ጠየቅሁ። በእርግጥም አማርኛ ነበር። የሻለቃ አብ ርሃም ጥርት ያለ አማርኛ ከቤተመንግሥ ቱ ላይ አልነቀል ላለው ቀልቤ ጥሩ ማባነ ኛ ነበር። ወደቢሯቸው ስገባ አንድ ሙዚ ቃ ይሰማኝ ነበር። ግን በቅጡ አላደመጥ ኩትም ነበር። ሻለቃ አብርሃም በመቀመ ጫቸው ላይ ራሳቸው ካመቻቹ በኋላ ወደ ሚወዘውዙበት ሙዚቃ አመላከቱኝ። “ም ነው ፊትህን አዙረህ ተቀመጥክ?” አሉኝ። ወይ ጉዴ! ለካንስ የሚያስደንቁ ነገሮች አ ላለቁም። የሻለቃ አብርሃም ኮምፒውተር የሚያጫ ውተውን ሙዚቃ አውቀዋለሁ። አረ! ማ ወቅም ብቻ አይደል። ስሰማው ተብረከረ ኩ። “አለምዬ ሶራ፤ ሶራ ሶራ!”። ‘የት ነው ያለሁት?’ ጥያቄዬ ቀጥሏል። ምንም አስገ ራሚ ነገር እንዳልተፈጠረ ሁላ ሻለቃ አብ ርሃም ያናግሩኝ ይዘዋል። አማርኛቸውን ስ ላላመኑት ይመስላል እንግሊዝኛ ጀምረዋ ል። የኮምፒዩተሩን ስክሪን የሞሉት ትከ ሻቸው እስክስታ የሚመታ ሳይሆን የሚ ርገብገብ የሚመስል ሰዎች በጣታቸው እ ያሳዩኝ “Look at this! This takes me back to Addis!” አሉኝ። አንገቴን በመ ስማማት ነቀነቅኩ። በስንቱ ተደንቄ እች

ላለሁ! ስለ ባጋንዳ ንጉስ የነበሩኝን ጥያቄዎች ለ ጊዜው ወደ ጎን አድርጌ ሻለቃ አብርሃም አ ንዴት እንዲህ ከኢትዮጵያ ጋር እንደተቆራ ኙ እንዲያጫውቱኝ ጠየቅኋቸው። ፊታቸ ው ላይ ደስታ እየተነበበ አመታት ወደ ኋ ላ ተመለሱ። ወደ ወጣትነታቸው ዘመን። ነገርን ከስሩ…..

ታሰርኩ እንዴ!” የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀው ወጣቱ አብርሃም በሁለት ምርጫዎች መ ካከል ልቡ ተከፍሏል። በአንድ በኩል እን ደማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ያጠናቀቀ ወጣት ማኬሬሬ ዩኒቨርሲቲ ገብ ቶ ትምህርቱን መቀጠል፤ በሌላ በኩል ደ ግሞ የንክሩማህን የአንዲት አፍሪካ (pan Africa) ሐሳብ በመቀበል አፍሪካን ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ለማውጣት በሚደረገው ትግል ውስጥ መሳተፍ እንደምርጫ ቀርበውለታ ል። አብርሃም የወጣትነት ልቡ ወደ ሁለ ተኛው አማራጭ አዘነበለ። የተባበረች አ ንዲት አፍሪካን እውን ለማድረግ እንደሚ ያስችል ባመነበት ትግል ለመሳተፍ ወሰነ። እዚህ ውሳኔ ላይ እንዲደርስ ያደረገው ደ ግሞ ናይሮቢ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤ ምባሲ የወጣ ማስታወቂያ ነበር። እ.ኤ.አ በ1959 የተላለፈው ይህ ማስታወቂያ በመ ላው አፍሪካ ለሚገኙ ወጣቶች የተሰጠ “የ ቀዳማዊ “ኃይለሥላሴ ስኮላርሺፕ” እድል ነበር። ከዚህ በፊት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ወታደራዊ ዩኒፎርም ለብሰው የተነሱትን ፎቶግራፍ ያየው አብርሃም ይህን የመሰለ እድል በቅኝ አገዛዝ በተያዙት ሌሎች የአፍ ሪካ አገሮች እንደማይሞከር ያውቅ ነበር። አንድ ጥቁር ወታደራዊ የማዕረግ ልብስ መ

ልበስ እንኳ የሚችልባት ብቸኛዋ የአፍሪ ካ አገር ኢትዮጵያ ነበረች። ልቡ ተሸነፈ። ናይሮቢ ወደሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባ ሲ አቀና። በወቅቱ በናይሮቢ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩትን አቶ ጌታቸው መካሻ ን አግኝቶ ያለውን ፍላጎት ገለጸ። በተመሳ ሳይ ኹኔታ ጥሪውን ተቀብለው የመጡ አ ፍሪካውያን ወጣቶች በዚያ ነበሩ። ወጣቶ ቹ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከጋና፣ ከናይጄሪያ እ ና ከኡጋንዳ የተውጣጡ ነበሩ። የመግቢያ ፈተና ወስደው ካለፉ በኋላ ወደ አዲስ አበ ባ እንዲሔዱ ተነገራቸው። እ.ኤ.አ ጥር 1960 አዲስ አበባ እንደደረ ሱም በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በአ ቶ ከተማ ይፍሩ የሚመራ አንድ ቡድን ቃ ለመጠይቅ አደረገላቸው። በኢትዮጵያ ሊ ያገኟቸው የሚችሏቸውንም የትምህርት እ ድሎች ጨምረው ነገሯቸው። “ምን መማ ር ትፈልጋለህ?” የሚለው ጥያቄ አንዱ ነበ ር። አብረዋቸው የነበሩትን ወጣቶች ምኞ ት እውን ያደረገችው ኢትዮጵያ አብርሃም ንም ምኞቱን አልነፈገችውም። ከሁሉ በላ ይ ወጣቱን አብርሃም ያስደነቀው የምላሹ ፍጥነት ነበር። አብረዋቸው ከነበሩት የእድሉ አሸናፊዎ ች መካከል አንዱ ሕክምና አንዱ አውሮፕ ላን አብራሪነት እንደመረጡ ወዲያው ወደ ሚመለከታቸው ትምህርት ቤቶች ተላኩ። “እኔ ወታደራዊ ሳይንስ መማር እንደምፈ ልግ ስናገር ይህን ትምህርት ለምን እንደመ ረጥኩ ተጠይቄ ነበር” የሚሉት ሻለቃ አብ ርሃም ለጥያቄው የሰጡትንም ምላሽ ያስታ ውሳሉ። “አፍሪካን ነፃ ለማውጣት!” ነበረ ምላሻቸው። “ብዙም ሳይቆይ ያለንበት ድ ረስ በወታደራዊ አለባበስ የተንቆጠቆጡት

ጄኔራል ገብረሥላሴ ያሉበት የወታደር ጂ ፕ መኪና መጣ” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም መጀመሪያ የተፈጠረባቸውን ስሜትም ያስ ታውሳሉ። “ምን ተፈጠረ ታሰርኩ እንዴ!” የሚል ድንጋጤ እንደተሰማቸውም ሲያስ ታውሱ ፈገግ ይላሉ።

እነኛ የአደሬ ሴቶች… ሻለቃ አብርሃም እንደ እርሳቸው ሁሉ ከ ተመለመሉ 49 ተማሪዎች ጋር በመኾን ወ ደ ሐረር ለመጓዝ የ60 የኢትዮጵያ ዶላር ተቀበሉ። ያኔ የኢትዮጵያ ገንዘብ እንዳሁ ኑ ብር ሳይሆን ዶላር ነበር። ወደ ሐረር አ ብረዋቸው ይጓዙ የነበሩት ተማሪዎች ምን ሲሉዋቸው እንደነበረም ያስታውሳሉ። “ከ የት ነው ደግሞ አንተ የመጣኸው? ለምን አገርህ አትማርም ነበር? እዚህ አገር ወታ ደር ኾነህ መሞት ትፈልጋለህ?” ከየአቅጣ ጫው የሚወረወሩ ጥያቄዎች ነበሩ። የአብ ርሃም ኹኔታ ለሌሎቹ የሐረር የጦር አካዳ ሚ ምልምሎችም ጥያቄ የፈጠረ ነበር። በ ጦር አካዳሚ ወታደራዊ ስልጠና ለመውሰ ድ ከሚሄዱ ምልምሎች መካከል ከእናቶ ቻቸው ተላቅሰው የተለያዩ ነበሩ። ይህ ሁ ኔታ አሁንም ድረስ ለሻለቃ አብርሃም ግር ምትን እንደፈጠረባቸው አለ። እርሳቸው የገቡበት ኮርስ ሶስተኛው ዙር ቢሆንም ሐረር የጦር አካዳሚ በነበሩ ጊዜ ግን ቀድመዋቸው ከገቡት የአንደኛ እና የ ሁለተኛ ኮርስ ተማሪዎች ጋር አብሮ የመቆ የት እድል ገጥሟቸው ነበር። በወቅቱ አስ ተማሪ የነበሩት ደግሞ ህንዳውያን እና የ ሆለታ ገነት ምሩቅ ኢትዮጵያውያን መኮን ኖች ነበሩ። “ስልጠናው እጅግ ደስ የሚያ ሰኝ ነበር” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም ትም ህርቱ በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ቋንቋዎ

ች ይሰጥ ስለነበር አስቸጋሪ እንዳልሆነባቸ ው ያስረዳሉ። ምንም እንኳን አብረዋቸው የቆዩት ስድ ስት ወር ብቻ ቢኾንም ከመካከላቸው ጄ ኔራል አበበን እና ጄኔራል ሙሉጌታን ያስ ታውሳሉ። በሁለተኛው ምድብ ከገቡት እ ጩ መኮንኖች መካከል በኋላ በመንግሥ ት ሥልጣን ላይ ከነበሩት መካከል፤ ጎሹ ወ ልዴን፣ ፍሰሐ ደስታን ከነበራቸው ቅርር ብ ጭምር ያስታውሷቸዋል። “ጎሹ የቅርብ ጓደኛዬ ነበር፣ ፍሰሐን የማስታውሰው ባስ ተማረኝ ጥቂት የትግርኛ ቃላት ነው” ይሉ ና ቃላቱን ያስታውሳሉ “ከመይለኻ፣ ጽቡ ቅ…”። ብርሃኑ ባየህንም “በመጠኑ ኩሩ ጎን ደሬ ነበረ” እያሉ ትዝታቸውን ያካፍላሉ። ሻለቃ አብርሃም የተማሩባትን ሐረርን በ ጣም እንደወደዷት ይናገራሉ። ሐረርን ለ ምን እንደወደዷት ሲናገሩ የድምፃቸው ከ ፍታ ይጨምራል። “አየሩ ተስማሚ ነው፣ የሴቶቹ ውበት!። እነኛ የአደሬ ሴቶች በጣ ም ውብ ነበሩ። ቋንቋ ባያግደኝ ኖሮ እንዴ ት ጥሩ ነበር! በዚያ ላይ ጥሩ የፍራፍሬ አገ ር ነበር” እያሉ ምክንያቶችን ይደረድራሉ።

ኡጋንዳዊው በጎጃም ስልጠናቸውን በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ ያጠናቀቁት ሻለቃ አብርሃም ከምረቃው በ ኋላ ፈተና ገጠማቸው። በወቅቱ ኡጋንዳ ገ ና ከቅኝ አገዛዝ ነፃ ያልወጣች በመኾኗ ወ ደ አገራቸው መመለስ እንደማይችሉ ታወ ቃቸው። ይህንን የሚያውቁት ብዙዎቹ ጓ ደኞቻቸውም እዚያው በኢትዮጵያ እንዲ ቀሩ መከሯቸው። “ዩጋንዳ በቅርቡ ነፃ ት ወጣለች። እስከዚያው ድረስ እዚህ ቆይ” የወዳጆቻቸው ምክር ነበር። ምክሩን ሰም ተው ኢትዮጵያ ቀሩ። እንደሌሎቹ ምሩቃ


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

19

ትዝታ

ሻለቃ አብርሃም ከአገራቸው ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ በተመለሱ ወቅት በጃንሆይ አማካኝነት በተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት የደህንነት ሰራተኛ ሆነው ተቀጥረው ነበር

ፎቶዎች- ከሻለቃ አብርሃም ስብስቦች

ፎቶ- መዝገቡ ኃይሉ

ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ በካባካ ሙቴሳ በዓለ ሲመት ላይ በክብር እንግድነት ሲገኙ የመቶ አለቃ አብርሃንም አስከትለው ነበር

ወጣቱ አብርሃም የሐረር ጦር አካዳሚ ካፈራቸው ወታደራዊ መኮንኖች አንዱ ነው

ከሻለቃ አብርሃም ጋር በሐረር ጦር አካዳሚ ከተማሩት መካከል እንደ ብርሃኑ ባየህ ያሉት (በፎቶው መነጽር ያደረጉት) በስተኋላ ላይ የመንግስት ባለስልጣን ሆነዋል

እስከ ካባካ ቤተመንግሥት ን ሁሉ እርሳቸውም ምድብ ክፍል እና ደ ሞዝ ተቆረጠላቸው። ያስተማረቻቸውን ኢትዮጵያን በውትድርና ለማገልገል ጎጃም ሁለተኛ ክፍለ ጦር ውስጥ በአሰልጣኝ መ ኮንንነት ተመደቡ። “ብዙም አማርኛ ስለማልችል የማሰለጥነ ው ሰልፍ ነበር” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። “ለሰልፍ እና ለስፖርት ስልጠና የሚኾኑ ትን የአማርኛ ቃላት በደምብ ስለማውቃ ቸው በቀላሉ ነበር ሥራውን የለመድኩ ት” ይላሉ። አሁንም እነዚህኑ የትእዛዝ ቃ ላት ከነቅላፄያቸው በደምብ ያስታውሷ ቸዋል። “አሳርፍ! ተጠንቀቅ! ወደፊት ሒ ድ!”። እዚያው ጎጃም እያሉ ነበር የህይወ ታቸውን የወደፊት አቅጣጫ የሚወስን መ ልዕክት የደረሳቸው። “በዚሁ ምድብ ሥራዬ ላይ እንዳለሁ አን ድ ቀን በሄሊኮፕተር የመጡ ክቡር ዘበኞች በአስቸኳይ አስጠሩኝ” የሚሉት ሻለቃ አብ ርሃም፤ በአስቸኳይ ጃንሆይ ቤተ መንግሥ ት እንዲደርሱ የተጠሩበትን ሁኔታ ይተር ካሉ። “የማእረግ ልብሴን እንደለበስኩ ወ ደ ሄሊኮፕተር ስጣደፍ አንዳንዶቹ ጓደኞ ቼ ለሹመት ልጠራ ለፍርድ ስላልገባቸው በጥያቄ ያጣድፉኝ ጀመር። አንዳንዶቹ ‘ም ን አድርገህ ነው?’ ሲሉኝ ሌሎቹ ደግሞ ‘ከ ተሾምክ እንዳትረሳን’ ይሉኝ ነበር።” አራት ኪሎ ቤተመንግሥት ሲደርሱ ያልጠረጠሩ ት ነገር ገጠማቸው። ጃንሆይ ብቻቸውን አልነበሩም። የባጋንዳ ው ሥርወ መንግሥት የወቅቱ ንጉሥ ካባ ካ ሙቴሳም አብረዋቸው ተቀምጠው ነበ ር። “ካባካው በሉጋንዳ ስሜን እና ጎሳዬን ጠየቁኝ” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። በኋላ እ ንደሰሙት የእርሳቸውን እዚያ መኖር አን

ድ ሰው ተናግሮ ስለነበረ ይህን ለማጣራ ት ነበር የተጠሩት። “ካባካው ከመደነቃቸ ው በላይ ጥርጣሬም የነበራቸው ይመስላ ል” ይላሉ ሻለቃ። “ምክንያቱም ካባካው እኔ በእንግሊዝ የተላኩ ሰላይ አለመኾኔን ም ለማጣራት ጥያቄዎች ይጠየቁኝ ነበር።” ካባካው ሻለቃ አብርሃምን ጥቂት የፈተ ነ ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር። ጥያቄው “ተመልሰህ አገርህን ለማገልገል ፈቃደኛ ነህ ወይ?” የሚል ነበር። “ደሞዝ ሳልቀበ ል፣ እንዲያው ሳልዘጋጅ ይዘውኝ ሊሄዱ ነ ው?” ብለው ሀሳብ ቢገባቸውም ያለማቅ ማማት መልስ ሰጡ። “እንዴታ ካባካ ምን ገዶኝ!”። የውስጣቸውን በውስጣቸው እን ደያዙ የሰጡት መልስ ነበር። የያኔው የመቶ አለቃ የአሁኑ ሻለቃ አብ ርሃም እንደፈሩት ያኔውኑ ወደ ኡጋንዳ አ ልተመለሱም። በአንድ ቀጭን ትእዛዝ ወ ደመጡበት ክፍላቸው እንዲመለሱ ተደረ ገ። “የመቶ አለቃ አብርሃምን ወደክፍላቸ ው መልሷቸው!”። ነገር ግን አንድ ተስፋ ከ ካባካው ተሰጥቷቸው ነበር። “ከነፃነት በኋ ላ እንጠራህና ወደአገርህ ትመጣለህ”። የ ማይታጠፈው የካባካ ሙቴሳ ቃል ነበር፤ ከባለ ግርማው የአራት ኪሎው ቤተ መን ግሥት።

የጃንሆይ “አጃቢ” እ.ኤ.አ በጥቅምት 1962 ዩጋንዳም ቀን ወ ጣላት። በገዛ ልጇ በካባካ ሙቴሳ ፕሬዚዳ ንትነት እንድትመራ ተደርጋ ከእንግሊዝ ቅ ኝ አገዛዝ ነፃ ወጣች። በንጉሡም በዓለ ሲ መት ላይ እንዲገኙ በክብር እንግድነት የ ተጠሩት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴም በባለሥ ልጣኖቻቸው አጃቢነት ወደ ኡጋንዳ ሊሄ ዱ ተነሱ። ጃንሆይ ወደ ኡጋንዳ ሲመጡ

የመቶ አለቃ አብርሃንም አልረሷቸውም። “ከንጉሡ ባለሥልጣኖች ጋር በአንድ አ ውሮፕላን በርረን ኡጋንዳ ደረስን” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም በኩራት። የዚያን ጊዜው ደስታቸው ከፊታቸው ላይ ይታያል። ኃይ ለሥላሴን አጅበው መምጣታቸውን እስ ካሁንም በኩራት ይናገሩታል። “እንደመ ጣን ያረፍነው አሁን ፓርክ ሆቴል ተብ ሎ በሚታወቀው የያኔው ሮያል ሆቴል ነ በር” የሚሉት ሻለቃ አብርሃም እንዴት ቤ ተሰቦቻቸውን እንዳገኙ ሲተርኩም በተመ ስጦ ነው። “ቀዳማዊ ኀይለሥላሴን አጅቤ በበዓለ ሲ መቱ ላይ ስገኝ የብዙ ኡጋንዳውያን ቀልብ በእኔ ላይ አርፎ ነበር” ይላሉ አብርሃም። በ ቦታው ከነበሩት ሰዎች መካከልም አንድ ሰ ው ወደ እርሳቸው መጥቶ “አንተ ሳንኮማ አይደለህም እንዴ?” ሲል እንዳስታወሳቸ ው ይገልጽላቸዋል። “ያም ሰው የእኔን መ ምጣት ለመንደሬ ሰዎች ሁሉ አዳረሰው” ይላሉ ሻለቃ። ብዙም ሳይቆዩ ከካባካው ፈቃድ ተቀብለው ለረጅም ጊዜ የተለዩዋ ቸውን ቤተሰቦቻቸውን የማየት እድል አገ ኙ:፡ “ካባካው ቀድመው የጠየቁኝን ጥያቄ በድጋሚ ያቀረቡልኝም ከዚያ በኋላ ነበር” ሲሉ የእናት አገራቸው ጥሪ እንዴት እንደ ደረሳቸው ያስታውሳሉ። ካባካው “እኛ አሁን የምታገኘውን ያህ ል ደሞዝ ልንከፍልህ አንችልም። መጥተ ህ ግን አገርህን እንድታገለግል እንፈልጋለ ን” ይሏቸዋል። አብርሃም በካባካው ንግ ግር ስሜታቸው ተነካ። እምቢ ሊሉት የ ማይችሉት ጥያቄ ነበር። ነገር ግን አንድ ቅድመ ሁኔታ አቀረቡ። “አሁን ድንገት ነ ው ተጠርቼ የመጣሁት። ተመልሼ እንድ

ሄድ እና ተዘጋጅቼ እንድመጣ ይፈቀድል ኝ” አሉ። ተፈቀደላቸው። የመልስ ጉዞ ወ ደ ኢትዮጵያ፤ ለማይቀረው የእናት አገር ጥ ሪ ዝግጅት!

አተረፈላቸው። ካባካውን ካስመለጡበት ኬንያ ታስረው በኡጋንዳውያን ፖሊሶች ተ መረመሩ። ለካባካው ታማኝ የነበሩት ሻለ ቃ አብርሃም ግን ምንም ትንፍሽ አላሉም።

የቁርጥ ቀን

“ጆሮ ጠቢ ኾንኩ!”

ኢትዮጵያን ተሰናብተው ወደ ኡጋንዳ የ መጡት ሻለቃ አብርሃም በካባካው የክብ ር ዘብ ውስጥ ተመደቡ። ለአራት ዓመት ካባካውን በታማኝነት እንዳገለገሉ ፈታኙ የቁርጥ ቀን መጣ። የካባካውን እውነተኛ ሰው ማንነት የሚፈትነው ችግር! አብርሃ ም ሳንኮማም ፈተናውን በቆራጥነት ለማለ ፍ ወደ ኋላ አላሉም። ህይወታቸውን እስ ከ መሥዋዕትነት በመሥጠት ፕሬዚዳንታ ቸው እና ንጉሣቸው የጣሉባቸው እምነት ትክክለኛ መኾኑን አስመሰከሩ። ነገሩ እንዲህ ነው። በወቅቱ ጠቅላይ ሚኒ ስትር የነበሩት ሚልተን ኦቦቴ ከፕሬዚዳን ቱ ካባካ ሙቴሳ ጋር የነበራቸው አለመግ ባባት ጦዞ ወደ መበጠሱ ደረሰ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉዳዩን በኃይል ለመፍታት ሞከ ሩ። እ.ኤ.አ ሜይ 24 ቀን 1966ም ወታደ ሮችን ወደ ንጉሡ ቤተ መንግሥት በመላ ክ ድንገተኛ ጥቃት ከፈቱ። የንጉሡ የክብ ር ዘቦች ጥቃቱን በመከላከል ንጉሡን ለማ ትረፍ የተቻላቸውን ሁሉ አደረጉ። ሻለቃ አብርሃም ከእነዚህ መካከል አንዱ ነበሩ። ሻለቃ አብርሃም በወቅቱ የነበራቸው ሚ ና ንጉሡን በስውር በር በማስወጣት በ“ና ሚሬምቤ” የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ውስ ጥ መደበቅ ድረስ ይሄዳል። በኋላም በጀል ባ ወደ ሞምባሳ እንዲያመልጡ አስተዋጽኦ አድርገዋል። ይህ ጀብዱ በህይወታቸው ከ ሚኮሩባቸው ተልዕኮዎች ቁንጮው ሳይሆ ን አይቀርም። ሆኖም ጀብዷቸው እስርን

ከእስር እንደተፈቱ በወቅቱ ለደህንነታቸ ው አስጊ ከነበረችው ከአገራቸው ከኡጋን ዳ ይልቅ ወደ ሁለተኛ ቤታቸው ወደ ኢ ትዮጵያ ፊታቸውን አዞሩ። “ወደጃንሆይም ቀርቤ ወደ እናት ክፍሌ እንዲመልሱኝ ጥያ ቄ አቀረብኩ” ይላሉ ሻለቃ አብርሃም። ጥ ያቄአቸው ግን አዎንታዊ ምላሽ አላገኘም። ምክንያቱም ከሻለቃ አብርሃም የተሰወረ አ ልነበረም። “ፋይሌ ተዘግቶ አልተሰናበትኩ ም” እያሉ መከራከሪያ ቢያቀርቡም ጉዳዩ ለጃንሆይ ቀላል አልነበረም። “ጃንሆይ በእኔ ምክንያት ከኡጋንዳ መንግ ሥት ጋር መቃረን አልፈለጉም ነበር” ይላ ሉ አብርሃም። ግን ጃንሆይ ጥለው አልጣ ሏቸውም። “ይህ የእኛ ሰው ነው በማለት በተባበሩት መንግስታት ጽሕፈት ቤት ው ስጥ በደህንነት ሰራተኝነት እንድቀጠር አደ ረጉኝ” ሲሉ የጃንሆይን ገለታ ያወሳሉ። “በ እርግጥም አማርኛ ማወቄ ሥራውን በቀላ ሉ እንድሰራው ረድቶኛል” ይላሉ አብርሃ ም አስቂኙን የአማርኛ የደህንነት ስም እያ ስታወሱ። “ጆሮ ጠቢ ኾንኩ!”። በዚህ ዙር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵ ያ ቤት ንብረት እንዲያፈሩ አድርጋቸዋለ ች። ከዚያም ከፍ ባለ ኢትዮጵያዊት ሚስ ትም አግኝተዋል። የሻለቃ አብርሃም ባለቤ ት ወይዘሮ መሠረት ገብረጻድቅ ይባላሉ። እ.ኤ.አ ከ1978 ጀምሮ ተጋብተው እስካሁ ንም በትዳር ዓለም አብረው አሉ። ይህም ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ያጠናከ

ሩበት ሌላው ማሰሪያ ነበር። ከባለቤታቸውም ሁለት ልጆች የወለዱ ሲ ኾን የመጀመሪያ ልጃቸው የዩኒቨርሲቲ ሁ ለተኛ ዓመት ተማሪ ነች። ልጆቻቸው አማ ርኛን አቀላጥፈው እንደሚናገሩ የሚገልጹ ት ሻለቃ አብርሃም በዚህም ምክንአት አን ዳንድ ጊዜ ሚስጥር እንደሚያልፋቸው ይ ናገራሉ። “ ‘እናንተ ቅድም ምንድነው ለ እናታችሁ የነገራችኋት’ እያልኩ ስቆጣ ሁ ሉም ይስቁብኛል” እያሉ እርሳቸውም ይ ስቃሉ። ሻለቃ አብርሃም አዲስ አበባ ገርጂ አካባ ቢ ቤት እንዳላቸው ይናገራሉ። “አቤት አ ሁንኮ ሰፈሩ ሁሉ ተቀይሯል!” እያሉ ያፏ ጫሉ የትውልድ ቀዬአቸውን እንደሚያስ ታውሱ ሁሉ። ቤት የሰሩበትን ቦታ የገዙበ ትን ገንዘብ ትንሽነት ያደንቃሉ። “45 ሺህ ብር! አሁን በዚህ ዋጋ መሬት ማግኘት የ ማይታሰብ ነው።” ሻለቃ አብርሃም የሁለተኛ አገራቸው ትዝ ታ የሚወዘውዛቸው ዓይነት ናቸው። “አ ብረውኝ የሰለጠኑት ጓደኞቼም አዛዦቼም ወደ ኡጋንዳ ስመጣ ደጋግመው የነገሩኝ አ ንድ ነገር ነበር ‘ኢትዮጵያ አገርህ ናት። ኢ ትዮጵያን እንዳትረሳ‘ ብለውኝ ነበር” ይላ ሉ። ሻለቃ አብርሃም ምላሻቸው ጥያቄም መልስም ነበር። “ኢትዮጵያን እንዴት እረ ሳታለሁ?!”። በእርግጥም አልረሷትም። ከሶስት ዓመት በፊት ገበያ ላይ የዋለው የገጠሪቱ ኢትዮጵ ያን ዘፈን እያደመጡ በሀሳብ ይነጉዳሉ። ሻ ለቃውን ተሰናብቼያቸው ወጣሁ። “አለም ዬ ሶራ!” እየሸኘኝ ነበር። በ“ባሲማ ኡጌን ዜ” ፋንታ “አለምየ ሶራ”! ለዚያውም በካባ ካው ቤተ መንግሥት!


ሐበሻዊ ቃና

20

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ሐበሻ በምስራቅ አፍሪካውያን ዓይን ጋታንጋ አሌክስ በጎ ፈቃደኛ የማህበራዊ አገልግሎት ሰራተኛ ነው፡፡ የዛሬ መኖሪያ ው ካምፓላ ይሁን እንጂ ትውልዱ ምዕራ ብ ኡጋንዳ ከሚገኝውና ኪሶሮ ከሚባለው ስፍራ ነው፡፡ ይህም ቢሆን አሌክስና እናት አባቶቹ የተወለዱበት እንጂ የአያት ቅደመ አያቶቹ እትብት የተቀበረበት ቦታ እንዳል ሆነ አሌክስ ይናገራል፡፡ አሌክስ የአያት ቅ ደመ አያቶቹን መነሻ ሲያስብ ትዝ የምትለ ው ኢትዮጵያ ነች፡፡ እርሱ ሩዋንዳውያንም ሆኑ ኡጋንዳውያን (በተለይ ዛሬ በምዕራቡ ክፍል የሚገኙት) ምንጫቸው ኢትዮጵያ ነ ው ብሎ ያምናል፡፡ ‹‹እንደሚባለው ቅድመ አያቶቼ የመጡት ከሁለት ሀገር ነው፡፡ ከኢትዮጵያና ከሶማ ሊያ፡፡ ከዚያም ወደታች ወረዱና ሩዋንዳ ገቡ፡፡ ሩዋንዳ ከገቡ በኋላ ደግሞ ወደ ኡ ጋንዳ ቀጠሉ›› ይላል፡፡ እንደ አሌክስ ግም ት ይህ ፍልሰት የተከሰተው በ18ኛው ክፍ ለ ዘመን ነው፡፡ አሌክስ እንደ ብዙዎች የዛሬ ምስራቅ አ ፍሪካ ኑዋሪዎች ሁሉ የመጣሁት ከኢትዮ ጵያና ከሶማሊያ ምድር ነው ለሚለው ታ ሪክ እውነትነት የሚጠቅሳቸው ምክንያቶ ች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል በተለይ ቱት ሲ በሚባሉት የሩዋንዳ ጎሳ አባላት፤ በምዕ ራብ ኡጋንዳ በሚገኙት በተለይ ባንኛኮሌ እና በኢትዮጵያውያን መካከል ያለውን የ መልክና የአኗኗር ዘይቤ መመሳሰል ነው፡፡ ‹‹በታሪኩ እውነትነት አምናለሁ ምክንያቱ ም የአኗኗር ሁኔታቸውንም ሆነ የሚያደር ጉትንና መልካቸውን ስትመለከት እኔ የመ ጣሁበት እና ኢትዮጵያውያን በእጅጉ ይ መሳሰላሉ፡፡ ለምሳሌ ከሶማሊያ የሚዋሰኑ ት ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያን በብ ዛት የሚተዳደሩት በከብት እርባታ ነው፡ ፡ ሩዋንዳዎችንና ምዕራብ ኡጋንዳዎችን ስ ትመልከት በብዛት የሚተዳደሩት በዚሁ በ ከብት እርባታ ነው፡፡ ሁለቱም እንስሳት ያ ረባሉ፡፡ ይህ ሁሉ አንድነት የመጣው ከደ ማቸው መመሳሰል ጋር ተያይዞ ነው›› ብሏ ል የሀሳቡን እውነትነት ለማስደገፍ በጠቀ ሰው ምሳሌ፡፡

ደማችን አንድ ነው እንደ አሌክስ ሁሉ ትውልዴ ከፕሬዚዳን ት ሙሴቬኒ የትውልድ መንደር ምዕራብ ኡጋንዳ ምባራራ ነው የሚለው ፕሪንስ ሪ ቻርድ “የዛሬዎቹ የምስራቅ አፍሪካ ነዋሪዎ ች የዘር ሀረጋቸው የሚመዘዘው ከቀድሞ ዋ ኢትዮጵያ ነው” ባይ ነው፡፡ ‹‹ከኢትዮ ጵያ ተነስተው በቱርካና ሀይቅ አቋርጠው ምዕራብ ኡጋንዳ ከዚያም ሩዋንዳና ብሩን ዲ ተበትነዋል›› ይላል የዛሬዎቹን የሶስቱ ሀ ገራት (ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ እና ቡሩንዲ) መነ ሻ ሲያብራራ፡፡ ‹‹እኔ ኡጋንዳውያን የመጡት ከኢትዮጵያ መሆኑን አውቃለሁ፡፡ ለዚህም ነው የኡጋ ንዳ መንግስት ለእነሱ አብዝቶ የሚጨነቀ ው፡፡ ኢትዮጵያውያንና ሶማሊያውያንም ደማቸው አንድ ነው፡፡ መጽሃፍትን ብታገ ላብጥ ኡጋንዳ ለሶማሊያውያንም ሆነ ለኢ ትዮጵያውያን ብዙ ነገር እንዳደረገች ትመ ለከታለህ፡፡ በጥቅሉ በምስራቅ አፍሪካ አካ ባቢ ሀገራት ያለነው ህዝቦች እንዲህ የምን ተባበረው የሁላችንም ደም አንድ በመሆ ኑ ነው፡፡ የዚህ ሁሉ ምንጩ ደግሞ ኢትዮ ጵያ ናት›› ሲል የዛሬው የአካባቢው ሀገራ ት ትብብር ከፖለቲካ ይልቅ በደም የተሳሰ

የዘር ግንድ ሲቆጠር ፎቶዎች- በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

በኡጋንዳ የሐበሻዊ ቃና ዘጋቢ

ጋታንጋ አሌክስ እንደ ብዙዎች የዛሬ ምስራቅ አፍሪካ ኑዋሪዎች ሁሉ የመጣሁት ከኢትዮጵያ ነው የሚል እምነት አለው

ረ ነው የሚለውን መከራከሪያ ያቀርባል፡፡ ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ ወደ ኢትዮጵ ያ በመሄድ እውነታውን በአይኔ ተመልክቼ አረጋግጫለሁ የሚለው ሪቻርድ በመልክ ና በቁመናም ቢሆን እነዚህ ህዝቦች ተመ ሳሳይነት እንዳላቸው ይገልጻል፡፡ ‹‹ዝም ብ ለህ ከምዕራብ ኡጋንዳ አንድ ሰው ከሩዋን ዳ ኪጋሊ ሌላ አንድ ሰው ውሰድና ከአን ድ ኢትዮጵያዊ ጋር አወዳድረው፡፡ ምን ያ ህል ተመሳሳይነት እንዳላቸው ታረጋግጣለ ህ›› ብሏል፡፡ የታሪክ ምሁራን ግን ምስራቅ አፍሪካውያ ን የዘር ግንዳቸው ከኢትዮጵያ ነው በሚለ ው እንደ አሌክስና ሪቻርድ በአንድ ወገን አ ይሰለፉም፡፡ ገሚሶቹ በሀሳቡ ሲስማሙ ሌ ሎች ደግሞ መሰረተ ቢስ መላምት ነው እ ስከማለት ይደርሳሉ፡፡

ቱትሲዎች ማናቸው? የእንግሊዙ አለም አቀፍ የዜና ማሰራጫ ቢቢሲ በአንድ ወቅት የሩዋንዳን ጅምላ ጭፍጨፋ በተመለከተ ዜና ሲጽፍ የሚከ ተለውን አስፍሮ ነበር፡፡ ‹‹ …በእርግጥ ሁለቱ ጎሳዎች (ሁቱና ቱት ሲ) በጣም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ አንድ አይ ነት ቋንቋ ይናገራሉ፡፡ በአንድ አካባቢ ይኖ ራሉ፡፡ ተመሳሳይ ባህል ይከተላሉ፡፡ ይሁን እንጂ ቱትሲዎች ከሁቱዎች ይልቅ ቀጠን እ ና ረዘም ያሉ ናቸው፡፡ አንዳንዶች እንደሚ ሉት የእነዚህ (ቱትሲዎች) የዘር ግንዳቸው የሚመዘዘው ከኢትዮጵያ ነው፡፡ በጅምላ ጭፍጨፋው ወቅት የቱትሲዎች አስከሬን በገዳዮቻቸው ወደ ወንዝ ይጣል ነበር፡፡ ገ ዳዮች ይህን በሚያደርጉበት ወቅት ወንዙ ቱትሲዎችን ወደመጡበት ኢትዮጵያ መል ሶ ይውሰዳቸው እያሉ ነበር..›› የተወሰኑ የታሪክ ምሁራን ያሰፈሩት መረ ጃ እንደሚጠቁመው የዚህ የቢቢሲ ጽሁፍ መነሻ ታሪክ ዓመታትን ወደኋላ የሚያሻግ ር ነው፡፡ ኢሪዊን ኤም በርግ የተባለ በኒው

ዮርክ የህግ ባለሙያ ፕሮፌሰር ዮቻናን ብ ዌጄሪ ነገሩኝ ብሎ እንደጻፈው የቱትሲ ህዝ ቦች መገኛቸው ኢትዮጵያ ነው፡፡ ራሳቸው ፕሮፌሰር ብዌጄሪ የሩዋንዳው ቱትሲ ህዝ ቦች “ቤኔ ግዌ” ጎሳ አባል መሆናቸውን የህ ግ ባለሙያው ጽፏል፡፡ በትውልድም አይ ሁድ መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ እሳቸው እ ንደሚሉት እ.ኤ.አ በ1270 የአይሁድ አገዛ ዝ ሲፈረካከስ “ቤኔ ዛግዌ”ን ጨምሮ በር ካታ ጎሳዎች ተፈጠሩ፡፡ እነዚህም ብዌጄሪ “ሀቪላ” ብለው ወደሚጠሯቸው ወደ ታላ ላቅ ሀይቆች አካባቢ ማለትም ወደ ብሩን ዲ፣ ሩዋንዳ፣ የኡጋንዳ የተወሰኑ አካባቢዎ ች፣ ታንዛኒያ እና ኮንጎ ተጓዙ፡፡ እነዚህ ጎሳዎች ከ 1270 እስከ 1527 የዘለ ቀና የደቡብ ኩሸቲክ የተባለ ግዛት እንደገ ና አቋቁመው ነበር፡፡ በ1880 መጀመሪያ አ ካባቢ የካቶሊክ ሚሲዮኖች ወደዚህ አካባ ቢ መጡ፡፡ በዚህ ወቅት ከቱትሲ እምነት በስተቀር በሌላ አናምንም ባሉ ቱትሲ ህዝ ቦችና በካቶሊክ ሚሲዮኖች መካከል ግጭ ት ተቀሰቀሰ፡፡ ይህም እስከ ሃያኛው ክፍለ ዘመን የዘለቀ ነበር፡፡ ይህንን ተከትሎ የጀር መን ሀይል ግዛቱን ሲቆጣጠር በወቅቱ የነ በረው ወታደራዊ ኃይል ድጋፉን ለሚሲዮ ኖች አደረገ፡፡ ሚሲዮኖችም የካቶሊክን እ ምነት ለማስፋፋት ከቱትሲዎች እምቢተኝ ነት የገጠማቸውን ያህል በሁቱዎች ተቀባ ይነት በማግኘታቸው በሁቱዎች ላይ ብ ቻ ድልን ተቀዳጁ ይላሉ ፕሮፌሰር ብዌጄ ሪ፡፡ ይህንን ተከትሎም የቱትሲዎች መሬት እየተቀማ ለሁቱዎች ተሰጣቸው፡፡ እንደጸ ሐፊው አባባል በዚህ የተጀመረው ግጭት ነው በኋላ ላይ ወደ ጅምላ ጭፍጨፋ የተ ሸጋገረው፡፡

እውነት የነበረ ቅዠት ወይስ..? እሳቸው ይህን ይበሉ እንጂ በኡጋንዳ ማ ኬሬሬ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ክፍለ ትምህርት ኃላፊውና የታሪክ ሊቁ ዶክተር አሲምዌ ጎ

የማኬሬሬ ዩኒቨርስቲው ዶክተር ጎድፍሬይ ግን ኡጋንዳውያንም ሆኑ ምስራቅ አፍሪካውያን የዘር ግንዳቸው ኢትዮጵያ ነው የሚለውን ሀሳብ ‹‹የነጮች ጭንቅላት የወለደው›› ሲሉ ያጣጥሉታል

ድፍሬይ ግን ኡጋንዳውያንም ሆኑ ምስራ ቅ አፍሪካውያን የዘር ግንዳቸው ኢትዮጵ ያ ነው የሚለውን ሀሳብ ‹‹የነጮች ጭንቅላ ት የወለደው መሰረት የለሽ መላምት›› ሲሉ ያጣጥሉታል፡፡ ቱትሲዎች የመጡት ከኢትዮጵያ ነው የ ሚለውን የጸሀፊዎችን መከራከሪያም አው ሮፓውያን አፍሪካውያንን ለመከፋፈል ከተ ጠቀሙበት ስልት እንደ አንዱ የሚወሰድ እንጂ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ክ ስተት አለመሆኑን ይገልጻሉ፡፡ እንደ ዶክተ ር ጎድፍሬይ የመከራከሪያ ሀሳብ ቤልጂየሞ ች በእምነት ሰበብ ወደ ሩዋንዳ በመጡ ጊ ዜ ህዝቦችን ለመከፋፈል ቀጥ ያለ አፍንጫ እና ረጅም ቁመት ያላቸውን መርጠው ለ ብቻ በማድረግ ይሄኛው የመጣው ከዚህ ነ ው ያኛው ደግሞ ከሌላ ነው በማለት ሁቱ ና ቱትሲን ለመከፋፈል የተጠቀሙበትና በ ኋላም ወደማያባራ የእርስ በእርስ እልቂት የተሸጋገረ ሴራ ነው፡፡ ዶክተር ጎድፍሬይ የምስራቅ አፍሪካውያ ን ጎሳዎች ከኢትዮጵያ የመምጣት ታሪክ አ ሁን ላይ መሰረት የለሽ ይበሉት እንጂ እር ሳቸውም ጉዳዩ ለዓመታት ምሁራንን ሲያ ፋጭ እንደቆየ ይመሰክራሉ፡፡ መመሳሰሉ የመጣው ከአካባቢ ነው የሚሉት ምሁሩ የኬንያው ማሳይ፣ የኡጋንዳዎቹ ቴሶ፣ ካራ ሞጆንግና ባንኛኮሌ እንዲሁም የሩዋንዳው ቱትሲ አርብቶአደሮች ከሞላ ጎደል ተመሳ ሳይ የአኗኗር ዘይቤ እንዳላቸው ይመሰክራ ሉ፡፡ ይህ ግን ድንበር ስለሚዋሰኑ በዘመና ት ሂደት የተወረሰ እንጂ ደማቸው አንድ ስ ለሆነ አይደለም ባይ ናቸው፡፡ ይህ ታሪክ የተበረዘው የአውሮፓውያን ርዕዮተ አለም ተጽዕኖ ባለባቸው አንዳንድ የቀድሞ ስነ-ሰ ው ተመራማሪዎች ነው፡፡ ከዘመናት በፊት ለረጅም ጊዜ ሲያከራክር የቆየ በአሁኑ ወቅ ት ግን ምንም የታሪክ ማረጋገጫ ያልተገኘ ለት መላምት ስለመሆኑ ከስምምነት የተደ

ረሰበት ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡ ምሁሩ ምስራቅ አፍሪካውያን በተለይ ም ዕራብ ኡጋንዳውያን የባንቱ ፍልሰት አካል ናቸው ይላሉ፡፡ ይህ ደግሞ መነሻው በመ ሆኑ የዛሬዎቹ ምስራቅ አፍሪካውያን የዘር ምንጫቸው አፍሪካ እንጂ አውሮፓውያን እንደሚሉት መካከለኛው ምስራቅ ወይም አውሮፓ አይደለም፡፡ ነጮች ቅኝ መግዛት ስለፈለጉ “አፍሪካ ኋ ላ ቀር ናት። ህዝቡም መሃይም፣ እምነት የ ለሽ ነው። ስለዚህ እኛ ሄደን ልናሰለጥነው ይገባል” ብለው መጡ፡፡ በዚህ መሀል እነ ሱ ለሽፋን ከሚጠቀሙበት በተቃራኒ የሆነ ነገር በተገኘ ጊዜ መቀበል ይከብዳቸው ነበ ር፡፡ “ይህም የእዚህ አንድ አካል ነው” ሲሉ የነጮች ርዕዮተ ዓለም ያስከተለው የታሪክ ብዥታ ያሉትን ሀሳብ ይቃወማሉ፡፡ “እንደ ቅኝ ገዥዎቹ ማንኛውም ጥሩ ነገር ከአፍሪ ካ ምድር ሊመጣ ወይም ሊገኝ አይችልም፡ ፡ ለዚህም ነው ኡጋንዳውያንንም ሆነ ሩዋ ንዳዎችን የመጣችሁት ከኢትዮጵያ ነው የ ሚል ጽሁፍ ማስነበብ የጀመሩት” ይላሉ፡፡ “ማንኛውም ሰልካካ አፍንጫና ለግላጋ ቁመና ያለው ሁሉ ከአፍሪካውያን ወይም እንደነሱ አጠራር ከኔግሮ (ጥቁር አፍሪካ ውያን) ሊገኝ አይችልም፡፡ በመሆኑም መ ልካሞችን የመጣችሁት ከኢትዮጵያ ነው ይሏቸዋል። ንጉስ ሰሎሞንንና ንግስተ ሳባ ን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምስ ራቅ ጋር ግንኙነት አድርጋ ስለነበር ዞሮ ዞ ሮ የኢትዮጵያም ከመካከለኛው ምስራቅ ነ ው በማለት ቆንጆ መገኛው አውሮፓ ወይ ም አካባቢው እንጂ አፍሪካ እንዳልሆነ ለ መስበክ የተፈጠረ መላምት ነው›› ሲሉ ዶ ክተር ጎድፍሬይ አጥብቀው ይከራከራሉ።

ፊቴን ተመልከው የታሪክ ምሁሩ ዛሬ ላይ መሰረት የለሽ መ ላምት ስለመሆኑ ስምምነት ተደርሶበታል ብለው ቢቋጩትም ለአብነት የኡጋንዳ የ

ጎብኝዎች መጠቆሚያ ድረ ገጽ ግን አሁን ም ድረስ ከእርሳቸው በተቃራኒ መቆሙን የሚያመላክት ጽሁፍ ነው የሚያስነብው፡፡ ድረ ገጹ ላይ የኡጋንዳን ታሪክና የህዝብ አ ሰፋፈር በተመለከተ የሰፈረው ጽሁፍ በሰ ሜን፣ በምስራቅ እና በሰሜን ምስራቅ የሚ ገኙ ኡጋንዳውያን ምንጫቸው ከኢትዮጵ ያ መሆኑን ያብራራል፡፡ ጽሁፉ እንደሚለው የአሁኗ ኡጋንዳ እ.ኤ.አ ከ1880 እስከ 1926 ባለው ጊዜ በ እንግሊዞች የተፈጠረች ናት፡፡ ከሁሉም ቀ ድመው በኡጋንዳ ይኖሩ የነበሩት የድንጋይ ዘመን ሰዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ሰዎች ቀሰ በ ቀስ በአንደኛው ምዕተ ዓመት አካባቢ ወደ ኡጋንዳ ይገቡ በነበሩ አርሶአደሮችና አርብ ቶአደሮች መተካት ጀመሩ፡፡ እንግሊዞች ኡ ጋንዳ በመጡበት ጊዜ ከ30 በላይ የተለያዩ ብሄርና ጎሳዎች ነበሩ፡፡ እነዚህ ጎሳዎች ሰፋ ባለ አራት መደብ ሊከፈሉ እንደሚችሉ የ ድረ ገጹ ጽሁፍ ያትታል፡፡ እነሱም ባንቱ፣ ሉኦ፣ አቴከሪን እና ሱዳኒክ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል አቴከሪን በሚባለው ሁ ለተኛው ቡድን ውስጥ የሚገኙትና በተለ ይም በሰሜን፣ በምስራቅ እና በሰሜን ም ስራቅ ኡጋንዳ የሚገኙ ሰፋሪዎች የመጡት ከኢትዮጵያ መሆኑን ጽሁፉ ያስረዳል፡፡ ይ ህ ቡድን ላንጊን፣ ካራሞጃውያን፣ ቴሶ፣ ካክ ዋ እና ኩማምን የሚያካትት ሲሆን የእነዚ ህ ብሔር አባላትም ራሳቸውን እንደ አንድ ህዝብ የሚቆጥሩ ናቸው፡፡ በጊዜ ሂደት በ ፍልሰትና ተያያዥ ምክንያቶች በተለያየ የ ኡጋንዳ አካባቢ ቢሰፍሩም የራሳቸውን ሰ ዎች ከሌላው ለይተው ማወቅ ይችሉ እንደ ነበር ይነገራል፡፡ በኡጋንዳ ጦር ውስጥ የሐላፊነት ቦታ ያላ ቸውና ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ ባለ ስልጣን የሚናገሩትም በድረ ገጹ የተጠቀሱ ትን ነጥቦች የሚያጠናክር ነው፡፡ “ታውቃ ለህ የእኛ አያት ቅድመ አያቶቻችን ከኢት ዮጵያ ነው የመጡት፡፡ እኔ ከቱትሲዎች ወ ገን ነኝ፡፡ ፊቴን ተመልከው ከአንተና ከመ ሰሎችህ ጋር ይቀራረባል፡፡ ያኛውን ወጣት ተመልከተው፡፡ ኢትዮጵያዊ አይመስልም? ግን ኡጋንዳዊ ነው፡፡ እኔ ከመጣሁበት ጎሳ ነው” ሲሉ ማን ከኢትዮጵያ እንደሆነና እን ዳልሆነ ከሰው መካከል እንኳን መለየት እ ስኪችሉ ድረስ ርግጠኛ መሆናቸውን ይናገ ራሉ ፡፡ “የምነግርህ ዛሬ ወይም ትላንት ስ ለሆነ ነገር አይደለም፡፡ እኔ እዚሁ ነው የ ተወለድኩት አባቴም እንዲሁ፡፡ የእኛን አ ባቶች የወለዱት ወይም ከዚያ በፊት ያሉ ት ግን የዘር ግንዳቸው ከኢትዮጵያ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ ከመልካችን ጀምሮ ብዙ ማሳ ያዎች አሉ።” ይህ ሁሉ ሆኖ አሁንም ድረስ ሁለቱን ጎራ የሚያስታርቅ ጠርቶ የወጣ እውነት የለም፡ ፡ ገሚሶቹ ሀረጋችን ከኢትዮጵያ ነው ሲሉ ገሚሶች ደግሞ እኛ ከኢትዮጵያ አይደለን ም ክርክሩ ቀጥሏል፡፡ ምን አልባት በጉዳዩ ላይ ገለልተኛና ሰፊ ጥናት ተደርጎ ዳግም ወ ደ አዲስ እውነት መድረስ ይቻል እንደሆን ለአጥኚዎቹ የሚሰጥ የቤት ስራ ይሆናል፡፡


ሐበሻዊ ቃና

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ማን ይናገር የነበረ… በዚህ መልኩ ያ አሰቃቂና ረጅሙ ሌሊ ት አለፈና ወደየቤታችን ሄድን፡፡ እኔ ወ ደ ቤቴ የሄድኩት ሌሊት አስራ አንድ ሰዓ ት ነው፡፡ እንደደነዘዝኩ መኝታ ቤቴ ገብ ቼ ጠዋት ልጄ ትምህርት ቤት ለመሄድ ስትነሳ ልብሴን ስታየው “ኡኡ” ብላ ጮ ኽች፡፡ ለካስ አስከሬንኑም የተጎዳውንም ስናነሳ ለብሴ በሙሉ ደም በደም ሆኗ ል፡፡ ልጄ የሆነውን አላወቀችም። “ከማ ን ጋር ተደባድበህ ነው የመጣኽው” እያ ለች ታለቅሳለች፡፡ ከአደጋው ማግስት ጀ ምሮ ባሉት ቀናትም አስከሬን መሸኘት ለ ቅሶ መድረስ ወዳጅ ዘመድ የሞተባቸው ን ማጽናናት ሆነ፡፡ ምንም በህይወት እያለን ብናወራ ብን ጣላ ወይም ብንሳሳቅ ብንጫወት በቅጽ በት ወዳለመኖር እንቀየራለን፡፡ ህይወታ ችን ካለፈ ደግሞ ሁሉም ነገር ወዲያው ያበቃል፡፡ የነበረን ተክለሰውነት እንኳ የ እኛ መሆኑ እስከማይታወቅ ድረስ ይሆ ናል፡፡ የሰው ልጅ ፈራሽ ነው የሚባለው እውነት ነው፡፡ ከአደጋው አንድ ቀን በ ኋላ አስከሬን የማን ይሁን የማን መለየ ት ተስኖን ነበር፡፡ በጋዜጣም እንዳነበባ ችሁት አንዳንዶች የራሳቸውን ወገን ሳይ ሆን የሌላ ሰው አስከሬን ይዘው እስከመ ሄድ ደርሰዋል፡፡ ለተከታዮቹ ዘጠኝ አስር ቀናት በድኔ ነ በር የሚንቀሳቀሰው፡፡ ድርጊቱ በህልም ወይም በእውን ስለመሰከቱ ሁሉ እርግ ጠኛ አልነበርኩም፡፡ እንቅልፍ ሁሉ ሊ ወስደኝ ስላልቻለ በመድሃኒት ኃይል ነበ ር የምተኛው፡፡ ከዚያ በኋላም ቢሆን ቅ ዠት ሁሉ ያስቸግረኝ ነበር፡፡ ሌሊቱ የ ረዘመውን ያክል ከአደጋው በኋላ ያለው ጊዜ ግን አጥሮ እንጂ ረዝሞ አልተሰማኝ ም፡፡ ምክንያቱም አደጋው መቼም ከጭ ንቅላት የሚወጣና የሚረሳ ባለመሆኑ ነ ው፡፡ አሁን አንድ ዓመት ሞላው ሲባል

ፎቶ- ሮይተርስ

ከገጽ 7 የዞረ

በአደጋው ወቅት አምቡላንስ እንኳን ባለመምጣቱ ፖሊሶች በራሳቸው መኪና ወዲያው ወዲያው እየተቀበሉ ወደ ሆስፒታል እየያዙ ይሄዱ ነበር

ገርሞኛል። ትናንትና፣ ከወር ሁለት ወር በፊት የተከሰተ ያህል ነው የሚሰማኝ፡፡ የቦነስ ህይወት ከዚያ በኋላ ደጋግሜ እንደተናገርኩት በ“ቦነስ ህይወት” ነው የምኖረው፡፡ ያን ን አይነት መጥፎ ገጠመኝ አልፈህ ከኖ ርክ በ“ቦነስ ህይወት” ነው የምትኖረው ማለት ነው፡፡ እኔ ብዙ ጊዜ ኑሮዬ ከታች ኛው የህብረተሰብ ክፍል ጋር ነው፡፡ በ ዚህ አደጋ ህይወታቸው ካለፈው መካከ ል ብዙዎቹ በዚህ አይነት ህይወት ወስጥ ያለፉ ናቸው፡፡ ምንም በማያውቁት በዛ መልኩ ህይወታቸው ማለፉ ያሳዝነኛል፡ ፡ ብዙዎቹ ታላላቆቻቸውን አክባሪዎች ሳቅ ጨዋታንም የሚወዱ ነበሩ፡፡ እነዚህን ሁሉ ካጣህ በኋላ የምትኖረ ው ህይወት ታዲያ እንዴት ነው ምታስና ግደው የሚለው ጥያቄ የራሱ መልስ ይ ፈልጋል፡፡ በተለይ እንዲህ አይነት ገጠ መኝ ውስጥ ተካፍለህ በህይወት ስትተር

ፍ መቼም እንደምትሄድ ታውቀዋለህ፡፡ እነዚህ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ሩቅ ያ ስቡ የነበሩ ሰዎች በ45 ወይም በ50 ደቂ ቃ ብልጭታ ውስጥ በዚያ መልኩ ካለፉ እኛስ ብለን ማሰብ አለብን፡፡ በመሆኑም እኔ በግሌ ከዚያ በኋላ የኖርኩትና እየኖ ርኩ ያለሁት በቦነስ ነው፡፡ ከአሁን በኋላ አንድ ነገር እንኳ ቢመጣ ብዙ እንደማልረበሽ አውቀዋለሁ:: ምክ ንያቱም ከምንም በላይ ልምድ አግኝቸ በታለሁ፡፡ የሰው ልጅ እንደ በዓል የቅር ጫ ስጋ እየተከፋፈለ ከማንሳት በላይ ም ን አለ? እኔ ሞቼ ቢሆን እንደዚያው ነበር እኮ ነው፡፡ በአንድ በኩል ወገኖቼን በመ ርዳቴ እርካታ ይሰማኛል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ለነገም እንዳላስብ፣ አንድ ነገር ቢ ገጥመኝም ብዙ እንዳልገረም አድርጎኛ ል፡፡ ፍንዳታውን በተመለከተ በወቅቱ ላልነበሩት ሰዎች ስነግራቸው ህልም ነ በር የሚመስላቸው፡፡ እውነትም ህልም

21

የሚመስል ግን በአንድ ምሽት የዘላለም ጠባሳን ያተረፈ ዘግናኝ እውነት ነው፡፡ ከዚያ በኋላ በተወሰነ መልኩም ቢሆን ከሰው ሀገር ሰው ጋር በተለይ ከሶማሊ ያውያንና ከነጮች ጋር መቅረብን መጥ ላት ጀምሬአለሁ፡፡ ምክንያቱም እኔ እን ደማስበው ፍንዳታው ኢላማ ያደረገው ነጮችን ነበር፡፡ እነሱ በተቀመጡበት አ ካባቢ ነበር፡፡ ቀደም ሲል እንዳልኩት የ ቦምብ ፍንዳታው ነጮችን ኢላማ ያደረ ገ ነበር፡፡ በመሆኑም ለእኛም ወገኖች መ ሞት ምክንያቶቹ እነሱ ናቸው ብዬ ማ ሰብ ጀመርኩ፡፡ በዚህም ምክንያት ነጮ ች የተሰበሰቡበት አካባቢ መቅረብ ጠ ልቻለሁ፡፡ እንዲያውም አደጋው ከተከ ሰተ በኋላ ባሉት የመጀመሪያ ቀናት ሐ በሻ የተሰበሰበበት አካባቢም መቅረብን ጠልቼ ነበር፡፡ ራሴን ለማረጋጋት በሚል ም ኡጋንዳን ለአንድ ወር ያህል ለቅቄ እ ስከመውጣት ደርሻለሁ፡፡ ወይኔ! በእለቱ ህይወታቸው ካለፈው መካከል አራቱ ከእኛ ጋር ኳስ የሚጫወቱ ሲሆኑ ሶስቱ በእለቱ ጠዋት አብረውን የተጫወ ቱ ነበሩ፡፡ እኔ እንዲያውም መሸኛ አድር ገልናቸዋል ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም ቀደ ም ሲል እንዳልኩት አንዱ (ዘላለም) ከና ይሮቢ በእንግድነት መጥቶ ነው ኳስም የተጫወተው፡፡ ከኳስ መልስም ከሁላች ን ጋር በአንድ ማዕድ እየበላን እንጫወት ና እንሳሳቅ የነበረው፡፡ ካሌብም ቢሆን ከሌላው ጊዜ በተለየ ጥሩ ጨዋታ ነበር የ ተጫወተው፡፡ በዚህ መልኩ ከቆየን በኋ ላ ማታ ኳስ ለማየት ተቀጣጥረን ነበር የ ተለያየነው፡፡ ማታ ታዲያ ካሌብ ከጓደኞ ቹ ጋር ሲገባ አንድ መቀመጫ ነው በሚ ል ሳልጠራው በመቅረቴ ዛሬም ድረስ ጸ ጸቱ ከአእምሮዬ ሊወጣ አልቻለም፡፡ ብ ዙ ጊዜ ካሌብን እኔ የገደልኩት ያክል ይ ሰማኛል፡፡ ካሌብ ከአፌ ነው ያመለጠኝ፡ ፡ ምናልባት ብቻውን ቢሆን ኖሮ እጠ ራው ነበር ፡፡ ሶስት ስለሆኑ ግን ይህንን ሳላደርገው ቀረሁ፡፡ አሁንም ድረስ ምነ ው ጠርቼ ባስቀመጥኩት ኖሮ እላለሁ፡፡

ማሜ እና… ከገጽ 5 የዞረ አዝኛለሁ። አንድ መታሰቢያ ማድረግ እ ንጂ ሌላ አቅም የለኝም። መታሰቢያው ሲከፈት አምባሳደሮች፣ የውጭ ሀገር ዜጎች እና የሞቱባቸው ቤ ተሰቦችን ጠርቼያለሁ። ብዙዎቹ ደስ ነ ው ያላቸው። አልፎ አልፎ ደግሞ የተለ የ አስተያየት ትሰማለህ። ሆኖም ቀረ መ ሆን ያለበት ነገር ስለሆነ ነው እንጂ ይ ሄ ነገር ባይመጣ ኖሮ አንድ ምግብ ቤ ት ውስጥ እንዲህ ዓይነት መታሰቢያ አ ይኖርም ነበር። እኔ ራሴን እንደ ደንበኛ አስበኝ። እዚህ “ቪሌጅ” መጥቼ፣ አንድ የሆነ ሰው አጥ ቼ፣ ምግብ ቤቱ የሆነ መታሰቢያ ቢሰራ በጣም ነው ደስ የሚለኝ። አሁን አንዳን ዴ ከሞቱባቸው ቤተሰቦች እየመጡ አበ ባ የሚያኖሩ አሉ። የውጭ ሀገር ዜጎች ደ ግሞ አበባ አምጥተው አስቀምጠው ፎ ቶግራፍ ያነሳሉ። የተለያዩ ሀገር ጋዜጠ ኞችም ይመጣሉ። እዚህ ሀገር ወደ ሃያ ዓመት ገደማ ቆይተሻል። የካምፓላን ክፉ እና ደግ አይተሻል። ከብዙ ሐበሾች ጋር ትተዋወቂያለሽ። ይህ ቤትም የኢትዮጵያ ባህል ማሳያ ተብሎ የሚጠቀስ ነው። ለሐበሾች ምንድነው የምትያቸው? እኔ መቼም በእውነት ነው የምለው ከ አደጋው በኋላ በተለምዶ እንደምናደርገ ው ቄጤማ ጎዝጉዘን፣ መሶባችን ወጥቶ፣ ፈንዲሻ አፈንድተን፣ ቡና ተፈልቶ፣ እጣ ኑ እየጤሰ እንግዶች እየገቡ እያለ ሰው ከቤተከርስቲያን ግልብጥ ብሎ መጥቶ ግቢውን ሲያጥለቀልቀው እኔ ወደ በረን

ሐበሻዊ

ዳ መጥቼ ስመለከት ፊቴን በእንባ ነው የ ራሰው። የምኮራባቸው ደንበኞቼ ቤቱን ግጥም አድርገው፣ ሲበሉ፣ ሲጠጡ፣ በየ ጠረጴዛው እየሄድን ቡና እያደልን፣ ሙ ዚቃ ተከፍቶ ሲጨፈር፣በቦታው ላይ ም ንም የተፈጠረ አይመስልም። ወገንህ አለሁ ሲል ከዚህ የበለጠ ምን የሚያስደስት ነገር አለ። ሰርተህ የሚበ ላልህ ሰው ከሌለ ምንም ዋጋ የለውም። ስለዚህ እጅግ በጣም የሚያኮራ ነው። የ ሀገራችንን ባህል እነሱ በመኖራቸው ያ ደመቁት እንጂ የእኔ ብቻ ስራ አይሆን ም። በጠቅላላ የ “ኢትዮጵያን ቪሌጅ” ደ ንበኞች ባሉበት በካምፓላም ይሁን በአ ሜሪካ፣ በካናዳም ይሁን በታንዛንያ፣ በ ኬንያም ይሁን በዓለም ላይ ላሉት ደን በኞቼ ልናገር የምፈልገው ከስራዬ በበለ ጠ ሁኔታ እጅግ በጣም ትልቅ ደንበኞች እንዳሉኝ ይሰማኛል። እኮራባቸዋለሁ። ቤቱ ከታደሰ በኋላ ምን የተለወጠ ነገር አለ? በተቻለ መጠን ከእንግዲህ ደንበኛው ንም ሆነ ራሳችንን ለመጠበቅ ጥብቅ ፍ ተሻ አለ። ሁለተኛ የሚከሰት ዓይነት ነገ ር አይደለም። የመፈተሻ መሳሪያዎች ተ ገዝተዋል። አሁን ኑሮ እየተወደደ በመሆኑ የምን ገዛቸው ዕቃዎች ውድ ናቸው። ባለው ደረጃ የምግቦችን ጥራት ጨምረን አን ዳንድ አዳዲስ ምግቦች ጀምረናል። ጠ ጅ፣ ጠላ ጀምረናል። ወደፊት ግን የፈረ ንጅ ምግቦችን፣ ባህላችንን ይበልጥ የሚ ያስተዋውቁ ነገሮች ለመጀመር ዕቅድ አ ለኝ። ። ለዚህ ሁሉ ላስደሰቱኝ ደንበኛቼ ከዚህ በበለጠ ሁኔታ አድርጌ ባልተወደ ደ ዋጋ ለማስተናገድ፣ የተሻሻለ ነገር ለማ ቅረብ ዕቅድ አለኝ።

ቃና

በየ 15 ቀኑ

ምጥን ማስታወቂያዎች

ከምርጥ የኢትዮጵያ ቡና እና ማኪያቶ ጋር

አድራሻ፦ ካሳንጋ/ ጋባ መንገድ ከጆን ሱፐር ማርኬት ገባ ብሎ

የልደት፣ የሰርግ፣ የመልካም ምኞት መልዕክቶችን በምጥን ማስታወቂያ ማውጣት ከፈለጉ

በ+256-778-693669

ሰኔ 18 ቀን 2003 ዓ.ም የጋብቻ በዓላችሁን ላከበራችሁት መስፍን ገብረስላሴ እና ሀና ተሾመ መልካም የትዳር ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን

ከጓደኞቹ


ሐበሻዊ ቃና

22

የእኛ ሰው ... ከገጽ 9 የዞረ ከሌለህ ቋንቋ ስላወቅህ ብቻ የምትናገረ ው ነገር የለም። እንደዚህ አድርገን ነገሮ ችን ማየት አለብን። ትልቁ ነገር የአቅ ምህን መሞከር ነው። ደፍረው የገቡ ኢ ትዮጵያውያን ውጤታማ እና ስኬታማ ሆነው እንደውም የከፍተኛ ማዕረግ ተ መራቂ ሆነው ሲወጡ ነው ያየኋቸው። ስለዚህ ቋንቋ ችግር መሆን የለበትም። መተጋገዝ ይቻላል። ቀድሞ የገባ ካለ “ምንድነው ያለው ነገር? እንዴት ልዘጋ ጅ? በምን መልኩ ባጠና ነው የተሻለ ው ጤት ማግኘት የምችለው” ብሎ መጠየ ቅ ነው። አሁንም እንዲህ ነው የምንመ ካከረው። ከእኔ ቀድመው የገቡት መክ ረውኛል። ከእኔ ቀጥሎ የሚመጡ ካሉ ደግሞ እንዲሁ ይቀጥላል። አንዳችን ለ አንዳችን አለኝታ መሆን አለብን። አንዳ ችን ለሌላችን መንገድ የምናሳይ መሆን አለብን። ፉክክር አለ። የተሻለ የምዘጋጅ ከሆነ ግ ን አይከብድም። ብዙዎቹ ወጣቶች ናቸ ው። በዕድሜ ከእኔ ያነሱ ሊሆኑ ይችላ ሉ። ለትምህርት ያለን ስሜት ግን እኩ ል አይደለም። ምክንያቱም እኔ የምማረ ው በዓላማ ነው። ለአስር ዓመት ያህል ፈልጌ ያጣሁትን አግኝቼ አሁን በጉጉት ነው የምማረው። እነሱ ደግሞ በእድሜ ያቸው መማር ስላለባቸው ወይም በቤ ተሰብ ጎትጎታ ይሆናል የሚማሩት። ይ ህ ሁሉ ስላለ ተጠቃሚ እሆናለሁ። ጊዜ ዬን በአግባቡ እጠቀማለሁ። አነባለሁ። እኔም ሆንኩ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጥሩ ውጤቶች አሉን። ምናልባት እኔ ካ ሁን ቀደም ዩኒቨርስቲ ስለነበርኩ የጀር ባ ታሪክ ስላለኝ ነው ሊባል ይችላል። ተ መሳሳይ የትምህርት ዓይነት እየተማር ኩ መሆኔ ጠቅሞኝ ሊሆን ይችላል። ከ እኔ ጋር ከሚማሩት ኢትዮጵያውያን መ ካከል ግን ሁለተኛ ደረጃ ብቻ የጨረሱ አሉ። ጥሩ ውጤቶች እያስመዘገቡ ናቸ ው። ከተማሩ በኋላ ጥሩ ቦታ ደርሰው በ አይኔ ያየኋቸው አሉ። እኔ ያለሁበት ት ምህርት ቤት ተምረው በአሁኑ ሰዓት ወ ደ ስራው ገብተው ጥሩ ህይወት የሚኖ ሩ አሉ። ለዚህ ግን የአእምሮ ዝግጅት ያስፈል ጋል። የትምህርት ስርዓቱ እንደእኛ አገ ር አይደለም። ፈተና ሲደርስ አይደለም የምታጠናው። ትምህርት በገባህ በመጀ መሪያው ቀን በዓመት ውስጥ የምትማ ራቸው ነገሮች በሙሉ በቀኖች ተከፋፍ ሎ ይሰጠሃል። ትምህርት ተጀመረ ማለ ት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ታጠናለህ ማለት ነው። ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ጊዜው የአንተ አይደለም። የትምህርቱ ነ ው። እያንዳንዱን የቤት ስራ ተከታትለ ህ ካልሰራ እንደእኛ አገር ፈተና ሲደርስ ተዘጋጅቼ ውጤታማ እሆናለሁ ማለት የ ማይታሰብ ነው። ደግነቱ “ክሪስማስ መ ጣ ትባረራለህ” የሚባል ነገር የለም። ከ ወደቅህ ወይ ጊዜ አልነበረህም አሊያም

ልፎ ... ከገጽ 14 የዞረ ሉ፤ የመጀመሪያውን ባልችልበት የሁለ ተኛውን ማን ይከለክለኛል? ያ ሰው ወ ይም እነዛ ሰዎች ስሟን ሊያጠፉ ሲለፉ ነው የእኔ ሃላፊነት የገባኝ። አብሮ መብላ ት መጠጣትማ ዋና ነገር መሆኑ አቆመ። እሱ ተፈትሾ ወድቋል። በእርግጥ ልብን የመስጠት እንጂ። አብሬ ቂጣ የተጓተት ኳቸውእንደ ቂል ልብን የመስጠት እን ጂ። አብሬ ቂጣ የተጓተትኳቸው እንደ ቂል ቆጥረውኛል። ለወዳጄ የውርደት ስ ጦታ ‘ዲሞክራሲ’ በሚባል ክርታስ ጠቅ ለው ሰጥተዋታል። እኔንም ‘በታድለሃል’ ጋርደው ከለመድኳትና ካሳደገችኝ ለገሃ ር አባረውኛል። ፍቅር እንዳይደርስእሱ

ስርዓቱ ሳይገባው አስቀድሞ አልተዘጋጀ ም ተብሎ ድጋሚ እድሉ ይሰጠሃል። እ ንደእኛ አገር ተባረረ ተብለው የምትሳቀ ቅበት፣ የምታፍርበት አይደለም። ኢትዮጵያውያን በአውስትራልያ እንዴት ነው የሚኖሩት? ህይወ ታቸው ምን ይመስላል? ኢትዮጵያውያን በተለያየ መስክ ውስ ጥ አሉ። ዩኒቨርስቲ አስተማሪ የሆኑ አ ሉ። የራሳቸውን ስራ የሚሰሩ አሉ። ከፍ ራፍሬ ለቃሚነት እስከ “ኮርፖሬት” ድር ጅቶች ዋና ስራ አስኪያጅ ድረስ አሉ። የፋብሪካ ሰራተኞች አሉ። ለአረጋውያን እንክብካቤ የሚሰጥባቸው ቦታዎች ው ስጥ የሚሰሩ አሉ። ታክሲ የሚሾፍሩ አ ሉ። በምድር ባቡር ውስጥ ባቡር ነጂነት ን ጨምሮ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የሚ ሰሩ ኢትዮጵያውያን አሉ። ኢትዮጵያዊ ብቻ ሳይሆን የአገሩ ዜጋም እንደዚያው ነው። የስራ ባህሉ አለ። በትምህርት ያል ገፋ አንድ አውስትራሊያዊ ምን ሊሰራ እንደሚችል ያውቃል። የኢትዮጵያውያንን ህይወትን ስትመለ ከት ተማርክም አልተማርክ ሰርተው የ ሚያገኙት ነገር በቂ ነው። ቤት ገዝተ ው የሚኖሩ አሉ። ቤቱን የራሳቸው ለ ማድረግ እየከፈሉ የሚኖሩ አሉ። ምን ም የማይሰራው እንኳ በመንግስት ድጋ ፍ ያለው መሰረታዊ ነገር አጥቶ አይኖር ም። ብዙ ኢትዮጵያውያን ጥሩ ህይወት ነው የሚኖሩት። ራሳቸውን የጣሉ በጣ ም ጥቂቶች አሉ። ከመንግስት የሚያገኟ ትን ድጋፍ እንኳ በአግባቡ ሳይጠቀሙ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የሚኖሩ አሉ። እንደእኔ አይነቱ የሚማረው መጠለያ አለው፣ ከመንግስት በሚያገኘው ድጋ ፍ የሚበላውን፣ የሚጠጣውን፣ የትራ ንስፖርት እና የመሳሰሉትን መሰረታዊ ነገሮቹን፣ የመጽሐፍ መግዢያውን ሸፍ ኖ ይኖራል። የመጨረሻው ህይወት ሊባ ል የሚችለው እኔ የምኖረው ህይወት ነ ው። በእኔም ህይወት ግን ለመሰረታዊ ነ ገሮችን ምንም ሳላስብ ነው የምኖረው። ሙሉ ጊዜዬን ትምህርት ላይ ስላዋልኩ በሳምንት አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እሰ ራለሁ። አውስትራልያ አንድ ስራ ሰርተ ህ መማር የምትችልበት አገር ነው። በት ርፍ ጊዜህ መማር ትችላለህ። ሙሉ ሰዓ ት እየተማርክ በትርፍህ ጊዜ ብትሰራ እ ንኳ በቂ እና የተደላደለ የሚባል ህይወ ት መኖር ትችላለህ። አንዲህ ስልህ ግን እዚያ እስኪደረስ ፈ ተናዎች የሉም ማለት አይደለም። ብዙ ፈተናዎች አሉ። ከዚህ ስትሄድ መጀመሪ ያ የምትጠብቀው ነገር ይኖራል። እንደ ሄድክ ስራ ላታገኝ ትችላለህ። አንዳንድ ቦታ ስራ ልታገኝ ትችላለህ። ነገር ግን ከ መቀጠረህ በፊት ቢያንስ ቋንቋ በትክክ ል እንደምታውቅ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ። ቋንቋ እንድታሻሽል ደግሞ መንግስት ስ ርዓት ዘርግቷል። እንደሄድክ ይቀበሉሃ ል እስከፈለግከው ጊዜ በነጻ ቋንቋ እንድ ትማር ያደርጉሃል። መጀመሪያ ነገር መ ግባባት መቻልህ ነው ወደ ስራህ የሚወ የተሰራባቸውን ንጥረ ነገሮችን ማፍረስ ነው ልፋታቸው። አፍታ እድል አልሰጣ ቸውም። ለማንም ዝም ብዬ በር አልከፍ ትም። ውሃ እየቀዳሁ አስባለሁ። ሻይ ስ ጥድም አስባለሁ። ማንንም ሰው……ድር ጊቱና አንደበቱን አወዳድሬ ነው የማምነ ው….ውሃ ቀድቼ እየሰጠኋት አስባለሁ። የሻይ ቅጠል ፓኮዎች እየመረጥኩ (ሶስ ት አይነት አሉኝ) አስባለሁ። በመስኮት ወደ ውጭ ታያለች። አልጋ ዳር ተቀም ጣ። እርግዝናዋ የከፈላቸው እግሮቿ ግ ራና ቀኝ ወዲያ ወዲያ። ትልቅ አእምሮ አላት ትዕግስት አላት። ውሃ ስትጠጣ እ ያየሁዋት አስባለሁ። ጥበብም መልመድ ነበረብኝ። ‘የሰው ልጅን፣ ዜጋውን ሳትወድ እንዴት አገርህ ን ትወዳለህ?’ አይነት ጥበብ። አስቸጋሪ ነበር። እሱን ከመቅደስ ተማርኩ።

ስድህ። ሁለተኛ እያንዳንዷን ስራ ለመስ ራት “ሰርተፍኬት” ሊኖርህ ይገባል። የጥ በቃ ስራ ወይም የአረጋውያን እንክብካ ቤ ሊሆን ይችላል። ስራ መያዝ በምትፈ ልግበት ሙያ ተምረህ “ሰርተፍኬት” ይዘ ህ ነው ስራ የምትጀምረው። እንዲህ አል ጋ በአልጋ የሆነ ምንም ነገር የለም። ታሽተህ ታሽተህ በአውስትራልያ ስርዓ ት ውስጥ መግባት የምትችለው ከአንድ ወይም ከሁለት ዓመት በኋላ ነው። ለዕ ድለኞች ስራ ሊገኝ ይችላል። በሄደ ማግ ስት ስራ ያገኘ አለ። ሁለት ዓመት ተቀ ምጦ ስራ ያላገኘም አለ። ለምሳሌ እኛ የ ሄድንበት ጊዜ በዓለም የፋይናንስ ቀው ስ ምክንያት ብዙ ሰዎች ከስራ የወጡበ ት ነበር። ብዙዎቻችን ስራ ብንፈልግም አላገኘንም። ከስራ የተፈናቀለው ወደሌ

ትቆርጥ ትችላለህ። ያችን ወቅት አልፈ ህ ስርዓቱ ውስጥ ከገባህ በኋላ ነገሮች በ ጣም የተስተካከሉ ይሆናሉ። የምትፈል ገውን ያህል ባይሆንም የተሻለ ህይወት ትኖራለህ። ኢትዮጵያውያን በሄዱበት ሁሉ ሀ ገራቸውን መልሰው በትንሹ ለመ ፍጠር ይሞክራሉ። በውጭው ዓ ለም “ሊትል ኢትዮጵያ” ተብሎ የተሰየሙ ቦታዎች ሁሉ አሉ። አ ማርኛ የስራ ቋንቋ የሆነበት ከተ ማም አለ። አውስትራልያ ያለው ሁኔታስ እንዴት ነው? እኛ መቼም ባህሪያችን የታወቀ ነው። ከእነ ምጣዳችን፣ ከእነእንጀራችን፣ ከእ ነሽሮ በርበሬያችን ነው የምንሄደው። ካ

ጥቂት ስለ አውስትራልያ q አውስትራልያውያን ራሳቸውን “ኦዚ” ብለው ነው የሚጠሩት q አብዛኞቹ አውስትራልያውያን ከሌላ ሀገር መጥተው የሰፈሩ ናቸው። የመጀመሪያዎቹ የአገሬው ተወላጆች “አቦርጂኒ” ይባላሉ። q ከ179 አገሮች የተውጣጡ ማህበረሰቦች በአውስትራልያ ውስጥ ይገኛሉ። q እንደ ሲድኒ ዓይነት ከተሞችን የሚጎበኝ ሰው እስያ ያለው ሊመስለው ይችላል። በርካታ እስያውያን በሲድኒ ይኖራሉ። q ቱርኮች እና ኢጣሊያውያን እንደ “ኦዚዎች” ሁሉ ለረጅም ዓመታት በአውስትራልያ በመኖራቸውበአገሩ ላይ የሚሰማቸው የባለቤትነት ስሜት ከፍተኛ ነው። q ቀድሞ 100 የአውስትራልያ ዶላር በ60 አሜሪካ ዶላር ይመነዘር ነበር። በአሁኑ ወቅት ግን ተመሳሳይ መጠን ያለው አውስትራሊያ ገንዘብ 110 የአሜሪካን ዶላር ድረስ እየተመነዘረ ይገኛል q የአውስትራልያ አነስተኛ የደመወዝ መጠን ተብሎ የሚጠቀሰው 15 ዶላር ነው። ዝቅተኛ የሚባለውን ክፍያ የሚያገኙ ኢትዮጵያውያን በሰዓት 18 ዶላር ያገኛሉ። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን በሰዓት ከ20 እስከ 25 ዶላር የሚከፈልባቸውን ስራዎች ይሰራሉ። q አውስትራልያ በዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር በኩል ከሚመጡላት ስደተኞች መካከል በዓመት ስድስት ሺህ ያህሉን ለመቀበል ቃል የገባች ሲሆን “ስፔሻል ሂዩማንቴሪያን ፕሮግራም” በተሰኘው የመንግስቷ የድጋፍ እቅድ በዓመት 7750 ስደተኞች ወደ ሀገሯ ታስገባለች። ላ ስራ የሚገባበት ስለነበር እዚያ ሀገር ል ምድ ያለው እያለ እኛን ማንም አይቀጥ ረንም ነበር። ስራ ለማግኘት ብቃት ያለው መሆን አ ለብህ። በዚህ በጣም ያምናሉ። የሚፈለ ገውን ወረቀት እስክትይዝ፣ ከዚያ ደግሞ የመጀመሪያውን አይን መግለጫ ስራ ይ ዘህ የአገሬውን እውቀት እስክታገኝ ድረ ስ ትታሻለህ። በመንግስት ድጋፍ ነው የ ምትኖረው። በዚህ ጊዜ ቤተሰብህን፣ ወ ንድምህን፣ ጓደኛህን ላትረዳ ትችላለህ። ከዚህ ስትሄድ የምታስበው ሌላ ነው። በዚህም ምክንያት ብዙዎች ጭንቀት ላ ይ ይወድቃሉ። በተለይ ከሶስት ወር በ ኋላ እስከተወሰነ ጊዜ ድረስ በጣም ተደ ብረህ፣ ሁሉ ነገር አስጠልቶህ፣ ተስፋ ል

ምፓላ የምታየውን። የሽሮ በርበሬ መደ ብር ሜልበርን ውስጥ ታገኘዋለህ። አም ስት ስድስት ተከታታይ የሐበሻ ሆቴሎች ያሉበት አለ። እንደ ዋሽንግተን 18ኛው ስትሪት ሜልበርን ላይ የሐበሻ ሰፈር እየ ተፈጠረ ነው። ሲድኒም እንደዚያ ነው። አሰፋፈራችን አንዱ ቀድሞ የሄደውን ተ ከትለህ ነውና የምትገባው ሲድኒ ላይም ሶስት አራት ቦታዎች ላይ ሐበሻ በብዛት ያለባቸው አካባቢዎች አሉ። እንጀራው ም፣ ከትፎውም፣ ሽሮውም፣ በየዓይነቱ ውም ሁሉም ነገር አለ። ተሰባስባችሁ በዓላት ታከብራላ ችሁ? የኢትዮጵያ ማህብረሰብ (ኮሚዩኒቲ) አ ለ። በኮሚዩኒቲ ደረጃ የሚዘጋጁ ፕሮግ

መጋረጃ ዘግቼ አጠገቧ ተቀመጥኩ። ፊቷን ቀና አድርጌ ውሃ ያቀዘቀዛቸው ከ ንፈሮቿን ሳምኳቸው። አስባለሁ …..ከእንግዲህ የበለጠ ቁም ነ ገረኛ እንድሆን። ግን ጠባብ የሆነ። የእህ ቴን ቁስል ለማባበል። ለማዳን። እጄን ወደ ጣፋጭነቷ እልካለሁ። ወደ ማሯ። ዳጥ እየሳበኝ። መውደድ ደግ ነ ው። ጀርባዬን ይበርደኛል። የሰሜን ባ ሕር አየር በባንኮኒ በር በኩል ይገባል። “በሩን አልዘጋሽም?” “መጋረጃውን ብቻ ነው” “ሰው በዚህ ቢመጣስ?” “አራተኛ ፎቅ ድረስ ማን በመሰላል እኛ ን ለማየት ይመጣል ሂሂሂ” አንቺስ አራተኛ ፎቅ የምትኖሪ የተገለ ልሽ ሴት አልነበርሽ? ምንሽ ሲሰለል ነው የተሰለልሽው ? የተሰደብሽው? የታማሽ

ው? ሕይወትሽ እንደ ማብሸቂያ የተቀመ ረው ? መጋረጃው በነፋስ ሲገለብ ባንኮ ኒው መደገፊአ ላይ አንድ ነገር ተቀምጦ አየሁ። ወይም ተቀምጦ ያየሁ መሰለኝ። የሞቀ እጄን ከጭኖቿ መሃል ሳላወጣ፣ እነበረበት ወደ ተመለሰው፣ ምንም ወደ ማያሳየኝ ውጭውን አለም ወደጋረደኝ መጋረጃ ላይ አፈጠጥኩ። አንድ እጅዋን ጭኔ ላይ ደረበች። መዘንጋትና መሰቃየት የማያፈርሳቸው ሁነቶች አሉ። ሁነቶች። ከየት መጣ ይ ሄ ቃል? በቀትር ሰክሬ ብሔራዊ ትያትር ጀርባ አሮጌ መጻሕፍት ተራ፣ አጥፊው ጓ ደኛዬ ማሙሽ ቢራቱ መጽሐፍ ልግዛ ብ ሎ፣ ከገዛ በኋላ እኔን ለማሳቅ ሲያነብ የ ያዝኩት ቃል? መጋረጃው በቀላል ነፋስ ተነሳና ቀድሜ ያየሁትን ፍጡር ነገር ባን ኮኒው መደገፊያ ላይ ተቀምጦ አየሁ። የ

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ራሞች አሉ። እያንዳንዱ ዓመት በዓል ተ ሰባስበን ድምቅ አድርገን ነው የምናከብ ረው። ጊዜው ስላለ በዓል መጠራራት አ ለ። አንድ ስራ ሰርቶ መኖር የሚቻልበት ሀገር ስለሆነ ያ ዕድሉን ፈጥሮታል። በዚ ያ ምክንያት የመገናኘቱ ደግሶ የመጠራ ራቱ ነገር አለ። ክርስትና ማስነሳት፣ ሰር ግ መደገስ አለ። እንደውም ደስ የሚለ ው ልጆች ተምረው ሲመረቁ ኢትዮጵያ ኖች በጣም ደስተኛ ከመሆናቸው የተነ ሳ ፕሮግራም አዘጋጅተው እየተሰባሰቡ ያስመርቃሉ። ለማበረታታት የሚደረ ጉ ጥረቶች ትመለከታለህ። እከሌ ይማ ራል ሲባል እንኳ የሚሰጡት ክብር የተ ለየ ነው። የኢትዮጵያውያን ማህብረሰብ በ ዓል ከማክበር በዘለለ የሚያደር ጋቸው እንቅስቃሴዎች አሉ? ወ ደ አውስትራልያ ለሚመጡ ኢት ዮጵያኖች የተዘጋጀ መረጃ ያቀር ባሉ? ቢታመሙ ይረዳሉ? ትም ህርት ቤት እንዲገቡ ስራዎች እን ዲያገኙ መረጃ ይሰጣሉ? የኢትዮጵያውያን ማህብረሰብ በ “ኒው ሳውዝ ዌልስ” በቅርቡ ቢሮ ከፍቷል። ለ ሚያስፈልገው ሰው በሚፈለገው መልኩ ትብብር ያደርጋሉ። እገዛ ለሚያስፈልገ ው ሰው ኢትዮጵያውያንን አሰባስበው እገዛ ይጠይቃሉ። በአጋጣሚ መጥቶ እ ዚያው መቆየት ለሚፈልግ ሰው ለኢሚ ግሬሽን ደብዳቤ ከመጻፍ አንስቶ ጉዳያ ቸውን አስተካክለው መጻፍ ለማይችሉ ሰዎች እገዛ እስከመስጠት ድረስ የተለያ የ እርዳታ ያደርጋሉ። አንድ ስደተኛ ወደ አውስትራልያ ሲመ ጣ አገር የሚያሳየው፣ የሚመዘገብበትን ቦታ ፣ የሚወጣ የሚገባበትን መንገድ፣ ትራንስፖርት አጠቃቀሙን ሁሉ የሚያ ሳየው አለ። የአውስትራልያ መንግስት ይህንን ስርዓት አመቻችቷል። በማህበረ ሰቡ ደረጃ ግን ይህ በቂ አይደለም የሚ ል እምነት አለ። ማህበረሰቡ አዲስ የሚ መጡ ስደተኞችን ተቀብሎ፣ አገር ለማ ላመድ፣ ከስርዓቱ ጋር እንዲዋህዱ ለማ ድረግ፣ ማድረግ የሚገባቸውን የሚጠቆ ም የምክር አገልግሎት ለመስጠት እንዲ ያስችለው እንደገና ተዋቅሯል። ለስደተ ኛው አስፈላጊውን መረጃ አዘጋጅቶ ለመ ጠበቅ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች እየተሰሩ ናቸው። በእርግጠኝነት የምነግ ርህ ከዚህ በኋላ ወደ ሲድኒ የሚመጡ ስ ደተኞችን ማህብረሰቡ ይቀበላቸዋል። የ ተለያየ መረጃ አዘጋጅቶ ይቆያቸዋል። የ ሚፈልጉት መስመር ላይ እንዴት መሄ ድ እንዳለባቸው፣ ምን ማድረግ እንደሚ ገባቸው ሀሳብ የሚሰጣቸው ይኖራል። የአውስትራሊያ ስም ከስደተኞች እስር ጋር በተደጋጋሚ ሰነሳ ይሰ ማል። በርካታ ስደተኞች በታጠ ረ ቦታ ለረጅም ጊዜ እንደሚቆ ዩ የሚያሳዩ የብዙሃን መገናኛ ዘገ ባዎች በየጊዜው ይደመጣሉ። የአ ውስትራሊያ መንግስት ወደ አገ ሆነ አሞራ ነገር ነው። ከእርግብ የሚተል ቅ ዱጭጭ ያለ ነገር። ከጨለማው የበለ ጠ የጨለመ። “እንዴ ምንድነው?” አልኩና እጄን ከ ጭኖቿ መሃል አውጥቼ ከተጋደምኩበት ቀና ብዬ ቁጭ አልኩ። መቅደስ ከተጋደመችበት አልተነሳች ም። ትስለመለማለች። ፈገግ ብላለች። ገ ጽዋ ብዙ ነገር የተገነዘበ፤ ማንም ያልደ ረሰበት ዕውነት ላይ የደረሰች ሳቤላ አ ይነት ሆኖ። “ሰማሽ መቅዲ…..” አልኩና ባትሰማኝ ም የበረንዳውን መብራት አብርቼ መጋ ረጃውን በፍጥነት ገለጥኩት። ባንኮኒው መደገፊያ ላይ ያየሁት የመሰ ለኝ አሞራ የለም። ባንኮኒ ላይ ወጣሁና ወደ ሰማይ አየሁ። ተሳስቼ ይሆናል ወይ ም አይኖቼ። ወዲያው ክንፎቹ የሚያብ

ሩ ለሚመጡ ስደተኞች ያለው አ ቀባበል ምን ይመስላል? የኢሚ ግሬሽን ፖሊሲውስ? አውስትራልያ ያደገች ሀገር እንደመሆ ኗ የሰው ኃይል ትፈልጋለች። በዚያ ሰፊ መሬት ላይ ከ25 ሚሊዮን የማይበልጥ ህዝብ ነው ያላት። ገና ብዙ ህዝብ የሚ ሰፈርባት ነች። አሰፋፈሩ ግን ያለውን ሁ ኔታ እና የኑሮ ደረጃ ሳይለወጥ መሆን አ ለበት። ለእንያንዳንዱ ነገር በፖሊሲ ደረ ጃ ያስቀመጡት ነገር አለ። ለምሳሌ የዋ ጋ ግሽበት እና የስራ አጥ ብዛት የት ድረ ስ ተቀባይነት እንዳለው ያስቀመጡት ነ ገር አለ። በዚህ ፖሊሲ ላይ ተጽእኖ ያለ ው ምንም አይነት የአሰፋፈር ሁኔታ አይ ቀበሉም። እዚያ ለመስፈር የሚፈልገው ሰው ቁጥር ደግሞ ከፍተኛ ነው። አውስትራልያ በዩ.ኤን.ኤች. ሲ. አር የ ሚመሩላትን ስደተኞች ትቀበላለች፡፡ ች ግሩ ያለው በግል “ስፖንሰር” ተድርገው የሚመጡት ጋር ነው። እንደ ፊጂ እና ፖ ለኔዥያን ደሴቶች ካሉ ጎረቤት ሀገሮች፣ ከኤንዶኔዥያ፣ ማሌዥያ፣ ቬትናም፣ጃፓ ን፣ ኮሪያ፣ ቻይና ፍልሰቱ በጣም ከፍተ ኛ ነው። ከእነዚህ ሀገራት በጀልባ የሚ መጣው ስደተኛ ብዙ ከመሆኑ የተነሳ ካ ምፖች መስርተዋል። ካምፖቹ የተከፈቱ ት የአውስትራልያ ዋናው መሬት ላይ ሳ ይሆን ደሴቶች ላይ ነው። በእነዚህ ካም ፕ ውስጥ ያሉትን እያጣሩ የሚገባቸው ን ሰዎች እየመረጡ ነው የሚያስገቡት። በቅርቡ ከጎረቤት ሀገሮች የአሁኗ ጠቅ ላይ ሚኒስቴሯ ጎረቤት ሀገሮች ከአንዱ ጋር ስምምነት ተፈራርመው ካምፕ ው ስጥ የሞነሩ ስደተኞችን ወስደው ስምም ነት የተፈራረመው ሀገር ወስደው አስፍ ረዋቸዋል። ይህ የተደረገው በአውስትራ ልያ ፖለቲከኞች ላይ ግፊቱ ከመጨመሩ የተነሳ ነው። የስደተኛ ጉዳይ ትልቅ የፖ ለቲካ አጀንዳ ነው። አዲሲቷ ጠቅላይ ሚኒስቴር ከመመረ ጧ በፊት አንዱ የምርጫ ቅስቀሳ አጀን ዳዋ የነበረው “አዲስ የኢሚግሬሽን ፖ ሊሲ አመጣለሁ” የሚል እንደነበር አስ ታውሳለሁ። ትክክል ነው። የቀድሞው ጠቅላይ ሚ ኒስቴር ኬቨን ራድ በተመረጠ ጊዜ እስ ከ 180 ሺህ ስደተኛ ለማስገባት ቃል ገ ብተው ነበር። እርሷ ስትመረጥ ግን በዓ መት ከ145ሺህ ስደተኛ በላይ አይገባም ብላ ነበር። ምክንያቷ ደግሞ አሁን ያለን በት ኢኮኖሚያችን ከዚህ በላይ አይሸከ ምም በሚል ነበር። አንዱ የምርጫ መ ወዳዳሪያ አጀንዳዋ ይሄ ነበር። የተቃዋ ሚው መሪ ቶኒ አቦት እኛ የተሻለ “ኢ ሚግሬሽን ፖሊሲ” እናጠብቃለን እያለ ይሞግታት ነበር። እርሷ ግን “አንተ ኢ ሚግሬሽን ፖሊሲ አጠብቃለሁ የምትለ ው በዓመት 170 ሺህ ስደተኛ እቀበላለ ሁ ብለህ ነው። እኔ ተሰርቶ በተጠናቀቀ ፖሊሲዬ 145 ሺህ ስደተኛ ለመቀበል ነ ው ያቀድኩት። እንዴት አድርጎ ነው ያን ተ ከእኔ የተሻለ ፖሊሲ ሊሆን የሚችለ ው” ብላ በክርክራቸው ወቅት ስትናገር አዳምጫለሁ። ለጨልጩ የከተማው መብራት ለአፍታ የፈለቀበት የመሰለ በራሪ ነገር ወደ ወደ ቡ አቅጣጫ ሲበር አየሁ”” ‘ዝናብ ያረጠ በው አሞራ ይሆናል፣ ወይም አይኔ ነው’ እያልኩ እየተገረምኩ ሳስብ መቅደስ መ ጣችና ራሴን ዳበሰችኝ። “ብጠራሽ ምን ሆንሽ፤ አትሰሚም?” “ጠራኸኝ?” በቀጣዩ እትም የዚህን ትረካ የመጨረሻ ክፍል እናቀርባለን። * ልፎ ማለት ወንዶች ሲገረዙ ከብል ታቸው ተቆርጦ የሚቀበረው (የሚጣለ ው) ቁራጭ ነው። ይህ አጭር ልቦለድ የተወሰደው አዳም ረታ በቅርቡ ካሳተመው አምስተኛ መጽሀፉ “ያመጣል መንገድ፣ ይወስዳል መንገድ” ነው


ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ሐበሻዊ ቃና

23

አንድሬ-የቼልሲ አዲሱ ሞሪንሆ? 5

ስፖርት ነጥቦች ለኢትዮጵያ ቡና በኤርሚያስ አማረ- ቤልጅየም

በካሳሁን ይልማ በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

“በዋናዎቹ የሀገር ውስጥ እና ሻምፕዮን ስ ሊግ ውድድሮች ለታላቅ ስኬት ይመራ ናል” ይላል የቼልሲ ድረ ገፅ ከአዲስ ተ ቀጣሪው አሰልጣኝ የሚጠብቀውን በግ ልፅ ሲያውጅ:: ቼልሲ በአብራሞቪች አገ ዛዝ ዘመን ስምንት የሀገር ውስጥ ዋንጫ ዎች ሲያገኝ፣ አራት ጊዜ የሻምፕዮንስ ሊ ግ ግማሽ ፍፃሜ እና አንድ የዋንጫ ተፋላ ሚ መሆኑ ሲታይ ግን የአሰልጣኙን የቤ ት ስራ ከባድ ያደርገዋል:: የ33 ዓመቱ አ ንድሬ ቪላስ ቦአስ የፕሪምየር ሊጉ ወጣ ት አሰልጣኝ ሲሆን ቢሊየነሩ አብራሞቪ ች ሰማያዊዎቹን ከተቆጣጠሩ ካለፉት ስ ምንት ዓመት ወዲህ የተቀጠረ ሰባተኛው አለቃ ነው:: ከአንድሬ መሾም ዕለት ጀምሮ ከሀገሩ ል ጅ ዦዜ ሞሪንሆ ጋራ ማነፃፀር የእንግሊዝ ብዙሃን መገናኛ ስራ ሆኗል:: ነገር ግን አ ሰልጣኙ በቅጥራቸው ማግስት ራሳቸው ን “ስፔሻል ዋን” ብለው ከሰየሙት ሞሪን ሆ ተቃራኒ አቀራረብን መርጧል:: በመ ጀመርያ ዕለት በሰጠው ቃለ መጠይቅ ላ ይም ለደጋፊው ያስተላለፈው መልዕክት ውጤት የሚገኘው በቡድኑ እንጂ በአን ድ ግለሰብ እንዳልሆነ ነው:: “ከአንድ ሰ ው ምንም አትጠብቁ” ብሏል ለክለቡ ቲ ቪ:: “በጋራ ስራ በሚገኝ ጥምረት የቡድን ጥንካሬ እንድንፈጥር ጠብቁ:: ይህም ለአ ዲሱ አመራር ወሳኝ እና አስፈላጊ ነው:: የ እኔ መምጣት ሳይሆን ዋናው ቁም ነገር የ ክለቡ ውጤታማነት ቀጣይ መሆኑ ነው” ያለው ፖርቱጋላዊ ከኃላፊነቱ ብዙ እንደ ሚፈለግ አልሸሸገም:: “የእኔ ፈተና በማሸ ነፍ መቀጠል እንደሆን ምንም ጥርጥር የ ለውም:: አንድ ሰው ብሆንም የስኬት ጥ ማቱ አለኝ:” ብሏል ቪላስ ቦአስ:: ቼልሲ ለአሰልጣኙ 4.4 ሚልዮን ፓው

“አርሰናል... ከገጽ 24 የዞረ ከ40ሺህ ፓውንድ ሳምንታዊ ደሞዝ የ ተሻለ ክፍያ እንዲቀርብለት ወኪሉ መ ወትወቱ የሚገርም አይሆንም:: የኤም ሬትስ ዓመታዊ የትኬት ሽያጭ በ6.5 በመቶ ማሻቀቡ ደጋፊውን እንዳያሸሸ ው እና ገቢ እንዳይቀንስ ተፈርቷል:: ቬንገር በእነዚህ ሁሉ ጥያቄዎች ው ስጥ ተከበውም ቢሆን ከአናታቸው ካ ሉት ማንዩናይትድ፣ ማን ሲቲ እና ቸ ልሲ ጋራ መፎካከር እንደ ክር የቀጠነ ውን የአርሰናል ሕይወታቸውን ይወስ ናል:: የቀድሞ ክብሩን ለመመለስ የሚ ተጋው ሊቨርፑል እና ቶተንሐም ተጨ ማሪዎቹ ተቀናቃኞች ናቸው :: የክፍያ መጠኑን ከግምት በማስገባት የአርሰና ል የግዢ ዝርዝር ውስጥ ሊካተቱ የሚ

“ቡና ገበያ... ከገጽ 24 የዞረ ስ ዘጠኝ ጊዜ ዋንጫውን ሲያነሳ ፣ መብ ራትና ሀዋሳ ከነማ እኩል ሁለት ጊዜ አግ ኝተዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቡድን ቡና አሁን አራተኛ ሆኖ ተመዘግቧል፡፡ ቡና የዘንድሮውን ዋንጫ በማሸነፉ 100 ሺ ብር ሲሸለም፣ ሁለተኛ የወጣው ጊዮርጊስ 50ሺ፣ ሶስተኛ የወጣው ደደ ቢት ደግሞ 25 ሺ ብር ተቀብለዋል፡፡ ቡ ና እና ጊዮርጊስን ከዋንጫ ያለያየው 1 ነ ጥብ ነው፡፡ ቡና 61፣ ጊዮርጊስ በበኩሉ 60 ነጥብ አስመዝግበው ነው ውድድሩ ን የጨረሱት፡፡ ለቡና ወሳኝ በነበረው የ መጨረሻው የሙገር ጨዋታ ቡድኑ ሶስ ት ሙሉ ነጥብ ቋጥሮ እንዲወጣ ያስቻለ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንደተጠናቀቀ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጋዜጠኛ ሰ ለሞን ክፍሌ ጋር አጭር የስልክ ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለ ብ መሥራችና የሥራ አመራር ቦርድ አባል መቶ አለቃ ፈቃደ ማሞ “ፕሪምየር ሊጉ በአዲስ ፎርማት ከተጀመረ አንስቶ የተለያዩ አስተዳደራዊ በደሎችን ስናስ ተናግድ ቆይተን ለዚህ ድል በመብቃታችን ተደስተናል” ብለዋል፡፡ የተገኘውን ድል ማጣጣም ራሱን የቻለ ቦታ ቢኖረውም በቀጣይ ስለ ወደፊቱ ማሰብ ግን ቡናን ወደኋላ ሲጎትቱት ከነበሩት ውስጣዊ ጣጣዎች ለመላቀቅ መንደርደሪያ ሊሆን ይገባል፡፡ ለዛሬ አምስት ነጥብ ነጥቦች ይታዩኛል፡፡

አዲሱ የቼልሲ አሰልጣኝ አንድሬ “እግር ኳስ የአንድ ሰው ትርኢት አይደለም” በማለት የሞሪንሆን “ስፔሻል ዋን” ፍልስፍና ወደ “ግሩፕ ዋን” ቀይሮታል

ንድ ዓመታዊ ደመወዝ ለመክፈል ሲስማ ማ ከፖርቶ ጋራ የነበረውን ውል ለማፍ ረስ የወጣው ወጪ ግን ከፍተኛ ዋጋ አስ ከፍሏል:: እግረ መንገዱንም በወጣቱ መ ሪ ላይ ያለውን አመኔታም አረጋግጧል:: 13.3 ሚልዮን ፓውንድ ለፖርቶ ካሳ ሲ ከፍል ያላቅማማው የአብራሞቪች አመ ራር እ.ኤ.አ ከ2004 ወዲህ አሰልጣኝ ለ መቅጠር እና ለማባረር 64 ሚልዮን ፓ ውንድ አውጥቷል:: ቀጣዩ ስራ ደግሞ አሰልጣኙ የሚፈልገ ውን ተጨዋቾች ለመግዛት የማይጎድለ ውን የሩሲያዊውን ሳምሶናይት ይዞ መን ቀሳቀስ ነው:: አንድሬ የአሰልጣኝ ቡድኑን ከፖርቶ በማምጣት ሲያጠናክር የቀድሞ የቸልሲ ኮከብ እና አምና ዌስትብሮምዊ ችን የመራውን ሮቤርቶ ዲማቴዮን ረዳቱ አድርጎ ሾሟል:: ከዚህ ቀደም ለሞሪንሆ በፖርቶ፣ ቼልሲ እና ኢንተር ሚላን ለሰባ

ት ዓመታት የተጨዋች መልማይ ሆኖ ማ ገልገሉ ለአሁኑ ስራው የሚሆኑ ተሰላፊዎ ችን ለማግኘት እንዳይቸገር ይረዳዋል:: ባለፈው ዓመት ፖርቶን ለአራት ዋንጫ ዎች ካበቃ ጀምሮ ከሞሪንሆ ጋራ ንግግ ር ማቆሙ ኮሎምብያዊውን አጥቂ ራዳ ሜል ፋላካኦን ለመግዛት የሚያደርጉትን ፍጥጫ አጓጊ አድርጎታል:: “ምርጥ ተጨ ዋቾች ቢኖሩንም ቡድኑን ለማጠናከር ሌ ሎችን ማስፈረም ያስፈልጋል” ያለው ቦአ ስ ከሞሪንሆ መልማይነት በሁለት ዓመታ ት ልዩነት ውስጥ የቼልሲ አሰልጣኝ መሆ ኑ እንደደነቀው ገልፅዋል:: “የሆነ እብደት ቢመስልም ከእውነታው መደበቅ አልች ልም:: ወጣት ብሆንም ልምዱን ለማግኘ ት እድሉን መጠቀም አለብኝ:: ፖርቶንም ሆነ ቼልሲን የዦዜን ፈለግ ለመከተል ብ ዬ አልተቀበልኩም:: ሁለቱም ክለቦች በዓ ለም የሚፈለጉ ናቸው:: የእኔና የሞሪንሆ

የሰባት ዓመት ግንኙነት ሞያዊ እና በጥሩ ጓደኝነት ላይ የተመሰረተ ነው:: ከእንደእ ርሱ ያለ አሰልጣኝ ጋራ ስትነፃፀር የበለጠ ኃላፊነት ይሰማሃል::” በእግር ኳስ ውስጥ ውስጣዊ ተነሳሽነት ቁልፍ ሚና ስለመጫወቱ ፍፁም እምነት እንዳለው የሚናገርው አንድሬ ከሞሪን ሆ ጥላ ለመውጣት የቼልሲን የረዥም ጊ ዜ ጥማት የሆነውን የሻምፕዮንስ ሊግ ዋ ንጫን ለአብራሞሺች ማበርከት ያስፈልገ ዋል:: ይህንንም ከግብ ለማድረስ ስታም ፎርድ ብሪጅን ጥራት ባላቸው ተጨዋ ቾች ለመገንባት ወጥኗል:: ለዚህም ፋል ካኦ፣ ሉካ ሞድሪች፣ ሳሚር ናስሪ እና ዦ አኦ ሙቲንሆን በግዢ እቅዱ ውስጥ አስ ገብቷል:: “ስፔሻል ዋንን” ወደ “ግሩፕ ዋ ን” ቀይሮታል “እግር ኳስ የአንድ ሰው ት ርኢት አይደለም” በማለት:: “እኔ” ሳይሆ ን “እኛ!”

ችሉ ተጨዋቾች ወጣት እና የግል ችሎ ታቸው ላቅ ያሉ ነገርግን ለመሻሻል የተ ጠሙእንደሚሆኑ እርግጥ ነው:: አስራ አንድ ሚልዮን ፓውንድ የወጣ በት የቡድኑ የመጀመርያ ፈራሚ አይቮ ሪኮስታዊው አጥቂ ጀርቪንሆ ከላይ የ ተባለውን መስፈርት የሚያሟላ ሲሆን ሌላኛው እጩ አርጀንቲናዊው ሪኪ አ ልቫሬዝ የመሐል ሜዳ አቀናባሪነት ሚ ናን ከፋብሪጋስ ይረከባል ተብሎ ይጠ በቃል:: የ24 ዓመቱን አማካይ ዝውው ር ለማሳካት ከኢንተር ሚላን ጋራ መፎ ካከር ያስፈልጋል:: የሳውዝሃምፕተኑ የ17 ዓመት የመስመር ተሰላፊ አሌክስ ቻምበርሊን የዋልኮትን ፈለግ ተከትሎ ወደ ኤምሬትስ ይመጣል ተብሎ ቢታ ሰብም እስካሁን ከወሬ የዘለለ ነገር አ ልታየም:: የክለቡ አሰልጣኝ ኒጀል አድ ኪንስም “ተጨባጭ የዝውውር ጥያቄ ከአርሰናል እንዳልቀረበላቸው” አረጋግ

ጠዋል። “ባለፈው ጥርም ይሄዳል ሲባ ል ነበር:: አሁንም ይወጣል የሚሉ ዜና ዎች ከመሰማታቸው በስተቀር አርሰና ልም ሆነ ሌላ ክለብ በራችንን አላንኳኳ ም” ሲሉ ገልፀዋል:: ሌላው እንቆቅልሽ የአንድሬ አርሻቪ ን ጉዳይ እልባት አለማግኘቱ ነው:: የባ ለፈው ዓመት እንቅስቃሴው ደካማነት ቆይታውን አጠያያቂ አድርጎታል:: አም ና ተከላካዮቹን ኮስቼንሊ እና ስኪላቺ በማስፈረም የተፈጠረው ስሕተት እን ዳይደገም የፕሪምየር ሊጉ ልምድ ያላቸ ው የቦልተኑ ጋሪ ካሂል፣ የብላክበርኑ ክ ሪስቶፈር ሳምባ እና የኤቨርተኑ ሲልቪ ያን ዲስታን ላይ አነጣጥረዋል:: የክሊ ሺን ቦታ ኬራን ጂብስ ወይም ቶማስ ቨ ርማለንን ወደ ግራ መስመር በመግፋት መተካት ሌላኛው አማራጭ ይሆናል:: የቡድኑ አስተዳደር አሰራሩን የማይቀ ይር እና የቬንገር ፍልስፍና ባለበት የ

ሚፀና ከሆነ አርሰናል በአዲሱ ውድድ ር ዘመን የሚቀርበው በእነዚህ ተጨዋ ቾች ነው:: የቡድኑን ተጨዋቾች ሊነጥ ቁ የመሚመጡ ቱጃር እና ባላንጣ ክለ ቦችን ከበር ለመመለስ የሚያስችል ዘ ዴ ያስፈልጋቸዋል:: አለበለዝያ የናስሪ እና የፍላሚኒ ዓይነት ክስተቶች በመ ጪዎቹ ዓመታትም ከመድፈኞቹ ጋራ ተያይዘው የሚነሱ ዜናዎች ይሆናሉ:: አርሰናሎች አምና ሜዳ ላይ ነጥብ ለ ማግኘት ተፎካክረው ሊሆን ይቸላል:: የግዢ ገበያው ላይም ጥረት ያደርጉ ይ ሆናል:: ይሁን እንጂ ስብስቡ የብዙኃኑ ን ደጋፊ ፍላጎት በበቂ ሁኔታ ይመልሳ ል ወይ የሚለው ጥያቄ እንዳወያየ ይቀ ጥላል:: ታዋቂው ተንታኝ ማርቲን ሳ ሙኤልም ይህን ከግምት አስገብቶ ይ መስላል “ተቀበሉት፣ አርሰናል ከእንግ ዲህ ኮከቦችን የሚስብ ሊሆን አይችል ም” ያለው::

ውን ሁለተኛውን እና የመዝጊያውን ጎል ያስቆጠረው 17 ቁጥር ለባሹ አጥቂ መድ ሀኔ ታደሰ ነበር። ይህ ተጨዋች ቡና የ ዚህ ዓመት የመጀመሪያ ጨዋታውን ከ ሲዳማ ቡና ጋር ይርጋለም ላይ ሲያደር ግ የመጀመሪያውን ጎል ያስቆጠረ ነበር፡ ፡ የቡና መጀመሪያውም፣ የመጨረሻው ም ግቦች የእርሱ ሆነዋል፡፡ እንደ መድሀኔ ሁሉ የቡናው አምበል ግ ጥምጥሞሽም ያስገርማል። የአምበሉ ስ ም እድሉ ደረጀ ነው። እውነትም እንደ ስሙ እድለኛ ነው፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ለ ቡና የመጀመሪያውን ዋንጫ አንስቷል፡፡ እድሉ ቡና ውስጥ ረጅም አመት የቆየ ተ ጨዋች ነው፡፡ የመጨረሻው ጨዋታ አ ንዳለቀ በለማመን ስሜት ራሱን ይዞ ሜ ዳ ላይ ቁጭ ብሎ ነበር፡፡ የ32 ዓመቱ እ ድሉ ደረጀ በሰው ኃይል አመራር ማኔጅ

መንት ዘንድሮ ይመረቃል፡፡ እንደ እድሉ ሁሉ ሌላው የቡና ተጫዋች አራዶምም በዚህ ዓመት ነው የሚመረቀው። የቡና ሌሎች ተጫዋቾች የትምህርት ደረጃም ከፍ ያለ ነው፡፡ በረኛው ወንድወሰን ዲ ግሪ አለው፣ ተስፋዬ ቢያቋርጥም የሕክ ምና ተማሪ ነበር። “እየተማርን ዋንጫ እ ንበላለን”፤ “እየተጫወትንም እንማራለ ን” ነው ነገሩ። ለቡና የዘንድሮ ውጤት ማማር ከፍተ ኛ አስተዋጾኦ ያደረጉት መሀል ሜዳ ያሉ ተጨዋቾች ናቸው፡፡ በተለይ ዳዊት፣ መ ሱድና ምንያህል ይጠቀሳሉ፡፡ በፕሪሚየ ር ሊግ ታሪክ የመጀመሪያ ዋንጫ በማም ጣታቸው ተጫዋቾቹ ሪከርድ ሽልማት አንደሚሰጣቸው እየተነገረ ነው፡፡ ደጋ ፊ ማህበሩ ለአሰልጣኙ መኪና ሊገዛ እ የተዘጋጀ ነው፡፡ ሰኔ 28 ቀን 2003 አዲ

ስ አበባ ስታዲየም አጠገብ ባለ ሆት ስፖ ት ሆቴል ውስጥ የቡና ደጋፊዎች ግብዣ አዘጋጅተው ነበር፡፡ ጭፈራውና ግብዣ ው የደመቀ ነበር፡፡ ሁሉም ቢጫ ማሊያ አድርገው የዋንጫውን ድል በደስታ አ ጣጥመውታል። ደጋፊው ለቡድናችን ውጤት ለአስገኙ ት ሽልማት ይገባቸዋል በሚል በየቦታ ው የተለያየ ዝግጅት እያደረገ ነው፡፡ አ ዲሱ የደጋፊ ማህበር ብዙ የአሰራር ለው ጥ በማድረግ፣ በደጋፊው ውስጥ ንቅናቄ በመፍጠር፣ ለተጫዋቾቹ ትጥቅ በማቅ ረብ እና ሞራል በመስጠት ለዋንጫው መገኘት ትልቅ ምክንያት ሆኗል፡፡ ይህ ጹሁፍ የተወሰደው ገነነ መኩሪያ ቀድሞ ያዘጋጀው በነበረው ጋዜጣው ስም ከከፈተው እና ሊብሮ ዶት ኮም ከተሰኘው ድረ ገጽ ሲሆን መጠነኛ አርትኦት ተደርጎበታል

1. የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ፡የዘንድሮው ሊግ በቡና አሸናፊነት መጠናቀቁ በቀጣይ የውድድር ዘመን ለሌ ሎች ክለቦቸም የሞራል ስንቅ ይሆናቸዋል፤ “ዋንጫ ማንሳት እንችላለን” የሚ ል ተስፋም ያስጨብጣቸዋል፡፡ ዋንጫ የለመደው ጊዮርጊስም ቢሆን በባላንጣ ው ትልቁን ዋንጫ መነጠቁ ከፍተኛ ቁጭት ውስጥ ይከተዋል፡፡ በዚህም የተነ ሳ የ2004 ፕሪምየር ሊግ ጥልቅ ፉክክር የሚታይበት ይሆናል፡፡ ደደቢት፣ ቡና እና ጊዮርጊስ ሊጉን የሶስት ፈረሶች ፉክክር ያደርጉታል፡፡ የመጀመሪያው የቡና ፈተና እዚህ ጋር ይሆናል፡፡

2. የካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ፡ከ1990 ዓ.ም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቡና ወደ ካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድ ር ተመልሷል፡፡ የኢትዮጵያ ክለቦች ብቃት በዚህ መድረክ ደከም ያለ በመሆኑ ቡድኑ የማጣሪያ ማጣሪያ ውስጥ ለመግባት ይገደዳል፡፡ በዚህ መድረክ መካፈ ል አዲስ የበጀት ርዕስ ይዞ ይመጣል፡፡ ቢያንስ አንድ የውጪ ጉዞ፤ በለስ ከቀና ቸው ደግሞ ሁለት እና ሶስት ጊዜ በአየር መብረራቸው አይቀርም፡፡ በአህጉራ ዊው መድረክ ላይ ብቁ ሆኖ ለመቅረብ ደግሞ የፋይናንስ አቅምን ማጎልበት በ እጅጉ ያስፈልጋል፡፡ የሥራ አመራር ቦርዱ እና አዲሱ የደጋፊ ማህበር በዚህ በ ኩል ትልቅ የቤት ሥራ ይጠብቃቸዋል፡፡

3. የዝውውር ገበያው፡ክለቡ ከዋንጫው በኋላ በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባደረገው ስብሰባ የአሁ ኑን ድል ተንተርሶ በቀጣይ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ለማሰባሰብ ዕቅድ ነድፏል፡ ፡ ይህ ዕቅድ መሬት ወርዶ ፍሬው የማይታይ ከሆነ ግን በተጫዋቾች ዝውው ር ላይ ትልቅ ፈተና ይፈጥርባቸዋል፡፡ ያሉትን ተጫዋቾች ለማሰንበትና አዳዲ ሶችን ለማስፈረም ቢያንስ 1.5 ሚሊዮን ብር ያስፈልጋል፡፡ በዝውውር ገበያው የክለቦች ጡንቻ ከዓመት ወደ ዓመት እየፈረጠመ መጥቷል፡፡ ቡና ዋንጫ ስላ ነሳ ብቻ የሚፈልገውን ተጫዋች የራሱ ማድረግ አይችልም፡፡ በድጋሚ በዝው ውር ገበያው ከተፎካካሪዎች አጠገብ ለመቆም ፋይናንስ ቁልፍ ጉዳይ ነው፡፡

4. የደጋፊዎች ሚና፡አሁን በኃላፊነት ላይ ያለው የደጋፊዎች ማህበር ጠንክሮ በመስራቱ ብዙ ነገሮ ችን ተከላክሎ ከውጤት ማማ ላይ ለመውጣት በቅቷል፡፡ ከዚህ በፊት በተደጋ ጋሚ እንደታየው በቡና ጓዳ ረጃጅም እጆች ይበዛሉ፤ አዛዡ ብዙ ነው፡፡ እነዚ ህ እጆች መረማመጃ የሚያደርጉት ደግሞ የራሱን ደጋፊዎች ነው፡፡ የደጋፊዎች መብትና እና ግዴታ ብሎም ሚናቸው ወሰን እና ልክ ካልተበጀለት በድል ማግ ስት ሌላ ችግር ይዞ ይመጣል፡፡

5. አስተዳዳሪዎቹ፡የቀድሞው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ዶክተር አሸብር ወ ልደ ጊዮርጊስ ግንቦት 8 ቀን 2001 ዓ.ም በሒልተን ሆቴል የስንብት ንግግር ሲ ያደርጉ “ለአንድ ክለብ እየሠራን ነበር” የሚል ማስተባበያ ቢያቀርቡም ቤቱ ሊ ሰማቸው አልፈቀደም፡፡ ጊዜው በመርፈዱ ያቀረቡት “ውንጀላ” አላተረፋቸው ም፡፡ የቡና ኃላፊዎችም ጣታቸውን ወደ ውጪ እየቀሰሩ የውስጥ ችግራቸውን ለመሸፈን የሚያደርጉት ሩጫ ከአሁን በኋላ ውሃ የማንሳት አቅሙ የወረደ ይ ሆናል፡፡ አመራሩ ራዕይ እና ግብ ይዞ ካልተነሳ አወዳደቁ የከፋ ይሆናል፡፡ በተ ለይ በጽህፈት ቤት አስተዳደር፣ በባለሙያ ቅጥር፣ በገበያ ማስፋፋት እና በክለ ብ አወቃቀር ዙሪያ ያለው ግዙፍ ጉድፍ ለውይይት የሚቀርብበትና መሠረት የ ሚጣልለት ጊዜ ቢኖር አሁን ነው፡፡ ይህ ጹሁፍ ከኤርሚያስ “ፌስ ቡክ” ገጽ የተወሰደ ነው

ማንዩናይትድን... ከገጽ 24 የዞረ ላን ከተማ ቢጓዙ ምናልባት ሰበር ዜና ይ ዘው ሊመጡ ይችላሉ:: ይህም ካልተሳካ ዋንጫ በታሪኬ ውስጥ እንዲካተት ስለ ምፈልግ ኋይት ኅርት ሌን በቃኝ የሚለ ው ጥበበኛው ሉካ ሞድሪች አማራጭ አ ላቸው:: ክሮሽያዊው ለአሰልጣኙ ሀሪ ሬ ድናፕ አሰናብቱኝ ማለቱ አሰፍስፈው ለ ሚጠብቁት ቼልሲ እና ዩናይትድ የምስ ራች ነው:: ስለዚህ የገንዘብ ችግር የሌለ ባቸው ፈርጉሰን ተቀናቃኛቸውን ቼልሲ ን መቅደም ይጠበቅባቸዋል:: ፈርጉሰን ከግዢ ዘመቻቸው ጎን ለጎን አ ላስፈላጊ ተጨዋቾችን በሽያጭ እያሰናበ ቱ ነው። በሻምዮንስ ሊግ ፍፃሜ ከተጠባ ባቂ አሰላለፍ ውጪ የሆነው አጥቂው ቤ

ርባቶቭ ቀዳሚው ተጠቃሽ ነው። ተከላ ካዩ ጆን ኦሼ የኦልድ ትራፎርድ ትዝታ ለመሆን ክለብ ሲያፈላልግ ዌስ ብራው ን ሰንደርላንድን ተቀላቅሏል:: ቤርባቶቭ መድረሻው ቫሌንሲያ ወይም ጁቬንቱስ ይሆናል ተብሎ እየተወራ ነው:: የቀድሞው የቀኝ መስመር ተከላካይ ጋ ሪ ኔቭል የዩናይትድ አካሄድን በማየት መጪውን የኦልድ ትራፎርድ ብሩኅ ጊዜ ተንብይዋል:: “ውጤት የተጠሙ ተጨ ዋቾች ስላሉ የ1999ኙን የአውሮፓ ድል የመድገም ተስፋ አላቸው:: ምክንያቱም እኛም ዋንጫ ከማግኘታችን በፊት ለሶስ ት ተከታታይ ዓመታት ከጫፍ እየደረስ ን ተሸንፈናል:: ስለዚህ ተራራውን ለመ ውጣት ከባድ ቢሆንም ማንችስተር እና ሪያል ማድሪድ በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታ ት የባርሳን ዝና ይነጥቁታል” ብሏል::


ሐበሻዊ ቃና

24

ሐምሌ 2- 15 ቀን 2003 (July 9-22, 2011)

ስፖርት

“አርሰናል ኮከቦችን አይስብም” በካሳሁን ይልማ በተለይ ለሐበሻዊ ቃና

በሮቢን ቫን ፐርሲ አዕምሮ ውስጥ አ ንድ ጥያቄ ይመሳሰላል:: የቡድን አጋሮ ቹ በኤምሬትስ የመውጫ በር ላይ መሆ ን ግርታ ቢፈጥርብትም እውነታውን በ ሚገባ ተርድቶታል:: ፋብሪጋስን እና ናስ ሪን ለመተቸት ከመጣደፍ ይልቅ ምክን ያታዊነትን ማየት መርጧል::“ አርሰናል ከተጫዋች ጋራ የደመወዝን ሁኔታ ሲደ ራደር ከተወሰነ ጣራ በላይ ፈቀቅ አይል ም” ይላል ሆላንዳዊው ሲያስረዳ:: “ ክለ ቡ የተትረፈረፈ ገንዘብ አይከፍልም:: ች ግሩን ለመቅረፍ ይህን ማሻሻል እና ወደ ከፍተኛ ክፍያ ማሳደግ አለባቸው :: 27 እና 28 ዓመት ዕድሜ ላይ ከደረስክ ሶስ ት እና አራት እጥፍ ወደ ምታገኝበት ሌ ላ ቦታ የመሄድ ውሳኔን እረዳለሁ:: ያን የሚያህል ክፍያ ደግሞ አርሰናል የሚያ ቀርብ ከሆነ ተጨዋቹ የመልቀቅ ፍላጎት አይኖረውም::” እንደዚህ ያለ ቀውስ ለመድፈኞቹ አዲ ስ አይደለም:: በ2008 የውድድር ዓመ ት መጨረሻ ላይ ማቲዩ ፍላሚኒ በቦስ ማን ሕግ (ነፃ ዝውውር) ወደ ኤሲ ሚ ላን መጓዝ እና የአሌክሳንደር ህሌብ በባ ርሴሎና እይታ ውስጥ መውደቅ ከዘንድ ሮው ክስተት ጋራ ያመሳስለዋል:: በወ ቅቱ የቁልፍ ተጨዋቾች ክለቡን ለመል ቀቅ መወሰን በሌሎች ተጨዋቾች ላይ የሚፈጠረው ስነ ልቡናዊ ተፅእኖ ስጋት ቢፈጥርም “ፕሮፌሰሩ” ቬንገር ስምንት ጊዜ ብቻ ለፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ወ ደተሰለፈው ሳሚር ናስሪ ፊታቸውን ለ ማዞር ጊዜ አልወሰደባቸውም:: ሶስት ዓመት ወደፊት ስንመጣ ታሪክ ራሱን ሊደግም ተቃርቧል:: በራሪው ሴ ስክ ፋብሪጋስ ወደ እናት ክለቡ ባርሴሎ ና፣ ናስሪ ሊቀራመቱት ካሰፈሰፉት የተ

መቸውን ለመምረጥ ሲዘጋጅ፣ ጋኤል ክ ሊሺ ገንዘብ “ለሚበትነው” ማን ሲቲ ፊ ርማውን አኑሯል:: ናስሪ የኤምሬትስ የ ደሞዝ ጫፍ የሆነው 90 ሺህ ፓውንድ ቀረቦለት አሻፈረኝ ማለት ግርምትን ፈጥ ሯል:: እምቢታው ፈላጊ ክለቦቹ ምንያህ ል የላቀ ክፍያ እንዳላቸው ያሳያል:: እና ም የአርሰናል የደመወዝ እርከን ባጣ ቆየ ኝ አድርጎ እየጠለፈው ነው:: የአዲሱ ውድድር ዓመት ዝግጅት በተ ጀመረበት በዚህ ሳምንት የቬንገር ቡድ ን መረጋጋት ውስጥ አይደለም:: ሰውዬ ው የቡድናችውን አምበል ፋብሪጋስን እ ና ናስሪን ለማሳመን ፈታኝ ድርድር ሲ ጠብቃቸው ብቁ ማጠናከርያ ተጨዋቾ ችን ለማስፈረም ጊዜአቸውን በአግባቡ መጠቀም አለባቸው:: በሁለቱም ሩጫ ዎች ለአሰልጣኙ ወሳኝ ሚና የሚጫወተ ው ፓውንድ ነው:: ከለንደኑ ክለብ ልው ጣ ለሚሉት በቂ ክፍያ ከማቅረበ ባሻገ ር እነርሱን ሐሳብ ለማስለወጥ ምርጥ ተ ጨዋቾችን መግዛት እንዲሁም አሳማኝ ፕሮጀክት መንደፍ ይጠበቅባቸዋል:: ኮ ከቦችን ለማስፈረም ደግሞ የክለቡን ካ ዝና መነቅነቅ ግድ ይላል:: በእርግጥ ቬንገር የበቁ ኢኮኖሚስት ና ቸው:: የአርሴናል “ራስን በአስተማማኝ ሁኔታ የመቻል ሞዴል” ጥሩ ፍሬ አሳይ ቷል:: በዋናው የክለቡ ባለቤት ስታን ክ ሮኤንክ የተወደደውም ይኸው አሰራር ነ ው :: ከደመወዝ ወጪ 50 በመቶ አትራ ፊ ሆነዋል :: ይሁን እንጂ አካሄዱ እያደ ር ከተፎካካሪነት ሐዲድ ውጪ እያደረ ጋቸው ነው:: እ.ኤ.አ በ2008 ማንችስተ ር ሲቲ የገንዘብ ጡንቻው እንደዛሬው አ ልፈረጠመም:: ቶተንሐሞችም ቢሆን የ ላይኛውን የደረጃ ሰንጠረዥ አያውቁት ም ነበር:: ልብ የሚያሸፍት የደመወዝ ክ ፍያ ከሚከፍሉ ክለቦች አንፃር ሲታይ አ ርሰናል አምስተኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ ለ

(ከላይ በስተግራ) ፋብሪጋስን እና ናስሪ በኤምሬትስ የመውጫ በር ላይ ናቸው (ከላይ መሃል) አይቮሪኮስታዊው አጥቂ ጀርቪንሆ (ከላይ በስተቀኝ) አርጀንቲናዊው ሪኪ አልቫሬዝ የመሐል ሜዳ አቀናባሪነት ሚናን ከፋብሪጋስ ይረከባል ተብሎ ይጠበቃል ጋኤል ክሊሺ ገንዘብ “ለሚበትነው” ማን ማንችስተር ሲቲ ፊርማውን አኑሯል

እነዚህ መጤ ባላንጣዎች ክፍተት እየሰ ጣችው ነው:: አዲስ ተጨዋቾችን ለመመልመል ቬን ገር ገንዘብ አላጡም:: ከአምና ብቻ ያል ተጠቀሙበት 30 ሚልዮን ፓውንድ አላ ቸው። ከክሊሺ ሽያጭ የተገኘው ሰባት ሚሊዮን ፓውንድ እና ከፋብሪጋስ እና ከቤንድትነር ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ ጋራ ሲደማመር የደጋፊውን አንገት ቀና የሚ ያስደርግ ተጨዋች ማምጣት ይቻላል::

“ቡና ገበያ አደገኛ!” ቀኑ ሰኔ 20 ቀን 2003 ዓ.ም ነው። ሙ ገር እና ቡና የፕሪሚየር ሊጉን የመዝጊያ ጨዋታ ለማድረግ እየተዘጋጁ ነው፡፡ የ ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን ይህን ጨዋታ ካሸነፈ ዋንጫውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያነሳ በመሆኑ ይህንን ታሪክ ለ መመልከት በርካታ ተመልካች ለገሀር የ ሚገኘውን የአዲስ አበባ ስታዲየም አጨ ናንቆታል፡፡ ወደ ስታዲየም ለመግባት የ ነበረው ግፊያ የተነሳ የአንድ ሰው ህይወ ት ያሳጣ ነበር።

እንዲህ ለገሃር ከሚገኘው የአዲስ አበባ ስታዲያም አንስቶ እስከ ዋሸንግተን ዲ ሲ ባሉ የቡና ደጋፊና የቀድሞ ተጨዋቾ ች በጉጉት የተጠበቀው ጨዋታ በኢት ዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቋል። ጨዋ ታውን የኢትዮጵያ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥ ን ድርጅት በሳተላይት አማካኝንት በቀ ጥታ በማስተላለፉ በየሀገራቱ ያሉ ደጋፊ ዎች ድሉን አጣጥመውታል፡፡ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ 13 ዓ መት ሲጀመር ከመሰረቱት ከለቦች አን

ዱ የሆነው ቡና የሊጉን ዋንጫ አግኝቶ አያውቅም። ከፕሪሚየር ሊግ መስራቾች ዘንድሮ ያሉት ሶስት ሲሆኑ ሁለቱ ከዚ ህ ቀደም ዋንጫውን ወስደዋል፡፡ ቡና ነበር የቀረው፡፡ ቡናም ቢሆን በ1990ና 1996 ሁለት ጊዜ ዋንጫው ጋር ደርሶ በ መጨረሻው ሰዓት ነው ያጣው፡፡ በፕሪ ሚየር ሊጉ የ13 ዓመት ታሪክ ሶስት ቡድ ኖች ብቻ ነበሩ ዋንጫ ያገኙት፡፡ ጊዮርጊ

የ2003 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ የኢትዮጵያ ቡና ክለብ

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

ምናልባት አሰልጣኙ ለሁዋን ማታ ዝው ውር 20ሚሊዮን ፓውንድ ቫሌንሲያ ጠ ረጴዛ ላይ ሊያስቀምጡ ይችላሉ:: ነገር ግን ለተጨዋቹ አሳማኝ ሳምንታዊ ክፍ ያ ለመክፈል የመድፈራቸው ሁኔታ አጠ ያያቂ ነው:: ናስሪን ሊገዙ ያሰቡት ማን ዩናይትድ እ ና ቸልሲ በሳምንት 150 ሺህ ፓውንድ ሊከፍሉት ፈቃደኛ ናቸው:: ተጨዋቾች ደግሞ በሞያቸው ላይ የሚቆዩት እስከ

የሳውዝሃምፕተኑ የ17 ዓመት የመስመር ተሰላፊ አሌክስ ቻምበርሊን የዋልኮትን ፈለግ ተከትሎ ወደ ኤምሬትስ ይመጣል ተብሎ ተገምቷል

30ዎቹ አጋማሽ እድሜ ስለሆነ የገንዝብ ፍቅር ሰለባ መሆናቸው አይቀሬ ነው:: የ አርሰናል የደመወዝ እርከን አቋም በአሁ ኑ የእግር ኳስ ገበያ የማያዛልቅ ነው:: ና ስሪን ለማቆየት 120ሺህ ፓውንድ ቢቀር ብ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሌሎች ቡ ድኖች የደመወዙን ሒሳብ ሰቅለውት ይ መጣሉ:: ከዚህ የክፍያ ቀውስ በተጨማ ሪ የዋንጫ ድርቅ የተጨዋቹን ፍልሰት አ ፍጥኖታል:: ናስሪም ምክንያቱ የዋንጫ

ጥማት እንደሆነ በግልፅ ተናግሯል:: “ጡ ረታ ስትወጣ ምን አገኘሁ ብለህ ትጠይ ቃለህ” ይላል። ቫን ፐርሲ እና ዋልኮትም የቀራቸው የሁለት ዓመት ኮንትራት ጊዜ ነው:: ታ ዳጊው ጃክ ዊልሸር የእንግሊዝ ብሔራ ዊ ቡድን ተሰላፊ መሆኑ እና ፋብሪጋስ ከለቀቀ እርሱ የቡድኑ ዋልታ ስለሚሆን

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

ማንዩናይትድን ከባርሳ በላይ በካሳሁን ይልማ በተለይ ለሐበሻዊ ቃና ማንችስተር ዩናይትዶች የፕሪምየር ሊ ግ ንግስናቸውን ካረጋገጡ በኋላ በፌሽ ታ ሻምፓኝ ከመክፈት ይልቅ የጭፈራ ስ ነስርዓታቸውን ለድርብ ድል ፈንጠዚያ ከሻምፕዮንስ ሊግ ፍፃሜ መልስ እንዲሆ ን ቀጠሮ አስይዘዋል:: በሁለትዮሽ ድል የ ሚገኝን ደስታ ለማጣጣም በደንብ የሚ ያውቁትን ባርሳ በሀገራቸው ዌምብሌይ ሜዳ ለመደምሰስ ዝግጅታቸውን አጡ ፈዋል:: የዋንጫን መንገድ መቀየስ የሚ ያውቁበት ሰር አሌክስ ፈርጉሰን “ሜሲ ን ለማቆም ልጆቼ ስራቸውን አጠናቀዋ ል ”ሲሉ፣ ልበ ሙሉው ሪዮ ፈርዲናንድ “በ2008 ሮም ላይ የሰራነውን ስኅተት አ ንደግምም” በማለት ፎከረ:: ሩኒም በጨ ዋታው ላይ ሊገኝ እንደሚችል የእንግሊ ዝ ብዙሃን መገናኛዎች ተነበዩ:: ከሜይ 28ቱ የፍፃሜ ጨዋታ 90 ደቂ ቃ በኋላ ፊሽካ ሲሰማ ሜሲንም፣ ባርሳን ም የሚያቆም አንዳች ልዩ ኃይል አልተ ገኘም:: ከዩናይትድ ካምፕ የሚወጡ አ ስተያየቶች “እጅ ሰጥተናል” የሚሉ ሆ ኑ:: አዎ! ባርሳን ለመቋቋም የታክቲክ ጋ ጋታ እና ኳስ የሚያጨናግፉ ተጨዋቾች ን መደርደር ብቻ ሳይሆን ያለእንከን ጨ ዋታን መቆጣጠር እንደሚያስፈልግ ለፈ ርጊ ነጋሪ አላሻቸውም:: “በአሰልጣኝነት ዘመኔ እንደዚህ ያለ ብልጫ ያሳየብኝ እና ኳስ የደበቀብን ቡድን አላየሁም” ሲሉ የ ጨዋ ምስክርነት ሰጥተዋል::

የአስቶንቪላው አሽሊ ያንግ

ከጎምዛዛው ሽንፈት በኋላ የታሰበው የ ጥንድ ዋንጫ ሕልም ባይሳካም የፕሪም የር ሊጉን ጣፋጭ ድል በበረዷማ ዝና ብ ታጅበው አጣጥመዋል:: በሆታው መ ካከል አሰልጣኙ ለደጋፊዎቻቸው ንግግ ር ሲያደርጉ ጆሮ የሚገባ መልዕክት አስ ተላልፈዋል:: “መላው የብሪታንያ ቡድኖ ች የባርሳን የአሰለጣጠን እና የአጨዋወ ት ዘይቤ መከትል አለብን” ሲሉ ቀጣይ እቅዳቸውን በግልፅ አስቀምጠዋል:: “እ ንደ ባርሳ አሳማኝ እግር ኳስን ማሳየት::” እቅዳቸውን ለማሳካት እና ቃላቸውን ለማክበር የእረፍቱ ጊዜ በአግባቡ ተጠ ቅመዋል:: በዌምብሌይ እጃቸው በንዴ ት ሲንቀጠቀጥ በገሃድ የታዩት ስኮትላን ዳዊ የሐሳባቸውን የሚያደርሱላቸው ተ ጨዋቾች ፍለጋ የጀመሩት በጊዜ ነበር:: አሽሊ ያንግን ከአስቶንቪላ፣ አስተማማ ኝ እና ለረዥም ጊዜ የጎል በሮችን የሚ ጠብቅ ወጣት በረኛ ፍለጋ ደግሞ ወደ

ስፔን ተጉዘው ደሄያን ገዝተዋል:: የ19 ዓ መቱን የብላክበርን ተከላካይ ፊል ጆንስ ን በ16.5 ሚልዮን ፓውንድ አስፈርመ ዋል:: ፈርጊ ፈጣሪ ተጨዋች ለማግኘት ሲሉ የጠላታቸውን አርሰናልን በር ለማ ንኳኳትም ፈራ ተባ አላሉም:: ልቡ የሸፈ ተውን ናስሪን ጠይቀዋል:: ቬንገር “በፍፁም የማይታስብ” ቢሉ ም የተጨዋቹ ኮንትራት ተጠናቆ በነፃ እ ንዳይሄድ በማሰብ ጥሩ ዋጋ ከቀረበላቸ ው ሳይዋጥላቸውም ቢሆን መስማማታ ቸው አይቀርም:: ሌላው የቀያይ ሰይጣ ኖቹ እቅድ የኢንተሩ ሽናይደር ነው:: ሆ ላንዳዊው በኔራዙሪ ደስተኛ እንደሆነ መ ናገሩ እና የሞራቲ የማይነካ ልጅ ቢመስ ልም በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ መጫወ ት ናፍቆቱ እንደሆነ መግለፁ ዩናይትዶ ች የግሌዘርን ገንዘብ ተሸክመው ወደሚ

ወደ ገጽ 23 ዞሯል

Habeshawi Kana 003  

Vol 1, 3rd edition

Read more
Read more
Similar to
Popular now
Just for you