ለ አእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6

Page 1

1


ለአእምሮየጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

ይ ዘ ት / Content ***

እራስህን እወቅ (ርዕስ አንቀጽ/Editorial) *

አይዲዮሎጂ ና ፋቡላ ? *

ካሲዮጵያ ና የ“ካሲዮጵያ ማህደር“ *

ከ -ካ ሲ ዮ ጵ ያ እስከ መ ገ ነ ጣ ጠ ል * ቤተ-ክርስቲያን ሲሸጥ ሲለወጥ!

**

ከታሪክ ሰነድ፥ -

የተላከ ከእቴጌ ጣይቱ ብረሃነ ዘኢትዮጵያ -

-

ቀኃሥ ና ማርቲን ሉተር ኪንግ

BLACK GERMAN HOLOCAUST VICTIMS ***

ለአእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6 2


እራስህን እወቅ (ርዕስ አንቀጽ/Editorial) ውድ አንባቢዎች ! የዛሬውን ሕትመታችንን የከፈትነው ለየት በአለ ጥያቄና መልስ ነው። ለዚህም ነው „ርዕዮተ፥ዓለም /አይዲኦሎጂ ወይስ እሴት/ ቫሊዩስ“ ያልነው። 3


መጽሔቱ በአጠቃላይ በርካታ ነጥቦችን አቅፎአል። ሁሉም ጉዳዮች የሚሸከረከሩትደግሞ እግዚአብሔር በሰጠን መብት – አንዳዶቹ ይህን ነገር ተፈጥሮ ነው ይሉታል – „በኢንላይትመንትና በሊበርቲ“ ዙሪያ ነው:- እኔም አንተም ሁላችንም ነጻ-ሰው ነን። አንደኛው -ከወዲሁ ግልጽ ለማድረግ-ሁለት ፍልስፍናዎችና ትምህርቶች ከጀርመን ተነስተው „የዓለም ሕዝብ ሁሉ በዚህ ሥርዓት ውስጥ የግድ መኖር አለበት“ ብለው አገሩቱንም ሕዝቡንም ምድርንም በየአለበት አተረማምሰው በሃያኛው ክፍለ ዘመን እንደሄዱ የሚታወቅ ነው። በብዙዎቹ ዘንድ የማይታወቀው ጀርመን እነዚህን ትምህርቶችና ፍልስፍናዎችን (ማርክሲዝምንና ፋሺዝምን) በምን ብልሃትና ዘዴ አራግፋ ከእነሱም ተገላግላ ወደ ነጻ-ሕብረተሰብ ተሸጋግራ በኢኮኖሚያዋ በልጽጋ ሁሉን ቀድማ ሕዝቦቹዋን አስደስታ እዚህ አሁን የምናየው ደረጃ ላይ ደረሰች ለሚለው ጥያቄ የሰጠቺው መልስ ነው። ይህንንም እኛ በዚህች ሕትመታችን ላይ ከሞላ ጎደል ብልሃቱንና ጥበቡን አንስተን እናንተ እንድትመለከቱት አድርገናል። ወረድ ብለን በዚህ በኩል አሸነፍናት ብለው ገና እፎይ ሳይሉ በሌላ በኩል ብቅ ስለምትልባቸው ኢትዮጵያ እናነሳለን። አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ በኩዋክብት ተመስላ ስሙዋን ቀየር አድርጋ „ካሲዮጵያ „ ተብላ እንዴት ብቅ እንዳለች እንመለከታለን። ስለዚህች የኢትዮጵያ ንግሥት ማንም የማይደርስባት ሰማይ ላይ ዘለዓለማዊ ሁና ስለቀረቺው ኮከብ-„ካሲዮጵያ“ እግረ መንገዳችንን አንስተን እናልፋለን። ከዚሁ ጋር እንደ „ማስቲካ“ ጥዋት ማታ ስለሚታኘከው ስለ አማራና ስለ ብሔር ብሔረሰብ እሰከ መገንጠል ድረስ ጥያቄም መለስ ብለን አንስተን 4


ገደቡና ልኩ የት ድረስ ነው ብለን እረራሳችንን ጠይቀን አንድ ግንዛቤ ሰንዝረን ወደ ሌላ ጉዳይ እንሸጋግረናል። በሦስተኛ ደረጃ ከሮማ ካቶሊክ ቤተክርስትያን አውሮፓ ውስጥ የዛሬ አምስት መቶ አመት ተገንጥሎ የራሱን መንገድ ሂዶ አሁን የመንፈስ ቀውስ ገብቶ ቤተ ክርስቲያኑን በበርካታ ከተማዎች ለመሸጥ ስለተገደደው የሉተር ኢቫንጀልስት/ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን እናነሳለን። ተሸጠውም ቤተ-ክርስቲያኖቹ ምግብ ቤትና መሸታ ቤት ሁነዋል። የወጣቶች ዳንኪራ መርገጫና መጨፈሪያ ጋለሪና የብስክሌት ማቆሚያ ወይም መቃብር ቤት ተደርገዋል። ይህ ጉዳይም ጀርመን ውስጥ ያስነሳውን ውይይት መጽሔቱ ገረፍ አድርጎ ያልፋል። ለኢትዮጵያ ሕዝብና ለባህሉዋ ለሃይማኖቱዋና ለታሪኩዋ ፍጹም እንግደ የሆነውን የማርክስና የስታሊን ትምህርትና ቲዎሪ እጃቸውን ዘርግተው ልባቸውን ከፍተው „የተቀበሉ ሰዎች“ ለምን አሁን አገሪቱ ማለት ሕዝቡ „…ሰበአዊና ዲሞክራሲ መብቱን ተጠቅሞ አብሮ በሰላም በእኩልነትና በአንድነት ለመኖርና የፈለገውን ዓይነት ሓሳቦቹን ተሰብስቦ ተደራጅቶ ተናግሮ ጽፎና መክሮ መርጦ መኖር የማይችልበት ደረጃ ላይ ነው „ የሚሉበት ምክንያት አይገባንም። ይህንንም ጉዳይ በተዘዋዋሪ አንስተንም በጽሑፋችን ላይ እንመላለስበታለን። መጽሔቱ በአራተኛደረጃ „በብሔርና በመደብ ትግል እሰከ መገንጠል…“ በሚባለው ፍቅርን ሳይሆን አምባጓሮን አንድነትን ሳይሆን መበታተንን ተቻችሎ ተከባብሮ በመልካም ጉርብትና አብሮ ተረዳድቶ መኖርን ሳይሆን ጥላችን እንዲያውም – ማርክስና እስታሊን እንደሚሉት- „አንዱ መደብ ሌላውን መደምሰስ አለበት“ ብሎ የሚለውንም ነገር እንደገና ተመልሶ ይመለከታል። ይህን ዓይነቱን ጥላቻ በሚያስተምረውም ጽንሰ ሓሳብ ዙሪያም ላይ ተሽከርክሮ -መጽሓፍ አይደለም የምንጽፈው- አይዲኦሎጂውን ይተቻል።

5


የአለፈው ሃምሣ አመት ታሪካችን ትውልዱ ለምን በከንቱ በዚህ ጉዳይ ላይ አሳለፈ? ብሎም በተዘዋዋሪ ይጠይቃል። „ትግል“ የሚለው ቃል ብዙ ትርጉም አለው። ኢትዮጵያ ውስጥ ቀስ ብሎ እየተንሸራተተ የገባው ይህ „የብሔርና የመደብ ትግል“ ቃል (መንግሥቱ ኃይለማሪያም „ጥሩ“ አድረጎ „በከርሰ መቃብራቸው ላይ እንቀመጣለን „ ብሎ አስቀምጦታል) ገፍትሮ አሁንም ቢሆን የት እንደከተተን በዓይናችን ጥዋት ማታ እናያለን።ከሩቅም ሆነን እንሰማለንም። እሱንም አንስተን እዚያና እዚህ ነስንሰን – ወረድ ብላችሁ እንደምትመለከቱት እናልፋለን። እንግዲህ ለዚህም ነው ይህን ጉዳይ ግልጽ ለማድረግ የውሾችን ታሪክ መርጠንም ያስቀደምነው። የአንበሳ ወይም የነብሮች ወይም ደግሞ የድመቶች ታሪክ ልንለውም እነችላለን። ይህን ያህል „ልዪነት“ የላቸውምአንድ ናቸው። ውሻ ግን ከነብር ታማኝ ነው። ንቁ ነው። ውሻ ከአስተማሩት -እስከ መቶ የተለያዩ ቃላቶችን መያዝ ይችላል። እነሱንም አቀነባብሮ ምን እንደ ተባለ መላ መምታትም ይችልበታል። በዚህም የሚሰማቸውን ነገሮች አዳምጦ-ትዕዛዝ ይቀበላል። እንደምናውቀው ደግሞ በጋራ የሚኖሩና አጥቂ፣ አውሬ ሲመጣባቸው ለጋራም ጩኸት የሚተባበሩ ናቸው። በዚያው መጠን አጥንት ከአዩ የሚቦጫጨቁምእነሱውናቸው። ርዕዮተ-ዓለም ወይስ እሴት ? ከማለት ይልቅ „አይዲኦሎጂ ወይስ ትሩፋት/ ቨርቺውስ?“ ብለን እሱን ማስቀድምና መመልከት ምርጫችን በሆነ ነበር። „ስለህሊና ስለልቦና ስለ ፍቅር ስለ ርህሩህነት ስለ መከባበር ስለ ተግሳጽና ምክር …“ ስለነዚህ ሁሉ ለማንሳትና ታሪክና ምሳሌን ተደግፎ ለማብራራት የሚፈልግ ሰው ቨርቺውስ/ትሩፋት ውስጥገብቶ ዋኝቶ ከዚያ ወጥቶ ብዙ ጠቃሚ ነገሮችን ሰብስቦ ለማሳየት ከዚህ የበለጠ ሜዳ የትም እሱ አያገኝም። 6


የኢትዮጵያ ባህልና ትውፊት (ካልቸርና ትራዲሽን) የተመሰረቱት በዚህ እላይ በአነሳነው በትሩፋትና አገሪቱ ከጥንት ጀምሮ በምትመራበት ሥነምግባርና ግብረገብም (ሞራልና ኤትክስም) ነው። እነዚህ ሁሉ አብረው የተያያዙ ናቸው። በሁዋላ ግን ሳይታሰብ ብቅ ያሉ አሁንም እየተጠናከሩ የመጡ አዲስ አመለካከቶች የነበረውን ሁሉ እንዳልነበር አድርገዋል። „ማጭበርበር፣ መዋሸት፣ መስገብገብ አለመደማመጥ …እግዚአብሔርን አለመፍራት …በአጭሩ አብዮታዊ እርምጃየሚባሉ ነገሮችና….ፍርደ ገምድልነትየሚሊተሪ የጦር ሜዳ ፍርድ “ የሚባሉት ጠበንጃ ለያዙት ብቻ የሚሰራና የሚያገለግል አዲስ ኖርሞችና „ሕግጋት“ …እነዚህ ሁሉ የተጻፉና ያልተጻፉ የአኗኗር ዘዴዎችን ገልብጠውና ገለባብጠው ነገሮችን ሁሉ -ነጮቹ እንደሚሉት-በእግራቸው ሳይሆን በጭንቅላታቸው አገራችንንአቁመው ለቀዋታል። ይመስላል እንጂ ነገሮች ሁሉ ቀስ እያሉ ከቅጥጥር ውጭ ሁነዋል። ከሆኑም ቆይቶአል። ጨርሶ መደማመጥ መግባባት በማንኛችንም ቤት የሌለው በሌላ ሳይሆን በዚሁ በአገራችን ቀስ ብሎ እግሩን በሰደደው አይዲኦሎጂ ምክንያት ነው። መጽሔቱ ይህንንም እዚያም እዚህም በገጹ ላይ ያነሳል። ስለትሩፋት ግን በቀጥታ ብዙ አያነሳም። ስለዚህ ቁም ነገር አንዳንድ ነገር ማስተዋል ለፈለገ፣ጥራዝ ነጠቅነት በአገሪቱ ሳይስፋፋ በኢትዮጵያኖች አስተሳሰብና ባህሪ ላይ ትልቅ ሚናና አስተዋጾ ያደረገውን „ መጽሐፈ ፈላስፋ „ የተባለውን መጽሑፍ ፕሮፌሰር ክሉድ ሰምነር አገላብጠው ወደአርባ የሚደርሱ የኢትዮጵያ ቨርቺውስን / ትሩፋትን „የኢትዮጵያ ፊሎሶፊ“ በሚለው ጥናታቸው ላይ እንድንመለከተው እሳቸው ቆጥረውልናል። እዚያም ላይ እንደ „…ችሎታና እንደ ዝምታ… እነደ መልካም አንደበትና እንደ ብልሃተኛነት እንደ ጥበብና እንደ ረጋ ማለት እንደ ታማኝነትና እነደ ይቅርታ… ይቅር ለእግዚአብሔር ብሎ መታረቅና መስማማትን፣ 7


“ምሁሩ አንስተው መጽሓፉ ውስጥ ያገኙትን ምርጥ ቨርቺውስን ቆጥረውልናል። እዚያው ላይ „ እንደ ደፋርነትና እንደ ተስፋ እንደ ጥንካሬና እንደ ሥራ ወዳድነት እንደ ትህትና እና እንደ ደስታን እንደ ፍርድና ፍትህ…እንደ ጥራትና እነደ ቻይነት- እንደ ልበ-ሰፊነት እንደ መቆጠብና ከስግብግብነት መራቅን እነደ አክብሮት እነደ አርቆ ማየት ….እነደ እምነትና ጠንካራ ሃይማኖታዊነት….“ያሉትን ፕሮፌሰሩ ሰብሰብው ያስቀመጡትን ውድ ሐብቶች እዚያም ውስጥ እናገኛለን። „ተግሣጽና ምክር „የሚባሉ ጽሑፎች ነበሩ። የሞራልና የግብረገብ ትምህርት በየትምህርት ቤቱ ለወጣቱ ትውልድ ይሰጥ ነበር። „መልካም ሶሳይት“ የሚባሉ የሥነ -ስርዓት ማስተማሪያ ጽሑፎች ነበሩ። እዚያም ላይ „የአቀራረብና የአነጋገር የአቋቋምና የአቀባበል ቅደም ተከተል የትህትና እና የአክብሮት ሥነ-ስርዓቶች“ ለልጆች ይተላለፉ ነበር። ይህ ሁሉ ግን ወይ „አብዮት“ በሚባለው ነገር ወይም“ አብዮታዊ እርምጃ …“ በሚባለው አዲስ „ባህልና ጌጥ“ ድረሻቸው እንዲጠፋም ተደርጎአል። የአገር ፍቅርም በዚያው አብሮ በተወሰኑ ሰዎች ዘንድ መሬት ላይ ተጥሎ ተረግጦአል። እሴት እና አይዲኦሎጂን በመጽሔቱ ላይ ያነሳነውም ከዚህ አንጻር ብቻ ነው። ሰዎች በዘር ወይም በአጥንት ቆጠራ ላይ ተመስርተው በኢትዮጵያ ከሚደራጁ -ይህ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነው- (እንደ ጤፍ የተደበላለቅን ስለሆን አንዱን ፍሬ ለቅሞ ከሌላው መለያያቱ ከባድ ነው)- በተለያዩ አይዲኦሎጂ ዙሪያና ሥር እንደ ሌላው የዓለም ሕዝብ ተሰባስበው ቢደራጁ እኛ የምንቃወመው ሳይሆን የምንደግፈው አካሄድ ነው። 8


እኛ የምንተቸውና የምንቃወመው፣መስተካከል አለበት የምንለው ጉዳይ ቢኖር„የራስንና የግል ወታደሮችን ሰብስበው አደራጅተው አስታጥቀው በጠበንጃ አፈ ሙዝ አስገድደው …እኛ ብቻ ለሕዝቡ የሚያስፈልገውን ነገር እናውቃለን እናንተ አርፋችሁ ተቀመጡ…“ የሚሉትን የአሥራ ዘጠነኛውና የሃኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካ አስተሳሰብ የሚያራምዱ ሰዎችን ነው። እንደዚህ ዓይነቱ አካሄድ ደግሞ አሁን በያዝነው በ21ኛ ክፍለ-ዘመን የትም አገር ምንም ቦታ በሥራ ተተርጉሞ ወጤት ያመጣ ሥርዓት አይደለም። ይህንንም ጉዳይ ለማሳየት ጀርመኖቹን እንደ ምሳሌ ወስደን ከብዙ በጥቂቱ በዚህ ሕትመታችን -ዘለቅ ስትሉ ታገኙታላችሁ – አንስተነዋል። እንደሚታወቀው የጀርመን ፋሽሽቶችና የጀርመን ኮሚኒስቶች የእራሳቸውን ሰዎች ሰብስበው የወታደር ልብስ አልብሰው የራሳቸውን የስለላ ድርጅት ዘርግተው የቅስቀሳና የፕሮፓጋንዳ ክፍል ከፍተው፣ በመንግሥት ሥር የራሳቸውን „መንግሥት „ መሥርተው ይህችን አገር አተረማምሰዋል። የዘር እና የመደብ ጥላቻ ትምህርትና ቲዎሪ -ፋሺዝምም ሆነ ኮሚኒዚምእነዚህ ዓለምን ያተረማመሱ ሁለቱ አይዲኦሎጂዎች የበቀሉት ቀስ ብለውም ዓለምን ያዳረሱት ከዚሁ ከጀርመን አገር :- ከሒትለርና ከማርክስ ብዕር፣ ከእነሱም ጭንቅላት ወጥተው ነው። እነሱን አባረው ደግሞ እላይ ገና ከመጀመሪያው እንዳልነው ይኸው ነጻው የጀርመን ሕዝብ ንጹሁን የዲሞክራሲ አየር እተነፈሰ ጋዜጣውንና መጽሓፉን እየጻፈ ድርሰቱን እየደረሰ ምርምሩን በነጻነት እያካሄደ ቲያትሩን እየተጫወተ ፊልሙን እየቀረጸ በዓለም ላይ ምን የመሰለ ምርጥ የእንዱስትሪ ዕቃዎችን እያመረተ ዛሬ ሁሉም የሚቀናባቸው አገርና ሕዝብ ወጥቶታል ። እሱንም ትንተና ወረድ ብላችሁ ስትዘልቁት ታገኙታላችሁ። ከሁሉም እቴጌ ጣይቱ ከዛሬ አንድ መቶ አመት በፊት ስለ „አንድነት“ ትልቅነት ለሃይማኖት አባቶች የጻፉት የቆየ ደብዳቤ አስደናቂና ግሩም 9


ስለ ሆና እሱንም ረጋ ብላችሁት እንድትመለከቱት እንጋብዛችሁዋለን። መልዕክቱ ለሃይማኖት አባቶች ብቻ አይደለም። መልዕክቱ ለአንተና ለአንች ለእሱና ለእኛ ለሁላችንም ነው። በመጨረሻም በ1969 ዓ. ም. ቀ ኃ ሥ በሰበአዊ መብት ታጋዩ በዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ መቃብር ላይ በአትላንታ የአበበ ጉንጉን ሲያስቀምጡ በዘመኑ ከወጣው ጋዜጣ ላይ ያገኘነውን ሰነድ አብረን እንድትመለከቱት አውጥተናል። እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ አደረሳችሁ። ዋና አዘጋጁ ይልማ ኃይለ ሚካኤል

ለአእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

10


አይዲዮሎጂና ፋቡላ ?

አይዲዮሎጂናፋቡላ ?

አይዲዮሎጂና ፋቡላ ? ወይስ

ሥ ል ጣ ኔ ና እ ሴ ት?

11


ሀ …ምንድንነው እነሱ ያላቸው ችሎታና ብልሃት እኛ ደግሞ የሌለን ነገር?“ ብሎ አንድ ውሻ እሱ እራሱ የሚያውቃቸውን ጋብዞና ጠርቶ ዛፍ ሥር እነሱንምሰብስቦ አጠገቡ የቆሙትን የመንደር ውሾች „…አንዲት መልስ ብቻ ከየትም አምጥተው ለጥያቄው እንዲሰጡት“ ያፋጥጣቸዋል። ከፊሉ ውሻ -እዚያ ከነበሩት ውስጥ- ብዙውን ክፉና ደጉን በአለፉት ቀናትና ረጅሙ አመታት ከእሱ ጋር አብረው የተካፈሉ የዕድሜ አኩዮቹ ናቸው።ሌሎቹ አብሮ አደጎቹ ናቸው። የተቀሩት ልጆቹና የልጅ ልጆቹ ናቸው። ሁሉም ጠባዩን ስለሚያውቁት መልስ ለመስጠት ተጨንቀዋል። ብዥ ብሎበት አይኑን ከጎለጎለና ክራንቻ ጥርሱን አሳይቶ የጀርባው ጠጉር ከተነሳ ማንም አይችለውም። ይቦጫጭቃቸዋል። ከእነሱም ጋር በዚያን ዕለት ከተገኙት ውስጥ የቆየ መንደራቸውን ጥለው – ስለፈረሰ የተቀላቀሉ ወዶ ገብ አዲስ መጤዎችም አሉበት። ትናንሽ ቡችሎች ራቅ ብለው -የዚህች ዓለም ነገር ወዴት እንደምታመረ ገና ያልገባቸው፣ ጮርቃ ምኑንም የማያውቁት እዚያ አፈሩ ላይ እነሱ ይተረማመሳሉ ፣ በሆዳቸውም ይገለባበጣሉ። ፍቅረኞቹም ሲተያዩ ይሽኮረመማሉ።መጪውን ቀን ክፉ ይሁን ወይም በአለው ይቀጥል ወይም ደግሞ ደህና ይሁን የሚያውቅ ከእነሱ መካከል የለም። አውራው ግን የገባው ይመስላል። „…ምንድነው እነሱ የተካኑበት ጸጋ ለእኛ ደግሞ ሥውር ሁኖ የማይታየን ነገር? „ እስቲ ንገሩኝ እያለ ውሻው ይንጎራደዳል። የእንስሶችንና የአውሬዎች ፋቡላ ታሪክ በደንብ ለተከታተለ አንድ ሰው ከእነሱ ብዙም ባይሆን ትንሽ ትምህርት ይገኝበታል ይባላል ። ታሪክ የማይረሳቸውናየሚያስታውሳቸው አሉ። 12


አንደኛው የጆርጅ ኦርቭል ድርሰት ነው። የእሱ „…የእንስሳት እርሻ „ የሚለው አጭር ልበ ወለድ ድርሰቱ ግሩምና ድንቅ ጽሑፍ ነው። „…አያ ጅቦ ሳታመከኝ ብላኝ“ ያላቸው የአህያዋ አነጋገር ከነተረቱ እንደዚሁ ሌላው የሚጠቀስ ምሳሌ ነው ። ፊታውራሪ ተክለ ሐዋሪያት የመጀመሪያ ድርሰታቸውን በቲያትር መልክ ጽፈውና አዘጋጅተው አዲስ አበባ ላይ በዘመናቸው መድረክ ላይ ያቀረቡት ጨዋታ በዚሁ በፋቡላ በእንስሶች ታሪክ ላይ የተመሰረተ ነው።

ለ ሰልችቶት

ይመስላል ወይም ተናዶ ወይም ደግሞ ድክመትና ጥንካሬአቸውን በሁለቱም ወገን መካከል ያለውን ለማወቅ ከአለው ፍላጎትና ጉግት ተነስቶ ሊሆን ይችላል ይህኛው አውራ ውሻ ስብሰባ የጠራበት ዋናው ምክንያት የትኛው እንደሆነ አይታወቅም። ወይስ ውሸትና እውነት ተለይቶና ተበጥሮ እንዲወጣ ፈልጎ ይሆን? ያ ውሻ የመንደሩን ውሾች ሁሉ ጠርቶ እንደገና ለሦስተኛ ጊዜ „…እስቲ ንገሩኝ …ምንድነው እነሱ ያላቸው ጥንካሬ እኛ ደግሞ የሌለን?“ ማለቱ ከዚህ ሁሉ አመት በሁዋላ -አጥንት ከአዩ ብዙ አመታቸው ነውየገርማል። አጥንቱ ትዝ እያለው„…እነሱ ያላቸው ትልቅ አብሮ የመኖር ፍልስፍና እና እኛ ደግሞ በእጃችን የሌለን ነገር እስቲ እባካችሁ ፈልጋችሁ መልስ ስጡኝ ብሎ?“ ቢጤዎቹን ሰልችቶት ወደ መጨረሻ ላይ እየተለመማመጠ እነሱን ይጠይቃል። 13


በዚያች አንዳንዶቹ ትክ ብለው መልስ ለመስጠት በሚያስቡበትና በሚያሳስሉበት ሰዓትና ደቂቃ ከየት እነደመጣች የማይታወቅ አንዲት ጥንቸል ሽው ብላ ታልፋለች። ስታልፍ ከሩቁ ያዩ ሁለት የስብሰባው ተሳታፊዎች ተጠቃቅሰው ብድግ ብለው በዚያ በረጃጅም እግሮቻቸው ወደፊት እየተሳቡና እየተገፋተሩ „…እሱዋማ የእኔ ናት። የለም የአንተ“ እየተባባሉ ማሳደድ ይጀምራሉ። የት እንደገቡ ሳይታወቅ:- ቢጠበቁ እነሱ ሳይመለሱ በዚያው ጭልጥ ብለው ጠፍተው ቀርተዋል። እነሱ ተረስተው:ወይይቱ እንደገና በሌላ ጥያቄ ይከፈታል። ያም ገና በደንብ ሳይደመጥ በመካከሉ አንዲት ተንኮለኛ እነሱን ውሾቹን በማነደድ ብቻ ደስታውን የምታገኝ ቅምጥ የሳሎን ድመት ተደብቃ ቀስ ብላ ጠጋ ብላ በጭረዋ የአንዱን ውሻ ጀርባ ገረፍ አድርጋ ፈትለክ ብላ ትሰወራለች። እሱና አጠገቡ የነበሩት ውሾች ተደፈርን ብለው ብድግ ብለው ዘለው በተራቸው እሱዋን ድራሹዋን ለመጥፈት ሲዘሉ -ሥራዋን በደንብ ታውቃለች- አፈትልካ በመጀመሪያ ዘላ ግንቡ ላይ ከግንቡ ጣራው ላይ ጉብ ብላ „ሚያው“ እያለች እየተንጎራደደች እነሱ የተሰበሰቡበትን ዓላማ ረስተው የተለመደው ጩኸት ውስጥ ይገባሉ። በጩኸት ቅላጼ በእሱዋ ምክንያት ስብሰባው ሊፈርስ ጥቂት ይቀረዋል። እንደተለመደው ጮኸው ሲሰለቻቸው ይረጋጋሉ ብላ ንቃቸው ግቢዋ ውስጥ ዘላ ገብታ እመቤትዋ እግር ሥር በረንዳው ላይ ጋደም ትላለች። ደፍሮ ከመካከላቸው አንድ ጎልማሳ ውሻ ብድግ ይልና „…እኔ ከእናንተ በዕድሜ ወጣት በመሆኔ እምብዛም ብዙ ነገር አላውቅም። አሳዳጊዎቼ ፈረንጆቹ እኔን እዚህ ሜዳ ላይ ጥለው ወደ አገራቸው ከመመለሳቸውና ከመሄዳቸው በፊት እንደአየሁትና እንደተገነዘብኩት እነሱም በደጉ ዘመን እንዳሳደጉኝ እኔም በደንብ እንደአዳመጥኩት የፈረንጅ ውሾች ትምህርት ቤት ተልከው እዚያ ‚ሁሉን ዓይነት የአብሮ መኖር ሥርዓት‘ እነሱ እንዲማሩ ይደረጋል።… የማናውቀው እንግዳ እንኳን ወደ ቤታችን 14


ሲመጣ -ብዙም ሊሆኑ ይችላሉ – ወጣ ብለን ከጌቶቻችን ጋር ሁነን ሳንጮህና ሳናስፈራራቸው እግራቸ ሥር እየተሽከረከርን በደስታ እንቀበላቸዋለን። „ከሌላም ከማናቀው ውሻም ጋር እንደዚሁ ገበያ ላይ ወይም ንፋስ ለመቀበል ለሽርሽር ስንወጣ ሜዳ ላይ ከተገናኘን ተጠያይቀን ትንሽ ‚እመቤትሽ የለበሸቺው ቀሚስ ጌታህ የያዘው ከዘራ ወይም ክራቫት ብለን ተቀላልደን‘ መንገዳችንን እንቀጥላለን እንጅ እዚህ እንደማየው አንዱን ሰብሰብን ብለን አሳደን አንቦጫጭቀውም። እናንተ እኔ ይህ ሳጫውታችሁ ‚አውሬነትህን ረሳኸው ብላችሁ እንደምትስቁብኝ አውቃለሁ። „ምግባችንን ከሳህናችን ላይ እንበላለን እንጅ ጌቶች ሲበሉ ሆነ ልጆች ዳቦአቸውን አስቀምጠው ሲጫወቱ ቦጭቀን እናንተ እንደምታደርጉት አንሮጥም። በዚያም ሳቢያ ጥዋት ማታ በድንጋይ አንደበደብም። አሁን ያቺ ድመት በዚህ ስታልፍ የሆነውን አይቼአለሁ። ከቤት ድመቶችም ጋር አብረን እንውላለን እንጅ አንጣላም። ምንም የሚያጣላን ምክንያት የለም። እሱዋ እራሱዋ አይጥ አይታ ስትፈራና እኔ ጋ መጥታ ስትወሸቅ አብረን እንስቃለን እንጅ እሱዋን አሳደን ጊዜአችንን በዚህ አናጠፋም…በጊዜአችን ሌላ ስንት የሚሰራ ነገር አለ። እኔ ለምሳሌ አስተማሪ ተቀጥሮልኝ ጋዜጣ ጥዋት ጥዋት ለጌታዬ ለማምጣት ትምህርት ወስጄ ነበር። ሌሎቹ ሲማሩም አ…“ እያለ እላይ የተሰነዘሩትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሙከራ በሚያደርግበት ደቂቃ አንዱ ዕድሜው ጠና ያለ ውሻ ተነስቶ „…ምን ይደረግ አንተ ‚ችሎ ማደር‘፣ አንተ እኮ ነህ በዚህ ውርጋጥ ዛሬ የምታሰድበን። እንተ እንደዚህ እኛ እንደዚያ እያለ …ይህ ትላንት የመጣ ጥጋበኛ ውሻ እኛን እየሰደበን ነው። የልብህን እየተናገርክ የስድብ ናዳ አወረድክብን …። እግዚሔር ይስጥህ። ጥፋተኛው አንተ ሳትሆን አንተ ስብሰባውን የጠራኸው አቶ ‚ችሎ ማደር ነህ!“ ብሎ ጋባዡንም ተናጋሪውንም በወቀሳ ያዋክባል። 15


ሌላው ተነስቶ „…አወቂ ሲጫወት ልጆች እየተነሱ ጣልቃ እንዳይገቡ ቁጥጥር ይደረግ „ ብሎ ማሳሰቢያውን ለቤቱ ያቀርባል። እሱም ሓሳብ ማሰሪያ ሳያገኝ እንደገና አንድ ያልታሰበ ነገር ስብሰባውን እንዳለ ገልብጦ በሰከንድ ውስጥ በጭንቅላቱ ያቆመዋል። አንድ ተንኮለኛ ዘበኛ- እነሱ ሲቦጫጨቁ ቁጭ ብሎ ማየቱን ይወዳል- የውሾቹን ስም አንድ በአንድ „ አንተ …ውስኪ…ቦቢ ዘብ ይደሩ የት ነህ?…እነ ነብሮ እነ ግሥላ እነ ፑሺኪን እነ ሉሉ … የትናችሁ…ተመልከቱ…“እያለ እየተጣራ እንደተለመደው እነሱ ሲቦጫጨቁ ቁጭ ብሎ እግሩን ዘርግቶ ለመሳቅ አንድ አጥንት እያሽከረከረ ያ ተንኮለኛ ዘበኛ መሓላቸው ይጥላል። ግልጽ ነው። ያችን አጥንት ለብቻው ቀምቶ ለመብላት ወንዱም ሴቱም ብድግ ብለው ተያያዙ። በቅጽበት በትንሽ ደቂቃ ጊዜ ውስጥ ያ በሰላም የተጠራው ስብሰባ ወደ ጦር ሜዳ ተቀየረ። ሁሉም አፈር ለበሱ። እንደፈለገው ተቦጫጨቁለት። ምን መጣ ብለው ቡችሎቹም ሸሽተው አፋፍ ላይ ቆመው ይህን ጉድ – እነሱም ነፍስ ሲገዙ የሚገቡበትን ነገር- ትንሽ ኮረብታ ላይ ሁነው መመልከት ጀመሩ። ሁለተኛው አጥንት በሌላ ዘበኛ ተወርውሮ እፎይ ሳይሉ መሓላቸው ወደቀ። እንደገና የይገባኛል/አይገባህም ግብግቡ በመካከላቸው ተከፈተ። አጥንቱዋም አፈር ትለብሳለች። በጥቂት ደቂቃ ከፊሉ ውሻ ቆስሎ በዚያች ትንሽ ጊዜ ውስጥ ያነክሳል። ሌላው ቁስሉን መላስ ጀምሮአል። አፍንጫው የደማ አለ… ቆዳው የተቀደደ። ጭንቅላቱንና ጆሮውን የሚነቀንቅ አለ። ቁና ቁናቸውን ይተነፍሳሉ። ያ ፈረንጆች ቤት „ለጥቂት ጊዜያት በልጅነቴ አሳልፌ ነበር“ ያለው ውሻ ቡችሎቹን ሰብስቦ „ ከዚህ የውሻ መብት ከማይከበርበት አገር ጠፍቶ 16


ሌላ አገር መብታችን የሚከበርበት ቦታ ሄዶ መኖር ያስፈልጋል እያለ…“ ሰበካውን ጀመረ። „… ታውቃላችሁ በአውሮፓ ለእንስሶች መብትና ክብር የሚሟገቱ ሰዎች አሉ፣ እነሱ ጋ በረሃውንም ባህሩንም አቋርጠን ተሻግረን እንሄዳለን።… ከዚያም ሰላም እናገኛለን። …ልንገራችሁ ውሻውን የሚደበድብ ቀርቶ የሚገላምጥ ሰው እንኳን እንደሰማሁት ይቀጣል… ይህን በጆሮዬ ነጮቹ ሲናገሩ ሰምቼአለሁ“ እያለ ይዞአቸው ከዚያ ከማያምር ግርግር በወሬው እየሳበ ዞር አለ። ታሪኩን እንግዲህ እንፍታው ።

ሐ ሁለቱ የተወረወሩት አጥንቶች „ሁለቱ እኛ የምናውቃቸው አይዲኦሎጂዎች“ ናቸው። አይዲኦሎጅ በአንድ በሌላ በኩል በኩል ብቻዬን አሸንፌ ሌሎቹን ከፊቱ ይሄዳል። በሌላ በኩል ያታልላል። ያባብላል። የሌለ ታሪክ ፕሮፓጋንዳውን ይሰልባል። ይጥራል።

በኩል ያሰባስባል ያከፋፍላል። በአንድ ልውጣ ብሎ የቆሞትን ደፍጥጦ የሚያንገራግሩትን ይሸነግላል። ያልነበረ የውሸት ለቆ አእምሮም ለመስለብም

ርዕዮተ- ዓለም ጥቂቶቹን ደጋፊዎቹን የመሰብሰቡን ያህል ከአላወቁበት ሁሉንም ሕዝብ አሳክሮ አጋጭቶ ያጣላል። አገርንም ያተረማምሳል። ደስ ከአለውም ያሸጣል። ይኸው ርዕዮተ ዓለም እንደገና በደንብ ከአልያዙት አሳብዶ ጎልጉለው ቆፍረው ያመጡትንም ሰዎች ሳይቀር ይዞ አያይዞ እነሱንም ገደል 17


ይከታል። ቢቀር ቢቀር እነሱን አጠፋችሁ ብሎ እሥር ቤት ያስወረውራል። ትልቁንም ትንሹንም አመሰቃቅሎ አንዱን በአንዱ ላይ አስነስቶ ያጨራርሳል። ምንም የማያውቀውንም እሳት ውስጥ ከቶ ያስጨርሳል። የዞረበት አይዲኦሎጂ ደግሞ አንድን ሰው እላይ ሰቅሎ መላ ሕብረተሰቡን ወደ የግል ሐብት ወደ እሥር ቤትም እንዳለ ይቀይራል። ሱማሌና…ሩዋንዳ ብሩንዲና ኬንያ፣ ሱዳናና ደቡብ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳንና የመን፣ ኮንጎ እና መካከለኛው አፍሪካ፣ ግብጽ ሊቢያ ማሊና ሞዛምቢክ፣ ናይጄሪያ ኡጋንዳ ኢትዮጵያና ኤርትራ …ኢራክ፣ ሶሪያ ሊባኖስ አፍጋኒስታን … እነዚህ ሁሉ አገሮች የሚተረማመሱት እርስ በራሳቸው የሚፋጁት በሌላ ነገር ሳይሆን ከውስጥ ሆነ ከውጭ በተወረወረላቸው በማያስማማ አደገኛ አይዶሎጂ ነው። ያንን ያዝን ብለው በሚያምኑት ርዕዮተ ዓለምም በእሱ ሳቢያ በተቆሰቆሰው እሳት አንዱ ተነስቶ በሌላው ላይ ጦር አውጆል። ያኛው በዚህኛው ይህኛው በዚያኛው ላይ ተነስቶአል። ሁሉም በአንዱ ላይ። አንዱ ብቻውን በሌላው ላይ! በመጨረሻውም ተናንቀዋል። አሸናፊ ደግሞ በመካከላቸው የለም። አይኖርም። የዛሬው ድል አድራጊ ነገ በተራው በሌላው ድል የሚመታ ነው። „…የማን ቤት ፈርሶ የማን ቤት ሊበጅ የአውሬ መፈንጫ ይሆናል እንጂ…“ ይህ በኢትዮጵያ የተለመደ አነጋገር ሌላም ቦታ በጎረቤት አገሮችም ይታያል። ሱማሌዎች እርስ በራሳቸው የሚገዳደሉት፣ ኬንያ የተራረደው ሴንትራል አፍሪካ… ዛሬ ጎረቤቱን ቤንዚን አርከፍክፎ የሚያቃጥለው-ሥጋውንም ቆርጦ የበላ አለ- በዚሁ በተጫረው የጥላቻ አይዲኦሎጂ ነው። አፍሪካን ያሳበደው ይኸው የጥላቻ ትምህርት ነው። በእርግጥ አይዶኦሎጂ የጠላትና የወዳጅ እንደ ጎራአቸው መሰባሰቢያ አዳራሽና መገናኛ ቤት 18


ነው። እንደ መጠለያ ድንኳንና ጎጆም ያገለግላቸዋል። ለአንዳዶቹማ እንደ „ቤተሰብም“ ነው። እንደ ዔሊ ቀፎ ጠንካራ ምሽግ በቀላሉ የማይሰበር ዛጎል ይመስላቸዋል። እንደ ጃንጥላም ሁኖ ከሚርከፈከፈው ዝናብና በትንሹ ከሚፈነጥቀው የጸሓይ ጮራ ለጊዜው ይከላከላል። ከአልተጠነቀቁ አዲዮሎጂ አእምሮን ሰልቦ „ባሪያ“ አድርጎ የሕልም ዓለም ውስጥ ከቶ አፍዝዞ ጦር ሜዳ ድረስ ይነዳል። አውሎ ንፋስ ሲመጣ ኃይለኛ ማዕበል ሲነሳ ደግሞ በቀላሉ ተኖ በመጣው ፍጥነት ተመልሶ ይጠፋል። ያ ሲሆን ደግሞ በኤርትራና በጠቅላላው ምሥራቅ አፍሪካ እንደምናየው ሰው ሁሉ ግራ ተጋብቶ ለካስ ያ ሁሉ ድካም ለዚህ ነው ብሎ ለስደት ይዳረጋል። ወይም ጆሮውን ዘግቶ ጀርባውን አዙሮ ይተኛል። በደንብ ለመመልከት ሁለቱን ጀርመኖች እንውሰድ: – ምዕራቡንና ምሥራቁን ጀርመን! ለምንደው ጀርመኖች የዛሬ ዘጠና አምስት ገደማ ንጉሡን አባረው የቫይመሩን ሪፓብሊክ አውጀው „…እኔ ልግዛ እኔ ልምራ“ በሚባለው የፓለቲካ ድርጅቶች ንትርክ ውስጥ ገብተው ያ እፎይ ብሎ ለመኖር የሚፈልገውን ሕዝብ በአንዴ በነገር አሳክረው በቀላሉ ሊያወናብዱት የቻሉት? ለምንድነው አብዛኛው የጀርመን የፖለቲካ ድርጅት በዚሁ በቫይመር ሪፓብሊክ ዘመን የራሱን ተደባዳቢና ተዋጊ ጦር ልዩ መለዮ የወታደር ልብስ የማዕከላዊ ኮሚቴ የስለላ ድርጅት የቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ክፍል ፈጥሮና መሥርቶ መንገድ ላይ እርስ በእራሱ መፋለጥ የጀመረው? እንግዲህ እንዴት ነው ሒትለር በጀርመን አገር አሸናፊ ሁኖ ሊወጣ የቻለው? ለምንድነው ከፋሽሽቱ ሒትለር አገዛዝ በሁዋላ ጀርመን ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በሁዋላ፣ ለሁለት ይህች አንድ አገር የተከፈለቸው? ለምንድ ነው – አንደኛው ኮሚኒስት ሁለተኛው ነጻ -የዲሞክራቲክ ሕብረተሰብ 19


ሁነው- በዓለም ፖለቲካ ምድር ላይ ብቅ ያሉት? እንግዲህ በመጨረሻውም :ለምንድነው የምዕራብ ጀርመን የዛሬ ሃያ አምስት አመት አሸናፊ ሁኖ የወጣው? ለምንድነውስ የምሥራቅ ጀርመኑ የኮሚኒስቶች ሥርዓት ተንኮታኩቶ የወደቀው? በሌላ አነጋገር ለምንድነው የኮሚኒስቶቹ ሥርዓት ብቻዬን ልግዛ ብሎ አጥር አጥሮ በጠበንጃ አፈ ሙዝ ሲገዛ ከርሞ በሁዋላ ሳይታሰብ በሰላማዊ የሕዝብ አመጽ ሊወድቅ የቻለው? እንዴትስ ወደቁ ? ለምንድነው ምዕራብ ጀርመን በሸንጎ ምርጫ ከፖለቲከኞቹ ለመገላገል ይህኛውን ሰላማዊ መንገድ እንደ መፍትሔ የመረጠው? የተለያዩ የፖለቲከ ድርጅት መሪዎችና አባሎቻቸው በነጻ-የፓርላማ ምርጫ ውድድር ውስጥ ገብተው ለመሳተፍ ለምን ተስማሙ? የጀርመን ኢኮኖሚንስ (የምዕራቡ) እንዴትና በምን ብልሃት ነው ከወደቀበትና አመድ ከለበሰበት ከሁለተኛ ዓለም ጦርነት በሁዋላ ( ኢትዮጵያ የዛሬን አያድርገውና ስንዴና የብርድ ልብስ እንዲሁም ቡና ለጀርመን፣ ለእንግሊዚ ለጃፓን በጊዜው ዕርዳታ ሰጥታለች) አሥራ ሁለት አመት በአልሞላ አጭር ጊዜ ውስጥ በልዩ ተአምር ከመቀመቅ ተነስቶ በአንዴ -በስድሳው አመተ ምህረት – ዓለምን ሊያስገርም የቻለው?… እረ ብልሃቱ፣ የእነሱ ብልሃታቸው ምንድነው? ምን ነበር? በመጨረሻው እንደገና በምን ብልሃትና ዘዴ ነው? በየትኛው መንገድ ነው? የጀርመኑ የፖለቲካና የኢኮነሚ ሥርዓት አሁን ሌሎቹ አገሮችና መንግሥታት በኢኮኖሚና በፊናንስ ቀውስ ውስጥ ገብተው ሲማቅቁ እነሱ በአውሮፓ/በዓለምም ውስጥ ጠንካራ ሁነው ሊወጡ የቻሉት?

መ መልሱ አጭር ነው። 20


እንደማመጥ ከተባለ! ምዕራብ ጀርመን አሸናፊ ሁና ሊትወጣ የቻለቺው በሚቀጥሉት አብይ ምክንያቶች ነው። መንገዳቸውን የቀየሱት ድርቅ በአለ የአምባገነን አይዲዎሎጂ አይደለም። በእሱ ሳይሆን በቫሊውስ- በእሴት ላይ በአተኮረና በእሱም ላይ በተመሰረተ አመለካከትና አሠራር ነው። እሴት ምንድነው? ምንድናቸው እነዚህ እሴቶች? የትኛው እሴት ነው ከሁሉም ወሳኝ? አንደኛው እሴት -ይህንንም ሕገ-መንግሥታቸው ላይ ገና -ሀ- ብለው ሲጀምሩ ጥሩ አድርገው አስቀምጠውታል- ይህ ደግሞ የሰው ልጆች በአጠቃላይ ከሕይወት ልምምዳቸውና ተመክሮአቸው ከሁሉም በላይ ከአምላካቸው በተፈጥሮ በእሱ አምሳል በመፈጠራቸው ያገኙት ትምህርት ነው- „የማንም ሰው ሰበአዊ መብቱና ክብሩ በማንም አይረገጥም አይደፈርም „የሚለው አንቀጻቸው ነው። ይህም አብሮ ተከባብሮ ተቻችሎና ተደጋግፎ ለመኖር የሰው ልጆች ጀርመኖች ያገኙት ጥበብና ጸጋ ከቀመሱት ከፋሺዚም እና ከኮሚኒዝም ከሁለቱ አደገኛ ፍልስፍና እና ሥርዓት ከእነሱ - እመኑኝ! ያገኙት ዕውቀት ነው ። እርግጥ በዚህች አጭር ጽሑፍ ከድንጋይ ዳቦ ዘመን ተነስተን ወደ 1948ቱ የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ መግለጫ ድረስ አሁን መጥተን ሁሉን ነገር ገበታው ላይ ዘርግተን ማሳየት አንችልም። በአጠቃላይ የሰው ልጆች ከጠብ ይልቅ ፍቅርን እንደሚመርጡ ማንኛችንም በደንብ እናውቃለን። በጦርነት ፋንታ ሰላምን ከመበታተን አንድነትን፣ ከሥራዓተ አልባነት ይልቅ መልካም አስተዳደርን፣ ከቀማኛነት መልካም ሥነ ምግባርን ከተንኮል መረዳዳትን ከበደል ፍርድን….እነዚህን ሁሉ የሰው ልጆች እንደሚያስቀድሙና እንደሚመርጡ ይህን ስለምናውቅ ይህን ስለምንረዳ መድገሙ አስፈላጊ አይደለም። 21


ታዲያ የነገሮች አቀማመጥ እንደዚህ ከሆነ የሰው ልጆች ሁሉ ችግር ከየት መጣ? ለጀርመኑ ፈላስፋ ለማርክሲ እና ለእሱ ተከታዮች ለኮሚኒስቶቹ መልሱ ቀላልና አጭር ነው። የሒትለር -ይታወቃል አይነሳ! በእነሱ ዕምነት „በዝባዡ ክፍል-አደሃሪ“ የሚሉት መደብ ስለ አለ „ይህን ሁሉ መዓት በሰው ልጆች ላይ ያመጣውና ያወረደው እሱ ወይም እነሱ ስለሆኑ „እነሱን ደምስሰን የላብ አደሩን አምባገነን ሥርዓት ከዘረጋን ይህች ዓለም በአንዴ ወደ ገነት ትቀየራለች“ ባይ ናቸው። ኢትዮጵያም -የሚያሳዝነው ታሪካችን ይህ ነው-የመረጠቺው መንገድ ይህኛውን ነው። ሓይማኖተኛውና የሃይማኖት አስተማሪው ከዚህ ለየት ያለ አመለካከት አለው። „ሰይጣንና መጥፎ መናፍስት በዓለም ላይ ስለተበተኑ እነሱ ናቸው የችግሮቻችን ሁሉ መነሻ „ ብለው ያስተምራሉ። ለአክራሪ ፋናቲከሮች ደግሞ ሌላው ሕዝብ ተቀብሎ የሚከተለው ከእነሱ የተለየ „ እምነትና ሃይማኖት ያለው ሰው ለዓለም ሁሉ ችግር ተጠያቂ እሱ“ ነው ባይ ናቸው። እንደዚህ ዓይነቱ አደገኛ አመለካከትዘንድሮአፍሪካ ገብቶአል። ለመለዮ ለባሹ ለጠበንጃ ያዢው ወታደር ሳይጠየቅ እሱ እራሱ የራሱ መልስ አለው። ተማሪውም እነደ ተማሪነቱ እንደዚሁ የችኮላ መልስ ታቅፎ ቁጭ ብሎአል። „ነጻ-አውጪው“ ደግሞ በተራው ሌላ ማንም ሰው ከአለ መሪው በስተቀር የማያውቀው የራሱ „ራዕይ“ አለው። አንዴ „አዲሱ ዲሞክራቲ ነው።“ አንዴ „ብሔራዊ ዲሞክራሲ።“ አንዴ „ዲሞክራቲክ አብዮት።“ ሌላ ጊዜ ….ሶሻሊዝም ኮመኒዝምነው። ወይም መገንጠል ተብሎ ፕሮግራማቸው ላይ ተጽፎአል። የሰው ልጆች ባህሪና አካሄዳቸውን እናውቃለን የሚሉት እነሱ እንደሚሉት ከሆነ (ይህ የታሪክና የፍልስፍና የሳይኮሎጂና የሕግ ሰዎች ምራቃቸውን የዋጡትን ፖለቲከኞች ያካትታል…) ተቆጣጣሪና ተቆጪ ከልካይ ኃይልና ተቋሞች ሕግና ሥርዓት ከሌሉ ነገ „…አንተም እኔም እሱዋም እሱም ማንም አረመኔ“ ከመሆን አትመለሱም ይላሉ። 22


እንግዲህ ማነው አሁን ትክክለኛው?

ሠ መልሱን ለማግኘት ወደ ጀመርንበት ወደ ጀርመን አገር ወደ እነሱ „ወድቆ መነሳት ታሪክ „ እንመለስ። የግድም መመለስ ያስፈልጋል ። ለጀርመን ችግር ለዚያ ሁሉ ጣጣ መንጣጣ መነሻ ዋና ተጠያቂዎቹ ለአገሪቱ መከፋፈል ሆነ ወደ ጦር ሜዳ ለመጓዝ ማርክስ በአንድ በኩል ሒትለር በሌላ በኩል እነሱ ናቸው ብለናል። ወደዚያው እንመለስ። የእሴትና የአይዲኦሎጂ ልዩነት የሚታየውም እዚሁ ላይ ነው። አንደኛው የጀርመን ግዛት – በኮሚኒስቶቹ ይመራ የነበረው የምሥራቁ በርሊን ከ„እሴት“ ይልቅ -እዚህ ላይ ትሩፋት እና ትውፊትን መጨመር ያስፈልጋል- በእነሱ ፋንታ የዚያ አካባቢ መሪዎች ያተኮሩትና ዕድሜአቸውን የገፉት አደባባይ ተወጥቶ ቢጮህ ምንም ነገር በማያመጣው የአይዲኦሎጂ መፍክርና እነሱን የሚቃወሙትንና የሚተቹትን ጭንቅላቶች- ሓሳባቸውን ወስዶ እንደማስተካከልና እንደመታረም – እነሱን አሳዶ በመያዝና በማሰር ላይ ነው። አይረሳም ምን የሚያካክሉ- ዕብድ የሚያክሉ የማርክስና የኤንግልስ የሌኒንና የስታሊን የብርጄኔቭና የሆኔከር ፎቶግራፎች አሥር ሰው አንዱን ፎቶ እንደ ሞኝ አውራ ጎዳናው ላይ „እንደ ታቦት „ተሸክመው እየዘመሩ (ወደው ሳይሆን ) ሲጓዙ። በዘመናቸው እነዚህ ሰዎች ኮሚኒስቶቹለአገራቸው አልሰሩም ማለት አይቻልም። ቤቶችና ሕንጻዎች በበቂ ሰርተዋል። ግን ምን ዓይነት ቤት ነው የሰሩት? ሐኪም ቤቶች በየአለበት ከፍተዋል። ግን ምን አይነት መድሓኒትና የሕክምና መሣሪያ ሰርተው አውጥተዋል? ትምህርት ቤትና ዩኒቨርስቲ ቆርቁረዋል። ግን ምን ዓይነት ትምህርት ሰጥተው ልጆቻቸውን በዚያ ኮትኩተው አስመርቀዋል? 23


… መንገድ ጠርገዋል። ድልድይ ዘርግተዋል። ሓውልትና ሓዲዲ ሆቴልና ምግብ ቤት የመኪና ፋብሪካ ሳይቀር ተክለው ሊሞዚን ተሽከርካሪ መኪናዎችና ካሚዮኖችም ሰርተው አውጥተዋል። ጥያቄው ግን ምን ምን ዓይነቱን ሠሩ፣ ምን ግሩም መኪና ሰሩ የሚለው ነው? የምሥራቁ መኪና እነ ትራቢና እነ ቫርተቡርግ…ከማርቼዲስ እና ከቢኤም ደብሊዩ ከፖርሸና ከአውዲ ከቮልስባገንና ከኦፔል…ጋር በምንም ዓይነት አይወዳደርም። የቤትና የመንገድ የድልድይና የሓዲዲ አሰራራቸውን ምሥራቅ ጀርመን ምናልባት ከአፍሪካውይኖቹ ሊበልጥ ይችላል- የምዕራቡን ግን በምንም ዓይነት ተወዳድሮ አይደርስበትም። የሁለቱ ጀርመኖች የምርመራና የአዳዲስ ነገሮች ፈጠራ ትምህርት ቤቶቻቸውም አንድ አይደሉም። የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት አላቸው። እንዴት ነው ? በምን ብልሃት ነው? ምዕራቡ ምሥራቁን ሊበልጠው የቻለው? „የቦኑ ሪፓብሊክ“ የወሰደውና የተጓዘበት መንገድ እላይ እንዳየነው ደረቅ አይዶሎጂ ሳይሆን -ትሩፋቱንም ለጊዜው እንተው- በቫሊዩ/በእሴት ላይ በተመሰረተ መፍትሔ ነው። በምሥራቅ ጀርመን ጋዜጣዎች እየታተሙ ይወጡ ነበር። ግን ምን ዓይነት ጋዜጣ ነበር? ስንት ጋዜጣዎች?…. የተለያዩ አስተሳሰቦችና አመለካከቶችን ይኸው ጋዜጣቸው ያስተናግድ ነበርወይ? ሰዎች እንዲከራከሩበት ይጋብዝ ነበር? እንደ ምዕራብ ጀርመን የኮሚስቶቹም ሥርዓት እንደ አቂሚት አልፎ አልፎ ምርጫ አካሂደው በ95% ከመቶ እነሱ እራሳቸው አሸንፈው ሸንጎአቸው ውስጥ የህዝብ እንደራሴዎችን ያስቀምጡ ነበር። ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች መናገርና መጠየቅ ይፈቀድላቸዋል?

24


በምሥራቅ ጀርመን በተለያዩ ስም የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነበሩ። ከእነሱስ ጀርባ እነማን ነበሩ? ተለጣፊ ድርጅቶች ናቸው ወይስ በነጻ የተደራጁ? በምሥራቅ ጀርመን እንደ ማንኛውም አገርና መንግሥት ፍርድ ቤትና ጠበቃ፣ ፖሊስና የስለላ ድርጅቶች ወታደርና የጦር ኃይሎች ነበሩ። ዋና የበላይ አዛዡ ለመሆኑ እነማን ነበሩ? ከኮሚኒስቶቹ ትዕዛዝ ውጭ ያስቡ ነበር? … ዳኞቹስ ተጠሪነታቸውስ ለማን ነው? ለአንድ ሕዝብ እንዲያስብ እንዲሰራ እንዲናገርና እንዲቃወም መብቱን ስጠው ተአምር በዚህች ምድር ላይ ይሰራልሃል። ይህን ኮሚኒስቶቹ ይቀበሉይፈቅዱ ነበር? በምሥራቅ ጀርመን ፊልም ይሰራል። መጽሓፍት ይጻፋል። ቲያትር ይደረሳል። መልዕክቱ ግን በመጨረሻ ምን ነበር? እንደማንኛው አገር በምሥራቅ ጀርመን የቴሌቪዥንና የራዲዮ ፕሮግራሞች ይሰራጩ ነበር። ስለምን ነበር በየቀኑ የሚወሩት?

ረ ምዕራቦቹ ይህን ተገንዝበው ያኔ በሚገበያዩበት በማርካቸው ላይ ሦሰት ቃላቶች ያኔ ጽፈው ማንም ሰው በየቀኑ እንዲያነበውና እንዲገነዘበው አድርገዋል። እነሱም:- „…አንድነት ነጻነትና ፍትህ-ማለት የሕግ በላይነት“ የሚባሉትን ሦስት መሰረታዊ የሆኑ ነገሮችን ሳንቲሞቻቸው ላይ አሥፍረው በጀመሩት ሥራቸው -ሌሎቹን ነገሮች ለታሪክ ጸሓፊዎችና ለጠበብቶች ለቀው- ሳይታክቱ ቀጥለውበታል።

25


አብራርተው ሕገ -መንግሥታቸው ላይ እሴቶቻቸውን ሲያሰፍሩትም እነሱእንደዚህ ብለው አስቀምጠውታል። ከሁሉም አረፍተ ነገር ቀድሞ በመጀመሪያ! „…የማንም ሰው በማንም ሰው አይረገጥም „ ሰፍሮአል።

መብቱና ክብሩ አይደፈርም የሚለው ቃል

ቀጠል አድርጎ ይኸው ሕገመንግሥታቸው „…ማንም ሰው የፈለገውን ሓሳቡን በጽሑፍ ይሁን በቃል በወረቀት ይሁን በፊልም መልክ አቅርቦ መበተን ማሰራጨት ይችላል። …ሣንሱር የሚባል ነገር የለም። „ ብሎ አዲሱን ዘመን ያበስራል። ይኸው ሕገ መንግሥታቸው „መደራጀት መደገፍና መቃወም መሰብሰብ መምረጥና መመረጥ… መመራመር…ማንም ሰው ይችላል“ ይላል። እነዚህ እሴቶች እነዚህ ቫሊዩዎች ናቸው የአገርንና የሕዝብ አንድነትን የሕግ በላይነትን ከሁሉም በላይ የግለሰብ ነጻነትን አረጋግጦ ጀርመንን ዛሬ የደረሰችበት የሥልጣኔን ዕድገትና ደረጃ ላይ ያደረሳት። ይህ ብቻ አይደለም። የጀርመን ሕገ-መንግሥት የተመሰረተበት እሴት ሰብሰብ አድርገን ስናየነው „…በግለ ሰብ ሙሉ ነጻነት ላይ „የቆመ ነው። እዚያም ውስጥ „ በሕግ ፊት ሁሉም እኩል “ እንደሆነ ያነሳል። „የሕዝብ ውሳኔና ዲሞክራሲም“ በአገሪቱ እንዳለ ያረጋግጣል። የሕገ- መንግሥቱ እሴት ነጻው ሕብረተሰብ እንዴት እንደሚንቀሳቀስ ያብራራል። እዚያም ውስጥ የግል ሕይወትና የግል ኑሮና የመኖሪያ ቤቶች በማንም እንደማይደፈሩ በግልጽ ቋንቋ ያነሳል። 26


…ሃይማኖትና የፖለቲካ አመለካከት የግል እንደሆነ፣ በዚያውም በንግድ ላይ መሰማራትና በኢኮኖሚ ዘርፍ ውስጥ ገብቶ መንቀስቃስ፣ በአካባቢና በአገር ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠት…ተዘዋዎሮ ሐሳብ በጋራ ጉዳይ ላይ ከሌሎቹ ጋር መለዋወጥና መነጋገር፣ መረዳዳትና መከባበር… ሕገ መንግሥቱ እነዚህን ሁሉ እሴቶች ያረጋግጣል። የተመረጠው መንግሥትም አስተዳደርም ኃላፊነትና ግዳጅ እንዳለበትም ያነሳል።…. ሕጉን ለማክበር የሕዝብን ደህንነት ለመጠበቅ አገሪቱን ከአስከፊና አደገኛ ነገሮች ለመጠበቅ፣ ትምህርትንና ዕውቀትን ለማስፋፋት ሰላምን ለማውረድ ተፈጥሮን ለመጠበቅና ለመንከባከብ…ባህልናና ትውፈትን /ትራዲሽን ቋንቋንና ቅርሳቅርሶችን ለማዳበር ለመጠበቅ እንደዚሁ መንግሥትም ሕዝብም ኃላፊነት እንደአለባቸው ይገልጻል። ከዚሁ ጋር ማንም ሰው የሸንጎ አባልም ይሁን ወይም ሚኒስትር የሕሊና ነጻነት እንዳለውና ይህን ነጻነቱን ተጠቅሞ መደገፍ መቃወም እንደሚችል የሕጉ እሴት ያረጋግጥለታል። … ማታለልና ማጫበርበር ሥልጣንን መከታ አደርጎ አገርንና ሕዝብን አደጋ ላይማንም ፖለቲከኛ መጣል እንደማይቻል ሕጉ ያግዳል ። ለዚህም ነው የመሓላ ቃል በአደባባይ የሚሰጠውም! ከሁሉም በላይ የግል ሐብትን ያረጋግጣል። የጀርመን ኢኮኖሚም ያደገው በግለሰቦች ድካምና በተመራመሪ ጠበብቶች ጥረት በሠራተኛው ሙሉ ተሳትፎና በእሱ አገርና ሥራ ወዳድነት በሦስቱ ሕብረት ነው። የአይዲኦሎጂ ዕብደት -በታሪክ እንደምናውቀው- ከዚህ በፊት በተለያዩ ዘመናት ይህችን አገር (ድፍን አውሮፓንም ጭምር) ጦርነት ውስጥ ከቶ አመድ አልብሶአት ለሁለት በመጨረሻም ከፍሎአት ሕዝቡን ችግር ላይ ጥሎም ሲጨፍርባት ከርሞአል። ይኸው የአይዲኦሎጂ ዕብደትም የምዕራብ ጀርመኑን ተወላጅ ኤርሽ ሆኔከርን -ዛር-ላንድ የተወለደውን- ምሥራቅ በርሊን ገብቶ „ዲዲአርን“ ከሠላሳ አመት በላይ እንዲገዛ አድርጎታአል። 27


በርካታ የምዕራብ ጀርመን ፖለቲከኞችም – የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሐንስ ዲትሪሽ ጌንሸርና ሌሎቸ ከምሥራቅ ጀርመን መጥተው ነጻው የምዕራቡ ሕብረተሰብ ውስጥ ተሳትፈው መርተው የአገሪቱን አንድነት በዲፕሎማቲክ መንገድና በፖለቲካ ትግል መልሰው እነሱም አቋቁመዋል። በመጨረሻው እንደምናየው በበርሊን ግንብ ውድቆ:-የነጻ ሕብረተሰብ ቫሊዩ በአሸናፊነት ወጥቶአል። እንዲያውም ፍራንሲስ ፉክያማ እንደአላው ይህ ሥርዓት ትክክለኛነቱን አሳይቶአል። ቫሊዩና አይዲኦሎጂ ይለያያሉ። በእርግጥ በሌላ በኩል ቫሊዩና አይዲኦሎጂም ይያዛሉ። -ይህ ደግሞ ሌላ እራሱን የቻለ ሰፊ አርዕስት ነው። ለጊዜው ከዕብደት ዓለም ለመውጣት ከአይዲኦሎጂ ይልቅ እሴቱ ላይ ማተኮሩ ለአንድ ሕዝብና ለአንድ አገር ለፖለቲከኛም ጠቃሚ ነው። እሱም ብቻውን አይበቃም። ከቫሊዩስ ጋር ቨርቺውስን/ ትሩፋትን አብሮ ማንሳት የበለጠ ጠቃሚ ነው። ሞራልና ኤትክስንም፣ ትራዲሽንም ሲጨመሩበት ደግሞ ውሽት ጥራዝነጠቅነትና ጥላቻ ከፖለቲካ ትግል-እንዳለ ማጥፋት ባይቻልምቢያንስ ይርቃል። ይህ ደግሞ ከሆነ በነጻነት አንድ ሰው ቀና ነገር ለአገሩና ለሕዝቡ ማሰብ ይችላል። እኛ ነጻ-ሰው ነን ! እዚህ ደረጃ ላይ – ጉዳዩን እንዝጋው- ያደረሳቸው „የጀርመን ሕገመንግሥት“ የተነደፈው ከሦስት ገብተውበት ከነበረበት መኣትና ጣጣ እንደገና ተመልሰው እንዳይገቡ ለመትረፍ ነው። 28


አንደኛው ንጉሡን አባረው ከገቡበት ከቫይመር የአይዲኦሎጂ ትርምስ ለመሸሽ ነው። ሁለተኛው ከዘረኛው ከሒትለር ፋሺዚም የጠበንጃ ክክትል ሥርዓት ለመራቅ ነው። ሦስተኛው ምክንያት ደግሞ ከኮሚንስቶቹ አምባገነን የጠበንጃ አገዛዝ ለመትረፍም ነው። ከዚያ አልፈው አሁን የአውሮፓ አንድነት ሞተሩም አንቀሳቃሽ ሹፌሩም እነሱ ሁነዋል። ለምን እና እንዴት?

ምርጫው ከዚህ በሁዋላ የአንተ ነው።…. ነጻነት ወይስ ባርነት? ተፈሪ መኮንን ለአእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

.....

አዲስ እትም ፣ ቅጽ 2 ቁጥር 6

29


ካሲዮጵያና የ “ካሲዮጵያ ማህደር“ በግሪኮች ታሪከ፥ንግርት/ሚቶሎጊ እቴጌ ካሲዮጵያ የኢትዮጵያው መስፍንና ንጉሥ የንጉሡ የኬፊዎስ ሚስት ናት። ከሁለቱም ትዳር ቤት አንዲት መልከ መልካም ውብ የሆነች ልጃቸው ልዕልት አንድሮሜዳ የሚባለውን ስም የያዘች ትወለዳለች።ልጅቱዋ ተወዳዳሪ የሌላት ቆንጆ ናት ይባልላታል። ያም ሆኖ በቁንጅና እና በውበት በቁመናዋና በደም ግባቱዋ ግን በዚያች በኢትዮጵያ ምድር እናትዮዋን እቴጌ ካሲዮጵያ ማንም የሚበልጥ የለም በዚያን ዘመን አብሮ ይባላል። እቴጌይቱም ይህን ስለምታውቅ ከኢትዮጵያ አልፎ በዓለም ላይ እኔን የሚበልጥ የለም ብላ የምትኩራራ ነበረች። እንዲያውም ከምድር አልፎ ማንም ቢሆን ከባህር ውስጥ ሆነ ወይም ከየትኛውም ትልቅ ውቅያኖስ በሰማይ ላይም ውብ ተፈልጎ ቢመጣ ከእኔ ጋር የሚስተካከል ማንም የለም ባይ ናት። ቆንጆ ነኝ ብላ በዚያን ዘመን የምትኮራው ሌላ መልከ መልካም ውብ ልጅ ከውቅያኖሱ ንጕሥ ከኔሮይስ የምትወለደውን ልዕልት ኔርአይደን ነበረች። ይህች ልዕልት እቴጌ ካሲዮጵያ አንዴ አደባባይ ላይ ለሰው ሁሉ በይፋ የተናገረቺውን ነገር አሳዝኖአት ለአባቱዋአፈ-ታሪኩ እንደሚለው - ዝም ብለህ ታያለህ ወይ ብላ አልቅሳ ታጫውተዋለች። አባቱዋም ተበሰጭቶ ፖሳይዶን ለሚባለው አምላክ ጉዳዩን አይቶ እንዲፋረደው አቤቱታውን ለንጉሡ አንድ ቀን ያቀርብለታል። ፖሳይዶን የአባትና ልጅ አዘኔታ ሰምቶ የባህር አሣነባሪዎችንና ዘንዶዎችን ልኮ ምድሩንና አካባቢውን በወሃ ጥፋት አንዴ ይመታውና ድብልቅልቁን ያወጣዋል።አገሪቱ የምትተርፈው ሕዝቡም ከወረደበት ማዓት አምልጦ ሰላም የሚያገኘው -ንግርት ተናጋሪዎችና ሕልም ፈቺዎች ያኔ እንዳሉት- የእቴጌ ካሲዮጵያና የኢትዮጵያው ንጉሥ 30


የኬፊዎስ ውድ ልጅ ልዕልት አንድሮሜዳ ለዘንዶው ወይም ለትልቁ ዓሣ -ነባሪ መስዋዕት ሆና ስትሰጥ ነው ያኔ መረጋጋት ጠሚመጣው ብለው የታያቸውን ይናገራሉ። „አገር ይጥፋ ወይስ አንዲት ልዕልት ትሙት?“ በዚህ አርዕስት ዙሪያ ብዙ ሕዝቡም መኳንንቱም መሣፍንቱም ተከራከሩ። በሁዋላ ልዕልቲቱን ዓሣ ነባሪው ወይም ዘንዶው መጥቶ እሱዋን በልቶ ሰላም የሚሰፍን ከሆነ ትሰጥ ብለው ሁሉም ይስማማሉ።በመጨረሻው የባህሩ ዳር በሚገኘው አንድ ትልቅ ቋጥኝ ላይ አሥረዋት ከገቡበት ጣጣ ለመገላገል እሱዋን ጥለዋት ይሄዳሉ። ዘንዶው ሳይደርስ አሞራዎች ሊገነጣጥሉወት ያንጃብባሉ። አውሬ ሊበሉዋት ያፏጫሉ። በመጨረሻው ጀግናው ፔርሲዮስ ከንፎ መጥቶ ከዚያ የባህር አውሬ ያቺን ልዕልት ብድግ አድረጎወስዶ -አፈ ታሪኩ እንደሚለው - አድኖአት በሁዋላ ተፋቅረው ተዋደው እሱ ያገባታል። ከዚያን ዘመን ጀምሮ በጥንታዊው ዓለም ከእነዚያ ስምና ዝና ካተረፉት አርባ ስምንት ክዋክብት ውስጥ እቴጌ ካሲዮጵያ ባለዋ ንጉሥ ኬፊዎስ ልዕልት አንድሮሜዳና ፐተርሲዮስ ዘለዓለማዊ ሁነው ሰማይ ላይ ኮከባቸው በስማቸው ተመዝግበው እንዲያዙ ተደርጎአል። በ17ተኛው ክፍለ ዘመን ብቻ ምን እንደሆን አይታወቅም „የካሲዮጵያን ኮከብ“ በመቅደላዊት ማሪያም ስም ለመቀየር ታስቦ ያ ሓሳብ በሥራ ሳይተረጎም እንዳው ተናፍሶ በዚያው ቀርቶአል። እኛ ከንትርክ ነጻ- አድርገውን ወደፊት ሊያራምዱን የሚችሉንን የፖለቲካ አመለካከቶችና አቋሞች ከዛሬ ጀምሮ አንስተን እየፈታን

„የካሲዮጵያ ማህደር“ ውስጥ ለመክተት አስበናል።

31


አንድ ውጤት ላይ ሳንደር- እንደማሲቲካ ሲታኘክ እሰከ አሁን ድረስ አጅቦን ስለመጣው ስለ „ብሔር /ብሔረሰብ ጥያቄ…እሰከ መገንጠል ድረስ… „ በእሱ እንጀምራለን።

ለአእምሮየጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

32


ከ -ካሲዮጵያ እስከ መገነጣጠል !

ከ – ካሲዮጵ ያ እስከ መ ገ ነ ጣ ጠ ል/[1] ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነት ጥያቄ ውስጥ ለማስገባት እንደ ማስቲካ መልሰው መላልሰው የሚታኘኩ አርዕስቶች አሉ። ይህ ደግሞ ዛሬ አይደለም የተጀመረው። ቆይቶአል። እንዲያውም የሺህ አመታት ዕድሜ አለው። አረቦች ሃይማኖትን ሰበብ አድርገው ይህቺን አገር በትነው ለመያዝ በተዳጋጋሚ ሞክረዋል። ግብጾች ከጥንት ከፈርኦን ዘመናት ጀምረው ያካሄዱት ተንኮል አንዴም ሳይሳካላቸው ቀርቶአል። ፋርስ ብዙ ደክማለች።ግን አልሆነላትም። ታላቁ እስክንድር ብቻ ነው ዓለምን ለመግዛት ሲነሳ እኛን ሳይነካን አክብሮ በድንበሩዋ ላይ በማለፉ „ቅዱስ“ የሚባለውን ስም እሱ ብቻ ሊያተርፍ የቻለው። 33


ከሮማው ቄሳሮች-ኃይለኛው የዩሊዮስ ሴዛር እንኳን ያልደፈረውን ከ2 ሺህ አመት በሁዋላ አርፍዳ የተቋቋመቺው የጣሊያን መንግሥት ኢትዮጵያን ቅኝ አድርጋ ልትገዛ ሁለት ጊዜ መጥታ ሁለት ጊዜ ድል ተመታ ወደ መንደሩዋ ተመልሳለች።

እነዚህ ሁሉ ያልቻሉትን አሁን አንዳንድ ልጆቹዋ በተለያዩ ስሞች „ኢትዮጵያ“ የሚባል ነገር የለም ብለው አድመው ተነስተውባታል። ጥያቄው እነሱ ስንት ናቸው የሚለው ነው? አንድ መቶ? አምስት መቶ? አንድ ሺህ? ወይስ እነደሚፎክሩት ሁለትና አምስት ሺህ? እነሱስ በየጊዜው ምን ይላሉ? የሚለው ቀጣዩ ጥያቄ ነው። ምንድነው ሁል ጊዜ እንደ አዲስ ነገር የሚነሳው?የትኛውን አይዲኦሎጂ ነው የሚከተሉት? አንደኛው „የብሔር /ብሔረሰብ እኩልነት?“ የሚለው ተገቢ የሆነ ጥያቄ ነው። ሁለተኛው „…. እሰከ መገንጠል „ የሚለው ቅጥ ያጣጣጣ ነገር ነው። 34


ይህ አመለካከት፣ እንደዚህ ዓይነቱ ጥያቄ ከየት መጣ? የት ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ይህ መፈክር የተሰማው? ማነው የዚህ „ግሩም „ቲዎሪ አባቱ? ስንት ሰዎች ናቸው የዚህ ጥያቄ አራማጆቹ ? የት ቦታ ነው ይህ አይዲኦሎጂ በሥራ ተተርጉሞ ሰውን የስደሰተው?-በኤርትራ? ይህን አንስተን -የነገር ቋንጣ የለውም – መልስ እንሰጥበታለን። ሁለተኛው ከዚሁ ጋር ተያይዞ የተወረወረውና ግራ የሚያጋበው „በአማራው ላይ ብቻ የሚወረወረው ቅኝ ገዢዎች“ የሚባለው ክስ ነው። ለመሆኑ ማን ነው ዛሬ? ማንን ዛሬ የሚገዛው? የኦሮም ክልል ተብሎአል። የትግራይ ክልል ተብሎአል። የኦጋዴን… የአፋር የደቡብ ሕዝቦች…ተብሎ ማን ነው ማንን አሁን የሚያስተዳድረው? የሚገዛውስ? ለዚህ የሚሰጠው መልስ በቂ ነው። ሦስተኛው ኢትዮጵያ ከተመሰረተች ቢበዛ „ አንድ መቶ ዓመት ነው“ የሚለው የሕዝባዊ ወያኔና የኦነግ – በቅርቡ እንደተነበበው ደግሞ አቶ ኢሳያስ ወደ ታች ቀንስው ከእራሳቸው ዕድሜ በታች አድረገው „65 አመቱዋ ነው“ የሚለው ትንተና ነው። ለምን 50 አይሉም?- ለምን 25 አመት ብቻ ነው „ታሪክ“ ጸሓፊዎቻችን አይሉንም? የእነሱን „ታሪክ“ አጻጻፍ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ አንስተን ማየትዕድሜ ልክ ስለ አንድ ነገር ዝም ተብሎ እንደ ሞኝ አይወራም- ነገር ለመቋጨት አስፈላጊ ነው። ምናልባት ለማዘናጋት አውቆ የተወረወረ ነገር ይሆን? የልባቸውን እየሰሩ ሰውን በዚህ ጥያቄ ጠምዶ ለመያዝ ይሆን? ነጮች እንደዚህ ዓይነቱን ጉዳይ -ነገር ለማዘናጋት የሚደረገውን የፖለቲካ ጨዋታ - በዚህ አሳይቶ በዚያ ለመሮጥ „ፊንታ“ ይሉታል። በእርግጥም ብዙ ሰው እንደዚህ ዓይነቱ „የተማሰ ጉድጓድ ውስጥ ገብቶ“ ጊዜውን በከንቱ ያጠፋል። 35


አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ „ታሪክ“ ቢያንስ በሌሎቹ ሒሳብ አርባ ሺህ ሲደርስ አንዳንዶቹም ጠበብቶች ቢያንስ „የአሥር ሺህ አመት ዕድሜ አላት“ ብለው ለማሳመን ተነስተዋል። ለቀስቃሽ ፖለቲከኞች ሳይሆን ለምን ጉዳዩን ለታሪክ ጸሓፊዎች አንተውም። ኢሳያስ አፈወርቂና ሌሎ የታሪክ ሰው እንዳልሆኑ እናውቃለን። „ኢትዮጵያኖች ተጋብተው ተዋልደው ተካልሰዋል ወይስ ሳይነካኩ በጉርብትና ብቻ ከሩቁ እየተያዩ ሳይካለሱ ኑረዋል ወይ?“ የሚለው ጥያቄ ወደፊት አራተኛውን ቦታ ይይዛል። የጋራ መገበያያና መግባቢያ መማሪያም ቋንቋ ሊንጉዋ ፍራንካ ለኢትዮጵያ ያስፈልጋል ወይስ አያስፈልግም? የሚለውም ጥያቄ አብሮ ወደፊት ይታያል። ይህም አምስተኛውን ቦታ ይዞአል። በስድስተኛ ደረጃ ደግሞ ደጋግሞ እንደ አዲስ ነገር ስለ ዜጎች መብት (በዘር ላይ የተመሰረተ ሳይሆን) ስለ እያንዳንዱ ኢትዮጵያው ግለሰብ መብት መከበርና መጠበቅ በኢትዮጵያ እንደዚሁ እናነሳለን። እንግዲህ በሰባተኛ ደረጃ ስለ „ዲሞክራሲና ስለ ዲሞክራሲ የምርጫ ሥርዓት „ ስለ እነሱም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜም ባይባልም፣ ቢያንስ ግልጽነት ሰፍኖ„ የወሃ ቅዳ የወሃ መልስ“ ጨዋታና ፌዝ በአገራችን ፖለቲከኞች መካከል ማሳረጊያውን እንዲያገኝ – ማሲቲካም ታኝኮ የዚያኑ ቀን ይጣላል- ይህ እንዲሆን ወደፊት ጥረት እናደርጋለን። „ለመሆኑ በድርጅቱ አመራር ውስጥ ማነው ከሌሎቹ እጩዎች ጋር በይፋ ተወዳድሮ በአባለቶቹ በድምጽ ብልጫ የተመረጠው?“ብለንም ሁሉንም ፓርቲ እንጠይቃለን። ስለብሔር እኩልነት እሰከ መገንጠል ድረስ የሚለውን ጥያቄ የሚያነሱ ሰዎች እዚያ ላይ ከመድረሳችሁ በፊት በእራሳችሁ ቤት በመጀመሪያ በእኩልነት ደረጃ ከሌሎች አባሎች ጋር አብራችሁ ቆማችሁ በድርጅታችሁ ውስጥ ምርጫ አካሁዳችሁ ተመረጡ እንላለን።እንደዚህ ዓይነቱን አሰራር በእያንዳንዱ ድርጅት ውስጥ መኖር አለበት ብለንም ይህን የድርጅት ውስጥ ዲሞክራሲ እናነሳለን። 36


ይህን ለማለት በቂ ምክንያት አለን። አንዳቸውም ቢሆኑ በገዛ ቤታቸው ጋዜጠኞችን ጠርተው በይፋ ከሌሎቹ ጋር ተወዳድረው በአባሎቹ በብዙሃኑ ድምጽ የተመረጡ ሕጋዊ ማንዴት ያላቸው የድርጅት መሪዎች አይደሉም። ለምን ሰለእሱ አንስተው ሰዎች አይከራከሩም? ሁለተኛ እንዲያው በዘልማድ „…እሰከ መገንጠል ድረስ „ ይባላል እንጂ ያንን ጥያቄ በተግባር በሥራ ለመተርጎም በሚደረገው ጉዞ „የሚወራረደው ሒሳብ“ ማለት ከመስዋዕትነት እሰከ ጥፋትና ፍጅት ከዚያም አልፎ በደርግ እና በእህአዴግ የግዛት ዘመን በኤርትራ ላይ እንዳየነው ያ ሁሉ ትርምስ በመጨረሻው ወዴት ያመራል የሚለው ጥያቄ በደንብ የታሰበበት -ከላይኛውም መራራ ጉዞ ትምህርት ያልተገኘበት ታሪክ ነው። ለምን ስለዚህ ጉዳይ አይነሳም? በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠረው የተካለሰው ቤተ ሰብ ምን ይሆናል? እነዚህንና ሌሎቹን ጥያቄዎች ያልመለሰ ሰው -አንዴ እጃችን ተፈጅቶአል- ይህን „የመገንጠል“ ጥያቄ ዝም ብሎ ወርውሮ አውላላ ሜዳ ላይ ሊንጎራደድ አይችልም ። ሕዝቡም አይቀበለውም። እንግዲህ ይህን እናነሳለን። አብዛኛውን የኢትዮጵያን „ፖለቲከኞች“ አእምሮና ልብ እሰከ ዛሬ ድረስ አሸንፈው የሳቡትና የማረኩት „የእነ ማርክስና የእነ ኤንግልስ የእነ ሌኒንና የእነስታሊን የነማኦና…የነ ምንትስ“ትምህርቶች በአጠቃላይ የኮሚንዝም ቲዎሪ – እነሱ ናቸው(በጀርመን ምሳሌ እንዳየነው) አገሪቱን አተረማምሰው እዚህ ደረጃ ላይ ያደረሱ ፍልስፍናዎች- ስለሆነ፣ ስለዚህ የእነሱ ትምህርትና ፍልስፍና ለአገሪቱ ችግር መፍትሔ እንዳልሆኑ ወደፊት ሳንታክት መልሰን መላልሰን እናነሳለን። የኢትዮጵያ ውስጣዊ ችግር ማሰሪያ ያላገኘው፣ደርጅቶችም በአገሪቱ ውስጥ የማይስማሙት አብዛኛው የፖለቲካ ደርጅት ይህን ፍልስፍና በመከተሉ ነው። ችግሩም ያለው እዚያ ላይ ነው። መቁጠር ይቻላል… የፈለገ ሰው እንደሌላው ዓለም (በጀርመን አገር ሕገ-መንግሥቱን እሰከ አከበሩ ድረስ ኒዎ ናዚዎቹ ሆነ ኮሚኒስቶቹ መደራጀት ይችላሉ) በዚያ አይዲኦሎጂ በዚያ ትምህርት ሥር መንቀሳቀሱ መብታቸው ስለሆነ 37


ይችላሉ- ግን እሱ ብቻ ነው ለኢትዮጵያ መፍትሔው ወይም እኔ ብቻ ነኝ መፍትሔውን የማውቃው ብለው ሲሟገቱ ከአገኘን- እንደዚህ እያሉ የሚተናነቁ ናቸው - ( ለአገሪቱ ለኢትዮጵያ ችግር ስታሊን ሆነ ማርክስ እሰከ አሁን ድረስ ምንም ዓይነት መፍትሔ አላመጡም)- ተገቢውን ትችታችንን እንሰነዝራለን ። የኤርትራ፣ የኦሮሞ የትግሬ፣ የኦጋዴን ….ጥያቄ ያለ ስታሊን ቲዎሪና ያለ ማርክስ እና ሌኒን ያለ ማኦ ትምህርትና አይዲኦሎጂ ስማቸውን እየቀያየሩ መጥተው ደጋፊ አባልና ተከታይ ጀሌ መሰብሰብ እንደማይችሉ አንስተን በየጊዜው እንደዚህ ዓይነቱ ጨዋታ ወደፊት መልክ እንዲይዝም እንጥራለን። በስታሊን ቲዎሪ በማርክስ ትምህርት በሌኒን እና በማኦ አይዲኦሎጂ የትም ቦታ የትም አገር፣-የታወቀውን ለመድገም- የትም አህጉር ጤነኛ መንግሥት እንዳልተገነባ በየጊዝው እናነሳለን። ቻይናንን የሚጠቅሱልን አሉ። ኪዩባን የሚጠሩ። ወይም እስከነአካቴው ደፍረው አንዴውኑ ሰሜን ኮሪያን የሚጠቅሱም ከመካከላችን አይጠፉም።ግን በእነዚያ መንግሥታት ሥር ሰበአዊ መብቶች ይከበራሉ? ለመሆኑ ሕዝቡ መሪዎቹን መምረጥ ይችላል? ነጻ-ጋዜጣ ነጻ ኢንተርኔት አለ? ሰው በሰላም አለ ሰላይ የልቡን መናገር ይችላል? እላይ በተጠቀሱት ሰዎች ትምህርትና ፍልስፍና ሥር „ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች፣ በእነሱ አይዲኦሎጂ ሥር የትም አገር-እንደገና የታወቀውን ለመድገም- በሥራ ተተርጉሞ እንዳልታየ፣እንዳልመጣ ፈጽሞ እንዳልተከበሩ ወደፊት በተከታታይ በሚወጡት „የካሲዮጵያ ማህደር“ ላይ እንመላለስበታለን። ከሃምሳ አመት በላይ ሁለት ትውልድ ያንኑ መልሶ መላልሶ (ገዢዎቹ እነማን እንደሆኑ ግልጽ በሆኑበት ዘመን) እንደ ማስቲካ መፈክሮችን ማኘክ- ነጮቹ እንደሚሉት በያፍዝ አደንግዝ የመንደር ጨዋታ ጊዜአችንን ማጥፋት ጨርሶ ተገቢ አይደለም። ነገሮች መቋጠር አለባቸው።

38


እንግዲህ በዚሁ ወደ ተነሳንበት፣ በአለፉት ሃምሳ አመታት ትልቁን ቦታ ይዘው ስለነበሩት ጥያቄዎች እንመለስ።

የመደብ ትግል /የብሔር ትግል ለአርባና ሃምሣ አመታት እንዲያውም ለአለፉት ስድሳ አመታት በተከታታይ እንደ ወሃ መውቀጥ በየጊዜው (ሌላ አማራጭ መፍትሔ የሚሰጡ ቲዎሪና ትምህርቶች በዓለም ላይ የሌሉ ይመስል) መልሰው መላልሰው የኢትዮጵያ „ፖለቲከኞች“ ያንኑ „ የመደብ ወይም ደግሞእሱ አላዋጣ ሲል የብሔር ትግል“ የሚባለውን መፈክር ሲወቅጡልን ከርመዋል። በአገራችን አነጋገር የነገር ቋንጣ የለውም ይባላል። እንደ ሌላው የሠለጠኑ ሕዝቦችና መንግሥታት ከጊዜው ጋር አብረን እየተራመድን እኛም ለአለንበትና ለገባንበት ችግሮች መፍትሔ እየሰጠን እንሂድ ከአልን ከረጅም አመታት ጀምሮ የተከፈቱት አንዳንድ አጀንዳዎች ተዘግተው ወደፊት መራመድ ይኖርብናል። ተንዛዛ እኮ ! ከዚህ ሌላ ምንም የሚታወቅ መፈክር የለም እንዴ! „…አንዴ መገንጠል ሌላ ጊዜ አለመገንጠል። አንዴ „ለዲሞክራሲ ሌላ ጊዜ እዚያ ላይ ለመድረስ ጊዜ ስጡን። አንዴ አንድነት ሌላ ጊዜ መበታተን…“ ምንድነው የተያዘው ነገር?…ሃይማኖት ነው ወይስ ፖለቲካ? ኤርትራም -ዓይናችን ከፍተን እንመልከት-ተገንጥላ ያገኘቺው ትርፍ ስታሊን እንደተለመው „ ያንኑ የአንድ ሰው አንድ አምባገነን ሥርዓትን ነው።“ መገመት እንደሚቻለው እንደ ኢሳያስ ዓይነቱ አምባገነኖች ደግሞ በኢትዮጵያ „እነሱን የሚቆጣጣር ሕግና ሕገ – መንግሥት ….ተቋምና ተቋሞች የምርጫ ሥርዓትና ነጻ-ጋዜጠዎች ከሌሉ“…. ቁጥራቸው ነገ ብቻ ሳይሆን አሁንም ቢሆን „ብዙ“ ነው። ሰለዚህም ጉዳይ ቀደም ብለን እንደአነሳናቸው ወደፊትም እናነሳለን። የምንጀምረው „በብሔር ጥያቄ …እሰከ መገንጠል „ በሚለው ፍልስፍና ነው። 39


ከየት መጣ? ማን ነው የዚህ ጥያቄ አባቱ?

የብሔር እኩልነት …እሰከ መገንጠል ድረስ አልፍሬድ ሮዝንበርግ የሒትለር ችፍ አይዲኦሊጂስት -ይህ ነበር ማዕርጉሶቭየት ኅብረትንና ምሥራቅ አውሮፓን ለመበተንና በቀላሉ ለመያዝ ከአወጣቸው እቅዶች ውስጥ አንዱ ያን የሰማይ ስባሪ የሚክለውን „ትልቁን አህጉር“ ከውስጥ ገብቶ ለመበተን ያለው አማራጭ „ሕዝቡን በዘርና በየብሔሩ ከፋፍሎ“ በኮሚኒስቶቹ በነእስታሊን ላይ እንዲነሳ ማድረግ ነው። ከእሱም ጋር „የሃይማኖትን ልዩነት አብሮ አዳምቆ መወርወር ነው።“ በስታሊን ላይ ፋሺሽቶቹ የጠነሰሱትን ተንኮልና ሤራ እነሌኒንና እነስታሊን በሩሲያ ቄሣር በዘውድ አገዛዙ ላይ ከሠላሣ አምስት አመት በፊት ቃል በቃል እነሱ ከነደፉት ፕላን ጋር አንድና ልዩነት የሌለው ኩታ ገጠም ነው። ተመሳሳይ ድርጊት ቀይሰውሁለቱ ሞገደኞች በዘመናቸው በሕዝቡ መካከል አሠራጭተዋል። ፕላኑ አንድ ነው። አላማቸው አንደኛው ፋሺዝምን ሌላው የኮሚኒስቶችን አምባገነን ሥርዓት በመሆኑ „የተለያዩ“ ናቸው። ውጤቱ ግን ዞሮ ዞሮ የሥልጣን ጉዳይ ስለሆነያውና አንድ ነው ። ሁለቱም የፈለጉት የሁዋላ ሁዋላ „አምባገነን ሥርዓታቸውን“ በተለያዩ ስሞች በሰው ልጆች ላይ ለመዘርጋት ነው። በሒትለር ወይም በስታሊን ትዕዛዝ የሚተኮሰው የፋሺሺቱ ወይም የኮሚኒስቱ ጥይት የሚገድለው ሰው ወይም ተቃዋሚዎቹ የሚታሰሩበት የእሥር ቤት ሁኔታ አንድ ነው።ያኛው ፍራሽ ላይ ሲያስተኛ ይህኛው እስረኛውን መሬት ላይ ጥሎት አይሄድም። ቅቤ ሁለቱም ለተቃዋሚዎቻቸው አያቀብሉም። ሌኒንና ስታሊን ያሰቡትን የኦስትሪያ መንግሥት በባልካን፣ ታለቁዋ ብርታኒያ ደግሞ በዘመኑዋ በቅኝ ግዛቶቹዋ ላይ በደንብ 40


ተጠቅመውበታል። አፍሪካም በቀላሉ በኃያላን መንግሥታት በአሥራ ዘጠነኛው ክፍለ-ዘመን የተያዘቺውም በዚሁ በዘርና በነገድ ከፋፍሎ እና ነጥሎ ተራ በተራ በማጋጨት በተወሰደው ብልሃትና መንገድ ነው። ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመያዝ የሞከረቺውና ባህረ-ነጋሽ ይባል የነበረውን የሰሜን አካባቢ „ኤርትራ“ ብላ በኁዋላ የያዘቺው በዚሁ ዘዴ ነው። በመጀመሪያ አሰብ ገዛች። በሁዋላ ምጽዋን ያዘች። ቀጥሎ አሥመራን … እንዲያውም ከዚያው ከእነሱ ሰዎች ወታደር መልምላ አስታጥቃ ኢትዮጵያን -ምኒልክ ቀድማአቸው እንጂእንዲወጉም ያደረገችውም በዚሁ ቲዎሪ ነው። „በልዩነት ጥያቄ“ በአጭሩ በዘርና በቋንቋ ልዩነት፣ በሃይማኖትና በጾታ፣ በቀለምና በቆዳ ፣ ሩዋንዳ እንደ ታየው …በአፍንጫ ልዩነት…አንድን ሕዝብ ያውም ለብዙ መቶ አመታት በሰላም የኖረን ሕዝብ ከውስጥ ገብቶ እንደ ቦንብ የዘር ጥያቄን አፈንድቶ እነሱን የሚሰማ ከተገኘ መበተን ይቻላል። መንግሥታትና ሕዝቦች ደግሞ በዚህ ጥያቄ ሳቢያብዙ ቦታ ተበትነዋል። እነ ሌኒንና እነስታሊን ደጋፊዎቻቸውን ሲያባብሉና ሕዝቡን ሲሸነግሉ ይህን ነገር „በሁለት ፍቅራቸውን በጨረሱ በተሰላቹ በባልና በሚስት ፍቺ“ በእነሱ ሁኔታ ነገሩን አስቀምጠው በዘመናቸው ምንም አትሆኑም ብትፈልጉ ትታረቃላችሁ ከአልሆነም…ትለያያላችሁ እያሉ „ግሩምና ጥሩ ትምህርት“ – መርዝ ብንለው ይሻላል – ሰጥተው የሩሲያን ሕዝብ አዋክበዋል።

41


የሚሰሩትን በደንብ የሚያውቁት ሁለቱ አምባገነኖች ቄሣሩን ጥለው ግን ቤተ-መንገሥቱን ሲይዙ „…ወይዱ ከዚህ ብለው ተገንጣዩን በሙሉ ሰብስበው አንድ ሞቆጫ ውስጥ ከተው ወቅጠዋቸዋል።“ እሱን ትምህርት ነው የኢትዮጵያ „ነጻ- አውጪ ድርጅቶች“፣ ስማቸው ብዙ ነው- ጎትተው ኢትዮጵያ አስገብተው „የብሔር እኩልነት….እሰከ መገንጠል ድረስ „ መብት ነው ብለው፣ እሰከ አሁን ድረስ የሚያነታረከው ፍልሰፍና እንደ ትልቅ ቁም ነገር ታይቶና ተሰምቶ፣ እንደማይታወቅ መፍትሔ ተሽሞንሙኖ አገሩን እንዳለ ይህ ትምህርት እንዲያተረማምስ የተደረገው! ! ይህ ጥያቄ ከተነሳ ጊዜ ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምን ሁኖአል? ይህን የሚክድ የለም….በዚህ ጥያቄ ሳቢያ ሰው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል። ንብረት ወድሞአል። መግባባት ጠፍቶአል። ዕድገትና መሻሻል ተረስቶ አንዳንዱ አካባቢ – ኤርትራ ጥሩ ምሳሌ ናትበመጨረሻው ዛሬ ወደ እሥር ቤት ተቀይሮአል። በየወሩ ሦስት ሺህ ሰው አገሩን ለቆ ይወጣል ወይም ሊወጣ ሲሞክር ይያዛል ይባላል። ይህ ነው ሥልጣኔ? ይህ ነው „የእኩልነት„ ጥያቄ መጨረሻው?ትርፉ አምባገነንነት ነው? ሶሻሊዝም? የብሔር ጥያቄ የሕዝብ ጥያቄ አይደለም። የብሔር ጥያቄ አንሽዎቹ ቀስቀሰሾቹ አደራጆቹ (የትም አገር) ተማሪና ምሁራን ከእነሱም ጋር ኢትዮጵያን ለመበተን ፍላጎት ያላቸው የውጭ ኃይሎች የእነዚህ የሦስቱ ጥምር ሥራ ነው። ከብሔር ጥያቄ በፊት የመደብ ጥያቄ -በኢትዮጵያ ተማሪዎችና ምሁራን ዘንድ- ትልቁን ቦታ ይህ ጉዳይ ይዞ ነበር። ይህን እናውቃለን። እሱ ግን ኢትዮጵያ ውስጥ የወጡ የተለያዩ ጽሑፎች እንደሚመሰክሩት „ከአንደኛ ቅራኔነት ቦታውን ለቆ ወደ ሁለተኛ ሲወርድ ሁለተኛው ቅራኔ የብሔር ትግል (ይህንንም ትንትና ዲያሌክቲክስ ይሉታል) የአንደኛውን ቦታ እንዲይዝ ተደርጎአል።“ 42


ደርግ /ኢሠፓ የመደብ ትግሉን አራማጅ ሠፈር -እየፈጀና እየገደለ ለብቻው ይህን ቦታ ይይዛል። ነጻ-አውጪዎቹ „ የብሔር ትግሉን እሰከ መገንጠል“ ይዘው ያቺን አገር – ዛሬ መለስ ብለን ስንመለከተው የትም አገር በአልሰራ ዕውቀትና ጥበብ ትምህርት- ሁለቱ ወገኖች ተነስተው ያን አካባቢ እንዳልነበር አድርገው እነሱ -የቫይመርን ታሪክ ተመልከትበይገባኛል ጥያቄ አተረማምሰዋል። የሚደንቀው ከዚህ ሁሉ ትርምስና ሕይወት መጥፋት በሁዋላ ደግሞ አሁንም ቢሆን እነሱው ናቸው መጽሐፍ እየጻፉ ወረቀት እያወጡ የፖለቲካ ሜዳውን ለብቻቸው የያዙት! ሌኒን እና ስታሊን በጀርመን ንጉሥ ዕርዳታ ነው ሥልጣን ላይ የወጡት። አብዮት ካለውጭ ዕርዳታ የማይሳካ ይመስል ደርግ በሶቭየት እሱን የተኩት „ነጻ-አውጪዎቹ“ ደግሞ በጎረቤት አገሮችና በምዕራቡ ዓለም በእነሱ ብርታት ሥልጣን ላይ ወጥተዋል። ደርግና እነ ኮነሬል ምንግሥቱ ኃይለ ማሪያም ሥልጣን ላይ ለ17 አመታት የቆዩት በሶቪየት ገንዘብና በእነሱ መሣሪያ፣ በምሥራቅ ጀርመን የስለላ ድርጅት ድጋፍና በሁዋላ በመጣችው ኪዩባ ነው። ደርግ በተራው-በሩ አሁን ለማንም ክፍት ነው- በውጭ ኃይሎች ትብብር ከሥልጣኑ ይወርዳል። መንግሥቱ ኃይለ ማሪያም በእነሱ ምክር፣ ንዋይና ድጋፍ አገሪቱን ለቆ ይወጣል። በብሔር ትግል ስም ሥልጣኑን የተረከቡት ኢትዮጵያን ለሁለት ከፍለው የያዙት ሕዝባዊ ወያኔና ሻቢያ ለአጭር ጊዜ ኦነግ -ሦስቱም ድርጅቶች ተመካክረው -ዩጎዚላቪያ እየተገነጣጠለች ሶቪየት ኅብረት እንደዚሁ እየተፈረካከሰች እያዩ፣ – ሕገ- መንግሥቱ ላይ „…እሰከ መገንጠል „ የሚለውን የስታሊን መፍትሔ ለኢትዮጵያ ይተልማሉ። ምሳሌ ሲሰጡ ሌኒን እና ስታሊን አንዴ የሰጡትን የባልና ሚስት የፍች ወረቀት ጉዳይ መልሰው መላልሰው እነሱ ያነሳሉ። 43


ኢትዮጵያኖች ተካልሰው ተደባቀልው በሃይማኖታቸውና በባህላቸው ተሳስረው ይኖሩ እንደ ነበረ በደንብ የታወቀው የባድሜ ጦርነትን አስታኮ የተነሳው አገር ልቀቁ የሚለው አዋጅ ከታወጀ በሁዋላ ነው። በዚህ ሳቢያ ስንቱ „ኤርትራዊ“ ኢትዮጵያን ለቆ እንዲወጣ ተደርጎአል። ስንቱ ኢትዮጵያዊ „ኤርትራን“ ለቆ እንዲሸሽ ተገዶአል። በሁዋላ እንደምንሰማው አቶ ኢሳያስ እና ሌሎች የአሥመራው የአመራር ሰዎች በአንድ በኩል አቶ መለሰና እንደዚሁ የእህአዴግ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎች በሌላ በኩል „የትግሬና የሐማሴን፣ የአከለጉዛዬና የሰራዬ …የወልቃይትና….ተወላጆች-የኢትዮጵያ ልጆች ሁነው ይገኛሉ።“

ይህ ነው የብሔር እኩልነት ጥያቄ መጨረሻው? ፖለቲካ ማለት-ከፖለቲካ ፍልስፍና አንዳንድ ነገር እንማር ከአልን- ነገና ከነገ ወዲያ ምን ይመጣል ብሎ አርቆ ማሰብ ማለት ነው። ፖለቲከኛ ማለት ችግር ፈቺ መፍትሔ አቅራቢ እንጂ በችግር ላይ ችግር ቀፍቃፊና ፈልፋይ መከራም ጠሪ ማለት አይደለም። ፖለቲካኛ በአንድ በሠለጠነ ሕብረተስብ ውስጥ ሰው ሁሉ ተቻችሎ ተከባብሮ የሚኖርበትን መንገድና ዘዴ ፈላጊ እንጂ እሳት ጫሪ ቤንዚን አርከፍካፊ ማለት አይደልም። በዚህ መልኩ „የብሔር እኩልነት ጥያቄ“ ልክ እንደ ሃይማኖት እኩልነት -እንደ እስላሙና እንደ ክርስቲያኑ ወይም እንደ አቴኢስቱ….- ሁሉም ሰው እንደ እምነቱና እንደ ዘሩ በሕብረተሰቡ ውስጥ ተቻችሎና ተከባብሮ ተረዳድቶና ተሳስቦ፣ ተሰባስቦም አንድ ላይ የሚኖርበትን ሥርዓት በጋራ ማዘጋጀት ማለት እንጂ -አንዱ በአንዱ ላይ ተነስቶ ወይም አንዱ ከሌላው ተገንጥሎ በሌላ አነጋገር „ ክርስቲያኑ ከእስላሙ ተለይቶ የራሱን ሪፓብሊክ መስርቶ ይኑር „ ማለት አይደልም። ይህ እንዳይሆን የዓለም አቀፍ ሕግም ይከለክላል። በጎረቤት አገር በኬንያ 40 ብሔር ብሔረሰቦች አብረው ይኖራሉ። በቱርክ 80 በናይጄሪያ 380 በአሜሪካን ደግሞ ከዓለም ዙሪያ የመጡ 44


በሺህና ሁለት ሦስት ሺህ የሚቆጠሩ ብሔር /ብሔረ ሰቦች አብረው አንድ ላይ ይኖራሉ። እነዚህ ሁሉ ቢገነጠሉና ቢገነጣጠሉ በተለይ በአፍሪካ – እንኳን ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛነሽ እንደሚባለው እራሳቸውን፣ በመድሓኒትና በልብስ ….ወታደሮቻቸውን ፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ አስተማሪዎችን ……እነዚህን ሁሉ የሚያስተዳድሩበት የቀለብ ገንዘብ የሌላቸው- አለ የውጭ ዕርዳታ- አንድ ቀን ብቻቸውን መቆም የማይችሉ አገሮች መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው። ነገ ተበታትነው ሦስት ሺህ መንግሥታት መሥርተው መጥተው የእህል መግዣ ብርና የምንኖርበትየዕርዳታ ገንዘብስጡን ብለው ቢለምኑም (እንደምናውቃው ሁሉም ደሃ ነው) ከእንዱስትሪ አገሮች ውስጥ እነሱን ዞር ብሎ የሚያያቸውና እጁን የሚዘረጋላቸው ቢቆጠሩ „ትንሽ“ ናቸው። ኤርትራ እንድትገነጠልም በኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት ስም የተጻፈው ደብዳቤም አንድ ቀን የሚያጠያይቅ ነው። የብሔር እኩልነት ጥያቄ እንደ ሃይማኖት እኩልነት ጥያቄ ተገቢ ጥያቄና መልስ ማግኘት ያለበትም የዲሞክራቲክ ጥያቄ ነው። ግን ለምንድነው የብሔር ጥያቄን የሚያነሱ „ነጻ-አውጪ“ ነን ብለው እራሳቸውን የሚጠሩ ድርጅት መሪዎችና ደጋፊዎች ስለ ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ጉዳይ ጮክ ብለው ሲናገሩ ሲጽፉ ሲቀሰቅሱ የማይታየው የማይሰማው?ወይም በኤርትራና በኢትዮጵያ ሁለቱም ነጻ-አውጪዎች ናቸው- ሰበአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ተከብረው የማናየው? ለምንድነው „አማራ አማራ…ጨቆነን „ ይሉ የነበሩ ሰዎች አሁን በይፋ ስለ ሰበአዊ መብቶች መከበር በኢትዮጵያ በይፋ የማይናገሩት? ትልቁ ጥያቄ እሱ ነው።

45


የተራው ሕዝብ ችግር የሚበላው ዳቦ፣ የሚጠጣው ንጹህ ወሃ፣የሥራ እድልና የቀን ልብሱ፣ የማታ ብርድ ልብሱ፣ የውጋት ማሰታገሻ መድሐኒቱና ጡረታው፣ የዓይን ብርሃኑና የልጆቹ ሆድና ትምህርት ጉዳይ፣የቤቱ ጣራና ቀዳዳ የበዛው የግድግዳው የምሶሶው የማሳው ጉዳይ ነው። ይህም ሌላው አብይና ዋና አንገብጋቢ የሕዝብ ጥያቄ ነው። የብሔር ጥያቄ መልስ የሚያገኘው የግለሰብ ሰበአዊ መብቶች በኢትዮጵያ በይፋ ሲታወቁ ነው። ዜጋው መምረጥና መመረጥ ሲችል መጻፍና መተቸት መሰብሰብና መደራጀት መናገርና መቃወም በአገሪቱ መብቱ ታውቆ ሲቻል ብቻ ነው። …ሕግና የሕግ በላይነት ሲሰፍን ብቻ ነው። [1]The Queen

Cassiopeia, wife of kingCepheus of Æthiopia

ለአእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

46


ቤተ-ክርስቲያን ሲሸጥ ሲለወጥ! ዘመኑ ተቀይሮአል። ተቀርጾ አንድ ቀን በዜና መልክ በቴሌቭዠን የተላለፈው ፊልም ከአእምሮ በቀላሉ አይጠፋም። ያኔ የተጀመረውም ጉዞ በፈጣን እርምጃ አሁን ወደፊት ቀጥሎአል። በጸሎት ሥነ-ስርዓት ነበር ያ መቅደስ ለመጨረሻ ጊዜ የተዘጋው።በርካታ ጋዜጠኞችም ታሪኩን አጅበውታል። ብዙዎቹ ደንግጠው አስተያታቸውን ሰጥተውበታል። አቴስቶቹ ምንም ነገር እንዳልሆነ በአጠገቡ አልፈዋል። ከመዘጋቱ በፊት ቀሳውስቶቹ የእሁድ ጥዋት ተሰብሰበው እንደተለመደው የቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት አካሂደዋል። ምዕመናን ሥጋ ወደሙ ለመጨረሻ ጊዜ ተቀብለዋል። መዝሙር ሁሉም አብረው ዘምረዋል። ከዚያ በሁዋላ ተራ በተራ እና አንድ በአንድ ቀስ እያሉ የቤተ ክርሰተያኑን መስቀሎች ሥዕሎች መጽሓፍትና ውድ የስጦታ ዕቃዎች ዋንጫና የቄሶች ልብሶች ካባና የሻማ መስቀመጫዎችን እየተሸከሙ አውጥተው መኪና ላይ እየዘመሩ ጭነው ወደ ቤታቸው በሩን ዘግተው ተመልሰዋል። እዚያ የቀረው የሕጻናት መጠመቂያ አሸንዳና አግዳሚ ወንበሮቹ ብቻ ናቸው። በዚያን ቀን ሆነ በሌሎች የጸሎት ቀናት ያለፉት አመታት በተከታታይ አንድም ልጅ አልተጠመቀበትም። ችግሩ ያለውም እዚያ ላይ ነው። 47


ወጣቱና ተተኪው ትውልድ እንደ አባቶቻቸውና እንደ እናቶታቸው ቤተክርስቲያን መሄድ ሄዶ መጸለይ እነሱ ከአቆሙ ጊዜው ረዘም ይላል። ጸሎት ለእነሱ መንፈስን ማደስ ሳይሆን ግዳጅ ይመስላቸዋል።መጽሓፍ መድገም ስብከት መስማት የእግዚአብሔርን ቃል ማዳመጥ ንስሓ መግባት እነዚህ ሁሉ -በእነሱ ዓይን -ጊዜው ያለፈበትና ከዘመኑ ዕውቀትና ሥልጣኔ ጋርም አብሮ የማይሄዱ ነገሮች ናቸው ባይ ናቸው። ከዚያም በላይ በሰበሰቡትና በአገኙት ዕውቀት „እግዚአብሔር የለም“ ከእነሱ መካከል የሚሉ ብዙ ናቸው። ይህ ሁሉ አመለካከት ደግሞ በመጨረሻው ለቤተ ክርስቲያን እንደወላጆቻቸውና እንደ አያት ቅድመ አያቶቻቸው በተራቸው ይህን ከትውልድ ወደ ትውልድ ማስተላለፍ የሚገባቸውን ኃላፊነት „እምቢ … ግብርም ለቤተ-ክርስቲያን አንከፍልም „ እነሱን ወደሚለው ውሳኔም ወስዶአቸዋል። „ቤተ-ክርስቲያኑን የምናስተዳድርበት ገንዘብ ቢኖረን „አስተዳዳሪው ቄሱ እንዳሉት „…ይህኛውን ባልዘጋነውና ቢያንስ በአሉትና ከቀሩት ሰዎች ጋር አብረን ተሰብስበን አንድላይ በየሳምንቱ እያስቀደስን በቆየን ነበር….“ ብለዋል። ከአሜሪካን አገር የመጡ አገር ጎብኚዎችና የሉተር ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ተከታዮች ጀርመን አገር ሲመጡና የጀርመንን ምዕምናን ሲመለከቱ „….ለመሆኑ እምነቱ የት ደረሰ ?“ብለው ሁሌ ያገኙትን ሰው እዚህ ይጠይቃሉ። በእርግጥ የቀድሞው የምሥራቅ ጀርመን ኮሚኒስት መንግሥት ሃይማኖትንና ቤተ ክርስቲያንን አጥላልቶ ብዙዎቹን ተከታዮች አዳክሞ ቤተ ክርስቲያኑዋን በጉልበቱና በፕሮፓጋንዳው ኦና ለማድረግ ብዙ ጥረት አድርጎአል።

48


አሁን ግን ሰውን ሁሉ ግራ እያጋባ የመጣው በሰሜን ጀርመን ትላልቅ ከተማዎች እንደ በረሊንና እንደ ሓምቡርግ እንዲሁም በዝቅተኛው ሳክሶኒያ ማለት በአብዛኛው ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን አማኞች መካከል እንደ ኮሚኒስቶቹ እዚህ መንግሥት ጫናውን በማያሳይበት አገር የምዕመናኑ ቁጥር ቀንሶ ቤተክርስቲያን እስከ መዝጋት ድረስ ያደረሰው ጉዳይ ምን እንደሆነ እሱን ለመረዳት ብዙ ሰው ግራ ተጋብቶታል። በደቡቡ ጀርመን በካቶሊክ ሃይማኖት ተከታዮች መካከል እንደዚህ ዓይነቱ ነገር ፈጽሞ እዚያ አካባቢ አይታይም። ካቶሊኮች ኃይለኛ ሥርዓትና የጠበቀ እምነት እንዳላቸው ይነገርላቸው። ወላጆችም ባህሉን ሥነሥርዓቱን ወጉን ትውፈቱን የመጽሓፍ ቅዱስ ጥናቱንና ሳምንታዊ ትምህርቱን ለልጆቻቸው ተቆጣጥረውና ጠብቀው ለእነሱ እንደተላለፈው እነሱም ማስተላለፉን-እዚህ እንደሚባለውይችሉበታል። የሉተር ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን አማኞች ግን ይህን ኃላፊነት እንዳአልቻሉበት አሁን የተፈጠረው ክስተት ያሳያል። በርካታ ቤተ-ክርስቲያኖች እዚህ ሰሜን ጀርመን መቅደሱ ኦና ሁኖ አሁን ለሽያጭ ቀርበዋል። እኔ እራሴ የዛሬ ሃያ አምስት አመት በፊት ለዕረፍት ወደ ዝቅተኛው ሳክሶንያ ክፍለ-አገር ከጓደኞቼ ጋር በወረድኩበት ጊዜ ራት የት ልንበላ እንችላላለን? ብለን ጠይቀን የተሰጠን አድራሻ በር ላይ ስንደርሰ ተደናግጬ ያለሁበትንና የደረስንበትን ቦታና ቤት ቀና ብዬ አይቼ ዓይኔን ማመን ፈጽሞ አቅቶኝ ነበር። ፈልገን እራት ለመብላት የደረስንበት ቤት አንድ ጥንታዊ ትልቅ ቤተክርስቲያን ነው። በሩን ከፍተን ስንገባ ለስላሳ ሙዚቃ ይሰማል። 49


መቅደሱ ላይ ዱሮ ቄሱ የሚቀድስበትና ሥጋው ወደሙ ሰዎች የሚቀበሉበት ቦታ ወይም ሠርገኞች ቀለበት ተለዋውጠው የፈቃደኛነት ቃለቸውን የሚሰጡበት ሥፍራ ቢራውና ሌሎች መጠጦች የሚቀዱበት „ባንኮኒ“ ነው። በመጽሓፍና በሻማ ፋንታ የአረቄ ጠርሙስና የምግብ ማዘዣ ደብተሮች የሲጋራ መተርኮሻ ትናንሽ ሳህኖች ሹካና ማንኪያ ተቀምጠዋል። አሰላፊ ሠራተኛ ሴቶች ከግራና ከቀኝ ቱር ቱር እያሉ መጠጡንና ምግቡን ዱሮ አግዳሚ ወንበር በነበረበት አሁን ጠረጴዛና ወንበር ይዘው ሲጋራቸውን እያጤሱ ለሚጠብቁ ሰዎች ያቀርባሉ። እምድር ቤቱ ሰለሞላ እኛን ወደላይ ወደ ሠገነቱ ቦታ እንዳለ አንደኛዋ ጠቁማን „ሂዱ ውጡ እኔ እመጣለሁ“ ብላ ሥራዋን ቀጠለች። ምግባችንን አዘን ቢራችንን እና ወይናችንን ጠጥተን ማዕድቤቱ ለመሆኑ የትነው ብዬ ጠየኩ። እሱም ከመቅደሱ ጀርባ እንደሆነ ተነገረኝ። መጸዳጃ ቤቱም -ለወንድና ለሴት ዱሮም ቢሆን የነበረበት ቦታ እዚያው ቤተ-ክርስቲያኑ ምድር ቤት ውስጥ እንዳለ ተነገረኝ። ይህ የዛሬ ሃያ አምስት አመት ታሪክ ነው። አሁን ጊዜው ተቀይሮ የቀድሞ ቤተክርስቲያኖች የወጣቶች ዳንኪራ መራገጫ፣ የልብስና የመጽሓፍት ወይም ሸቀጣሸቀጥ መሸጫ ቤቶች ሁነዋል። አንዳንዴም የሙዚቃ መደገሻ ቤቶችእና የሥዕል ኤግዚቪዥን መድረኮችም ሁነው ያገለግላሉ። አንዳንዶቹ ተሸጠው የግሪክና የራሸያ የሶሪያና የግብጽ ኦርቶዶክሶች ፣ የፖላንድ ካቶሊኮች፣ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተከታዮችም ገንዘብ ከአላቸው የሚገዙት ሁነዋል። ይህ ብዙዎቹ ከሆነ አይቀር ሲጠየቁ የሚመኙት ነው። ያለፈው አመት ደግሞ የሓምቡርጉን የእቫንጀሊስት ቤተክርስትያን ለመግዛት እንፈልጋለን ብለው የቀረቡት እንግዶች ሌሎች ሁነዋል። 50


„አል- ኑር“ የሚባል አንድ በሕግ የተመዘገበ የእስላም ሃይማኖት ተከታዮች ማህበር ይህን ሕንጻ ገዝቶ ወደ መስጊድ ለመቀየር ሓሳቡን ግልጽ ከአደረገ ወዲህ ኃይለኛ ክርክር ተነስቶ ደጋፊውንም ተቃዋሚውንም አነጋግሮ „…ለምን ይህ ይሆናል? ….ለምን መሆን የለበትም?“ ወደሚለው ጥያቄ ሻጮቹንም አማኞቹንም ሰውንም ሁሉ ወደዚያ ወስዶአቸዋል። „…እንዴት መስቀልን በግማሽ ጨረቃ እንለውጣለን? እነዴትስ ዓናችን እያየ ወደዚያ ይለወጣል?“ አንዳዶቹ ሲሉ „…ከዳንኪራና ከመሸታ ቤት መስጊድ ቢሆን ይሻላል።“ የሚል መልስም ከአንዳንዶቹ እንደዚህ ሲባል ተሰምቶአል። „…ዘመናዊሥልጣኔና አጉል የሃይማኖት ንቀት ይህን አምጥቶ ሜዳውን ለሞስሊሞቹ አመቻችቶ ሰጠ „ ብለው ሌሎቹ አማረው ተናግረዋል። „በምንም ዓይነት መሽጥ የለበትም።ሁለቱ ሃይማኖቶች ካቶሊክና ኢቫንጀሊስቶቹ አንድ ላይ ቆመው ይህን ነገር ማገድ አለባቸው። „ ብለው አንድንድ ቀሳውስቶች ተነስተዋል። ግን የሁለቱ አንዴ ተለያይተው ይኖሩ የነበሩ ቤተ ክርስቲያኖች ስምምነት „አንድ ለመሆን“ ብዙ ጊዜ ይጠይቃል። ይህ ሁሉ የሆነው „…ብዙ ቤተ-ክርስቲያኖች በስድሳውና በሰባው አመተ ምህረት አለ ፕላን በመሰራታቸው ነው …“የሚሉም ሰዎች ድምጽ ሓምቡርግ ላይ ተሰምቶአል። ችግሩ ያለው እሱ ላይ ሳይሆን ብዙው ወጣት ትውልድ ከቤተክርስቲያን በመራቁ ነው። ወጣ ወረደ ገዢዋቹ የሞስሊም ማህበረሰብ መስጊድ አድርገን እንሰግድበታለን“ብለዋል።

„…ውስጡን አድሰን

51


በአምስተረዳም ከተማ ማቆሚያም ሁኖአል።

በሆላንድ

ቤተ-ክረስቲያን

የብስክሌት

ማርቲን ሉተር ይህ ቀን ይመጣል ብሎ እንቅስቃሴውን ሲጀምር ፈጽሞ አላሰበም ነበር። እንደ መከፋፈል መጥፎ ነገር የለም። ክፉ ቀን ሲመጣ እነደ መጠጊያና መጠለያ እምነትና ተሰፋ የሚሰጥ ቤት የትም አይገኝም። „…እስላሞቹ እነሱን የሚያሰባስብና አንድ የሚያደርጋቸው ጠንካራ ሃይመኖት አላቸው። እኛን ምዕራቦቹን ግን ምን የሚያሰባስበን ነገር አለ? ዋናው ጥያቄ „ አንዱ እንዳለው „እሱ ነው ብሎ“ ከእኔ ተሰናብቶአል። ዕውነት አለው።

ለአእምሮየጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

52


ከታሪክ ሰነድ * -

የተላከ ከእቴጌ ጣይቱ ብረሃነ ዘኢትዮጵያ -

-

ቀኃሥ ና ማርቲን ሉተር ኪንግ

BLACK GERMAN HOLOCAUST VICTIMS

53


የተላከ ከእቴጌ ጣይቱ ብረሃነ ዘኢትዮጵያ

54


(የላይኛው ሰነድ እንደገና ሲጻፍ) የተላከ ከእቴጌ ጥይቱ ብረሃነ ዘኢትዮጵያ ይድረስ ከማህበረ ዲር ሥልጣን ወደብረ ገነት ዘኢየሩሳሌም። እንዴት ሰንብታችኀል። እኔ እግዚአብሔር ይመስገን ደህና ነኝ። እናንተ ብትስማሙ እርስ በርሳችሁ ብትፋቀሩ አንድነታችሁን ብታጸኑ ይሻልል እንጂ ትግሬ የብቻው ነው ሸዋ የብቻው ነው ቢገምድር ጎጃም የብቻው ነው እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ። እኛስ በኢየሩሳሌም ነገር ይህን ያህል መድከማችን ያንን ያህል ብር ባንክ አግብተን የዚያን ወለድና አቤቱ የሚወጣውን ክራይ መስጠታችን እንዳትቸገሩ የሰው ፊት እንዳታዩ ያንን እየበላችሁ ለኛም የጌታችን ደም ከፈሰሰበት ላይ ዳዊት እብድትደግሙልን እንድታዝኑልን እናንተም ፩ ነታችሁን እንዲጸና ብለን ነው እንጅ ገንዘቡ ተርፎ ባገራችን በኢትዮጵያ ለምንሰጠው ሰው አጥተን አይደለም።አሁንም ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ እናንተም እርስ በእርሳቸሁ ተፋቀሩ ለኛም ዳዊት ድገሙልን እዘኑልን ሳትቸገሩ እንዴት የድፍን አውሮፓ መሣቂያ ትሆናላችሁ። አሁንም ይኸው እማሆይ ወለተ ተክሌ መቃብሬ ከዚያውይሁን ብላ መጥታለችና አደራችሁን በምኑም በምኑም ነገር እንዳታስቀይሟት። እንግዲህ ሷ እንዲህ አደረጉኝ ብላ የላከብችን እንደሆን እናንተንም እጠላችኀለሁ።እኔንም እንዳስትቀይሙኝ። 29 ቀን 1900 ዓመት አዲስ አበባ ከተማ ተጻፈ ***

መልዕክቱ በነገር አሁን ለተሳከረውና ለማይደማመጠው ትውልድ የተጻፈ ይመስላል

55


ወደፊት „በባዕድ ፊት መሳቂያና መሳለቂያ“ እንደይሆኑም ምክርና ተግሣጽ ይኸው ደብዳቤ ይሰነዝራል። የተለያዩና የተበጣበጡ የኢትዮጵያ ልጆችንም ያስጠነቅቃል። ፩ ነታችሁን አጽኑም …ይላል። የተጻፈው ከመቶ አመት በፊት ነው። የተላከውም ከሺህ ሰምንት መቶ አመት በፊት ጅምሮ ኢትዮጵያ በመካከለኛው ምሥራቅ በኢየሩሳሌም ለምስታተዳድረው ገዳም ኑዋሪዎች ነው። „…እናንተ ብትስማሙ እርስ በእርሳችሁ ብትፋቀሩ አንድነታችሁን ብታጸኑ ይሻላል …“ የሚለው ደብዳቤው ላይ የሰፈረው የዓረፍተ ነገር አሰካክ የሐዋሪያው ጳውሎስን መልዕክት -አንድ አንባቢን ያስታውሳል። ይህም እቴጌይቱ አርቀው የሚያስቡ የስው ልጆች ባህሪና የሰው ልጆች የተፈጥሮ ድክመት የት ላይ እንደሆነ አንዴትም መታረም እነደ አለበት ደህና አድረጎ የገባቸው መሆኑን ከደብዳቤው መልዕክት መገንዘብምይችላል። እቴጌይቱ ከባለቤታቸው ከአጼ ምኒልክ ጋር ጥሩ የፖለቲካ ቀያሽ (ስታረተጂስት) መሆናቸው አደዋ ላይ ብቻ ሳይሆን በሌላም መስክ ላይ ደህና አድርገው በጊዜአቸው ማን መሆናቸውን አሳይተው አስመስክረዋል። ። እቴጌ ጣይቱ እንደ አጼ ምኒልክ-ብዙዎቹ እንደሚሉት-የሰው ምክር አዳምጠውም መርምረው አመዛዝነው ውሳኔ መስጠትም ይችሉበታል። „…አንድነታችሁን ብታጸኑ ይሻላል እንጂ… „ -ይህ ነው መልዕክቱን ከመቶ አመት በሁዋላ አሁን እንደገና ትኩስ አድርጎ እኛም እንድናነሳው ያደረገን አዲስ የሚያደርገውም- „…ትግሬ የብቻ ነው ሸዋ የብቻ ነው ቢገምድር ጎጃም የብቻ ነው እያላችሁ ጎሣ እየለያችሁ ብትጣሉ ምን ትረባላችሁ።…አሁን ስለእግዚአብሔር ብላችሁ እናንተም እርስ በእራሳችሁ ተፋቀሩ( ….) ሳትቸገሩ እንዴት የድፍን አውሮፓ መሣቂያ 56


ትሆናለችሁ።“ የሚለውን ዓረፍተ ነገር ነውመርጠው በደብዳቤአቸው ላይ አስፍረዋል። „ጎሣ መለየት“ የሚለው ቃልም „የአውሮፓ መሣቂያ እንዳትሆኑ „ ከሚለው ጋርም በትክክል አብሮ ተቀምጦአል። ደብዳቤው ለአሁኑ የሃይማኖት አባቶቻችንትላንት የተጸፈም ይመስላል። ከእነሱም ጋር ወደውም ሆነ ሳይወዱ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተገደው „ለተገነጠለቱም“ የኤርትራ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን አብሮም የተሰነዘረ ይመስላል። በዚሁ ሳቢያም ከእነሱ ጋር አብረው (ሳይወዱ)ለሄዱት ለካቶሊኩም ለውንጌላዊቱም፣ ለሞስሊም ሃይማኖት ተከታዮች ይመስላል። አንድነት ተፋልሶ „እንደ ሽርሽር„የታየው „…መገንጠል“ ትዳር በብዙ ቦታዎች አፍረሶአል። ቤተሰቦች በትኖአል። ልጆችን አለወላጅ ወላጆችን አለልጆቻቸው አስቀርቶአል። ጦርነት ተከፍቶም ሥፍር ቁጥር የሌለው ሰው ከሁለቱም ወገን ሞተዋል።… ተበትነው ለሄዱትም ወገኖቻችን ደብዳቤው የተጻፈም ይመስላል። ከሁሉም አሁን ቢሆን „ጌጥ“ እየሆነ ለመጣው ለዘር ክፍፍል አራጋቢዎች ከመጥፎ ሓሳባቸው ቆጠብ እንዲሉና እንዲያስቡበት የተወረወረም ማስጠንቀቂያ ይመስላል። ጣይቱ „…ሳትቸገሩ እንዴት የድፍን አውሮፓ መሣቂያ ትሆናላችሁ“ ስሉ በተዘዋዋሪ የአደዋን ድል ለካህናቶቹ መልሰው ማስታወሳቸው ነው። ቀደም ሲል ኢትዮጵያኖች ተለያይተው ሳይሆን ተባብረው አንድ ላይ ሁነው ተነስተው የውጭ ወራሪን መንግሥት ጣሊያንን ድል አድርገው በዓለም ሕዝብ ፊት-በአውሮፓ ትልቅ አድናቆትን እንዳተረፉ እቴጌይቱ በደንብ አዲስ አበባ ከተቀመጡ ልዩ መልዕክተኛ- አምባሳደሮች አፍ በእነሱ በኩል ስለ እኛ ምን በውጭ አገሮች እንደሚወራ ጥሩ አድርገው ያውቃሉ። ለዚህም ነው ከአልጠፋ ነገር „…መሣቂያ“ አትሁኑ የሚለውን መልዕክታቸውን ደብዳቤአቸው ላይ ያሰፈሩት። 57


ወረድ ብለው አሳቢ እናትም ፖለቲከኛም መሆናቸውን እቴጌይቱ በደንብ – በዘመኑ በነበረው አነጋገር ግልጽ አድርገዋል። „…እማሆይ ወለተ ተክሌ መቃብሬ ከዚያም ይሁን ብላ መጥታለችና አደራችሁን በምኑም በምኑም ነገር እንዳታሰቀይሟት። እንግዲህ ሷ እንዲህ አደረጉኝ ብላ የላከችብኝ እንደሆነ እንናንተንም እጠላችኋለሁ። እኔንም እንዳታስቀይሙኝ።“ ከዚህ ዓረፍተ ነገር ቀደም ሲል ስለ ዕርዳታ ገንዘብ ጉዳይ አንሰተዋል። „…ይህን ያህል መድከማችን ያንን ያህል ብር ባንክ አግብተን የዚያን ወለድ ከቤቱ የሚወጣውን ክራይ መስጠታችን እንዳትቸገሩ የሰው ፊት እንዳታዩ (…ነው) እንጂ ገንዘብ ተርፎን አይደለም።“ በአጭሩ „ …፩ነታችሁ እንዲጸና ብለን ነው እንጂ ገንዘብ ተርፎ ባገራችን በኢትዮጵያ ለምንሰጠው ሰው አጥተን አይደለም።“ የሚለው አረፍተ ነገር ትልቅ ትምህርት አሁንም ቢሆን ከአንድ መቶ አመት በሁዋላ የሚሰጥ ቃል ነው። እሱንም ብቻውን አላሰቀመጡትም። „ተስማሙ ተፋቀሩ“ አለበለዚያ….የሚለውን መልዕክት እቴጌይተዋ ጮክ ሳይሉ አብረው ሰደዋል። „ስምምነት፤ ፩ ድነት፣ ፍቅርና ሃይማኖት … በሰው ፊትም ኢትዮጵያኖች መሣቂያ አለመሆንና ተቸግሮም የሰው ፊት (ልመና ማለት ነው) አለማየት „ አገሪቱ የተገነባችበት የቆየ ትሩፋት /ቨርቺውስ ናቸው። መረዳት ለሚፈልግሰው የደብዳቤው መልዕክት ግልጽ ነው። የጣይቱን ደብዳቤ ጊዜ እንዳነሳው፣ „አንድነትን „ የማይፈልጉትን ሰዎች አንድ ቀን ታሪክ አንስቶ እነሱን ይወቅሳቸዋል። በተለይ „፩ነታችን እንዳይጸና- የኢትዮጵያ „ የሚፈልጉትን ኃይሎች ጊዜ ሳይረሳቸው ይፋረዳቸዋል። እሰከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሜዳውን ይዘው የነበሩ ሰዎች „የልዩነት ቆጣሪዎች“ ነበሩ አሁን ደግሞ ዘመኑ ጊዜውም „የኢትዮጵያና የአፍሪካ አንድነት“ ፈላጊዎች ነው። ደብዳቤው መነበብ ብቻ ሳይሆን መሠራጨትም ያለበት ነው። ለአእምሮየጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

58


ቀኃሥና ማርቲን ሉተር ኪንግ

ስድሣው

አመተ ምህረት የእኩልነትጥያቄ ዘመን ነበር።

በ1969 (እ.አ.አ.) የሰብዓዊ መብት ታጋዩ ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ በዘረኞቹ "በነጭ ዘር በላይነት" በሚያምኑ ነፍስ ገዳዮች የተገደለበት ዓመትም ነበር። የማርቲን ሉተር ኪንግ ጥያቄ "...የመገንጠል" ሳይሆን የነጮችና የጥቁር ዘሮች የእኩልነት ጥያቄ ነበር። በዚያን ዘመን ለማስታወስ በአገራችን በኢትጵያ ወጣቱ ትውልድ በብዙዎቹ ዘንድ ያኔ ማንነቱ ምን እንደሆነ እንደ አሁኑ ዘመን በግልጽ በአልታወቀው አይዶሎጂ ተሳከረው ከእኩልነት አልፎ የሚሄደውን "...የመገንጠል" ጥያቄም በአገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ "ኢትዮጵያ የሚባል ነገር የለም ብለው" በስታሊን ስም ተነስተው አሁን ያለንበት ሁኔታ ውስጥ ሳያመዛዝኑ እነሱ ከተውን ሄደዋል። 59


የዘረኝነት የፖለቲካ ጉዞና ተንኮል የገባቸው ቀ ኃ ሥ በማርቲን ሉተር ኪንግ መገደል አዘናቸውን ለመግለጽ ከመንገድ ወጥተው፣ ለጥቁር ህዝብና ትግል ወገናዊነታቸውን ለመግለጽ ወላጆቹንም ለማጽናናት ፎቶውና ጋዜጣው ላይ የሰፈረው ዜና እንደሚያሳየው የአበባ ጉንጉን መቃብሩ ላይ አስቀምጠው መንገዳቸውን ቀጥለዋል። ለአእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

60


BLACK GERMAN HOLOCAUST VICTIMS

This is a bit of history that few of us are aware of, I hope it enlightens. So much of our history is lost to us because we often don't write the history books, don't film the documentaries, or don't pass the accounts down from generation to generation. One documentary now touring the film festival circuit, telling us to "Always Remember" is "Black Survivors of the Holocaust" (1997). Outside the U.S.., the film is entitled "Hitler's Forgotten Victims" (Afro-Wisdom Productions). It codifies another dimension to the "Never Forget" Holocaust story--our dimension. Did you know that in the 1920's, there were 24,000 Blacks living in Germany, and how many of them were eventually caught unaware by the events of the Holocaust? Like most West European nations, Germany established colonies in Africa in the late 1800's in what later became Togo, Cameroon, Namibia, and Tanzania. German genetic experiments began there, most notably involving prisoners taken from the 1904 Heroro Massacre that left 60,000 Africans dead, following a 4-year revolt against German colonization. After the shellacking Germany received in World War I, it was stripped of its African colonies in 1918. As a spoil of war, the French were allowed to occupy Germany in the Rhineland--a bitter piece of real estate that has gone back and forth between the two nations for centuries. The French willfully deployed their own colonized African soldiers as the occupying force. Germans viewed this as the 61


final insult of World War I, and soon thereafter, 92% of them voted in the Nazi party. Hundreds of the African Rhineland-based soldiers intermarried with German women and raised their children as Black Germans. In Mein Kampf, Hitler wrote about his plans for these "Rhineland Bastards". When he came to power, one of his first directives was aimed at these mixedrace children. Underscoring Hitler's obsession with racial purity, by 1937, every identified mixed-race child in the Rhineland had been forcibly sterilized, in order to prevent further "race polluting", as Hitler termed it. Hans Hauck, a Black Holocaust survivor and a victim of Hitler's mandatory sterilization program, explained in the film "Hitler's Forgotten Victims" that, when he was forced to undergo sterilization as a teenager, he was given no anesthetic.

Once he received his sterilization certificate, he was "free to go", as long as he agreed to have no sexual relations whatsoever with Germans. Although most Black Germans attempted to escape their fatherland, heading for France where people like Josephine Baker were steadily aiding and supporting the French Underground, many still encountered problems elsewhere. Nations shut their doors to Germans, including the Black ones. Some Black Germans were able to eke out a living during Hitler's reign of terror by performing in Vaudeville shows, but many Blacks, steadfast in their belief that they were German first, Black second, opted to remain in Germany. Some fought with the Nazis (a few even became Luft waffe pilots)! Unfortunately, many Black Germans were arrested, charged with treason, and shipped in cattle cars to concentration camps. Often these trains were so packed with people and (equipped with no bathroom facilities or food), that, after the four-day journey, box car doors were opened to piles of the dead and dying. Once inside the concentration 62


camps, Blacks were given the worst jobs conceivable. Some Black American soldiers, who were captured and held as prisoners of war, recounted that, while they were being starved and forced into dangerous labor (violating the Geneva Convention), they were still better off than Black German concentration camp detainees, who were forced to do the unthinkable--man the crematoriums and work in labs where genetic experiments were being conducted. As a final sacrifice, these Blacks were killed every three months so that they would never be able to reveal the inner workings of the "Final Solution". In every story of Black oppression, no matter how we were enslaved, shackled or beaten, we always found a way to survive and to rescue others. As a case in point, consider Johnny Voste, a Belgian resistance fighter who was arrested in 1942 for alleged sabotage and then shipped to Dachau. One of his jobs was stacking vitamin crates. Risking his own life, Voste distributed hundreds of vitamins to camp detainees, which saved the lives of many who were starving, weak and ill--conditions exacerbated by extreme vitamin deficiencies. His motto was "No, you can't have my life; I will fight for it." According to Essex University's Delroy Constantine-Simms, there were Black Germans who resisted Nazi Germany, such as Lari Gilges, who founded the Northwest Rann--an organization of entertainers that fought the Nazis in his home town of Dusseldorf--and who was murdered by the SS in 1933, the year that Hitler came into power. Little information remains about the numbers of Black Germans held in the camps or killed under the Nazi regime.

Some victims of the Nazi sterilization project and Black survivors of the Holocaust are still alive and telling their story in films such as "Black Survivors of the Nazi Holocaust", but they must also speak out for justice, not just history. Unlike Jews (in Israel and in Germany), Black Germans receive no war reparations because their German citizenship was revoked (even though they were German-born). The only pension they get is from those of us who are 63


willing to tell the world their stories and continue their battle for recognition and compensation. After the war, scores of Blacks who had somehow managed to survive the Nazi regime, were rounded up and tried as war criminals. Talk about the final insult! There are thousands of Black Holocaust stories, from the triangle trade, to slavery in America, to the gas ovens in Germany. We often shy away from hearing about our historical past because so much of it is painful; however, we are in this struggle together for rights, dignity, and, yes, reparations for wrongs done to us through the centuries. We need to always remember so that we can take steps to ensure that these atrocities never happen again. For further information, read: Destined to Witness: Growing Up Black in Nazi Germany, by Hans J. Massaquoi. PLEASE PASS THIS ON, AND ALWAYS REMEMBER...LEST WE FORGET!

ለአእምሮ የጥር 2006 / January 2014/ እትም፣ቅጽ 2 ቁጥር 6

64